Search

説教集

ርዕስ 3፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል

[3-1] ዘላለማዊው ቤዛነት (ዮሐንስ 8፡1-12)

ዘላለማዊው ቤዛነት (ዮሐንስ 8፡1-12)
 
(ዮሐንስ 8፡1-12)
“ኢየሱስ ግን ወደ ደብረ ዘይት ሄደ። ማለዳም ደግሞ ወደ መቅደስ ደረሰ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፤ ተቀምጦም ያስተምራቸው ነበር። ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ፤ በመካከልም እርሱዋን አቁመው። እነሱም እንዲህ አሉት፦ መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ፦ ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው። ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ፦ አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት። እርስዋም፦ ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ ማንም የለም። ኢየሱስም፦ እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት። ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።”
 
 
ኢየሱስ የደመሰሰልን ኃጢአት ምን ያህል ነበር?
የአለምን ኃጢአቶች በሙሉ ነው
 
 
ኢየሱስ ዘላለማዊ ቤዛነትን ሰጠን። ኢየሱስን አዳኙ አድርጎ ቢያምን በዚህ ዓለም ላይ ቤዛነትን ማግኘት የማይችል አንድም ሰው የለም። እርሱ ሁላችንንም ዋጀን። በኃጢአቶች የሚሰቃይ ኃጢአተኛ ካለ፣ ኢየሱስ በጥምቀቱ እንዴት ከኃጢአት ሁሉ እንዳዳናቸው ስላልገባቸው ነው።
ሁላችንም የመዳንን ምስጢር ማወቅ እና ማመን አለብን። ኢየሱስ በጥምቀቱ ኃጢአታችንን ሁሉ ወስዶ በመስቀል ላይ በመሞት ለኃጢአታችን ፍርድን ተሸክሟል።
ከኃጢአቶች ሁሉ ዘላለማዊ ቤዛነት፣ በሆነው የውሃውና የመንፈሱ መዳን ማመን ይገባችኋል። አስቀድሞ ጻድቅ ያደረገህን ታላቅ ፍቅሩን ማመን አለብህ። ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ እና በመስቀል ላይ ለመዳንዎ ያደረገውን እመኑ።
ኢየሱስ የተደበቁ ኃጢአቶቻችንንም በሙሉ አውቋል። አንዳንድ ሰዎች ስለ ኃጢአት የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው። አንዳንድ ኃጢአቶች ሊቤዡ አይችሉም ብለው ያስባሉ። ኢየሱስ ግን ሁሉንም ኃጢአቶች፣ እያንዳንዳቸውን ቤዟል።
በዚህ ዓለም እርሱ ያላነሳው ኃጢአት የለም። በዚህ ዓለም ያሉትን ኃጢአቶች ሁሉ ስለቤዛቸው፣ ከእንግዲህ ኃጢአተኞች የሉም። ኃጢያቶቻችሁን ሁሉ፣ የወደፊቱን ኃጢያቶቻችሁንም ሳይቀር የተዋጀውን ወንጌል ታውቃላችሁ? በዚህ አምናችሁ ዳኑ። እና ወደ እግዚአብሔር ክብር ተመለሱ።
 
 
በምንዝር ድርጊት የተያዘችው ሴት
 
በምድር ላይ ምን ያህል ሰዎች ያመነዝራሉ?
ሁሉም ሰው
 
በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 8 ላይ በምንዝርና ድርጊት ስለተያዘችው ሴትን እናያለን። በኢየሱስም እንዴት እንደዳነች እናያለን። ያገኘችውን ፀጋ ልናካፍል ወደድን። ሁሉም የሰው ልጆች በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ምንዝር ይፈጽማሉ ማለት በጣም ብዙ አይደለም። እያንዳንዱ ሰው ያመነዝራል።
እንደዚህ የማይመስለው ከሆነ፣ በጣም ብዙ ጊዜ ስለምናደርገው እንደማናደርግ የሚመስል በመሆኑ ብቻ ነው። ለምን? በሕይወታችን ውስጥ በጣም ብዙ ምንዝር ይዘን እንኖራለን።
ሴቷን እያየሁ ከእኛ መካከል ዝሙት ያልፈጸመ አንድ ሰው እንኳን አለ ወይ ብዬ በጥልቀት አስባለሁ። ስታመነዝር እንደተያዘችው ሴት ያላመነዘረ ማንም ሰው የለም። ሁላችንም እንዳላመነዘርን እንመስላለን።
እንደተሳሳትሁ ታስባላችሁን? አይ እኔ አይደለሁም። የራሳችሁን ውስጣዊ ሁኔታ በጥልቀት ተመልከቱ። በምድር ላይ የሚኖር እያንዳንዱ ሰው ዝሙት ፈጽሟል። ሴቶችን በመንገድ ላይ ሲመለከቱ፣ በሐሳባቸውና በድርጊቶቻቸው በማንኛውም ጊዜ እና በማንኛውም ቦታ ያመነዝራሉ።
እነሱ ዝሙት እየፈጸሙ መሆናቸውን ብቻ አያውቁም። በሕይወታቸው ሙሉ በማይቆጠር ጊዜ ምንዝርን እንዳደረጉ እስከሚሞቱ ድረስ የማይገነዘቡ ብዙ ሰዎች አሉ። የተያዙት ብቻ ሳይሆን፣ ተይዘን የማናውቅ ሁላችንም ዝሙትን እንፈጽማለን። ሰዎች ሁሉ በአእምሮና በድርጊት ምንዝር ይፈጽማሉ። ይህ የሕይወታችን ክፍል አይደለምን?
ተበሳጫችሁ? ይህ እውነት ነው። እኛ እያፈርን ስለሆነ ይህን ነገር እንደዚሁ እየደበቅን ነው። በእነዚህ ቀናት ሰዎች ሁልጊዜ ዝሙት እየፈጸሙ እንደሆነ እና እየፈጸሙት መሆናቸውን እንደማያውቁ አምናለሁ።
ሰዎች በነፍሳቸውም ዝሙት ይፈጽማሉ። እኛ በእግዚአብሔር የተፈጠርን ሰዎች በዚህ ምድር ላይ የምንኖረው በነፍሳችን ውስጥ ዝሙትን እንደምንፈጽም ሳንገነዘብ ነው። ሌሎችን አማልክትን ማምለክ መንፈሳዊ ዝሙት ነው፣ ምክንያቱም ጌታ የሰው ሁሉ ብቸኛ ባል ነው።
በዝሙት ድርጊት ላይ የተያዘችው ሴት እንደተቀረነው ሰዎች ሰብዓዊ ፍጡር ነበረች፣ እኛም የተዋጅነው እኛ እንዳደረግነው የእግዚአብሔርን ጸጋ ተቀበለች። ግብዞቹ ፈሪሳውያን ግን በፊታቸው አቁመው ዳኞች የሆኑ ይመስል ጣቶቻቸውን በእርስዋ ላይ ቀስረው በድንጋይ ሊወግሩት ተዘጋጁ። እነርሱ ራሳቸው ንጹህ እንደሆኑ አድርገው ሊዘባበቱባትና ሊፈርዱባት ነበር፣ ዝሙትን ፈፅመው የማያውቁ ይመስል።
አጋር ክርስቲያኖች፣ ራሳቸውን የኃጢአት ጅምላ አድርገው የሚያውቁ ሰዎች በሌሎች እግዚአብሔር ፊት አይፈርዱም። ይልቁንም በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ እንደሚያመነዝሩ ስለሚያውቁ ነው፣ ሁላችንንም የዋጀንን የእግዚአብሔርን ጸጋ ይቀበላሉ። እራሳቸው ሁልጊዜ ዝሙት የሚፈጽሙ ኃጢአተኞች መሆናቸውን የሚገነዘቡ ብቻ በእግዚአብሔር ፊት ለመዳን ብቁ ናቸው።
 
 

የእግዚአብሔርን ጸጋ የሚቀበለው ማነው?

 
ዝሙት ሳይፈጽም በንጽህና የሚኖር ሰው የእርሱን ጸጋ ይቀበላልን፣ ወይስ ራሱን እጅግ ኃጢአተኛ እንደሆነ የሚናዘዝ የማይገባ ሰው ጸጋውን ይቀበላልን? ጸጋን የሚቀበለው የእርሱን የተትረፈረፈ የቤዛነት ጸጋ የሚቀበለው ኃጢአተኛ መሆኑን አምኖ የሚቀበል ሰው ነው። ራሳቸውን መርዳት የማይችሉ ደካሞችና ረዳተ ቢሶች ቤዛነትን ይቀበላሉ። በእርሱ ጸጋ ውስጥ ያሉት እነርሱ ናቸው።
 
