Search

説教集

ርዕስ 1፡ ሐጢያት

[1-2] ሰዎች ኃጢአተኞች ሆነው የተወለዱ ናቸው (ማርቆስ 7፡20-23)

ሰዎች ኃጢአተኞች ሆነው የተወለዱ ናቸው (ማርቆስ 7፡20-23)
 
(ማርቆስ 7፡20-23)
“እርሱም አለ፦ ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው። ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፦ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና። ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል።”
 
 

ሰዎች ግራ ተጋብተው በራሳቸው ምናቦች ውስጥ ይኖራሉ

 
ይበልጥ የመዳን ዕድል ማን ነው?
ራሱን የዓለም የከፋ ኃጢአተኛ እንደሆነ አድርጎ የሚያስብ ሰው ነው
 
ከመቀጠሌ በፊት አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ እወዳለሁ። ስለ ራሳችሁ ምን ታስባላችሁ? መልካሙ ወይም ክፉውን እንደሆናችሁ ታስባላችሁን? ምን ታስባላችሁ?
ሰዎች ሁሉ የሚኖሩት በራሳቸው ምናቦች ውስጥ ነው። እናንተ ምናልባት እንደምታስቡት ክፉ አትሆኑም፣ እንዲሁም እንደምታስቡት መልካምም አትሆኑም።
የተሻለ የእምነት ሕይወትን የሚመራ ማን ይመስላችኋል? እራሳቸውን እንደ መልካሙንና አድርገው የሚቆጥሩ ወይስ ራሳቸውን እንደ ክፉውን አድርገው የሚቆጥሩት?
የኋለኞቹ፣ ማለትም ራሳቸውን ክፉ አድርገው የሚቆጥሩት ናቸው። ስለዚህ ይበልጥ የመዳን ዕድል ያለው ማነው፦ ብዙ ኃጢአቶችን የሠሩ ሰዎች ወይስ ጥቂት ኃጢአቶችን ብቻ የሠሩ ሰዎች? ብዙ ኃጢያት ያለባቸው ሰዎች ራሳቸውን ኃጢአተኞች እንደሆኑ ስለሚያውቁ ለመቤዠት ዕድላቸው ሰፊ ነው። እነርሱ ኢየሱስ ያዘጋጀላቸውን የቤዛነት ቃል በተሻለ መንገድ መቀበል ይችላሉ።
ራሳችንን በትክክል ስንመለከት የኃጢአት ጅምላ ብቻ እንደሆንን ማየት እንችላለን። ሰዎች ምንድናቸው? የሰው ዘር ‘የክፉዎች ዘር’ ብቻ ነው። በኢሳይያስ 59 ላይ በሰዎች ልብ ውስጥ ሁሉም አይነት በደሎች እንዳሉ ይናገራል። ስለዚህ የሰው ልጅ የኃጢአት ጅምላ ነው። ነገር ግን፣ የሰውን ልጅ የኃጢአት ጅምላ ብለን ከገለፅን ብዙዎች አይስማሙም። ግን ሰውን እንደ ‘የክፉዎች ዘር’ መግለጽ ትክክለኛው ፍቺ ነው። ራሳችንን በቅንነት ከተመለከትን ክፉ መሆናችንን ወደ መደምደሚያው እንደርሳለን። ለራሳቸው እውነተኞች የሆኑ ሰዎች ወደዚህ ተመሳሳይ ድምዳሜ ላይ መድረስ አለባቸው።
በእርግጥም የኃጢአት ጅምላ መሆናቸውን የሚቀበሉ ብዙዎች ያሉ አይመስሉም። ብዙዎች ራሳቸውን ኃጢአተኛ አድርገው ስለማይቆጥሩ ተመችቶዋቸው ይኖራሉ። ክፉ አድራጊዎች ስለሆንን ኃጢአተኛ ሥልጣኔን ፈጥረናል። ብዙ ሰዎች ኃጢአታቸውን የሚያውቁ ቢኖሩ ኖሮ ኃጢአት ለመሥራት በጣም ያፍሩ ነበር። ሆኖም ብዙዎች ኃጢአተኝነታቸውን ስለማያውቁ በኃጢአታቸው አያፍሩም።
ሕሊናዎቻቸው ግን ያውቃሉ። እያንዳንዱ ሰው “ይህ አሳፋሪ ነው” ብሎ የሚነግረው ሕሊና አለው። አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከሠሩ በኋላ በዛፎች መካከል ተሸሸጉ። ዛሬ፣ ብዙ ኃጢአተኞች ራሳቸውን ከክፉ ባህላችን ጀርባ ይደብቃሉ — የኃጢአት ባህላችን። እነርሱ የእግዚአብሔርን ፍርድ ለመሸሽ አብረዋቸው ባሉ ኃጢአተኞች መካከል ይደብቃሉ።
ሰዎች በራሳቸው ቅዠት የተታለሉ ናቸው። ከሌሎች ይልቅ በጣም ቅዱስ እንደሆኑ አድርገው ራሳቸውን ያስባሉ። በቁጣ በማለት ይጮሃሉ፣ “ሰው እንዴት እንዲህ ያሉ ነገሮችን ሊያደርግ ይችላል? አማኝ እንዴት እንዲህ ማድረግ ይችላል? ልጅ በገዛ ወላጆቹ ላይ እንዴት ያንን ሊያደርግ ይችላል?” እነርሱ ራሳቸው እነዚህን ነገሮች እንደማያደርጉ ያስባሉ።
የተወደዳችሁ ወዳጆች የሰውን ተፈጥሮ ማወቅ በጣም አዳጋች ነው። በእውነት ለመዳን ከፈለግን፣ በመጀመሪያ የራሳችንን ኃጢአተኛ ተፈጥሮ ምን እንደሆነ ማወቅ አለብን። ይህ ጊዜ የሚወስድ ሒደት ነው፣ እና እኛ እስከ ዕለተ ሞታችን ድረስ ይህንን ፈጽሞ የማናውቅ በጣም ብዙ ነን።
 
