Search

Sermons

ርዕስ 8፡ መንፈስ ቅዱስ

[8-16] መንፈስ ቅዱስን ያገኙ ሰዎች ተልዕኮ ‹‹ ኢሳይያስ 61፡1-11 ››

መንፈስ ቅዱስን ያገኙ ሰዎች ተልዕኮ
‹‹ ኢሳይያስ 61፡1-11 ››
‹‹የጌታ የእግዚአብሄር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሄር ቀብቶኛልና፡፡ ልባቸውን የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፣ ለተማረኩትም ነጻነትን፣ ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል፡፡ የተወደደችውን የእግዚአብሄር ዓመት፤ አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፣ እግዚአብሄር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፣ በአመድ ፈንታ አክሊልን፣ በልቅሶም ፈንታ የደስታን ዘይት፣ በሐዘንም መንፈስ ፈንታ የምስጋናን መጎናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል፡፡ ከጥንትም ጀምሮ ባድማ የነበሩትን ይሠራሉ፤ ከቀድሞ የፈረሱትንም ያቆማሉ፤ ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትውልድ በፊት የፈረሱትን ከተሞች እንደገና ይሠራሉ፡፡ መጻተኞችም ቆመው በጎቻችሁን ያሰማራሉ፤ ሌሎች ወገኖችም አራሾችና ወይን ጠባቂዎች ይሆኑላችኋል፡፡ እናንተ ግን የእግዚአብሄር ካህናት ትባላላችሁ፤ ሰዎቹም የአምላካችን አገልጋዮች ብለው ይጠሩአችኋል፤ የአሕዛብን ሀብት ትበላላችሁ፤ በክብራቸውም ትመካላችሁ፡፡ በእፍረታችሁ ፋንታ ሁለት እጥፍ ይሆንላችኋል፡፡ በውርደታችሁም ፋንታ ዕድል ፈንታችሁ ደስ ይላቸዋል፡፡ ስለዚህ በምድራቸው ሁሉ እጥፍ ይገዛሉ፤ የዘላለምም ደስታ ይሆንላቸዋል፡፡ እኔ እግዚአብሄር ፍርድን የምወድድ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፡፡ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፡፡ ዘራቸውም በአሕዛብ መካከል ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፤ ያያቸው ሁሉ እግዚአብሄር የባረካቸው ዘር እንደሆኑ ይገነዘባል፡፡ አክሊልን እንደለበሰ ሙሽራ፤ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፤ የጽድቅንም መጎናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሄር እጅግ ደስ ይለኛል፡፡ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች፡፡ ምድርም ቡቃያዋን እንደምታወጣ፤ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል እንዲሁ ጌታ እግዚአብሄር ጽድቅንና ምስጋናን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ያበቅላል፡፡››
 
 
መንፈስ ቅዱስን የሚቀበሉ ሰዎች ተልዕኮ ምንድነው?
የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለመላው የዓለም ሕዝቦች መስበክ ነው፡፡
 
መንፈስ ቅዱስን የተቀበለ ሰው ምን ማድረግ ይገባዋል? የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለሰዎች ሁሉ መስበክ አለበት፡፡ እግዚአብሄር ዳግም ከውሃና ከመንፈስ የመወለድን ወንጌል በአደራ የሰጠው ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ ለተቀበሉ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ለሐጢያቶቻቸው ይቅርታን ያገኙ መንፈስ ቅዱስን ይቀበላሉ፡፡ ታዲያ እግዚአብሄር የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ለእነርሱ የሚሰጣቸው ለምን ይመስላችኋል?
የእርሱ ልጆች እንዳደረጋቸው የመጨረሻውን ዋስትና ሊሰጣቸው መንፈስ ቅዱስን ሰጣቸው፡፡ የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ ላገኙትና ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ ለተቀበሉት ሰዎች የሚከተለውን እንዲያደርጉ አደረገ፡፡
 

 
ለድሆች የምሥራችን እንዲሰብኩ አደረጋቸው
 

ለድሆች የሚሰበከው የምሥራች ምንድነው? የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ነው፡፡ እግዚአብሄር ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ የተቀበሉ ውብ የሆነውን ወንጌል ለድሆች እንዲሰብኩ አዘዛቸው፡፡ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ ሰዎች የሰማይ ተስፋ ስላላቸው በምድር ላይ ባሉት ነገሮች በጭራሽ አይረኩም፡፡
እግዚአብሄር የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለድሆች በመስጠት ሐጢያቶቻቸውን ይቅር አለ፡፡ ከዚያም ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ ሰጣቸውና ወደ ዘላለማዊው ዓለም እንዲገቡ ፈቀደላቸው፡፡ እግዚአብሄር የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለድሆች ይሰብኩ ዘንድ ጻድቃንን አዘዛቸው፡፡ በእግዚአብሄርና በኢየሱስ የማመንን እምነትም እንዲያሰራጩ አሳመናቸው፡፡ እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስን የሰጠን የምሥራቹን በስፋት ለዚህ ዓለም ድሆች እንድንሰብክ ነው፡፡
 
