Search

Preken

ርዕስ 9፡ ሮሜ (በሮሜ መጽሐፍ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[Chapter 5-1] የሮሜ መግቢያ ምዕራፍ 5

የመንጻት ትምህርት እውነት አይደለም፡፡

 
ጳውሎስ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ‹‹ከእግዚአብሄር ጋር ሰላም የሚያደርጉ›› በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ሰዎች ብቻ እንደሆኑ ያውጃል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት እግዚአብሄር አብ ኢየሱስ ክርስቶሰ ለእኛ እንዲጠመቅና ደሙንም በመስቀል ላይ እንዲያፈስስ ስላደረገው ነው፡፡
 
ነገር ግን እኛ ብዙውን ጊዜ ዛሬ አብዛኞቹ ክርስቲያኖች ከእግዚአብሄር ጽድቅ በሚመለከት ቅንጣት ያህል እውቀት ስለሌላቸው እንደሆነ እናያለን፡፡ በዘመኑ ክርስትና የሚያምኑ ሰዎች እውነታ ይህ ነው፡፡ ስለዚህ የመንጻት ትምህርት በእግዚአብሄር ፊት ትክክል አይደለም፡፡
 
በመንጻት ትምህርት ከማመን ይልቅ የእግዚአብሄርን ጽድቅ በእምነት ማግኘት የበለጠ ትክክል ነው፡፡ እግዚአብሄር አብ በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ቢኖርባቸውም በኢየሱስ የሚያምኑ አማኞችን የራሱ ሕዝብ አድርጎ አይቀበልም፡፡ እግዚአብሄር እንዲህ አይነት አምላክ አይደለም፡፡ እርሱ በልቡ ውስጥ ሐጢያት ያለበትን ሰው የራሱ ሕዝብ አድርጎ በፍጹም የሚመለከት አዳኝ አይደለም፡፡ እኛ የምናምነው አምላክ ሁሉን ቻይ ነው፡፡ ሁሉን ቻይና ሁሉን አዋቂ የሆነ አምላክ ስለ እያንዳንዱ ሰው የሐሰት እምነት በትክክል አያውቅምን? እንግዲያውስ እርሱ የሐሰት እምነት ያለውን ክርስቲያን የሆነ ሐጢያተኛ ከራሱ ሕዝብ እንደ አንዱ አድርጎ እንደማይጠራው ማወቅና ማመን ይገባናል፡፡
 
እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሄር ፊት እውነተኛ ሊሆን ይገባል፡፡ ሰዎች በውሸት የሚያውቁትና የሚያምኑበት የመንጻት ትምህርት እግዚአብሄርን የሚያዋርድ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ስለ እግዚአብሄር ጽድቅ ያለውን እውነት በትክክል ከተረዳን በኋላ ኢየሱስን አዳኛችን አድርገን ልናምነው ይገባናል፡፡ እግዚአብሄር አብ ሰው በኢየሱስ የሚያምን ወይም የማያምን ይሁን ሐጢያት ያለበት ሆኖ ከተገኘ ትክክል ነው አላለም፡፡ እርሱ ሐጢያተኛውን ስለ ሐጢያቱ የሚፈርድበት አምላክ ነው፡፡
 
ስለዚህ የሐጢያት ችግሮቻችሁ ይፈቱላችሁ ዘንድ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ማወቅና ማመን ያስፈልጋችኋል፡፡ እግዚአብሄር በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም ላይ ያለውን እምነታችንን ያይና ከሐጢያቶቻችን ያነጻናል፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ ስለምናምን እግዚአብሄር የራሱ ሕዝብ አድርጎ ይጠራናል፤ ያቅፈናል፤ ይባርከንማል፡፡ እግዚአብሄር አብ በእርሱ ጽድቅ ማመናችን ትክክል እንደሆነም ያረጋግጣል፡፡
           
 

እግዚአብሄር ምድራዊ ዳኛ አይደለም፡፡ 

 
በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምነው እምነት በግልጽ በእግዚአብሄር ቃሎች ባመነው የአብርሃም እምነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች ስለ መንጻት ትምህርት የተሳሳተ መረዳት አላቸው፡፡ ከዚህ የተነሳ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥርት ያለ ግንዛቤ ሊኖረን ያስፈልገናል፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ባለ በማንኛውም ችሎት ውስጥ ፍጹም ትክክል ወይም ቀና ፍርድ የሚባል ነገር እንደሌለ በእርግጠኝነት ታውቃላችሁ፡፡ የዚህ ዓለም ዳኛ በውሳኔዎቹ ሁልጊዜም ስህተቶችን እንደሚሰራ ማወቅ ያስፈልጋችኋል፡፡
 
ይህ የሆነበት ምክንያት ሰብዓዊ ዳኛዎች በሙሉ ብቁ ስላልሆኑና ለበጎና ለክፉም መሰረታዊ መስፈርት የሆነውን የእግዚአብሄርን ጽድቅ ስለማያውቁ ነው፡፡ አብዛኞቹ ክርስቲያኖች ‹‹በእምነታችን ጽድቅ›› (ሮሜ ምዕራፍ 5) የሚፈርድብንን የእግዚአብሄርን ጽድቅ በተሳሳተ መንገድ ለመረዳት የፈጠኑ ናቸው፡፡ ምክንያቱም የእርሱ ፍርድ አንድ ዳኛ በሐጢያተኛ ላይ የሚያሳልፈውን ብያኔ የሚከተል ተመሳሳይ ስነ አመክንዮን የሚጠቀም ነው ብለው ያስባሉ፡፡
 
የመንጻት ትምህርት የተሳሳተ ፍርድ ትምህርት ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ይህ ትምህርት በሰዎች አስተሳሰብ ላይ ተመስርቶ የተፈጠረ ስለሆነ ነው፡፡ ሰዎች የተሳሳቱ ፍርዶችን በመፍረድ የተካኑ ናቸው፡፡ ምክንያቱም እነርሱ ሁሉን ቻይ አይደሉምና፡፡ ስለዚህ በመንጻት ትምህርት ላይ በተመሰረቱት አስተሳሰቦቻቸው በትክክል ባጸደቃቸው አምላክ በውሸት ያምናሉ፡፡ ይህም እግዚአብሄር ‹‹በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ስለምታምንብኝ ሐጢያት አልባ አድርጌ እቆጥርሃለሁ›› ይላል ብለው እንዲያምኑ ይነዳቸዋል፡፡
 
