Search

Predigten

ርዕስ 9፡ ሮሜ (በሮሜ መጽሐፍ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[Chapter 6-2] የኢየሱስ ጥምቀት እውነተኛው ትርጉም፡፡ ‹‹ ሮሜ 6፡1-8 ››

‹‹ ሮሜ 6፡1-8 ››
‹‹እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በሐጢያት ጸንተን እንኑርን? አይደለም፡፡ ለሐጢአት የሞትን እኛ ወደፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን? ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደተነሳ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን፡፡ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፡፡ ከእንግዲህስ ወዲያ ለሐጢአት እንዳንገዛ የሐጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደተሰቀለ እናውቃለን፡፡ የሞተስ ከሐጢአቱ ጸድቋልና፡፡ ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን፡፡
 
 

ጥምቀት ምን ማለት ነው?

 
ኢየሱስን ያጠመቀውን ዮሐንስ አጥማቂው ዮሐንስ ብለን እንጠራዋለን፡፡ ታዲያ ጥምቀት ምን ማለት ነው? ‹‹ጥምቀት›› በግሪክ ‹‹βάφτισμα›› ነው፡፡ ይህም ‹‹መጥለም›› ማለት ነው፡፡ የጥምቀት እጅግ ጠቃሚው ትርጉም ‹‹ሐጢየትን መውሰድና መሞት›› ነው፡፡
 
‹‹መጥለም›› የሚለው ሐረግ ሞትን ያመላክታል፡፡ የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ወደ እርሱ ተላልፈዋል፡፡ በዚህም ሁሉንም ወስዶ የሐጢያቶቻችንን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ ኢየሱስ በእኛ ምትክ ሞተ፡፡ ሞት ማለት የሐጢያት ውጤት ነው፡፡ ምክንያቱም ‹‹የሐጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፡፡›› (ሮሜ 6፡23)
 
ጥምቀት ‹‹መታጠብ›› ማለትም ነው፡፡ ሐጢያቶቻችን በሙሉ አንዲት ቅንጣት ሐጢያት ሳትቀር ታጥበው ተወግደዋል፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ አማካይነት በሥጋው ወስዶዋል፡፡ በሰዎች ልብ ውስጥ ያሉ ሐጢያቶች በሙሉ ታጥበው ተወግደዋል፡፡ ምክንያቱም በጥምቀት አማካይነት ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋልና፡፡
 
ጥምቀት ‹‹እጆችን መጫን›› የሚል አይነት ተመሳሳይ ትርጉም አለው፡፡ ‹‹እጆችን መጫን›› ማለት ‹‹ማስተላለፍ›› ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ ጥምቀትን የተቀበለበት ድርጊት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ የተሸከመበት ድርጊት ነበር፡፡ ካህኑ እጆቹን በመስዋዕቱ ራስ ላይ በመጫን በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን የእስራኤልን ሐጢያቶች ወደ እርሱ ማስተላለፉ የእግዚአብሄር ዘላለማዊ የስርየት ሕግ ነበር፡፡
 
ዘሌዋውያን 16፡21-22 እንዲህ ይላል፡- ‹‹አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፡፡ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ፣ መተላለፋቸውንም ሁሉ፣ ሐጢአታቸውንም ሁሉ ይናዘዛል፡፡ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፡፡ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል፡፡ ፍየሉም ሐጢአታቸውን ሁሉ ወደ በረሀ ይሸከማል፡፡ ፍየሉንም በምድረ በዳ ውስጥ ይለቅቀዋል፡፡›› ሊቀ ካህኑ አሮን እጆቹን በሕያው ፍየሉ ራስ ላይ ሲጭን ፍየሉ የእስራኤልን ሐጢያቶች ተሸክሞ በሕዝቡ ምትክ ይታረደል፡፡
 
 