የእግዚአብሔርን ጸጋ የሚቀበለው ማነው?
የማይገባቸው ሰዎች
 
ኃጢአት የሌለባቸው ናቸው ብለው የሚያስቡ ሰዎች ሊዋጁ አይችሉም። የሚቤዥ ምንም ነገር ሳይኖር እንዴት የቤዛነቱን ጸጋ ሊቀበሉ ይችላሉ?
ጸሐፍትና ፈሪሳውያን እየጎተቱ በመንዝር ድርጊት የተያዘችውን ሴት ወደ ኢየሱስ ፊት አመጡና በመካከላቸው አቁመዋት ከዚያም እንዲህ በማለት ጠየቁት፦ “ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን። አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ?” እነርሱ ሴቲቱን በፊቱ ያቀረቡዋትና የፈተኑት ለምንድነው?
እነሱ ራሳቸውም ብዙ ጊዜ ምንዝር ፈጽመዋል፣ ነገር ግን ሊፈርዷት እና በኢየሱስ በኩል ሊገድሏት እና ጥፋቱን በእሱ ላይ ለማድረግ እየሞከሩ ነበር።
ኢየሱስ በአእምሮዋቸው ውስጥ ያለውን አወቀ፣ ስለ ሴቲቱም ሁሉንም አወቀ። ስለዚህ እንዲህ አለ፦ “ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።” ያን ጊዜ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ከሽማግሌው ጀምሮ እስከ ልጁ ድረስ አንድ በአንድ ሄዱና ኢየሱስና ሴቷ ብቻ ቀሩ።
ትተው የሄዱት ጸሐፍትና ፈሪሳውያን፣ የሃይማኖት መሪዎች ነበሩ። እነርሱም በመንዝር ድርጊት የተያዘችውን ሴት ሊፈርዱ ተዘጋጅተው ነበር፣ እነርሱ ራሳቸው ኃጢአተኞች ያልነበሩ ይመስል።
ኢየሱስ ፍቅሩን በዚህ ዓለም አወጀ። ኢየሱስ የፍቅር አስተናጋጅ ነበር። ኢየሱስ ለሰዎች መብል ሰጠ፣ ሙታንን እንደ ገና አስነሳ፣ ለመበለት ልጅ ሕይወትን ሰጠ፣ ላዛራስን እንደ ገና ከሞት አስነሳ፣ ለምጻሞች ፈወሰ፣ ለድሆችም ተዓምራትን አደረገ። እየሱስ የኃጢአተኞችን ኃጢአቶች በሙሉ ወስዶ መዳን ሰጣቸው።
ኢየሱስ ይወደናል። እርሱ ማንኛውንም ነገር ማድረግ የሚችል ሁሉን ቻይ አምላክ ነው፤ ፈሪሳውያንና ጸሐፍት ግን ጠላታቸው እንደሆነ አሰቡ። ሴቲቱን ወደ እርሱ ይዘው የመጡትና የፈተኑት ለዚህ ነው።
እነርሱ ኢየሱስን እንዲህ ብለው ጠየቁት፦ “ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ?” ኢየሱስ እንዲወግሯት እንደሚነግራቸው አሰቡ። ለምን? በእግዚአብሔር ሕግ በተጻፈው መሠረት ብንፈርድባት ዝሙትን የፈጸሙ ሰዎች ሁሉ ያለ ምንም ልዩነት በድንጋይ ተወግረው ይገደላሉ።
ሁሉም በድንጋይ ተወግረው መሞት አለባቸው እና ሁሉም ወደ ገሃነም ለመሄድ የታጩ ናቸው። የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው። ነገር ግን ኢየሱስ እንዲወግሩዋት አልነገራቸውም፣ በፈንታው እንዲህ አለ፦ “ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።”
 
እግዚአብሔር 613ቱን የሕግ አንቀፆች የሰጠን ለምንድነው?
እኛ ኃጢአተኞች መሆናችንን እንድንገነዘብ ለማድረግ
 
ሕጉ ቁጣን ያመጣል። እግዚአብሔር ቅዱስ ነው፣ ሕጉም ደግሞ ቅዱስ ነው። ይህ ቅዱስ ሕግ በ613 አንቀጾች ተሰጥቶናል። እግዚአብሔር 613 የሕግ አንቀጾችን የሰጠን ምክንያት እኛ ኃጢአተኞች መሆናችንን እና ያልተሟላን ፍጡራን መሆናችንን እንድንገነዘብ ነው። ይህ ለመዳን የእግዚአብሔርን ጸጋ መመልከት እንዳለብን ያስተምረናል። ይህንን ሳናውቅ በሕጉ ውስጥ ስለተጻፈው ብቻ የምናስብ ከሆንን፣ እጅ በድርጊቱ እንደተያዘች ሴት ሁላችንም በድንጋይ ልንሞት ይገባናል።
የእርሱን ሕግ እውነት ያላወቁት ጸሐፍትና ፈሪሳውያን በሴቲቱ ላይና ምናልባትም በእኛም ላይ እንደዚሁ ድንጋይ መወርወር እንደሚችሉ አስበው ይሆናል። ረዳተ ቢስ በሆነችው ሴት ላይ ድንጋዮችን መወርወር የሚችል ማነው? በድርጊቱ ተይዛ ብትሆንም በዚህ አለም ላይ ማንም ሰው ድንጋይ ሊወረውርባት አይችልም።
ሴቲቱና እያንዳንዳችን በሕጉ መሠረት ብቻ ብንፈረድ እኛም ሆንን ሴቲቱ አስከፊ ፍርድ እንቀበል ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ እኛን ኃጢአተኞችን ከኃጢአቶቻችንንና ከትክክለኛ ፍርድ አዳነን። በኃጢአታችን ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ሕግ በተጻፈው መሠረት በጥብቅ በእኛ ላይ ተተግብሮ ቢሆን ኖሮ ከመካከላችን በሕይወት መቆየት የሚችል ማን ነበር? እያንዳንዳችን በገሃነም እንወድቃለን።
ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ግን ሕጉን ያወቁት በተጻፈው መሠረት ብቻ ነበር። የእርሱ የአምላክ ሕግ በትክክል ተተግብሮ ቢሆን ኖሮ እነርሱ፣ እንደኮነኑዋትት ሴት በእርግጠኝነት ይገድላቸው ነበር። የእግዚአብሔር ሕግ ለሰዎች የተሰጠው ኃጢአቶቻቸውን ማወቅ እንዲችሉ ነበር፣ ነገር ግን ሕጉን በተሳሳተ መንገድ ስለተረዱትና በተሳሳተ መንገድ ስለተገበሩት ተቸገሩ።
የዛሬዎቹ ፈሪሳውያን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዳሉት ፈሪሳውያን ሕጉን የሚያውቁት እንደተጻፈው ብቻ ነው። እነርሱ የእግዚአብሔርን ጸጋ፣ ፍትህ እና እውነት መገንዘብ አለባቸው። ለመዳንም የቤዛነትን ወንጌል መማር ይኖርባቸዋል።
ፈሪሳውያን እንዲህ አሉ፦ “እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን። አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ?” ድንጋዮቻቸውን በድፍረት ይዘው ጠየቁ። ኢየሱስ ስለዚህ ጉዳይ የሚናገረው አንዳች ነገር አይኖረውም ብለው በእርግጠኝነት አሰቡ። ኢየሱስ በወጥመዳቸው እንዲገባ ጠበቁት።
ኢየሱስ እንደ ሕጉ ተናግሮ ቢሆን ኖሮ፣ እነርሱም በድንጋይ ይወግሩት ነበር። አላማቸው ሴቲቱንና ኢየሱስን በድንጋይ መውገር ነበር። ኢየሱስ ሴቲቱን እንዳይወግሯት ቢል ኖሮ፣ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ሕግ እንዳናቀ በማለት ስለ ስድብ በድንጋይ ይወግሩት ነበር። ይህ እንዴት ያለ አደገኛ ሴራ ነበር!
ኢየሱስ ግን ጎንበስ አለና በጣቱ መሬት ላይ ጻፈ፣ ኢየሱስንም መጠየቃቸውን ቀጠሉ፦ “አንተ ምን ትላለህ? በመሬት ላይ የምትጽፈውስ ምንድነው? ጥያቄያችንን ብቻ መልስ። ምን ትላለህ?” ጣቶቻቸውን ወደ ኢየሱስ እየጠቆሙ ያስጨንቁት ነበር ቀጠሉ።
ኢየሱስ ተነስቶ ከእነርሱ መካከል ኃጢአት የሌለበት ሰው አስቀድሞ በድንጋይ እንዲወውራት ነገራቸው። ከዚያም ጎንበስ ብሎ በመሬት ላይ መጻፉን ቀጠለ። ይህንን የሰሙት ሕሊናቸው ስለወቀሳቸው ከሽማግሌው ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ አንድ በአንድ ትተው ሄዱ። ኢየሱስም ብቻውን ቀረ፣ ሴቲቱም በፊቱ ቆማ ነበር።
 
 
“ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው”
 