እግዚአብሄር ግን እንዲህ ያለ ነገር በጭራሽ ሊያደርግ አይችልም፡፡ ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሐጢያት ቢኖርባቸውም እግዚአብሄር የራሱ ሕዝብ አድርጎ እንደሚቀበላቸው ያምናሉ፡፡ ምክንያቱም እነርሱ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በኢየሱስ ያምናሉና፡፡ ይህ በራሳቸው አስተሳሰቦች ላይ የተመረኮዘና በአጋንንት የመታለል ውጤት ከሆነው የሐሰት እምነት የሚልቅ አንዳች ነገር አይደለም፡፡
 
ስለዚህ የእምነት ቤቶቻቸውን በእግዚአብሄር ጽድቅ ባላቸው እምነት ላይ ደግመው ሊገነቡ ይገባቸዋል፡፡ ቅዱስና ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክ በልቡ ሐጢያት ያለበትን ሰው እንዴት ሐጢያት አልባ ነው ብሎ ሊፈርድ ይችላል? እግዚአብሄር በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ያለባቸውን ሰዎች ሐጢያት አልባ ናቸው ብሎ ይወስናልን? የዚህ አይነት ነገር እውነት ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብና ማመን የሰው አስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡ እግዚአብሄር የእውነት አምላክ ስለሆነ የተሳሳተ ፍርድ አይሰጥም፡፡ ራሱ እውነት የሆነ አምላክ ሰዎች እንደሚያደርጉት በብያኔዎቹ እንዴት ስህተቶችን ሊሰራ ይችላል? ይህ በፍጹም ሊሆን አይችልም፡፡ እግዚአብሄር በእርሱ ጽድቅ የሚያምኑትን በራሱ ጽድቅ ላይ ተመርኩዞ ሐጢያት አልባ እንደሆኑ አድርጎ የሚፈርድ ጻድቅ አምላክ ነው፡፡
 
ስለ እግዚአብሄር ጽድቅ ታውቃላችሁን? የእርሱን ጽድቅ አውቃችሁ ታምኑበታላችሁን? ይህ ጽድቅ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ቃሎች ውስጥ በሙላት ሊገኝ ይችላል፡፡ በሮሜ ውስጥ የተነገረውን የእግዚአብሄርን ጽድቅ ለመረዳት የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መረዳትና ማመን ያስፈልጋችኋል፡፡ ይህንን ሳታደርጉ የእግዚአብሄርን ጽድቅ በፍጹም መረዳት አትችሉም፡፡ እያንዳንዱ ሰው ይህንን እውነት መገንዘብ አለበት፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚያስተውል ሰው ያጸደቀውን እውነት በትክክል የሚረዳ ሰው ነው፡፡
 
ሁላችንም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠውን የእግዚአብሄር ጽድቅ ማመን ይገባናል፡፡ አለበለዚያ እምነታችሁ በሐሰት የሰው ብያኔና አስተሳሰብ ላይ ተመስርቶ ይስታል፡፡ እስከ አሁን ድረስ የዚህ አይነት የሐሰት እምነት ይዛችሁ ከሆነ ከአሁን ጀምራችሁ በእግዚአብሄር የጽድቅ ቃሎች መሰረት ልታምኑ ይገባችኋል፡፡
 
አብዛኞቹ ክርስቲያኖች በሥነ መለኮት የመንጻትን ትምህርት ተምረው እስከ አሁን ድረስ ትክክል ነው ብለው አስበዋል፡፡ ነገር ግን አሁን በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ወደ እውነተኛው እምነት መመለስ ይገባችኋል፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ኢየሱስ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በማመን ጥርት ብሎ ተገልጦዋል፡፡
         
 
መከራ ትዕግስትን እንደሚያደርግ ተነግሮዋል፡፡
 
በሮሜ 5፡3-4 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ይህም ብቻ አየደለም፤ ነገር ግን መከራ ትዕግስትን እንዲያደርግ ትዕግስትም ጠባይን፣ ጠባይም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን በመከራችን ደግሞ እንመካለን፡፡›› ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖች በሙሉ እግዚአብሄር ከሁሉም አይነት መከራዎች በእርግጥ እንደሚያድናቸው ተስፋ አላቸው፡፡ ይህ ተስፋ ትዕግስትን ያደርጋል፡፡ ትዕግስትም ጠባይን ያደርጋል፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ጻድቃን በመከራ ጊዜም ቢሆን ይደሰታሉ፡፡
 
ጳውሎስ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምን እምነት የእግዚአብሄርን መንግሥት ተስፋ እንደሚያደርግ ተስፋም እንደማያሳፍር ተናግሮዋል፡፡ ጻድቃን ምን አይነት ተስፋ አላቸው? ወደ እግዚአብሄር መንግሥት የሚገቡበትና በዚያ የሚኖሩበት ተስፋ አላቸው፡፡ የዚህ አይነት እምነት የሚመጣው ከየት ነው? በእግዚአብሄር ፍቅር አማካይነት በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ከማመን የሚመጣ ነው፡፡
     
 
ጌታ እኛ ሐጢያተኛ በመሆን የለመድን ሰዎች መሆናችንን ይናገራል፡፡
 
‹‹ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ሐጢያተኞች ሞቶዋልና፡፡›› (ሮሜ 5፡6)
 
ከመጸነሳችን በፊት ከነበረው ጊዜ አንስቶ ወይም በእናታችን ማህጸን ከነበርንበት ጊዜ አንስቶ ወይም ተወልደን ጌታን የማናውቅ ከነበርንበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዕለት ሞታችን ድረስ ሐጢያቶችን ከመስራትና ውሎ አድሮም በሲዖል ውስጥ ፍጻሜያችንን ከማድረግ በቀር ሌላ ምርጫ አልነበረንም፡፡
 
