Search

Sermones

ርዕስ 10፡ ራዕይ (በራዕይ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[11-1] ሁለቱ የወይራ ዛፎችና ሁለቱ ነቢያቶች እነማን ናቸው? ‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 11፡1-19 ››

ሁለቱ የወይራ ዛፎችና ሁለቱ ነቢያቶች እነማን ናቸው?
‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 11፡1-19 ››
‹‹በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፡፡ እንዲህም ተባለልኝ፤ ተነስተህ የእግዚአብሄርን መቅደስ፣ መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ፡፡ በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው፤ አትለካውም፡፡ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል፡፡ ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ፡፡ እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው፡፡ ማንምም ሊጎዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል፤ ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጎዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል፡፡ እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፡፡ ውሃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ፣ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሰፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው፡፡ ምስክራቸውንም ከፈጸሙ በኋላ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ ይዋጋቸዋል፤ ያሸንፋቸዋል፤ ይገድላቸውማል፡፡ በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል፡፡ እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞም ጌታቸው የተሰቀለባት ናት፡፡ ከወገኖችና ከነገዶች፣ ከቋንቋዎችም፣ ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኩል በድናቸውን ይመለከታሉ፡፡ በድናቸውም ወደ መቃብር ሊገባ አይፈቅዱም፡፡ እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስላሰቃዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል፡፡ በደስታም ይኖራሉ፤ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ፡፡ ከሦስቱ ቀን ተኩል በኋላ ከእግዚአብሄር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው፡፡ በእግሮቻቸውም ቆሙ፡፡ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው፡፡ በሰማይም፡- ወደዚህ ውጡ የሚላቸውን ታላቅ ድምጽ ሰሙ፡፡ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ በደመና ወጡ፡፡ በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም አሥረኛው እጅ ወደቀ፡፡ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፡፡ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ፡፡ ሁለተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ ሦስተኛው ወዮ ይመጣል፡፡ ሰባተኛውም መልአክ ነፋ፤ በሰማይም የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሳል የሚሉ ታላላቅ ድምጾች ሆኑ፡፡ በእግዚአብሄርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሄር እየሰገዱ እንዲህ አሉ፡- ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሄር ሆይ ትልቁን ሐይልህን ስለያዝህ፣ ስለነገስህም፣ እናመሰግንሃለን፡፡ አሕዛብም ተቆጡ፤ ቁጣህም መጣ፡፡ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፡፡ ለባርያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ፡፡ በሰማይም ያለው የእግዚአብሄር መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምጽም፣ ነጎድጓድም፣ የምድርም መናወጥ፣ ታላቅም በረዶ ሆነ፡፡›› 
 
 
የራዕይ 11 ቃል እንደ እግዚአብሄር ቃል ሁሉ ለእኛ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ እግዚአብሄር ቃል ሁሉ ለእኛ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ እግዚአብሄር ዓለምን ለማጥፋት አስቀድሞ ሊሰራው የሚያስፈልገው ወሳኝ ሥራ አለ፡፡ ይህም ለመጨረሻ ጊዜ ሕዝበ እስራኤልን መሰብሰብ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለእስራኤሎችና ለአህዛቦች የሚሰራው ሌላም ሥራም ደግሞ አለው፡፡ ይህ ሰማዕት እንዲሆኑ በማድረግ በመጀመሪያው ትንሳኤና ንጥቀት እንዲሳተፉ ማድረግ ነው፡፡ 
 
መጽሐፍ ቅዱስ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ጠቅለል ያለ ታሪክ ስለሚያቀርብልን በሐጢያት ስርየት ላይ የተመሰረተው የእግዚአብሄር ማዳን እንዴት በአዲስ ኪዳን ውስጥ እንደደሚፈጸም ማወቅ ያስፈልገናል፡፡ ቅዱሳት መጻህፍት በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚነግሩንን በቅርበት ካልመረመርናቸው በራዕይ መጽሐፍ እንደተገለጠው ስለ ቅዱሳን፣ ስለ እግዚአብሄር ባሮችና ስለ ሕዝበ እስራኤል ግራ ስለምንጋባ ነው፡፡ 
 
 

ትንታኔ፡፡ 

 
ቁጥር 1፡- በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፡፡ እንዲህም ተባለልኝ፤ ተነስተህ የእግዚአብሄርን መቅደስ፣ መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ፡፡
ይህም እስራኤሎችን በእግዚአብሄር ጸጋ ከሐጢያት የማዳኑ ሥራ አሁን ሊጀምር እንደተወሰነ ይነግረናል፡፡ እዚህ ላይ ‹‹መለካት›› ማለት እግዚአብሄር በመጨረሻው ዘመን ሕዝበ እስራኤልን ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን ራሱ ጣልቃ ይገባል ማለት ነው፡፡
በምዕራፍ 11 ዋና ምንባብ ውስጥ ትኩረታችን ከሐጢያት ወደሚድኑት እስራኤሎች ላይ ማድረግ አለብን፡፡ ይህ ቃል የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለሕዝበ እስራኤል እንደሚሰራጭ በመንገር እስራኤሎችን በኢየሱስ ክርስቶስ በተሰጠው የደህንነት ጸጋ አማካይነት ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ የዳኑ የእግዚአብሄር ሕዝቦች የማድረጉን የእግዚአብሄር ሥራ ጅማሬ እንደሚያመላክት ይነግረናል፡፡ እግዚአብሄር ራዕይ 11ን የጻፈው የሐጢያት ስርየቱን በመጨረሻው ዘመን ለእስራኤሎች ለመስጠትም ጭምር ነው፡፡ በቁጥር 1 እና 2 ላይ ያለው ‹‹መለካት›› ለነገሮች ሁሉ ደረጃን ማስቀመጥ ማለትም ነው፡፡ እግዚአብሄር መቅደሱን የሚለካበት ዓላማው አስቀድሞ እስራኤሎችን ለማዳን በማቀዱ ልባቸው ደህንነታቸውን ለመቀበል ተዘጋጅቶ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ለማወቅ ነው፡፡ ልቦቻቸው ያልተዘጋጁ ከሆኑ ልቦቻቸው የቀኑ ይሆኑ ዘንድ ያዘጋጃቸዋል፡፡
 