በብሉይ ኪዳን ‹‹በሐጢያት መስዋዕቱ ላይ እጆችን መጫን በአዲስ ኪዳን ‹‹ጥምቀትን›› ያመላክታል፡፡

 
የጥምቀት ትርጉም ‹‹መጥለም›› ማለት ነው፡፡ ይህም ‹‹መቀበርን፣ መታጠብን ወይም ማስተላለፍን›› ይጨምራል፡፡ የብሉይ ኪዳን ሰዎች ነውር የሌለባቸውን ፍየሎች ወይም ጠቦቶች በማቅረብ ሐጢያቶቻቸውን ወደ እነርሱ ለማስተላለፍ እጆቻቸውን በመስዋዕቶቹ ላይ ይጭናሉ፡፡ ይህ በአዲስ ኪዳን ከጥምቀት ድርጊት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ፍየሉ ‹‹በእጆች መጫን›› ሐጢያቶችን ይወስድና ይታረዳል፡፡ ኢየሱስ የሰው ዘር ሁሉ ወኪል በነበረው በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠምቆ የዓለምን ሐጢያቶች ሁሉ በመውሰድ ተሰቀለ፡፡
 
ሊቀ ካህኑና የእስራኤል ወኪል የሆነው አሮን የእስራኤሎችን ሐጢያቶች ወደ ፍየሉ ለማስተላለፍ በፍየሉ ራስ ላይ እጆቹን በመጫን ፍየሉን ያርደዋል፡፡ በጣቱም ከደሙ በመውሰድ በሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያ ቀንዶች ላይ ይቀባዋል፡፡ ስለዚህ ሊቀ ካህኑ አሮን የእስራኤሎች ሁሉ ወኪል እንደነበረ ሁሉ ሉቃስ ከአሮን ቤተሰብ የተወለደው አጥማቂው ዮሐንስም የእስራኤሎች ሁሉ ወኪል እንደነበር ይናገራል፡፡
 
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም፡፡›› (ማቴዎስ 11፡11) አጥማቂው ዮሐንስ እንደ ምድራዊ ሊቀ ካህን በእግዚአብሄር ዘላለማዊ ስርዓት መሰረት በጥምቀት አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ የማስተላለፍ መብት ነበረው፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ የመጨረሻው ሊቀ ካህን ነበር፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ ሊቀ ካህን ነበር በምልበት ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ‹‹አጥማቂው ዮሐንስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሊቀ ካህን እንደሆነ የተጻፈው የት ቦታ ነው?›› ይላሉ፡፡ ተጽፎዋልን? ዘካርያስ የተወለደው ሰው አጥማቂው ዮሐንስ ነበር፡፡ ካህኑ የሊቀ ካህኑ የአሮን የልጅ ልጅና የካህኑ የአብያ ክፍል የነበረው ዘካርያስ የአሮን ቤተሰብ ዘር እንደነበር ግልጽ ነው፡፡
 
መጽሐፍ ቅዱስ በ1ኛ ዜና ላይ ከአሮን ዘር ስለሆኑት የካህናት ሰሞኖች ይናገራል፡፡ በዳዊት ዕድሜ መጨረሻ ላይ ብዙ ካህናቶች ነበሩ፡፡ እነርሱም መደራጀት ነበረባቸው፡፡ ስለዚህ በ24 የአሮን ቤተሰቦች የልጅ ልጅ ላይ ተመስርተው በ24 ክፍሎች ተደራጅተው ነበር፡፡ ስምንተኛው ዕጣ አብያ ላይ ወድቆ ነበር፡፡ እያንዳንዱ ክፍል ቤተመቅደሱንና የጌታን ቤት ለ15 ቀናት ያገለግል ነበር፡፡ ከካህኑ ከአብያ ክፍል የሆነው ዘካርያስ በክፍሉ ተራ በስራ ላይ ያለ ካህን ሆኖ በእግዚአብሄር ተመረጠ፡፡
 
ሉቃስ 1፡9 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እንደ ካህናት ስርዓት ወደ ጌታ ቤተመቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት፡፡›› ይህም አጥማቂው ዮሐንስ ከሊቀ ካህኑ ከአሮን ቤተሰብ የተወለደና ሰዎችን ሁሉ የሚወክል የመጨረሻው ሊቀ ካህን እንደነበር ያሳየናል፡፡ (ማቴዎስ 11፡11፤3፡13-17) በሕጉ መሰረት ሊቀ ካህን መሆን የሚችለው ከሊቀ ካህን ቤተሰብ የተወለደ ብቻ ነው፡፡ የአንበሳ ደቦሎችን መውለድ የሚችሉት አንበሶች ብቻ ናቸው፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ የአያቱን የአሮንን ሊቀ ክህነት ወስዶዋል፡፡
 
