Search

Sermones

ርዕስ 4፡ የዘወትር ሐጢያቶችን መፍታት

[4-1] የተትረፈረፈው ቤዛነት ወንጌል (ዮሐንስ 13፡1-17)

የተትረፈረፈው ቤዛነት ወንጌል (ዮሐንስ 13፡1-17)
(ዮሐንስ 13፡1-17)
“ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው። እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው አሳብ ካገባ በኋላ፥ ኢየሱስ አብ ሁሉን በልጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥ ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ። በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ። ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ። እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው። ጴጥሮስም፦ የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም አለው። ኢየሱስም፦ ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም ብሎ መለሰለት። ስምዖን ጴጥሮስም፦ ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው። ኢየሱስም፦ የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው፤ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፥ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም አለው። አሳልፎ የሚሰጠውን ያውቅ ነበርና ስለዚህ ሁላችሁ ንጹሐን አይደላችሁም አለው። እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ፥ እንዲህም አላቸው፦ ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን? እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ። እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል። እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም፤ መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም። ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።”
 
 
ኢየሱስ ከፋሲካ በዓል በፊት ባለው ቀን የጴጥሮስን እግር ያጠበው ለምንድነው? የጴጥሮስን እግሮች በማጠብ ላይ እያለ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ።” ጴጥሮስ ከኢየሱስ ደቀ መዛሙርቶች ምርጥ የተባለ ሰው ነበር። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደነበር አምኖ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደነበርም መስክሮዋል። ኢየሱስ እግሩን ሲያጥበው ይህንን ያደረገበት ጥሩ ምክንያት ያለው መሆን አለበት። ጴጥሮስ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ያለውን እምነት በመሰከረ ጊዜ ኢየሱስ እርሱን ከኃጢአቶቹ ሁሉ የሚያድነው አዳኝ መሆኑን እንዳመነ መናገሩ ነበር።
 
ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበው ለምንድነው?
ምክንያቱም ደቀ መዛሙርቱ የእርሱን ፍጹም ድኅነት እንዲያስተውሉ ስለፈለገ ነበር።
 
እርሱ የጴጥሮስን እግር ለምን አጠበ? ኢየሱስ ጴጥሮስ በቅርቡ ሦስት ጊዜ እንደሚክደውና ወደፊትም ኃጢያት መሥራት እንደሚቀጥል ስላወቀ ነበር።
ኢየሱስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ጴጥሮስ በልቡ ውስጥ የቀረች አንዲት ኃጢአት ኖሮበት ቢሆን ኖሮ ከኢየሱስ ጋር ሊስማማ አይችልም ነበር። ኢየሱስ ግን የደቀ መዛሙርቱን ድክመቶች በሙሉ ያውቅ ስለነበር ኃጢአቶቻቸው በእርሱና በደቀ መዛሙርቶቹ መካከል ጣልቃ እንዲገቡ አልፈለገም። ስለዚህ ኢየሱስ ኃጢአቶቻቸው በሙሉ ቀድሞውኑ እንደተነጹ ሊያስተምራቸው አስፈላጊ ነበር። የደቀ መዛሙርቱን እግሮች ያጠበበት ምክንያቱ ያ ነበር። ኢየሱስ ከመሞቱና ከእነርሱ ከመለየቱ በፊት፣ በጥምቀቱ ወንጌል አማካኝነት በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ የሠሩትን ኃጢአቶች ሙሉ በሙሉ እንዳስወገደ እንዲረዱ አደረጋቸው።
ዮሐንስ 13 ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ስለፈጸመው ፍጹም መዳን ይናገራል። ኢየሱስ እግሮቻቸውን እያጠበ ሳለ፣ ሰዎች ሁሉ ከበደሎቻቸው ሁሉ የሚነጹበትን የጥምቀቱ ወንጌል ጥበብ ነገራቸው።
“ወደፊት በዲያብሎስ አትታለሉ። በዮርዳኖስ ወንዝ በተቀበልሁት ጥምቀቴ ኃጢአቶቻችሁን በሙሉ ወስጃለሁ፣ እናም በመስቀል ላይ ለእነርሱ ፍርድን እቀበላለሁ። ከዚያም ከሙታን እነሣለሁ እናም ለሁላችሁ ዳግም መወለድን የሚያመጣውን መዳን እፈጽማለሁ። የወደፊት ኃጢአቶቻችሁን አስቀድሜ እንዳጠብኩ ላስተምራችሁ፣ የኃጢአቶችን በሙሉ የሚያስወግደውን እውነተኛውን ወንጌል ላስተምራችሁ፣ ከመሰቀሌ በፊት እግሮቻችሁን እያጠብኩ ነው። ይህ የዳግም መወለድ ወንጌል ምስጢር ነው። እናንተም ሁላችሁ በዚህ ማመን አለባችሁ።”
ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግሮች ያጠበበትን ምክንያት እና “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ” ያለበትን ምክንያት ሁላችንም መረዳት አለብን። ያን ጊዜ ብቻ ነው ዳግም በመወለድ ወንጌል ማመን የምንችለውና እኛም በእውነት ዳግም መወለድ የምንችለው።
 
 
እርሱ በዮሐንስ 13 ላይ እንዲህ አለ
 
መተላለፍ ምንድነው?
ደካሞች በመሆናችን ምክንያት በየቀኑ የምንሠራቸው ኃጢአቶች ናቸው።
 
በመስቀል ላይ ከመሞቱ በፊት፣ ኢየሱስ የፋሲካን በዓል አደረገ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እና የኃጢአቶቻቸው ሙሉ በሙሉ መታጠብን የሚመለከተውን ወንጌል አረጋገጠላቸው በራሱ እጆች እግሮቻቸውን በማጠብ።
“ኢየሱስ አብ ሁሉን በልጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥ ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ። በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ። ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ። እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው” (ዮሐንስ 13፡3-7)።
ለደቀ መዛሙርቱም በጥምቀቱ ውሃ አማካይነት የጥምቀትንና የኃጢአቶችን ማስተስረያ ወንጌል አስተማራቸው።
በወቅቱ ለኢየሱስ ታማኝ የሆነው ጴጥሮስ ጌታ ኢየሱስ ለምን እግሮቹን እንዳጠበው መረዳት አልቻለም ነበረ። ኢየሱስ ለጴጥሮስ ከተናገረ በኋላ፣ ጴጥሮስ በኢየሱስ ያመነበት መንገድ ተለወጠ። ኢየሱስ ስለ ኃጢአት ሙሉ በሙሉ መንጻት፣ ስለ እርሱ ጥምቀት ውሃ ወንጌል ሊያስተምረው ፈለገ።
እርሱ ጴጥሮስ ወደፊት ከሚሠራቸው ኃጢአቶቹ ሁሉ በተለይም ወደፊት በሥጋው ከሚሠራቸው ኃጢአቶች የተነሳ ወደ እርሱ ሊመጣ እንደማይችል ተጨንቆ ነበር። ኢየሱስ እግሮቻቸውን ያጠበው ዲያብሎስ የደቀ መዛሙርትን እምነት እንዳይወስድ ነበር። በኋላም ጴጥሮስ ምክንያቱን ተረዳ።
ኢየሱስ በእርሱ የጥምቀት ውሃና ደም ያመነ ማንኛውም ሰው ለዘላለም ከኃጢአቶቹ ሁሉ እንዲዋጅ መንገዱን አዘጋጀ።
በዮሐንስ 13 ላይ ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቶቹን እግሮች እያጠበ ሳለ የተናገራቸው ቃሎች ተጽፈዋል። እነዚህ ዳግም የተወለዱ ሰዎች ብቻ በትክክል ሊያስተውሉዋቸው የሚችሉዋቸው በጣም አስፈላጊ ቃሎች ናቸው።
ኢየሱስ ከፋሲካ በዓል በፊት የደቀ መዛሙርቶቹን እግሮች ያጠበበት ምክንያት አስቀድሞ የዕድሜ ዘመናቸውን ኃጢአቶች በሙሉ እንዳጠበላቸው እንዲረዱ ለመርዳት ነበር። ኢየሱስ “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ” አለ። ለጴጥሮስ የተነገሩት እነዚህ ቃሎች ዳግም የመወለድን እውነት ይዘዋል።
ኃጢአቶቻችንንና በደሎቻችንን ሁሉ ያነጻውን የኢየሱስን ጥምቀት ሁላችንም ማወቅና ማመን አለብን። ኢየሱስ በዮርዳኖስ የተቀበለው ጥምቀት፣ እጆችን በመጫን ኃጢአቶችን ሁሉ ‘የማስተላለፍ’ ወንጌል ነበር። ሁላችንም በኢየሱስ ቃሎች ማመን አለብን። ኢየሱስ በጥምቀቱ የዓለምን ኃጢአቶች ሁሉ አስወገደ፣ እንዲሁም በመሰቀል ኃጢአትን ሙሉ በሙሉ አስወገደና ድኅነትን አጠናቀቀ። ኢየሱስ የተጠመቀው ሰዎችን ሁሉ ከኃጢአቶቻቸው ሁሉ ለማንጻት ነበር።
 
 

ዕድሜ ልካችንን የሠራናቸው ኃጢአቶች ሁሉ በኢየሱስ ጥምቀትና ደም በሙሉ ተታጥበዋል

 
በጻድቃን ላይ የዲያብሎስ ‘ወጥመድ’ ምንድነው?
ዲያብሎስ ጻድቃንን እንደገና ኃጢአተኞች ለማድረግ ለማታለል ይሞክራል።
 
ኢየሱስ ከተሰቀለ፣ ከተነሳና ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ዲያብሎስና የውሸት እምነት አራማጆች መጥተው ደቀ መዛሙርትን ለማታለል እንደሚሞክሩ ያውቅ ነበር። “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” በሚለው የጴጥሮስ ምስክርነት እርሱ በኢየሱስ እንዳመነ ማየት እንችላለን። ነገር ግን ኢየሱስ ጴጥሮስን ዳግመኛ ሊያስታውሰው ፈለገ፣ የኃጢአቶች ሙሉ በሙሉ መታጠብ የመዳን ወንጌልን በአእምሮው እንዲጠብቅ። ያ ወንጌል የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ የወሰደበት የኢየሱስ ጥምቀት ነበር። ይህንንም እንደገና ለጴጥሮስ፣ ለደቀ መዛሙርትና ለእኛም በኋላ ለምንመጣው ማስተማር ፈለገ። “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ።”
የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ኃጢአት በሚሠሩበት ጊዜ ሁሉ ዲያብሎስ “ተመልከት! አሁንም ድረስ ኃጢአቶችን የምትሠራ ከሆንህ እንዴት ኃጢአት የለብኝም ማለት ትችላለህ? አንተ አልዳንክም። አንተ ኃጢአተኛ ብቻ ነህ፣” ብሎ ይፈትናቸውና ይኮንናቸው ነበር። ኢየሱስ ይህን ለመከላከል በኢየሱስ ጥምቀት ላይ ያላቸው እምነት አስቀድሞ የዕድሜ ዘመን ― ያለፈውን፣ የአሁኑንና የወደፊቱን ኃጢአቶቻቸውን በሙሉ እንዳነጻ ነገራቸው።
“ሁላችሁም እኔ እንደተጠመቅሁ ታውቃላችሁ! እኔ በዮርዳኖስ የተጠመቅሁበት ምክንያቱ በሕይወታችሁ ዘመን ሙሉ የምትሠሩዋቸው ኃጢአቶች ሁሉ እንዲሁም የሰው ዘር የመጀመሪያውን ኃጢአት ለማጥረግ ነበር። አሁን ለምን እንደተጠመቅሁ፣ ለምን በመስቀል ላይ መሰቀልና መሞት እንደነበረብኝ መረዳት ትችላላችሁን?” ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበው በጥምቀቱ አማካይነት የዕለት ተዕለት ኃጢአቶቻቸውን ሁሉ እንደወሰደና፣ በመስቀል ላይ ለኃጢአቶቻቸው ፍርድን እንደሚቀበል ሊያሳያቸው ነበር።
አሁን እናንተና እኔ ኃጢአቶቻችንን ሁሉ በሙሉ እንድንነጻ የሚያደርገውን የኢየሱስን የጥምቀትና የደም ወንጌል በማመናችን ከኃጢአቶቻችን ሁሉ ተድነናል። ኢየሱስ ስለ እኛ ተጠመቀ ተሰቀለም። በጥምቀቱና በደሙ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ አነጻ። የኃጢአቶችን ማስተስረያ ወንጌልን የሚያውቅና የሚያምን፣ እውነትን የሚያምን ማንኛውም ሰው ከኃጢአቶቹ ሁሉ ይዋጃል።
ታዲያ ሰው ከዳነ በኋላ ምን ማድረግ አለበት? በየቀኑ ኃጢአቶቹን ተገነዘብና ለኃጢአቶቹ ሁሉ የማስተሰረያ ወንጌል በሆነው የኢየሱስ ጥምቀትና ደም መዳን ማመን ይኖርበታል። ሰው ኢየሱስ በጥምቀቱና በደሙ ኃጢአቶችን ሁሉ ያስወገደበትን ወንጌል በልቡ ማኖር ይኖርበታል።
ዳግመኛ ኃጢአት ስለሠራችሁ ያ ማለት እንደገና ኃጢአተኛ ናችሁ ማለት ነውን? አይደለም። ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደ እያወቅን እንዴት እንደገና ኃጢአተኞች ልንሆን እንችላለን? የኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደሙ ለኃጢአቶቻችን ሁሉ ማስተስረያን ያስገኘ ወንጌል ነበር። በዚህ ኃጢአቶችን ሁሉ የሚያስወግድ መጀመሪያው ወንጌል የሚያምን ማንኛውም ሰው ‘ጻድቅ ሰው’ ሆኖ ዳግመኛ ሊወለድ ይችላል።
 
 

ጻድቃን ዳግመኛ ፈጽሞ ኃጢአተኞች ሊሆኑ አይችሉም

 
ጻድቃን ፈጽሞ ዳግመኛ ኃጢአተኞች የማይሆኑት ለምንድነው?
ምክንያቱም ኢየሱስ የዕድሜ ልክ ኃጢአቶቻቸውን በሙሉ አስቀድሞ ስላጠበላቸው ነው።
 
ኃጢአትን ሙሉ በሙሉ የሚያጠፋውን ወንጌል፣ ማለትም የውሃና የመንፈስ ቅዱስን ወንጌል እያመናችሁ፣ ነገር ግን አሁንም በየቀኑ በምትሠሩዋቸው መተላለፎች ምክንያት ኃጢአተኛ እንደሆናችሁ የሚሰማችሁ ከሆነ፤ ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ለመውሰድ ወደተጠመቀበት ዮርዳኖስ መሄድ ይኖርባችኋል። ከኃጢአት ከዳናችሁ በኋላ እንደገና ኃጢአተኞች ከሆናችሁ ኢየሱስ እንደገና መጠመቅ ይኖርበታልን? በኢየሱስ የጥምቀት ወንጌል ኃጢአቶቻችን ሙሉ በሙሉ እንደታጠቡ እምነት ሊኖረን ይገባል። ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት በአንድ ጊዜ ኃጢአቶቻችሁን በሙሉ እንደወሰደ ማስታወስ ይኖርባችኋል። ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችሁ ስለመሆኑ ጽኑ እምነት ሊኖራችሁ ይገባል።
ኢየሱስን አዳኛችሁ አድርጋችሁ ማመን ማለት የሕይወታችሁን ዘመን ሙሉ የምትሠሩዋቸው ኃጢአቶች ሁሉ በሙሉ በወሰደው የኢየሱስ ጥምቀት ማመን ማለት ነው። በእርግጥም በእርሱ ጥምቀት፣ መስቀል፣ ሞትና በኢየሱስ ትንሣኤ የምታምኑ ከሆነ ምንም ኃጢአት ብትሠሩም ዳግመኛ ፈጽሞ ኃጢአተኛ ልትሆኑ አትችሉም። በሕይወት ዘመናችሁ ከምትሠሩዋቸው ኃጢአቶች በሙሉ በእምነት ተዋጅታችኋል።
ኢየሱስ ክርስቶስ የወደፊት ኃጢአቶችን፣ ከድክመቶቻችን የተነሣ የምንሠራቸውንም ኃጢአቶች ሳይቀር አጠበ። ኢየሱስ የጥምቀቱን ጠቀሜታ ማጉላት ስለነበረበት ከኃጢአት ሙሉ በሙሉ የሚያነጻውን የመዳን ወንጌል፣ ማለትም የእርሱን ጥምቀት ለማመልከት የደቀ መዛሙርቱን እግሮች በውሃ አጠበ። ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ለዓለም ኃጢአቶች በሙሉ ቃል የገባውን የተትረፈረፈ ማስተስረያ ለመፈጸምና የሰውን ዘር ሁሉ ለማዳን ተጠመቀ፣ ተሰቀለ፣ ተነሣ፣ ወደ ሰማይም አረገ። ከዚህ የተነሣ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ኃጢአትን የሚያጠብ ወንጌልን፣ የኢየሱስን ጥምቀት፣ መስቀሉንና ትንሳኤውን እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ መስበክ ችለው ነበር።
 
 
የጴጥሮስ ሥጋዊ ድክመት
 
ጴጥሮስ ኢየሱስን የካደው ለምንድነው?
ምክንያቱም ደካማ ስለነበረ ነው
 
መጽሐፍ ቅዱስ ጴጥሮስ ከሊቀ ካህኑ ከቀያፋ ባሪያዎች ጋር በተገናኘና ከኢየሱስ ተከታዮች አንዱ እንደነበር በተከሰሰ ጊዜ “ሰውየውን አላውቀውም ብሎ” በማለት ሁለት ጊዜ ካደ። ከዚያም እየረገመና እየማለ ለሦስተኛ ጊዜ ተናገረ።
ምንባቡን እዚህ ላይ እናንብብ። ከማቴዎስ 26፡69 ጀምሮ፦ “ጴጥሮስም ከቤት ውጭ በአጥሩ ግቢ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት ገረድም ወደ እርሱ ቀርባ። አንተ ደግሞ ከገሊላው ከኢየሱስ ጋር ነበርህ አለችው። እርሱ ግን፦ የምትዪውን አላውቀውም ብሎ በሁሉ ፊት ካደ። ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና በዚያ ላሉት፦ ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ አለች። ዳግመኛም ሲምል፦ ሰውየውን አላውቀውም ብሎ ካደ። ጥቂትም ቈይተው በዚያ ቆመው የነበሩ ቀርበው ጴጥሮስን፦ አነጋገርህ ይገልጥሃልና በእውነት አንተ ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ አሉት። በዚያን ጊዜ፦ ሰውየውን አላውቀውም ብሎ ሊራገምና ሊምል ጀመረ። ወዲያውም ዶሮ ጮኸ። ጴጥሮስም፦ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው። ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ” (ማቴዎስ 26፡69-75)።
ጴጥሮስ በኢየሱስ በተጨባጭ አመነና በታማኝነትም ተከተለው። ጌታ ኢየሱስ “ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ” እንደነበር አምኖዋል። ነገር ግን ኢየሱስ ወደ ቀያፋ ፍርድ ቤት በተወሰደ ጊዜ፣ ከኢየሱስ ጋር መገናኘት አደገኛ በሆነበት ወቅት፣ እሱ ኢየሱስን ካደውና ረገመው።
ጴጥሮስ ኢየሱስን እንደሚክደው አላወቀም ነበር። ኢየሱስ ግን እንደሚክደው አውቆ ነበር። ኢየሱስ የጴጥሮስን ድክመት በሚገባ አውቆታል። ስለዚህ ኢየሱስ የጴጥሮስን እግሮች አጠበና በዮሐንስ 13 ላይ እንደተጻፈው “አንተ ወደፊት ኃጢአት ትሠራለህ፣ ነገር ግን እኔ አስቀድሜ የወደፊት ኃጢአቶችህን ሁሉ አጥቤአለሁ” በማለት ውስጥ የመዳን ወንጌልን አስተማረው።
ጴጥሮስ ሕይወቱ አደጋ ላይ ሲወድቅ በእርግጥም ኢየሱስን ካደው፣ ይህንን እንዲያደርግ ያደረገው ግን የሥጋው ድካም ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቶቹን ከወደፊት በደሎቻቸው ሁሉ እንዳዳናቸው ለማስተማር፣ አስቀድሞ እግሮቻቸውን አጠበ።
“እኔ ከወደፊት ኃጢአቶቻችሁም በሙሉ አድናችኋለሁ። ስለተጠመቅሁና ኃጢአቶቻችሁን በሙሉ ስለወሰድሁ እሰቀላለሁ፣ ለሁላችሁም እውነተኛ አዳኝ ለመሆንም የሁሉንም ኃጢአቶች ዋጋ እከፍላለሁ። እኔ አምላካችሁ አዳኛችሁ ነኝ። ለኃጢአቶቻችሁ ሁሉ በሙሉ እከፍላለሁ፣ በጥምቀቴና በደሜም እረኛችሁ እሆናለሁ። እኔ የመዳናችሁ እረኛ ነኝ።”
ኢየሱስ ይህንን እውነት በልቦቻቸው ውስጥ በጽኑ ለመትከል ሲል ከፋሲካ በዓል በፊት እግሮቻቸውን አጠበ። የወንጌል እውነት ይህ ነው።
ዳግም ከተወለድን በኋላም ቢሆን ሥጋችን ደካማ ስለሆነ እንደገና ኃጢአት እንሠራለን። በእርግጥ ኃጢአት መሥራት አይገባንም ነበር፣ ነገር ግን ጴጥሮስ ያለ ማወቅ በሠራው ኃጢአት ምክንያት ከባድ ችግሮች እንደገጠሙት ሁሉ፣ ያለ ማወቅ የምንሠራው ኃጢአት ሊኖር ይችላል። የምንኖረው በሥጋ ስለሆነ በኃጢአቶቻችን ወደ ጥፋት እንገሰግሳለን። በዚህ ዓለማዊ ዓለም እስካለን ድረስ ሥጋ ኃጢአትን መሥራቱን ይቀጥላል፣ ነገር ግን ኢየሱስ እነዚያን ኃጢአቶች በሙሉ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ አስወግዶዋቸዋል።
ኢየሱስ አዳኛችን እንደሆነ አንክድም፣ ነገር ግን በሥጋ ስንኖር ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር የሚቃረኑ ኃጢአቶችን በመሥራት እንቀጥላለን። ይህ የሆነበት ምክንያት ከሥጋ ስለተወለድን ነው።
ነገር ግን ኢየሱስ በሥጋ ኃጢአተኞች እንደሆንን በሚገባ አወቀ። ኢየሱስ በጥምቀቱና በደሙ የኃጢአቶቻችንን ዋጋ በመክፈል አዳኛችን ሆነ። እርሱ በመዳኑና በትንሳኤው በማመናችን ከኃጢአቶቻችን ሁሉ ነጻ አወጣን።
አራቱም ወንጌሎች በሙሉ በመጥምቁ ዮሐንስ በሆነው የኢየሱስ ጥምቀት ይጀምራሉ። የኢየሱስ በሥጋ ተሰውሮ ወደዚህ ዓለም የመጣበት ዓላማ ዳግመኛ ልትወለዱ ወንጌልን፣ የመዳን ወንጌልን ለመፈጸም ነበር።
 