ቅድመ አያቶቻችን አዳምና ሄዋን ሐጢያት በሰሩ ጊዜ እግዚአብሄር ‹‹እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም (እባቡ) ሰኮናውን ትቀጠቅጣለህ›› (ዘፍጥረት 3፡15) በማለት አዳኝ እንደሚልክልን ተስፋ ሰጠ፡፡ በዚህ ተስፋ መሰረት እኛ ሐጢያት ከመስራታችን በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ከሐጢያታችን ሁሉ አዳነን፡፡ የዓለምን ሐጢያቶች ለመውሰድም በዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስም ደመሰሳቸው፡፡ ከሞት በመነሳትም ሐጢያቶቻችንን አስወገዳቸው፡፡ ጌታ የሰውን ዘር ሐጢያቶችና እንደ እናንተና እንደ እኔ ያሉትን ሐጢያተኞች ሐጢያቶች በጥምቀቱ ወስዶ በመስቀል ላይ በመሞት ምዕመናንን ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ አዳናቸው፡፡
 
እኛ ጻድቃን ነን? ጻድቅ ሰው እግዚአብሄርን በመፍራት የሚቆምና ራሱን ከሐጢያት የሚጠብቅ ነው፡፡ ኢየሱስ ሐጢያተኛ ለሆንነው ለእናንተና ለእኔ እንዲጠመቅና እንዲሰቀል ከዚያም እንዲነሳ የፈቀደለት የእግዚአብሄር ፍጹም ጽድቅ ነበር፡፡ ገና ደካሞች ሳለን ያዳነንም እንደዚሁ የእግዚአብሄር ፍቅር ነበር፡፡
 
በብሉይ ኪዳን ውስጥ እስራኤሎች አንድ ዓመት ሙሉ የሰሩዋቸው ሐጢያቶች በሊቀ ካህኑ እጅ መጫን ወደ መስዋዕቱ እንስሳ ይሻገሩ እንደነበረ ሁሉ (ዘሌዋውያን 16፡20-21) ኢየሱስ ክርስቶስም በአዲስ ኪዳን በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ በአንድ ጊዜ ከመውሰዱም በላይ የዓለምን ሐጢያቶች ተሸክሞ ስለነበር ሊሰቀል ወደ መስቀል ሄደ፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጠመቅና ደሙን በማፍሰስ የሐጢያተኞችን ሐጢያቶች በሙሉ የማንጻቱን እውነታ ይጠቁማል፡፡
 
እናንተና እኔ ጻድቃን ነን? ጌታ እኛን ሐጢያተኞቹን ለማዳን የመጣው ጻድቃን ስላይደለን አይደለምን? እግዚአብሄር ሁላችንም ሐጢያተኞች እንደሆንን በሚገባ ያውቃል፡፡ ከተወለድንበት ቀን ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታችን ድረስ ሐጢያቶች ከማድረግ መቆጠብ ስለማንችል ሐጢያተኞች ነን፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ በዮሐንስ በመጠመቅና በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ ገና ሐጢያተኞች ሳለን ለእኛ ያለውን ፍቅር አሳየ፡፡
          
 
ኢየሱስ ዕጣ ፈንታችንን ቀይሮታል፡፡
 
እኛ ሰዎች ከተወለድንበት ቀን ጀምሮ ምን አይነት ዕጣ እንደሚገጥመን ልናስብ ይገባናል፡፡ ከተወለድንበት ቀን አንስቶ ዕጣ ፈንታዎቻችን ምን ነበሩ? እኛ ወደ ሲዖል ለመውረድ የታጨን ነበርን፡፡ ታዲያ እናንተና እኔ ወደ ሲዖል ከመውረድ ከዚህ ዕጣ ፈንታ እንዴት መዳን ቻልን? በእግዚአብሄር ጽድቅ ስላመንን ዕጣ ፈንታዎቻችን ተቀይረዋል፡፡ ዕጣ ፈንታዎቻችንን የቀየረው እውነት የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ በፈጸመው በኢየሱስ ክርስቶስ ስላመንን ዕጣ ፈንታዎቻችን ተባርከዋል፡፡
 
ቀጣዩን የታወቀ መዝሙር ስንኞች ታውቁዋቸው ይሆናል፡፡ ‹‹♪ግሩም ጸጋ! ድምጹ ምንኛ ጣፋጭ ነው፡፡ ♫እኔን ጎስቋላውን አዳነኝ! ♫በአንድ ወቅት ጠፍቼ ነበር፤ አሁን ግን ተገኘሁ፡፡ ♫እውር ነበርሁ፤ አሁን ግን አያለሁ♪፡፡›› የእግዚአብሄር ምህረትና ጽድቅ ስለ ደህንነታችን የሚመሰክር እውነት ነው፡፡ ማንም ሰው የእግዚአብሄርን ጽድቅ አውቆ ሲያምንበት በልቡ ውስጥ ካለው ሐጢያት ሁሉ ይቅርታን አግኝቶ በሰማያዊ ሰላም ሊደሰት ይችላል፡፡ በዚህ ዓለም ላይ የሚኖርና በልቡ ውስጥ ሐጢያት ያለበት ሰው ሁሉ በኢየሱስ ቢያምንም የእግዚአብሄርን ጽድቅ ለማወቅ ወደ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል መመለስ ይገባዋል፡፡
 
በእርግጥ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የማያውቁ ክርስቲያኖች ሐጢያቶቻቸው ወደ ኢየሱስ መተላለፋቸውን አያውቁም፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ማግኘት አይችሉም፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በመስቀል ላይ በመሞት ከሐጢያቶቻቸው እንዳዳናቸው ቢያምኑም ስለ መዳናቸው እርግጠኞች አይደሉም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ዓለም ሳይፈጠር በፊት ምናልባት መርጦዋቸው እንደሆነ በደምሳሳው በማሰብ የዕፎይታ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ በሌላ አነጋገር በክርስትና የሚያምኑት በዓለም ላይ ያለ ሌላ ሃይማኖት ብቻ እንደሆነ አድርገው ነው፡፡
 
