Search

Sermons

ርዕስ 8፡ መንፈስ ቅዱስ

[8-17] በመንፈስ ቅዱስ እምነትና ተስፋ ሊኖረን ይገባል ‹‹ ሮሜ 8፡16-25 ››

በመንፈስ ቅዱስ እምነትና ተስፋ ሊኖረን ይገባል
‹‹ ሮሜ 8፡16-25 ››
‹‹የእግዚአብሄር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል፡፡ ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን ማለት የእግዚአብሄር ወራሾች ነን፡፡ አብረንም ደግሞ እንድንከብር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን፡፡ ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ፡፡ የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሄርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና፡፡ ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፤ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም፡፡ ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነጻነት ወጥቶ ለእግዚአብሄር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነጻነት እንዲደርስ ነው፡፡ ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና፡፡ እርሱም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን የመንፈስ በኩራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን፡፡ በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፡፡ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን፡፡››
 
 

አሁን ዘመኑ ተስፋ የሌለበት ነው

 
ጻድቃን በመንፈስ ቅዱስ ተስፋ የሚያደርጉት ለምንድነው?
ምክንያቱም ዳግም ያልተወለዱ ሰዎች ከዚህ አለም መውደቅ ጋር አብረው ቢጠፉም  እኛ ዳግም የተወለድን ክርስቲያኖች የአዲሲቱ ሰማይና ዓለም ወራሾች ስለምንሆን ነው፡፡
 
አሁን በዚህ ዓለም ላይ እውነተኛ ተስፋ አለን? የለም፡፡ ተስፋ ያለው በኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ ይህ ዘመን የጥርጣሬና የተስፋ ቢስነት ዘመን ነው፡፡ ሁሉም ነገር በየቀኑ በፍጥነት ይለዋወጣል፡፡ ሰዎችም ከእነዚህ ፈጣን ለውጦች ጋር አብረው ለመዝለቅ በርትተው ይሞክራሉ፡፡ እነርሱ መንፈሳዊ እውነት አይፈልጉም፡፡ ለመንፈሳዊ ሐሴትም አንዳች ትኩረት የላቸውም፡፡ በፈንታው ውድቀትን ለማስወገድና የዚህ ዓለም ባሮች ሆነው ለመኖር ይታገላሉ፡፡
አዳዲስ ሥራዎች ይፈጠራሉ፡፡ አሮጌ ሥራዎች ይሞታሉ፡፡ ሰዎችም እንደዚሁ አስገራሚ በሆኑ ለውጦች ውስጥ እያለፉ ነው፡፡ ስለዚህ በጣም ባተሌ የሆነና የሚያስጨንቅ ኑሮን ይኖራሉ፡፡ ቀስ በቀስም በዚህ ዓለም ላይ ያላቸው ተስፋ ይከስማል፡፡ ለዚህም ምክንያቶች ከሆኑት አንዱ ለወደፊቱ ምንም ዋስትና የሌለው ሕይወት እየመሩ መሆናቸው ነው፡፡ እየኖርን ያለነው እንደዚህ ባለው ያልተረጋጋ ዓለም ውስጥ ነው፡፡
 
 