በሥጋ ኃጢአትን የምንሠራው እስከ መቼ ነው?
እስከምንሞትበት ቀን ድረስ በሕይወታችን ሁሉ ኃጢአትን እንሠራለን።
 
ጴጥሮስ ዶሮ ሳይጮህ በፊት ኢየሱስን አንድ ጊዜ ሳይሆን፣ ሁለት ጊዜም ሳይሆን፣ ሦስት ጊዜ በካደው ጊዜ ልቡ ምንኛ ተሰብሮ ነበር? ምንኛስ አፍሮ ነበር? በኢየሱስ ፊት ፈጽሞ እንደማይክደው ምሎ ነበር። ጴጥሮስ ኃጢአት የሠራው ከሥጋው ድካም የተነሳ ነበር፣ ነገር ግን በድካሙ ተሸንፎ ኢየሱስን አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሦስት ጊዜ በመካዱ ምንኛ የጎስቋላነት ስሜት ተሰምቶት ይሆን? ጴጥሮስ ኢየሱስን እንደገና በተመለከተው ጊዜ ምን ያህል አፍሮ ይሆን?
ነገር ግን ኢየሱስ እነዚህን ሁሉና ከዚያም በላይ ነገሮችን ያውቅ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ደጋግመህ ኃጢአት እንደምትሠራ አውቃለሁ። ነገር ግን ኃጢአቶችህ እንዳያሰናክሉህና ኃጢአተኛ እንዳያደርጉህ ወደ እኔ መመለስም እንዳያስቸግርህ እነዚያን ኃጢአቶች በሙሉ አስቀድሜ በጥምቀቴ ወስጃለሁ። በመጠመቅና ለኃጢአቶችህ ሁሉ በመኮነን ፍጹም አዳኝህ ሆኛለሁ። አምላክህና እረኛህ ሆኛለሁ። በኃጢአቶችህ ሙሉ መታጠብ ወንጌል እመን። የሥጋ ኃጢአቶችን በተደጋጋሚ ብትሠራም አንተን መውደዴን እቀጥላለሁ። ቀድሞውኑም በደሎችህን ሁሉ አንጽቻለሁ። ኃጢአቶችህን ሁሉ የሚያስወግድ የመዳን ወንጌል ለዘላለም ነው። እኔ ለአንተ ያለኝ ፍቅርም እንደዚሁ ዘላለማዊ ነው።”
ኢየሱስ ለጴጥሮስና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ሲል ነገራቸው፦ “ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም።” እርሱ በዮሐንስ 13 ላይ ስለሚገኘው ስለዚህ ወንጌል የተናገረበት ምክንያት ሰዎች ከውሃውና ከመንፈስ ቅዱስ ወንጌል ዳግም መወለዳቸው ጠቃሚ ስለሆነ ነበር። በዚህ ታምናላችሁን?
በቁጥር 9-10 ላይ ደግሞ “ስምዖን ጴጥሮስም፦ ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው። ኢየሱስም፦ የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው።”
ውድ ወዳጆች፣ ወደፊት ‘የሥጋ’ ኃጢአቶችን ትሠራላችሁ ወይስ አትሠሩም? በእርግጥ ኃጢአትን ትሠራላችሁ። ነገር ግን ኢየሱስ የወደፊት ኃጢአቶችንም ጨምሮ፣ የሥጋችን በደሎች ሁሉን አስቀድሞ በጥምቀቱና በደሙ እንዳጠበ ተናግሯል፤ ከመሰቀሉ በፊትም ለደቀ መዛሙርቱ የእውነትን ቃል፣ የቤዛነት ወንጌልን በግልጽ ነግሯቸዋል።
እኛ ከድክመቶቻችን ሁሉ ጋር በሥጋችን ስለምንኖር ኃጢአት እንሠራለን። ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ በጥምቀቱ አንጽቷል። እርሱ ያጠበው ራሶቻችንንና ሰውነቶቻችንንን ብቻ ሳይሆን እግሮቻችንንም ማለትም የወደፊት ኃጢአቶቻችንንም ሁሉ ነው። ዳግመኛ ልትወለዱ የኢየሱስ ጥምቀት ወንጌል ይህ ነው።
ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ መጥምቁ ዮሐንስ እንዲህ ሲል መሰከረ፦ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ዮሐንስ 1፡29)። እኛም የዓለም ኃጢአቶች በሙሉ በጥምቀቱ ወቅት ወደ ኢየሱስ ተላልፈው እንደነጹ ማመን አለብን።
በዚህ ዓለም ላይ ስንኖር፣ ሰዎች ከኃጢአት መቆጠብ አይችሉም። ያንን ግልጽ ሐቅ መቀበል ይኖርብናል። የሥጋ ድክመቶቻችን በሚገለጡበት ጊዜ ሁሉ ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በሙሉና የዓለምን ኃጢአቶችም በሙሉ በጥምቀት ወንጌል እንዳነጻና በደሙም ዋጋቸውን እንደከፈለ ራሳችንን ማስታወስ ይኖርብናል። ከልባችን ለእርሱ ምስጋናን ማቅረብ ይገባናል። ኢየሱስ አዳኛችንና እግዚአብሔር እንደሆነ በእምነት እንናዘዝ። ጌታ ይመስገን።
በዚህ ዓለም ላይ የሚኖር እያንዳንዱ ሰው በሥጋው ኃጢአቶችን ይሠራል። ሰዎች በሥጋ የሕይወት ዘመን ኃጢአቶቻቸው ይሞታሉ። ሰዎች በሥጋቸው ያለ ማቋረጥ ኃጢአት ይሠራሉ።
 
 
በሰዎች ልቦች ውስጥ ያሉ ክፉ አሳቦች
 
ሰውን የሚያረክሰው ምንድነው?
የተለያዩ ኃጢአቶችና ክፉ አሳቦች
 
ኢየሱስ በማቴዎስ 15፡19-20 ላይ እንዲህ አለ። “ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና። ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው እንጂ፥ ባልታጠበ እጅ መብላትስ ሰውን አያረክሰውም።” በሰው ልብ ውስጥ ያሉ የተለያዩ የኃጢአት አይነቶች ስለሚያረክሱዋቸው፣ እነርሱ ርኩሳን ናቸው።
 
 
ሰው የራሱን ክፉ ተፈጥሮ ማወቅ አለበት
 
በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ያለው ምንድነው?
አስራ ሁለት አይነት ኃጢአቶች (ማርቆስ 7፡21-23)
 
እኛ “እነዚህ አሥራ ሁለት አይነት ኃጢአቶች በሰዎች ልቦች ውስጥ አሉ። በእኔም ልብ ውስጥ ሁሉም አሉ። በውስጤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉት አሥራ ሁለት ዓይነት ኃጢአቶች አሉብኝ” ማለት መቻል ይኖርብናል። ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም ከመወለዳችን በፊት ቀድሞውኑም ኃጢአቶች በልቦቻችን ውስጥ እንዳሉ ማመን ይኖርብናል። እኛ በእግዚአብሔር ፊት ሙሉ ኃጢአተኞች እንደሆንን መቀበል ይኖርብናል። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ያንን አናደርግም። ብዙዎቻችን “በልቤ ውስጥ እነዚያ አሳቦች ፈጽሞ አልነበሩም፣ ለጊዜው ብቻ ተሳስቼ ነበር” በማለት ለኃጢአቶቻችን ምክንያቶችን እናቀርባለን።
ኢየሱስ ግን ስለ ሰዎች ምን አለ? እርሱ ከሰው ልብ የሚወጣው እርሱን ‘እንደሚያረክሰው’ በግልጽ ተናገረ። ሰዎች በውስጣቸው ክፉ አሳቦች እንዳላቸው ነገረን። ምን ይመስላችኋል? እናንተ ጥሩ ናችሁ ወይስ ክፉ? እያንዳንዱ ሰው ክፉ አሳቦች እንዳለው ታውቃላችሁን? አዎ የእያንዳንዱ ሰው አሳቦች ክፉ ናቸው።
ከረጅም ጊዜ በፊት በሴዑል የሚገኘው የሳምፖንግ ሱቅ ህንጻ በድንገት ፈረሰ። ውዶቻቸውን ያጡ ቤተሰቦች ሐዘናቸው ጥልቅ ነበር። ነገር ግን ብዙ ሰዎች አሳዛኝ በሆነው ትዕይንት ለመደሰት ወደዚያ ሄደው ነበር።
አንዳንዶች ‘ምን ያህል ሰዎች ሞቱ? 200? አይ፤ ያ ቁጥር ትንሽ ነው። 300? ምናልባት? እንግዲህ፣ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ አንድ ሺህ ቢሆን በጣም የሚያስደስትና የሚያስደንቅ በሆነ ነበር’ ብለው አሰቡ። የሰዎች ልቦች እንደዚህ ክፉ ሊሆኑ ይችላሉ። ይህንን ልንቀበለው ይገባናል። ለሟቾች ምን ያህል አክብሮት የጎደለው ነበር! ለቤተሰቦቻቸውም እንዴት ያለ አጥፊ ነገር ነበር! አንዳንዶቹ በገንዘብ አቅምም ፈራርሰዋል።
በግልጽ፣ ከተመልካቾቹ አንዳንዶቹ ብዙም ርህራሄ አልነበራቸውም። ‘ብዙ ሞተው ቢሆን ኖሮ ይበልጥ ያስደስት ነበር! እጅግ አስደናቂ ትዕይንት ሊሆን ነው! በሰዎች በተሞላው ቦልፓርክ ላይ ተመሳሳይ ነገር ቢከሰትስ? በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከፍርስራሹ በታች ይቀበሩ ነበር፣ አይደለምን? ኦ አዎ! ያ በእርግጥ ከዚህም የበለጠ አስደሳች በሆነ ነበር!’ ምናልባት አንዳንዶች እንዲህ አይነት አሳቦች ነበሩዋቸው።
ሁላችንም አንዳንድ ጊዜ ምን ያህል ክፉዎች እንደምንሆን እናውቃለን። በእርግጥ እነርሱ እነዚህን ክፉ አሳቦች ፈጽሞ ጮክ ብለው አልተናገሩዋቸውም። ውጫዊ በሆነ መልኩ ሐዘናቸውን ቢገልጹም፣ ነገር ግን በድብቅ በልቦቻቸው ውስጥ አደጋው ይበልጥ አስገራሚ እንዲሆን ይናፍቃሉ። ከፍላጎቶቻቸው ጋር እስካልተቃረነ ድረስ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚገደሉባቸው አሰቃቂ አደጋዎችን ማየት ይፈልጋሉ። የሰዎች ልቦች የሚሠሩበት መንገድ ይህ ነው። አብዛኞቻችን ዳግም ከመወለዳችን በፊት እንደዚህ ነበርን።
 
 
በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ያለ የነፍስ መግደልት
 
ኃጢአት ለምን እንሠራለን?
ምክንያቱም በልቦቻችን ውስጥ ክፉ አሳቦች ስላሉ።
 
እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ነፍስ መግደል እንዳለ ነገረን። ነገር ግን ብዙዎች ይህንን ይክዳሉ። “እንዴት እንደዚያ ትላለህ? በልቤ ውስጥ ምንም የነፍስ መግደል አሳብ የለኝም! እንዴት እንደዚህ ዓይነት ነገር እንኳን ማሰብ ትችላለህ!” ይላሉ። እነርሱ በልቦቻቸው ውስጥ ነፍስ መግደል እንዳለ በጭራሽ አያምኑም። ነፍሰ ገዳዮች ከእነርሱ የተለዩ ዘሮች እንደሆኑ ያስባሉ።
“በሌላ ቀንና በዜና የተነገረው ክፉ ነፍሰ ገዳይ፣ ከመሬት በታች ባሉት ቤቶቻቸው ውስጥ ሳሉ ሰዎችን የገደሉትና ያቃጠሉት ወሮበሎች በልቦቻቸው ውስጥ ነፍስ ማጥፋት ያላባቸው ሰዎች ናቸው! እነርሱ የተለየ ዝርያ ናቸው። እኔ በፍጹም እንደነርሱ መሆን አልችልም! እነርሱ ወንበዴዎች ናቸው! ነፍሰ ገዳዮች ናቸው!” እነርሱ በወንጀለኞች ላይ ተቆጥተው “ከክፉ ዘር የተወለዱ ሰዎች ከዚህ ምድር ላይ ተጠርገው መወገድ አለባቸው! ሁሉም ሞት ሊፈረድባቸው ይገባል” በማለት ይጮሃሉ።
ነገር ግን አሳዛኙ ነገር የግድያ አሳብ በእነዚያ በቁጣ የተሞሉ ሰዎች ልቦች፣ እንደዚሁም ተደጋጋሚ ገዳዮችና ነፍስ አጥፊዎች ልቦች ውስጥ ያለ መሆኑ ነው። እግዚአብሔር በሰዎች ሁሉ ልቦች ውስጥ መግደል እንዳለ ነገረን። እኛ በልቦቻችን ውስጥ የተደበቁትን ነገሮች እንኳን የሚያውቀውን የእግዚአብሔር ቃል መቀበል አለብን። ስለዚህ “እኔ በልቤ ውስጥ ግድያ ያለብኝ ኃጢአተኛ ነኝ” በማለት ማመን ይኖርብናል።
አዎ፣ እግዚአብሔር በሰዎች ሁሉ ልቦች ውስጥ ግድያን ጨምሮ ክፉ አሳቦች እንዳሉ ነግሮናል። የእግዚአብሔርን ቃል እናውቅና እንቀበል። የሰው ልጆች ትውልዶች እየከፋ ሲሄድ፣ ሁሉም ዓይነት የግል መጠበቂያ መሣሪያዎች የግድያ መሣሪያዎች ይሆናሉ። ይህ በልቦቻችን ውስጥ ያለው ግድያ ውጤት ነው። በቁጣ ወይም በፍርሃት ጊዜ ሰውን መግደል ትችላላችሁ። እያንዳንዳችን በእርግጥም ሌሎችን እንገድላለን ማለቴ አይደለም፣ ነገር ግን በልቦቻችን ስለ ግድያ እናስባለን።
ሰዎች ክፉ አሳቦችን ይዘው ስለሚወለዱ፣ ሁላችንም እነዚህን በልቦቻችን እናካትታለን። አንዳንዶች በእርግጥ መግደል ላይ ይደርሳሉ፣ ይህም የሚሆነው ነፍሰ ገዳዮች ሆነው ስለተወለዱ ሳይሆን ሁላችንም ነፍሰ ገዳዮች የመሆን አቅም ስላለን ነው። እግዚአብሔር በልቦቻችን ውስጥ ክፉ አሳቦችና ግድያ እንዳለን ይነግረናል። ይህ እውነት ነው። ማናችንም ከዚህ እውነት ውጪ አይደለንም።
ስለዚህ እኛ ልንወስደው የሚገባን ትክክለኛው መንገድ የእግዚአብሔርን ቃል መቀበልና መታዘዝ ነው። በዚህ ዓለም ላይ ኃጢአትን የምንሠራው በልቦቻችን ውስጥ ክፉ አሳቦች ስላሉ ነው።
 
 
በልቦቻችን ውስጥ ያለ አመንዝራነት
 
እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ምንዝርነት እንዳለ ተናገረ። ትስማማላችሁን? በልባችሁ ውስጥ ምንዝርነት እንዳለ ታምናላችሁን? አዎ በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ምንዝርነት አለ።
በማህበረሰባችን ውስጥ ሴተኛ አዳሪነትና ሌሎች የወሲብ ወንጀሎች የበዙት ለዚህ ነው። ይህ በሰው ታሪክ በእያንዳንዱ ዘመን ውስጥ ገንዘብ ከሚገኝባቸው እጅግ አስተማማኝ መንገዶች አንዱ ነው። ሌሎች የንግድ ሥራዎች በኢኮኖሚ ችግር ሊመቱ ይችሉ ይሆናል፣ እነዚህ የረከሱ የንግድ ሥራዎች ግን ብዙም አይጎዱም፤ ምክንያቱም በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ምንዝርነት አለና።
 
 
የኃጢአተኞች ፍሬ ኃጢአት ነው
 
የሰው ልጅ የሚነጻጸረው ከምን ጋር ነው?
የኃጢአትን ፍሬ ከሚያፈራ ዛፍ
 
የአፕል ዛፎች አፕልን፣ የፒር ዛፎች ፒርን፣ የቴምር ዛፎች ቴምርን፣ የፐርሲሞን ዛፎችም ፐርሲሞንን እንደሚያፈሩ ሁሉ፣ በልቦቻችን ውስጥ 12 ዓይነት ኃጢአቶችን ይዘን የተወለድነው እኛም የኃጢአት ፍሬዎችን እናፈራለን።
ኢየሱስ ከሰው ልብ የሚወጣው እርሱን እንደሚያረክሰው ይናገራል። ትስማማላችሁን? እኛ ከኢየሱስ ቃሎች ጋር ብቻ በመስማማት “አዎ እኛ የኃጢአተኞች ዘሮች፣ ክፉ አድራጊዎች ነን። አዎ ጌታ ሆይ አንተ ትክክል ነህ” ማለት እንችላለን። አዎ፣ ክፋታችንን መታወቅ አለብን። በእግዚአብሔር ፊት የራሳችንን እውነተኛ ማንነት መቀበል አለብን።
ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደታዘዘ እኛም የእግዚአብሔርን ቃል መቀበልና እርሱን መታዘዝ ይኖርብናል። በውሃውና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከኃጢአቶቻችን ሁሉ መዳን የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነው። እነዚህ ከእግዚአብሔር የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው።
አገሬ በአራት ውብ ወቅቶች የተባረከች ነች። ወቅቶች ሲለዋወጡም የተለያዩ ዓይነት ዛፎች ፍሬዎቻቸውን ያፈራሉ። በተመሳሳይ መንገድ በልቦቻችን ውስጥ ያሉት አሥራ ሁለት ኃጢአቶች እኛን አጥብቀው ይይዙናል፣ ያለ ማቋረጥም ወደ ኃጢአት ይነዱናል። ዛሬ ልቦቻችንን የሚይዘው ነፍስ ማጥፋት ሊሆን ይችላል፣ ነገ ደግሞ ምንዝርና ሊሆን ይችላል።
ከዚያም በሚቀጥለው ቀን፣ ክፉ አሳቦች፣ ከዚያ ዝሙት፣ ስርቆት፣ በሐሰት መመስከር፣ እና ሌሎችም ይሆናሉ። ዓመቱን ሙሉ በየወሩ፣ በየቀኑ፣ በየሰዓቱ ኃጢያት መሥራታችንን እንቀጥላለን። አንዳች ኃጢአት ሳንሠራ ቀኑ አያልፍብንም። ኃጢአት እንደማንሠራ ለራሳችን እንምላለን፤ ነገር ግን ኃጢአት ከመሥራት መቆጠብ አንችልም፣ ምክንያቱም የተወለድነው በዚህ መንገድ ነውና።
አንድ የአፕል ዛፍ ማፍራት ስላልፈለገ የአፕል ፍሬዎችን ማፍራት እምቢ ሲል አይታችሁ ታውቃላችሁን? “አፕሎችን ማፍራት አልፈልግም!” ፍሬ ማፍራቱን እምቢ ቢል እንኳን እንዴት አፕሎችን ማፍራት አይቻለውም? በጸደይ አበቦች በማንኛውም ሁኔታ ያብባሉ፣ በበጋ አፕሎች ያድጋሉና ይበስላሉ፣ በበልግም ፍሬዎቹ ለመለቀምና ለመበላት ዝግጁ ይሆናሉ።
ይህ የተፈጥሮ ሕግ ነው፣ እናም የኃጢአተኞችም ሕይወት እንደዚሁ ተመሳሳይ የሆነ የተፈጥሮ ሕግን መከተል አለበት። ኃጢአተኞች የኃጢአትን ፍሬዎች ከማፍራት በቀር ምንም ነገር ማድረግ አይችሉም።
 