 
ራሳችሁን እወቁ
 
ራሳቸውን የማያውቁ ሰዎች የሚኖሩት እንዴት ነው?
የሚኖሩት ኃጢአተኛነታቸውን ለመደበቅ በመሞከር ይኖራሉ።
 
አንዳንድ ጊዜ ራሳቸውን በትክክል የማያውቁ ሰዎች ያጋጥሙናል። ሶቅራጥስ “ራሳችሁን እወቁ” አለ። ነገር ግን ብዙዎቻችን በልባችን ውስጥ ምን እንዳለ አናውቅም፦ መግደል፣ መስረቅ፣ መጐምጀት፣ ክፋት፣ ተንኰል፣ ዝሙት፣ ምቀኝነት፣ ወ.ዘ.ተ።
በልቡ የእባብ መርዝ አለ ነገር ግን ስለ መልካምነት ይናገራል። ለዚህ ምክንያቱ ሰውየው ኃጢአተኛ ሆኖ መወለዱን ስለማያውቅ ነው።
በዚህ ዓለም ውስጥ ራሳቸውን እንዴት ማየት እንዳለባቸው የማያውቁ በጣም ብዙ ናቸው። ራሳቸውን አታለዋል እናም ህይወታቸውን በራሳቸው ማታለያ ተጠቅልለው ይኖራሉ። ራሳቸውን ወደ ገሃነም ይጥላሉ። በራሳቸው ማታለያ ምክንያት ወደ ገሃነም ይሄዳሉ።
 
 