 

የኢየሱስ ሐዋርያት የኢየሱስን ጥምቀት መስክረዋል፡፡

 
ሐዋርያቶች በሙሉ በተለይም ጳውሎስ ፔጥሮስ ማቴዎስና ዮሐንስ የኢየሱስን ጥምቀት መስክረዋል፡፡ በዛሬው ዋና ምንባብ ላይ የተጻፈውን የሐዋርያውን ጳውሎስን ምስክርነት እንመልከት፡- ‹‹እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በሐጢያት ጸንተን እንኑርን? አይደለም፡፡ ለሐጢአት የሞትን እኛ ወደፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን? ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደተነሳ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን፡፡ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፡፡ ከእንግዲህስ ወዲያ ለሐጢአት እንዳንገዛ የሐጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደተሰቀለ እናውቃለን፡፡ የሞተስ ከሐጢአቱ ጸድቋልና፡፡ ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን፡፡
 
ገላትያ 3፡27 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና፡፡›› የጴጥሮስን ምስክርነት እንመልከት፡፡ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፡፡ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፤ ለእግዚአብሄር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፡፡››
 
ሐዋርያው ዮሐንስ በ1ኛ ዮሐንስ 5፡5-8 ላይ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ኢየሱስም የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው? በውሃና በደም የመጣ ይህ ነው፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ በውሃውና በደሙ እንጂ በውሃው ብቻ አይደለም፡፡ መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው፡፡ የሚመሰክሩት መንፈሱና ውሃው ደሙም ሦስት ናቸውና፡፡ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ፡፡››
 
የማቴዎስ ምስክርነት በማቴዎስ 3፡13-17 ላይ ተጽፎዋል፡- ‹‹ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ ዮሐንስ ግን፡- እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር፡፡ ኢየሱስም መልሶ፡- አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው፡፡ ያን ጊዜ ፈቀደለት፡፡ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃ ወጣ፡፡ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ፡፡ የእግዚአብሄርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፡፡ እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡››
 
ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፡፡ ‹‹እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና፡፡›› ኢየሱስ እጅግ ተገቢ በሆነ መንገድ በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠምቆ የዓለምን ሐጢያቶች በራሱ ላይ ወሰደ፡፡ ‹‹ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃ ወጣ፡፡ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ፡፡ የእግዚአብሄርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፡፡ እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡›› ኢየሱስ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደ፡፡ ለሦስት አመታት የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መሰከረ፡፡ ተሰቅሎ ሞተ፡፡ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተነሳ፡፡ አሁን እርሱ በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀምጦዋል፡፡
 
ኢየሱስ እርሱን ለሚጠብቁት ዳግመኛ ያለ ሐጢያት ሆኖ ይመጣላቸዋል፡፡ ዕብራውያን 9፡28 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ የብዙዎችን ሐጢያት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ሐጢአት ይታይላቸዋል፡፡›› እግዚአብሄር ራሱ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፡፡›› መንፈስ ቅዱስም የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ የወሰደው ሰው አዳኙ ኢየሱስ እንደነበር መስክሮዋል፡፡ ነገር ግን ሰዎች መንፈሳዊ ዓይኖቻቸው ስለታወሩ መጽሐፍ ቅዱስን አይረዱም፡፡ መንፈሳዊ ዓይኖቻቸው መገለጥና ከውሃና ከመንፈስ ወንጌልም ዳግም መወለድ ይገባቸዋል፡፡ (ዮሐንስ 3፡5)
 
ስለዚህ እነዚህ ለሰው ዘር ደህንነት ያገለገለው ኢየሱስ ብቻ ነው ብለው የሚያስቡ ብቻ ናቸው፡፡ እውነቱ ግን ኢየሱስ የእግዚአብሄር በግ መሆኑና የሰው ዘር ሁሉ ወኪል የሆነውና የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ ያስተላለፈው አጥማቂው ዮሐንስ አስፈልጎት ነበር፡፡ ምክንያቱም ሊቀ ካህኑ አሮንም እጆቹን በመስዋዕቱ እንስሳ (ሕያው ፍየል) ራስ ላይ በመጫን የእስራኤሎችን ሐጢያቶች ሁሉ ወደ እርሱ ያስተላለፈው በዚህ መንገድ ነበርና፡፡ ከዚያም አሮን የሐጢያት መስዋዕቱን በማረድ ሕዝቡን ከሐጢያቶቻቸው ነጻ ያወጣቸዋል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር በኢየሱስ ፊት መልዕክተኛውን ላከ፡፡
 
 
አጥማቂው ዮሐንስ ማነው?
 