 

‘የኢየሱስ ጥምቀትና መስቀሉ’ ኃጢአቶቻችን ለማስተሰረይ ነበረባቸው

 
የኢየሱስ አስተስረይ ማለት ምን ማለት ነው?
ይህ በኢየሱስ ጥምቀትና (በእጆች መጫን) በመስቀሉ ደሙ የኃጢአትን ደመወዝ መክፈል ነው።
 
የክፉ አድራጊዎች ዘር የሆኑት ኃጢአተኞች በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአቶቻቸውን ማስተስረይ እንደሚችሉና ሕይወታቸውንም በደስታ እንደሚኖሩ ለማወቅ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ምንባብ እናንብብ። ይህ የኃጢአቶች አስተስረይ የሚገኝበት ወንጌል ነው።
በዘሌዋውያን 4 ላይ እንዲህ ተብሎዋል፦ “ከአገሩ ሕዝብም አንድ ሰው ኃጢአትን ሳያውቅ ቢሠራ እግዚአብሔርም አትሥራ ያለውን ትእዛዝ ቢተላለፍ፥ ቢበድልም፥ ለእርሱም የሠራው ኃጢአት ቢታወቀው ስለ ሠራው ኃጢአት ነውር የሌለባትን እንስት ፍየል ለቍርባኑ ያመጣል። እጁንም በኃጢአት መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፥ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአትን መስዋዕት ያርዳል። ካህኑም ከደምዋ በጣቱ ወስዶ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፥ ደሙንም ሁሉ ከመሠዊያው በታች ያፈስሰዋል። ስቡም ሁሉ ከደኅንነት መሥዋዕት ላይ እንደሚወሰድ ስብዋን ሁሉ ይወስዳል፤ ካህኑም ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። ካህኑም ስለ እርሱ ያስተሰርያል፥ እርሱም ይቅር (ኃጢአት ጠፍቷል) ይባላል” (ዘሌዋውያን 4፡27-31)።
በብሉይ ኪዳን ዘመን ሰዎች ለኃጢያቶቻቸው ለማስተሰረይ ያገኙት እንዴት ነበር? በመጀመሪያ እጆቻቸውን በኃጢያት ቁርባኑ ራስ ላይ ይጭኑና ኃጢአቶቻቸውን ወደ እርሱ ያስተላልፋሉ።
በዘሌዋውያን ተጽፏል። “ከእናንተ ማናቸውም ሰው ለእግዚአብሔር መባ ሲያቀርብ መባችሁን ከእንስሳ ወገን ከላሞች ወይም ከበጎች ታቀርባላችሁ። መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፥ በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል። እጁንም በሚቃጠለው መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፥ ያስተሰርይለትም ዘንድ የሠመረ ይሆንለታል” (ዘሌዋውያን 1፡2-4)።
እግዚአብሔር ለእስራኤል ኃጢአቶች ማስተሰርያ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የኃጢአት ቁርባኖችን እንዲያዘጋጁ አደረገ። ኃጢአቶችን ለማስተላለፍም በኃጢአት ቁርባኖች ላይ ‘እጆቻቸውን እንዲጭኑ’ ነገራቸው። በቅዱሱ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ ውስጥ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ነበር። እርሱ ከምንበር ጠረጴዛ ትንሽ የሚበልጥ ሳጥን ሲሆን፣ በአራቱም ማዕዘኖቹ ላይም ቀንዶች ነበሩት። የእስራኤል ሕዝብ ኃጢአቶቻቸውን በኃጢአት ቁርባኑ ራስ ላይ በማስተላለፍና ሥጋውንም በሚቃጠለው መሥዋዕት መሠውያ ላይ በማቃጠል ለኃጢአቶቻቸው ያስተሰርያሉ።
እግዚአብሔር በዘሌዋውያን መጽሐፍ ውስጥ ሰዎች “በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል” ሲል ተናገረ። እጆቻቸውን በኃጢአት ቁርባኑ ራስ ላይ በሚጭኑበት ጊዜ የእነርሱ ኃጢአቶች ወደ ኃጢአት ቁርባኑ ይተላለፉ ነበር፣ ከዚያም ኃጢአተኞቹ ቁርባኑን ለመግደል ጉሮሮውን ይቆርጡ ነበር። ካህናቱም ደሙን በሚቃጠለው መሥዋዕት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያኖሩ ነበር።
ከዚያ በኋላ የቁርባኑ በድን በውስጡ ካሉት ብልቶቹ ይጸዳና ሥጋው ተቆራርጦ በሚቃጠለው መሥዋዕት መሠዊያ ላይ አመድ እስኪሆን ድረስ ይቃጠላል። ከዚያም የሥጋው ጣፋጭ ሽታ ለስርየታቸው ይሆን ዘንድ ለእግዚአብሔር ይቀርባል። የዘወትር ኃጢያቶቻቸውን የሚያስተሰርዩት እንዲህ ነበር።
ከዚያ በኋላ ለዓመታዊ ኃጢአቶቻቸው የሚቀርብ የኃጢአት ማስተሰሪያ መሥዋዕት ነበር። ይህ ለዘወትር ኃጢአቶች ከሚቀርበው የስርየት መሥዋዕት ይለያል፤ በዚህ ሁኔታ ሊቀ ካህኑ የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ ወክሎ እጆቹን በኃጢአት ቁርባኑ ላይ ይጭንና በስርየት መክደኛው በስተ ምሥራቅ ደሙን ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። እንደዚሁም ሕያው በሆነው ፍየል ራስ ላይ እጆቹን መጫኑ በየአመቱ በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን በእስራኤል ሕዝብ ፊት ይደረጋል (ዘሌዋውያን 16፡5-27)።
 
የብሉይ ኪዳን የኃጢአት መሥዋዕት የሚያመለክተው ማንን ነው?
ኢየሱስ ክርስቶስን
 
አሁን የመሥዋዕቱ ስርየት በአዲስ ኪዳን እንዴት እንደተለወጠና የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ስርዓትም በዓመታት ውስጥ እንዴት እንዴት ሳይለወጥ እንደቆየ እንመልከት።
ኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞት የነበረበት ለምንድነው? እግዚአብሔር ልጁ በመስቀል ላይ እንዲሞት የፈቀደው ኢየሱስ በዚህ ምድር ላይ ምን ስህተት ስለሠራ ነበር? በመስቀል ላይ እንዲሞትስ ማን አስገደደው? የዓለም ኃጢአተኞች ሁሉ፣ ማለትም እኛ ሁላችንም፣ ወደ ኃጢአት ወድቀን ሳለን፣ ኢየሱስ ሊያድነን ወደዚህ ዓለም መጣ።
እርሱ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጥምቁ ዮሐንስ ተጠመቀ፣ በሰው ዘር ፋንታም ለኃጢያቶች ሁሉ በመስቀል ላይ ቅጣትን ተቀበለ። ኢየሱስ የተጠመቀበትና በመስቀል ላይ ደሙን ያፈሰሰበት መንገድ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ካለው የስርየት መሥዋዕት በኃጢአት ቁርባን ላይ ከሚደረገው እጆች መጫንና ከመሥዋዕቱ ደም መፍሰስ ጋር ተመሳሳይ ነው።
በብሉይ ኪዳን ሲደረግ የነበረው እንደዚህ ነበር። ኃጢአተኛ በኃጢአት መሥዋዕት ራስ ላይ እጆቹን ይጭንና “ጌታ ሆይ ኃጢአትን ሠርቻለሁ። ነፍስ አጥፍቻለሁ፣ አመንዝሬአለሁ” በማለት ኃጢአቶችን ይናዘዛል። ከዚያም ኃጢአቶቹ ወደ ኃጢአት መሥዋዕት ይተላለፋሉ።
ኃጢአተኛው የኃጢአት መሥዋዕቱን አንገት እንደሚቆርጥና በእግዚአብሔር ፊት እንደሚያቀርብ፣ እንዲሁም ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን ሁሉ ለማስተሰረይ በተመሳሳይ መንገድ ተሰዋ። ኢየሱስ እኛን ለማዳንና በመሥዋዕቱ አማካይነት ኃጢአቶቻችንን ሁሉ ለማስተሰረይ ተጠመቀ፣ በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰ።
እንዲያውም ኢየሱስ የሞተው በእኛ ምክንያት ነው። ስለዚህ ነገር ስናስብ እንከን የሌለባቸውን እነዚያን እንስሶች ለሕዝቡ ሁሉ ኃጢአቶች ቁርባን አድርጎ የማቅረቡ ትርጉም ምንድነው? እነዚያ እንስሶች በሙሉ ኃጢአት ምን እንደሆነ ያውቁ ነበርን? እንስሶች ኃጢአትን አያውቁም። የሰዎችን ሁሉ ኃጢአቶችም ማስወገድ አይችሉም።
እነዚያ እንስሶች ሙሉ በሙሉ ያለ እንከን እንደነበሩ ሁሉ ኢየሱስም እንደዚሁ ኃጢአት የሌለበት ነበር። እርሱ ቅዱስ አምላክ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፣ እርሱ ፈጽሞ ኃጢአት አልሠራም። ስለዚህ ኢየሱስ 30 ዓመት ሲሆነው በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀው ጥምቀቱ አማካይነት ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ወሰደ።
ይህ የሆነው ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ለመውሰድ ነበር፣ እናም እርሱ በመስቀል ላይ የሞተው ከእኛ በወሰዳቸው ኃጢአቶች ምክንያት ነው። የሰውን ዘር ኃጢአቶች በሙሉ ያጠበው የእርሱ የመዳን አገልግሎት ነበር። ይህም በማቴዎስ 3 ላይ ተጽፎአል።
 
 
የኃጢአቶች ማስተስረያ ወንጌል መጀመሪያ
 
ኢየሱስ በመጥምቁ ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ የተጠመቀው ለምን ነበር?
እንደዚህ ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም
 
በማቴዎስ 3 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፦ “ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር። ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንደዚህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው” (ማቴዎስ 3፡13-15)።
ኢየሱስ 30 ዓመት ሲሆነው ለምን እንደተጠመቀ ማወቅና ማስተዋል ይኖርብናል። ኢየሱስ የተጠመቀው የሕዝቡን ሁሉ ኃጢአቶች ለማስተሰረይና የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሁሉ ለመፈጸም ነበር። እንከን የሌለበት ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎችን ሁሉ ከኃጢአቶቻቸው ለማዳን በመጥምቁ ዮሐንስ መጠመቅ ነበረበት።
በዚህም ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአቶች ወሰደ፣ የሰዎችን ሁሉ ኃጢአቶች ለማስተሰረይም ራሱን አቀረበ። እኛም ከኃጢአት ለመዳን ምሉዕ የሆነውን እውነት ማወቅና በእርሱ ማመን አለብን። በእርሱ መዳን ማመንና መዳን የእኛ ፋንታ ነው።
የኢየሱስ ጥምቀት ምን ማለት ነው? ይህ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከሚደረገው እጆችን መጫን ጋር አንድ ዓይነት ነው። በብሉይ ኪዳን፣ የሕዝቡ ሁሉ ኃጢአቶች በእጆች መጫን ወደ የኃጢአት መሥዋዕቱ ራስ ይተላለፉ ነበር። በአዲስ ኪዳንም እንደዚሁ ኢየሱስ ራሱን ለኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብና በመጥምቁ ዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ኃጢአቶች ወስዶዋል።
መጥምቁ ዮሐንስ ከሰዎች ሁሉ መካከል እጅግ ታላቁ ሰው እና በእግዚአብሔር የተሾመ የሰው ዘር ወኪል ነበር። እርሱ የሰው ዘር ወኪል፣ የሁሉም ሊቀ ካህን በመሆኑ እጆቹን በኢየሱስ ራስ ላይ ጭኖ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ወደ እርሱ አስተላለፈ። ‘ጥምቀት’ የሚያመላክተው ‘ማስተላለፍን፣ መቀበርንና መታጠብን’ ነው።
ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ለምን በመጥምቁ ዮሐንስ እንደተጠመቀ ታውቃላችሁን? የኢየሱስን የጥምቀት ትርጉም እያወቃችሁ በእርሱ ታምናላችሁን? የኢየሱስ ጥምቀት ኃጢአቶቻችንን በሙሉ፣ እኛ የክፉ አድራጊ ዘሮች በሕይወት ዘመናችን ሁሉ በሥጋችን የምንሠራቸውን ኃጢአቶች ለመውሰድ ነበር። ኢየሱስ በመጥምቁ ዮሐንስ የተጠመቀው ለኃጢአቶቻችን ሁሉ ማስተስረያ የሚሆነውን እውነተኛ ወንጌል ለመፈጸም ነበር።
በማቴዎስ 3፡13-17 ላይ ‘ያን ጊዜ’ የሚል ቃል ተጽፎዋል፣ ይህ የሚያመለክተው ኢየሱስ የተጠመቀበትን ጊዜ፣ የዓለም ኃጢአቶች በሙሉ ወደ እርሱ የተላለፉበትን ጊዜ ነው።
‘ያን ጊዜ’ ኢየሱስ የሰውን ዘር ኃጢአቶች በመሉ ወሰደ፣ ከሦስት ዓመት በኋላም በመስቀል ላይ ሞተ፣ በሦስተኛው ቀን ተነሣ። እርሱ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ለማንጻት ለአንዴና ለመጨረሻ ተጠመቀ፣ ለአንዴና ለመጨረሻም በመስቀል ላይ ሞተ፣ ከሙታንም ለአንዴና ለመጨረሻ ተነሣ። እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ከኃጢአቶቻቸው ሁሉ መዳን ለሚፈልጉ ሰዎች ኢየሱስ ለአንዴና ለመጨረሻ አዳናቸው።
ኢየሱስ ለምን መጠመቅ አስፈለገው? ኢየሱስ እንደ ተራ ወንጀለኛ የእሾህ አክሊልን መልበስና በጲላጦስ ፍርድ ቤት መፈረድ ለምን አስፈለገው? በመስቀል ላይ መሰቀልና እስከ ሞት ድረስ መድማት ያስፈለገውስ ለምን ነበር? ከላይ ለተጠቀሱት ሁሉ ምክንያቱ በጥምቀቱ አማካይነት የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ የእናንተንና የእኔን ኃጢአቶች በሙሉ በራሱ ስለወሰደ ነው። እርሱ ስለ ኃጢአቶቻችን በመስቀል ላይ መሞት ነበረበት።
እግዚአብሔር እንዳዳነን በሚናገረው የመዳን ቃል ማመንና እርሱን ማመስገን ይኖርብናል። ያለ ኢየሱስ ጥምቀት፣ ያለ መስቀሉና ትንሣኤው መዳን አናገኝም።
ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ለመውሰድ በዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ኃጢአቶቻችንን ወስዶ በመዳን ወንጌሉ የምናምነውን አዳነን። ‘ኢየሱስ የወሰደው ኦሪጅናልን ኃጢአት ብቻ ነው አይደል?’ ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ፣ ነገር ግን ተሳስተዋል።
ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ እንደወሰደ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ተጽፎዋል። ኃጢአቶቻችን በሙሉ የመጀመሪያው ኃጢአት ጨምሮ ነጽተዋል። በማቴዎስ 3፡15 ላይ እንዲህ ተጽፎአል፦ “አሁንስ ፍቀድልኝ፥ እንደዚህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው።” እንደዚህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ማለት ሁሉም ኃጢአቶች፣ ያለ ምንም ልዩነት፣ ሙሉ በሙሉ ከእኛ ተወስደዋል ማለት ነው።
ኢየሱስ የሕይወት ዘመናችን ኃጢአቶችንም አንጽቷልን? አዎ፣ ሁሉንም አንጽቷል። በቅድሚያ የዚህን ማረጋገጫ በዘሌዋውያን ውስጥ እናግኝ። ይህም ስለ ሊቀ ካህኑና ስለ ማስተስረያ ቀን መሥዋዕት ይነግረናል።
 