ኃጢያቶች የተመዘገቡት የት ነው?
በልቦቻችን ጽላቶች ላይና በምግባሮች መጽሐፎች
 
ኢየሱስም እንዲህ ሲል ተናገራቸው፦ “ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው፣” በመሬት ላይም መጻፉን ቀጠለ። ከዚያም ከትልልቆቹ ጀምሮ አንድ በአንድ መተው ጀመሩ። ብዙ ኃጢአት የሠሩት ትልልቅ ፈሪሳውያን አስቀድመው ሄዱ። ወጣቶቹም እንዲሁ ሄደዋል። ኢየሱስ በመካከላችን ቆሞ እኛ ደግሞ በሴቲቱ ዙሪያ ቆመን እናስብ። ኢየሱስ ከእኛ መካከል ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ ድንጋይ ይውገር ብሎ ተናግሮ ቢሆን፣ ምን ታደርጉ ነበር?
ኢየሱስ በመሬት ላይ ሲጽፍ የነበረው ምንድነው? እኛን የፈጠረን እግዚአብሔር ኃጢአቶቻችንን በሁለት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጽፋል።
በመጀመሪያ ኃጢአቶቻችንን በልባችን ጽላት ላይ ይጽፋል።
“የይሁዳ ኃጢአት በብረት ብርዕና በተሾለ ዕብነ አልማዝ ተጽፎአል፤ በልባቸው ጽላትና በመሠዊያቸው ቀንዶች ተቀርጾአል” (ኤርምያስ 17፡1)።
እግዚአብሔር በይሁዳ በኩል ያናግረናል። የሰዎች ኃጢአቶች በብረት ብዕርና በተሾለ ዕብነ አልማዝ ተጽፈዋል። በልቦቻችን ጽላት ላይ ተመዝግበዋል። ኢየሱስ አጎንብሶ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች መሆናቸውን በመሬት ላይ ጻፈ።
እግዚአብሔር ኃጢአት እንደምንሠራ ያውቃል፣ ኃጢአቶችንም በልባችን ጽላት ላይ ይቀርጻል። በመጀመሪያ፣ እርሱ ሥራዎቻችንን ይመዘግባል፣ በሕግ ፊት ደካሞች ስለሆንን የምንፈጽማቸውን ኃጢአቶች። ኃጢአቶች በልቦቻችን ውስጥ ስለተመዘገቡ ሕጉን ስንመለከት ኃጢአተኞች እንደሆንን እንገነዘባለን። እግዚአብሔር እነዚህ ኃጢያቶችን በልቦቻችን፣ በሕሊናዎቻችን ላይ ስለተመዘገቡ እኛ በእርሱ ፊት ኃጢያተኞች እንደሆንን እናውቃለን።
ኢየሱስ በመሬት ላይ ለመጻፍ ለሁለተኛ ጊዜ አጎነበሰ። መጽሐፍ ቅዱስም ደግሞ ኃጢያቶቻችን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በምግባሮች መጽሐፎች ውስጥ እንደተጻፉ ይናገራል (ዮሐንስ ራእይ 20፡12)። የአንድ ሰው ስም እና ኃጢአቱ በመጽሐፉ ውስጥ ተመዝግቧል። እና እነሱ ደግሞ በሰው ልብ ጽላት ላይ ተመዝግበዋል። ኃጢያቶቻችን በምግባሮች መጽሐፍና በልቦቻችን ጽላት ላይ ሁለት ጊዜ የተጻፉ ናቸው።
ኃጢያቶች በወጣቱም ሆነ በሽማግሌው በእያንዳንዱ ሰው የልቦ ጽላት ላይ ተመዝግበዋል። በኢየሱስ ፊት ስለ ኃጢያቶቻቸው የሚናገሩት አንዳች ነገር የማይኖረው ለዚህ ነው። ሴቲቱን በድንጋይ ሊወግሩት የሞከሩት ከቃሉ በፊት አቅመበት ቢስ ነበሩ።
 
በእነዚህ ሁለት ቦታዎች የተጻፉት ኃጢአቶቻችን የሚሰረዙት መቼ ነው?
በልባችን የኢየሱስን የውሃና የደም ቤዛነት ስንቀበል ነው።
 
ነገር ግን፣ መዳንን ስትቀበል፣ በምግባሮች መጽሐፍ ውስጥ ያሉት ኃጢአቶቻችሁ በሙሉ ይደመሰሱና ስማችሁ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ይገባል። ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ያለ ሰዎች መንግሥተ ሰማይ ይገባሉ። በዚህ ዓለም ለእግዚአብሔር መንግሥትና ለጽድቁ ያደረጓቸው መልካም ሥራዎቻቸውም በሕይወት መጽሐፍ ላይ ተመዝግበዋል። ወደ መንግሥተ ሰማያትም ተቀባይነት አላቸው። ከኃጢአቶቻቸው የዳኑ ሰዎች ወደ ዘላለማዊው አገር ይገባሉ።
የእንዳንዱ ሰው ኃጢያቶች በሙሉ በሁለት ስፍራዎች ላይ እንደተጻፉ ይመዘገባል። ስለዚህ ማንም ሰው እግዚአብሔርን ማታለል አይችልም። በልቡ ኃጢአትን ያልሠራ ወይም ያላመነዘረ ሰው የለም። እኛ ሁላችንም ኃጢአተኞችና ያልተሟላን ነን።
በልባቸው የኢየሱስን ቤዛነት ያልተቀበሉ ሰዎች በኃጢአታቸው ሊሠቃዩ ይገደዳሉ። እነርሱ በራሳቸው የተማመኑ አይደሉም። እነርሱ በኃጢአታቸው ምክንያት እግዚአብሔርን ይፈራሉ፣ በእግዚአብሔርና በሌሎች ሰዎች ፊት ይፈራሉ። ነገር ግን የውሃውንና የመንፈሱን ቤዛነት ወንጌል በልባቸው ውስጥ በተቀበሉበት ቅጽበት በልቦቻቸው ጽላቶችና በምግባር መጽሐፎች ውስጥ የተጻፉት ኃጢአቶች በሙሉ ይነጻሉ። ከኃጢአቶቻቸውም ሁሉ ይድናሉ።
በሰማይ የሕይወት መጽሐፍ አለ። በውሃውና በመንፈሱ የቤዛነት ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ስሞችም በመጽሐፉ ውስጥ ስለተጻፈ መንግሥተ ሰማይ ይገባሉ። መንግሥተ ሰማይ የሚገቡት በዚህ ዓለም ላይ ኃጢአት ስላልሠሩ ሳይሆን በውሃውና በመንፈሱ የቤዛነት ወንጌል በማመን ከኃጢአቶቻቸው ሁሉ ስለዳኑ ነው። ይህ ‘የእምነት ሕግ’ (ሮሜ 3፡27) ነው።
ባልደረቦች ክርስቲያኖች፣ እነዚህ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን በምንዝር ድርጊት እጅ እንደተያዘችው ሴት ኃጢአተኞች ነበሩ።
በእውነቱ፣ ኃጢአተኞች አለመሆናቸውን በመምሰልና ራሳቸውን በማታለል ይበልጥ ኃጢአት ፈጽመዋል። የሐይማኖት መሪዎች ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ሌቦች ነበሩ። እነርሱ የነፍስ ሌቦች፣ የሕይወት ሌቦች ነበሩ። እነርሱ ራሳቸው ገና ሳይቤዠዩ፣ ሌሎችን በአስተማማኝነት ለማስተማር ደፈሩ።
በሕጉ መሠረት ኃጢአት የሌለበት ማንም ሰው የለም። ሰው ግን አንድ ሰው ጻድቅ ይሆናል እንጂ ኃጢአት ስለማይሠራ አይደለም፣ ነገር ግን ከኃጢአታቸው ሁሉ ስለተዋጁ እና ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቧል። ዋናው ነገር የሰውየው ስም በሕይወት መጽሐፍ ላይ መጻፉ ወይም አለመጻፉ ነው። ሰዎች ከኃጢአት ነፃ ሆነው መኖር ስለማይችሉ፣ መቤዠት አለባቸው።
በመንግሥተ ሰማይ ተቀባይነት ማግኘታችሁ የሚመረኮዘው በእውነተኛው ወንጌል በማመናችሁ ወይም በአለማመናችሁ ነው። የእግዚአብሔርን ጸጋ መቀበላችሁ ወይም አለመቀበላችሁ የሚወሰነው የኢየሱስን መዳንን በመቀበላችሁ ላይ ነው። በድርጊቱ የተያዘችው ሴት ምን አጋጠማት? እርስዋ መሞት እንዳለባት ስላወቀች ዓይኖቿን ጨፍና ቆማ ነበር። ምናልባት በፍርሃትና በንስሐ እያለቀሰች ነበር። ሰዎች ሞትን ሲገጥሙ ከራሳቸው ጋር ቅን ይሆናሉ።
“አቤቱ እግዚአብሔር፣ እኔ መሞት እንዳለብኝ ተገቢ ነው። እባክህ ነፍሴን በእጆችህ ተቀበል፣ ራራልኝም። ኢየሱስ ሆይ እባክህ ራራልኝ።” ኢየሱስ የቤዛነትን ፍቅር እንዲሰጣት ተማጸነችው። “እግዚአብሔር፣ ሆይ ከፈረድክብኝ ይፈረድብኛል፣ ኃጢአት የለብሽም የምትል ከሆነም ኃጢአቶቼ ይደመሰሳሉ። ሁሉም በአንተ እጅ ነው።” እርስዋ ምናልባት እነዚህን ሁሉ ነገሮች እየተናገረች ነበር። ሁሉም ነገር ለኢየሱስ የተተወ ነበር።
ወደ ኢየሱስ የተመጣችው ሴት “ስህተት ሠራሁ፣ እባክህ ስለ ዝሙቴ ይቅር በለኝ” አላለችም። ይልቁንስ እንዲህ አለች፦ “እባክህ ከኃጢአቶቼ አድነኝ። ኃጢአቶቼን ብትዋጅ እድናለሁ። ካልሆነ ወደ ገሃነም እሄዳለሁ። ቤዛነትህን እፈልጋለሁ። የእግዚአብሔርን ፍቅር ያስፈልገኛል፣ እናም ለእኔ እንዲራራልኝ እፈልጋለሁ።” ዓይኖችዋን ጨፍና ኃጢአተኝነትዋን ተናዘዘች።
ኢየሱስም ጠየቃት፦ “እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን?” እርስዋም መለሰች፦ “ጌታን ሆይ፥ አንድ ስንኳ ማንም የለም።”
ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “እኔም አልፈርድብሽም።” ኢየሱስ አላወገዛትም ምክንያቱም በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀበት ጊዜ ኃጢአቷን ሁሉ ስለወሰደ ነው፣ እርስዋም ቀድሞውኑም ተቤዥታለች። አሁን፣ ለኃጢአቶችዋ ሊፈረድበት ያለው ኢየሱስ እንጂ እርስዋ አይደለችም።
 