አጥማቂው ዮሐንስ በሚልክያስ 3፡1-3 ላይ የተተነበየለት የእግዚአብሄር መልዕክተኛ ነው፡፡ ጌታ የሰውን ዘር ሁሉ የሚወክለው መልዕክተኛ አጥማቂው ዮሐንስ አስፈለገው፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን በአጥማቂው ዮሐንስ አማካይነት የሰዎችን ሁሉ ዘላለማዊ ሐጢያቶች ወስዶ የሐጢያትን ዋጋ ለመክፈል ተሰቀለ፡፡ በብሉይ ኪዳን ግን በጎች የወሰዱት በተወሰኑ ጊዜ ውስጥ የተሰሩ ሐጢያቶችን ነበር፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ከዘላለም ሐጢያቶች አድኖዋል፡፡
 
ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት ሁለት ታላላቅ ሁነቶች ተከስተው ነበር፡፡ አንዱ ማርያም ኢየሱስን ማርገዝዋ ሲሆን ሌላው ደግሞ አጥማቂው ዮሐንስ ከአብያ ክፍል መወለዱ ነበር፡፡ እነዚህ ሁለት ሁነቶች በመለኮት እቅድ የተከናወኑ ነበሩ፡፡ በእግዚአብሄር የተጻፉ ምርጥ ተውኔቶች ነበሩ፡፡ እግዚአብሄር ከኢየሱስ ስድስት ወራት ቀደም ብሎ አጥማቂውን ዮሐንስን ወደ ዓለም ላከው፡፡ ከዚያም እኛን ከጦርነትና ከስቃይ ነጻ ለማውጣት አንድያ ልጁን ላከ፡፡ ገባችሁ? እስቲ መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት እንመልከት፡፡
 
ማቴዎስ 11፡7-14ን እንመልከት፡- ‹‹እነዚያም ሲሄዱ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ፡፡ እንዲህም አለ፡- ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ? ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ፡፡ ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን፡፡ እነሆ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልዕክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና፡፡ እውነት እላችኋለሁ፤ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፡፡ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል፡፡ ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፤ ግፈኞችም ይናጠቋታል፡፡ ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፡፡ ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው፡፡››
ሰዎች ‹‹መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ›› (ማቴዎስ 3፡20 እያለ የሚጮኸውን አጥማቂውን ዮሐንስን ለማየት ወደ ምድረ በዳ ወጡ፡፡ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ? ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ፡፡ ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን፡፡››
 
በብሉይ ኪዳን ዘመን ንጉሥ ከነቢይ የሚበልጥ ሥልጣን አልነበረውም፡፡ ነገሥታቶች ነቢያቶች የተናገሩትን ይታዘዙ ነበር፡፡ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከነገሥታቶችና ከነቢያቶች ሁሉ ይበልጥ የነበረው ማነው? አጥማቂው ዮሐንስ ነበር፡፡ ይህንን ኢየሱስ ራሱ መስክሮዋል፡፡ የሰው ዘር ሁሉ ወኪል ማን ነበር? ከኢየሱስ ውጪ ሥጋ የለበሰ የሰዎች ሁሉ ወኪል ማን ነበር? አጥማቂው ዮሐንስ ነበር፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ የሰው ዘር ሁሉ ምድራዊ ሊቀ ካህን ነበር፡፡ እርሱ በራሱ በጌታ ተሹሞ ወደ ዓለም በመላክ ሚናውን ተጫወተ፡፡
 
‹‹ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን፡፡ እነሆ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልዕክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና፡፡››
 