በመንፈስ ቅዱስ ለዘላለማዊ ሕይወት ተስፋ ማድረግ አለብን

 
እውነተኛ ተስፋ ልናገኝ የምንችለው እንዴት ነው? ይህንን ተስፋ ልናገኝ የምንችለው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ ሰዎች ተስፋ ያለው በምድር ላይ ሳይሆን በሰማይ ነው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ እውነተኛው ሰማያዊ ተስፋ ተናገረ፡፡ አስቀድመን ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ የተቀበልን ሰማያዊ ነገሮችን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ይህንን የምናደርገው ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ለመውሰድ እንደመጣና በዮሐንስ በኩል በሆነው ጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ እንዳዳነን ስለምናምን ነው፡፡ ጌታ የሐጢያት ይቅርታ በሚያስገኘው ወንጌል ለሚያምኑ ሰማያዊ ተስፋን ለገሰ፡፡
ሮሜ 8፡19-21 እንዲህ ይላል፡- ‹‹የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሄርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና፡፡ ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፤ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም፡፡ ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነጻነት ወጥቶ ለእግዚአብሄር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነጻነት እንዲደርስ ነው፡፡››  ፍጥረት ሁሉ ከጥፋትና ከሞት ባርነት ነጻ ለመውጣት ተስፋ ያደርጋል፡፡
በዚህ ዓለም ላይ ያሉት ነገሮች ሁሉ እንከን ያለባቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄር ልጆች እንዲገለጡ በመቃተት ይጠብቃሉ፡፡ በተጨማሪም ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥተው ለዘላለም ለመኖር ይናፍቃሉ፡፡ ፍጥረት ሁሉ ከቶውኑም የማይበሰብስበትንና የማይጠወልግበትን ነገር ግን ለዘላለም የሚኖርበትን ቀን ይጠብቃል፡፡
አንድ ቀን በእግዚአብሄር የተፈጠሩ ፍጥረቶች ሁሉ ይታደሳሉ፡፡ በዚህ ዓለም ላይ አበባ ቢደርቅና ቢጠወልግም በአዲሱ ዓለም ግን ሁሌም እያበበ ለዘላለም ይኖራል፡፡ እኛ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ያለን ሰዎችም እንደዚሁ ይህንን አዲስ ዓለም እናያለን፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ይመጣና ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ያለባቸውን እንደሚያስነሳና ለእያንዳንዳቸውም የማይበሰብስና የማይሞት አዲስ አካልና የዘላለምን ሕይወት እንደሚሰጣቸው ቃል ገባ፡፡ ለዘላለምም ከእግዚአብሄር ጋር አብረው በሰማይ እንደሚኖሩም ተስፋ ሰጠ፡፡ በዓለም ላይ ያሉ ፍጥረቶች ሁሉ ያንን ቀን እየጠበቁ ነው፡፡ እነርሱም ደግሞ ያ ቀን ሲመጣ የእግዚአብሄር ልጆች ከሆንነው ከእኛ ጋር አብረውን ይኖራሉ፡፡
 