 
እርሱም አላት፦ “እኔም አልፈርድብሽም።”
 
እርስዋ በኢየሱስ የተወገዘች ነበርን?
አይ
 
ይህች ሴት በኢየሱስ ውስጥ በመዳን የተባረከች ነበረች። ከኃጢአቶችዋ ሁሉ ተቤዣለች። ጌታችን ኢየሱስ ኃጢአታችንን ሁሉ እንደቤዠልን እና ሁላችንም ጻድቃን እንደሆንን ይነግረናል።
እርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ ይነግረናል። ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በጥምቀቱ ኃጢአታችንን አስወገደ፣ ከዚያም በመስቀል ላይ ለኃጢአታችን ክፍያ ሞተ። በመጥመቁ እና በመስቀል ላይ ያለውን ፍርድ ቤዛነት የሚያምኑትን ሁሉ እንደዋጀ በግልፅ ይነግረናል። ሁላችንም የተጻፈው የኢየሱስ ቃል ያስፈልገናል፣ ቃሉንም አጥብቀን መያዝ ያስፈልገናል። ያን ጊዜ ሁላችንም በቤዛነት እንባረካለን።
“እግዚአብሔር፣ በፊትህ ምንም ጠቀሜታ የለኝም። ምንም ችሎታ የለኝም። ከኃጢአቶቼ በቀር የማሳይህ ምንም ነገር የለም። ኢየሱስ የቤዛነት ጌታዬ እንደሆነ ግን አምናለሁ። በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ በጥምቀቱ ኃጢአቶቼን ሁሉ ወሰደ እና ኃጢአቶቼን ሁሉ በመስቀል ላይ አስተሰረየባቸው። በጥምቀቱና በደሙም ኃጢአቶቼን በሙሉ ወሰደ። በአንተ አምናለሁ፣ ጌታ ሆይ።”
የምትድኑበት መንገድ ይህ ነው። ኢየሱስ ‘አይኮንነንም።’ የእግዚአብሔር ጻድቅ ልጆች እንድንሆን መብት ሰጠን፦ በውሃ እና በመንፈሱ ቤዛነት ለሚያምኑ።
ውድ ወዳጆች! ሴትየዋ ተቤዥታለች። በምንዝር የተያዘችው ሴት በጌታችን በኢየሱስ ፊት በቤዛነት ተባርካለች። እኛም ደግሞ እንደዚያ ልንባረክ እንችላለን። ኃጢአቶቹን አውቆ እግዚአብሔር እንዲራራለት የሚጠይቅ ማንኛውም ሰው፣ በኢየሱስ በውሃውና በመንፈሱ ቤዛነትም የሚያምን ማንኛውም ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ የቤዛነትን በረከት ይቀበላል። በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአቱን የሚያውቅና የሚቀበል ሰው ሊድን ይችላል። ኃጢአት የሠራና የራሱን ኃጢአት የማይገነዘብ ሰው በመቤዠት ሊባረክ አይችልም።
ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአቶች ወሰደ (ዮሐንስ 1፡29)። በዓለም ላይ የሚኖር ማንኛውም ኃጢአተኛ በኢየሱስ ቢያምን መዳን ይችላል። ኢየሱስ ለሴቲቱ “እኔም አልፈርድብሽም” አላት። ኢየሱስ እንዳላወገዛት አለ፣ ምክንያቱም ኃጢአቶችዋ ሁሉ አስቀድሞ በጥምቀቱ ወደ እርሱ ተላልፈው ስለነበር ኃጢአታችንን ሁሉ በራሱ ላይ ወስዶ፣ በእኛ ፈንታ ሊፈረድበት ነበርና።
 
 
እኛም ደግሞ በኢየሱስ ፊት መቤዠት አለብን
 
የሚበልጠው የትኛው ነው የእግዚአብሔር ፍቅር ወይስ የእግዚአብሔር ፍርድ?
የእግዚአብሔር ፍቅር
 
ፈሪሳውያን በእጃቸው ድንጋይ ይዘው፣ እንዲሁም የዛሬው የሃይማኖት መሪዎች፣ ሕጉን እንደ ፊደሉ ይተረጉማሉ። ሕጉ አታመንዝሩ ስለሚለን፣ ኃጢአት የሚሠራ ሰው በድንጋይ ተወግሮ እንደሚሞት ያምናሉ። አታመንዝር ብለው ይመስላሉ ነገር ግን ሴቶችን በፍትወት ይመለከታሉ። ከኃጢያት ሊዋጁ ወይም ሊድኑ አይችሉም። ፈሪሳውያንና ጸሐፍቶች የዚህ ዓለም ሞራሊስቶች ነበሩ። እነዚህ ኢየሱስ የጠራቸው አልነበሩም። እነዚህ ሰዎች ከእርሱ “እኔም አልፈርድብሽም” የሚለውን ቃል በጭራሽ አልሰሙም።
እነዚያን የሚያስደስቱ ቃሎች የሰማችው በምንዝር የተያዘችው ሴት ብቻ ነበረች። በእርሱ ፊት እውነተኞች ከሆናችሁ እናንተም ደግሞ እንደ እርስዋ መባረክ ትችላላችሁ። “እግዚአብሔር ሆይ፣ በሕይወቴ ሁሉ አመንዝራለሁ። ብዙ ጊዜ አመንዝሬ ስለነበር እንደዚህ እያደረግኩ እንደሆነ እንኳን አላወቅሁም። እኔ በእያንዳንዱ ቀን ይህንን ኃጢአት ብዙ ጊዜ አደርገዋለሁ።”
በሕግ ፊት ስንቆም እና መሞት ያለብን ኃጢአተኞች መሆናችንን ስንቀበል፣ በእውነት በእግዚአብሔር ፊት ቆመን፣ እንዳለን ራሳችንን ስናውቅ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔ እንዲህ ነኝ። እባክህ አድነኝ” ብለን ስንናገር። እግዚአብሔር በቤዛነት ይባርከናል።
የኢየሱስ ፍቅር የሆነው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የእግዚአብሔርን ትክክለኛ ፍርድ አሸንፏል። “እኔም አልፈርድብሽም።” እርሱ አይኮንነንም፣ እርሱ “ተቤዣችኋል” ይለናል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የርህራሄ አምላክ ነው። ከዓለም ኃጢአቶችም ሁሉ አድኖናል።
የእኛ እግዚአብሔር የፍትህ አምላክና የፍቅር አምላክ ነው። የውሃውና የመንፈስ ቅዱሱ ፍቅርም፣ ከእግዚአብሔር ፍርድ እንኳን የበለጠ ነው።
 
 

የኢየሱስ ፍቅር ከእግዚአብሔር ፍትህ የበለጠ ነው

 
እርሱ ሁላችንንም የዋጀን ለምንድነው?
ፍቅሩ የእሱ ፍትህ ስለሚበልጥ ነው።
 
እግዚአብሔር ፍትሁን ለማሟላት ፍርዱን ቢፈጽም ኖሮ፣ ኃጢአተኞችን ሁሉ ፈርዶ ወደ ገሃነም በላካቸው ነበር። ነገር ግን ከፍርድ ያዳነን የኢየሱስ ፍቅር ስለሚበልጥ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ኢየሱስን ላከው። ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ ወስዶ ስለ ሁላችንም ፍትሃዊ ፍርድን ተቀበለ። አሁን፣ ኢየሱስን አዳኙ አድርጎ የሚያምን ማንኛውም ሰው የእርሱ ልጅና ጻድቅ ይሆናል። ፍቅሩ የእሱ ፍትህ በላይ ስለሚበልጥ ሁላችንንም አዳነን።
እግዚአብሔር በፍትህነቱ ብቻ አይፈርድብንም ስለሆነ እንደምናመስግነው አለብን። ልክ ኢየሱስ ለጻፎች፣ ለፈሪሳውያን እና ለደቀ መዛሙርቶቻቸው እንደነገራቸው፣ እግዚአብሔር የሚፈልገው ምህረትንና እግዚአብሔርን ማወቅ እንጂ መባዎቻችንን አይደለም። አንዳንድ ሰዎች በየቀኑ ላም ወይም ፍየል ገድለው በእግዚአብሔር ፊት አቅርበው ይጸልያሉ፦ “እግዚአብሔር በየቀኑ ኃጢአቴን ይቅር በላቸው።” እግዚአብሔር የሚፈልገው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ያለንን አመኔታ እንጂ ቁርባኖቻችንን አይደለም። እንድንዋጅ እና ከኃጢአታችን እንድንድን ይፈልጋል። እርሱ ፍቅሩን ሊሰጠን ይፈልጋል እናም እምነታችንን ሊቀበል ይፈልጋል። ይህን ሁሉ ተረድተሃል? ኢየሱስ ፍጹም የሆነውን መዳንን ሰጥቶናል።
ኢየሱስ ኃጢአትን ይጠላል፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር መልክ ለተፈጠሩት ለሰዎች የሚቃጠል ፍቅር አለው። እኛን የእግዚአብሔር ልጆች ሊያደርገን ከዘመን መጀመሪያ በፊት ወስኖ ነበር፣ እና ኃጢአታችንን ሁሉ በጥምቀቱ እና በደሙ ደምስሶአል። እግዚአብሔር እኛን ሊዋጀን እና በኢየሱስ ሊያለብሰን የራሱ ልጆች ሊያደርገን የፈጠረን ነው። ይህ ለእኛ ያለው ፍቅር ነው፣ የእርሱ ፍጥረታት።
እግዚአብሔር እንደ ፍትሐዊ ሕጉ ብቻ ቢፈርደን፣ ኖሮ እኛ ኃጢአተኞች ሁላችንም በሞትን ነበር። እግዚአብሔር ግን በልጁ ጥምቀትና በመስቀሉ ላይ በፍርዱ አዳነን። ይህንን ታምናላችሁ? ይህንን ከብሉይ ኪዳን እናረጋግጥ።
 
