Search

FAQ sulla Fede Cristiana

Soggetto 4: FAQ dai Lettori dei nostri Libri

4-7. አንተ እኔ ከዚህ ቀደም በጭራሽ ያልሰማሁትን ‹‹የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል›› የሚል ለየት ያለ የቃላት አገላለጥ ትጠቀማለህ፡፡ ‹‹የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል›› የሚለወ ሐረግ የመጣው ከየት ነው?

የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል›› የሚለው ሐረግ መነሻው ዮሐንስ 3፡3-5 እና 1ኛ ዮሐንስ 5፡4-8 ናቸው፡፡
ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ ‹‹እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡›› (ዮሐንስ 3፡5) ስለዚህ ቃሉን ‹‹አማኞቹ ዳግመኛ እንዲወለዱና ወደ እግዚአብሄር መንግሥት እንዲገቡ የሚያደርጋቸው ብቸኛውና እውነተኛ ወንጌል›› በማለት ልንተነትነው እንችላለን፡፡
በመጀመሪያ በተለይም ቅጽ 1 እና 2 ተከታታይ የክርስቲያን መጽሐፋችንን አንድታነብ እጋብዝሃለሁ፡፡ በመጽሐፎቹ አማካይነት ይህንን በሚመለከት ግልጽና ተጨባጭ መረዳት እንደሚኖርህ እርግጠኛ ነኝ፡፡ መጽሐፎቹን ፈጽሞ በነጻ ማግኘት ትችላለህ፡፡ ከታች ያለውን ድረ ገጻችንን ተመልከትና ማንበብ የምትፈልጋቸውን መጽሐፎቻችንን ጠይቅ፡፡