Search

FAQ sulla Fede Cristiana

Soggetto 1: Rinasce d'acqua e di Spirito

1-31. እግዚአብሔር ቸር እና ርህሩህ ስለሆነ በልባችን ውስጥ ኃጢአት ቢኖርብንም በኢየሱስ ብናምን ብቻ ጻድቅ አድርጎ አይቆጥረንምን?

እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ ጻድቅም ደግሞ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ምንም ቢሆን ኃጢአትን በቅንነት ይፈርዳል። “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና” (ሮሜ 6፡23)። ይህ ማለት አንድ ኃጢአተኛ ከተፈረደበት በኋላ ለሲዖል የታጨ ነው ማለት ነው። እርሱ ብርሃንን ከጨለማ እንደለየ ጻድቃንን ከኃጢአተኞች ይለያል። እግዚአብሔር ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ በሞቱ አማካይነት ኃጢአቶቻቸውን ሁሉ እንዳጠበ በማመን ኃጢአት የሌለባቸውን ሰዎች ጻድቃን ብሎ ይቆጥራቸዋል።
ሆኖም በኢየሱስ ጥምቀት ባለማመን አሁንም ድረስ በውስጣቸው ኃጢአት ያለባቸው ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአተኞች ናቸው። እነርሱ በኖህ ዘመን የነበሩት ሰዎች እንዳደረጉት በውሃው፣ ማለትም በኢየሱስ ጥምቀት የማያምኑ ሰዎች ናቸው። እግዚአብሔር አሁንም ድረስ ኃጢአት ያለባቸውን ኃጢአተኞች ጻድቃንና ኃጢአት አልባ አድርጎ የሚያያቸው ከሆነ እየዋሸ መሆን አለበት፣ ስለዚህም ፍጥረቶቹን ሁሉ መፍረድ ወይም መግዛት አይችልም።
እርሱ እንዲህ አለ፦ “እኔ ኃጢአተኛውን አላጸድቅምና” (ዘጸአት 23፡7)። ኃጢአተኞች እግዚአብሔር እኛን እጅግ ቀናና ተገቢ በሆነ መንገድ ከኃጢአቶቻችን ሁሉ ያዳነበትን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ትተው የሰዎችን ትውፊቶች የሚከተሉና የሚደግፉ ሰዎች ናቸው። ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ስለ ኃጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው” (ዮሐንስ 16፡9)። አሁን በዚህ ምድር ላይ የቀረው ኃጢአት ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀሉ አማካይነት ኃጢአቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደና አዳኛችን እንደሆነ እውነቱን አለማመን ነው። ይህ ፈጽሞ ማስተስረያ የማይገኝለት መንፈስ ቅዱስን የመሳደብ ኃጢአት ነው። መንፈስ ቅዱስን የሚሳደቡ ሰዎች የሚድኑበት ፈጽሞ ሌላ መንገድ የለም፣ ምክንያቱም ኢየሱስ ኃጢአቶቻቸውን በሙሉ እንዳጠበላቸው አያምኑምና።
ሐዋርያው ዮሐንስ እንዲህ አለ፦ “ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን ደግሞ ያደርጋል፥ ኃጢአትም ዓመፅ ነው። እርሱም ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም። በእርሱ የሚኖር ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም። ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ አላየውም አላወቀውምም” (1ኛ ዮሐንስ 3፡4-6)። ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀሉ አማካይነት ኃጢአቶቻችንን በሙሉ የመውሰዱን እውነት አለማመን ዓመፅ ነው። እርሱ እንዲህ ያለውን ዓመፅ የሚያደርጉ ሰዎችን በመጨረሻው ቀን ይጥላቸዋል።
በእርሱ የሚኖሩ ሰዎች ኃጢአት የለባቸውም፣ በእርሱ ውስጥ በመጠመቅም ከኢየሱስ ጋር አንድ ሆነዋል። በኢየሱስ ጥምቀት ላይ ባላቸው እምነት አማካይነት የሕይወታቸውን ኃጢአቶች በሙሉ በእርሱ ላይ ያኖሩ ሰዎች፣ አሁንም ድረስ ከሥጋቸው ድክመቶች የተነሣ ኃጢአት ቢሠሩም፣ ኃጢአት የለባቸውም።
እግዚአብሔር ኃጢአቶቻቸውን ወደ ኢየሱስ ያስተላለፉትንና በሕይወት መንፈስ ሕግ የተቀደሱትን ሰዎች ጻድቃን ብሎ ያውጃል። እርሱ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ይሰጣቸዋል። መንፈስ ቅዱስ በልባቸው ውስጥ ኃጢአት ባለባቸው ሰዎች ላይ ፈጽሞ አይመጣም። ዳዊት በመዝሙረ ዳዊት ላይ እንዲህ ብሎዋል፦ “አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፥ ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም” (መዝሙረ ዳዊት 5፡4)። የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ በውስጣቸው ኃጢአት ባለባቸው ሰዎች ልብ ውስጥ ፈጽሞ አይኖርም። በውስጡ መንፈስ ቅዱስ የሌለበት ኃጢአተኛ እንኳን በሐይማኖት ትምህርቶችና በራሱ አስተሳሰቦች ላይ ተመርኩዞ ከኃጢአት እንደዳነ ይናገር ይሆናል። ነገር ግን ሰው ሕሊናው ስለሚወቅሰው በእምነት በልቡ ኃጢአት የለኝም፣ ጻድቅ ነኝ ማለት በጭራሽ አይችልም።
ስለዚህ ይህ ሰው በሌሎች ሰዎች ፊት ኃጢአተኛ እንደሆነ ይናገራል፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥም ጻድቅ ሰው እንደሆነ ያስባል።

እግዚአብሔር ግን ኃጢአተኛውን ፈጽሞ ጻድቅ ብሎ አይቆጥረውም። ኃጢአተኛ ለእግዚአብሔር ፍርድ የተመደበ ነው፣ እንዲድንም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን አለበት።