ሰዎች በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ያለ ማቋረጥ ኃጢአትን ያንጠባጥባሉ

 
እነርሱ ገሃነመ የሚገቡት ለምንድነው?
ራሳቸውን ስለማያውቁ ነው።
 
ማርቆስ 7፡21-23ን እንመልከት። “ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፦ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና። ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል።” የሰዎች ልቦች ከተጸነሱበት ዕለት አንስቶ በክፉ አሳቦች የተሞሉ ናቸው።
የሰው ልብ ከብርጭቆ የተሠራና እስከ አፍ ገደፉ ድረስ በቆሻሻ ፈሳሽ ማለትም በኃጢአቶቻችን የተሞላ ነው ብለን እናስብ። ይህ ሰው ወደኋላና ወደፊት ሲንቀሳቀስ ምን ይፈጠራል? በእርግጥ፣ ቆሻሻው ፈሳሽ (ኃጢአት) ያለማቋረጥ በሁሉም አቅጣጫ እንደሚፈስ እርግጥ ነው። ወደዚህም ወደዚያም ሲዘዋወር፣ ኃጢአት ደጋግሞ ይፈሳል።
እኛ፣ የኃጢያት ጅምላች የሆንን፣ ሕይወታችንን እንዲሁ እንኖራለን። በየሄድንበት ሁሉ ኃጢአትን እናንጠባጥባለን። የኃጢአት ጅምላች ስለሆንን በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ኃጢአት እንሰራለን።
ችግሩ የኃጢአት ጅምላች መሆናችንንና የኃጢአት ዘሮች መሆናችንን አለማወቃችን ነው። እኛ የኃጢአት ጅምላች በልቦቻችንም ውስጥ ኃጢአት ያለብን ነን። ሰዎች በተጨባጭ እንደዚህ ናቸው።
የኃጢአት ጅምላ ሞልቶ ለመፍሰስ ተዘጋጅቷል። የሰው ዋና ኃጢአት በእውነቱ በተፈጥሮአቸው ኃጢአተኞች መሆናቸውን አለማመናቸው ነው፤ ይልቁንም ሌሎች ወደ ኃጢአት እንደሚመሩዋቸው ያስባሉ፣ ስለዚህም በእውነት የሚወቀሱት እነርሱ እንዳልሆኑ ያምናሉ።
ስለዚህ ሰዎች ኃጢአቶችን ከሠሩ በኋላ እንኳን፣ የሚፈለገው ኃጢአት እንዲወገድ ራሳቸውን እንደገና በንጽሕና መታጠብ ብቻ ነው ብለው ያስባሉ። በየጊዜው ኃጢአት ሲሠሩ፣ በእውነቱ የራሳቸው ጥፋት አለመሆኑን ለራሳቸው እየነገሩ፣ ከኋላቸው እየጥረግ ይቀጥላሉ። ብጠራርገውም ብቻ ዳግመኛ አናፈስሰውም? እኛ ያን ኃጢአት እንደገና እንደገና መጥረግ ይኖርብናል።
ብርጭቆው በኃጢአት ሲሞላ መፍሰሱን ይቀጥላል። የውጭን ብንጠርገውም አንዳች አይጠቅምም። ውጭውን በሰናይ ምግባሮቻችን አዘውትረን ብንጠርገውም ብርጭቆው በኃጢአት እስከተሞላ ድረስ ጥቅም የለውም።
እኛ በኃጢአት ተሞልተን ስለተወለድን፣ በመንገዳችን ላይ ምን ያህል ብዙ ኃጢአት ብንፈስስም፣ ልባችን ፈጽሞ ባዶ አይሆንም። ስለዚህ በሕይወታችን ዘመን ሁሉ ኃጢአትን መሥራት እንቀጥላለን።
ሰዎች የኃጢአት ጅምላ እንጂ ሌላ እንዳልሆኑ አይገነዘቡም እናም ኃጢአተኛ ተፈጥሮአቸውን ለመደበቅ መሞከራቸውን ቀጥለዋል። ኃጢአት በሁሉም ሰው ልብ ውስጥ ያለ ስለሆነ ውጭውን በማጽዳት አይወገድም። ትንሽ ኃጢአት ስንፈስ በጨርቅ እናጸዳዋለን፣ እንደገና ኃጢአትን ስንፈስስ፣ በፎጣ፣ በሞፕ እና ከዚያም ምንጣፍ እናጸዳዋለን። እንደገና ማጥፋቱን ከቀጠልን እንደገና ንጹህ እንደሚሆን እናስባለን። ሆኖም ግን በቀላሉ እንደገና እና እንደገና እየፈሰሰ ነው።
ይህ የሚቀጥለው እስከ መቼ ይመስላችኋል? ሰውየው እስከሚሞትበት ቀን ድረስ ይቀጥላል። ሰው እስከሚሞትበት ቀን ድረስ ኃጢአትን ያደርጋል። ለመዳን በኢየሱስ ማመን የሚኖርብን ለዚህ ነው። ለመዳን ራሳችንን ማወቅ ይኖርብናል።
 