 
ይህ ዓለም በተስፋ ሲታይ  
 
ይህ ሕልም ለጻድቃን የሚፈጸመው መቼ ነው? የሚፈጸመው ጌታችን ሲመጣ ነው፡፡ ይህንን ዓለም ስንመለከት በተስፋ መሆን አለበት፡፡ ኢየሱስ ረሃብ፣ ቸነፈር፣ የመሬት መናወጥና ጦርነቶች በተለያዩ ሥፍራዎች እንደሚሆኑ ተናገረ፡፡ (ማቴዎስ 24፡7) ፍጻሜው ግን ገና አልመጣም፡፡ በዚህ ዓለም የመጨረሻ ቀን ጌታችን ዳግመኛ ይመጣና ዓለማዊ ነገሮችን ሁሉ በማደስ መንፈሳዊ የሆነውን የማይሞት አካል ይሸልመናል፡፡ ይህ ማለት ተክሎችና እንስሶችም አለመሞትን ይቀበላሉ ማለት ነው፡፡ ይህንን በማመን ዓለምን በታደሰ ተስፋ ማየት ይገባናል፡፡
በዚህ ዓለም ላይ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ያላቸውም ሰዎች እንደዚሁ የእርሱ ልጆች ሆነን የሰውነቶቻችንን የቤዛነት ክብር በጉጉት እየተጠባበቅን ከፍጥረት ሁሉ ጋር አብረው በራሳቸው ውስጥ ይቃትታሉ፡፡ ጌታ በሚመለስበት ጊዜ በጭራሽ የማንበሰብስና የማንሞት ልጆቹ ስለሚያደርገን አለምን በተስፋ እናያለን፡፡ 
አንድ ቀን ዓለም የሚጠፋ ቢሆንም ጌታ ዳግመኛ ሲመጣ ሁሉም ነገር ይታደሳል፡፡ ያንን በማመን በተስፋ መኖር አለብን፡፡ የታደሰው ዓለም በአፈ ታሪክ ውስጥ እንዳነበባችሁት እንደ ማንኛውም ውብ ዓለም አስደሳችና አስደናቂ ይሆናል፡፡ እንደዚህ ባለ ዓለም ውስጥ ለሺህ አመት ስለ መኖር አስቡ፡፡  መንግሥተ ሰማይ ስንገባም ደግሞ የእርሱ ልጆች ሆነን የዘላለም ሕይወት ይኖረናል፡፡ እንደዚህ ባለ ተስፋ መኖር አለብን፡፡
በዚህ ዓለም ውስጥ አንዳች ተስፋ ታያላችሁን? አታዩም፡፡ ሰዎች በፈንጠዚያ ይኖራሉ፡፡ ምክንያቱም በዚህ ዓለም ውስጥ አንዳች ተስፋ የላቸውምና፡፡ ጌታችን ግን ይቅርታን ላገኙትና ጻድቃን ለሆኑት የሰማይን ተስፋ ሰጥቶዋቸዋል፡፡ ‹‹ተስፋ አይደለም፡፡ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን፡፡›› ይህ ማለት በእግዚአብሄር ቃሎች አምነን ስለዳንን የኢየሱስን መመለስ በትዕግስት መጠበቅ አለብን ማለት ነው፡፡      
ከሐጢያቶቻችን ስለዳንን በነፍሳችን ውስጥ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ አለን፡፡ ያም ማለት በኢየሱስ ይቅርታን ያገኙ በልባቸው ውስጥ በሐጢያት ፋንታ መንፈስ ቅዱስ አለ ማለት ነው፡፡ ታዲያ ሰውነቶቻችንስ? ደካማዎቹ ሰውነቶቻችንም እንደዚሁ ትንሣኤን ያገኙና አዲስ ሕይወትንና አለመሞትን ይቀበላሉ፡፡ ኢየሱስ ሲመጣ ከእግዚአብሄር ጋር አብረን ለዘላለም እንኖራለን፡፡ ይህንን በተስፋ ማድረግ መብቱ ያላቸው ዳግም የተወለዱት ብቻ ናቸው፡፡ ስለዚህ መንፈሳችንና ሥጋችን ፍጹማን ይሆናሉ፡፡ ሥጋችን ዘላለማዊ ይሆናል፡፡ በጭራሽ አንታመምም፡፡ ዓለማዊ ሰውነቶቻችን ደካማ ናቸው፤ ስለዚህ ፍጹም የሆነ ሕይወት መኖር አይቻለንም፡፡ ያን ጊዜ ግን ፍጹም የሆነ ሕይወት እንኖራለን፡፡ የጌታችንን ዳግም መምጣት እንጠብቅ፡፡ የዚያ አይነት ተስፋና ሕይወት ሊኖራቸው የሚችለው ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ያላቸው ብቻ ናቸው፡፡
የቅዱሳን ተስፋ ያለው በሰማይ ብቻ ሳይሆን በዚህ ዓለም ላይም እውነተኛ ይሆናል፡፡ ጌታችን ይህ ዓለም በታላቁ መከራ ውስጥ ከወደቀ በኋላ ዳግመኛ እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ እርሱ በእርግጥም ይመጣል፡፡ ለመጀመሪያ በመጣ ጊዜ ለሐጢያተኞች ሲል ተጠመቀ፡፡ እነርሱን ጻድቃን ለማድረግም በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ በመጨረሻም ወደ ሰማይ አረገ፡፡ አሁን ጌታ ዳግም የሚመጣበት ዘመን ነው፡፡ 
ያን ጊዜ በኢየሱስ ያመኑትና ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ የተቀበሉትን ያንቀላፉ ቅዱሳን በሙሉ ያነቃቸውና ከመበስበስ ባርነት ነጻ ያወጣቸዋል፡፡ ከቶውንም የማይበሰብሱና የማይታመሙ አዲስ ሰማያዊ አካሎችም ይሰጣቸዋል፡፡ በተጨማሪም እርሱን በአየር ለመገናኘት በደመናት ይነጠቃሉ፡፡ እርሱም ሁሉን አዲስ ያደርጋል፡፡ 
ከዚያ በኋላ እኛም ከጌታችን ከኢየሱስ ጋር አብረን እንኖራለን፡፡ ወንጌልን በማገልገላችንም ካሳ ይሆነን ዘንድ በአዲሱ ዓለም ውስጥ ለሺህ አመት እንነግሳለን፡፡ ይህ ወደ ሰማይ ለሚሄዱት መዘጋጂያ ነው፡፡ ይህ የሰማይ ተስፋና እውነታ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ፍጹም ያልሆኑት ነገሮች ሁሉ ወደ ፍጹምነት ይለወጣሉ፡፡ የሚበሰብሱትም ከቶውኑ አይበሰብሱም፡፡ ‹‹የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው፤ በመበስበስ ይዘራል፤ ባለመበስበስ ይነሳል፡፡›› (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡42) የሚሉት ቃሎችም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በዚያን ጊዜ ይፈጸማሉ፡፡ 
ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ያለን ሰዎች ተስፋ እናድርግ! ሁሉም ነገር የሚደክምና የሚሞት ቢሆንም መጨረሻው ይህ እንዳልሆነ ማስታወስ ይኖርባችኋል፡፡ ጌታችን መላውን ዓለም ዳግም አዲስ እንደሚያደርገው ተስፋ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ አዲሱን ሰማይና ምድር ተስፋ በማድረግ ልንኖር ይገባናል፡፡ ይህ ተስፋ ካለን ወንጌልን መስበክ እንችላለን፡፡ 
ከዓለም ሐጢያቶች ስለዳንን ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ አለን፡፡ ልክ እንደዚሁ በውስጣችን ያለው መንፈስ ቅዱስም የጌታን ምጽዓት አርቆ ይመለከታል፡፡ በልቦቻችን ተስፋ ሳንቆርጥ በተስፋና በእምነት እንድንኖርም በእኛ ፋንታ ለእግዚአብሄር አብ ምልጃዎችን ያደርግልናል፡፡
 

