Search

キリスト教信仰に関するFAQ

主題1:水と御霊によって新しく生まれる

1-19. በኢየሱስ ማመን ያለብን ለምንድነው? 

በኢየሱስ ማመን ያለብን፡- 
① የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመፈጸም፣ 
② ከሐጢያቶች ሁሉ ለመዳን፣
③ ከጌታ ጋር ለዘላለም እንኖር ዘንድ መንግሥተ ሰማይ ለመግባት ነው፡፡ 
ሁላችንም በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ከሌለን ሲዖል የምንገባ ሐጢያተኞች ነን፡፡ ከሲዖል ሊያድነን የሚችለው አዳኛችን ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ 
• በኢየሱስ የሚያምኑና ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ የዳኑ ሰዎች መጨረሻቸው የት ነው?-- ሰማይ ነው፡፡-- 
• በኢየሱስ የማያምኑና ያልዳኑ ሰዎች መጨረሻቸው የት ነው? --ለሐጢያቶቻቸው ሲዖል በእሳትና በዲን ወደሚቃጠል ባህር ይጣላሉ--፡፡ (ዮሐንስ ራዕ 21፡8)  
• የእግዚአብሄር በጎች እነማን ናቸው? --በኢየሱስ ጥምቀትና ደም በማመን የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ያገኙ ሰዎች ናቸው፡፡-- 
‹‹ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ›› (ዮሐንስ 10፡16) የተባሉት ፍየሎች ናቸው፤ ምክንያቱም በደመ ነፍስ የሚረዱትን በዘፈቀደ ያምናሉ፡፡ አሁንም ድረስ ሐጢያተኞች ናቸው፡፡ በኢየሱስ ጥምቀትና ደም የሚያምኑ ሰዎች በአንድ ጊዜ ድነው የእግዚአብሄር በጎች ይሆናሉ፡፡