ኢየሱስን በአመስጋኝነት ማን ሊቀበል ይችላል?
ብዙ ስህተቶችን እንደፈጸሙ የሚቀበሉ ኃጢአተኞች
 
ከሁለቱ ቆሻሻ ፈሳሽ የተሞሉ ብርጭቆዎች ጋር ሊነጻጸሩ የሚችሉ ሁለት ሰዎች አሉ እንበል። ሁለቱም ብርጭቆዎች በኃጢአት የተሞሉ ናቸው። ከእነዚህ መካከል አንዱ ራሱን ተመልክቶ “ኦህ፣ እኔ እንዲህ ያለ ኃጢአተኛ ሰው ነኝ” ይላል። ከዚያም ተስፋ ይቆርጥና ሊረዳው የሚችል ሰው ለመፈለግ ይሄዳል።
ነገር ግን ሌላኛው እሱ በጣም ክፉ እንዳልሆነ ያስባል። በራሱ ውስጥ የኃጢአት ጅምላን ሊያይ አይችልም እና እሱ ራሱ ክፉ እንዳልሆነ ያስባል። በሕይወት ዘመኑ ሁሉ የፈሰሰውን እየጠራረገ ይቀጥላል። አንዱን ጎን ያጸዳል፣ ከዚያም ሌላውን ጎን ያብሳል፣ በፍጥነት ወደ ሌላኛው ጎን ይንቀሳቀሳል።
ህይወታቸውን በሙሉ በኃጢአት በልባቸው ውስጥ በጥንቃቄ የሚኖሩ እና እንዳይፈስሱ የሚሞክሩ ብዙ አሉ። ነገር ግን አሁንም ድረስ በልባቸው ውስጥ ኃጢአት ስላለባቸው ይህ ምን ጥሩ ነገር ያመጣል? ጥንቃቄ ማድረግ ወደ መንግሥተ ሰማያት የበለጠ አያቀርባቸውም። ‘ጥንቃቄ ማድረግ’ ወደ ገሃነም በሚወስደው መንገድ ላይ ያስቀምጣችኋል።
ውድ ወዳጆች፣ ‘ጥንቃቄ ማድረግ’ የሚመራው ወደ ገሃነም ብቻ ነው። ሰዎች ጥንቃቄ ሲያደርጉ ኃጢአቶቻቸው ብዙ አይፈስሱ ይሆናል። ነገር ግን አሁንም ራሳቸውን የሚደብቁ ኃጢአተኞች ናቸው።
በሰው ልብ ውስጥ ምን አለ? ኃጢአት? ብልግና? አዎ! ክፉ ሀሳቦች? አዎ! መስረቅ አለ? አዎ! ዕብሪት? አዎ!
እኛ ራሳችንን ሳንማር ኃጢአተኛና ክፉ ነገር ስናደርግ ስናይ የኃጢአት ጅምላዎች መሆናችንን እናውቃለን። በወጣትነታችን ያን ያህል ግልጽ ላይሆን ይችላል።
ነገር ግን በዕድሜ እየገፋን ስንሄድ እንዴት ነው? ወደ ከፍተኛ ትምህርት፣ ወደ ኮሌጅና ወ.ዘ.ተረፈ ስንገባ በውስጣችን ያለው ነገር ሁሉ ኃጢአት እንደሆነ እንገነዘባለን። ይህ እውነት አይደለምን? በዚህ ጊዜ፣ ኃጢአትን ለመደበቅ የማይቻል ይሆናል። ትክክል አይደለም? ኃጢአትን ማፍሰሱንን እንቀጥላለን። ከዚያም ንስሐ እንገባለን። “ይህንን ማድረግ አይገባኝም ነበር።” ሆኖም፣ በተጨባጭ መለወጥ የማይቻል ሆኖ እናገኘዋለን። ለምን እንደዚያ ይሆናል? ምክንያቱም እያንዳንዳችን የኃጢአት ጅምላ ሆነን ስለተወለድን ነው።
ጥንቃቄ በማድረግ ብቻ ንጹሕ መሆን አንችልም። ልናውቀው የሚገባን ነገር እኛ ሙሉ በሙሉ ለመዳን የኃጢአት ጅምላ ሆነን እንደተወለድን ማወቅ ያስፈልገናል። መዳን የሚችሉት ኢየሱስ ያዘጋጀውን ቤዛነት በምስጋና የሚቀበሉ ኃጢአተኞች ብቻ ናቸው።
“ብዙ ስህተት አልሰራሁም በጣም ብዙ ኃጢአት አልሰራሁም” ብለው የሚያስቡ ሰዎች ኢየሱስ ኃጢአቶቻቸውን በሙሉ እንደወሰደና ለገሃነመ የታጩ እንደነበሩ የማያምኑ ናቸው። በውስጣችን ይህ የኃጢአት ጅምላ እንዳለ ማወቅ ይኖርብናል። እያንዳንዳችን ከኃጢአት ጋር የተወለድን ነበርን።
አንድ ሰው ቢያስብ፣ “ብዙ ስህተት አልሰራሁም፣ ለዚህ ትንሽ ኃጢአት መቤዠት ብችል ኖሮ፣” ከዚያ በኋላ ከኃጢአት ነፃ ይሆናሉ? ይህ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም።
መዳን የሚችሉ ሰዎች የኃጢአት ጅምላ መሆናቸውን ያውቃሉ። ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጠመቅ ኃጢአታቸውን በሙሉ እንደወሰደና ስለ እነርሱ በሞተ ጊዜም የእነርሱን ኃጢአቶች እንዳሟሟ በትክክል ያምናሉ።
ተቤዠን ወይም አልተቤዠን፣ ሁላችንም በቅዠት ውስጥ እንኖራለን። እኛ የኃጢአት ጅምላች ነን። እኛ የሆንነው ያ ነው። ልንዋጅ የምንችለው ኢየሱስ ኃጢአታችንን ሁሉ እንደወሰደ ካመንን ብቻ ነው።
 