 
ለእስራኤል ሕዝቦች ዓመታዊ ኃጢአቶች የሚቀርበው የስርየት መሥዋዕት
 
እስራኤላውያን በዚህ ምድር ላይ በሚቀርበው የኃጢአት መሥዋዕት ሁልጊዜ ቅድስናን መጠበቅ ይችላሉን?
በፍጹም አይቻልም
 
“አሮንም ለእርሱ ያለውን የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈን ያቀርባል፥ ለራሱም ለቤተ ሰቡም ያስተሰርያል። ሁለቱንም አውራ ፍየሎች ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት ያቆማቸዋል። አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሔር ሌላውንም ዕጣ ለሚለቀቅ። አሮንም የእግዚአብሔር ዕጣ የሆነበትን ፍየል ያቀርባል፥ ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት ያደርገዋል። የመለቀቅም ዕጣ የሆነበትን ፍየል ያስተሰርይበት ዘንድ፥ ለመለቀቅም ወደ ምድረ በዳ ይሰድደው ዘንድ በሕይወቱ በእግዚአብሔር ፊት ያቆመዋል” (ዘሌዋውያን 16፡6-10)። እዚህ ላይ አሮን የእስራኤሎችን ዓመታዊ ኃጢያቶች ለማንጻት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ሁለት ፍየሎችን አቀረበ።
“አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሔር ሌላውንም ዕጣ ለሚለቀቅ።” የሚለቀቀው ፍየል ያስፈለገው ለስርየት ነበር።
በተቃራኒው፣ የዕለት ተዕለት ኃጢአቶች የስርየት መሥዋዕት፣ ኃጢአተኛው ኃጢአቶቹን ለማስተላለፍ በመሥዋዕትኑ ራስ ላይ እጆቹን ይጭናል። ነገር ግን ለእስራኤላውያን ዓመታዊ ኃጢአቶች፣ በየዓመቱ በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን፣ ሊቀ ካህኑ ሕዝቡን ሁሉ ወክሎ የዓመቱን ኃጢአቶች ለኃጢአት በቀረበው መሥዋዕት ላይ ያስተላልፋል።
በዘሌዋውያን 16፡29-31 ላይ እንዲህ ተጻፈ፦ “በሰባተኛው ወር ከወሩም በአስረኛው ቀን ራሳችሁን አስጨንቋት፥ የአገር ልጅም በእናንተ መካከል የተቀመጠም እንግዳ ሥራን ሁሉ አትሥሩበት። በዚህ ቀን ትነጹ ዘንድ ማስተስረያ ይሆንላችኋልና፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ። ታላቅ ሰንበት ይሆንላችኋል ራሳችሁንም ታዋርዳላችሁ፥ የዘላለም ሥርዓት ነው” (ዘሌዋውያን 16፡29-31)።
በብሉይ ኪዳን፣ የእስራኤል ሕዝብ የዕለት ተዕለት ኃጢአቶቻቸውን ማስተስረያ ለማድረግ የኃጢአት መሥዋዕትን አቀረቡ፣ ኃጢአታቸውን ወደ መሥዋዕቱ ራስ በማስተላለፍ፣ “ጌታ ሆይ፣ እንዲህና እንዲህ ያለ ኃጢአት ሠርቻለሁ” ብለው ተናዘዙ። ከዚያም ለኃጢአት መሥዋዕት ሆኖ የቀረበውን እንስሳ በማረድ ደሙን ለካህኑ ይሰጠውና አሁን ከኃጢአቶቹ ነጻ እንደሆነ አምኖ ወደ ቤቱ ይሄዳል። ለኃጢአት የቀረበው መሥዋዕት ኃጢአቱን በራሱ ላይ ተሸክሞ ለኃጢአተኛው ይሞታል። በዚህም ለመሥዋዕት የቀረበው እንስሳ በኃጢአተኛው ፋንታ ይገደላል። በብሉይ ኪዳን የኃጢአት መሥዋዕት ፍየል፣ ጥጃ፣ ወይም ወይፈን ሊሆን ይችላል፤ እነዚህም ሁሉ እግዚአብሔር ከለያቸው ነውር የሌለባቸውና ንጹሃን እንስሶች ናቸው።
እግዚአብሔር ወሰን በሌለው ምህረቱ ኃጢአተኛው ለኃጢአቶቹ በመሞት ፋንታ የእንስሳ ሕይወት እንዲቀርብ ፈቀደ።
በብሉይ ኪዳን ኃጢአተኞች በዚህ መንገድ በስርየቱ መሥዋዕት አማካይነት ኃጢአቶቻቸውን ማስተሰረይ ቻሉ። የኃጢአተኛው መተላለፍ በእጆች መጫን ወደ ኃጢአት መሥዋዕቱ ተላልፎዋል፣ ደሙም የኃጢአተኛውን ኃጢአት ለማስተሰረይ ለካህኑ ተሰጥቶዋል።
ሆኖም በየቀኑ ኃጢአቶችን ማስተሰረይ አይቻልም ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር ሊቀ ካህኑ በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፋንታ በየዓመቱ በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን የዓመቱን ሁሉ ኃጢአቶች እንዲያስተሰርይ ፈቀደለት።
ታዲያ ማስተስረያ ቀን የሊቀ ካህኑ ሚና ምን ነበር? በመጀመሪያ ሊቀ ካህኑ አሮን በኃጢአት መሥዋዕቱ ላይ እጆቹን በመጫን “ጌታ ሆይ የእስራኤል ሕዝብ እንዲህና እንዲህ ያሉትን ኃጢአቶች ፈጽመዋል፤ ነፍስ መግደል፣ ምንዝርና፣ ዝሙት፣ ስርቆት፣ በሐሰት መመስከር፣ ስድብ...” ብሎ የሕዝቡን ኃጢአቶች ይናዘዛል።
ከዚያም የኃጢአት ቁርባኑን ያርድና ደሙን ወስዶ ያንን ደም በቅዱሱ መቅደስ ውስጥ ባለው የስርየት መክደኛ ላይ ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። (በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 7 ቁጥር ፍጹም ቁጥር ተብሎ ይቆጠራል።)
የእስራኤላውያንን ሁሉ በመወከል፣ የሕዝቡን ዓመታዊ ኃጢአቶች ለኃጢአት በቀረበው መሥዋዕት ራስ ላይ ማስተላለፍ የእርሱ ተግባር ነበር፣ የኃጢአት መሥዋዕቱም በእነርሱ ፋንታ ይሠዋል።
እግዚአብሔር ጻድቅ ስለሆነ ሰዎችን ሁሉ ከኃጢአቶቻቸው ለማዳን ለኃጢአት የሚቀርበው መሥዋዕት በሕዝቡ ፋንታ እንዲሞት ፈቀደ። እግዚአብሔር በእውነት መሐሪ ስለሆነ ሕዝቡ በእነርሱ ምትክ የመሥዋዕቱን እንስሳ ሕይወት እንዲያቀርቡ ፈቀደላቸው። ከዚያም ሊቀ ካህኑ በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን በሚውለው የስርየት ቀን ደሙን በስርየት መክደኛው በስተ ምሥራቅ በመርጨት የእስራኤላውያንን ሁሉ ባለፈው ዓመት የሠሩዋቸውን ኃጢአቶች በሙሉ ያስተሰርያል።
 
በብሉይ ኪዳን መሠረት መሥዋዕት በግ ማነው?
ነውር የሌለበት ኢየሱስ
 
ሊቀ ካህኑ ማስተስረያ ቀን ለእስራኤል ሕዝብ ሁለት ፍየሎችን ማቅረብ ነበረበት። ከእነርሱ አንዱ የሚለቀቅ ፍየል ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም ‘ማውጣት’ ማለት ነው። በተመሳሳይ መንገድ የአዲስ ኪዳን የሚለቀቅ ፍየል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐንስ 3፡16)።
እግዚአብሔር አንድያ ልጁን የመሥዋዕት በግ አድርጎ ሰጠን። እርሱ ለሰው ዘር ሁሉ የመሥዋዕት በግ በመሆኑ በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠምቆ አዳኝ፣ የዓለም መሲህ ሆነ። መሲህ ማለት ‘አዳኝ’ ማለት ሲሆን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት ‘ሊያድነን የመጣው ንጉሥ’ ማለት ነው።
ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ማስተስረያ ቀን የእስራኤላውያን ዓመታዊ ኃጢአቶች ማስተስረያ እንዳገኙ ሁሉ፣ ኢየሱስ ክርስቶስም ከ2,000 ዓመታት ገደማ በፊት ለኃጢአቶቻችን ሁሉ የሚሆነውን የስርየት ወንጌል ለማጠናቀቅ ሊጠመቅና፣ በመስቀል ላይ እስከሞት ድረስ ደሙን ሊያፈስስ ወደዚህ ዓለም መጣ።
እዚህ ላይ በዘሌዋውያን ላይ የሚገኝ አንድ ምንባብ እናንብብ። “አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፥ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ፥ መተላለፋቸውንም ሁሉ፥ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይናዝዛል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፥ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል። ፍየሉም ኃጢአታቸውን ሁሉ ወደ በረሀ ይሸከማል፤ ፍየሉንም በምድረ በዳ ውስጥ ይለቅቀዋል” (ዘሌዋውያን 16፡21-22)።
በዘሌዋውያን 16 ላይ እንደተጠቀሰው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ኃጢአቶች በፍየሉ ራስ ላይ እንደተላለፉ ተጽፎዋል። ‘መተላለፋቸውንም ሁሉ’ ማለት በልቦቻቸው የሠሩዋቸው ኃጢአቶች ሁሉና በሥጋቸው የሠሩዋቸው ኃጢያቶች ሁሉ ማለት ነው። ‘መተላለፋቸውንም ሁሉ’ በሊቀ ካህኑ እጆችን መጫን ለኃጢአት በቀረበው መሥዋዕት ራስ ላይ ተጭኖዋል።
 
 
በእግዚአብሔር ሕግ መሠረት ሁላችንም ስለ ኃጢአቶቻችን እውነተኛ እውቀት ሊኖረን ይገባል
 
እግዚአብሔር ሕግን የሰጠን ለምንድነው?
የኃጢአትን እውቀት ሊሰጠን ነው
 
የእግዚአብሔር ሕግና ትዕዛዛት 613 አንቀጾችን ይዞዋል። እንዲያውም ስለዚህ ስናስብ እርሱ አታድርጉ ያለንን እናደርጋለን፣ እንድናደርግም የነገረንንም አናደርግም።
ስለዚህ እኛ ኃጢአተኞች ነን። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር እነዚያን ሕጎች የሰጠን ኃጢአቶቻችንን እንድናውቅ እንደሆነ ተጽፎዋል (ሮሜ 3፡20)። ይህ ማለት እግዚአብሔር ሕጉንና ትዕዛዛቱን የሰጠው ኃጢአተኞች እንደሆንን ለማስተማር እንደሆነ ነው። እነርሱን የሰጠን በእነርሱ መሠረት መኖር ስለምንችል ሳይሆን ኃጢአቶቻችንን እንድናውቅ ነው።
እርሱ ሕጉንና ትዕዛዛቱን የሰጠን እንድንጠብቃቸው አይደለም። ውሻ እንደ ሰው እንዲኖር መጠበቅ አትችሉም። በተመሳሳይ መንገድ እኛም ፈጽሞ የእግዚአብሔርን ሕግ በመጠበቅ መኖር አንችልም፣ ነገር ግን በሕጉና በትዕዛዛቱ አማካይነት ኃጢአቶቻችንን ብቻ ማወቅ እንችላለን።
እግዚአብሔር ሕጉን የሰጠን እኛ በራሳችን የኃጢአት ጅምላዎች መሆናችንን ስለማንገነዘብ ነው። “እናንተ ነፍሰ ገዳዮች፣ ዝሙተኞችና ክፉ አድራጊዎች ናችሁ።” እግዚአብሔር እንዳንገድል ነገረን፣ እኛ ግን በልቦቻችን አንዳንድ ጊዜም በተግባር እንገድላለን።
ነገር ግን መግደል እንደማይገባን በሕጉ ውስጥ ስለተጻፈ፣ እኛ ራሳችን ግድያ እንደፈጸምን እንገነዘባለን፣ እናም “አሃ ተሳስቼ ነበር። እኔ ማድረግ የማይገባኝን ነገር በማድረጌ ኃጢአተኛ ነኝ። ኃጢአትን ሠርቻለሁ፣” እንላለን።
ስለዚህ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ከኃጢአት ለማዳን በብሉይ ኪዳን አሮን የስርየት መሥዋዕት እንዲያቀርብ ፈቀደለት እና በዓመት አንድ ጊዜም አሮን ለሕዝቡ ያስተሰርይ ነበር።
በብሉይ ኪዳን ማስተስረያ ቀን ሁለት የኃጢአት መሥዋዕቶች ለእግዚአብሔር መቅረብ ነበረባቸው። አንዱ ፍየል በእግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ፣ ሌላው እጆችን መጫን ተጭነውበት የእስራኤላውያንን ዓመታዊ ኃጢአቶች በሙሉ ይዞ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል። ፍየሉ በተዘጋጀው ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ከመሰደዱ በፊት፣ ሊቀ ካህኑ እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ጭኖ የእስራኤልን ኃጢአቶች ይናዘዛል። “ጌታ ሆይ፣ ሕዝቡ ገድሎዋል፣ አመንዝሮዋል፣ ሰርቋል፣ ጣዖታትን አምልኮዋል... ኃጢአትን ሠርተናል።”
ምድረ በዳ የአሸዋና የበረሃ መሬት ነው። የሚለቀቀው ፍየል ማለቂያ ወደሌለው ምድረ በዳ ይሰደድና ውሎ አድሮ ይሞታል። ፍየሉ ሲሰደድ፣ የእስራኤል ሕዝብ ርቆ እስኪሰወር ድረስ ይመለከቱታል፣ ኃጢአቶቻቸውም ከሚለቀቀው ፍየል ጋር አብሮ እንደተወሰደ ያምናሉ። በዚህም ሕዝቡ የአእምሮ ሰላም ያገኛል፣ የሚለቀቀው ፍየልም የእስራኤላውያንን ሁሉ ዓመታዊ ኃጢአቶች ተሸክሞ በምድረ በዳ ይሞታል።
እግዚአብሔርም የአምላክ በግ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ኃጢአቶቻችንን በሙሉ አስተሰርዮዋል። ኃጢአቶቻችን በሙሉ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ አማካይነት ፈጽመው ተወግደዋል።
ኢየሱስ አምላክና አዳኛችን ነው። እርሱ የሰውን ዘር ሁሉ ከኃጢአት ለማዳን የመጣ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፣ እርሱ በአምሳሉ የሠራን ፈጣሪ ነው። እርሱ እኛን ከኃጢአት ለማዳን ወደዚህ ዓለም ወረደ።
ወደ ኢየሱስ የተላለፉት በሥጋችን የምንሠራቸው የዘወትር ኃጢአቶች ብቻ ሳይሆኑ የወደፊት ኃጢአቶቻችን፣ የአእምሮዋችንና የሥጋችንም ኃጢአቶች ሁሉ ናቸው። ስለዚህ እርሱ ለዓለም ኃጢአቶች በሙሉ የተሟላ ስርየት የሆነውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሁሉ ይፈጽም ዘንድ በመጥምቁ ዮሐንስ መጠመቅ ነበረበት።
ኢየሱስ ከመሰቀሉ ከሦስት ዓመት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ አገልግሎቱን ሲጀምር በዮርዳኖስ ወንዝ በመጥምቁ ዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ወሰደ። ኃጢአቶቻችንን በሙሉ በማስተሰረይ ለሰው ዘር መዳኑን የጀመረው በጥምቀቱ ነው።
በዮርዳኖስ ወንዝ፣ እስከ ወገብ ድረስ በሚደርስ ጥልቀት፣ መጥምቁ ዮሐንስ እጆቹን በኢየሱስ ራስ ላይ ጭኖ በውሃው ውስጥ አጠለመው። ይህ ጥምቀት ከብሉይ ኪዳኑ እጆችን መጫን ጋር አንድ ዓይነት ሲሆን ኃጢአቶችን ሁሉ የማስተላለፍ ያው ዓይነት ውጤት የነበረው ነው።
በውሃ ውስጥ መጥለም ማለት ሞት ማለት ነው፣ ከውሃ ውስጥ መውጣት ማለት ደግሞ ትንሣኤ ማለት ነው። ስለዚህ ኢየሱስ በመጥምቁ ዮሐንስ በመጠመቅ ሦስቱንም ነገሮች ፈጸመና ገለጠ፦ ኃጢአቶችን በሙሉ መውሰድ፣ መሰቀልና ትንሣኤ።
እኛ መዳን የምንችለው ኢየሱስ እኛን ከኃጢአት ያነጻባቸውን ቃሎች ስንታዘዝ ብቻ ነው። እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል ሊያድነን ወሰነ፣ እንዲሁም በብሉይ ኪዳን የገባው ቃል ኪዳን በዚህ መንገድ ተፈጸመ። ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ ተሸክሞ ወደ መስቀል ሄደ።
 
ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን ሁሉ ከደመሰሰ በኋላ ለእኛ የቀረው ሥራ ምን ዓይነት ነው?
እኛ ማድረግ የሚኖርብን በእግዚአብሔር ቃሎች ላይ እምነት እንዲኖረን ብቻ ነው።
 
በዮሐንስ 1፡29 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፦ “በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።” መጥምቁ ዮሐንስ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” በማለት መሰከረ። የሰው ዘር ኃጢያቶች በሙሉ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ወደ እርሱ ተላልፈዋል። ይህንን እመኑ! ያን ጊዜ ለኃጢአቶቻችሁ ሁሉ ማስተስረያ በማግኘት ትባረካላችሁ።
በእግዚአብሔር ቃል ላይ እምነት ሊኖረን ይገባል። የራሳችንን አስተሳሰቦችና ግትርነት ወደ ጎን ማድረግ አለብን፣ እንዲሁም ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ የወሰደ መሆኑን እውነት በቀላሉ ማመንና የተጻፉትን የእግዚአብሔር ቃሎች መታዘዝ አለብን።
ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ወስዶዋል ማለትና ኃጢአቶቻችንን በማስተሰረይ የእግዚአብሔርን ጽድቅ ፈጽሞዋል ማለት በትክክል ተመሳሳይ ነገር ነው። ‘እጆችን መጫን’ እና ‘ጥምቀትም’ እንደዚሁ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው።
‘ሁሉም’፣ ‘እያንዳንዱ ነገር’ ወይም ‘ሙሉ’ ብንልም ትርጉሙ ያው ተመሳሳይ ነው። በብሉይ ኪዳን ‘እጆችን መጫን’ የሚለው ቃል ትርጉም በአዲስ ኪዳን ተመሳሳይ ነው፣ ነገር ግን ‘ጥምቀት’ የሚለው ቃል በምትኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
ይህም ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ለማስተሰረይ የተጠመቀና በመስቀል ላይ የተፈረደበት መሆኑን ወደሚለው ግልጽ እውነት ይደርሳል። በዚህ የእውነት በኩረ ወንጌል ስናምን መዳን እንችላለን።
መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ‘የዓለምን ኃጢአት’ (ዮሐንስ 1፡29) በሙሉ እንደወሰደ ሲናገር የዓለም ኃጢአት ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ማለት ይዘናቸው የተወለድናቸው ኃጢአቶች በሙሉና በአእምሮዋችን ውስጥ ያሉ ክፉ አሳቦች፣ ምንዝርና፣ ዝሙት፣ ግድያ፣ ስርቆት፣ መመኘት፣ ክፋት፣ ተንኮል፣ መዳራት፣ ክፉ ዓይን፣ ስድብ፣ ትዕቢት፣ ስንፍና ማለት ነው። ይህ ማለት በሥጋና በልብ የምንሠራቸውን ክፉ ኃጢአቶችና መተላለፎች በሙሉ ማለት ነው።
“የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው” (ሮሜ 6፡23)። “ደም ሳይፈስ ስርየት (ኃጢአት ሙሉ በሙሉ የሚጠፋበት) የለም” (ዕብራውያን 9፡22)። በእነዚህ ቁጥሮች ውሰጥ እንደተባለው ኃጢአቶች በሙሉ ደመወዛቸው መከፈል ይኖርበታል። ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር በሙሉ ከኃጢአት ለማዳን የራሱን ሕይወት አቀረበና ለአንዴና ለመጨረሻ ስለ እኛ የኃጢአትን ደመወዝ ከፈለ።
ስለዚህ ከኃጢአቶቻችን ነጻ ለመውጣት እኛ ማድረግ የሚኖርብን በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ፣ ይህም እውነተኛ ወንጌል፤ እንዲሁም አምላካችንና መድኃኒታችን በመሆኑ በኢየሱስ ማመን ነው።
 