ቁጥር 11 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ይህም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን አሁን መታረቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሄር ደግሞ እንመካለን፡፡›› እኛን ሐጢያተኞቹን ከእግዚአብሄር ጋር ያስታረቀን ማነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ጋር አስታረቀን፡፡ እንዴት? ራሱ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በ30 ዓመቱ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቁና በመሰቀሉ ከዚያም ከሙታን ተነስቶ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሁሉ የፈጸመውን ሥራ በማጠናቀቅ ነው፡፡ ኢየሱስ በእግዚአብሄር ጽድቅ ለምናምን ምዕመናኖች ሰማያዊ ሊቀ ካህን ሆኖ በመምጣትና የሰውን ዘር ሐጢያቶች በመውሰድ አዳኛችን ሆነ፡፡ ምድራዊ ሊቀ ካህን በሆነው በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ ደሙን በመስቀል ላይ አፈሰሰ፡፡ ከዚያም ከሙታን በመነሳት አዳኛችን ሆነ፡፡
 
ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በማስወገዱ በእምነታችን አማካይነት የእግዚአብሄርን ጽድቅ ማግኘት ችለናል፡፡ ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ እንዳዳነን የሚያምን ማንኛውም ሰው በእግዚአብሄር ይደሰታል፡፡ በልቡ ውስጥ እጅግ ቅንጣት ሐጢያት ያለበት ማንኛውም ሰው የእግዚአብሄር ልጅ አይደለም፡፡
 
እናንተ ወንድሞች ምናልባትም የዚህ ዓለም ሰዎች የመንጻት ትምህርትና የመቀደስ ትምህርት ትክክል ነው ብለው እንደሚያስቡ ታውቁ ይሆናል፡፡ በልባችን ውስጥ ሐጢያቶች ቢኖሩም በኢየሱስ እናምናለን ብንል ሐጢያት አልባ መሆናችንን ማጽናቱ ትክክል ነውን? ወይስ ራሳችንን ክርስቲያኖች ብለን ስለምንጠራ የእግዚአብሄር ሕዝብ ተብለን መታወቃችን ይበልጥ ትክክል ነው?      
 
በጌታ ጸሎት ውስጥ ‹‹በሰማያት ያለህ አባታችን ሆይ ስምህ ይቀደስ›› እንላለን፡፡ ይህ ሐረግ በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያቶች ያሉባቸው ሰዎች እግዚአብሄርን ‹‹አባታችን›› ብለው መጥራት አይችሉም ማለት ነው፡፡ አሁንም ድረስ በመንጻት ትምህርት ማመን ይኖርብናልን? በአሁኑ ጊዜ ሐጢያተኛ የሆነ ሰው ጌታን አዳኝ ብሎ መጥራት ይችላልን? ጌታን ለሁለት ዓመታት ያህል ይጠራው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ክርስቲያን ተብሎ በመጠራቱ የሐፍረት ስሜት ስለሚሰማው ውሎ አድሮ ጌታን ይተወዋል፡፡ ስለዚህ የመንጻት ትምህርት ከእግዚአብሄር ጽድቅ እንደሚነጥላችሁ ልታውቁ ይገባችኋል፡፡
 
የቅድስና ትምህርትም እንደዚሁ የተሳሳተ ነው፡፡ ይህ ትምህርት እኛ ከመሞታችን በፊት በመጨረሻዋ ቅጽበት ፈጽሞ ቅዱስ እስከምንሆን ድረስ ቀስ በቀስ በለውጦች ውስጥ እናልፋለን፤ ከዚያም ቅዱስ ሰዎች ሆነን እግዚአብሄርን እንገናኘዋለን ይላል፡፡ በራሳችሁ ሐጢያቶች ሳይኖሩባችሁ እግዚአብሄርን ለመገናኘት የሚያበቃችሁን ቅድስና ቀስ በቀስ ማግኘት የምትችሉ ይመስላችኋልን? አይሆንም፡፡ ሰው ወደ እግዚአብሄር መንግሥት መግባት የሚችለው የእግዚአብሄርን ጽድቅ በማወቅና በማመን በቻ እንደሆነ እውነቱ ይነግረናል፡፡
    
 
እንዲሁ በአንድ ሰው ሐጢያት ወደ ዓለም ገባ!
 
አሁን ቁጥር 12ን እናንብብ፡- ‹‹ስለዚህ ምክንያት ሐጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ፡፡ በሐጢአትም ሞት፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ሐጢአት ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፡፡›› ሐጢያት ወደ ሰው ልብ የገባው በማን ነበር? ሐጢያት ወደ ዓለም የገባውስ በስንት ሰዎች ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሐጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ፡፡››  
 
በሌላ አነጋገር ሐጢያት ሕልውና ያገኘው በአንድ ሰው በአዳም እንደሆነ ተነግሮዋል፡፡ እኛም ሁላችን የእርሱ ዘሮች ነን፡፡ የዓለም ሐጢያቶች የተወገዱትስ በማን በኩል ነበር? ይህ የሆነው ሐጢያት መጀመሪያ ወደ ዓለም በገባበት ተመሳሳይ መንገድ ነው ማለት ይቻላል፡፡
 
የሰው ዘር ሐጢያቶች የመጡት ሰው እግዚአብሄር የደነገገውን ሕግ ባለማመኑ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን በእግዚአብሄር ቃሎች የማያምን ሰው ሐጢያተኛ ሆኖ ይቀራል፡፡ መጨረሻውም ሲዖል ይሆናል፡፡
 
ስለዚህ የሚከተለውን ማወቅ ይገባናል፡፡ እኛ ሐጢያተኞች የሆንነው በሐጢያቶቻችን ምክንያት ሳይሆን ሐጢያት በነበረባቸው አያቶቻችን ምክንያት ነው፡፡ ሰዎች ሐጢያት የሚሰሩት ደካሞች ስለሆኑና በልባቸው ውስጥም ሐጢያት ስላለባቸው ነው፡፡ ሰዎች የሚሰሩት ሐጢያት በደል ተብሎ ይጠራል፡፡ እነርሱ ሐጢያት የሚሰሩት በዚህ ዓለም ላይ የተወለዱት ሐጢያትን ይዘው ስለሆነ ነው፡፡ ሰው ሁሉ ጉድለት ስላለበትና ወደዚህ ዓለም ሲወለድም ሐጢያትን ይዞ በመሆኑ ሐጢያቶችን ከመስራት ሊቆጠብ አይችልም፡፡
 