 
እግዚአብሔር ‘ትንሽ ኃጢአት’ ያለባቸውን አላዳናቸውም
 
ጌታን የሚያታልለው ማነው?
በየቀኑ ለሚሠራቸው ኃጢአቶች ይቅርታን የሚለምን ሰው ነው
 
እግዚአብሔር ‘ትንሽ ኃጢአት’ ያለባቸውን አላዳናቸውም። እግዚአብሔር “እግዚአብሔር ሆይ ሆይ፣ ይህ ትንሽ ኃጢአት አለኝ” የሚሉትን እንኳን አይመለከትም። እግዚአብሔር የሚመለከታቸው፣ “እግዚአብሔር፣ እኔ የኃጢአት ጅምላ ነኝ የሚሉ ናቸው። ወደ ገሃነም እሄዳለሁ። እባካችሁ አድኑኝ።” እነዚያ ሙሉ ኃጢአተኞች እንዲህ የሚሉ፦ “እግዚአብሔር፣ አንተ ብታድነኝ ብቻ እድናለሁ። እንደገና ኃጢአት ስለምሠራ ከእንግዲህ በንስሐ መጸለይ አልችልም። እባክህ አድነኝ።” 
እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የተመኩትን ሙሉ በሙሉ ያድናቸዋል። እኔም በየቀኑ የንስሐ ጸሎትን ለመጸለይ ሞክሬያለሁ። ነገር ግን የንስሐ ጸሎቶች ፈጽሞ ከኃጢአት ነጻ አያወጡንም። “እግዚአብሔር፣ ሆይ እባክህ ራራልኝና ከኃጢአቴ አድነኝ።” እንዲህ የሚጸልዩ ሰዎች ይድናሉ። እነርሱ በእግዚአብሔር ቤዛነት፣ በመጥምቁ ዮሐንስ በተከናወነው የኢየሱስ ጥምቀት ያምናሉ። ይድናሉም።
እግዚአብሔር የሚያድነው ራሳቸውን የኃጢአት ጅምላች፣ የክፉ አድራጊ ዘሮች አድርገው የሚያውቁትን ሰዎች ብቻ ነው። “እኔ የሰራሁት ይህችን ቅንጣት ኃጢአት ብቻ ነው። እባክህ ለዚህ ኃጢአት ይቅር በለኝ፣” የሚሉ ሰዎች አሁንም ድረስ ኃጢአተኞች ስለሆኑ እግዚአብሔር ሊያድናቸው አይችልም። እግዚአብሔር የሚያድናቸው ራሳቸውን ፍጹም የኃጢአት ጅምላች እንደሆኑ የሚያውቁትን ሰዎች ብቻ ነው።
በኢሳይያስ 59፡1-2 ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፎዋል፦ “እነሆ፥ የእግዚአብሔር እጅ ለማዳን አላጠረችም፤ ጆሮውም እንዳይሰማ አልከበደም። ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።”
