Search

FAQ sur la Foi Chrétienne

Sujet 1: Renaître d'eau et d'Esprit

1-9. እውነተኛው ወንጌል ምንድነው?  

እውነተኛው ወንጌል በእርሱ ስናምንበት ሙሉ በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ከሐጢያቶቻችን ነጻ መውጣት የሚያስችለን ወንጌል ነው፡፡ የእግዚአብሄር ወንጌል ሐይል ልክ እንደ ድማሚት ነው፡፡ 
የእግዚአብሄር ወንጌል ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ የራሱን ዕዳ መክፈል የማይችለውን የባለ ዕዳውን (ሐጢያተኛውን) ዕዳ የከፈለበት›› ነው፡፡ ይህ ወንጌል ‹ድማሚት› ተብሎ የተጠራው እኛ ለሐጢያቶቻችን መሞትና ለኩነኔም ወደ ሲዖል መሄድ ሲገባን የእግዚአብሄር ልጅ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለመደምሰስ የመስዋዕት ቁርባን በመሆኑ ነው፡፡   
እርሱ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በዮርዳኖስ ወንዝ በተቀበለው ጥምቀቱ አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በመውሰድ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለዘላለም አስወገዳቸው፡፡ 
በዮርዳኖስ ወንዝ በተቀበለው ጥምቀቱና በመስቀል ላይ ሞቱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በመውሰድ የሐጢያቶቻችንን ደመወዝ ከፈለ፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በጥምቀቱና በደሙ ልክ እንደ ድማሚት አፈነዳቸው፡፡  
እውነተኛው ወንጌል ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በመጠመቅና በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ማዳኑ ነው፡፡ 
በ1ኛ ዮሐንስ 5፡6 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹በውሃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ በውሃውና በደሙ እንጂ በውሃው ብቻ አይደለም፡፡ መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው፡፡››