Search

キリスト教信仰に関するFAQ

主題3: 黙示録

3-8. በእግዚአብሄር ዙፋን ፊት የሚቆሙት አራቱ እንስሶች ማን ወይም ምንድናቸው? 

ዮሐንስ ራዕይ 4፡6-9 አራቱን እንስሶች እንደሚከተለው አበራርቶዋቸዋል፡- ‹‹በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባህር ነበረ፡፡ በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉባቸው አራት እንሰሶች ነበሩ፡፡ ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፡፡ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፡፡ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፡፡ አራተኛውም እንሰሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል፡፡ አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፡፡ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፡፡ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ የነበረውና ያለው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም፡፡ እንስሶቹም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ውዳሴ ምስጋናም በሰጡት ጊዜ…›› 
በእግዚአብሄር ዙፋን ዙሪያ ያሉት አራቱ እንስሶች ከ24ቱ ሽማግሌዎች ጋር አብረው የእርሱን ፈቃድ ሁልጊዜም የሚፈጽሙና ቅድስናውንና ክብሩን የሚያገለግሉ ታማኝ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ናቸው፡፡ እግዚአብሄር ሲሰራ በራሱ አይሰራም፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜም በባሪያዎቹ አማካይነት ይሰራል፡፡ ለእግዚአብሄር እጅግ ቅርብ የሆኑት አገልጋዮች አራቱ እንስሶች ሁልጊዜም የእርሱን ፈቃድ ሁሉ የሚፈጽሙበት ችሎታን ተቀብለዋል፡፡ 
አራቱ እንስሶች እያንዳንዳቸው የተለያየ መልክ ያላቸው ሲሆን ይህም አራቱ እንሰሶች እግዚአብሄርን በተለያዩ ብቃቶች እንደሚያገለግሉ ያመለክታል፡፡ እነርሱ በውስጥና በዙሪያ ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፡፡ ይህም እነዚህ ሕያዋን እንሰሶች ያለ ማቋረጥ በእግዚአብሄር ዓላማዎች ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ የሚያሳይ ነው፡፡ ስለዚህ አራቱ ሕያዋን እንስሶች ሁልጊዜም የእርሱን ፈቃድ ያገለግላሉ፤ ይፈጽሙማል፡፡ 
በተጨማሪም እግዚአብሄር ከቶ እንደማይተኛ ሁሉ አራቱ ሕያዋን እንስሶችም የእግዚአብሄርን ክብርና ቅድስና ከማመስገን አያርፉም፡፡ እነርሱ የእግዚአብሄር አብንና አምላክና በግ የሆነውን የጌታችን ኢየሱስን ቅድስናና ሁሉን የሚገዛ ሐይል ያመሰግናሉ፡፡ በዚህ መንገድም አራቱ ሕያዋን እንስሶች በእግዚአብሄር ዙፋን ፊት ቆመው በግዴታ ሳይሆን በቅን ልባቸው ያመሰግኑታል፡፡ ለምን? ባደረገው ነገር የተነሳ ማለትም በሰው መልክ ራሱን አዋርዶ በድንግል ማርያም ሥጋ በኩል ወደዚህ ዓለም በመወለዱ፣ ጥምቀትንም ከዮሐንስ በመቀበል የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ በመውሰዱ፣ እነዚህን ሐጢያቶችም በመስቀል ላይ በመሸከሙና በዚያም በመሞቱ በዚህም የሰውን ዘር ሁሉ ከሐጢያት በማዳኑ ነው፡፡ አሁን እርሱ በእግዚአብሄር ዙፋን ላይ ተቀምጦዋል፡፡ ለእነዚህ ውብ ሥራዎቹ ከፍጥረታቶቹ ሁሉ ክብርን ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሊቀበል ይገባዋል፡፡ 
አራቱ ሕያዋን እንሰሶች ከ24ቱ ሽማግሌዎች ጋር አብረው ከልባቸው ጥልቅ ውስጥ የሚፈልቅ እውነተኛ ምስጋና ለእርሱ በመስጠት እዚአብሄርን ከፍ ያደርጉታል፡፡