እኛ ከመነሻችንም ሐጢያተኞች፤ የሐጢያት ዘሮች ሆነናል፡፡ ምክንያቱም ሐጢያቶችን የወረስነው ከአያቶቻችን ነውና፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን በአንድ ጊዜ ቅዱስና ጻድቅ መሆን እንደሚችል ልታውቁ ይገባል፡፡
 
 
ሐጢያት በሰው ውስጥ መኖር የጀመረው መቼ ነበር?
 
‹‹ሕግ እስከመጣ ድረስ ሐጢአት በዓለም ነበረና፡፡ ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ሐጢአት አይቆጠርም፡፡›› (ሮሜ 5፡13) የእግዚአብሄርን ሕግ ከማወቃችን በፊት ሐጢያት ነበርን? የእግዚአብሄርን ሕግ ከማወቃችን በፊት በአግዚአብሄር ፊት ሐጢያት የሆነ ምግባር ሆኖ የተኮነነው ምን እንደነበር አልተረዳንም፡፡ እግዚአብሄር ‹‹በፊቴ ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ፤ በላይ በሰማይ ወይም በታች በምድር ወይም ከምድር በታች በውሃ ውስጥ ያለን የማንኛውንም አምሳያ የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፡፡ የእግዚአብሄር የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፡፡ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ›› ብሎ ነግሮናል፡፡ ምን ማድረግ ‹‹እንዳለብንና እንደሌለብን›› የሚነግሩንን እነዚህን የእግዚአብሄር ሕጎችና  የትዕዛዛቶቹን 613 አንቀጾች ከማወቃችን በፊት ሐጢያቶቻችንን በተጨባጭ አናውቃቸውም ነበር፡፡
 
ስለዚህ ‹‹ሕግ እስከመጣ ድረስ ሐጢአት በዓለም ነበርና፡፡ ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ሐጢአት አይቆጠርም፡፡›› እኛ አሕዛቦች ሕግ ስላልነበረንና ስለማናውቀው ያንን ባለማወቅ ሐጢያቶችን ሰርተናል፡፡ አብዛኞቹ ኮርያውያን ቡድሃ ነው ብለው በማሰብ ለዓለት ሲጸልዩ ነበር፡፡ ነገር ግን አሁንም ድረስ የተቀረጸ ምስልን እያመለኩ እንደሆኑ አላወቁም፡፡ ለሌሎች አማልክቶች ማጎንበስ በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት እንደሆነ አላወቁም፡፡     
ሆኖም ሕጉ ከመምጣቱ በፊት ሐጢያት ቀድሞውኑም በዓለም ላይ ነበረ፡፡ እግዚአብሄር አዳምን ከፈጠረ ከ2,500 ዓመታት በፊት ሕጉን ሰጠን፡፡ እግዚብሄር በግምት በ1,450 አ.አለም በሙሴ በኩል ለእስራኤሎች ሕግን ቢሰጥም ሐጢያት በአንድ ሰው በአዳም በኩል ከዚያ ቀደም ብሎ ወደ ዓለም ገብቶ ሕጉ ከመምጣቱ በፊት በሰዎች ሁሉ ልብ ውስጥ ይኖረ ነበር፡፡
 
 
ኢየሱስ የሕዝቡ አዳኝ ነው፡፡
 
ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች ብቻውን አስወግዶዋልን? አዎ፡፡ እዚህ ቁጥር 14 ላይ በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ሐጢያት ባልሰሩት ወይም ባላጠፉት ሰዎች ሁሉ ላይ ሞት እንደነገሰ ተነግሮዋል፡፡ ስለዚህ አዳም ሊመጣ ያለው የእርሱ ምሳሌ ነበር፡፡ የሰው ዘር በአንድ ሰው በኩል ሐጢያተኛ ሆነ፡፡ ልክ እንደዚሁ ኢየሱስ ክርስቶስም ወደዚህ ዓለም መጥቶ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት ከሐጢያቶቻችን ሁሉ አዳነን፡፡
 
ኢየሱስ ሕዝቡን ከሐጢያቶቻቸው ያዳነ አዳኝ ሆነ፡፡ እኛን የአዳምን ዘሮች ከሐጢያት ያዳነን አንድ አዳኝ ብቻ አለ፡፡ ‹‹መዳንም በሌላ ማንም የለም፡፡ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 4፡12) ስሙ ዘላለማዊ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
 
እኛ በአንድ ሰው በአዳም በኩል ያለ ፈቃዳችን ሐጢያተኞች እንደሆንን መረዳት አለብን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ሐጢያቶች በአንድ ጊዜ ያስወገደ አዳኝ እንደሆነ ታውቃላችሁን? ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ የዓለምን ሐጢያቶች በአንድ ጊዜ የደመሰሰ አምላክ እንደሆነ ታምናላችሁን? አዳም አንድን ሐጢያት በመስራት የሐጢያቶች ሁሉ ምንጭ እንደሆነ ሁሉ ኢየሱስም የዚህን ዓለም ሐጢያቶች በማስወገድ የሰዎች ሁሉ እውነተኛ አዳኝ እንደሆነ ታምናላችሁን?
 