 

ልባቸው የተሰበረውን እንድንፈውስ ላከን
 

ጌታችን አእምሮዋችንን የሚፈውሰው እንዴት ነው? እርሱ ልባቸው የተሰበረውን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ይፈውሳቸዋል፡፡ ልባቸው የtሰበረ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ሕይወት ለእነርሱ ዋጋ የለውም፡፡ የራሳቸው ጽድቅም አይረባም፡፡ በሐጢያቶቻቸው ምክንያት ዝቅ ያለና በስቃይ የተሞላ ሕይወትን ይኖራሉ፡፡ ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ ስለ ሕይወት ባሉዋቸው ጥርጣሬዎች ይሰቃያሉ፡፡ ሰዎች ሁሉ በሞገስ መኖርና በአካልና በነፍስ ክንውን መደሰት ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ግን ሰዎች በቤት ሰርሳሪዎች ንብረቶቻቸውን በሙሉ በተዘረፉበት ተመሳሳይ መንገድ በቀላሉ የሚሆን ነገር አይደለም፡፡
ልክ እንደዚሁ በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ያለባቸው ሰዎች ሁሌም ጽድቃቸውን ሁሉ እንደተዘረፉ ናቸው፡፡ በመጨረሻም በሐጢያቶቻቸው ምክንያት ወደ ሲዖል ይወርዳሉ፡፡ ጌታ ልባቸው ለተሰበረው በማዘን ውብ የሆነውን ወንጌል እንድንሰብክላቸው ያዘዘን ለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሄር በምን አይነት ቃሎች ፈወሳቸው? ይህንን ያደረገው ውብ በሆነው የውሃና የመንፈስ ወንጌል ነው፡፡ እርሱ ልባቸው የተሰበረውን ፈወሰና የዘላለምን ሕይወት ደግሞ ሰጣቸው፡፡
 
 

ለሐጢአት ምርኮኞችም አርነትን አወጀ
 

እርሱ ለምርኮኞች ነጻነትን ለገሰ፡፡ ይህ ምን ማለት ነው? ይህ ማለት እግዚአብሄር የሰዎችን ነፍስ ከዓለም ሐጢያቶች ሁሉ ነጻ አውጥቶዋል ማለት ነው፡፡ እርሱ ይህንን ተልዕኮ የሰጠው መንፈስ ቅዱስን ለተቀበሉት ብቻ ነው፡፡ እነርሱም ሌሎችን ከሐጢያቻቸው ነጻ ማውጣት ይችላሉ፡፡
ሰው አካልና ነፍስ አለው፡፡ አካሉና ነፍሱም በሐጢያትና በሕግ እርግማን ታስረው በሕይወት ይኖራሉ፡፡ እርሱ በእግዚአብሄር ቢያምንም ባያምንም የሐጢያት ምርኮኛ ሆኖ ከመኖር በስተቀር አንዳች ነገር ማድረግ አይችልም፡፡ በሐጢያት ስለተወለደ ሐጢያት ከመስራት በቀር ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ በዚህ መንገድ ይኖራል፤ በመጨረሻም ለጥፋት የታጨ ይሆናል፡፡
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያስቀመጠውን ድካሙን በመመልከት ለራሱ እያዘነ ይህንን የማይገፋ ሕይወት የሚኖረው ለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሄር ውብ የሆነውን ወንጌል ለሐጢያት እስረኞች እንዲሰብኩና ምርኮኞችንም ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ነጻ እንዲያወጡ መንፈስ ቅዱስን ሐጢያት ለሚሰሩና ለሞት ለታጩ ላከላቸው፡፡
 