 
አሮን በለየመስዋዕት በግው ላይ እጆቹን ጫነ 
 
ወኪላቸው ሆኖ የእስራኤልን ኃጢአቶች ወደ ሕያው ፍየል ያስተላለፈው ማነው?
ሊቀ ካህናቱ
 
የብሉይ ኪዳን እጆችን በመጫን እና በአዲስ ኪዳን ጥምቀት የዚህ ዓለም ኃጢአቶች ሁሉ ተሰርዘዋል። በብሉይ ኪዳን የእስራኤሎች ዓመታዊ ኃጢአቶች በሙሉ እጆችን መጫን አንዳች ነውሮች በሌሉበት ሕያው ፍየል ራስ ላይ በጫነው ሊቀ ካህናቱ አማካይነት ማስተስረያ አግኝተዋል።
“አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፥ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ መተላለፋቸውንም ሁሉ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይናዝዛል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፥ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል” (ዘሌዋውያን 16፡21)።
በብሉይ ኪዳን ዘመን የማስተሰረያ የተቀበሉት በዚህ መንገድ ነበር። ከዕለት ተዕለት ኃጢአት ለመቤዠት አንድ በግ ወይም ፍየል ያለ እንከን ወደ ማደሪያው ድንኳን አምጥቶ በመሠውያው ላይ አቀረበው። እጆቹን መባው ራስ ላይ ይጭናል፣ ከዚያም ኃጢአቶቹ ወደ መሥዋዕቱ ይተላልፈው። ከዚያም መሥዋዕቱ ተገደለ እና ደሙ በካህኑ በመሠዊያው ቀንዶች ላይ ተቀመጠ።
በመሠውያው በአራቱ ማዕዘናት ላይ ቀንዶች ነበሩ። እነዚህ ቀንዶች የሚያመላክቱት በዮሐንስ ራእይ 20፡12 ላይ የተጻፉትን የምግባር መጽሐፎች ነው። ቀሪው የመሥዋዕቱ ደምም በመሬቱ ላይ ይረጫል። መሬቱ የሚያመላክተው የሰውን ልብ ነው፣ ምክንያቱም ሰው የተፈጠረው ከአፈር ነውና። ሕዝቡ የዕለት ተዕለት ኃጢአታቸውን ያስተሰርዩት በዚህ መንገድ ነው።
ነገር ግን እነርሱ በየቀኑ የኃጢአት ቁርባኖችን ማቅረብ አልቻሉም። ስለዚህ እግዚአብሔር ለአመቱ ኃጢአቶች በአመት አንድ ጊዜ የማስተሰረያ እንዲያገኙ ፈቀደላቸው። ይህም በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን፣ ማስተስረያ ቀን ነበር። በዚያ ቀን፣ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ተወካይ የሆነው ሊቀ ካህናቱ፣ ሁለት ፍየሎችን አምጥቶ፣ የሕዝቡን የአንድ ዓመት ኃጢአት ሁሉ ወደ እነርሱ እንዲተላልፈው እጆችን ጫነባቸውና፣ ለእስራኤል ሕዝብ የማስተሰረያቸው ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ።
“አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፥ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ፥ መተላለፋቸውንም ሁሉ፥ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይናዝዛል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል” (ዘሌዋውያን 16፡21)።
እግዚአብሔር አሮንን የእስራኤል ሊቀ ካህናቱ አድርጎ ሾመው። ሁሉም ሰው ለብቻው በመሥዋዕቱ ላይ እጆቹን ከመጫን ይልቅ፣ ሊቀ ካህናቱ የእስራኤላውያን ሁሉ ተወካይ በመሆን፣ የአንድ ዓመት ኃጢአቶችን ለማስተሰረይ በሕያው ፍየል ራስ ላይ እጆቹን ጫነ።
እርሱ በእግዚአብሔርም ፊት የእስራኤልን ኃጢአት ሁሉ ይተርክል ነበር፦ “እግዚአብሔር ሆይ፣ የእስራኤል ልጆችህ ኃጢአትን ሰርተዋል። ጣዖታትን አምልከናል፣ የሕግህን አንቀጾች ተላልፈናል፣ ስምህን በከንቱ ጠርተናል፣ ሌሎች ጣዖታትን ሰርተን ከአንተ ይልቅ ወደናቸዋል። የሰንበትን ቀን ቅዱስ አድርገን አልጠበቅንም፣ ወላጆቻችንን አላከበርንም፣ ገድለናል፣ አመንዝረናል፣ ሰርቀናል… ምቀኝነትና ጥልን ተግብረናል።”
እርሱ ኃጢአቶችን ሁሉ ዘረዘረ። “እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ሕዝብም ሆነ እኔ ከሕግህ አንዳቸውንም መጠበቅ አልቻልንም። ከእነዚህ ሁሉ ኃጢአቶች ለመዳን እጆቼን በዚህ ፍየል ራስ ላይ ጭኜ እነዚያን ኃጢአቶች በሙሉ ወደ ፍየሉ አስተላልፈውለሁ።” ሊቀ ካህናቱ በእስራኤላውያንን ፋንታ እጆቹን በቁርባኑ ላይ ጭኖ ኃጢአቶቹን ሁሉ በመሥዋዕቱ ራስ ያስተላልፈው። እጆችን መጫን ማለት ኃጢአት ‘ማስተላለፍ’ ማለት ነው (ዘሌዋውያን 1፡1-4፣ 16፡20-21)።
 
በብሉይ ኪዳን ዘመን የማስተሰረያ የተፈጸመው እንዴት ነበር?
በኃጢአት መስዋዕት ራስ ላይ እጆችን በመጫን
 
እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ የኃጢአት መሥዋዕት ሥርዓትን የሰጣቸው ኃጢአታቸውን ሁሉ እንዲያስተላልፉና እንዲቤዠዋቸው ነው። እርሱ ነውር የሌለበት የኃጢአት መስዋዕት መቅረብ እንዳለበትም ተናግሯል፣ ለእስራኤል ሕዝብ ለኃጢአታቸው ሁሉ በሚያቀርበው የኃጢአት ራስ ላይ እጆችን መጫን እና የኃጢአት ቁርባኑም በግለሰቡ ፋንታ መሞት እንዳለበት በግልጽ ዘረዘረ።
ማስተስረያ ቀን የኃጢአት መስዋዕት ይታረድና ደሙ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ተወስዶ በስርየት መክደኛው ላይ ሰባት ጊዜ ይረጫል። በዚህም የእስራኤል ሕዝብ በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን የአንድ ዓመት ኃጢአት ያስተሰርይ ነበር።
ሊቀ ካህናቱ መሥዋዕቱን ለማቅረብ ብቻውን ወደ ቅዱስ ቦታ ገባ፣ ሰዎች ግን በውጭ ተሰብስበው፣ ሊቀ ካህናቱ በስርየት መክደኛው ላይ ደሙን ሲረጭ በኤፉድ ካባው ላይ ያለውን የወርቅ ደወል ድምፅ ሰባት ጊዜ እንዲደውል ያዳምጡ ነበር። በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን ኃጢአቶቻቸው ሁሉ ማስተስረያ መሆኑን አውቀው ይደሰታሉ። የወርቅ ደወል ድምፅ አስደሳች የወንጌል ድምፅ ነበር።
ኢየሱስ የሚወደው አንዳንድ የተመረጡ ሰዎችን ነው፣ የሚያድናቸውም እነርሱን ብቻ ነው የሚለው አባባል እውነት አይደለም። ኢየሱስ በጥምቀቱ የዓለምን ኃጢአት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አስወገደ። ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊያደርሰን ፈለገ። ኃጢአቶቻችን በየቀኑ ሊዋጁ አይችሉም፤ እነርሱ ለአንዴና ለመጨረሻ ድነዋል።
በብሉይ ኪዳን ስርየት የሚሰጠው እጆችን በመጫን እና በኃጢአት መስዋዕት ነው። አሮን በእስራኤላውያን ሁሉ ፊት እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ጭኖ ሕዝቡ በዓመቱ ውስጥ የሠራቸውን ኃጢአቶች በሙሉ ዘረዘረ። በእስራኤሎች ሁሉ ፊትም ኃጢአቶችን ወደ ፍየሉ አስተላለፈ። ሊቀ ካህናቱ በሚለቀቀው ፍየል ላይ እጆቹን ከጫነ በኋላ የሕዝቡ ኃጢአቶች የት ናቸው? ሁሉም ወደ ፍየሉ ተላልፈው ነበር።
ከዚያም ፍየሉ ‘በተስማሚ ሰው’ ተመርታ ተወሰደች። የእስራኤሎችን ኃጢአቶች በሙሉ የተሸከመው ፍየል ውሃና ሳር ወደሌለበት ምድረ በዳ ተወሰደ። ከዚያም ፍየሉ በምታቃጥለው ጸሐይ እየነደደ በምድረ በዳ ይቅበዘበዝና በመጨረሻም ይሞታል። ፍየሉ የሞተው ለእስራኤላውያን ኃጢአቶች ነው።
ይህ የእግዚአብሔር ፍቅር ማለትም የቤዛነት ፍቅር ነው። በዚያም ወራት የአንድ ዓመት ኃጢአታቸውን የሚያስተሰርዩት በዚህ መንገድ ነበር። እኛ የምንኖረው ግን በአዲስ ኪዳን ዘመን ነው። ኢየሱስ ወደ ዓለማችን ከመጣ ወደ 2,000 አካባቢ አመታት ሆነውታል። እርሱ መጥቶ በብሉይ ኪዳን የተናገረውን ትንቢት ፈጸመ። መጥቶም ከኃጢአቶቻችን ሁሉ ዋጀን።
 
