Search

Κηρύγματα

ርዕስ 10፡ ራዕይ (በራዕይ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[3-1] ለሰርዴስ ቤተክርስቲያን የተጻፈ ደብዳቤ፡፡ ‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 3፡1-6 ››

ለሰርዴስ ቤተክርስቲያን የተጻፈ ደብዳቤ፡፡
‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 3፡1-6 ››
‹‹በሰርዴስም ወዳለው ቤተክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ ሰባቱ የእግዚአብሄር መናፍስትና ሰባቱ ከዋክብት ያሉት እንዲህ ይላል፡፡ ሥራህን አውቃለሁ፤ ሕያው እንደመሆንህ ሥም አለህ ሞተህማል፡፡ ሥራህን በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን፡፡ ሊሞቱ ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና፡፡ እንግዲህ እንዴት እንደተቀበልህና እንደሰማህ አስብ፤ ጠብቀውም፡፡ ንስሐም ግባ፡፡ እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ፡፡ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታውቅም፡፡ ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፡፡ የተገባቸውም ስለሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ፡፡ ድል የነሳው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጎናጸፋል፤ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፡፡ በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ፡፡ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ፡፡›› 
 
 

ትንታኔ፡፡ 

 
ቁጥር 1፡- ‹‹በሰርዴስም ወዳለው ቤተክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ ሰባቱ የእግዚአብሄር መናፍስትና ሰባቱ ከዋክብት ያሉት እንዲህ ይላል፡፡ ሥራህን አውቃለሁ፤ ሕያው እንደመሆንህ ሥም አለህ ሞተህማል፡፡››
ጌታ ሰባቱን መናፍስትና ሰባቱን ከዋክብቶች ይዞዋል፡፡ የሰርዴስ ቤተክርስቲያን በእምነት ሕይወቷ ብዙ ጉድለቶች ነበሩባት፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያኒቱን በእምነት እንድትኖር መከራት፡፡ እግዚአብሄር እዚህ ላይ ለሰርዴስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ‹‹ሕያው እንደመሆንህ ሥም አለህ ሞተህማል›› ይለዋል፡፡ እግዚአብሄር እንዲህ ማለቱ የሰርዴስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ በሁሉም ሁኔታ ሞቷል ማለቱ ነው፡፡
 
ቁጥር 2፡- ሥራህን በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን፡፡ ሊሞቱ ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና፡፡››
ጌታ የሰርዴስ ቤተክርስቲያን መልአክ በታማኝነቱ እንዲቀጥል አልፈቀደለትም፡፡ እርሱ ይህችን ቤተክርስቲያን የነቀፈው በእግዚአብሄር ቃል ላይ ሙሉ የሆነ እምነት ስላልነበራት ነው፡፡ ቅዱሳን የተጻፈውን ቃል ከሙሉ ልባቸው አምነው ሕይወታቸውን የማይኖሩ ከሆኑ በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያትን እየሰሩ ይኖራሉ፡፡
ቅዱሳን ደካሞች ሆነው ሳሉ እንኳን በእግዚአብሄር ቃል ላይ ባላቸው እምነት የሚኖሩ ከሆኑ በእግዚአብሄርና በሰው ፊት ከፍ ይላሉ፡፡ እምነታቸው ምሉዕ እንደሆነ እንደ እነዚህ ቅዱሳን ለመኖር ቅዱሳኖችን ምሉዕ ያደረጋቸውን የእግዚአብሄር ቃል በታማኝነት በማመንና በመከተል ሕይወታችንን መኖር አለብን፡፡
 
ቁጥር 3፡- ‹‹እንግዲህ እንዴት እንደተቀበልህና እንደሰማህ አስብ፤ ጠብቀውም፡፡ ንስሐም ግባ፡፡ እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ፡፡ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታውቅም፡፡››
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ቅዱሳንና አገልጋዮች የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለመስማትና ለመጠበቅ ከፍተኛ መስዋዕትነቶችን ከፍለዋል፡፡ ስለዚህ ጌታ በዚህ ክብሩ በሆነው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ብዙ መስዋዕቶችን ባስከፈለውና እንዲቀበሉትም የራሳቸውን ሕይወት ሳይቀር ባስከፈላቸው ወንጌል ላይ ያላቸውን እምነት እንዳያጡ ነገራቸው፡፡ ምዕመናን ይህንን ፍጹም የሆነ ደህንነት የሚሰጥ የውሃና የመንፈስ ወንጌል አጥብቀው በመያዝ እምነታቸውንና ምግባሮቻቸውን በግልጽ ማሳየት አላባቸው፡፡
የዳኑ ሰዎች የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እንዴት በመጀመሪያ እንደሰሙት ሁልጊዜም እያስታውሱ ለደህንነት ጸጋው ሕይወታቸውን በአመስጋኝነት ሊኖሩ ይገባል፡፡ ዳግመኛ የተወለዱ ቅዱሳንና አገልጋዮች ሁልጊዜም ከጌታ የተቀበሉት ወንጌል ምን ያህል ታላቅና የተባረከ እንደሆነ ማሰብ አለባቸው፡፡ አንደዚያ ካልሆኑ ጌታ ወደዚህ ምድር መቼ እንደሚመጣ ሳያውቁ በሞኞች ስፍራ ይቀመጣሉ፡፡
 
