Search

FAQ sulla Fede Cristiana

Soggetto 1: Rinasce d'acqua e di Spirito

1-25. በወንጌል ውስጥ የኢየሱስን ጥምቀት የደህንነት ግዴታ አድርጎ መረዳት በመስቀል ላይ የሆነውን የእርሱን ሞት ከንቱ የሚያደርገው አይመስልህምን? 

የኢየሱስ ጥምቀትና የመስቀል ላይ ሞቱ በእኩል ደረጃ ለደህንነታችን አስፈላጊ ናቸው፡፡ አንዱ ከሌላው ይበልጥ አስፈላጊ ነው ማለት አንችልም፡፡ ነገር ግን ችግሩ ዛሬ ብዙዎቹ ክርስቲያኖች የሚያውቁት ኢየሱስ በመስቀል ላይ ያፈሰሰውን ደሙን ብቻ መሆኑ ነው፡፡ እነርሱ ይቅርታን ያገኙት እርሱ በመስቀል ላይ ስለሞተ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች የወሰደው በመስቀል ላይ ብቻ አይደለም፡፡ እርሱ በአጥማቂው ዮሐንስ ስለተጠመቀና የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በጀርባው ስለተሸከመ የመስቀል ላይ ሞቱ በተግባር የከፈለው የሐጢያቶቻችን ሁሉ ፍርድ ነው፡፡    
ያለ ኢየሱስ ጥምቀት በመስቀሉ ብቻ ማመን እጆችን በላዩ ላይ ሳይጭኑ ለጌታ መስዋዕትን እንደ ማቅረብ ነው፡፡ እንዲህ አይነት መስዋዕቶችን ያቀረቡ ሰዎች ከሐጢያቶቻቸው መዳን አይችሉም፡፡ ምክንያቱም መስዋዕቱ እግዚአብሄር አምላክ ሊቀበለው የማይችለው ሕገወጥ መስዋዕት ነው፡፡ እግዚአብሄር ከመገናኛው ድንኳን ሆኖ ሙሴን በመጥራት እንዲህ ሲል ተናገረው፡- ‹‹መባውም የሚቃጠል መስዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን ነውር የሌለበትን ተባዕቱን ያቀርባል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት እንዲሰምር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል፡፤ እጁንም በሚቃጠለው መስዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፡፡ ያሰተሰርይለትም ዘንድ የሰመረ ይሆንለታል፡፡›› (ዘሌዋውያን 1፡3-4)      
ጌታ ጻድቅና ሕጋዊ ነው፡፡ ሐጢያቶቻችንን ለማስወገድም ተገቢና ቀና የሆነ የመስዋዕት ስርዓትን ደንግጎዋል፡፡ ሕጋዊ መስዋዕት ስናቀርብ መስዋዕቱ ለእኛ ስርየትን ያመጣልን ዘንድ በጌታ ተቀባይነት ያገኛል፡፡ ያለ እጆች መጫን ምንም መስዋዕት በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ልክ እንደዚሁ በእርሱ ላይ ካለን እምነት የተነሳ የኢየሱስን ጥምቀት ብንገድፍ በዚህ አይነቱ እምነት የሐጢያቶቻችንን ስርየት መቀበል አንችልም፡፡    
የዘመኑ ክርስቲያኖች ከሚያምኑባቸው እጅግ የተለመዱ ውሸቶች አንዱ ጌታ ፍቅር ስለሆነ ኢየሱስን አዳኛቸው አድርገው በመመስከር ብቻ መዳን የሚችሉ መሆናቸው ነው፡፡ በእርግጥም መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 2፡21፤ ሮሜ 10፡13) ደግሞም እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡›› (ማቴዎስ 7፡21)   
ኢየሱስ አዳኛችን እንደሆነ ለመመስከር እግዚአብሄር የደነገገውን የደህንነት ሕግ ማወቅ ይገባናል፡፡ በኢየሱስ በማመን ብቻ መዳን የምንችል ብንሆን ኖሮ ቅዱሳት መጽሐፍት ስለ ብሉይ ኪዳን የመስዋዕት ስርዓትና በማቴዎስ 7፡21 ላይም ዓመጻን ስለሚያደርጉ ሰዎች የሚጽፉበት ምንም ምክንያት ባልኖራቸውም ነበር፡፡  
ነገር ግን አስገራሚና ፍጹም የሆነው የጌታ የደህንነት መንገድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ተመዝግቦዋል፡፡ በእርግጥም አንድ ሐጢያተኛ የሐጢያትና የደህንነት መስዋዕቶችን ሲያቀርብ ሐጢያቶቹን በራሱ ላይ ለማስተላለፍ እጆቹን በመስዋዕቱ ራስ ላይ መጫን፣ ማረድና ደሙን መርጨት አንደነበረበት ከዘሌዋውያን ምዕራፍ 3 እና 4 በግልጽ ማየት እንችላለን፡፡ ያለ እጆች መጫን መስዋዕትን ማቅረብ ወይም ነውር ያለበትን መስዋዕት ማቅረብ ስርየትን የማያስገኝ በጣም ሕገወጥ ነው፡፡  