ቁጥር 2፡- ‹‹በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው፤ አትለካውም፡፡ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል፡፡››
እግዚአብሄር ሰይጣን አህዛቦችን ለሦስት ዓመት ተኩል እንዲረግጣቸው ሥልጣን ሰጥቶታል፡፡ ስለዚህ አህዛቦች ሁሉ በተቻለ ፍጥነት በሰባቱ ዓመት የታላቁ መከራ ክፍለ ጊዜ በመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመት ተኩል ውስጥ የደህንነት ቃል የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በልባቸው መቀበል አለባቸው፡፡ ታላቁ መከራ ተጋምሶ ሲያልፍና ወደ ሁለተኛው አጋማሽ ክፍለ ጊዜ ሲገባ የዚህ ዓለም ታሪክ ያበቃል፡፡ ወዲያውም ከሐጢያቶቻቸው አስቀድመው የዳኑ አህዛቦች እንዲሁም ቅዱሳን ሁሉ በሰይጣን የሚረገጡበት ጊዜ በጣም በቅርቡ ይመጣል፡፡
ስለዚህ አህዛቦች የመከራው የመጀመሪያው ሦስት ዓመት ተኩል ሳያልፋቸው በፊት የሐጢያቶቻቸውን ስርየት መቀበል አለባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሕዝበ እስራኤልም በመጀመሪያው ሦስት ዓመት ተኩል ወቅት በአስፈሪው መከራ ውስጥ ይሰቃያሉ፡፡ ነገር ግን እነርሱ በዚህ ጊዜ አዳኛቸው ኢየሱስ የመሆኑን እውነትም ይቀበላሉ፡፡ በመጨረሻም ሕዝበ እስራኤል በሦስት ዓመት ተኩሉ ታላቅ መከራ ወቅት ከሐጢያቶቻቸው ይድናሉ፡፡ እግዚአብሄር በታላቁ መከራ ወቅትም ቢሆን ለእስራኤሎች የሐጢያትን ስርየት እንደሚፈቅድላቸው መረዳት አለብን፡፡
 
ቁጥር 3፡- ‹‹ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ፡፡››
እግዚአብሄር ለሕዝበ እስራኤል በተለየ መንገድ ሁለቱን ምስክሮች ባሮቹ አድርጎ ያስነሳል፡፡ እግዚአብሄር ለእስራኤሎች የሚያስነሳላቸው ሁለቱ ነቢያቶች ከጥንት ነቢያቶች በሁለት ዕጥፍ የሚበልጥ ሥልጣን ተሰጥቶዋቸዋል፡፡ በምስክርነታቸው ቃሎች አማካይትም ሕዝበ እስራኤል ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛቸው አድርገው ይቀበሉ ዘንድ በመካከላቸው መስራት ይጀምራል፡፡ በእነዚህ ሁለት ነቢያቶች ሥራዎች አማካይነትም ብዙ እስራኤሎች በትክክል ዳግመኛ የተወለዱ የእግዚአብሄር ሕዝቦች ይሆናሉ፡፡
እግዚአብሄር እስራኤሎችን ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን በመጨረሻው ዘመን በሚልካቸው ሁለት ነቢያቶች ተዓምራቶችንና ድንቆችን በማድረግ በእነዚህ ነቢያቶች የሚመሩትን እስራኤሎች ወደ ክርስቶስ መልሶ እርሱን አዳኛቸው አድርገው እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል፡፡ እነዚህ ሁለት ነቢያቶች በታላቁ መከራ የመጀመሪያ ሦስት ዓመት ተኩል ወቅት ሕዝበ እስራኤልን ለ1,260 ቀናት የእግዚአብሄርን ቃል ይመግቡዋቸዋል፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለእስራኤሎች በመስጠትና ይህንን እንዲያምኑ በማድረግ እግዚአብሄር በአዲስ ኪዳን ዘመን በእምነት አማካይነት አህዛቦችን ከሐጢያቶቻቸው በሙሉ ያዳነበትን ያንኑ ደህንነት ይፈቅድላቸዋል፡፡
 