ኢሳይያስ በኢየሩሳሌም ያለው ጦርነት እንደሚያበቃ ተንብዮአል፡፡ ትንቢቱ አጥማቂው ዮሐንስ ‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ›› (ዮሐንስ 1፡29) ብሎ በተናገረ ጊዜ እንደተፈጸመ እናገኛለን፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነና የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ እንደወሰደ መስክሮዋል፡፡
 
በሌላ በኩል ኢየሱስ አጥማቂው ዮሐንስ የሚመጣው የእግዚአብሄር የተመረጠ መልዕክተኛ እንደነበር መስክሮዋል፡፡ ማቴዎስ 11፡11 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እውነት እላችኋለሁ፤ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም፡፡›› ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ ተነስቶ ያውቃልን? አያውቅም፡፡ ‹‹ከሴቶች ከተወለዱት መካከል›› ማለት ምን ማለት ነው? ‹‹በዓለም ላይ ከሚገኙ ሰዎች ሁሉ›› ማለት ነው፡፡ ‹‹ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም›› የሚሉት ቃሎች አጥማቂው ዮሐንስ በዓለም ላይ የሚገኙ ሰዎች ሁሉ ወኪል ነው ማለት ናቸው፡፡ እርሱ ከአሮን ቤተሰብ በመወለዱ ሊቀ ካህን ነበር፡፡
 
 
አጥማቂው ዮሐንስ በዓለም ላይ የሚገኙ ሰዎች ሁሉ ወኪል ነበር፡፡
 
አጥማቂው ዮሐንስ እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳን አሮንና ዘሮቹን በዘላለም ክህነት ያገለግሉ ዘንድ እንደሾማቸው በማወቅ በዓለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ ወኪልና ሐጢያቶችን ሁሉ ወደ ኢየሱስ ያስተላለፈ ሊቀ ካህን እንደሆነ ታምናላችሁን?
 
የሰው ዘር ሁሉ ወኪል ማን ነበር? ከኢየሱስ ውጪ በሥጋ የሰዎች ሁሉ ወኪል የነበረው ማነው? ኢየሱስን ያጠመቀው አጥማቂው ዮሐንስ ነበር፡፡
‹‹አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን፡፡ እነሆ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልዕክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና፡፡››
 
‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ›› (ዮሐንስ 1፡29) ብሎ የመሰከረውም አጥማቂው ዮሐንስ ነበር፡፡
 
ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- ‹‹ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፤ ግፈኞችም ይናጠቋታል፡፡ ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፡፡›› (ማቴዎስ 11፡12-13) ይህ ምንባብ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ እንደወሰደና የሰው ዘር ሁሉ አዳኝ እንደሆነ ያሳያል፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ እንደወሰደና የሰው ዘር ሁሉ አዳኝ እንደሆነ ያሳያል፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ እንደወሰደና የሰው ዘር ሁሉ አዳኝ እንደሆነ ያሳያል፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ እንዳስተላለፈም ያሳያል፡፡ ኢየሱስ ራሱ እንዲሁ ብሎዋል፡፡ ይህ ማለት አጥማቂው ዮሐንስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ አስተላልፎዋል፤ በዚህ እውነት የሚያምን ሁሉ ከሐጢያቶቹ ሁሉ ድኖ መንግሥተ ሰማይ ይገባል ማለት ነው፡፡ ይህ እውነት ነው ወይስ ስህተት? ይህ በእግዚአብሄር ቃል መሰረት በጣም ትክክል ነው፡፡ ስለዚህ እኛ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የምንሰብክ ሰባኪዎች ይህንን እውነታ በከበረ መንገድ ልናቀርበው እንችላለን፡፡ እውነትን የሚያምን ሰው ሁሉ መንግሥተ ሰማይ ይገባል፡፡
 
 
አጥማቂው ዮሐንስ የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ሊቀ ካህን ሆኖ የዓለምን ሐጢያቶች ወደ ኢየሱስ አስተላለፈ፡፡
 