 
የሚያለቅሱትንም ሁሉ ያጽናናቸዋል
 
እግዚአብሄር ለሚያለቅሱት ምን ሰጣቸው? እግዚአብሄር የይቅርታን ወንጌል በመስጠት የሚያለቅሱትን የዓለም ሕዝቦች በሙሉ ያጽናናል፡፡ እርሱ የሰውን ዘር ሐጢያቶች ይቅር ለማለት ኢየሱስ ክርስቶስን ወደዚህ ዓለም ላከው፡፡ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ ለማሻገርም በዮሐንስ እንዲጠመቅና በመስቀል ላይ እንዲሞት አደረገው፡፡ እግዚአብሄር ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ያነጻን በዚህ መንገድ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ እግዚአብሄር ከዓለም ሐጢያቶች ሁሉ አዳነን፡፡
ጌታችን ውብ የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማስታወቅ የሚያለቅሱትን ሁሉ ያጽናናል፡፡ ይህንን በማድረግ ምሉዕ ባልሆነ እምነት የሚሰቃዩትን ይባርካቸዋል፡፡ ይህንን ውብ ወንጌል እንዲሰብኩ፣ ልባቸው የተሰበረውን እንዲጠግኑና የሐጢያት ምርኮኞችን ነጻ እንዲያወጡ የሚመራው መንፈስ ቅዱስ ያላቸውን ብቻ ነው፡፡
በዚህ ዓለም ላይ የምንኖርበት አላማ በጌታችን ይቅርታን አግኝተን ውብ የሆነውን ወንጌል በሐጢያት ለታሰሩት መስበክና ከሐጢያት ነጻ መውጣት ለሚያስፈልጋቸው መጽናናትን መስጠት ነው፡፡ ሕይወታችን አጭር ቢሆንም ነገር ግን ከንቱ እንዳይደለ እግዚአብሄር ይነግረናል፡፡ እግዚአብሄር ለሰው ዘር የሐጢያት ስርየትንና ድንቅ በረከቶችን ማዘጋጀቱ ለዚህ እውነት ማረጋገጫ ነው፡፡
ጌታችን የሚያለቅሱትን ሁሉ በክብር አክሊል ሸለማቸው፡፡ ይህ ማለት ለኢየሱስ ጥምቀት ምስጋና ይግባውና ሐጢያተኞች የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ አግኝተው መንግስተ ሰማይ ሊገቡ ይችላሉ ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው ለሐጢያቶቹ ይቅርታን ሲያገኝ አእምሮው ይታደስና ይህንን ድንቅ በረከት ያደንቃል፡፡ ጌታችንም በክብር አክሊል ይሸልመዋል፡፡ እርሱ ለሐጢያተኞች የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመስጠት ያመኑትን ልጆቹ አደረጋቸው፡፡ በዚህ ውብ ወንጌል የሚያምኑ ከሐዘን ይልቅ ደስታ ይሰማቸዋል፡፡
ሰዎች ሁሉ የሚወለዱትና የሚሞቱት እያለቀሱ እንደሆነ ሁሉ ደስታ ጊዜያዊ ነው፡፡ አእምሮዋቸውም በአብዛኛው በሐዘን የተሞላ ነው፡፡ ይሁንና እግዚአብሄር ተገናኛቸውና በተስፋና በደስታ ዳግም እንዲወለዱ አደረጋቸው፡፡ ልክ እንደዚሁ ውብ በሆነው ወንጌል በማመን ዳግም የተወለዱ አዲስ ሕይወት ይኖራሉ፡፡ አዲስ ሥራም ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሄር የሚሻውን ለማድረግ ይችላሉ፡፡ ያም በዓለም ላይ ለሚኖሩ ሐጢያተኞች ሁሉ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመስበክ ሐዘንን ሁሉ ከልቦቻቸው አስወግደው በደስታና በሐሴት እንዲጥለቀለቁ ማድረግ ነው፡፡