 
ሁላችንንም ለመዋጀት
 
‘የኢየሱስ’ ትርጉም ምንድነው?
እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው የሚያድነው አዳኝ
 
ማቴዎስ 1ኛን እናንብብ።
“እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ። ልጅም ትወልዳለች፥ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ” (ማቴዎስ 1፡20-21)።
በሰማይ ያለው አባታችን የዓለምን ኃጢአት ሁሉ ለማጠብ ልጁን ወደዚህ ዓለም ለመላክ ማርያምን ሥጋ ተዋሰ። መልአክን ወደ ማርያም ልኮ እንዲህ አለው፦ “እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።” ወልድ በማርያም በኩል መጥቶ አዳኝ ይሆናል ማለት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት ሕዝቡን ከኃጢአቶቻቸው የሚያድን ማለትም አዳኝ ማለት ነው።
ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ የወሰደበት መንገድ በዮርዳኖስ ወንዝ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት ነው። እርሱ በመጥምቁ ዮሐንስ ተጠመቀ፣ የዓለም ኃጢአቶች በሙሉ ወደ እርሱ ተላለፉ። እስቲ ማቴዎስ 3፡13-17ን እናንብብ።
“ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር። ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፥ እንደዚህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት። ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።”
ኢየሱስ ሁላችንንም ከኃጢአታችን ሁሉ ሊያድነን ወደ መጥምቁ ዮሐንስ ሄደ።
ወደ ውሃው ውስጥ ገባ እና በዮሐንስ ፊት ራሱን ዝቅ አደረገ። “ዮሐንስ፣ አሁን አጥምቀኝ። እንደዚህ ለእኛ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ተገቢ ነው። እኔ የዓለምን ኃጢአት ሁሉ እንዳስወግድ እና ኃጢአተኞችን ሁሉ ከኃጢአታቸው እንዳዳነኝ፣ ኃጢአታቸውንም በጥምቀት ማስወገድ አለብኝ። አሁኑኑ አጥምቀኝ! ፍቀድ!”
ስለዚህ፣ እንደዚህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ተገቢ ነበር። ኢየሱስ በመጥምቁ ዮሐንስ ተጠመቀ። በዚያች ቅጽበትም ኃጢአታችንን ሁሉ የዋጀው የእግዚአብሔር ጽድቅ በሙሉ ተፈጸመ።
እርሱ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ የወሰደው በዚህ መንገድ ነው። የእናንተም ኃጢአቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል። ይህ ይገባችኋልን?
በኢየሱስ ጥምቀትና መንፈስ ቤዛነት አምናችሁ ዳኑ።
 
ጽድቅ ሁሉ የተፈጸመው እንዴት ነበር?
በኢየሱስ ጥምቀት አማካይነት
 
እግዚአብሔር በመጀመሪያ ለእስራኤል ተስፋ ሰጥቶአል እንደዚህ የእስራኤል ሕዝብ በዚያ አንድ ዓመት ውስጥ የሠሩትን ኃጢአት ሁሉ በእጆችን መጫን እና በኃጢአት መስዋዕት መንገድ እንደሚያጠብ ተስፋ ሰጥቶአል። ነገር ግን፣ ሁሉም ሰው በፍየሉ ራስ ላይ በተናጠል እጆችን መጫን ስለማይቻል፣ እግዚአብሔር አሮንን ሊቀ ካህናቱ እንዲሆን ቀደሰው ይህም ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፋንታ መሥዋዕቱን ያቀርብ ዘንድ ነው። ስለዚህም የዓመት የእስራኤል ሕዝብ ኃጢአትን በሙሉ በአንድ ጊዜ ለኃጢአት በቀረበው ቁርባን ራስ ላይ አስተላለፈ። ይህ የእግዚአብሔር ጥበብና የቤዛነቱ ሐይል ነበር። እግዚአብሔር ጠቢብና አስገራሚ ነው።
እግዚአብሔር መላውን ዓለም ለማዳን ልጁን ኢየሱስን ላከው። ስለዚህ የኃጢአት መስዋዕት ተዘጋጅቶ ነበር። አሁን፣ እጆችን በኢየሱስ ራስ ላይ የሚጭን እና የአለምን ኃጢያት ሁሉ በእርሱ ላይ የሚያስተላልፍ፣ የሰው ልጆች ሁሉ ተወካይ መኖር ነበረበት። ይህ ተወካይ መጥምቁ ዮሐንስ ነበር። በማቴዎስ 11፡11 ላይ፣ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ሁሉ ተወካይ በኢየሱስ ፊት ልኳል።
የሰው ልጅ የመጨረሻው ሊቀ ካህናቱ የሆነው መጥምቁ ዮሐንስ ነበር። በማቴዎስ 11፡11 ላይ እንዲህ ተጻፈ፦ “ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም።” እሱ ብቸኛው የሰው ልጅ ተወካይ ነው። እግዚአብሔር ኢየሱስን ሊያጠምቅና የዓለምን ኃጢአቶች ሁሉ ወደ እርሱ እንዲያስተላልፍ ለመፈጸም ዮሐንስን እንደ ሰው ልጆች ሁሉ ተወካይ ላከ።
በምድር ላይ ስምንት ቢሊዮን ሰዎች አሁን ወደ ኢየሱስ ቢሄዱ እና እያንዳንዱ ኃጢአታቸውን ለእርሱ ለማስተላለፍ እጆቻቸውን በኢየሱስ ላይ ቢጭኑ፣ በራሱ ላይ ምን ይደርስ ይሆን? በዚህ ዓለም ላይ የሚኖረው ከስምንት ቢሊዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ እጆቻቸውን በኢየሱስ ላይ ቢጭኑ ደስ የሚል ትዕይንት አይታይም። አንዳንድ ጥልቅ ስሜት ያላቸው ሰዎች የኢየሱስ ጸጉሩ ሁሉ እስኪወድቅ ድረስ በጣም ተጭነው ሊጫኑ ይችላሉ። እግዚአብሔር በጥበቡ ዮሐንስን ወኪላችን ሆኖ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ወደ ኢየሱስ እንዲያስተላልፍ ዮሐንስን ሾመው።
በማቴዎስ 3፡13 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፦ “ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።” ይህ የሆነው ኢየሱስ 30 አመት በሆነው ጊዜ ነበር። ኢየሱስ የተገረዘው በተወለደ በ8 ቀኑ ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ 30 ዓመት እስኪሆነው ድረስ ስለ እርሱ የተጻፉት ነገሮች ጥቂቶች ናቸው።
ኢየሱስ ሰማያዊ ሊቀ ካህናቱ ለመሆን 30 ዓመት እስኪሆነው ድረስ መጠበቅ የነበረበት ምክንያት ብሉይ ኪዳንን ለመፈጸም ነው። በኦሪት ዘዳግም ውስጥ፣ እግዚአብሔር ለሙሴ ሊቀ ካህናቱ ሊቀ ካህናትን ከማገልገል በፊት ቢያንስ 30 ዓመት መሆን እንዳለበት ነገረው። ኢየሱስ ሰማያዊ ሊቀ ካህናቱ ነበር። ይህንን ታምናላችሁን?
በአዲስ ኪዳን የማቴዎስ 3፡13-14 ላይ እንዲህ ይላል፦ “ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?፥ ብሎ ይከለክለው ነበር።” የሰው ልጅ ተወካይ ማን ነው? አመጥምቁ ዮሐንስ ነው። ታዲያ የሰማይ ተወካይ ማነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ተወካዮቹ ተገናኙ። ታዲያ ማን ከፍ ያለ ነው? እርግጥ ነው፣ የሰማይ ተወካይ።
በዚያ ዘመን ለነበሩት የሐይማኖት መሪዎች “የእፉኝት ልጆች! ንስሐ ግቡ!” በማለት በድፍረት የጮኸው መጥምቁ ዮሐንስ ድንገት በኢየሱስ ፊት ትሁት ሆነ። “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?”
በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “አሁንስ ፍቀድልኝ፥ እንደዚህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው።” ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም የመጣው የእግዚአብሔርን ጽድቅ ለመፈጸም ነው፣ እናም በመጥምቁ ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ተፈጸመ።
“ያን ጊዜ ፈቀደለት። ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።”
ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ የሆነው ይህ ነው። ኢየሱስ በመጥምቁ ዮሐንስ በተጠመቀና የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ በወሰደ ጊዜ የሰማይ ደጆች ተከፈቱ።
“ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ወረራለች፥ ወራሪችም ይናጠቋታል” (ማቴዎስ 11፡12)።
ነቢያት ሁሉና የእግዚአብሔር ሕግ እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ። “ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ወረራለች፥ ወራሪችም ይናጠቋታል።” በኢየሱስ ጥምቀት የሚያምን ሁሉ ያለ ምንም ልዩነት መንግሥተ ሰማይ መግባት ይችላል።
 