በመንፈስ ቅዱስ ተስፋ ልንኖር ይገባናል
 
የጻድቃን ስፍራ የት ነው? ጌታ ዳግም መጥቶ ይህችን ምድር በሚያድስበት 5በሺህው ዓመት በመንግስተ ሰማይ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ያ ቀን እስኪመጣ ድረስ በትዕግስት መጠበቅ አለብን፡፡ ይህ ዓለም ሲወድቅ ጌታችን አካላችንን ፍጹም እንደሚያደርገው ማመን አለብን፡፡ ለነገው ክብር ተስፋ ሊኖረን ይገባል፡፡ ለነገው ክብር ተስፋ ሊኖረን ይገባል፡፡
 
[5] በቃሉ መሰረት ጌታ ኢየሱስ ወደዚህ ምድር ዳግም ሲመጣ ከሰማይ ይወርዳል፡፤ በመጀመሪያም በክርስቶስ የሞቱትን ያስነሳል፡፡ ይህነን ተከትሎም በሕይወት ያሉትንና የተነሱትን ቅዱሳኖች በሙሉ ወደማይበሰብስና ወደማይሞት አካሎች ይለውጣቸዋል፡፡ ጌታን በአየር እንዲገናኙትም ቅዱሳንን ሁሉ ወደ ደመናዎች ይነጥቃቸዋል፡፡ (1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16-17፤1ኛ ቆሮንቶስ 15፡51-53) 
ከዚያም በሚቀሩት ሐጢያተኞች ላይ ሰባቱን የቁጣውን ጽዋዎች ካፈሰሰ በኋላ ሁሉንም ነገሮች አዲስ ያደርጋል፡፡ በታደሰችው ምድር ላይም መንግስቱን ይመሰርታል፡፡ በመጀመሪያው ትንሳኤ ዕድል ፈንታ ካገኙት ጋርም ለሺህ አመት ይነግሳል፡፡ (ዮሐንስ ራዕይ 20፡4-5) ከሺህው አመት በኋላ በሙታኖች ሁሉ ይፈርድና ወደ እሳት ባህር ይጥላቸዋል፡፡ (ዮሐንስ ራዕይ 20፡11-15) ከዚያም የእርሱን ሕዝቦች በሙሉ ወደ ሰማያዊቷ ከተማ ወደ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ያስገባቸዋል፡፡ ለዘላለምም ከእነርሱ ጋር ይኖራል፡፡ (ራዕይ 21፡1-4) 
 