ኢየሱስ በአንድ ሰው በአዳም የተነሳ ሐጢያተኞች የሆኑትን ሁሉ ለማዳን መጣ፡፡ በዮሐንስ በመጠመቅም የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ወስዶ ደሙን በማፍሰስ የሐጢያቶችን ፍርድ በመስቀል ላይ ተቀበለ፡፡ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ያስወገደውንም የእግዚአብሄር ጽድቅ ሁሉ ፈጸመ፡፡ በዚህም ፍጹም አዳኛችን ሆነ፡፡
 
ደህንነትን ያገኘነው በኢየሱስ ካመንን በኋላ በመንጻት ትምህርት ወይም በቅድስና ትምህርት በማመን አይደለም፡፡ ኢየሱስ የዘላለምን ደህንነት የሰጠን በአንድ ጊዜ ነው፡፡ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት መግባትና ማየት የሚችሉት ከውሃና ከመንፈስ ዳግም የተወለዱ ብቻ እንደሆኑ ኢየሱስ ተናግሮዋል፡፡
 
በሰው ሕሊና ውስጥ ተቀብሮ ያለው እሳቤ ምንድነው? ይህ የመጥፎ አጋጣሚ መርህ ነው፡፡ በአእምሮዋቸው ጥልቅ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ጥረቶቻቸውና ውጥኖቻቸው ለደህንነታቸው እንደሚሰሩላቸው ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ሰው ሁሉ ከሐጢያት እውነተኛ ደህንነትን የሚያገኘው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በአንድ ጊዜ ሲያምን ብቻ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ እኛን ከሐጢያት ለማዳን ተሰቅሎዋል፡፡ እርሱ በእውነተኛው ወንጌል ለሚያምኑ ሁሉ አዳኝ ሆንዋል፡፡
ሰው የንስሐ ጸሎቶችን በማቅረብ ቅድስና ላይ መድረስና ውሎ አድሮም ጻድቅ መሆን ይችላል ከሚለው ጠማማ እሳቤ ራሳችሁን ነጻ አድርጉ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዱ ሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለመውሰድ ተጠምቆ በመስቀል ላይ ባደረገው የሐጢያቶች ስርየት አማካይነት ደህንነታችን ሁሉ ፈጸመ፡፡
      
 
ኢየሱስ እንደ በደላችን ያልሆነ ዘላለማዊ የሐጢያት ስርየትን ሰጠን፡፡
 
ቁጥር 15 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም፡፡ በአንድ ሰው በደል ብዙዎች ሞተዋልና፤ ነገር ግን የእግዚአብሄር ጸጋና በአንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ፡፡››
 
ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ የእናንተና የእኔ ሐጢያቶች ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋልን? ተላልፈዋል፡፡ ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች ተሸክሞ ወደ መስቀል በመሄድ በእኛ ፋንታ ለእነዚያ ሐጢያቶች ፍርድን ተቀበለ፡፡
 
የእግዚአብሄር ደህንነት ነጻ ስጦታ ነው፡፡ ከበደሉ እንደሚለይ ተነግሮዋል፡፡ 
 
ኢየሱስ በ33 ዓመት ዕድሜው በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ሐጢያቶችን ከመስራት መቆጠብ የማንችለውን እኛን አዳነን፡፡ በአንድ ጊዜ የተፈጸመውን የሐጢያት ስርየት በማመን ደህንነትን ካገኘን በኋላ እንኳን ሥጋችን ጎዶሎና ደካማ ስለሆነ ሐጢያት መስራቱን ሊቀጥል ይችላል፡፡ ሥጋችን አሁንም ድረስ ሐጢያት መስራቱን ቢቀጥልም ኢየሱስ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ የመውሰዱንና ደሙን በማፍሰስም የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሁሉ የመፈጸሙን እውነታ ብናምን ዘላለማዊውን የሐጢያት ስርየት ማግኘት እንችላለን፡፡
 
በሐጢያት ስርየት የመዳኑ ስጦታ እንደ አዳም በደል አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የሚሰጠው የሐጢያት ስርየት ስጦታ ሰዎች በየቀኑ እንደሚሰሩዋቸው ሐጢያቶች በየቀኑ የሚሰጥ አይደለም፡፡ የሐጢያት ስርየት እውነት ጌታ ከ2,000 ዓመታት በፊት በጥምቀቱና ባፈሰሰው ደሙ አስቀድሞ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ አንድ ጊዜ እነዳዳነን ይናገራል፡፡
 
ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ያዳነን የእግዚአብሄር የደህንነት ስጦታ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በአንድ ጊዜ የተፈጸመው ጽድቅ ነው፡፡ ዘላለማዊው የሐጢያቶች ስርየት በዚህ ዘመን ብዙዎቹ ክርስቲያኖች በሚሹት የንስሐ ጸሎቶች አማካይነት በየቀኑ ይቅርታን እንደ ማግኘት አይደለም፡፡ ይህ እውነት ጌታ በየቀኑ ሐጢያት እንደምንሰራ አስቀድሞ ስላየ በተጠመቀ ጊዜ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች በሙሉ እንደወሰደ ይናገራል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር በልጁ ጥምቀትና ስቅለት ጽድቁን ሁሉ ፈጽሞዋል፡፡ ኢየሱስ ስለተጠመቀ በመስቀል ላይ ደሙን ስላፈሰሰና ከሙታን ስለተነሳ የእግዚአብሄር ጽድቅ ሁሉ ተፈጽሞዋልና፡፡
 
በዚህ ዘመን አብዛኞቹ ክርስቲያኖች የንስሐ ጸሎቶችን በማቅረብ ሐጢያቶቻቸው እንደሚሰረይ ያምናሉ፡፡ ይህ በእርግጥ እውነት ነውን? በፍጹም አይደለም፡፡ ሰው ከገደለ በኋላ የንስሐ ጸሎቶችን በማቅረብ ሐጢያቶቹ እንደሚሰረዩለት የሚያስብ ሰው ተሳስቷል፡፡ የዚህ አይነቱ አስተሳሰብ የሰው አስተሳሰብ ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር አንጻር ሐጢያቶቹን ለማስወገድ ሁልጊዜም የሐጢያትን ዋጋ መክፈል ያስፈልገዋል፡፡ ይህንን ለማድረግም እግዚአብሄር ልጁ ኢየሱስ እንዲጠመቅና ደሙን በመስቀል ላይ በማፍሰስም ሐጢያቶቻችንን ሁሉ እንዲደመስስ አደረገው፡፡ የሰዎች ሐጢያቶች ሊነጹና ሊወገዱ የሚችሉት የንስሐ ጸሎቶችን በማቅረብ ሳይሆን በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በማመን ነው፡፡
 