 
ነገ ለሚሠሩ ኃጢአቶች የሚሆን ስርየት
 
ዳግመኛ ለኃጢአቶቻችን መሥዋዕት ማቅረብ ያስፈልገናልን?
ዳግመኛ መሥዋዕት ማቅረብ በፍጹም አያስፈልገንም
 
የነገ፣ የከነገ በስቲያ ኃጢአቶችና እስከ ዕለተ ሞታችን የምንሠራቸው ኃጢአቶችም እንደዚሁ ‘የዓለምን ኃጢአት’ ውስጥ ተጨምረዋል፤ የዛሬው፣ የትናንትናውና ከትናትና በፊት የተሠሩት ኃጠአቶችም እንደዚሁ ‘የዓለምን ኃጢአት’ ውስጥ ተጨምረዋል። ሰዎች ከውልደት እስከ ሞት ድረስ ሰዎች የሚሠሩዋቸው ኃጢአቶች ሁሉም ‘የዓለምን ኃጢአት’ ክፍል ናቸው፣ እና የዓለም ኃጢአቶችም በጥምቀቱ አማካይነት ፈጽመው ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል። እስከ ዕለተ ሞታችን ድረስ የምንሠራቸው ኃጢአቶች በሙሉ አስቀድመው ከእኛ ተወስደዋል።
ለመዳን የሚያስፈልገን በዚህ እውነተኛው ወንጌል፣ በተጻፉት የእግዚአብሔር ቃሎች ማመንና መታዘዝ ብቻ ነው። ከኃጢአቶቻችን ሁሉ ለመዋጀት የራሳችንን አስተሳሰቦች ማስወገድ ይገባናል። “ገና ያልተሠሩትን ኃጢአቶች እንዴት ሊወስድ ይችላል?” ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል። እኔም በመልሱ እንዲህ እጠይቃችኋለሁ፦ “እኛ በየጊዜው ኃጢአት በሠራን ቁጥር ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም ተመልሶ መጥቶ ደሙን እንደገና እና እንደገና ማፍሰስ አለበትን?”
ዳግም በመወለድ ወንጌል ውስጥ ለኃጢአቶቻችን ማስተስረያ የሚሆን ሕግ አለ። “ደም ሳይፈስ ስርየት (ኃጢአት ሙሉ በሙሉ የሚጠፋበት) የለም” (ዕብራውያን 9፡22)። በብሉይ ኪዳን ዘመን አንድ ሰው ከኃጢአቶቹ ለመዳን በፈለገ ጊዜ እጆቹን በኃጢአት መሥዋዕቱ ላይ በመጫን ኃጢአቶቹን ማስተላለፍ ነበረበት፣ እና ለኃጢአት የቀረበውም መሥዋዕት ለኃጢአቶቹ መሞት ነበረበት።
በዚሁ ተመሳሳይ መንገድ የእግዚአብሔር ልጅ የሰውን ዘር ሁሉ ለማዳን ወደዚህ ዓለም መጣ። ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ለመውሰድ ተጠመቀ፣ የኃጢአቶቻችንን ደመወዝ ለመክፈልም በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰ፣ እንዲሁም “ተፈጸመ” በማለት በመስቀል ላይ ሞተ። ከ3 ቀን በኋላ ከሙታን ተነሣ፣ አሁንም በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦዋል። እርሱ ለዘላለም አዳኛችን ሆንዋል።
ሙሉ በሙሉ ከኃጢአቶቻችን ነጻ ለመውጣት ግትር አሳቦቻችንን መጣልና በየቀኑ ከምንሠራቸው ኃጢአቶች መዳን እንዳለብን የሚነግረንን የሐይማኖት እምነት መተው ይኖርብናል። የሰው ዘር ኃጢአቶች ማስተስረያን ያገኙ ዘንድ መሥዋዕት ለአንዴና ለመጨረሻ መቅረብ ነበረበት። በሰማይ ያለው አምላክ በጥምቀቱ አማካይነት የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ወደ ገዛ ልጁ በማስተላለፍ ስለ እኛ እንዲሰቀል አደረገው። እርሱ ከሙታን በመነሣቱም መዳናችን ተጠናቋል።
“በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ... እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።” በኢሳይያስ 53 ላይ የዓለምና የሰው ዘር መተላለፎችና በደሎች ሁሉ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተላለፉ ተነግሮዋል።
በአዲስ ኪዳን ውስጥ በኤፌሶን 1፡4 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፦ “ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።” ይህ እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር በፊት በክርስቶስ እንደመረጠን ይነግረናል። ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እንኳን እግዚአብሔር በክርስቶስ የእርሱ ሕዝብ፣ እንከን የሌለብን ጻድቃን ሊያደርገን ወሰነ። ከዚህ በፊት ያሰብነው ምንም ነገር ቢኖር አሁን የእግዚአብሔርን ቃሎች፣ የውሃውን፣ የደሙንና የመንፈሱን ቃሎች ማመንና መታዘዝ ይገባናል።
እግዚአብሔር የእርሱ በግ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ኃጢአቶች እንደወሰደና የሰው ዘር ሁሉን ኃጢአት እንዳጸዳ ነግሮናል። በዕብራውያን 10 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፦ “ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፥ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር በሚያቀርቡት በዚያ መሥዋዕት የሚቀርቡትን ፍጹም ሊያደርጋቸው ከቶ አይችልም” (ዕብራውያን 10፡1)።
እዚህ ላይ ቃሉ በየዓመቱ የሚያቀርቡዋቸው እነዚያው መሥዋዕቶች እነርሱን በጭራሽ ፍጹማን ሊያደርጉዋቸው እንደማይችሉ ይናገራል። ሕጉ ሊመጣ ያለው በጎ ነገር ጥላ እንጂ የእውነተኛው ነገር ትክክለኛ አምሳል አይደለም። የሚመጣው መሲህ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአቶቻችንን ሁሉ ለማስተሰረይ በመጠመቅና በመሰቀል ለአንዴና ለመጨረሻ፣ (የእስራኤል አመታዊ ኃጢአቶች በአንድ ጊዜ እንደጠፉ ሁሉ) ፍጹማን አደረገን።
ስለዚህ ኢየሱስ በዕብራውያን 10 ላይ እንዲህ አለ፦ “ቀጥሎ፦ እነሆ አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ ብሎአል። ሁለተኛውንም እንዲመሥርት ዘንድ የፊተኛውን ይሽራል። በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል። ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል። እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥ ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደ ፊት ይጠብቃል። አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና። መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፤ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፦ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ፥ ብሎ ከተናገረ በኋላ፦ ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል። እነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ (ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል)፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም” (ዕብራውያን 10፡9-18)።
ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ከዓለም ኃጢአቶች ሁሉ እንዳዳነን እናምናለን።
 
 
በልቦቻችንና በልቡናዎቻችን ላይ የተጻፈው ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም የመወለድ መዳን
 
ዳግመኛ ኃጢአትን ስለማንሠራ ብቻ ጻድቃን ነን?
አይደለንም። እኛ ጻድቃን የሆንነው ኢየሱስ ኃጢአታችንን በሙሉ ስለወሰደና እኛም በእርሱ ስለምናምን ነው።
 
ሁላችሁም በእርሱ ፍጹም መዳን ታምናላችሁን? —አሜን።— ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እኛን ለማዳን እንደተጠመቀና በመስቀል ላይ ደሙን እንዳፈሰሰ የሚናገሩትን የእግዚአብሔር ቃሎች በእምነት ትታዘዛላችሁን? ዳግም ለመወለድ በእርሱ ቃል መታዘዝ አለብን። ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአትን ሙሉ በሙሉ የሚያጸዳ የእውነት ወንጌል አማካይነት የእኛን ኃጢአቶች በሙሉና የዓለምን ኃጢአቶች ሁሉ እንዳነጻ ስናምን መዳን እንችላለን።
የእግዚአብሔርን ሕግ በመጠበቅ ፈጽሞ ኃጢአት አልባ መሆን አንችልም፣ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራዎች ላይ ባለን እምነት ፍጹማን ልንሆን እንችላለን። ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጠመቅ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ወሰደና በመስቀል ላይም ለኃጢአቶቻችን ሁሉ ፍርድና ቅጣትን ተቀበለ። ይህንን ወንጌል ከሙሉ ልባችን በማመን ከኃጢአቶቻችን ሁሉ ልንድንና ጻድቃን ልንሆን እንችላለን። ይህንን ታምናላችሁን?
የኢየሱስ ጥምቀት፣ ስቅለቱና ትንሣኤው የሰው ዘር ኃጢአቶችን በሙሉ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የሚያገለግሉና ወሰን በሌለውና በሁኔታ ላይ ባልተመሠረተ የእግዚአብሔር ፍቅር ላይ የተመሠረቱ የመዳን ሕግ ናቸው። እግዚአብሔር ባለንበት ሁኔታ ወዶናል፣ እርሱ ጻድቅ ነው፣ ስለዚህ አስቀድሞ ጻድቃን አደረገን። ኃጢአቶቻችንን በሙሉ በእርሱ ጥምቀት አማካይነት ወደ ኢየሱስ በማስተላለፍም ጻድቃን አደረገን።
እርሱ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ለማንጻት አንድያ ልጁን ኢየሱስን ስለ እኛ ወደዚህ ዓለም ላከው። ኢየሱስ በጥምቀቱ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ እንዲወስድ ፈቀደ፣ ከዚያም እግዚአብሔር የኃጢአቶቻችንን ፍርድ በሙሉ ወደ ልጁ አስተላለፈ። የእግዚአብሔር አጋፔ በሆነው የውሃና የደም መዳን አማካይነት ጻድቅ ልጆቹ አደረገን።
በዕብራውያን 10፡16 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፦ “በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ።”
እኛ በልቦቻችንና በአእምሮዋችን በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአተኞች ነን ወይስ ጻድቃን ነን? በእግዚአብሔር ቃል ላይ እምነት ካለን ጻድቃን እንሆናለን። ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ወስዶ ለእነርሱ ተፈርዶበታል። ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን ነው። “እኛ በየቀኑ ኃጢአት ስለምንሠራ እንዴት ጻድቃን ልንሆን እንችላለን? እኛ በእርግጥም ኃጢአተኞች ነን” ብለን ልናስብ እንችላለን። ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ አባቱን እንደታዘዘው የእግዚአብሔርን ቃል ስንታዘዝ ጻድቃን እንሆናለን።
በእርግጥ ቀደም ብዬ እንዳልሁት፣ ዳግም ከመወለዳችን በፊት፣ በልቦቻችን ውስጥ ኃጢአት ነበረብን። የኃጢአቶቻችንን በሙሉ የሚያጠፋ የመዳን ወንጌል ወደ ልባችን ከወሰድን በኋላ ከኃጢአቶቻችን ሁሉ ዳንን። ወንጌልን ሳናውቅ በነበርንበት ጊዜ ኃጢአተኞች ነበርን። ነገር ግን በኢየሱስ መዳን ባመንን ጊዜ ጻድቃን ሆንን፣ ከዚያም የእግዚአብሔር ጻድቅ ልጆች ሆንን። ሐዋርያው ጳውሎስ የተናገረለት ጻድቃን የመሆን እምነት ይህ ነው። ኃጢአታችንን በሙሉ ሙሉ በሙሉ የሚያጸዳ የመዳን ወንጌል ያለን እምነት ‘ጻድቃን’ አደረገን።
ሐዋርያው ጳውሎስም ሆነ አብርሃም ወይም የእምነት አባቶች ጻድቃን የሆኑት በሥራዎቻቸው ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃሎች የሆኑትን የእርሱን የበረከት ቃሎች በማመንና በመታዘዝ ነው።
ዕብራውያን 10፡18 እንዲህ ይላል፦ “እነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ (ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል)፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም።” እንደተጻፈው በኃጢአቶቻችን እንዳንሞት እግዚአብሔር አዳነን። በዚህ ታምናላችሁን? —አሜን።—
በፊልጵስዩስ 2 ላይ፦ “በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ። በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው” (ፊልጵስዩስ 2፡5-11)።
ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ላይ እምነትን ያስፋፋው ለራሱ ታላቅ ዝና በመፈለግ አልነበረም። በፋንታው ለራሱ የባሪያን መልክ ወሰደ፣ በሰው አምሳልም መጣ። እርሱ እኛን ለማዳን ራሱን አዋረደና እስከ ሞት ድረስ ታዘዘ።
ስለዚህ ኢየሱስን እናመሰግነዋለን፦ “እርሱ አምላካችን፣ አዳኝና ንጉሥ ነው።” ለእግዚአብሔር ክብር የምንሰጠውና ኢየሱስን የምናመሰግነው ምክንያት ኢየሱስ እስከ መጨረሻው ድረስ የአባቱን ፈቃድ ስለታዘዘ ነው። እርሱ ባይታዘዝ ኖሮ አሁን የእግዚአብሔርን ልጅ ክብር ባልሰጠነውም ነበር። ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጅ የአባቱን ፈቃድ እስከ ሞት ድረስ ስለታዘዘ በዚህ ምድር ላይ ያለ ፍጥረትና ሕዝብ ሁሉ ክብር ይሰጠዋል ይህንኑም ለዘላለም ያደርገዋል።
ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ኃጢአቶች የወሰደ የእግዚአብሔር በግ ሆነ፣ እርሱም እነዚህን ኃጢአቶች በጥምቀቱ አማካይነት እንደወሰዳቸው ተጽፎዋል። እርሱ የዓለምን ኃጢአቶች ከወሰደ 2,000 ዓመታት ያህል አልፎዋል። እናንተና እኔ ከውልደታችን ጀምሮ በዚህ ዓለም ላይ ስንኖር ስለነበር፣ ኃጢአቶቻችንም ሁሉ በዓለም ኃጢአቶች ውስጥ ተካተዋል።
 
ነገ ኃጢአትን ብንሠራ ኃጢአተኞች እንሆናለን?
አንሆንም። ምክንያቱም ኢየሱስ ያለፈውን፣ የአሁኑንና የወደፊቱንም ኃጢአት ሁሉ ወስዶዋል።
 
ኦሪጅናል ኃጢአትና የራሳችንን የዕድሜ ዘመን በደሎች ሳንለይ፣ ከተወለድንበት ጊዜ ጀምሮ አስቀድመን ኃጢአት የሠራን አይደለንምን?
ኢየሱስ ከተወለድንበት ቀን እስከምንሞትበት ቀን ድረስ ኃጢአት እንደምንሠራ ስላወቀ አስቀድሞ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ወሰደ። አሁን ይህንን ማየት ትችላላችሁን? እስከ 70 አመት ድረስ ብንኖር ኃጢአቶቻችን ከመቶ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ የጭነት መኪናዎች በላይ ይሞሉ ነበር። ኢየሱስ ግን ኃጢአቶቻችንን በሙሉ በጥምቀቱ በአንድ ጊዜ ለሁሉም ሰው ወሰደ፣ በመስቀል ላይም የኃጢአቶቻችንን ፍርድ ተቀበለ።
ኢየሱስ ኦሪጅናል ኃጢአት ብቻ ወስዶ ቢሆን ኖሮ ሁላችንም ሞተን ሲዖል እንወርድ ነበር። እርሱ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ መውሰድ እንዳልቻለ ብናስብ እንኳን፣ ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ የመደምሰሱን ሐቅ ፈጽሞ አይለውጠውም።
በዚህ ዓለም ላይ ምን ያህል ኃጢአት መሥራት እንችላለን? የምንሠራቸው ኃጢአቶች በሙሉ በዓለም ኃጢአቶች ውስጥ ተካተዋል።
ኢየሱስ ዮሐንስን እንዲያጠምቀው በነገረው ጊዜ፣ የፈለገው ይህንኑ ነው። ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደ ራሱ መሰከረ። እግዚአብሔር ከኢየሱስ በፊት ባርያውን ልኮ ኢየሱስን እንዲያጠምቀው አደረገው። ስለዚህ ኢየሱስ የሰው ዘር ወኪል በሆነው በዮሐንስ በመጠመቅና ለመጠመቅም በፊቱ ራሱን፣ ዝቅ በማድረግ የሰውን ዘር ኃጢአቶች በሙሉ ወሰደ።
ከ20 እስከ 30፣ ከ30 እስከ 40፣ እና ወደፊትም ያሉ ዕድሜዎች ድረስ የሠራናቸው ኃጢአቶችና የልጆቻችንም ኃጢአቶች እንኳን ሳይቀሩ ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት በወሰዳቸው የዓለም ኃጢአቶች ውስጥ ተካተዋል።
በዚህ ዓለም ላይ ኃጢአት አለ ብሎ መናገር የሚችል ማነው? ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ወስዶዋል። ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን ሁሉ ለማስተሰረይ ያደረገውን ነገር ማለትም ጥምቀቱንና የክቡር ደሙን መፍሰስ ያለ አንዳች ጥርጥር በልቦቻችን ስናምን ሁላችንም መዳን እንችላለን።
አብዛኛዎቹ ሰዎች ሕይወታቸው ሁሉ ነገር እንደሆነ አድርገው ስለ ሕይወታቸው በመናገር በራሳቸው አስተሳሰቦች ውስጥ ተጠቅልለው ያልተረጋጋ ኑሮ ይኖራሉ። ነገር ግን ከዚህ የበለጠ አስቸጋሪ ሕይወት የሚኖሩ ብዙ ሰዎች አሉ። እኔን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ያልተረጋጋ ሕይወት ኖረዋል። ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ሙሉ በሙሉ የሚያጸዳ የመዳን ወንጌል፣ የኢየሱስን ጥምቀትና የደሙን ወንጌል እንዴት መረዳት ወይም መቀበል አትችሉም?
 
 
የኃጢአተኞች መዳን ተፈጽሞዋል
 
ኢየሱስ ለምን የጴጥሮስን እግር አጠበ?
ምክንያቱም እርሱ በጥምቀቱ አማካይነት የጴጥሮስን የወደፊት ኃጢአትም ጭምር እንዳነጻለት ጠንካራ እምነት እንዲኖረው ስለፈለገ ነው።
 
ዮሐንስ 19ን እናንብብ። “መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ። በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ። ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም፦ የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሚል ነበረ። ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር” (ዮሐንስ 19፡17-20)።
ውድ ወዳጆች፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ወሰደና በጲላጦስ ችሎት እንዲሰቀል ተፈረደበት። አሁን ስለዚህ ትዕይንት አብረን እናስብ።
ከቁጥር 28 ጀምሮ “ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ።” ኢየሱስ መጽሐፍ የሚለውን ለመፈጸም ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ወሰደ። እርሱም “ተጠማሁ” አለ።
“በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት። ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ” (ዮሐንስ 19፡28-30)።
ከሦስት ቀናት በኋላም ከሙታን ተነሣ።
ኢየሱስ በመጥምቁ ዮሐንስ መጠመቁና በመስቀል ላይ መሞቱ አንዱ ከሌላው የማይነጣጠል ግንኙነት አላቸው፣ አንዱ ያለ ሌላው መኖር አይችልም። ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ ኃጢአታችንን በሙሉ በሚያጠፋ የእውነት ወንጌሉ ስላዳነን እናመስግነው።
የሰው ዘር ሥጋ ሁልጊዜም የሚከተለው የስጋን ፍላጎቶች ስለሆነ በሥጋችን ኃጢአት ከመሥራት ማምለጥ አንችልም። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋችን ኃጢአቶች ሊያድነን ጥምቀቱንና ደሙን ሰጠን። በወንጌሉም ከሥጋ ኃጢአቶቻችን አዳነን።
ከኃጢአት ሙሉ በሙሉ የተቤዡ ሰዎች በቤተልሄም በተወለደው፣ በዮርዳኖስ በተጠመቀው፣ በመስቀል ላይ በሞተውና በ3ተኛው ቀን በተነሣው ኢየሱስ በማመን በማንኛውም ጊዜ መንግሥተ ሰማይ መግባት ይችላሉ። ጌታን እናመሰግነዋለን፣ ስሙንም ለዘላለም እናከብራለን። 
በመጨረሻው የዮሐንስ ምዕራፍ ውስጥ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ወደ ገሊላ ሄዶ ነበር። ወደ ጴጥሮስም ሄደና እንዲህ አለው፦ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?” ጴጥሮስም፦ “አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ” በማለት መለሰለት። ያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ “ግልገሎቼን አሰማራ።”
ጴጥሮስ ሁሉን ነገር ተረዳ፣ የኢየሱስን ጥምቀትና የደሙን ወንጌል፣ ከሁሉም ኃጢአቶች የሚያጸዳውን የመዳን ወንጌል። አሁን ከሁሉም ኃጢአቶች የሚያጸዳውን የውሃና የደም ወንጌል በማመኑና ኢየሱስ ለምን እግሮቹን እንዳጠበለት በመረዳቱ፣ በኢየሱስ ላይ ያለው እምነቱ የበለጠ ጠንካራ ሆነ።
እንደገና ዮሐንስ 21፡15ን እናንብብ። “ምሳ ከበሉ በኋላም ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን፥ አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ፥ አለው። ግልገሎቼን አሰማራ፥ አለው።” እርሱ ግልገሎቹን ለጴጥሮስ በአደራ መስጠት የቻለው ጴጥሮስ ሙሉ በሙሉ የዳነ የእርሱ ደቀ መዝሙር ስለነበርና ጴጥሮስ ጻድቅና ፍጹም የሆነ የእግዚአብሔር አገልጋይ ስለነበር ነው።
ጴጥሮስ በየቀኑ በሚሠራቸው ኃጢአቶቹ ዳግመኛ ኃጢአተኛ ቢሆን ኖሮ ኢየሱስ የመዳን ወንጌልን እንዲሰብክ ባልነገረውም ነበር፣ ምክንያቱም ሌሎች ደቀ መዛሙርቶችን ጨምሮ እርሱም በሥጋ በየቀኑ ኃጢአት ከመሥራት ማምለጥ ስለማይችል ነበር። ነገር ግን በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በማመናቸው ኃጢአቶቻቸውን በሙሉ የደመሰሰውን ወንጌል እንዲሰብኩ ነገራቸው።
 
 
“ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ”
 
ዳግመኛ ኃጢአትን ስትሠሩ ዳግመኛ ‘ኃጢአተኞች’ ትሆናላችሁን?
አትሆኑም። ኢየሱስ በዮርዳኖስ የወደፊት ኃጢአቶቻችሁን በሙሉ ቀድሞውኑ ወስዶዋል።
 