ቁጥር 4፡- ‹‹እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው፡፡››
እዚህ ላይ ‹‹ሁለቱ የወይራ ዛፎች›› የሚያመላክቱት ሁለቱን የእግዚአብሄር ነቢያቶች ነው፡፡ (ዮሐንስ ራዕይ 11፡10) በሌላ በኩል ‹‹ሁለቱ መቅረዞች›› የሚያመለክቱት እርሱ በአህዛቦች መካከል የመሰረታትን የእግዚአብሄርን ቤተክርስቲያንና ለሕዝበ እስራኤል የፈቀዳትን ቤተክርስቲያን ነው፡፡ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያኑን በአይሁዶችና በእኛ በአህዛቦች መካከል መስርቷል፡፡ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስም ነፍሳቶችን የማዳን ሥራውን ይቀጥላል፡፡
እግዚአብሄር ‹‹በሁለቱ የወይራ ዛፎች›› እና ‹‹በሁለቱ መቅረዞች›› በብሉይ ኪዳን ዘመን እስራኤሎችን ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን ነቢያቶቹን እንዳስነሳና ለእነርሱ በመናገርም በእነዚህ ነቢያቶች በኩል እንደሰራ ሁሉ የዘመኑ ፍጻሜ ሲመጣም ከሕዝበ እስራኤል መካከል ቃሉን የሚሰብኩ ሁለት ነቢያቶችን ያስነሳና እስራኤሎችን በእነዚህ ነቢያቶች አማካይነት ወደ ኢየሱስ ይመራቸዋል፡፡
እስራኤሎች ከአህዛብ የሆኑ የእግዚአብሄር አገልጋዮችን ከልባቸው መቀበል ስለተሳናቸው እነዚህ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ለእነርሱ የሚነግሩዋቸውን አልሰሙም፡፡ እነርሱ ስለ መስዋዕት ሥርዓትና ስለ ብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ሁሉን ነገር ስለሚያውቁ በመጨረሻው ዘመን የሚነሱት የእግዚአብሄር ነቢያቶች ከራሳቸው ከሕዝበ እስራኤል መነሳት ያስፈልጋቸዋል፡፡ እስራኤሎች ቅዱሳት መጻህፍትን በሚገባ ስለሚያውቁ በጥድፊያ ላይ እያሉም ቢሆን ቶራን በሙሉ በሚገባ ማነብነብ ይችላሉ፡፡ ከአሕዛብ የሆኑትን የእግዚአብሄር አገልጋዮች ፈጽሞ መስማት የማይፈልጉት ለዚህ ነው፡፡
ነገር ግን አሁን እናንተና እኔ የምንሰብከውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የሚያደምጡ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ከራሳቸው ሕዝብ ይነሳሉ፡፡ ከራሳቸው ውስጥ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ምዕመናኖች ሲነሱና የእግዚአብሄርን ቃል ለእነርሱ የሚያብራሩና የሚሰብኩ የእግዚአብሄር ድጋፍ ያላቸው ሁለት ነቢያቶች ከእነርሱ ሲነሱ ያን ጊዜ ብቻ እስራኤሎች ወደ ማመን ይመጣሉ፡፡
ሕዝበ እስራኤል እነዚህ ሁለት ምስክሮች በመጨረሻው ዘመን እነርሱን ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን በራሱ በእግዚአብሄር የተላኩና የተነሱ ነቢያቶች መሆናቸውን ያውቃሉ፡፡ እነዚህ ነቢያቶች እስራኤሎች በሚገባ የሚያውቁዋቸውና የሚያምኑባቸው የብሉይ ኪዳን የእግዚአብሄር አገልጋዮች ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ሁሉ ብርቱ ሥልጣናቸውን ይተገብራሉ፡፡ ስለዚህ እስራኤሎች ሁለቱ ምስክሮች በተጨባጭ የሚፈጽሙዋቸውን ሐይለኛ ድንቆች በገዛ ዓይኖቻቸው ያያሉ፡፡ በዚህም ሕዝበ እስራኤል ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሰው በጌታ ያምናሉ፡፡ እኛ እንደምናደርገው ኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሄር ልጅና አዳኝ አድርገው ሲቀበሉ የእኛ ዓይነት ተመሳሳይ እምነት ይኖራቸዋል ማለትም እነርሱም ደግሞ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ይድናሉ፡፡
እነዚህ ሁለት ምስክሮች በሰባቱ ዓመት ታላቅ መከራ ወቅት ለ1,260 ቀናት ለሕዝበ እስራኤል የእግዚአብሄርን ቃል ያብራራሉ፤ ይመግቡዋቸውማል፡፡ የአዲስ ኪዳን ዘመን አሕዛቦች ሆነን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን እንደዳንነው እንደ እናንተና እንደ እኔ እግዚአብሄር በመጨረሻው ዘመን በዚህ የውሃና የመንፈስ ወንጌል በማመን ይድኑ ዘንድ ለእስራኤሎችም ይፈቅድላቸዋል፡፡
ቁጥር 4 ‹‹እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙት ሁለቱ የወይራ ዛፎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው›› ብሎ እንደሚነግረን መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ሁለት ምስክሮች ‹‹ሁለት የወይራ ዛፎች›› ብሎ ይጠራቸዋል፡፡ በቁጥር 10 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡፡ ‹‹እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስላሰቃዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል፡፡ በደስታም ይኖራሉ፤ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ፡፡›› እዚህ ላይ ሁለቱ የወይራ ዛፎች እነማን እንደሆኑ ትኩረት በማድረግ ይህንን ቃል መፍታት አለብን፡፡
በብሉይ ኪዳን ዘመን የቤተመቅደሱን ዕቃዎችና በእግዚአብሄር መቅደስ ውስጥ ያለውን መሠዊያ በዘይት በመቀባት ለመቀደስ የወይራ ዛፎች ጥቅም ላይ ይውሉ ነበር፡፡ ይህ የወይራ ዘይት የመቅደሱን መብራቶች እንደ ማብራት ላሉ ሌሎች አላማዎችም እንደዚሁ ጥቅም ላይ ይውል ነበር፡፡ እነርሱ በመቅደሱ ውስጥ መጠቀም የነበረባቸው ንጹህ ዘይትን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር በመቅደሱ ውስጥ ማንኛውም ዘይት ጥቅም ላይ እንዲውል አልፈቀደም፡፡ ነገር ግን የወይራ ዘይት ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል አዞዋል፡፡ ስለዚህ የወይራ ዛፍና የበለስ ዛፍ የእስራኤልን ሕዝብ እንደሚያመለክቱ ማወቅ ይኖርብናል፡፡
በእነዚህ የወይራ ዛፎችና ሁለት መቅረዞች ላይ ብዙ ትርጓሜዎች ተሰጥተዋል፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች እነርሱ ራሳቸው የወይራ ዛፎች እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ ሁለቱ የወይራ ዛፎች የሚያመለክቱት ግን የተቀቡትን ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሰዎች ነቢይ፣ ንጉሥ ወይም ካህን መሆናቸው ሲጸና ይቀቡ ነበር፡፡ አንድ ሰው እንደዚህ በሚቀባበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ይወርድበታል፡፡ ስለዚህ የወይራው ዛፍ የሚያመለክተው በመንፈስ ቅዱስ የተጸነሰውን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፡፡ (ሮሜ 11፡24) ሰዎች ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ የተሳሳቱ መረዳቶች አሉዋቸው፡፡
የሆኖ ሆኖ በዋናው ምንባብ ላይ ሁለቱ ምስክሮች ሆነው የተጠቀሱት ሁለቱ የወይራ ዛፎች እርሱ እስራኤሎችን ለማዳን በመጨረሻው ዘመን በተለየ ሁኔታ የሚያስነሳቸውን ሁለቱን የእግዚአብሄር አገልጋዮች ያመለክታሉ፡፡
ቁጥር 4 የሚነግረን ይህንን ነው፡፡ እዚህ ላይ ሁለቱ መቅረዞች የሚያመለክቱት በአሕዛቦች መካከል የፈቀዳትን የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያንና ለእስራኤል ሕዝቦች የፈቀዳትን ቤተክርስቲያን ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን እስራኤሎች ከመነሻውም የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ነበራቸው፡፡ ነገር ግን ከአዲስ ኪዳን ዘመን ጀምሮ ይህች የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ፈጽሞ አልነበረቻቸውም፡፡ ለምን? ገና ኢየሱስ ክርስቶስን አላወቁትምና፡፡ በልባቸው ውስጥም መንፈስ ቅዱስ አልነበራቸውም፡፡
የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌልም ሆነ ኢየሱስ ክርስቶስን ስላልተቀበሉ የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን በእነርሱ መካከል አልተገኘችም፡፡ ነገር ግን የዓለም መጨረሻ ፍጻሜ ከመሆኑ በፊት በታላቁ መከራ የመጀመሪያ ሦስት ዓመት ተኩል ወቅት እግዚአብሄር ለእስራኤል ሕዝቦችም የራሱን ቤተክርስቲያን ይፈቅድላቸዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት ምስክሮች ስለሆኑት ሁለቱ የወይራ ዛፎች የሚነግረን ለዚህ ነው፡፡
ጌታ በአይሁዶችና በእኛ በአሕዛቦች መካከል ቤተክርስቲያኑን ይመሰርትና ነፍሳቶችን ከሐጢያት የማዳን ሥራውን ይሰራል፡፡ በእነዚህ ቤተክርስቲያኖች አማካይነትም ጸረ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ይህንን ነፍሳቶችን ከሐጢያት የማዳን መንፈሳዊ ሥራ እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህም እግዚአብሄር በሐጢያት የጠፉትን ነፍሳቶች የማዳን አገልግሎቱን ያገለግሉ ዘንድ የእርሱ ቤተክርስቲያን አባላት የሆኑትን ቅዱሳን ዕቃዎቹ ያደርጋቸዋል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ቀሪ አገልግሎታችንን በትጋት በእምነት መፈጸም አለብን፡፡
 