የብሉይና የአዲስ ኪዳናት ቃሎች እርስ በርሳቸው የሚጣጣሙ አምሳያዎች አሉዋቸው፡፡ (ኢሳይያስ 34፡16) ኢየሱስ በዮርዳኖስ የተቀበለው ጥምቀት በብሉይ ኪዳን ሐጢያተኛ ለሐጢያት በሚቀርበው መስዋዕት ራስ ላይ ከሚጭናቸው እጆቹ ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ኢየሱስ በዮርዳኖስ በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ እንዲህ አለ፡- ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና፡፡›› (ማቴዎስ 3፡15)    
እዚህ ላይ ‹‹ጽድቅን ሁሉ›› ማለት ‹‹ፍትህና ትክክለኛነት›› ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ኢየሱስ በዚያ ዘዴ ለሰው ዘር ሐጢያት መስዋዕት መሆኑ ተገቢ ነው ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳን በመሰረተውና በእጆች መጫንና ደም በተዋቀረው የመስዋዕት ስርዓት መሰረት የዓለምን ሐጢያቶች እጅግ ትክክለኛ በሆነ መንገድ በእጆች መጫን መልክ በአጥማቂው ዮሐንስ መጠመቁ ለእርሱ ተገቢ ነው፡፡   
በመስቀሉ ብቻ ማመን ማለት የእርሱ ጥምቀት ከሐጢያቶቻችን ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ሐጢያቶቻችን ያለ ኢየሱስ ጥምቀት ፈጽመው ወደ እርሱ መተላለፍ አይችሉም ነበርና፡፡ የዚህ ውጤቱም የእርሱን ደም እንደ ርኩስ ነገርና ማንጻት እንደማይችል መቁጠር ነው፡፡ (ዕብራውያን 10፡29)  
ስለዚህ የእርሱ ደም በምዕመናን ልብ ውስጥ ያሉትን ሐጢያቶች በትክክል ለማንጻት ብቃት የሚኖረው አጥማቂው ዮሐንስ በእጆች መጫን አማካይነት እርሱን ባጠመቀው ጊዜ ሐጢያቶቻቸው በሙሉ በእርሱ ላይ እንደተጫኑ ሲያምኑ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ዮሐንስ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነና በውሃውና በመንፈሱ የሚያምን ሰው ዓለምን እንደሚያሸንፍ መስክሮዋል፡፡ ኢየሱስ የመጣው በውሃና በደም እንጂ በውሃ ወይም በደም ብቻ አይደለም፡፡ (1ኛ ዮሐንስ 5፡4-6)  
ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ እርሱን የሚመለከቱትን ነገሮች ሁሉ ለደቀ መዛሙርቱ አብራርቷል፡፡ እርሱ ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለው የሐጢያት መስዋዕት ራሱ እንደነበር አሳየ፡፡ ዳዊት ስለ እርሱ በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ እንዲህ አለ፡- ‹‹እኔ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፡፡ አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፡፡›› (መዝሙረ ዳዊት 40፡7፤ ዕብራውያን 10፡7) 
ከዚህ የተነሳ የእርሱ ጥምቀት መስቀሉን ከንቱ አላደረገውም፡፡ ነገር ግን የመስቀሉን ትርጉም የሚያጠናቅቅና የሚፈጽም የጌታ ወንጌል አስፈላጊ ክፍል ነው፡፡ ይህ የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትና ክቡር ደም እስከሌለ ድረስ ቤዛነት ልናገኝ እንደማንችል ያስተምረናል፡፡ መዳን ስትል በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በማመን የሐጢያቶችን ስርየት ማግኘትና የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ መቀበል ማለትህ ነው፡፡ (1ኛ ዮሐንስ 5፡8፤ የሐዋርያት ሥራ 2፡38)