Video Boodschappen van Medewerkers
እግዚአብሔር የዓለምን ኃጢአት ይቅር ያለው በአንድ ጊዜ ነው‼️ እግዚአብሔር ፍጹም ነው‼️ በአንድ ጊዜ ላንዴና ለመጨረሻ የዓለምን ኃጢአት በሙሉ ይቅር ብሏል‼️
Mesfin Berhanu Ubba
Ethiopia
12/13/2021 57130
VIDEO
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ዕብራውያን 10 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹¹ ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፤ ¹² እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥
… ¹⁴ አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና። ¹⁵-¹⁶ መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፤ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ ብሎ ከተናገረ በኋላ፥ ¹⁷ ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል። ¹⁸ የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም። ይላል። _____________________________________________ እዚህ ላይ "እርሱ ግን ስለ ኃጢአት #አንድን #መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ" ሲባል #ኢየሱስ ክርስቶስ #የዓለምን #ኃጢአት የተሸከመውና የዓለምን ኃጢአት የደመሰሰው በአንድ ጊዜ ላንዴና ለመጨረሻ ነው ማለት ነው። ❤❤❤ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን የልጁን ሥራ ያመኑ የሰዎቹን ኃጢአታቸውንና አመጻቸውንም ደግሜ አላስብም በማለት አዲስ ኪዳን መግባቱ የሚያረጋግጥልን እግዚአብሔር የዓለምን ኃጢአት በሙሉ በአንድ ጊዜ ላንዴና ለመጨረሻ ይቅር ማለቱን ነው።............... ሃሌሉያ‼️ ____________________________________________ በተከታታይ የሚነበቡ ነጻ የክርስቲያን መጽሐፍትን በpdf, በAudio እና በመጽሐፍ ከፈለግኩ ከታች ያሉትን አድራሻዎችን በመጫን ተጠቃሚ ይሁኑ‼️ Website
LIJST