ቁጥር 5፡- ‹‹ማንምም ሊጎዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል፤ ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጎዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል፡፡››
እግዚአብሄር ይህንን ሥልጣን ለሁለቱ ነቢያቶች የሰጠው ልዩ ተልዕኮዋቸውን መፈጸም እንዲችሉ ነው፡፡ የእስራኤል ሕዝቦች በመጨረሻው ዘመን ንስሐ እንዲገቡና ሰይጣንን እንዲያሸንፉ ለማድረግ እግዚአብሄር ሁለቱን ምስክሮች ለመግደል የሚሞክሩ ሰዎች ሁሉ ራሳቸው እንደሚጎዱና የቃሉ ሥልጣንም ከእነዚህ ከሁለቱ ምስክሮች ጋር አብሮ እንዳለ አሳየን፡፡
ስለዚህ የእስራኤል ሕዝቦች በእነዚህ በሁለቱ ነቢያቶች ትምህርቶች በማመን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለሳሉ፡፡ እግዚአብሄር ሁለቱን የወይራ ዛፎች ማለትም ሁለቱን ምስክሮች ለእስራኤሎች የሚፈቅድላቸው በመጨረሻው ዘመን ከሐጢያቶቻቸው ይድኑ ዘንድ ነው፡፡ 
 
ቁጥር 6፡- ‹‹እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፡፡ ውሃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ፣ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሰፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው፡፡››
እርሱ ለእነርሱ የሚያስነሳላቸው የእግዚአብሄር ባሮች እነዚህን የሥልጣን ተግባራቶች እስካልፈጸሙ ድረስ የእስራኤል ሕዝቦች ንስሐ ስለማይገቡ እግዚአብሄር ሁለቱ ምስክሮች የእርሱን ሥልጣን ተጠቅመው እንዲሰሩ ይፈቅድላቸዋል፡፡ ሁለቱ ነቢያቶች እስራኤሎችን ወደ ኢየሱስ ከመምራታቸውም በላይ የእግዚአብሄርንም ጠላቶች በሥልጣን በማሸነፍ የተጠሩባቸውን ሥራዎቻቸውን ይፈጽማሉ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የቆየው መሲሃቸው መሆኑን በመመስከርና እንዲያምኑ በማድረግ የትንቢቱን ቃል ሁሉ ይሰብኩ ዘንድ እግዚአብሄር ልዩ ሥልጣን ይሰጣቸዋል፡፡
 
ቁጥር 7፡- ‹‹ምስክራቸውንም ከፈጸሙ በኋላ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ ይዋጋቸዋል፤ ያሸንፋቸዋል፤ ይገድላቸውማል፡፡››
ይህ ቃል ጸረ ክርሰቶስ የሰባቱ ዓመት ታላቅ መከራ የመጀመሪያ ሦስት ዓመት ተኩል ሲያልፍ በዚህ ዓለም ላይ እንደሚገለጥ ይነግረናል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን የተጠበቀው መሲህ አድርገው የሚያምኑ ሰዎች በመጨረሻ ከእስራኤል ሕዝብ የሚነሱት በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን ከእነርሱ ብዙዎቹ ጸረ ክርስቶስ ከሆነው አውሬና ከተከታዮቹ እምነታቸውን ለመከላከል ሲሉ ሰማዕት ይሆናሉ፡፡ ሁለቱ የእግዚአብሄር ነቢያቶችም እንደዚሁ የተጠሩባቸውን ሥራዎቻቸውን ከፈጸሙ በኋላ ሰማዕት ይሆናሉ፡፡
እነዚህ ሁለቱ ምስክሮች በጸረ ክርስቶስ መገደላቸው የእግዚአብሄር ፈቃድ ነው፡፡ ለምን? ምክንያቱም እግዚአብሄር ለሰማዕታቶች ያዘጋጀውን ሽልማት ለእነርሱም ሊሰጣቸው ፈልጎዋልና፡፡ ይህ ሽልማት በመጀመሪያው ትንሳኤ መሳተፍ፣ በበጉ ሰርግ እራትም ከጌታ ጋር መገናኘት፣ ለዘላለም መደሰትና የዘላለምን ሕይወት መቀበል ነው፡፡ እግዚአብሄር ይህንን በረከት ለቅዱሳን ሁሉ ለመስጠት ስለ እምነታቸው ሰማዕት እንዲሆኑ ይሻል፡፡ ስለዚህ ቅዱሳን ሁሉ ሰማዕትነትን መሸሽም ሆነ መፍራት የለባቸውም፡፡ ነገር ግን ጽኑ በሆነ እምነት ሊቀበሉትና የተባረከ ሽልማታቸውን ሊያገኙ ይገባቸዋል፡፡
 