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹በአንድ ሰው በደል ብዙዎች ሞተዋልና፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄር ጸጋና በአንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ  ለብዙዎች በዛ፡፡›› እግዚአብሄር የደህንነት ስጦታ የተትረፈረፈ ነው፡፡ ቧንቧው ሌሊቱን ሙሉ በሚፈስስበት ጊዜ ውሃው እንደሚጎርፍ ሁሉ እኛም ምንም አይነት ሐጢያቶችን እንስራ የእርሱ ማዳን እኛን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ለማዳን የተትረፈረፈ ነው፡፡
 
ኢየሱስ በጥምቀቱ የዓለምን ሐጢያቶች ወስዶዋል፡፡ የእግዚአብሄር ማዳን እኛ ከሰራናቸው በደሎች በላይ እጅግ የሚልቅ ስለሆነ ከዳንን በኋላም እንኳን የእርሱ ማዳን የትተረፈረፈ ነው፡፡ ይህ ግልጽ ነውን?       
 
 
በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል፡፡
 
ቁጥር 16 እና 17 እንዲህ ይላል፡- ‹‹አንድ ሰውም ሐጢአትን በማድረጉ እንደሆነው መጠን እንደዚያው ስጦታው አይደለም፡፡ ፍርድ ከአንድ ሰው ለኩነኔ መጥቶአልና፡፡ ስጦታው ግን በብዙ በደል ለማጽደቅ መጣ፡፡ በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሰ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሳሉ፡፡››   
 
በአንድ ሰው በደል ሞት በሰው ሁሉ ላይ ነገሰ፡፡ ይህም የአንድ ሰው የአዳም ሐጢያት ሁሉም ሁሉም ሐጢያተኞች እንዲሆኑ አደረጋቸው፡፡ በዚያ ሐጢያት ምክንያትም ሰው ሁሉ የእግዚአብሄርን እርግማን ይጋፈጣሉ፡፡ ሐጢያት ያደረገ ማንኛውም ሰው መሞትና ወደ ሲዖል መውረድ ነበረበት፡፡ በተመሳሳይ መንገድ የእግዚአብሄር ጽድቅ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በሕይወት ይነግሳል፡፡ የተትረፈረፈውን የጸጋና የጽድቅ ስጦታ የተቀበሉ ሁሉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመናቸው የደህንነት ስጦታ ተሰጥቶዋቸዋል፡፡ እነርሱ ከእግዚአብሄር ዘንድ እጅግ የላቀ ጸጋን ይቀበላሉ፡፡ በሕይወትም ይነግሳሉ፡፡
 
ቁጥር 18 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኩነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደመጣ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ፡፡››
 
እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ጠይቀን መልሱን መስጠት አለብን፡፡ ‹‹በአንድ ሰው ሐጢያት ሁላችንም ሐጢያተኞች መሆናችን እውነት ነው? ሐጢያተኞች የሆናችሁት በራሳችሁ ሐጢያቶች ነው ወይስ አዳም በእግዚአብሄር ላይ በፈጸመው በደል? ሁላችንም ሐጢያተኞች የሆንነው በአዳም በደል ከሆነ ኢየሱስ እኛን ከሐጢያቶቻችን ለማዳን በሰራው የጽድቅ ሥራ የሚያምኑ ሰዎች ጸድቀዋል፡፡ አንድ ሰው በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምን ከሆነ ሐጢያቱ በእርግጥ ተወግዶዋልን? -- አዎ-- እርሱ ሐጢያት አልባ ሆንዋል፡፡
 
‹‹በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ፡፡›› የእግዚአብሄርን ነጻ የጽድቅ ስጦታ መቀበል ማለት በኢየሱስ አምኖ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የዳነ ሰው ቅድስና ላይ ለመድረስ በየቀኑ የንስሐ ጸሎቶችን ማቅረብ አለበት ማለት አይደለም፡፡ በፍጹም! ሐዋርያው ጳውሎስ ‹‹በእምነት ማጽደቅ››ን ሲናገር ‹‹ጽድቅን በእምነት ማግኘት›› ተብሎ ስለሚጠራው የክርስትና ትምህርት መናገሩ አይደለም፡፡
 
አብዛኞቹ ክርስቲያኖች በልባቸው ውስጥ ሐጢያት አለባቸው፡፡ ምክንያቱም የሚያምኑት በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደሙ ብቻ ነውና፡፡ ስለዚህ ‹‹በልባችን ውስጥ ሐጢያቶች ቢኖሩም እርሱ ሐጢያት አልባ እንደሆንን አድርጎ ይቆጥረናል›› ብለው ራሳቸውን በማጽናናት ሐጢያቶችን በልባቸው ውስጥ ለመደበቅ ሲሉ የመንጻትን ትምህርት ይቀበላሉ፤ ያምኑበታልም፡፡ ነገር ግን ይህ ትምህርት አስቂኝ ስለሆነ ይገርማል፡፡        
 
ቁጥር 19 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ሐጢያተኞች እንደሆኑ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ፡፡››
 
እዚህ ላይ ያልታዘዘ ሰውና የታዘዘ ሰው አሉ፡፡ አንዱ አዳም ሲሆን ሌላው ደግሞ የሰው ዘር አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር፡፡ የአዳም አለመታዘዝ የሰውን ዘር በሙሉ ሐጢያተኞች ስላደረገ ኢየሱስ በዮሐንስ በመጠመቅ፣ ለዓለም ሐጢያቶችም በመስቀል ላይ በመሞትና እኛን ከሐጢያቶቻችን ለማዳን ዳግመኛ በመነሳት ሰዎችን ከእግዚአብሄር ጋር ለማስታረቅ የአባቱን ፈቃድ ታዘዘ፡፡ እግዚአብሄር አብ በኢየሱስ የሚያምኑትን ምዕመናን ሁሉ በጽድቁ ፈጽሞ አጽድቆዋቸዋል፡፡
 