እግዚአብሄር የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ የሰጣቸው ሰዎች ለእርሱ ክብርን ይሰጣሉ፡፡ እርሱ ጻድቃን ውብ የሆነውን ወንጌል እንዲሰብኩ ነገራቸው፡፡ እርሱ ማን እንደሆነ፣ ምን ወንጌል እንደሰጠንና ለእኛ ያዘጋጀው መንግስተ ሰማይ ምን ያህል ክቡር እንደሆነ እንዲሰብኩ ነገራቸው፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር እርሱ ይቅር ባላቸው ሰዎች ውስጥ ማየት እንችላለን፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ከመሞላታቸው በፊት ሲያለቅሱ የነበሩ አሁን በደስታ ይጥለቀለቃሉ፡፡ በሐጢያት ታስረው የነበሩ አሁን ነጻነት ይሰማቸዋል፡፡ ከንቱ ሕይወትን ሲኖሩ የነበሩም አሁን የጽድቅ ሕይወትን ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሄርን ክብር ያንጸባርቃሉ፡፡ እግዚአብሄር ጻድቃንን የጥንት ፍርስራሾችን እንደገና የሚገነቡ የቀድሞ ባድማዎችን የሚያነሱና የፈረሱትን ከተሞች የሚጠግኑ አድርጎ ገለጣቸው፡፡ በእርግጥ ይህ ውብ የሆነው የውሃና የመንፈስ ወንጌል በጥንቷ ቤተክርስቲያን ዘመን በሐዋርያቶች የተሰበከ ነበር፡፡ ኢየሱስ የዛሬ ሁለት ሺህ አመት ገደማ ወደዚህ ዓለም ተላከ፡፡ ውብ የሆነው የውሃና የመንፈስ ወንጌል እስከ 300 አ.ም ድረስ በዚህ ዓለም ላይ ተሰብከዋል፡፡ ዛሬ በጻድቃን የሚሰበከው ወንጌልም ሐዋርያቶች በዚያን ዘመን የሰበኩት ያው የመንፈስ ቅዱስ ወንጌል ነው፡፡ ነገር ግን በ4ኛው ምዕተ አመት መጀመሪያ ላይ ሮም ክርስትናን የመንግሥት ሐይማኖት በማድረግ ለዜጎች የሐይማኖት ነጻነትን በመስጠትዋ የኢየሱስ ጥምቀት ወንጌል ተበላሸና ቀስ በቀስም ጠፋ፡፡ ክርስትና ጽኑ ሐይማኖት ሆኖ ይበልጥ እያደገ በመጣበት በዚህ ጊዜ እውነተኛውን ወንጌል ይሰብኩ የነበሩት ሰዎችም የጠፉት ከዚህ በኋላ ነበር፡፡
በእውነተኛው ክርስትናና በእውነተኛው ወንጌል አምነው ይሰብኩ የነበሩት ሰዎች እምነት ለምን ተለወጠ? ክርስትና የሮማውያን መንግሥት ሐገራዊ ሐይማኖት ከሆነ በኋላ ክርስቲያኖች ከተለያዩ ዕቀባዎች ነጻ ወጥተው አንድ የሮም ዜጋ ያሉትን ተመሳሳይ መብቶች አገኙ፡፡ ያን ጊዜ ክርስቲያኖች የሮም መሳፍንቶችን ማግባት ቻሉ፡፡ በመንግሥት አገልግሎት ውስጥም ተሳታፊ ሆኑ፡፡ ከዚህ መብት የተነሳ እምነታቸው ከትነንሳኤ እምነት ወደ ተራ ሐይማኖት ዘቀጠ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ውብ የሆነው የውሃና የመንፈስ ወንጌል ጠፋ፡፡ የዘቀጠው አለማዊ የክርስትና መልክ ማበብ ጀመረ፡፡
በቅርቡ በሚሆነው ምጽዓቱ ወቅት ላይ የምንገኘውን እኛን የመጨረሻዎቹን ክርስቲያኖች ለረጅም ጊዜ የፈረሰውን የነበረውን ውብ የውሃና የመንፈስ ወንጌል እንድንሰብክና የሰውን ዘር ከሐጢያቶቻቸው እንድናድናቸው አዘዘን፡፡ እርሱ በሐዋርያት ዘመን ተሰብኮ የነበረውን የውሃና የመንፈስ ወንጌል ያድሳል፡፡ በሐዋርያት ዘመን የተሰበከው ወንጌል ውብ የሆነው የኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደሙ ወንጌል ነበር፡፡ እኛን የፈረሱትን ከተሞች የሚጠግኑ ሰዎች አድርጎ ጠራን፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እንድንማርና በእርሱም እንድናምን አድርጎናል፡፡ በወይኑ ቦታም የእርሱ ገበሬዎች አደረገን፡፡
እግዚአብሄር በሐዋርያት በኩል ያደረገውን ያንኑ ተልዕኮ ሰጠን፡፡ እናንተንና እኔንም ይህንን እውነተኛ የውሃና የመንፈስ ወንጌል እንድንሰብክ አደረገን፡፡ ‹‹የጌታ የእግዚአብሄር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እንድሰብክ ቀብቶኛልና፡፡›› እግዚአብሄር አስቀድመው መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት ወንጌልን እንዲሰብኩ አደረገና መንፈስ ቅዱስን ሰጠን፡፡
