Search

FAQ sulla Fede Cristiana

Soggetto 2: Lo Spirito Santo

2-7. የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት በሐጢያት ይቅርታ አማካይነት ከሐጢያቶቻቸው ስለዳኑ ነው ወይስ ይህ የሐጢያት ይቅርታን በማይመለከት ሁኔታ የተነጠለ ልምምድ ነበር? 

መንፈስ ቅዱስ ከቤዛነት የተነጠለ ልምምድ አይደለም፡፡ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መንፈስ ቅዱስን ከመቀበላቸው በፊት እንኳን ኢየሱስ በዮሐንስ ጥምቀት አማካይነት የአለምን ሐጢያቶች በሙሉ መውሰዱን ቀደሞውኑም አውቀውና አምነው እንደነበር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማየት እንችላለን፡፡ (1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 ‹‹ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፡፡››) 
የሐጢያት ይቅርታ ማለት ከሐጢያት መዳን ማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ይህ ማለት በልቦቻችን ውስጥ ያሉት ሐጢያቶች በሙሉ ነጽተው ተወግደዋል ማለት ነው፡፡ ዛሬ ብዙ ክርስቲያኖች ኢየሱስ ስለሰጠን የሐጢያት ይቅርታ ትርጉም አብዛኛውን ጊዜ ግራ ይጋባሉ፡፡ ሰዎች እንዴት የሐጢያት ይቅርታን መቀበል እንደሚችሉ አያውቁም፡፡ ኢየሱስን ጌታቸው አድርገው ስለሚያምኑ ብቻ እንደዳኑ ያስባሉ፡፡
የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ የተቀበሉ ሰዎች በራሳቸው ውስጥ ምስክር አላቸው፡፡ ሆኖም አንድ ሰው የቤዛነቱ ምስክር ቃል ከሌለው መንፈስ ቅዱስን አልተቀበለም፤ ከሐጢያቶቹም ሁሉ ይቅርታን አላገኘም፡፡ በመንፈስ የተሞሉ ስሜቶች ካሉትም ያ በገዛ ራሱ ስሜቶች እየተታለለ የመሆኑ ውጤት ብቻ ነው፡፡ ሰይጣን ራሱን ወደ ብርሃን መልአክ ይለውጥና (2ኛ ቆሮንቶስ 11፡14-15፤ ገላትያ 1፡7-9) ከእውነት እንዲርቅ ያታልለዋል፡፡ (ማቴዎስ 7፡21-23) 
የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ያገኙ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ስለሚያምኑ በውስጣቸው ምስክር አላቸው፡፡ በ1ኛ ዮሐንስ 5፡4-12 ላይ በውሃና በደም ለመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንድ ሰው ስለ ልዩ መንፈስ ወይም ልዩ ወንጌል የሚሰብክ ከሆነ (2ኛ ቆሮንቶስ 11፡4) እርሱ የሐጢያት ስርየትንም ሆነ መንፈስ ቅዱስን እንዳልተቀበለ ይናገራል፡፡ ሰዎች የሐጢያት ይቅርታን መቀበል የሚችሉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ በሚያምኑበት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ የሐጢያት ይቅርታ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል ወሳኝ ነው፡፡