Search

キリスト教信仰に関するFAQ

主題1:水と御霊によって新しく生まれる

1-14. ዘለቄታ ላለው ስርየት የሚቀርበው መስዋዕት ምን ነበር? 

ይህ በኢየሱስ በማመን በአንድ ጊዜ ለዓለም ሐጢያቶች በሙሉ የሆነ ስርየት ነበር፡፡ ኢየሱስ ለዘላለም የሚኖር የእግዚአብሄር ልጅና ጌታችን ስለሆነ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለዘላለም መውሰድ ይችላል፡፡ እርሱ ሐጢያቶቻችን ለዘላለም የወሰደው እንዴት ነበር?   
ይህን ያደረገው 
① የሰው ሥጋ ለብሶ በመወለድ፣
② በዮርዳኖስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ፣ 
③ በእኛ ፋንታ ፍርድን ሁሉ ለመውሰድ በመስቀል ላይ በመሰቀል ነው፡፡ 
የእግዚአብሄር ልጅ የሰው ሥጋ ለብሶ ወደዚህ ዓለም መጣ፡፡ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድም በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ የሰውን ዘር ለዘላለም ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ለማዳንም በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰ፡፡ (ዘሌዋውያን 16፡6-22፤ ማቴዎስ 3፡13-17፤ ዮሐንስ 1፡29፤ ዕብራውያን 9፡12፤10፡1-18)