ጳውሎስ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ስለነበረው እኛ የያዝነውን አይነት ተስፋ ይዞ ነበር፡፡ እኛም ሺህዉን አመትና መንግሥተ ሰማያትን እየተጠባበቅን በዚሁ አይነት ተስፋ እንኖራለን፡፡ ዳግም ያልተወለዱት ይህ ዓለም ሲጠፋ አብረው ይጠፋሉ፡፡ ነገር ግን እኛ ዳግም የተወለድን ክርስቲያኖች አዲሱን ሰማይና ምድር እንወርሳለን፡፡ ይህ ተስፋ በእርግጥም ይመጣል፡፡ አካሎቻችንም ፍጹም ይሆናሉ፡፡ እኛም በአዲሱ ዓለም ውስጥ ለሺህ አመት ከጌታ ጋር እየኖርን እንገዛለን፡፡ ያንን ቀን አርቀን ስንመለከት ተስፋ ስለሚኖረን በዚህ ዓለም ላይ ያለ ፍርሃት እንኖራለን፡፡
እንታገስና እንጠብቅ፡፡ ሕይወታችን አሰልቺ ቢሆንም ተስፋዎቻችን ይፈጸማሉ፤ ምክንያጡም በእግዚአብሄር እናምናለንና፡፡ ተስፋ የሌላቸው ሰዎች ከሙታን ተለይተው አይታዩም፡፡ እባካችሁ ተስፋ ይኑራችሁ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃሎች በማመንም ሕልሞቻችሁን ጠብቁ፡፡
ይቅርታችን ተጨባጭ እንደሆነ ሁሉ በአካሎቻችን ላይ የሚሆኑት ለውጦችም ተጨባጭ ይሆናሉ፡፡ ፍጥረታት በሙሉም የዘላለምን ሕይወት የሚያገኙ መሆናቸውም እንደዚሁ ተጨባጭ ነው፡፡ ተስፋችንም እንደዚሁ ተጨባጭ ነው፡፡ በምታምኑት ነገር እምነት ይኑራችሁ፡፡ ተስፋ ያላቸው ውብና ደስተኞች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሰዎች ደስታ የሚርቃቸው ተስፋ ቢስ ሲሆኑ ነው፡፡ አንዳች ሕልሞች የሌላቸው ደስታ የላቸውም፡፡ በሺህው አመት፣ በመንግስተ ሰማይና በአዲሱ ሰማይና ምድር ተስፋ ስለምናደርግ ደስተኛ ኑሮ መኖር እንችላለን፡፡
ጻድቃን ተስፋ ሊኖራቸውና ይህንንም ተስፋ በመንፈስ ቅዱስ ሊሰብኩ ይገባቸዋል፡፡ ወንጌላችን በመላው ዓለም እንዲሰራጭ ተስፋ ማድረግ አለብን፡፡ ጽኑ እምነት ካላችሁ ዓለም ያን ያህል ትልቅ እንደሆነ ትገነዘባላችሁ፡፡ ጅማሬያችን ታናሽ ቢሆንም ከተስፋ ጋር ጽናት ካለን ወንጌልን በዓለም ሁሉ መስበክ እንችላለን፡፡ ጳውሎስ እንዳደረገው ማመን አለብን፡፡
ተስፋ ያላቸው ይህንን ውብ ወንጌል በመስበክ ሥራቸው ታማኞች ናቸው፡፡ በዚህ የተስፋ ቢስነት ዘመን ውስጥ ወንጌል እንዲሰራጭ ተስፋ ማድረግ አለብን፡፡ ለተሰላቹት፣ ተሰፋ ለቆረጡት፣ ለድሆችና ለትሁታን ውብ የሆነውን ወንጌል በማመን የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ ያገኙት ብቻ መግባት ስለሚችሉበት መንግሥተ ሰማይ ተስፋን በመስበክ ከጨለማ ነጻ ልናወጣቸው እንችላለን፡፡ የእግዚአብሄር ዓለም ከዚህ የመከራ ዘመን በኋላ ድንገት እንደ ሌባ እንደሚመጣ በመንገር ተስፋ እንዲኖራቸው ልናነሳሳቸው ይገባል፡፡
ዳግም የተወለዱ አገልጋዮችና ቅዱሳን የሰማይ ተስፋችሁን አጥብቃችሁ በመያዝ እባካችሁ ይህንን ወንጌል እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ስበኩ፡፡ ይህ ዓለም ምንም ያህል ፈጥኖ ቢወድቅም ተስፋ ያላቸው ከቶውኑም አይጠፉም፤ ምክንያቱም ከዚህ ምድራዊ ሕይወት ያለፈ አንዳች ዘላለማዊ ነገር አላቸውና፡፡ ጌታ የሰጣቸው ሁለተኛ ሕይወት እንዳላቸው እርግጥ ነው፡፡