Search

EBOOKS Y AUDIOLIBROS GRATUITOS

El Evangelio del agua y el Espíritu

Amhárico  2

ወደ ውኃውና መንፈሱ ወንጌል ተመለሱ [አዲስ የተከለሰ ዕትም]

Rev. Paul C. Jong | ISBN 9788928262328 | Páginas 331

Descargue eBooks y audiolibros GRATIS

Elija su formato de archivo preferido y descárguelo de forma segura en su dispositivo móvil, PC o tableta para leer y escuchar las colecciones de sermones en cualquier momento y lugar. Todos los eBooks y audiolibros son completamente gratuitos.

Puede escuchar el audiolibro a través del reproductor de abajo. 🔻
📖 Leer en línea ahora
Tenga un libro en rústica

ማውጫ

  • 0. መቅድም — 7
  • 1. የጥንቱ ዳግም የመወለድ ወንጌል ምንድነው? (ዮሐንስ 3፡1-6) — 17
  • 2. በክርስትና ውስጥ ያሉ አምልኮተ ሰቦችና መናፍቃን (ኢሳይያስ 28፡13-14) — 73
  • 3. ወንጌል በደም ብቻ፣ በውሃ ብቻ ነው ወይስ በውሃና በደም በሁለቱም? (ዘጸአት 12፡43-49) — 135
  • 4. ትክክለኛው ኑዛዜ ምንድነው? (1ኛ ዮሐንስ 1፡9) — 185
  • 5. የቅድመ መወሰንና የምርጫ ጽንሰ አሳቦች ስህተቶች (ሮሜ 8፡28-30) — 195
  • 6. የተለወጠ መሥዋዕት (ዕብራውያን 7፡1-28) — 225
  • 7. ስለ መጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎት የተሳሳቱ መረዳቶችን ድል በመንሳት ምስጋናን በእምነት ለጌታ እንስጥ (ማቴዎስ 11፡1-11) — 269
  • 8. ኢየሱስ በተቀበለው ጥምቀትና ባፈሰሰው ደሙ ሥራ በማመን መዳን እንችላለን (ኢሳይያስ 53፡4-10) — 291

ወደ ውኃውና መንፈሱ ወንጌል እንመለስ፡፡

የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ኃጢአቶቼን በሙሉ አንጽቷል

‹‹በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን?›› በሚለው መጽሐፌ ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጠው የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መስክሬያለሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ የመጀመሪያው መጽሐፍ ተከታይ ነው፡፡ እግዚአብሔር ባቀደው መንገድ ዳግም የመወለድን እውነት በጥልቀት ለመቆፈር ሞክሬያለሁ፡፡
የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በእነዚህ ቀኖች ገናና ከሆነው ሐሰተኛ ወንጌል ጋር በማነጻጸር የእውነተኛው ወንጌል መረዳታችሁ እንዲጨምር ለማገዝ ሞክሬያለሁ፡፡ ከሁሉም በላይ አሁን ያለው ሥነ መለኮት እንዴት ብዙ ሰዎችን ወደ ስህተት እንደከተታቸውና እውነተኛውን ወንጌል እንዳያዩ እንዳደረጋቸው ላግዛችሁ ሞክሬያለሁ፡፡
ሥነ መለኮትና ትምህርቶች በራሳቸው ሊያድኑን አይችሉም፡፡ ነገር ግን ብዙ ክርስቲያኖች አሁንም እነርሱን ይከተላሉ፣ ከዚህ የተነሣ ገና ዳግም አልተወለዱም፡፡ ይህ መጽሐፍ ሥነ መለኮትና ትምህርቶች ምን ስህተቶችን እንደሠሩና ተገቢ በሆነ መንገድም እንዴት በኢየሱስ እንደምናምን በግልጥ ይነግረናል፡፡
አሁን ሁላችንም እግዚአብሔር ወደሰጠን አስገራሚ የተባረከ የውሃና የመንፈስ ወንጌል እንመለስ፡፡
Más
Libro Impreso Gratis
Agregar libros al Carrito
Reproductor de audiolibros

Revisiòn de libros por lectores

  • እውነተኛው ዳግም የመወለድ ወንጌል ትርጉም ምንድነው?
    Daniel Tesfaye , Ethiopia

    እውነተኛው ዳግም የመወለድ ወንጌል ትርጉም ምንድነው?
    ኢየሱስ የእስራኤል መምህር ለነበረው ለኒቆዲሞስ " እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።" ብሏል።(የዮሐንስ ወንጌል 3:5)
    እግዚአብሔር የሰው ዘርን በሙሉ በክርስቶስ ለማዳን ዓለሙን እንዲሁ ወዷል (ዮሐንስ3:16) እግዚአብሔር እንዴት እንደወደደን ያለማያውቅና ያለማመን እንጂ በእግዚአብሔር ያልተወደደ ሰው የለም።
    የእግዚአብሔርን ፍቅር በትክክል ባለማወቅ ምክንያት የብዙዎች ክርስትና የማስመሰል ሕይወት ሆኗል። ይህ አሳዛኝ ነው! አስመሳይ ክርስቲያን ወይም መናፍቅ ላለመሆን በክርስቶስ ጥምቀትና ሞት የተደረገልንን የልብ ግርዛት መቀበል አለብን።
    እውነተኛ የልብ መገረዝ የምናገኘው ደግሞ ኃጢአቶቻችንን በትክክል ተረድተን (ማርቆስ 7:21-23) በእግዚአብሔር ፊት መናዘዝ ስንችል ነው። እውነተኛ ኑዛዜ ተፈጥሮአዊ ማንነትን የክፉ ዘሮች መሆናችንን ለእግዚአብሔር መንገር ነው።
    ከዚያም በሙሉ ልባችን
    እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት የእድሜ ዘመን ኃጢአቶቻችንን ከእኛ ላይ ቆርጦ እንደወሰደውና ኢየሱስ በመስቀል ጠርቆ እንዳስወገደው ማመን ይገባናል።
    የኢየሱስን ዘላለማዊ ክህነት እና ቤዛነቱን በማመን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ልናደርግ ይገባል።

    Más

Libros relacionados con este título