አጥማቂው ዮሐንስ አባት ዘካርያስ ከጌታ መልአክ አንድ ነገር ሰማ፡፡ ዘካርያስ ለልጁ የመሰከረውን ምስክርነት እንመርምር፡፡ የአባቱ ምስክርነት ከትክክለኛነትም በላይ አይደለምን? በመዝሙር መልክ የተዘመረውን ምስክርነት እንመልከት፡- ‹‹አባቱ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ ሞላበትና ትንቢት ተናገረ፡፡ እንዲህም አለ፡- የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፤ ጎብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፡፡ ከጥንት ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያት አፍ እንደተናገረ በብላቴናው በዳዊት ቤት የመዳን ቀንድን አስነስቶልናል፡፡ ማዳኑም ከወደረኞቻችንና ከሚጠሉን ሁሉ እጅ ነው፡፡ እንደዚህ ለአባቶቻችን ምህረት አደረገ፡፡ ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሐላውን ቅዱሱን ኪዳን አሰበ፡፡ በእርሱም ከጠላቶቻችን እጅ ድነን በዘመናችን ሁሉ ያለ ፍርሃት በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገልግለው ሰጠን፡፡ ደግሞም አንተ ሕጻን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፡፡ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሄዳለህና፡፡ እንደዚህም የሐጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፡፡ ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጎበኘበት በአምላካችን ምህረትና ርህራሄ ምክንያት ነው፡፡ ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል፡፡ እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል፡፡ ሕጻኑም አደገ፡፡ በመንፈስም ጠነከረ፡፡ ለእስራኤልም እስከታየበት ቀን ድረስ በምድረ በዳ ኖረ፡፡›› (ሉቃስ 1፡67-80)
 
አባቱ ዮሐንስ ምን አይነት ነቢይና ካህን እንደሚሆን ተነበየ፡፡ ለልጁ የተነበየውን እስቲ እንመልከት፡- ‹‹ደግሞም አንተ ሕጻን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፡፡ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሄዳለህና፡፡ እንደዚህም የሐጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፡፡ ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጎበኘበት በአምላካችን ምህረትና ርህራሄ ምክንያት ነው፡፡ ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል፡፡ እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል፡፡›› (ሉቃስ 1፡76-79)
 
እዚህ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንዲህ ይላል፡- ‹‹የሐጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፡፡›› (ሉቃስ 1፡76) ይህ ሰው አጥማቂው ዮሐንስ እንደሆነ ጠቁሞዋል፡፡ እኛ ኢየሱስን ያወቅነውና በእርሱም ያመንነው አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስ ሐጢያቶችን ለመውሰድ እጅግ ቅንና ጥሩ በሆነ መንገድ ከእርሱ በመጠመቅ ሐጢያተኞችን ከሐጢያቶቻቸው እንዳዳናቸው በመመስከሩ ነው፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ ‹‹ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ እንጂ እርሱ ብርሃን አልነበረም፡፡›› (ዮሐንስ 1፡7-8)
 
 
መዳን አለብን፡፡
 
ኢየሱስ እጅግ ቀናና በጎ በሆነ መንገድ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሕዝብ በሙሉ እንዳዳነ በማመን ቤዛነትን ማግኘት ይገባናል፡፡ የእገዚአብሄር ጽደቅ ኢየሱስ በሰዎች አምሳል ሆኖ ወደዚህ ምድር እንደመጣ፣ በአጥማቂው ዮሐንስም እጅግ ቀናና በጎ በሆነ መንገድ በመጠመቅ ሐጢያተኞችን ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ እንዳዳነና ከተሰቀለ በኋላም ከሙታን እንደተነሳ ይናገራል፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ውስጥ ተሰውሮዋል፡፡
 
በወንጌል ውስጥ የተገለጠው የእግዚአብሄር ጽድቅ ኢየሱስ በሰዎች አምሳል እንደተላከ፣ እንደተጠመቀ፣ እንደተሰቀለና በሦስተኛው ቀን ዳግመኛ ከሙታን እንደተነሳ ያስተምራል፡፡ እኛ በአጥማቂው ዮሐንስ ምስክርነት በኢየሱስ ወደ ማመን ደርሰን በኢየሱስ ጽድቅ በማመን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ድነናል፡፡ የሰዎች ሁሉ ሐጢያቶች ተደምስሰዋል፡፡ እነርሱም በአጥማቂው ዮሐንስ አማካይነት በኢየሱስ በማመን የዘላለም ሕይወትን አግኝተዋል፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች እንደሆንን የሚመሰክርልንንም መንፈስ ቅዱስ በስጦታ ተቀብለዋል፡፡