ቁጥር 8፡- ‹‹በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል፡፡ እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞም ጌታቸው የተሰቀለባት ናት፡፡››
ይህ ቁጥር ‹‹ሁለቱ ምስክሮች›› በትክክል ከእስራኤል ሕዝብ እንደሚሆኑ ይነግረናል፡፡ እግዚአብሄር ለእስራኤሎች የሚያስነሳቸው ሁለቱ አገልጋዮች ከአሕዛቦች የሚነሱ ሳይሆኑ ከራሳቸው ከእስራኤል ሕዝብ የሚነሱ ናቸው፡፡ ስለዚህ ሁለቱ ምስክሮች ኢየሱስ በተሰቀለበት ተመሳሳይ ቦታ ይገደላሉ፡፡ ይህ እውነታ እነዚህ ሁለት ምስክሮች እስራኤላውያን እንደሆኑ በግልጽ ይነግረናል፡፡ እነርሱ ለእስራኤል ሕዝብ የተላኩ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ናቸው፡፡
በመንፈሳዊ ሁኔታቸው ልክ እንደ ሰዶምና ግብጽ ሕዝብ ለሚመስሉት የእስራኤል ሕዝቦች እግዚአብሄር ሁለቱን ነቢያቶቹን ያስነሳላቸዋል፡፡ ሥልጣንም ይሰጣቸዋል፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ንስሐ ገብቶ በኢየሱስ ያምን ዘንድም ኢየሱስ እስራኤሎች የጠበቁት መሲህ መሆኑን ይመሰክሩላቸዋል፡፡
ጸረ ክርስቶስ ሁለቱን የእግዚአብሄር ባሮች ክርስቶስ በተሰቀለበት በጎልጎታ ስፍራ ይገድላቸዋል፡፡ የጸረ ክርስቶስ ተከታዮች በርኩሳን መናፍስቶች የተያዙ ስለሆኑ በኢየሱስ የሚያምኑትንና ስለ እርሱ የሚመሰክሩትን እነዚህን ሁለት ምስክሮች እስከ ሞት ድረስ ይጠሉዋቸዋል፡፡ ኢየሱስን እንደሰቀሉትና ጎኑን በጦር እንደወጉት ሮማውያን ወታደሮች በርኩሳን መናፍስት የተያዙ ሰዎችም ኢየሱስን ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሄርን ሁለቱን ምስክሮች ይጠላሉ ይገድሉዋቸውማል፡፡
 
ቁጥር 9፡- ‹‹ከወገኖችና ከነገዶች፣ ከቋንቋዎችም፣ ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኩል በድናቸውን ይመለከታሉ፡፡ በድናቸውም ወደ መቃብር ሊገባ አይፈቅዱም፡፡››
ከእስራኤል ሕዝቦች መካከልም ቢሆን ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛቸው አድርገው የማያምኑ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች የሁለቱን ባሮች (ሁለት የወይራ ዛፎች) በድን ሲመለከቱ በአሸናፊነት ስሜታቸው በደስታ ይዋጣሉ፡፡ ይህንን የድል ስሜት ለማጎልበትም ለሰለባዎቻቸው ተገቢ ቀብር እንኳን አያደርጉላቸውም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ‹‹ሁለቱን ምስክሮች›› እንደገና ወደ ሕይወት ሲያመጣቸው ድላቸው ይፈረካከሳል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄርን ይፈሩታል፡፡
ሁለቱን የእግዚአብሄር ባሮች በመግደላቸው እርስ በርሳቸው እንኳን ደስ አለህ ይባባሉ ይሆናል፡፡ ይህ ግን ብዙም አይቆይም፡፡ ወዲያውኑ ጸረ ክርስቶስ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንደማይመጣተን ሲያውቁ ተስፋ መቁረጥና ባዶነት ያጥለቀልቃቸዋል፡፡
እነዚህ ሰዎች በሁለቱ ነቢያቶች የተሰበከውን የእግዚአብሄር የትንቢት ቃል ይጸየፋሉ፡፡ እግዚአብሄር ያስነሳቸውን እነዚህን ሁለት ነቢያቶች በመቃወማቸው ውሎ አድሮ ከመጨረሻው የደህንነት መከር ተቆርጠው ፍጻሜያቸው የሰይጣን ተከታዮች መሆን ይሆናል፡፡
 
ቁጥር 10፡- ‹‹እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስላሰቃዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል፡፡ በደስታም ይኖራሉ፤ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ፡፡››
እነርሱ የእግዚአብሄርን የትንቢት ቃል ስለሚሰብኩ ሁለቱ ምስክሮች ለእስራኤሎች መዳን በመነሳታቸው የሰይጣን ተከታዮች በአያሌው ይታወካሉ፡፡ ስለዚህ ሁሉም በእነዚህ ምስክሮች ሞት ተደስተው እርስ በርሳቸው እንኳን ደስ አለህ ለመባባል ስጦታዎችን ይሰጣጣሉ፡፡
እኛም እንደዚሁ የሚያውቁን ሲጠፉ ደስ እንሰኛለን፡፡ እግዚአብሄር ሁለቱን ምስክሮች አስነስቶ ቃሉን ሲሰብኩ ጸረ ክርስቶስና ተከታዮቹ ይህንን ይጠሉታል፡፡ እነርሱ የእግዚአብሄርን ቃል በሚሰሙበት ጊዜ ሁሉ መንፈሳቸው በጭንቀት ይታወካል፡፡ ሁለቱ ምስክሮች ስለ ኢየሱስ በሚናገሩበት ጊዜ ሁሉ እንዲህ ስለሚሰቃዩ በጸረ ክርስቶስ እንደዚህ ሲገደሉ ሲያዩ ይደሰታሉ፡፡ ስጦታዎችን የሚለዋወጡትና እርስ በርሳቸው እንኳን ደስ አለህ የሚባባሉት ለዚህ ነው፡፡
 
ቁጥር 11፡- ‹‹ከሦስቱ ቀን ተኩል በኋላ ከእግዚአብሄር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው፡፡ በእግሮቻቸውም ቆሙ፡፡ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው፡፡››
ነገር ግን እግዚአብሄር ሁለቱን ምስክሮች በመጀመሪያው ትንሳኤ እንዲሳተፉ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህ ቃል ጌታ በሰጠው የደህንነት ቃል በማመን ከዳኑ በኋላ እምነታቸውን ለመጠበቅ ሰማዕት ለሆኑት ቅዱሳኖች በመጀመሪያው ትንሳኤ ውስጥ ተሳታፊ ለመሆኑ እውነታ ማስረጃ ነው፡፡
‹‹በሦስት ቀን ተኩል›› ውስጥ በእነርሱ ውስጥ የሕይወት እስትንፋስ የገባባቸው መሆኑ እርሱ ራሱ ከሥጋ ሞቱ እንደተነሳ ጌታ በቅርቡ ለእነርሱም ትንሳኤን እንደሚፈቅድላቸው ይነግረናል፡፡ እግዚአብሄር ለቅዱሳን ሁሉ ይህንን የመጀመሪያውን ትንሳኤ እምነት መፍቀዱ ለራሳቸው ለቅዱሳኑም ታላቅ የእግዚአብሄር በረከት ነው፡፡ ለሐጢያተኞች ሁሉ ግን ታላቅ ተስፋ መቁረጥንና ፍርሃትን ያመጣል፡፡ የቅዱሳን የመጀመሪያው ትንሳኤ የእግዚአብሄር ተስፋና ለእምነታቸው የሚሰጠው ሽልማት ነው፡፡
 