እኛ የኃጢአት ጅምላ ሆነን ስለተወለድን እግዚአብሔር በፍቅር ሊመለከተን አይችልም። ይህ የሆነበት ምክንያት እጁ ስላጠረች፣ ጆሮው ስለከበደች ወይም ይቅርባይነቱን ስንጠይቀው ሊሰማን ስለማይችል አይደለም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይነግረናል፦ “በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።” በልቦቻችን ውስጥ ብዙ ኃጢአት ስላለ በሮቹ ምንም ያህል ወለል ብለው ቢከፈቱም መንግሥተ ሰማይ ልንገባ አንችልም።
እኛ የኃጢአት ጅምላ የሆንን ሰዎች ኃጢአት በሠራን ቁጥር ይቅርታን ብንጠይቅ እግዚአብሔር ልጁን በተደጋጋሚ መግደል ሊኖርበት ነው። እግዚአብሔር ይህንን ማድረግ አይፈልግም። ስለዚህም፣ እርሱ እንዲህ ይላል፦ “በየቀኑ ኃጢአቶቻችሁን ይዛችሁ ወደ እኔ አትምጡ። ከኃጢአቶቻችሁ ሁሉ ያድናችሁ ዘንድ ልጄን ላኩላችሁ። እናንተ ማድረግ የሚገባችሁ ነገር ቢኖር ኢየሱስ ኃጢአቶቻችሁን መውሰዱንና ያም እውነት መሆኑን መቀበል ብቻ ነው። ከዚያም ለመዳን በቤዛነት ወንጌል እመኑ። ይህ ለእርስዎ ያለኝ ከፍተኛ ፍቅር ነው፣ የእኔ ፈጠራዎች።”
እግዚአብሔር የነገረን ይህንን ነው። “በልጄ እመኑና ዳኑ። እኔ አምላካችሁ ለኃጢያቶቻችሁ እና ለበደሎቻችሁ ሁሉ ያስተሰርይ ዘንድ የራሴን ልጄን ላክሁ። በልጄ አምናችሁ ዳኑ።”
የኃጢያት ጅምላች መሆናቸውን የማያውቁት ለራሳቸው ትንሽ ኃጢአታቸው ይቅርታን ብቻ ይጠይቃሉ። ኃጢአታቸው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ሳያውቁ ወደ ጌታ ቀርበው “እባክህ ይህን ትንሽ ኃጢአት ይቅር በለኝ። ዳግመኛ እንደዚህ ያለ ኃጢአት አልሰራም፣” ብለው ይጸልያሉ።
እግዚአብሔርንም ለማታለልም እየሞከሩ ነው። እኛ ኃጢአት የምንሠራው አንድ ጊዜ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን እስክንሞት ድረስ በየጊዜው ኃጢአትን እንሠራለን። እስከ መጨረሻው የሕይወታችን ቀን ድረስ ይቅርታን በመጠየቅ እንቀጥላለን።
ለአንድ ትንሽ ኃጢአት ይቅርታ መደረጉ ምንም ሊፈታ አይችልም ምክንያቱም በሕይወታችን ውስጥ በየቀኑ ኃጢአት እንሠራለን እስክንሞት ድረስ። ስለዚህ ከኃጢአት ነጻ መሆን የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ወደ ኢየሱስ ማስተላለፍ ነው።
 
