Search

Preguntas Frecuentes sobre la Fe Cristiana

Tema 2 : El Espíritu Santo

2-5. መንፈስ ቅዱስ በዚህ ዘመን የሚሰራው ምንድነው? 

በዚህ ዘመን መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሄር ቃል እውነተኛ አስተምህሮቶችን ከሐሰተኛዎቹ የመለየትን ሥራ በግልጽ ይሰራል፡፡ በዚህ የውዥንብር ዘመን በበደል ምክንያት እየሞቱ ያሉ ነፍሳቶችን ለማዳን ጌታ የሰጠንን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ይሰብካል፡፡ 
ዛሬ በመላው አለም በክርስትና ውስጥ የሚሰሩ ብዙ ሐሰተኛ ነቢያቶች እንዳሉ ማወቅ ይገባናል፡፡ በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያት ቢኖርባቸውም በልሳን በመናገር ሐሰተኛ ድንቆችን በማድረግና ራዕዮችን በማየት አሁንም ስህተት እያደረጉ ነው፡፡ ‹‹አጋዡ›› መንፈስ ቅዱስ በዚህ ዘመን ግራ ለተጋቡት ነፍሳቶች አለምን ስለ ሐጢያት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ ይወቅሳል፡፡ (ዮሐንስ 16፡8) 
በመጀመሪያ የእውነት መንፈስ የሰውን ዘር ሐጢያት ይወቅሳል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት አምላክ በሰጠን የውሃና የመንፈስ ወንጌል አለማመን ነው፡፡ በአጥማቂው ዮሐንስ የኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ደሙ ውብ ወንጌል የማያምኑትን ለሲዖል የተመደቡ ሐጢያተኞች መሆናቸውን በማስጠንቀቅ ይወቅሳቸዋል፡፡ 
እርሱ ለእግዚአብሄር ጽድቅም ይመሰክራል፡፡ እዚህ ላይ የእግዚአብሄር ጽድቅ ትርጉም የአለምን ሐጢያቶች በሙሉ ይቀበል ዘንድ እግዚአብሄር ኢየሱስን በሰው ገጽታ ወደዚህ ዓለም መላኩ ነው፡፡ በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የሐጢያት ይቅርታን እንዲቀበሉ ያግዛቸዋል፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ቢያውቁም እውነተኛውን ወንጌል የማይታዘዙትን ሰዎች በኋላ ለሐጢያቶቻቸው እንደሚፈረድባቸው ደግሞ ያሰጠነቅቃቸዋል፡፡
እግዚአብሄር በመጀመሪያ ይህንን ዓለም በቃሉ በፈጠረ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ጋር ሰራ፡፡ ከዚያም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለማብራት የእውነትን ብርሃን ግራ በተጋቡት የሰው ዘር ልቦች ውስጥ አበራ፡፡ (ዘፍጥረት 1፡2-3) በዚህም መንፈስ ቅዱስ በዚህ ዘመን በሚኖሩት ግራ የተጋቡ ነፍሳቶች በእግዚአብሄር ጽድቅና በሐጢያቶቻቸው ፍርድ ላይ ብርሃኑን ያበራል፡፡