ኢየሱስ ለጴጥሮስ ስለተናገራቸው ቃሎች እናስብ። “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?” “አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ።” የእርሱ የፍቅር ኑዛዜ ለኃጢአቶች ሁሉ ማስተሰረያ በሆነው ወንጌል ላይ ካለው እምነት የመነጨ እውነተኛ ኑዛዜ ነበር።
ኢየሱስ እግሮቻቸውን በማጠብ ጴጥሮስንና ሌሎቹን ደቀ መዛሙርት ከሁሉም ኃጢአቶች ሙሉ በሙሉ የሚያጸዳውን ወንጌል አስተምሮዋቸው ባይሆን ኖሮ ፍቅራቸውን በዚያ መንገድ መመስከር ባልቻሉም ነበር።
በፋንታው ኢየሱስ ወደ እነርሱ መጥቶ “ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?” ኢየሱስ ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ፣ ጴጥሮስ “ጌታ ሆይ እኔ ያልተሟላሁና ኃጢአተኛ ነኝ። እኔ ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች በላይ ይበልጥ ልወድህ የማልችል ኃጢአተኛ ነኝ። እባክህ ተወኝ” ማለት ይችል ነበር። ጴጥሮስም ምናልባት ከኢየሱስ ለመደበቅም ሮጦ በሸሸ ነበር።
ነገር ግን እስቲ የጴጥሮስን መልሶች እናስብ። እርሱ ኃጢአትን በሚያጸዳው ወንጌል፣ ማለትም የሰውን ዘር ሁሉ ባዳነው የኢየሱስ ጥምቀትና ደም ወንጌል ተባርኮ ነበር።
ስለዚህ ጴጥሮስ፦ “አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ።” ይህ የፍቅር ኑዛዜ የመነጨው ኃጢአትን በሙሉ በሚያጸዳው የኢየሱስ እውነተኛ ወንጌል ላይ ካለው እምነቱ ነበር። ጴጥሮስ ኃጢአትን በሙሉ ሙሉ በሙሉ በሚያጸዳው እውነተኛ ወንጌል አመነ፤ በዚህ ወንጌል አማካይነት ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ሰዎች ከጉድለታቸውና ከሥጋ ድክመታቸው የተነሳ የሚፈጽሟቸውን የወደፊት ኃጢአቶችን ሳይቀር በራሱ ላይ ወሰደ።
ጴጥሮስ የኃጢአት ማጽዳት ወንጌልን በጽናት በማመኑና ኢየሱስ የእግዚአብሔር በግ እንደሆነ በማመኑ፣ ያለ ምንም ማመንታት ለጌታ መልስ መስጠት ቻለ። የኢየሱስ መዳን የመጣው ኃጢአትን በሙሉ ሙሉ በሙሉ የሚያጠፋው የእውነት ወንጌል ነው፣ በዚህም ጴጥሮስ ከዕለት ተዕለት ኃጢአቶቹ ሁሉ ደግሞ ድኖ ነበር። ጴጥሮስ የዓለምን ኃጢአቶች ሁሉ ሙሉ በሙሉ በሚያጠፋው የእውነት ወንጌል አማካይነት የሚገኘውን መዳን አመነ።
እናንተም ደግሞ እንደ ጴጥሮስ ናችሁን? ኃጢአትን በሚያጸዳው ወንጌል፣ ማለትም በጥምቀቱና በደሙ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ያጠፋውን ኢየሱስን መውደድና ማመን ትችላላችሁን? እንዴት እርሱን ላታምኑትም ሆነ ላትወዱት ትችላላችሁ? ሌላ መንገድ የለም።
ኢየሱስ የያለፉትን ወይም የአሁኑን ኃጢአቶች ብቻ ወስዶ የወደፊቱን ኃጢአቶች ለእኛ ቢተውልን ኖሮ፣ አሁን እንደምናደርገው ልናመሰግነው ባልቻልንም ነበር። ከዚህ በተጨማሪ፣ ሁላችንም በእርግጥ ወደ ገሃነም እንሄድ ነበር። ስለዚህ ሁላችንም ከሁሉም ኃጢአቶች ሙሉ በሙሉ የሚያጸዳውን ወንጌል በማመን እንደዳንን መመስከር አለብን።
ሥጋ ሁልጊዜም ኃጢአትን ለመሥራት ያዘነብላል፣ እኛም ሁልጊዜ ኃጢአትን እንሠራለን። ስለዚህ ኢየሱስ በሰጠን የተትረፈረፈ ቤዛነት ወንጌል፣ በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ወንጌል ማመናችን እንዳዳነን መመስከር አለብን።
የኢየሱስ ጥምቀትና ደም በሆነው የማስተስረያ ወንጌል ባናምን ኖሮ ማንም አማኝ ከዕድሜ ልክ ኃጢአቶቹ ባልዳነም ነበር። በተጨማሪም በየጊዜው በመናዘዝና ንስሐ በመግባት ከዕድሜ ልክ ኃጢአቶቻችን ሁሉ ተቤዥተን ቢሆን ኖሮ፣ ምናልባት ሁልጊዜ ጻድቃን ሆነን ለመቆየት በጣም ሰነፎች እንሆን ነበር፣ እንዲሁም ሁልጊዜም በልቦቻችን ውስጥ ኃጢአት ይኖረን ነበር።
ይህ ቢሆን ኖሮ፣ እንደ ኃጢአተኛ መሆን እንቀጥል ነበር፣ እንዲሁም ኢየሱስን መውደድ ወይም ወደ እርሱ መቅረብ አንችልም ነበር። በኢየሱስ መዳን ማመን አንችልም ነበር፣ እንዲሁም እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ ድረስ እርሱን መከተልም አንችልም ነበር።
ሆኖም ኢየሱስ ኃጢአትን የሚያጸዳውን ወንጌል ሰጠንና፣ ያመኑትን አዳነ። ኢየሱስ ፍጹም የሆነ አዳኝ በመሆን በእውነት እንወደው ዘንድ በየቀኑ የምንሠራቸውን ኃጢአቶች ሁሉ አጠበ።
ስለዚህ እኛ ምዕመናኖች የኢየሱስን ጥምቀትና ደም፣ ማለትም ኃጢአቶችን በሙሉ የሚያጸዳውን ወንጌል ከመውደድ ማምለጥ አንችልም። ምዕመናኖች ሁሉ ኢየሱስ በሰጠን ኃጢአቶችን በሙሉ የሚያጸዳው የእውነት ወንጌል አማካይነት ኢየሱስን ለዘላለም መውደድና የመዳን ፍቅር ምርኮኞች መሆን እንችላለን።
የተወደዳችሁ ወዳጆች ኢየሱስ ኢምንት ኃጢአትን እንኳን ትቶ ቢሆን ኖሮ በኢየሱስ ማመን ባልቻላችሁም፣ እንዲሁም ከኃጢአት ሙሉ በሙሉ የሚያጸዳውን ወንጌል ምስክር መሆን ባልቻላችሁም ነበር። የእግዚአብሔር አገልጋይ ሆናችሁም መሥራት ባልቻላችሁ ነበር።
ነገር ግን ኃጢአትን የሚያጸዳውን ወንጌል ብታምኑ ከዓለም ኃጢአቶች ሁሉ መዳን ትችላላችሁ። በኢየሱስ ቃል ውስጥ የተጻፈውን እውነተኛውን የእውነት ወንጌል ስትገነዘቡ፣ ከዓለም ኃጢአቶች ሁሉ እንድትድኑ ያደርጋችኋል።
 
 
“ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?”
 
ኢየሱስን ከማንኛውም ሌላ ነገር ይበልጥ እንድንወደው ያደረገን ምንድነው?
በጥምቀቱ አማካይነት ኃጢአቶቻችንን ሁሉ፣ እንዲያውም የወደፊት ኃጢአቶቻችንንም ጭምር ያጠበልን ለእኛ ያለው ፍቅሩ ነው
 
እግዚአብሔር ከሁሉም ኃጢአቶች በሙሉ የሚያጸዳውን የመዳን ወንጌል በሙሉ ለሚያምኑ አገልጋዮቹ ጠቦቶቹን በአደራ ሰጠ። ኢየሱስ ሦስት ጊዜ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?” በማለት ሲጠይቀው ጴጥሮስ በእያንዳንዱ ጊዜ “አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ” በማለት መለሰ። አሁን ስለ ጴጥሮስ መልሶች እናስብ። ይህ የጴጥሮስ የራሱ ፈቃድ መገለጫ ሳይሆን ኃጢአቶችን በሙሉ ሙሉ በሙሉ በሚያጸዳው ወንጌል ላይ ያለው እምነቱ መገለጫ እንደነበር ማየት እንችላለን።
አንድን ሰው ስንወድና ያም ፍቅር በፈቃዳችን ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ ፈቃዳችን ሲደክም፣ ሊንገዳገድ ይችላል። ነገር ግን ያ በእግዚአብሔር ፍቅር ጉልበት ላይ የተመሠረተ ከሆነ ለዘላለም ይኖራል። የእግዚአብሔር ፍቅር ማለትም ለኃጢአቶቻችን የሆነው የተትረፈረፈ ማስተስረያ የኢየሱስ ጥምቀት ውሃና መንፈስ ቅዱስ መዳን ልክ እንደዚያ ነው።
ኃጢአቶችን በሙሉ ሙሉ በሙሉ በሚያጸዳው ወንጌል ላይ ያለን እምነታችን ጌታ ለእኛ ላለው ፍቅር መሠረት መሆን አለበት። ፍቅራችን በፈቃዳችን ብቻ የተመሠረተ ቢሆን፣ ነገ እንሰናከላለን እንዲሁም በበደሎቻችን ምክንያት ራሳችንን መጥላት እንጨርሳለን። ነገር ግን ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ፣ የኦሪጅናል ኃጢአት፣ ያለፉትን፣ የቀን ተቀን ኃጢአቶቻችንን፣ የነገውንና የሕይወት ዘመን ኃጢአቶቻችንን በሙሉ አነጻ። እርሱ በዚህ ምድር ገጽ ላይ ካለው ማንንም ከመዳኑ አላስቀረም።
ይህ ሁሉ እውነት ነው። ፍቅራችንና እምነታችን የተመሠረቱት በፈቃዳችን ላይ ቢሆን ኖሮ በእምነታችን እንወድቅ ነበር። ነገር ግን ፍቅራችንና እምነታችን ኢየሱስ በሰጠን ከኃጢአት ሙሉ በሙሉ የሚያጸዳው የመዳን ወንጌል ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ቀድሞውኑም የእግዚአብሔር ልጆች፣ ጻድቃን ሆነናል። እኛ በውሃውና በመንፈስ ቅዱስ መዳን ስለምናምን ኃጢአት የለብንም።
መዳናችን የመጣው በራሳችን ባለን እምነት ሳይሆን ከእግዚአብሔር ፍቅርና ኃጢአቶችን በሙሉ ሙሉ በሙሉ ከሚያጸዳው እውነተኛው የመዳን ሕግ ከመሆኑ እውነታ የተነሳ በተጨባጩ ሕይወታችን ምንም ያህል ጎዶሎዎች ወይም ደካሞች ብንሆንም ጻድቃን ነን። መንግሥተ ሰማይ ገብተንም በመጨረሻ ጌታን ለዘላለም እናመሰግነዋለን። ይህንን ታምናላችሁን?
1ኛ ዮሐንስ 4፡10 እንዲህ ይላል፦ “ፍቅርም እንደዚህ ነው፣ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።” ኢየሱስ በውሃና በመንፈስ ቅዱስ ስላዳነን፣ እኛ በእውነት ወንጌል፣ ማለትም በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ ማመን አለብን።
እግዚአብሔር በውሃና በመንፈስ ቅዱስ ወንጌል ባያድነን ኖሮ ምንም ያህል በግለት ብናምንም መዳን ባልቻልንም ነበር። ኢየሱስ ግን በልቦቻችንና በሥጋችን የምንሠራቸውን ኃጢአቶች በሙሉ አጠበልን።
እኛ በእግዚአብሔር እናምን ዘንድ፣ ጻድቃን እንሆን ዘንድ፣ ማለትም ኃጢአትን ሙሉ በሙሉ የሚያጸዳውን ወንጌል በሆኑት የውሃውና የመንፈስ ቅዱስ ቃሎች ላይ ባለን እምነት አማካይነት ስለ መዳናችን እርግጠኞች መሆን አለብን። የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ሙሉ በሙሉ የሚያጸዳው ወንጌል በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ ማመን ነው። ኃጢአትን ሙሉ በሙሉ የሚያጸዳው የእውነት ወንጌል እውነተኛ እምነት ሲሆን፣ እውነተኛ የመዳን መሠረትና የእግዚአብሔር ወንጌል ቁልፍ ነው።
 
 
የራሳችንን የፈቃድ እምነት መተው አለብን
 
እውነተኛ እምነት የሚመጣው ከየት ነው?
ይህ የሚመጣው ቀድሞውኑም የአሁንና የወደፊት ኃጢአቶቻችንን ሁሉ ካነጻው ከጌታ ፍቅር ነው።
 
በአንድ ሰው ፈቃድ የተያዘ እምነት ወይም ፍቅር እውነተኛ ፍቅርም ሆነ እውነተኛ እምነት አይደለም። በዚህ ዓለም ውስጥ መጀመሪያ በበጎ ፈቃድ በኢየሱስ የሚያምኑ፣ በኋላ ግን በልቦቻቸው ውስጥ ባለው ኃጢአት ምክንያት እምነታቸውን ሙሉ በሙሉ የሚተዉ ብዙ ሰዎች አሉ።
ነገር ግን ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ እንዳነጻ መገንዘብ አለብን፣ ኢምንት የሆኑ በደሎችን ብቻ ሳይሆን ከእውቀት ማነስ የተነሳ የተሠሩ ታላላቅ ኃጢአቶችንም ጭምር።
በዮሐንስ 13 ላይ ኢየሱስ የእርሱ መዳን ምን ያህል ሁሉን አቀፍ እንደሆነ ለደቀ መዛሙርቱ ለማስተማር ከመሰቀሉ በፊት ደቀ መዛሙርቱን ሰበሰባቸው። ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ባደረገው እራት ወቅት የመዳኑን እውነት ለማብራራት ተነሥቶ እግሮቻቸውን አጠበ። ሁላችንም ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግሮች በማጠብ ያስተማራቸውን የውሃና የመንፈስ ቅዱስ ወንጌል ማወቅና ማመን ይኖርብናል።
ጴጥሮስ ግን መጀመሪያ ላይ ኢየሱስ እግሮቹን እንዳያጥበው በጽኑ ተቃውሞ ነበር። “የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም።” ይህ በራሱ ፈቃድ የያዘው እምነት መግለጫ ነበር። ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ።”
አሁን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የኢየሱስን ቃላት መረዳት እንችላለን። እነዚህ የእውነት ቃል፣ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል፣ ኃጢአቶችን በሙሉ ሙሉ በሙሉ የሚያጸዳ ናቸው፣ ኃጢአተኛው በሙሉ ልቡ በማመን ጻድቅ እንዲሆን የሚያደርገው።
ጴጥሮስ ከደቀ መዛሙርት ጋር ዓሳ ለማጥመድ ሄደ። እነርሱ ኢየሱስን ከማግኘታቸው በፊት እንደሚያደርጉት ዓሣ እያጠመዱ ነበር። ከዚያ ኢየሱስ በፊታቸው ተገለጠና ጠራቸው። ኢየሱስ ቁርስ አዘጋጅቶላቸው ነበር፣ ቁርስ እየበሉ ሳለ ጴጥሮስ ኢየሱስ ቀደም ብሎ የተናገራቸውን ቃሎች ትርጉም ተረዳ። “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ።” በመጨረሻ ከዚህ በፊት እግሮቹን ባጠበው ጊዜ ኢየሱስ በእርግጥም ምን ማለቱ እንደነበር ተገነዘበ።
“ጌታ ኃጢአቶቼን በሙሉ አጠበልኝ። ከድክመቶቼ የተነሣ የሠራኋቸው ኃጢያቶች በሙሉ፣ ወደፊት የምሠራቸውም ኃጢአቶች በሙሉ ጨምሮ ነጽተዋል።” ጴጥሮስ በራሱ ፈቃድ የያዘውን እምነት ትቶ ኃጢአቶችን በሙሉ ሙሉ በሙሉ የሚያጸዳው የእውነት ወንጌል በሆነው በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ላይ ማመን ጀመረ።
ከቁርስ በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ “ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?” አሁን፣ በኢየሱስ ፍቅር ላይ ባለው እምነት ተጠናክሮ፣ ጴጥሮስ እንዲህ ሲል መሰከረ። “አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ።” ጴጥሮስ እንዲህ ማለት የቻለው ኢየሱስ “በኋላ ግን ታስተውለዋለህ” ሲል ምን ማለቱ እንደነበር ስለተገነዘበ ነበር። እርሱ እውነተኛ እምነቱን፣ ማለትም በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ያለውን እምነት፣ ኃጢአቶችን በሙሉ ሙሉ በሙሉ የሚያጸዳውን የእውነት ወንጌል መመስከር ቻለ።
 
 
ከዚያም በኋላ እርሱ እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሆነ
 
ስለዚህ፣ ከዚያ በኋላ ጰጥሮስና ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት እስከ መጨረሻው እስትንፋሳቸው ድረስ ወንጌልን ሰበኩ። ክርስቲያኖችን ያለ ምሕረት ሲያሳድድ የነበረው ጳውሎስም እንኳን በእነዚያ የሮም መንግስት ጭካኔ የበዛባቸው ቀናት ወቅት ወንጌልን መስክሮዋል።
 
የእግዚአብሔር እውነተኛ አገልጋይ የምትሆኑት እንዴት ነው?
ለኃጢአቶቼ ሁሉ በሆነው ዘላለማዊ ማስተስረያ በማመን ነው
 
ከአሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መካከል ይሁዳ ኢየሱስን ሸጠውና በኋላም ራሱን ሰቀለ። የእርሱን ቦታ የወሰደው ሐዋርያው ጳውሎስ ነበር። ደቀ መዛሙርት በመካከላቸው ማትያስን መርጠው ነበር፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የመረጠው ጳውሎስን ነበር፣ ስለዚህ ጳውሎስ የኢየሱስ ሐዋርያ ሆኖ ከሌሎች ደቀ መዛሙርት ጋር ከሁሉም ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ንጹህ መሆን የሚያስችለውን የመዳን ወንጌል ሰበከ።
አብዛኞቹ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የሞቱት ሰማዕታት ሆነው ነው። የሞት ዛቻ ሲደርስባቸው እንኳን እምነታቸውን አልካዱም፣ እውነተኛውን ወንጌል መስበካቸውን ቀጠሉ።
“ኢየሱስ ክርስቶስ የሥጋችሁን ኃጢአቶች በሙሉ በጥምቀቱና በደሙ ወንጌል፣ ማለትም ከኃጢአት ሙሉ በሙሉ ንጹህ መሆን በሚያስችለው የመዳን ወንጌሉ አነጻ። ኢየሱስ በዮርዳኖስ ጥምቀቱ ኃጢአቶቻችሁን በሙሉ ወሰደና ስለ እናንተ በመስቀል ላይ ፍርድን ተቀበለ። በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም ወንጌል እመኑና ተዳኑ።”
ብዙዎች ወንጌልን በመስማትና በእርሱም በማመን በእርግጥ ዳኑ። ይህ በኢየሱስ ጥምቀት፣ በደሙና በመንፈስ ቅዱስ ወንጌል ላይ ያለ የእምነት ሐይል ነበር።
ደቀ መዛሙርት “ኢየሱስ አምላክና አዳኝ ነው” በማለት የውሃውንና የመንፈስ ቅዱስን ወንጌል ሰበኩ። እነርሱ የውሃውንና የመንፈስ ቅዱስን ወንጌል ስለመሰከሩ ነው፣ እናንተና እኔ አሁን የኢየሱስን ጥምቀትና ደም ወንጌል፣ የመዳን ወንጌልን መስማት የቻልነውና ከኃጢአት የዳንነው። ከእግዚአብሔር ወሰን የለሽ ፍቅርና ከኢየሱስ የተሟላ መዳን የተነሳ ሁላችንም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሆነናል።
ሁላችሁም ታምናላችሁን? ኢየሱስ አብዝቶ ስለወደደን የውሃና የመንፈስ ቅዱስ ወንጌል፣ ማለትም ከሁሉም ኃጢአት ሙሉ በሙሉ የሚያድነንን እውነት ሰጠን፣ እኛም ጻድቃን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሆንን። ኢየሱስ እውነተኛውን ከሁሉም ኃጢአት ሙሉ በሙሉ የሚያነጻውን እውነተኛ ወንጌል ለማስተማር የደቀ መዛሙርቱን እግሮች አጠበ።
ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግሮች ያጠበው የዓለም ኃጢአቶች በሙሉ፣ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ የምንሠራቸውን ኃጢአቶች ጨምሮ እርሱ በተጠመቀና በመስቀል ላይ ደሙን ባፈሰሰ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንደነጹ እነርሱንና እኛን ለማስተማር ነው። ለፍቅሩና ለኢየሱስ ሁሉንም ኃጢአት የሚያጸዳውን የመዳን ወንጌል እናመሰግናለን።
ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግሮች በማጠብ ሁለት ነገሮችን አስተምሮናል። የመጀመሪያው “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ” ብሎ እንደተናገረው እነርሱን ለማስተማር ነበር። ይህም ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ከሁሉም ኃጢአት ሙሉ በሙሉ የሚያጸዳው የመዳን ወንጌል፣ ማለትም የኢየሱስ ጥምቀትና የደሙ ወንጌል መንጻታቸውን ለማስተማር ነበር።
ሁለተኛው ትምህርት ኢየሱስ ኃጢአተኞችን ለማዳንና ጻድቃን ለማድረግ ራሱን ዝቅ እንዳደረገ እኛ ዳግም የተወለድን ሰዎች ከሁሉም ኃጢአት ሙሉ በሙሉ የሚያነጻውን የመዳን ወንጌል በመስበክ ሌሎችን ማገልገል የሚገባን መሆኑ ነው። መጀመሪያ የመጣነው እኛ በኋላ የሚመጡትን እነርሱን ማገልገላችን ተገቢ ነው።
ኢየሱስ በፋሲካ በዓል ከመጀመሩ በፊት ቀን የደቀ መዛሙርቱን እግሮች ያጠበባቸው ሁለት ምክንያቶች ግልጽ ናቸው፣ እና እነዚህ አሁንም በቤተክርስቲያን ውስጥ ይገኛሉ።
ደቀ መዝሙር በፍጹም ከመምህሩ ሊበልጥ አይችልም። ስለዚህ እኛም ወንጌልን ለዓለም እንሰብካለን፣ ኢየሱስን እንደምናገልግል ሆነንም እናገለግለዋለን። እኛ፣ መጀመሪያ የዳንን ሰዎች፣ ከእኛ በኋላ የሚመጡትን ማገልገል አለብን። ኢየሱስ ይህንን ለማስተማር የደቀ መዛሙርቱን እግሮች አጠበ። በተጨማሪም፣ የጴጥሮስን እግሮች በማጠብ፣ እርሱ ለእኛ ፍጹም አዳኝ እንደሆነ አሳየን፤ ስለዚህ ዳግመኛ በፍጹም በዲያብሎስ እንዳንሳሳት ነው።
ሁላችሁም ከሁሉም ኃጢአት ሙሉ በሙሉ የዳንን የሚያስገኘው በውሃውና በመንፈስ ቅዱስ ወንጌል በማመን መዳን ትችላላችሁ። ኢየሱስ በጥምቀቱ፣ በስቅለቱና በትንሳኤው ኃጢአቶቻችንን በሙሉ አንጽቷል፣ እና ለዘላለም ከዓለም ኃጢአቶች መዳን የሚችሉት በእርሱ ወንጌል የሚያምኑ ብቻ ናቸው።
 