የሰው ዘር ምንድነው?
የኃጢአት ጅምላ
 
መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ኃጢአቶች መዝግቦዋል። ኢሳይያስ 59፡3-8 እንዲህ ይላል “እጃችሁ በደም ጣታችሁም በበደል ረክሳለች፥ ከንፈራችሁም ሐሰትን ተናግሮአል፥ ምላሳችሁም ኃጢአትን አሰምቶአል። በጽድቅ የሚጠራ በእውነትም የሚፈርድ የለም። በምናምንቴ ነገር ታምነዋል ሐሰትንም ተናግረዋል፥ ጕዳትን ፀንሰዋል በደልንም ወልደዋል። የእባብን እንቍላል ቀፈቀፉ፥ የሸረሪትንም ድር አደሩ፤ እንቍላላቸውንም የሚበላ ሰው ይሞታል፥ እንቍላሉም ሲሰበር እፉኝት ይወጣል። ድሮቻቸውም ልብስ አይሆኑላቸውም፥ በሥራቸውም አይሸፈኑም፤ ሥራቸውም የበደል ሥራ ነው፥ የግፍም ሥራ በእጃቸው ነው። እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፥ ንጹሑን ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤ አሳባቸው የኃጢአት አሳብ ነው፥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ። የሰላምን መንገድ አያውቁም፥ በአካሄዳቸውም ፍርድ የለም፤ መንገዳቸውን አጣምመዋል፥ የሚሄድባትም ሁሉ ሰላምን አያውቅም።”
የሰዎች ጣቶች በበደል የረከሱ ናቸው፣ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ክፋትን ያደርጋሉ። እነርሱ የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ክፉ ነው። ምላሶቻችንም ‘ሐሰትን ተናግሮአል።’ ከአፋችን የሚወጡት ነገሮች ሁሉ ውሸቶች ናቸው።
“እርሱ (ዲያብሎስ) ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል” (ዮሐንስ 8፡44)። ዳግመኛ ያልተወለዱ ሰዎች “እውነቱን እየነገርኩህ ነው። በእርግጠኝነት እየነገርኩህ ነው። እኔ የምለው ነገር እውነት ነው” ማለት ይወዳሉ። ነገር ግን እነርሱ የሚናገሩት ሁሉ ውሸት ነው። ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። “እርሱ (ዲያብሎስ) ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል።” 
ሰዎች በባዶ ቃሎች ይታመኑና ውሸቶችን ይናገራሉ። ሰዎች ክፋቶችን ጸንሰው በደሎችን ይወልዳሉ። የእባብን እንቁላሎች ይቀፈቅፋሉ እና የሸረሪት ድሮችንም ያደራሉ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እንቍላላቸውንም የሚበላ ሰው ይሞታል፥ እንቍላሉም ሲሰበር እፉኝት ይወጣል።” እግዚአብሔር በልባችሁ ውስጥ የእፉኝት እንቁላሎች እንዳሉ ይናገራል። የእፉኝት እንቁላሎች! በልባችሁ ውስጥ ክፋት አለ። በውሃውና በደሙ ወንጌል በማመን መዳን የሚኖርብን ለዚህ ነው።
ስለ እግዚአብሔር መናገር በምጀምርበት ጊዜ ሁሉ “ኦ ውዴ። እባካችሁ ስለ እግዚአብሔር አታናግሩኝ። አንድ ነገር ለማድረግ በምሞክርበት ጊዜ ሁሉ ኃጢአት ከውስጤ ይንጠባጠባል። እንደ ጎርፍ ይፈስሳል። በየቦታው ኃጢአት ሳልፈስ አንድ እርምጃ እንኳን መውሰድ አልችልም። ምንም ላደርገው አልችልም። እኔ እጅግ በኃጢአት ተሞልቻለሁ። ስለዚህ ስለ እግዚአብሔር እንኳን አታናግረኝ” የሚሉ ሰዎች አሉ።
ይህ ሰው የኃጢአት ጅምላ ብቻ መሆናቸውን በእርግጠኝነት ያውቃል፣ ነገር ግን ሊያድናቸው የሚችለውን ወንጌል ብቻ አያውቁም። የኃጢአት ጅምላ መሆናቸውን የሚያውቁ መዳን ይችላሉ።
በእውነቱም ሁሉም እንደዚያው ነው። ሁሉም ሰው በየሄደበት ያለማቋረጥ ኃጢያትን እያፈሰሰ ነው። ሁሉም ሰው የኃጢያት ጅምላ ስለሆነ፣ ያለማቋረጥ ብቻ ሞልቶ ይፈስሳል። እንደዚያ ያለ ሰው የሚድንበት ብቸኛው መንገድ የእግዚአብሔር ሐይል ነው። ይህ የሚያስገርም አይደለምን? በተበሳጩ፣ በተደሰቱ ወይም በተመቻቸው ቁጥር ሁልጊዜ ኃጢአታቸውን የሚያፈሱ ሰዎች መዳን የሚችሉት በጌታችን በኢየሱስ አማካይነት ብቻ ነው። ኢየሱስ እነዚያን ሰዎች ለማዳን መጣ።
እርሱ ለኃጢአቶቻችሁ በሙሉ ፈጽሞ ማስተስረ ሰጥቷል። የኃጢአት ጅምላ መሆናችሁን እወቁና ዳኑ። 

ይህ ስብከት በየኤሌክትሮኒክ መጽሐፍት ቅርጸት ደግሞ ይገኛል። ከዚህ በታች ባለው የመጽሐፉ ሽፋን ላይ ጠቅ ያድርጉ።
በውኑ በውሃውና በመንፈስ ቅዱስ ዳግም ተወልዳችኋልን? [አዲስ የተሻሻለ እትም]