እግዚአብሄር በአበቦች ሸለመን፡፡ ሐዘንን ሁሉ አስወገደ፡፡ ደስታን በመለኮስ የምስጋናን መጎናጸፊያ አለበሰን፡፡ በልቦቻቸው ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ያለባቸው ሰዎች ሌሎችም እንዲቀበሉት የዚህን ውብ ወንጌል ዘሮች ይዘራሉ፡፡ ያን ጊዜ እነርሱም ደግሞ በጌታችን የተሰጠውን ወንጌል ይቀበላሉ፡፡ ይቅርታን ያገኙና በመጨረሻ መንፈስ ቅዱስን ይቀበላሉ፡፡
እኛ የእግዚአብሄር ሰራተኞች ሆነናል፡፡ እናንተና እኔ በመንግስተ ሰማያት ክብር ተባረክን፡፡ ሆኖም እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ የሌላቸውን ይህንን ውብ ወንጌል ማወቅ፣ ማየት ወይም መረዳት እንዳይችሉ አሳወራቸው፡፡ እነርሱ ሌሎችን በደፈናው በኢየሱስ እንዲያምኑ ሊያደርጉዋቸው ይችሉ ይሆናል፤ ነገር ግን በጭራሽ መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ሊያደርጉዋቸው አይችሉም፡፡
ጌታ መንፈስ ቅዱስ ባላቸው ሰዎች አማካይነት ቀጣዮቹን ነገሮች አድርጓል፡፡ ውብ የሆነው የምሥራች ለድሆች እንዲሰብኩና ልባቸው የተሰበረውን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እንዲጠግኑ አደረጋቸው፡፡ የሐጢያት ምርኮኞች ለሆኑትም እውነተኛውን የደህንነት ነጻነት አቀረበላቸው፡፡ የሚያለቅሱትንም ሁሉ ውብ በሆነው የውሃና የመንፈስ ወንጌል አጽናናቸው፡፡ ከድካሞቻቸው የተነሳ በሐጢያት የታሰሩትን ነጻ አወጣቸው፣ ደስታንና ተስፋን ሰጣቸውና ወደ ሰማይ አረገ፡፡
ይህንን ተከትሎ በውስጣችን ያደረው መንፈስ ቅዱስ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለሰዎች ሁሉ እንድንሰብክ አደረገን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የሐጢያት ይቅርታን ላገኙትና በውስጣቸው መንፈስ ቅዱስ ላላቸው ሐጢያተኞች ሁሉ ከሐጢያቶቻቸው እንዲድኑ ነገራቸው፡፡ እግዚአብሄር ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ላላቸው ሰዎች ሊያደርገው ያቀደውን እንዲቆጣጠሩ ሐይልን አስታጠቃቸው፡፡ ጻድቃን ሰዎች ሁሉ የእርሱን ሥራ እንዲሰሩ አደረገ፡፡ እኛ የእርሱ ሰራተኞች ነን፡፡ የወይኑ ቦታ በሆነችው የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ መጋቢዎች ሆነን ተሹመናል፡፡ እኛ የእርሱ ባሮች ነን፤ እግዚአብሄርም እነዚህን አስገራሚ በረከቶች ሰጥቶናል፡፡
ሥጋችንን ስንመለከት ድካሞቻችንን እንገነዘባለን፡፡ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ስለሚሰራ በእርሱ አምነን በእምነት የእርሱ ባሮች ሆነናል፡፡ እግዚአብሄር በእኛ አማካይነት ብዙ ታላላቅ ሥራዎች እንደሚሰራና ግዛቱን በእኛ ላይ እንደሚያስፋፋ እናምናለን፡፡
እግዚአብሄር በፈራረሱት ከተሞች ውስጥ ባድማ የሆነውን የወንጌል ግምብ እንደገና ለመገንባት ወሰነ፡፡ የጥንቶቹን ባድማዎች እንደሚያስነሳና የፈራረሱትንም ከተሞች እንደሚጠግን ተሰፋ ሰጠ፡፡ እንደገና በዓለም ሁሉ ላይ የወንጌል መነቃቃት እንደሚሆን አምናለሁ፡፡
ሆኖም ይህ የእኔ ፈቃድ አይደለም፡፡ ይህንን ያመንሁት እግዚአብሄር እንደሚሆን ስለተናገረ ነው፡፡ ጌታችን መንፈስ ቅዱስ ያለባቸው ሰዎች ይህንን ውብ የሆነ ወንጌል ለመላው ዓለም እንዲሰብኩ አደረጋቸው፡፡ እርሱ ልጁን ወደዚህ ዓለም ላከና ወንጌልን ፈጸመ፡፡ እርሱ መንፈስ ቅዱስ ባለን በእኛ አማካይነት እንደገና ፈቃዱን እንደሚያከናውን አምናለሁ፡፡ በዚህ ውብ በሆነው ወንጌል የሚያምኑ የእግዚአብሄርን ክብር ያያሉ፡፡ ሐሌሉያ!