 
“እኔም አልፈርድብሽም”
 
ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለምን ተፈረደበት?
የእኛን ኃጢአቶች በሙሉ ስለወሰደ።
 
ኢየሱስ በመጥምቁ ዮሐንስ ተጠምቆ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ወሰደ። በኋላም በመንዝር ለተያዘችው ሴት “እኔም አልፈርድብሽም” አላት። ኢየሱስ ሴቲቱን ያልኮነነው በዮርዳኖስ የዓለምን ኃጢአቶች ሁሉ ስለወሰደ እና ለእነዚህ ኃጢአቶች መፈረድ የነበረበት ሴቲቱ ሳትሆን ኢየሱስ ራሱ ስለነበረ ነው።
ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ደመሰሰ። ‘የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና’ (ሮሜ 6፡23) ስለሆነ በመስቀል ላይ የሚደርስበትን ስቃይ ኢየሱስ ምን ያህል ፈርቶ እንደነበር ማየት እንችላለን። እግዚአብሔር ይህንን ፍርድ እንዲያስወግድለት በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሦስት ጊዜ ጸልዮ ነበር። ኢየሱስ የሰው ሥጋ ነበረው ስለዚህም ሕመሙን እንደፈራው መረዳት ይቻላል። ኢየሱስ ፍርዱን ለመፈጸም መድማት ነበረበት።
በብሉይ ኪዳን የነበረው የኃጢአት መስዋዕት ለኃጢያት ክፍያ ደም መፋሰስ እንዳለበት ሁሉ እርሱ በመስቀል ላይ መሰዋት ነበረበት። ቀደም ብሎ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ወስዶዋል፣ አሁን ለእኛ ቤዛነት ሲል ሕይወቱን መስጠት ነበረበት። ኢየሱስ በእግዚአብሔር ፊት ፍርድን መቀበል እንደነበረበት አወቀ።
ኢየሱስ በልቡ ውስጥ ምንም ኃጢአት አልነበረበትም። ነገር ግን ሁሉም ኃጢአቶች በጥምቀቱ ወደ ኢየሱስ ሲተላለፉ፣ እግዚአብሔር አሁን በልጁ ላይ መፍረድ ነበረበት። ስለዚህም፣ በመጀመሪያ፣ የእግዚአብሔር ፍትህ ተፈፀመ እና በሁለተኛ፣ ደረጃ እርሱ ለመዳንታችን ሲል ፍቅሩን ሰጠን። ስለዚህ ኢየሱስ በመስቀል ላይ መኮነን ነበረበት።
“እኔም አልኮንንሽም፣ አልፈርድብሽምም።” አቅደንም ሆነ ሳናቅድ፣ አውቀንም ሆነ ሳናውቅ የሠራናቸው ኃጢአቶቻችን በሙሉ በእግዚአብሔር ሊፈረድባቸው ይገባ ነበር።
እግዚአብሔር በእኛ ላይ አልፈረደም፣ ነገር ግን በጥምቀቱ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ በወሰደው በኢየሱስ ላይ ፈረደ። እግዚአብሔር በፍቅሩ እና በርህራሄው ምክንያት በኃጢአተኞች ላይ ሊፈርድ አልፈለገም። ኢየሱስ ጥምቀቱና በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደሙ እርሱ ለእኛ ያለው የቤዛነት ፍቅሩ ነበር። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐንስ 3፡16)።
ፍቅሩን የምናውቀው በዚህ መንገድ ነው። ኢየሱስ በምንዝር የተያዘችውን ሴት አልኮነናትም።
እርስዋ በምንዝርና ድርጊት ተይዛ ስለነበር ኃጢአተኛ መሆንዋን አውቃለች። እርስዋ በልቧ ውስጥ ኃጢአት የነበራት ብቻ ሳይሆን በሥጋዋም ኃጢአትን ፈጽማ ነበር። ኃጢአትዋን የምትክድበት ምንም መንገድ አልነበረም። ነገር ግን ኢየሱስ ኃጢአቶችዋን በሙሉ እንደወሰደ ስላመነች ዳነች። እኛም በኢየሱስ ቤዛነት ብናምን እንድናለን። ይህንን እመኑ! ለራሳችን ጥቅም ነው።
 
በእጅጉ የተባረኩትእነማን ናቸው?
ኃጢአት የሌለበት ሰው
 
ሰዎች ሁሉ ኃጢአትን ይሠራሉ። ሁሉም ሰው ምንዝር ይፈጽማል። ነገር ግን ሰዎች ሁሉ ስለሠሩት ኃጢአቶቻቸው አልተፈረደባቸውም። ሁላችንም ኃጢአት ሠርተናል፣ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት የሚያምኑ ሰዎች በልቦቻቸው ኃጢአት አልባ ናቸው። በኢየሱስ ማዳን የሚያምኑት በጣም ደስተኛ ሰዎች ናቸው። ከኃጢአቶቻቸው ሁሉ የዳኑ ሰዎች፣ አሁን በኢየሱስ ጻድቃን የሆኑ እጅግ የተባረኩ ናቸው።
እግዚአብሄር በሮሜ 4፡7 ላይ ስለ ደስታ ይነግረናል፦ “ዓመፃቸው የተሰረየላቸው (ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል) ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው።” ሁላችንም እስከምንሞትበት ጊዜ ድረስ ኃጢአት እንሠራለን። በእግዚአብሔር ፊት አክብሮት የጎደለን ነን እና ያልተሟላ ነን። የእግዚአብሔርን ሕግ ብናውቅም ኃጢአትን እንቀጥላለን። እኛ በጣም ደካሞች ነን።
እግዚአብሔር ግን በአንድያ ልጁ ጥምቀትና ደም አድኖን ለእናንተና ለእኔ ዳግመኛ ኃጢአተኞች እንዳይደለንና አሁን በፊቱ ጻድቃኖች መሆናችንን ነገረን። የእርሱ ልጆች እንደሆንንም ነገረን።
የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የዘላለም ቤዛነት ወንጌል ነው። ይህንን ታምናላችሁን? ለሚያምኑት፣ ጻድቃን፣ ድነዋል እና ልጆቹ መሆናቸውን እውቅና ሰጥቷል። በዚህ አለም ላይ እጅግ ደስተኛው ሰው ማነው? ያመነና የዳነ ሰው ነው። ድናችኋልን?
ኢየሱስ ኃጢአቶቻችሁን መውሰድን ረሳው? አይ፣ ኃጢአቶቻችሁን ሁሉ በጥምቀቱ ወሰደ። ይህንን እመኑ። እመኑና ከኃጢአቶቻችሁ ሁሉ ተዋጁ።
 
 
ልክ በመጥረጊያ እንደተጠረገ ያህል
 
ኢየሱስ የወሰደው ምን ያህል ኃጢአት አስወገደ?
የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ
 