ቁጥር 12፡- ‹‹በሰማይም፡- ወደዚህ ውጡ የሚላቸውን ታላቅ ድምጽ ሰሙ፡፡ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ በደመና ወጡ፡፡››
ይህ ቃል የቅዱሳኖችን ሁሉ ትንሳኤና ንጥቀት ይጠቁማል፡፡ የጌታን የትንቢት ቃል አምነው ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ የዳኑ ሰዎች እምነታቸውን ለመጠበቅ ሰማዕት ከመሆን በቀር ሌላ ምርጫ የላቸውም፡፡ ይህ ቁጥር ጌታ እነዚህን ቅዱሳን ሁሉ አስነስቶ እንደሚነጥቃቸው ያሳየናል፡፡ ለእርሱ ባላቸው ታማኝነት ሰማዕት የሆኑ ቅዱሳኖችና የእግዚአብሄር ባሮች በጌታ ባላቸው እምነት የተነሳ ወደ አየር ከፍ በማለት (በመነጠቅ) ይባረካሉ፡፡ እርሱ በሰጠን የሐጢያት ስርየት በማመን ከዳንን በኋላ ትንሳኤያችንንና ንጥቀታችንን ሽልማት አድርጎ ስለሰጠን ጌታን ከማመስገን በቀር ልናደርገው የምንችለው ነገር የለንም፡፡
እግዚአብሄር አብ በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማመን ጸረ ክርስቶስን ለተቃወሙና ሰማዕት ለሆኑ ሁሉ ትንሳኤንና ንጥቀትን ይሰጣቸዋል፡፡ በዚህ እውነት ማመን አለብን፡፡ የቅዱሳን ትንሳኤና ንጥቀት እግዚአብሄር በሰጠው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ባላቸው እምነት አማካይነት ከተገኘው ደህንነታቸው የሚፈስሱ በረከቶች ናቸው፡፡ የዘመን መጨረሻው ሰይጣንና ተከታዮቹ አብዝተው ያሳደዱዋቸውና የገደሉዋቸው ቅዱሳኖች ተነስተው ሲነጠቁ ሲያዩ ጥረቶቻቸው ሁሉ ተንነው ሲጠፉ ያገኛሉ፡፡
እግዚአብሄር ሰማዕት የሆኑትን ቅዱሳን አስነስቶ ይነጥቃቸዋል፡፡ ነገር ግን በዚህ ምድር ላይ ገና የቀሩትን ሰዎች የሰባቱን ጽዋዎች መቅሰፍቶች በማውረድ ያጠፋቸዋል፡፡ ይህ ሥራ በፍጥነት ሲጠናቀቅ ከቅዱሳን ጋር አብሮ ወደዚህ ምድር ይወርድና ጻድቃንን ወደ ክርስቶስ የሰርግ እራት ይጋብዛቸዋል፡፡ ጌታችን ይህ በዓል ለሺህ ዓመት እንዲቆይ ያደርጋል፡፡ ይህ ሺህ ዓመት ሲጠናቀቅ ሰይጣን ለጥቂት ጊዜ ከጥልቁ ጉድጓድ እንዲወጣና እግዚአብሄርንና ቅዱሳኖችን እንዲዋጋ ይፈቀድለታል፡፡ ነገር ግን እርሱ ውሎ አድሮ ሰይጣንንና ተከታዮቹን በማጥፋት ወደ ዘላለም እሳት እንዲጣሉ ይፈቅድላቸዋል፡፡ ሆኖም ጻድቃን ወደ ጌታ መንግሥተ ሰማይ ይገቡና ለዘላለም ከእርሱ ጋር ይኖራሉ፡፡
 
ቁጥር 13፡- ‹‹በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም አሥረኛው እጅ ወደቀ፡፡ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፡፡ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ፡፡››
እግዚአብሄር ለእስራኤሎች ደህንነት ያስነሳቸው ሁለቱ ነቢያቶች ሰማዕት ከሆኑ፣ ከተነሱና ከተነጠቁ በኋላ መላዕክቶቹ የሰባቱን ጽዋዎች መቅሰፍቶች በዚህ ምድር ላይ በነጻነት እንዲያወርዱ ይፈቅድላቸዋል፡፡ ቅዱሳን ከተነጠቁ በኋላ ገናም በምድር ላይ የሚቀሩ ሰዎች እነዚህን የሰባቱን ጽዋዎች መቅሰፍቶች ስጦታ ይቀበላሉ፡፡ እነርሱ በፍርሃት ተይዘው ለእግዚአብሄር ክብርን የሚሰጡት ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ይህ ግን እነርሱን አይጠቅማቸውም፡፡ ምክንያቱም በእግዚአብሄር ፍቅር ውስጥ ያለ የእውነተኛ እምነት ድርጊት አይደለምና፡፡
ይህ ዓለም ሲወድም ጻድቃን ዘላለማዊ ሰማይ፣ ዘላለማዊ ትንሳኤና ዘላለማዊ ባርኮቶች ይኖራቸዋል፡፡ ሐጢያተኞችን የሚጠብቃቸው ግን በሲዖል ያለው የዘላለም እሳት መከራ ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ሰው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የሐጢያቶቹን ስርየት መቀበል ያለበት ለዚህ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ከሐጢያቶቻቸው የዳኑ ሰዎች እግዚአብሄር ቃል በገባላቸው በአዲሱ ዓለም ስለማያምኑ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለሰው ሁሉ ይሰብካሉ፡፡
 