 
የዘወትር ኃጢአቶቻችን በሙሉ ባነጻልን ወንጌል እምነት ይኑረን
 
ከሁሉም ኃጢአት ሙሉ በሙሉ የዳንን የሚያስገኘው የውሃውና የመንፈሱ ቃሎች በማመን የዲያብሎስን ማታለያዎች በሙሉ መቁረጥ እንችላለን። ሰዎች በቀላሉ በዲያብሎስ ይታለላሉ፣ እና ዲያብሎስም ሁልጊዜ በጆሮዎቻችን ያንሾካሹካል። የሰዎች ሥጋ በዓለም ላይ ኃጢአት እንደሚሠራ እያወቅን፣ እንዴት ያለ ኃጢአት ሊሆኑ ይችላሉ? ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች ናቸው።
እኛ ግን መልሱን እናውቃለን። “ኢየሱስ በጥምቀቱ የሥጋችንን ኃጢአቶች በሙሉ እንደወሰደ ካወቅን እንዴት አማኝ ከኃጢአት ጋር ሊሆን ይችላል? ኢየሱስ የኃጢአትን ደመወዝ ሙሉ በሙሉ ከፈለ፣ ስለዚህ ለእኛ የቀረልን ምን የምንከፍለው ኃጢአት አለ?”
በውሃውና በደሙ ወንጌል የማናምን ከሆንን የዲያብሎስ ቃሎች ምክንያታዊ ይመስላሉ። ነገር ግን ወንጌል በኛ በኩል ከሆነ፣ በእግዚአብሔር ቃል እውነት ላይ የማይናወጥ እምነት ሊኖረን ይችላል።
ስለዚህ ከውሃውና ከደሙ ወንጌል ዳግም የመወለድ ወንጌል እምነት ሊኖረን ይገባል። እውነተኛ እምነት በኢየሱስ ጥምቀት፣ በመስቀል ላይ ደሙ፣ በሞቱና በትንሣኤው ወንጌል ማመን ነው።
የተቀደሰውን ድንኳን ሞዴል ስዕል አይታችሁ ታውቃላችሁን? ይህ ትንሽዬ የድንኳን ቤት ነው። ቤቱ በሁለት ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን ውጭኛው ክፍል ቅድስት ስፍራ፣ ውስጠኛው ክፍል ደግሞ የስርየት መክደኛው ያለበት ቅድስተ ቅዱሳን የተባለው መቅደስ ነው።
በተቀደሰው ድንኳን ውጫዊ አደባባይ ላይ የቆሙ በአጠቃላይ 60 ምሰሶች አሉ፣ ቅድስቱ ስፍራ 48 ሳንቃዎች አሉት። የእግዚአብሔርን ቃሎች ትርጉም ለመረዳት የተቀደሰውን ድንኳን ምስል በአእምሮአችን ሊኖረን ይገባል።
 
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያው በር የተሰራው ከምንድነው?
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያው በር የተሰራው ከምንድነው?
የተሠራው ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ የተሰራ መጋረጃ ነው።
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር በዘጸአት 27፡16 ላይ ተገልጦዋል፦ “ለአደባባዩም ደጅ ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከጥሩ በፍታም በጥልፍ አሠራር የተሠራ ሀያ ክንድ መጋረጃ ይሆናል፤ ምሰሶቹም አራት፥ እግሮቹም አራት ይሁኑ።” ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋሉት ቁሶች ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ግምጃ እንደዚሁም ጥሩ በፍታ ነበሩ። ይህም በደምብ የተፈተለና በጣም ውብ ነበር።
እግዚአብሔር እያንዳንዱ ሰው የመግቢያውን በር ለማግኘት ቀላል እንዲሆንለት የመግቢያውን በር በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ግምጃ በቀለም አሸብርቆ እንዲፈትል ሙሴን አዘዘው። ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ የተሠራው የመግቢያው በር በአራት ምሰሶች ላይ ተንጠልጥሎ ነበር።
እነዚህ አራቱ ቁሳቁሶች እግዚአብሔር በልጁ፣ በኢየሱስ ጥምቀትና ደም፣ እንዲሁም እርሱ አምላክ መሆኑን በሚያምኑ ሁሉን የሚያድንበትን የእግዚአብሔርን የመዳን ንድፍ ያመላክታሉ።
የተቀደሰውን የመገናኛ ድንኳን ለመሥራት ጥቅም ላይ የዋሉት ቁሳቁሶች እያንዳንዳቸው የተለየ ትርጉም አላቸው፣ እና የሰውን ዘር በኢየሱስ አማካይነት ለማዳን ያለውን የእግዚአብሔር ቃልና የእርሱን እቅዶች ያመላክታሉ።
አሁን፣ ለተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋሉት ምን ያህል የተለያዩ ቁሳቁሶች ነበሩ? ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ግምጃና ጥሩ በፍታ ነበሩ። እነዚህ አራቱ ዳግም በምንወለድበት ወንጌል ላይ ያለንን እምነት በማጠንከር ረገድ በጣም ወሳኝ ናቸው። አስፈላጊ ባይሆኑ ኖሮ ይህ መረጃ እንዲህ ባለ ዝርዝር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባልተጻፈ ነበር።
ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በርና፣ ለመገናኛው ድንኳን ጥቅም ላይ የዋሉት ቁሳቁሶች በሙሉ የመዳናችን አቢይ ክፍል ስለነበሩ ከሰማያዊ ከሐምራዊ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ መሠራት ነበረባቸው። ይህ መዳን በየቀኑ የምንሠራቸውን ኃጢአቶች፣ የኦሪጅናል ኃጢአትና የወደፊት ኃጢአቶችን አነጻ። ስለዚህ እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ለሙሴ ገለጠለትና በትክክል እንደተነገረው እንዲያደርግ ነገረው።
 
 
ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ግምጃ በእግዚአብሔር ወንጌል ውስጥ ምን ማለት ናቸው?
 
ለመገናኛው ድንኳን ጥቅም ላይ የዋሉት ቁሶች የሚያመላክቱት ምንድነው?
በጥምቀቱና በደሙ አማካይነት የሆነውን የኢየሱስን መዳን ነው
 
በተቀደሰው የመገናኛ ድንኳን ውስጥ በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል ለተንጠለጠለው መጋረጃ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ግምጃና ጥሩ በፍታ ዳግም ጥቅም ላይ ውለዋል። በተቀደሰው የመገናኛ ድንኳን ውስጥ የሚያገለግለው ሊቀ ካህን የሚለብሳቸው ልብሶችም ከተመሳሳይ ቁሳቁሶች የተሠሩ ነበሩ።
ሰማያዊው ግምጃ የኢየሱስን ጥምቀት ያመለክታል። በ1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 ላይ እንዲህ ይላል፦ “ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል።” ጴጥሮስ በዚህ ቁጥር ላይ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ የወሰደበት የኢየሱስ ጥምቀት የስርየት መዳን ምሳሌ እንደሆነ አረጋገጠ። ኃጢአቶቻችን በሙሉ፣ የዓለም ኃጢአቶች በሙሉ በጥምቀቱ አማካይነት ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል። ስለዚህ የኢየሱስን ጥምቀት የሚያመላክተው ሰማያዊ ግምጃ የመዳን ቃል እጅግ አስፈላጊ ክፍል ነው።
ቀዩ ግምጃ የኢየሱስን ደም ያመለክታል፣ እና ሐምራዊው ግምጃ ንግሥናን ያመለክታል—ኢየሱስ ንጉሥና አምላክ የመሆኑን ማዕረግ። የግምጃው ሦስቱ ቀለማት በኢየሱስና በመዳኑ ላይ ላለን እምነታችን አስፈላጊ ነበሩ።
ሊቀ ካህኑ የሚለብሰው ውብ ልብስ ኤፉድ ተብሎ ይጠራል፣ እና የኤፉዱ ቀሚስ ሙሉ በሙሉ ሰማያዊ ነበር። ሊቀ ካህኑ በንጹህ የወርቅ ምልክት ላይ ‘ቅድስና ለእግዚአብሔር’ የሚል የተቀረጸበት ጥምጣም በራሱ ላይ አድርጎዋል። ምልክቱ በሰማያዊ ፈትል ከጥምጣሙ ጋር ተያይዞዋል።
 
 
በሰማያዊው ግምጃ የተገለጠው እውነት
 
ሰማያዊው ግምጃ ምንን ያመለክታል?
የኢየሱስን ጥምቀት
 
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰማያዊውን ግምጃ ትርጉም ተመለከትሁ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰማያዊ ምን ይላል? በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ግምጃዎች መካከል ያለውን ሰማያዊውን ግምጃ መረዳት አለብን።
ሰማያዊ ግምጃ የኢየሱስን ጥምቀት ያመላክታል። ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ለመውሰድ በመጥምቁ ዮሐንስ ተጠምቆዋል (ማቴዎስ 3፡15)።
ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአቶች በጥምቀቱ ባይወስድ ኖሮ በእግዚአብሔር ፊት መቀደስ ባልቻልንም ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ለመውሰድ ወደዚህ ዓለም መምጣትና በዮርዳኖስ ወንዝ በመጥምቁ ዮሐንስ መጠመቅ ነበረበት።
በተቀደሰው የመገናኛ ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ ሰማያዊ ግምጃ የተደረገበት ምክንያት ያለ ኢየሱስ ጥምቀት መቀደስ ስለማንችል ነው።
ቀዩ ግምጃ የእርሱን ደም ማለትም የኢየሱስን ሞት ያመላክታል። ሐምራዊው ግምጃ መንፈስ ቅዱስን ያመለክታል፣ ስለዚህ “ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ” (1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡15) የተባለውን የኢየሱስን ማዕረግ ያሳያል።
ቀዩ ግምጃ ለሰው ዘር ሁሉ የኃጢአትን ደመወዝ ለመክፈል በመስቀል ላይ የደማውን የክርስቶስ ደም የሚያመላክት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአትን ሙሉ በሙሉ የሚያጠፋውን ወንጌል ለማሳካት ራሱን በመስቀል ላይ መሥዋዕት ከማድረጉ በፊት በጥምቀቱ አማካይነት የሰውን ዘር ኃጢአቶች በሙሉ በራሱ ላይ ለመውሰድ በሥጋ ወደዚህ ዓለም መጣ። የኢየሱስ ጥምቀት በብሉይ ኪዳን በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን ጥቅም ላይ በዋሉት ግምጃዎች ቀለማት አማካይነት የተተነበየ እውነተኛ የመዳን ወንጌል ነው።
የመገናኛው ድንኳን ምሰሶዎች ከግራር እንጨት የተሠሩ ሲሆን፣ መያዣዎቹ ከናስ የተሠሩ ነበሩ፣ እና የናሱ መያዣዎች በብር ማሠሪያዎች ተሸፍነው ነበር።
ኃጢአተኞች በሙሉ ለኃጢአቶቻቸው የተፈረደባቸው የኃጢአት ደመወዝ ሞት ስለሆነ ነው። አንድ ሰው በእግዚአብሔር ተባርኮ እንደገና ሊወለድ ከመቻሉ በፊት ለኃጢአቶቹ መፈረድ እንዳለበት ማወቅ አለበት።
ስለዚህ በብሉይ ኪዳን በተቀደሰው የመገናኛ ድንኳን በሰማያዊ ግምጃ የተመሰለው፣ በአዲስ ኪዳን የኢየሱስ ጥምቀት ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ወስዶዋል። ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን ወደ መስቀል ወሰደና ደማ፣ ለእነርሱም ተፈረደበት። እንዲህ በማድረጉም ከኃጢአት ሙሉ በሙሉ የመንጻት ወንጌል እምነት ያለንን ሰዎች ሁሉ አዳነን። እርሱ የነገሥታት ንጉሥና ቅዱስ አምላክ ነው።
የተወደዳችሁ የኢየሱስ ጥምቀት ኃጢአቶቻችንን በሙሉ በመውሰድ ያዳነን የኢየሱስ ማዳን ነው። አምላክ የሆነው ኢየሱስ በሥጋ ወደ ዓለም መጣ፤ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ለመውሰድም ተጠመቀ፤ በእኛ ፋንታ ፍርድን ለመቀበልም ተሰቀለና ደሙን አፈሰሰ። የኢየሱስ ጥምቀት እርሱ ለሰው ዘር ሁሉ እውነተኛ አዳኝ እንደሆነ ያለ ጥርጥር ያስተምረናል።
ይህንን ለተቀደሰው የመገናኛ ድንኳን የመግቢያ በር ጥቅም ላይ በዋሉት ቀለማቶች ውስጥም ማየት እንችላለን። የጥሩ በፍታ ክር መጠቀም እርሱ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ያለ ልዩነት እንዳዳነን ያሳያል።
ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ የተፈተለው የመግቢያው በር መጋረጃ የእግዚአብሔርን የመዳን እውነት በግልጽ የሚነግረን ነበር። ይህ ለማስተስረያ መዳን ፈጽሞ አስፈላጊ ነበር።
ለተቀደሰው የመገናኛ ድንኳን የመግቢያ በር ጥቅም ላይ ከዋሉት ቁሳቁሶች ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ኃጢአተኞችን ያለ እቅድ እንዲያው በዘፈቀደ እንዳላዳነን ማየት እንችላለን። እርሱ የእግዚአብሔርን ዝርዝር እቅድ በጥንቃቄ በመታዘዝ የሰውን ዘር መዳን ለመፈጸም ተጠመቀ ተሰቀለ፣ ከሙታንም ተነሣ። ኢየሱስ ኃጢአትን ሙሉ በሙሉ የሚያስወግድ ወንጌል ቁሳቁሶች በሆኑት በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ግምጃ በእርሱ ማዳን ያመኑትን ሁሉ አዳናቸው።
 
 
የብሉይ ኪዳኑ የናስ መታጠቢያ ሰን በአዲስ ኪዳን የጥምቀት ጥላ ነበር
 
ካህናቱ ወደ ቅዱስ ቦታው ከመግባታቸው በፊት እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ለምን ይታጠባሉ?
ምክንያቱም በእግዚአብሔር ፊት ያለ ምንም ኃጢአት መቆም ስለነበረባቸው ነው።
 
የመታጠቢያውም ሰን የተሠራው ከናስ ነበር። ናስ ኢየሱስ ስለእኛ የተሰቃየበትን ፍርድ ያመላክታል። የውሃ መያዣው ኃጢአቶቻችን በሙሉ እንደነጹ የሚነግረንን የወንጌል ቃል ያመላክታል።
ይህም ኃጢያቶቻችን እንዴት እንደተወገዱ ያሳየናል። ይህ የዓለም ኃጢአቶች በሙሉ በኢየሱስ ጥምቀት ቃሎች ላይ ባለ እምነት አማካይነት ሊነጹ እንደሚችሉ የሚያሳይ የእውነት ጥላ ነው።
የሚቃጠል መሥዋዕት መሠውያ ፍርድን ያመላክታል። ሰማያዊ የሆነው የኢየሱስ ውሃ፣ የመዳን ወንጌል ማለትም በመጥምቁ ዮሐንስ የሆነው የኢየሱስ ጥምቀት ነው (ማቴዎስ 3፡15፣ 1ኛ ዮሐንስ 5፡5-10)። ይህም በስርየት አማካይነት የመዳን ወንጌልን የሚመሰክር ቃል ነው።
1ኛ ዮሐንስ 5 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፦ “ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው። የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፦ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ።” እርሱ በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን ሰው በውስጡ የውሃው፣ የደሙና የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት እንዳለው ይነግረናል።
እግዚአብሔር በስርየቱ ወንጌል እምነት አማካይነት እንድንቀደስና ወደተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን እንድንገባ ፈቀደልን። ስለዚህ አሁን በእምነት መኖር፣ የእግዚአብሔርን ቃሎች መመገብ፣ በእርሱ መባረክና የጻድቃን ሕይወትን መኖር እንችላለን። የእግዚአብሔር ሕዝብ መሆን ማለት በውሃና በመንፈስ ቅዱስ ወንጌል እምነት አማካይነት መዳንና በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን ውስጥ መኖር ማለት ነው።
ዛሬ ብዙ ሰዎች በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ላይ ስላለው ስለ ሰማያዊው ሐምራዊውና ቀዩ ግምጃ ትርጉም ሳያስቡ ማመን ብቻ በቂ ነው ይላሉ። አንድ ሰው እነዚህን ነገሮች ሳያውቅ በኢየሱስ አምኖ ከሆነ በልቡ ውስጥ አሁንም ገና ኃጢአት ስላለ እምነቱ እውነተኛ አይሆንም። ይህ ሰው በእውነተኛው ወንጌል፣ ማለትም በውሃ፣ በደምና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ዳግም የመወለድን እውነት ባለማመኑ አሁንም ድረስ በልቡ ውስጥ ኃጢአት አለበት።
አንድ ሰው በጣም ጥቂት የሚያውቀውን ሰው እንዲመዝን ቢጠየቅ አድማጩን ለማስደሰት ሲል “አዎ ይህንን ሰው አምነዋለሁ። በእርግጥ ፈጽሞ አግኝቼው አላውቅም፣ ነገር ግን አምነዋለሁ” ይላል። አድማጩ ይህንን በመስማት የሚደሰት ይመስላችኋልን? ምናልባት አንዳንዶቻችሁ ትደሰቱ ይሆናል፣ ነገር ግን ይህ እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው እምነት አይደለም።
እግዚአብሔር በሰማያዊው (የኢየሱስ ጥምቀት)፣ በሐምራዊው (የኢየሱስ መለኮታዊነት)፣ እና በቀዩ (የኢየሱስ ደም) ግምጃ አማካይነት የኢየሱስ መዳን በሆነው ከኃጢአት ሙሉ በሙሉ የሚያነጻ የእውነት ወንጌል እንድናምን ይፈልግብናል። በኢየሱስ ከማመናችን በፊት እኛን ከኃጢአቶች ሁሉ እንዴት እንዳዳነን ማወቅ ይገባናል።
በኢየሱስ ስናምን እንዴት በውሃ (የኢየሱስ ጥምቀት)፣ በደም (ሞቱ)፣ እና በመንፈስ ቅዱስ (ኢየሱስ አምላክ መሆኑ) ከኃጢአቶቻችን ሁሉ እንዳዳነን ማወቅ ይገባናል።
በትክክል ስንረዳ እውነተኛና የተሟላ እምነት መያዝ እንችላለን። ይህንን እውነት ሳናውቅ እምነታችን በጭራሽ የተሟላ አይሆንም። እውነተኛ እምነት የሚመጣው የኢየሱስን መዳን፣ ኃጢአትን ሙሉ በሙሉ የሚያነጻውን ወንጌል፣ እና ኢየሱስ እውነተኛ የሰው ዘር አዳኝ መሆኑን በመረዳት ብቻ ነው።
ታዲያ በኢየሱስ ላይ የሚያፌዝ እምነት ምን ይመስላል? እስቲ እንመልከት።
 
