Search

Fragen und Antworten zum christlichen Glauben

Thema 4: FAQ von den Lesern unserer Bücher

4-11. ኢየሱስ የአሁኑን፣ ያለፈውንና የወደፊቱን ሐጢያት ቀድሞውኑም ስለከፈለ ይህ ሰው የግድየለሽነት ሕይወት እንዲኖርና በሐጢያት ውስጥ በመኖር እንዲቀጥል ሊያደርገው የሚችል አይመስልህምን?

መልሱ ‹‹አይችልም›› ነው፡፡
በእርግጥ ዳግመኛ የተወለዱ ቅዱሳኖችም ደግሞ በቀሪው ሕይወታቸው ሐጢያቶችን ይሠራሉ፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በልቦቻቸው ውስጥ ስለሚኖር ወደው ሐጢያትን ሊሠሩ አይችሉም፡፡ በእርግጥ ዳግመኛ ከተወለዱ በኋላ ለእያንዳንዱ ሐጢያት ይበልጥ ስሜት አላቸው፡፡ እነርሱ እስከሚሞቱ ድረስ ሐጢያት እንደሚሠሩና ሐጢያትን የመሥራት ዕድሎችን ለማምለጥ ብቸኛው መንገድም የእግዚአብሄርን ጽድቅ ማለትም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ማገልገል እንደሆነ የሚያውቁ ሰዎች ናቸው፡፡ በአጭሩ በውስጣቸው የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ከስጋ ፍትወት ተለይተው በመጀመሪያ የእግዚአብሄርን ሥራ እንዲሰሩ ይመራቸዋል፡፡ 
በሐዋርያት ዘመን ይህንኑ ጥያቄ ለሐዋርያት የጠየቁዋቸው ይመስላል፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ አለ፡- ‹‹እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በሐጢአት ጸንተን እንኑርን? አይደለም፡፡ ለሐጢአት የሞትን እኛ ወደፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን? ወይስ ከክርስቶሰ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን፡፡››
      
እንደገናም እርሱ እንዲህ አለ፡- ‹‹እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላይደለን ሐጢአትን እንሥራን? አይደለም፡፡ ለመታዘዝ ባሪያዎች እንድትሆኑ ራሳችሁን ለምታቀርቡለት ለእርሱ ለምትታዘዙለት ባሪያዎች እንደሆናችሁ አታውቁምን? ወይም ለሞት የሐጢአት ባሪያዎች ወይም ለጽድቅ የመታዘዝ ባሪያዎች ናችሁ፡፡ ነገር ግን አስቀድማችሁ የሐጢአት ባሪያዎች ከሆናችሁ ለተሰጣችሁለት ለትምህርት ዓይነት ከልባችሁ ስለታዘዛችሁ ከሐጢአትም አርነት ወጥታችሁ ለጽድቅ ስለተገዛችሁ ለእግዚአብሄር ምስጋና ይሁን፡፡››    
በተጨባጭ በውሃውና በመንፈሱ ዳግመኛ የተወለደ ሰው ከዚህ ቀደም ከሠራው በላይ ሐጢያት ሊሰራ አይችልም፡፡ ይልቁንም እርሱ/እርስዋ በቀኑ በወንጌል ይደሰታሉ፤ በመላው ዓለምም ሊሰብኩት ይሞክራሉ፡፡ በሌላ አነጋገር እርሱ/እርስዋ አስቀድመው የእግዚአብሄርን መንግሥትና ጽድቁን ከልባቸው በመንፈስ ቅዱሰ ይሻሉ፡፡ (ማቴዎስ 6፡33)