ቁጥር 14፡- ‹‹ሁለተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ ሦስተኛው ወዮ ይመጣል፡፡››
ከእግዚአብሄር የሚመጣው ሦስተኛው ወዮ ድነው ሰማዕት በመሆን በትንሳኤያቸው ተሳታፊ ከሆኑት በስተቀር አሕዛቦችንና እስራኤሎችን ሁሉ ይመለከታል፡፡
መልአኩ ስድስተኛውን መለከት ከነፋበት ጀምሮ ሰባተኛው መለከት ሲነፋ የሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶች እስከሚጀምሩበት ድረስ ያለው ጊዜ ሁለተኛው ወዮ ተብሎ ተጠርቷል፡፡ የሰባቱ መለከቶች መቅሰፍቶች በሦስት ክፍለ ጊዜዎች ማለትም በቀደምት፣ በመካከለኛና በረፋድ ክፍለ ጊዜዎች ተከፋፍለዋል፡፡ የተፈጥሮ መቅሰፍቶችና በጸረ ክርስቶስ የሚሆነው የቅዱሳን ሰማዕትነት በመጀመሪያውና በሁለተኛው ወዮዎች ውስጥ ተካተዋል፡፡ በሌላ በኩል ሦስተኛው ወዮ ዓለምን ሙሉ በሙሉ የሚያጠፉ መለከቶች ናቸው፡፡ ይህ ሦስተኛው ወዮ ገናም በዚህ ምድር ላይ በቀሩት ሐጢያተኞች ላይ የሚወርዱ የእግዚአብሄር ቁጣ ጽዋዎች ናቸው፡፡
 
ቁጥር 15፡- ‹‹ሰባተኛውም መልአክ ነፋ፤ በሰማይም የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሳል የሚሉ ታላላቅ ድምጾች ሆኑ፡፡››
‹‹በሰማይም ታላላቅ ድምጾች ሆኑ›› የሚለው ሐረግ ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ የዳኑ ቅዱሳኖችና ባሮች የሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶች በዚህ ዓለም ላይ መውረድ በሚጀምሩበት ጊዜ ቀድሞውኑም ሰማይ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጊዜ የእግዚአብሄር ሕዝቦች ዳግመኛ በዚህ ዓለም ላይ አይገኙም፡፡ ይህንን መገንዘብ አለብን፡፡ ‹‹የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሳል፡፡››
በዚህ ጊዜ ቅዱሳን ጌታን በሰማይ ያመሰግኑታል፡፡ ነገር ግን የሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶች በሙሉ ከወረዱ በኋላ እነርሱም ከጌታ ጋር አብረው ወደታደሰችው ምድር ይወርዱና በዚህ ዓለም ላይ ለሺህ ዓመት ይነግሣሉ፡፡ ይህንን ተከትሎም ጌታና ቅዱሳን በአዲስ ሰማይና ምድር ውስጥ ለዘላለም ይነግሳሉ፡፡
ጌታችን እኛን ከሐጢያት ለማዳን በእኛ ላይ ንጉሥ ሆኖ በመንገሥ ፋንታ ይህንን ሁሉ ጊዜ ባርያ ሆኖ አገልግሎናል፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ደህንነታችን አድርገን ለምናምንም ልጆቹ የምንሆንበትን ጸጋውን ለግሶናል፡፡ ጌታችን ለእኛ ዘላለማዊ ንጉሥ ስለሆነ የራሱን ሕዝብም ለዘላለም እንዲነግስ ያደርገዋል፡፤ ሐሌሉያ! ጌታ ሆይ ተመስገን!
 
ቁጥር 16፡- ‹‹በእግዚአብሄርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሄር እየሰገዱ::››
እግዚአብሄር ክብርን ሁሉ ሊቀበል የተገባው ነው፡፡ ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ የዳኑ ሰዎች በግምባራቸው ተደፍተው እየሰገዱ እግዚአብሄርን ማመስገናቸው ትክክል ነው፡፡ ሐጢያተኞችን የማዳን እነዚህን ሥራዎች ሁሉ የሰራው ጌታችን ምስጋናንና ስግደትን ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ከቅዱሳንና ከፍጥረታት ሁሉ ሊቀበል የተገባው ነው፡፡
 
ቁጥር 17፡- ‹‹እንዲህ አሉ፡- ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሄር ሆይ ትልቁን ሐይልህን ስለያዝህ፣ ስለነገስህም፣ እናመሰግንሃለን፡፡››
ጌታችን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለዘላለም ከሕዝቡ ጋር ይነግሥ ዘንድ ሰይጣንን አሸንፎ ከእግዚአብሄር አብ ዘንድ ትልቅ ሐይል ይቀበላል፡፡ ስለዚህ ጌታ ለዘላለም ይነግሳል፡፡ ሊመሰገንም የተገባው ነው፡፡ እኔ ክብርን እሰጠዋለሁ፡፡ ምክንያቱም የዓለምን ሐጢያት በሙሉ ያስወገደ፣ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑትን ሁሉ ያዳነና በጠላቶቹ ላይ የፈረደ ጌታ ትልቁን ሐይሉን ሊወስድና ለዘላለም ሊነግሥ የተገባው ነው፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄርን ሉአላዊነት የሚያውቁ ሁሉ እግዚአብሄርን በጌታ ሁሉን ቻይ ሐይልና ፍቅር ለዘላለም በማመስገን ክብር ይሸፈናሉ፡፡ 
 
ቁጥር 18፡- ‹‹አሕዛብም ተቆጡ፤ ቁጣህም መጣ፡፡ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፡፡ ለባርያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ፡፡››
ከሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶች ጋር አብሮ መንፈሳዊ አሕዛቦች ሆነው የቀሩት ሰዎች የሥጋ ጥፋት ይመጣል፡፡ ይህ ቃል ያን ጊዜ እግዚአብሄር የሁሉ ዳኛ ሆኖ እያንዳንዱ ሰው የሚፈርድበት፣ ለባሮቹ ለነቢያት፣ ለቅዱሳንና ስሙን ለሚፈሩት ዋጋ የሚሰጥበት፣ የእርሱን ፈቃድ የሚቃወሙትንና በፈቃዱ ላይ የሚያምጹትን የሚያጠፋበት ጊዜ እንደሚሆን ይነግረናል፡፡ ጌታ የቁጣውን ፍርድ የእርሱን ሉአላዊነት በማያውቁት ላይ ያመጣል፡፡ ነገር ግን ቅዱሳኖች ከእርሱ ጋር እንዲከብሩ ይፈቅድላቸዋል፡፡ ይህ ማለት ጌታ የሁሉም ማለትም የበጎውም የክፉውም ዳኛ ሆኖዋል ማለት ነው፡፡
ጌታ ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ንጉሥ ሆኖ በዙፋኑ ላይ በመቀመጥ ሰውን ሁሉ ሲዳኝ የዓለም ሐጢያተኞችና ጻድቃኖች ሁሉ ተገቢውን ፍርዳቸውን ያገኛሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ጌታ በፍርዱ ውሳኔ መሰረት ለቅዱሳን ሰማይንና የዘላለምን ሕይወት ይሰጣል፡፡ ሐጢያተኞችን ግን ለዘላለም ያጠፋቸዋል፡፡ የሲዖል ቅጣትንም ያከናንባቸዋል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ሉአላዊነትና የህዝቡ የንግሥና በረከት ለዘላለም ይቀጥላሉ፡፡ በዚህ ጊዜ የመጀመሪያው ዓለም ይጠፋል፡፡ የክርስቶስ መንግሥት የሆነው ሁለተኛው ዓለምም እንዲህ ይጀምራል፡፡
 