ቁጥር 20 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ፡፡ ዳሩ ግን ሐጢአት በበዛበት ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ፡፡››
 
ሕግ የገባው በደላችንን ለማብዛት እንደሆነ ተነግሮዋል፡፡ ሰዎች የአዳም ዘር በመሆናቸው ከመነሻው በሐጢያት የተወለዱ ናቸው፡፡ ነገር ግን ሐጢያትን እየሰሩም እንኳን ሐጢያትን አላወቁትም፡፡ ሰው ያለ ሕግ ሐጢያት ሐጢያት መሆኑን በፍጹም አያውቅም፡፡ ሰው ሐጢያቶቹን ወደ ማየት የሚመጣው በእግዚአብሄር ሕግ አማካይነት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ሕጉን ስናውቅ ሐጢያቶቻችንንም ይበልጥ ማወቅ እንጀምራለን፡፡ ሰዎች ከመጀመሪያውም በሐጢያቶች የተሞሉ ቢሆኑም ሕጉን ከተቀበሉ በኋላ ቀስ በቀስ የሐጢያት ምግባሮቻቸውን ወደ መገንዘብ እስኪደርሱ ድረስ ስለ ሐጢያተኝነታቸው አያውቁም፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ›› ይላል፡፡
 
‹‹ዳሩ ግን ሐጢአት በበዛበት ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ፡፡›› ይህ ማለት ሰው ሐጢያቶቹን በእግዚአብሄር ሕግ አማካይነት ያውቅና በእርሱ ጽድቅ በማመን የእርሱ ልጅ ይሆናል ማለት ነው፡፡ የሰው ዘር የእግዚአብሄርን ጽድቅ በያዘው እውነተኛ ወንጌል አማካይነት የእግዚአብሄርን ጸጋ መረዳት የሚችለው በሕጉ አማካይነት ጉድለቶቹንና ሐጢያተኝነቱን ሲያውቅ ብቻ ነው፡፡ በሕጉ ፊት ሐጢያቶቻቸውን በሚገባ የሚያውቁ ሰዎች መጨረሻቸው ሲዖል እንደሚሆን ስለሚያምኑ በላቀ ምስጋና በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ሞቱ ባዳናቸው ኢየሱስ ያምናሉ፡፡ በሕጉ አማካይነት ሐጢያተኝነታችንን አብዝተን በተረዳን ቁጥር በእግዚአብሄር ጽድቅ እንዲህ ያለ ትልቅ መዳን በመመስረቱ ይበልጥ አመስጋኞች እንሆናለን፡፡
 
ቁጥር 21 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሐጢአት በሞት እንደነገሰ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሳ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግስ ዘንድ፡፡››
 
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሐጢያት በሞት እንደነገሰ ተነግሮዋል፡፡ ነገር ግን ውሃውንና የኢየሱስን ደም የያዘው የእግዚአብሄር ጸጋ ከእርሱ ጽድቅ የመነጨ ነው፡፡ የእርሱ ጽድቅ ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ስላዳነን የእግዚአብሄር ልጆች ሆነናል፡፡
 
የቅድስና ትምህርትና የመንጻት ትምህርት ከሰው ስነ አመክንዮ የመነጩና የእግዚአብሄርን ቃሎች ከማያውቁ ሰዎች የፈለቁ ስሜት የማይሰጡ መላ ምቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ትምህርቶች በፍልስፍና የተካኑ የስነ መለኮት ምሁራን ያመነጩዋቸውና ፈጽሞ ሊቀናጁ የማይችሉ ማጭበርበሪያዎች ናቸው፡፡ የእግዚአብሄር እውነቶች ግልጽና የማይነቃነቁ ናቸው፡፡
 
እኛ በሰው ሥጋ ምሳሌ አምላክ ሆኖ የመጣው ኢየሱስ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ እንዳዳነን በማመን ከዓለም ሐጢያቶች ድነናል፡፡ በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች ድነዋል፡፡ በዚህ ታምናላችሁን? --አዎ--፡፡
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ የምታምኑ ከሆናችሁ ድናችኋል፡፡ በእርግጥም ከሐጢያቶቻችሁ ሁሉ ነጻ ወጥታችኋል፤ ድናችሁማል፡፡ ቅድስና ላይ ለመድረስ ያለ ማቋረጥ የንስሐ ጸሎቶችን በመጸለይና እንከን የሌለበት ሕይወት በመኖር መዳን እንደምትችሉ ሙጭጭ የምትሉ ከሆነ ያለ ኢየሱስ መዳን እንደምትችሉ በግትርነት እየከረራችሁ ነው፡፡ የቅድስና ትምህርት እውነትን ወደዚያ ገፍቶ በራስ ምግባሮች መዳን የሚቻል መሆኑን የስህተት ትምህርት ቢያስተምርም ወደ ደህንነት መግቢያው ብቸኛ በር ኢየሱስ ነው፡፡
 
የሕጉን 0.1% መፈጸም አለመቻል 100% መፈጸም ከአለመቻል ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከሕጎቹ 0.1% እንኳን መታዘዝ እንደማንችል ነግሮናል፡፡ በግምት የሕጉን 5% እየፈጸሙ ስለመሆናቸው የሚያስቡና በጊዜ ሒደት ውስጥ ወደ 10% ለማሳደግ የሚያቅዱ ሰዎች አቅሞቻቸውን የማያውቁና የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚቃወሙ ሰዎች ናቸው፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ በራሳችሁ እሳቤና ሎጂክ ለመረዳት አትሞክሩ፡፡  የእርሱ ጽድቅ ከሐጢያቶቻችን አድኖን እኛም የእርሱ ልጆች እንሆን ዘንድ በዚህ ጽድቅ እንድናምን እየጠበቀን ነው፡፡
 
እግዚአብሄር ሁሉን ቻይና መሐሪ ስለሆነ በጽድቁ በአንድ ጊዜ አድኖናል፡፡ እኛን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ፈጽሞ ላዳነን የኢየሱስ ጥምቀትና የመስቀል ላይ ደሙ እግዚአብሄርን እናመሰግናለን፡፡