 
በኢየሱስ የሚያፌዝ እምነት
 
ለእምነት እጅግ የሚያስፈልገው ምንድነው?
ትክክለኛ የሆነ የኢየሱስ ጥምቀት እውቀት
 
ኢየሱስን በዘፈቀደ ማመን በእርሱ ማፌዝ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርባችኋል። “ማመን አስቸግሮኛል፣ ነገር ግን እርሱ አምላክና የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነ የሆኖ ሆኖ በእርሱ ማመን ይኖርብኛል” ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ በኢየሱስ ላይ እያፌዛችሁ ነው። እውነተኛ እምነት ለመያዝ፣ ማስተስረያ ወንጌል በሆነው የኢየሱስ ጥምቀትና ደም ማመን አለባችሁ።
ኃጢአት ሙሉ በሙሉ የሚነጻበትን የእውነት ወንጌል ሳያውቁ በኢየሱስ ማመን ጨርሶ በኢየሱስ ከአለማመንም የከፋ ነው። የኢየሱስን ደም ብቻ የሚያምነውን ወንጌል መስበክ እውነትን ሳያውቁ በከንቱ መሥራት ነው።
ኢየሱስ ማንም በዘፈቀደ ወይም ያለ ምክንያት በእርሱ እንዲያምን አይፈልግም። እርሱ የስርየትን ወንጌል አውቀን በእርሱ እንድናምን ይፈልግብናል።
በኢየሱስ ስናምን የስርየት ወንጌል የኢየሱስ ጥምቀትና ደም እንደሆነ እናውቃለን። በኢየሱስ ስናምን በቃሉ አማካይነት የስርየትን ወንጌል መረዳትና ኃጢአቶቻችንንም ሁሉ እንዴት እንዳነጻልን በግልጽ ማወቅ ይኖርብናል።
በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ላይ ያሉት ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ግምጃ የሚያመላክቱት ምን እንደሆነ ማወቅ ይኖርብናል። ያን ጊዜ ለዘላለም የሚኖር እውነተኛ እምነት ሊኖረን ይችላል።
 
 
የሰማያዊው፣ የሐምራዊውና የቀዩ ግምጃ መገለጫ በሆነው በኢየሱስ ሳናምን ፈጽሞ ዳግም መወለድ አንችልም
 
ወደ ቅድስቱ ስፍራ ከመግባታቸው በፊት ካህናቱ ምን ያደርጋሉ?
በናሱ የመታጠቢያ ሰን ውስጥ ባለው ውሃ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ይታጠባሉ።
 
ጌታችን ኢየሱስ አዳነን። እንዴት ፍጹም በሆነ መንገድ ጌታ እንዳዳነን ስንመለከት፣ እርሱን ካለማመስገን አንቆጠብም። የተቀደሰውን የመገናኛውን ድንኳን መመልከት ይገባናል። እርሱ በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ግምጃ አማካይነት የስርየትን ወንጌል ቃሎች ሰጠንና በእነርሱም አዳነን። ጌታን እናመሰግናለን፣ እናወድሰዋለንም።
ኃጢአተኞች ወደ ቅድስቱ መግባት አይችሉም። ኃጢአት ያለበት ሰው እንዴት ወደ ቅድስቱ ሊገባ ይችላል? ይህ የማይቻል ነው። እንዲህ ያለው ሰው ቢገባ እዚያው ይሞታል። ይህ በረከት ሳይሆን ኩነኔ ይሆናል። ኃጢአተኛ ቅድስቱ ስፍራ ሊገባም ሆነ በሕይወት መኖርን ሊጠብቅ አይችልም።
ጌታችን በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ውስጥ በተሰወረው ምስጢር በኩል አዳነን። እርሱ በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ግምጃዎች እንደዚሁም በጥሩ በፍታ አዳነን። በእነዚህ ነገሮች አማካይነትም የማዳኑን ምስጢር ነገረን።
እኛ በዚያ መንገድ አልዳንንምን? በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ግምጃ ቃሎች ካላመናችሁ ስርየትን ወንጌል አማካይነት መዳን ሊኖር አይችልም። ሰማያዊው ቀለም እግዚአብሔርን አያመላክትም፣ የሚያመለክተው የኢየሱስን ጥምቀት ነው። ይህም ኃጢአቶቻችንን በሙሉ የወሰደ የኢየሱስ ጥምቀት ነው።
አንድ ሰው በሰማያዊው ግምጃ ሳያምን የሚቃጠለው መሥዋዕት መሠውያ እስካለበት ሥፍራ ድረስ መሄድ ይችላል። ነገር ግን እግዚአብሔር ወደሚኖርበት ቅድስት ሥፍራ መግባት አይችልም።
ስለዚህ በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን በር ውስጥ ከመግባታችን በፊት በሰማያዊው ግምጃ (የኢየሱስ ጥምቀት)፣ በቀዩ ግምጃ (በመስቀሉ ደም) እና በሐምራዊው ግምጃ (ኢየሱስ አምላክና የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ) ማመን ይኖርብናል። ስናምን ብቻ ነው፣ እግዚአብሔር የሚቀበለንና የቅድስተ ቅዱሳኑን መጋረጃ አልፈን እንድንገባ የሚፈቅድልን።
አንዳንዶች ወደ መገናኛው ድንኳን ውጫዊ አደባባይ ገብተው እራሳቸውን ውስጥ እንዳሉ ያስባሉ። ይህ ግን መዳን አይደለም። ለመዳን ምን ያህል ርቀን መሄድ ይኖርብናል? ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት መቻል አለብን።
ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት የናሱን የመታጠቢያ ሰን ማለፍ ይኖርብናል። የናሱ የመታጠቢያ ሰን የኢየሱስን ጥምቀት የሚወክል ሲሆን፣ በዚህ ጥምቀት በየቀኑ የምንሰራቸውን ኃጢአቶች በሙሉ መታጠብና ወደ ቅድስቱ ሥፍራ ለመግባት መቀደስ አለብን።
በብሉይ ኪዳን ካህናት ከመግባታቸው በፊት መታጠብ እንደነበረባቸው፣ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ የሠሩትን በደሎች መታጠቡን ለማሳየት እግሮቻቸውን አጠበ።
የእግዚአብሔር ሕግ እንዲህ ይላል፦ “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው” (ሮሜ 6፡23)። እግዚአብሔር የሰዎችን ኃጢአቶች ያለ ልዩነት ይፈርዳል፣ ነገር ግን እነዚህን ኃጢአቶች ወደ ልጁ አስተላልፎ እርሱ ላይ ፈረደበት። ይህ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ የእርሱ መዳን። እውነተኛ መዳን የሚገኘው የኢየሱስን ጥምቀት፣ ደም፣ ሞት፣ ትንሳኤና የስርየት ወንጌል ስናምን ብቻ ነው።
 
 
አንድ ሰው ዳግም ይወለድ ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን የተጻፈ ቃል፣ ለኃጢአት የማስተስረያ ወንጌልን በጭራሽ ማላገጥ የለበትም
 
እኛ እንድናደርገው የተተወልን ብቸኛው ነገር ምንድነው?
በተጻፉት የእግዚአብሔር ቃሎች ማመን ነው።
 
እኔ በጭራሽ ሌሎችን አላጥላላም። አንድ ሰው እኔ የማላውቀውን አንዳች ነገር ሲናገር እንዲያስተምረኝ እጠይቀዋለሁ። ነገር ግን ስለ ተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን ፍቺ በጠየቅሁ ጊዜ ማንም ሊነግረኝ አልቻለም።
ታዲያ ምን ማድረግ እችል ነበር? ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መመለስ ነበረብኝ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን የተነገረው የት ቦታ ላይ ነው? በዝርዝር የተብራራው በዘጸአት ውስጥ ነው። አንድ ሰው ይህንን መጽሐፍ በጥንቃቄ ቢያነብ በተጻፉት የእግዚአብሔር ቃሎች አማካይነት ትርጉሙን መረዳት ይችላል።
ውድ ወዳጆች፣ በኢየሱስ በዐይን ጨፍን እምነት ቢኖራችሁ እንኳን መዳን አትችሉም። በየጊዜው ቤተክርስቲያን በመሄድም ዳግም ልትወለዱ አትችሉም። ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ ምን እንደነገረው እናውቃለን። “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም… አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን?” (ዮሐንስ 3፡5፣10)
በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች ሁሉ በሰማያዊው ግምጃ (ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ የዓለም ኃጢአቶች በሙሉ ወደ እርሱ ተላልፈዋል)፣ በቀዩ ግምጃ (ለኃጢአቶቻችን ሁሉ የሆነው የኢየሱስ ሞት)፣ እና በሐምራዊው ግምጃ (ኢየሱስ አዳኝ ነው፣ እርሱም አምላክ ነው፣ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው) ማመን አለባቸው።
ኢየሱስ የዓለም ኃጢአተኞች ሁሉ አዳኝ እንደሆነ ማመን ይኖርብናል። ከዚህ እምነት ውጭ ሰው ፈጽሞ ዳግም ሊወለድ አይችልም፣ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ቅዱስ ሥፍራም መግባት አይችልም። ያለዚህ ማንም ሰው በዚህ ዓለም ላይ በታማኝነት መኖር እንኳን አይችልም።
ሰው በኢየሱስ በማመን ብቻ ዳግም መወለድ ቢችል በጣም ቀላል አይሆንም ነበርን? —አዎ።— “♫ድነሃል። ድኛለሁ። ሁላችንም ድነናል።♫” እንዴት ግሩም ነው! ነገር ግን በእውነት ‘ዳግም ሳይወለዱ’ በኢየሱስ የሚያምኑ በጣም ብዙ ሰዎች አሉ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን እውነት ልናውቅና በኢየሱስም ላይ እምነት ሊኖረን ይገባል። ወደተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለመግባትና በእምነት ግዛት ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ለመሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን ኃጢአት ሙሉ በሙሉ የሚነጻበትን የእውነት ወንጌልና የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውንና የቀዩን ግምጃ ትርጉም መረዳት አለብን። በእምነት ድንኳን ውስጥ ወደ መንግሥተ ሰማያት እስክንሄድ ድረስ በደስታ መኖር እንችላለን። በትክክለኛው መንገድ እንዴት በኢየሱስ ማመን እንደሚኖርብን ማወቅ ለእኛ አስፈላጊ ነው።
 
 
እውነተኛው ወንጌል በሰማያዊው ግምጃ ቅድስናን ይወልዳል
 
በመዳን ወንጌል ውስጥ የማይቀር አካል ምንድነው?
የኢየሱስ ጥምቀት
 
አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰው ስህተቶችን ሳይሠራ ፍጹም ሆኖ መኖር እንደሚችሉ ወደ ማሰብ ያዘነብላል። አንድ ነገር ለማድረግ በሚሞክርበት ጊዜ ግን ወዲያውኑ ጉድለቶቹን ይገነዘባል። ሰዎች እጅግ ያልተሟሉ ናቸው፣ እና ኃጢአት አለመሥራት አይቻላቸውም። ሆኖም ኢየሱስ የስርየት ወንጌል በሆነው ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ግምጃ ስላዳነን መቀደስና ወደ እግዚአብሔር ቅዱስ ሥፍራ መግባት እንችላለን።
እግዚአብሔር በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ግምጃ ባያድነን ኖሮ በራሳችን ፈጽሞ ወደ ቅድስቱ ሥፍራ መግባት ባልቻልን ነበር። ለዚህ ምክንያቱ ምንድነው? ወደ ቅድስቱ ሥፍራ መግባት የሚችሉት በሥጋቸው ፍጹማን ሆነው የሚኖሩ ሰዎች ብቻ ቢሆኑ ኖሮ ብቁ የሚሆን ማንም ባልኖረ ነበር። አንድ ሰው እውነተኛውን ወንጌል ሳያውቅ በኢየሱስ ቢያምን የሚጨምረው ነገር በልቡ ላይ ተጨማሪ ኃጢአቶችን መጨመር ብቻ ነው።
ኢየሱስ በጥንቃቄ ባቀደው የሰማያዊው፣ የሐምራዊው፣ የቀዩ ግምጃና ጥሩ በፍታ መዳን አዳነን። እርሱ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ አነጻ። በዚህ ታምናላችሁን? —አዎ።— በልባችሁ ውስጥ ኃጢአት ሙሉ በሙሉ የሚነጻበትን የወንጌል እውነት ይዛችሁ ትመሰክሩታላችሁ? —አዎ።—
‘ቅድስና ለእግዚአብሔር’ የሚለውን ምልክት በግንባራችሁ ላይ ማድረግ የምትችሉትና ‘የንጉሥ ካህና’ (1ኛ ጴጥሮስ 2፡9) ከሆኑት ጋር የምትቀላቀሉት ወንጌልን ስትመሰክሩ ብቻ ነው። በሰዎች ፊት ቆማችሁ ሊቀ ካህን በመሆን የምትሠሩ የእግዚአብሔር ባርያ እንደሆናችሁ ልትነግሩዋቸው የምትችሉት ያን ጊዜ ብቻ ነው።
የሊቀ ካህኑ ጥምጣም የወርቅ ምልክት አለው፣ ምልክቱም በሰማያዊ ፈትል ተያይዞዋል። ለምን ሰማያዊ? ኢየሱስ ኃጢአታችንን ሙሉ በሙሉ በሚያነጻ ወንጌል ስላዳነንና በጥምቀቱ አማካይነትም (በብሉይ ኪዳን እጆችን መጫን፣ በአዲስ ኪዳንም ጥምቀት) ኃጢአቶቻችንን ስለወሰደና ኃጢአት አልባ አደረገን።
ምንም ያህል በትጋትና በታማኝነት በኢየሱስ ብናምንም የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውንና የቀዩን ግምጃ የምስጢር ቃሎች ሳናውቅ ‘ቅድስና ለእግዚአብሔር’ የሚለው ጽሁፍ የተቀረጸበትን ምልክት ማግኘት አንችልም።
ጻድቃን የሆንነው እንዴት ነው? በማቴዎስ 3፡15 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፦ “እንደዚህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና።” ኢየሱስ ተጠመቀና ከዓለም ኃጢአቶች ሁሉ አዳነን። እርሱ በጥምቀቱ አማካይነት ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ወስዶ፣ እኛ ምዕመናኖችም ጻድቃን ሆነናል።
የኢየሱስ ጥምቀት ባይኖር ኖሮ እንዴት ያለ ኃጢአት ነን ማለት እንችል ነበር? በኢየሱስ ብናምንም፣ የኢየሱስን መሰቀል በማሰብ ብናለቅስም፣ በዚህ ዓለም ያሉ ዕንባዎች ሁሉ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ማጥበት አይችሉም። አይ። አይ፣ ምንም ያህል ብናለቅስና ንስሐ ብንገባ፣ ኃጢአቶቻችን በውስጣችን ይቀራሉ።
‘ቅድስና ለእግዚአብሔር።’ እርሱ በጥምቀቱና በደሙ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ስለወሰደ፣ እግዚአብሔር የእኛ የኃጢአተኞችን ኃጢአቶች ሁሉ ወደ ኢየሱስ እንዲተላለፉ ስለፈቀደ፣ የመዳን ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጻፈ፣ ድክመቶቻችን ሁሉ ቢኖሩም በእምነታችን ጻድቃን ሆነናል።
ስለዚህ አሁን በእግዚአብሔር ፊት መቆም እንችላለን። አሁን ጻድቃን ሆነን መኖርና ወንጌልን ለዓለም ሁሉ መስበክ እንችላለን። “♪ድኛለሁ። ድነሃል። ሁላችንም ድነናል።♪” በእግዚአብሔር እቅድ መሠረት ድነናል።
በልባችሁ ውስጥ የስርየት ወንጌል ቃል ከሌለ ምንም ያህል በርትታችሁ ብትሞክሩም መዳን የለም። ይህ ምላሽ ስለማይሰጥ ፍቅር ከሚዘመረው ታዋቂ መዝሙር ጋር ይመሳሰላል። “♫ኦ እርስዋን ባየኋት ጊዜ ሁሉ፤ በቀረብሁዋት ጊዜ ሁሉ፤ ልቤ ያለ ምክንያት በፍጥነት ይደልቃል። ምላሽ በማይሰጥ ፍቅር ውስጥ ያለሁ መሆን አለብኝ።♫” ልቤ በፍጥነት ይደልቃል፣ የእርስዋ ግን አይደልቅም። አሳዛኝ ነገር ሆኖ፣ ፍቅሬ ፈጽሞ ምላሽ አያገኝም።
ሰዎች መዳን በብዙ የተለያዩ መንገዶች ይመጣል ብለው ለማሰብ ያዘነብላሉ። “በጥምቀት ወንጌል አማካይነት ብቻ መምጣት ያለበት ለምንድነው?” በማለትም ይጠይቃሉ። ነገር ግን መዳን በኢየሱስ የጥምቀት ወንጌል በኩል ካልመጣ የተሟላ መዳን አይሆንም። በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን መሆን የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነው፣ ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ ከኃጢአቶቻችን ሁሉ መንጻት የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነውና።
 
 
ኢየሱስ የሰጠን የሰማያዊው ግምጃ መዳን ምንድነው?
 
ጻድቃን ያደረገን ምንድነው?
የሰማያዊው፣ የሐምራዊውና የቀዩ ግምጃ ወንጌል ነው
 
በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ግምጃ ወንጌል አማካይነት የመጣው መዳን እግዚአብሔር ለሰው ዘር ሁሉ የሰጠው ስጦታ ነው። ይህ ስጦታ ወደተቀደሰው የመገናኛ ድንኳን እንድንገባና በሰላም እንድንኖር አስችሎናል። ጻድቃንም አድርጎናል። ጻድቃን አድርጎናል እንዲሁም በቤተክርስቲያን ውስጥ እንድንኖርና በቤተክርስቲያን ውስጥ በቅዱሳት ቃላት እንድንሰለጥን አስችሎናል።
በእግዚአብሔር ፊት ለመጸለይ በምንቀርብበት ጊዜ ሁሉ ወንጌል በእርሱ ፍቅር ይባርከናል። መዳን ለእኛ እንዲህ ክቡር የሆነው ለዚህ ነው። ኢየሱስ ‘በዓለት’ ላይ ቤት እንድንሰራ ነግሮናል። ዓለቱ የኢየሱስ ጥምቀት ነው። ሁላችንም መዳን፣ የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን በጸጋ እንድንኖር፣ ከዚያም ወደ ሰማይ ሄደን ለዘላለም እንድንኖር ነው።
ውድ ወዳጆች፣ ከቤዛነት ወንጌል የተነሣ በእምነት ወደተቀደሰው ድንኳን መግባት እንችላለን። ከኃጢአቶቻችን መንጻት (የኢየሱስ ጥምቀት) እና በመስቀል ላይ ከሆነው ፍርድ የተነሣ በማመን ድነናል።
ለኃጢአቶቻችን ሁሉ የሆነው የትተረፈረፈ ቤዛነት የኢየሱስ ጥምቀትና ደም ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ያነጻ ወንጌል ነው። ይህንን ታምናላችሁን? እውነተኛው ወንጌል ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ፈጽሞ ያነጻ ሰማያዊ የስርየት ወንጌል ነው።
በውሃና በመንፈስ ቅዱስ ወንጌል በማመን ዳግም ተወልደናል። ኢየሱስ በየቀኑ የምንሠራቸውን ኃጢአቶችና የወደፊት ኃጢአቶቻችንንም ሁሉ ሳይቀር ሙሉ በሙሉ ያነጻውን የቤዛነት ወንጌል ሰጥቶናል። ጌታን እናመስግን። ሃሌሉያ! ለጌታ ምስጋና ይሁን።
የውሃውና የመንፈስ ቅዱስ ወንጌል (የውሃውና የደሙ ወንጌል) በኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረና የተሰበከ እውነተኛ ወንጌል ነው። ይህ መጽሐፍ የተጻፈው የውሃውና የመንፈስ ቅዱስ ወንጌል የሆነውን የኢየሱስን ወንጌል ለመግለጥ ነው።
ብዙ ሰዎች ሙሉ እውነትን ሳያውቁ በኢየሱስ ስለሚያምኑ፣ እነሱ አሁንም እስካሁን በክርስቲያን የሥነ መለኮት ዓለም (ፍልስፍናዊ ሥነ መለኮት ተብሎ የሚጠራ) ውስጥ ብቻ እየሠሩ ነው፤ በአጭሩ በመናፍቅነትና በውዥንብር ውስጥ ይኖራሉ። ስለዚህ ወደኋላ ተመልሰን በእውነተኛው ወንጌል ማመን አለብን። ገና በጣም አልረፈደም።
ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም ስለ መወለድ ወንጌል ጥያቄዎች ላሉዋቸው ሰዎች በሁለተኛው መጽሐፍ ላይ ይበልጥ በዝርዝር መግለጽ እፈልጋለሁ።

ይህ ስብከት በየኤሌክትሮኒክ መጽሐፍት ቅርጸት ደግሞ ይገኛል። ከዚህ በታች ባለው የመጽሐፉ ሽፋን ላይ ጠቅ ያድርጉ።
በውኑ በውሃውና በመንፈስ ቅዱስ ዳግም ተወልዳችኋልን? [አዲስ የተሻሻለ እትም]