ቁጥር 4፡- ‹‹ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፡፡ የተገባቸውም ስለሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ፡፡››
ሆኖም ጌታ እዚህ ላይ የሰርዴስ ቤተክርስቲያን እምነታቸውን አጥብቀው የያዙና ልብሳቸውን ያላረከሱ ጥቂቶች ሰዎች እንዳሉዋት ይነግረናል፡፡ ጌታ እነዚህ ታማኝ ቅዱሳን የእርሱን ጽድቅ የለበሱ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ሆነው ከጌታ ጋር እንደሚመላለሱም ይናገራል፡፡ እምነታቸው ከእርሱ ጋር ለመመላለስ የሚያበቃቸው ስለሆነ ከጌታ ጋር መመላለስ ይችላሉ፡፡
እግዚአብሄር እምነታቸውን የደገፈላቸው ቅዱሳን ጌታን ወደሚመራቸው ሁሉ ይከተሉታል፡፡ ልብሳቸውን አለማርከሳቸው በጌታ ቃል ስለሚታመኑ ለዓለም ነገሮች እንደማይማረኩ የሚያሳይ ነው፡፡ ጌታ በሰጠው የውሃና የመንፈስ ወንጌል የጽድቅ ልብስ የለበሱ ሰዎች ቃሉን አጥብቀው በመያዝ ከዓለም ጋር አያመቻምቹም፡፡ በሌላ አነጋገር ከሐሰተኛ ወንጌሎች የሚለያቸውን ግልጽ የሆነ የመለያ መሰመር ያሰምራሉ፡፡
በጌታ ወንጌል በማመን ነጭ ልብስ የለበሱ ሰዎች ለእርሱ ወንጌል ይለፋሉ፡፡ ከእርሱ ጋር የሚመላለስ ሕይወትንም በዚህ ዓለም ላይ ይኖራሉ፡፡ ጌታ ሁልጊዜም ከእነርሱ ጋር የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡ ምክንያቱም እነርሱ ቃሉን በማመን ሁልጊዜም ይከተሉታልና፡፡
 
ቁጥር 5፡- ‹‹ድል የነሳው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጎናጸፋል፤ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፡፡ በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ፡፡››
በእግዚአብሄር ቃል በማመን ዓለምን የሚያሸንፉ ሰዎች የእርሱ ቅዱሳኖች ሆነው የጌታን ሥራዎች በመስራት የእግዚአብሄርን ጽድቅ ይለብሱና ለዘላለም ይኖራሉ፡፡ ጌታም እምነታቸውን ይደግፍና ስሞቻቸውን በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ይጽፈዋል፡፡ እነዚህ ስሞች ለዘላለም አይደመስሱም፡፡
የጌታችን የተስፋ ቃል እውነተኛ እምነት ያላቸው ከእግዚአብሄር ጠላቶች ጋር በሚያደርጉት የእምነት ትግል አሸናፊዎች እንደሚሆኑ ይነግረናል፡፡ ‹‹ድል የነሳው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጎናጸፋል፡፡›› እዚህ ላይ ነጩ ልብስ የሚያመላክተው ከእግዚአብሄር ጠላቶች ጋር በሚደረገው ጦርነት የተገኘውን ድል ነው፡፡ የእምነት ድል አድራጊዎች ስሞቻቸው ለዘላለም ከሕይወት መጽሐፍ ውስጥ የማይደመሰስበት በረከት ተሰጥቶዋቸዋል፡፡ ስሞቻቸው ለዘላለም ከሕይወት መጽሐፍ ውስጥ የማይደመሰስበት በረከት ተሰጥቶዋቸዋል፡፡ ስሞቻቸው በአዲሲቷ ኢየሩሳሌምም ላይ እንዲህ ይጻፉሉ፡- ‹‹በአባቴና በመላዕክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ፡፡›› እዚህ ላይ ‹‹መመስከር›› ማለት ጌታ እምነታቸውን ይደግፍላቸዋል ማለት ነው፡፡
 
ቁጥር 6፡- ‹‹መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮው ያለው ይስማ፡፡››
እውነተኛ እምነት ያላቸው ሰዎች መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ቤተክርስቲያኖች በኩል የሚናገረውን ሁልጊዜ ይሰማሉ፡፡ ስለዚህ ከእግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር ይኖራሉ፡፡ ሁልጊዜም በመንፈስ ቅዱስ ይመራሉ፡፡