ዮሐንስ 1፡29ን እናንብብ። “በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ዮሐንስ 1፡29)።
“እነሆ፣ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ!”
መጥምቁ ዮሐንስ በዮርዳኖስ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ አስተላለፈ። በማግስቱ፣ መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ያስወገደ የእግዚአብሔር በግ መሆኑን መስክሯል። እርሱ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ በጫንቃዎቹ ተሸከመ።
ሁሉም የዓለም ኃጢአቶች ማለት የሰው ልጅ በዚህ ዓለም፣ ዓለም ከፍጥረት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ የሚፈጽመውን ኃጢአት ሁሉ ማለት ነው። የዛሬ 2,000 ዓመት ገደማ፣ ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት ሁሉ አስወግዶ ዋጀን። እንደ እግዚአብሔር በግ፣ ኢየሱስ ሁሉንም ኃጢአቶቻችንን ወሰደ እና ስለ እኛ ተፈርዶበታል።
እኛ ሰዎች የምንሠራው ማንኛውም ኃጢአት ወደ ኢየሱስ ተላለፈ። እርሱም የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ የወሰደ የእግዚአብሔር በግ ሆነ።
ኢየሱስ አዳኝ ሆኖ፣ የዓለምን ኃጢአተኞች በሙሉ የሚያድን ሰው ሆኖ ወደዚህ ዓለም መጣ። እኛ ደካማ ስለሆንን ኃጢአትን እንሠራለን፣ ምክንያቱም እኛ ክፉዎች ነን፣ ምክንያቱም እኛ አላዋቂ ነን፣ ምክንያቱም ከንቱ ነን፣ እና ያልተሟላ ስለሆንን። በዮርዳኖስ ጥምቀቱ በኢየሱስ ራስ ላይ እነዚህ ሁሉ ኃጢአቶች ተላልፈዋል። እርሱም በመስቀል ላይ በሥጋው ሞት ሁሉንም ጨረሰ። የተቀበረው ግን ከ3 ቀን በኋላ ከሞት ተነስቷል።
እርሱ አሁን የኃጢአተኞች ሁሉ አዳኝ፣ ቪክቶር አድራጊና ፈራጅ ሆኖ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦዋል። እርሱ እንደገና እና እንደገና ሊቤዠን አያስፈልገውም፣ እኛ ለመዳን ማድረግ ያለብን ኢየሱስ ያደረገውን ማመን ብቻ ነው። የሚያምኑ ሰዎች የዘላለም ሕይወት ይጠብቃቸዋል፣ የማያምኑ ሰዎች ግን ጥፋት ይጠብቃቸዋል። ሌላ ምርጫ የለም።
ኢየሱስ ሁላችሁንም አዳናችሁ። እናንተ በምድር ላይ እጅግ ደስተኛ ሰዎች ናችሁ። በድክመትህ ምክንያት ወደፊት የምትፈጽማቸው ኃጢአቶች ሁሉ እርሱ ግን ሁሉንም ወሰደ።
በልባችሁ ውስጥ የቀረ አንዳች ኃጢአት አለን? —የለም።—
ኢየሱስ ሁሉንም ወስዶታል? —አዎን! ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን ሁሉ ወስዶታል።—
ሰዎች ሁሉ ተመሳሳይ ናቸው። ማንም ከጎረቤታቸው የተቀደሰ የለም። ነገር ግን ብዙ ሰዎች ግብዞች ስለሆኑ በእርግጥ ኃጢአተኞች አይደሉም ብለው ያስባሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን እነሱም ኃጢአተኞች ናቸው። ይህ ዓለም ኃጢአትን የሚንከባከበው የግሪን ሃውስ ነው።
ሴቶች ከቤታቸው ሲወጡ ቀይ ሊፕስቲክ ለብሰው፣ ፊታቸውን በዱቄት፣ ፀጉራቸውን ይከርክማሉ፣ ጥሩ ልብሶችን ይለብሳሉ፣ ተረከዙን ይለብሳሉ። ወንዶችም ፀጉራቸውን ለመቁረጥ ወደ ፀጉር አስተካካዩ ይሄዳሉ፣ ራሳቸውን ያዘጋጃሉ፣ ንጹህ ሸሚዝ እና ፋሽን ክራባት ይለብሳሉ፣ ጫማቸውን ያበራሉ።
ነገር ግን በውጭው ላይ እንደ መኳንንት እና ልዕልቶች ቢመስሉም፣ ልባቸው እንደ እጅግ በጣም ቆሻሻ የሆነ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ነው።
ገንዘብ ሰዎችን ደስተኛ ያደርጋልን? ጤና ሰዎችን ደስተኛ ያደርጋልን? አያደርግም። መቤዠት ብቻ ሰዎችን በእውነት ደስተኛ ያደርጋል። ሰው ከውጭ ሲታይ ምንም ያህል ደስተኛ ቢመስል በልቡ ውስጥ ኃጢአት ካለበት ይህ ሰው ምስኪን ነው። ፍርድን በመፍራት ይኖራሉ።
የተቤዠ ሰው በጨርቅ ለብሶ እንኳን እንደ አንበሳ ደፋር ነው። በልባቸው ኃጢአት የለም። “አመሰግናለሁ፣ ጌታ ሆይ፣ እንደራሴ ያለ ኃጢአተኛ አዳነህ፣ ኃጢአቴን ሁሉ አጠፋህ። ዋጋ እንደሌለኝ አውቃለሁ፣ ነገር ግን ስለ ዳነኝ ጌታን አመሰግናለሁ። ከኃጢአቴ ለዘላለም ተቤዣለሁ። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!”
የዳነ ሰው በእርግጥም ደስተኛ ሰው ነው። በእርሱ የቤዛነት ጸጋ የተባረከ ሰው በእርግጥም ደስተኛ ሰው ነው።
ኢየሱስ፣ ‘የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ፣’ ኃጢአታችንን ሁሉ እንደወሰደ፣ እኛ ያለ ኃጢአት ነን። በመስቀል ላይ ለእኛ ማዳንን ‘ጨርሷል’። የእርስዎን እና የእኔን ጨምሮ ሁሉም ኃጢአቶቻችን ‘በዓለምን ኃጢአት፣’ ውስጥ ተካትተዋል እና ስለዚህ ሁላችንም ድነናል።
 
 

በእግዚአብሔር ፈቃድ

 
በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ስንሆን በልባችን ኃጢአት አለን?
አይ፣ አናደርግም
 
ውድ ወዳጆች በምንዝር የተያዘችው ሴት በኢየሱስ ቃሎች አመነችና ዳነች። ታሪክዋ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈው በእርሱ የዘላለም ቤዛነት ስለተባረከች ነበር። ግብዞቹ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ግን ከኢየሱስ ሸሹ።
በኢየሱስ ብታምኑ የሚጠብቃችሁ መንግሥተ ሰማይ ነው፣ ኢየሱስን ብትተዉት ግን ገሀነም ትወርዳላችሁ። በእርሱ የጽድቅ ምግባሮች ብታምኑ መንግሥተ ሰማይ ይሆንላችኋል፣ በእርሱ ሥራዎች የማታምኑ ከሆነ ግን ገሀነም ይሆንባችኋል። መዳን በግለሰብ ጥረት ላይ የተመካ አይደለም፣ ነገር ግን በኢየሱስ መዳን በኩል ይመጣል።
ዕብራውያን 10ን እናንብብ። “ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፥ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር በሚያቀርቡት በዚያ መሥዋዕት የሚቀርቡትን ፍጹም ሊያደርጋቸው ከቶ አይችልም። እንደዚህማ ባይሆን፥ የሚያመልኩት አንድ ጊዜ ነጽተው ከዚያ በኋላ በሕሊናቸው ኃጢአትን ስላላወቁ ማቅረብን በተዉ አልነበረምን? ነገር ግን በዚያ መሥዋዕት በየዓመቱ የኃጢአት መታሰቢያ አለ። የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና። ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ፦ መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ። በሙሉ በሚቃጠል መሥዋዕትና ሰለ ኃጢአት በሚሰዋ መሥዋዕት ደስ አላለህም። በዚያን ጊዜ፦ እነሆ፥ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ አልሁ። ይላል፦ በዚህ ላይ፣ መሥዋዕትንና መባን በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ስለ ኃጢአትም የሚሰዋ መሥዋዕትን አልወደድህም በእርሱም ደስ አላለህም ብሎ፥ እነዚህም እንደ ሕግ የሚቀርቡት ናቸው፥ ቀጥሎ፦ እነሆ አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ ብሎአል። ሁለተኛውንም እንዲመሥርት ዘንድ የፊተኛውን ይሽራል። በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል” (ዕብራውያን 10፡1-10)።
“በእግዚአብሔር ፈቃድ” ኢየሱስ ህይወቱን አንድ ጊዜ ለሁሉም ሰው በማቅረብ፣ በጥምቀቱ ኃጢአታችንን ወሰደ፣ ለሁሉም አንድ ጊዜ ተፈርዶበት እንደገና ተነሳ።
ስለዚህ ተቀድሰናል። “ተቀድሰናል” (ዕብራውያን 10፡10)፣ የተጻፈው ባለፈው ፍጹም ጊዜ ነው። ይህ ማለት ቤዛነታችን ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፣ ዳግመኛም መጠቀስ አያስፈልገውም ማለት ነው። እናንተ ተቀድሳችኋል።
“ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል። እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥ ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደ ፊት ይጠብቃል። አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና” (ዕብራውያን 10፡11-14)።
ሁላችሁም ለዘላለም ተቀድሳችኋል። ነገ ኃጢአቶችን ብትሠሩ እንደገና ኃጢአተኞች ትሆናላችሁን? ኢየሱስ እነዚያንም ኃጢአቶች ደግሞ አልወሰደምን? ኢየሱስ እነዚያን ኃጢአቶች ሁሉ ወስዶዋል። እርሱ ወደፊት የሚሠሩ ኃጢአቶችንም ደግሞ ወስዶዋል።
“መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፤ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፦ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ፥ ብሎ ከተናገረ በኋላ፦ ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል። እነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ(ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል)፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም” (ዕብራውያን 10፡15-18)።
“ስርየት ባለበት ዘንድ(ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል)” የሚለው ሐረግ እርሱ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ አስተሰረያዋል ማለት ነው። ኢየሱስ አዳኛችን ነው። የእናንተም የእኔም አዳኝ ነው። በኢየሱስ በማመን ድነናል። ይህ በኢየሱስ የሆነው ቤዛነት ነው፣ እንዲሁም ከእግዚአብሔር የተሰጠ እጅግ ታላቅ ጸጋና እጅግ ታላቅ ስጦታ ነው። ከኃጢአቶቻችን ሁሉ የተዋጀነው እናንተና እኔ ከሰዎች ሁሉ እጅግ የተባረክን ነን! 

ይህ ስብከት በየኤሌክትሮኒክ መጽሐፍት ቅርጸት ደግሞ ይገኛል። ከዚህ በታች ባለው የመጽሐፉ ሽፋን ላይ ጠቅ ያድርጉ።
በውኑ በውሃውና በመንፈስ ቅዱስ ዳግም ተወልዳችኋልን? [አዲስ የተሻሻለ እትም]