ቁጥር 19፡- ‹‹በሰማይም ያለው የእግዚአብሄር መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምጽም፣ ነጎድጓድም፣ የምድርም መናወጥ፣ ታላቅም በረዶ ሆነ፡፡››
እግዚአብሄር ለቅዱሳኑ ለጻድቃን በእርሱ መቅደስ ውስጥ የመኖር በረከቱን ይሰጣቸዋል፡፡ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እግዚአብሄር በኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ዘር በሰጠው የእግዚአብሄር ተስፋ ቃል መሰረት ይፈጸማሉ፡፡ የእግዚአብሄር መንግሥት በእግዚአብሄር የትንቢት ቃል ትጀምራለች፡፡ በዚህ ትንቢት ፍጻሜም ትጠናቀቃለች፡፡
ከቅዱሳን ትንሳኤና ንጥቀት ጀምሮ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረው በበጉ ሰርግ እራት ላይና ነገሥታቶች ሆነው ለዘላለም እስከሚነግሱበት በረከት ድረስ ያሉት የእግዚአብሄር ተስፋዎች በሙሉ ለእስራኤል ሕዝብና ለእኛ ለአሕዛቦች ያለ አድልዎ ተሰጥተውናል፡፡ እርሱ በመጨረሻው ዘመን የሚሆነውን የእስራኤሎች ደህንነትና የእኛን ደህንነት በተመሳሳይ መንገድ ይመለከተዋል፡፡ ይህም በዚህ ጊዜ ሁላችንንም ሰማዕት እንድንሆን ያደርገናል፡፡ ተመሳሳይ ትንሳኤና ከዚያ በኋላም ተመሳሳይ ንጥቀት እንድናገኝ ይፈቅድልናል፡፡ ተመሳሳይ ክብርም ይሸፍነናል፡፡ ቃሉ እስራኤሎችና እኛ አህዛቦች በሥጋ የተለያዩ ሰዎች ብንሆንም በመንፈሳዊ ሁኔታ ግን አንድ ዓይነት የእግዚአብሄር ሕዝቦች ነን፡፡
ብዙ ሰዎች ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች የሰባቱ ዓመት ታላቁ መከራ በትክክል ከመጀመሩ በፊት ይነጠቃሉ ብለው ያምናሉ፤ ይናገሩማል፡፡ ነገሩ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ አነጋገር ሰዎች በሰባቱ ዓመት ታላቅ መከራ በመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመታት ተኩል እውነተኛውን ወንጌል መስማታቸውንና መዳናቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ያን ጊዜ ጸረ ክርስቶስ ይገለጣል፡፡ ቅዱሳንም ሰማዕት ይሆናሉ፡፡ ከትንሳኤያቸውና ከንጥቀታቸው በኋላ የክርስቶስ የሆነው የበጉ ሰርግ እራት ይመጣና ቅዱሳን ለሺህ ዓመት ከእርሱ ጋር እንዲነግሱ ይፈቀድላቸዋል፡፡
ቅዱሳን ሰማዕትነታቸው፣ ትንሳኤያቸውና ንጥቀታቸው የሚሆንበትን ትክክለኛ ጊዜ ማወቅ አለባቸው፡፡ ይህንን ጊዜ የማያውቁ ከሆነ ግራ በመጋባት ይቅበዘበዛሉ፡፡ መንፈሳዊ ሞትም ይሞታሉ፡፡
ስለ መጨረሻው ዘመን ትክክለኛ የሆነ የእግዚአብሄር ቸርነት ዕውቀት ያላቸው ሰዎች ትንሳኤያቸውንና ንጥቀታቸውን ተስፋ ስለሚያደርጉ ወንጌልን በትጋት ያገለግላሉ፡፡ በዚህ ምድር ላይ ምንም ተስፋ እንደሌለ የሚያውቁ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ልክ ዳግመኛ እንደተወለዱ ሰዎች ያንኑ ተስፋ ሊያገኙ ይገባቸዋል፡፡ ቅዱሳኖችም በእግዚአብሄር ቃል በማመን ሰማዕት ይሆናሉ፡፡
ዘመናትን ለይቶ የሚያውቅ እምነት በዚህ ዘመን ያለ ልክ ያስፈልጋል፡፡ አስፈሪዎቹ መቅሰፍቶችና መከራዎች በመላው ዓለም ላይ የሚወርዱበትና ጸረ ክርስቶስም የሚገለጥበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፡፡ አሁን ጊዜው ከእንቅልፍ የመነሳት ነው፡፡ እኛ በአብዛኛዎቹ የታላቁ መከራ መከራዎች ውስጥ እንደምናልፍ ማሰብ አለብን፡፡ በክርስቶስ ምጽዓት፣ በትንሳኤያችን፣ በንጥቀታችንና ከክርስቶስ ጋር በበጉ ሰርግ እራት ላይ በመሳተፋችን ማመናችን ወሳኝ ነው፡፡ እኛ ለዚህ ዘመን የሚሆን እጅግ ትክክለኛ እምነት እንዲኖረን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል መርከብ ውስጥ መግባት አለብን፡፡
ይህንን የአሁኑን ዘመን በማወቅ ለዚህ ዘመን እጅግ ፈጥኖ የሚያስፈልገውና በጣም ተገቢ የሆነው እምነት እንዲኖራቸው ተስፋ አደርጋለሁ፤ እጸልያለሁም፡፡