Search

Preken

ርዕስ 10፡ ራዕይ (በራዕይ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[15-2] የዘላለማዊው ዕጣ ፈንታ መለያ ነጥብ፡፡ ‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 15፡1-8 ››

የዘላለማዊው ዕጣ ፈንታ መለያ ነጥብ፡፡
‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 15፡1-8 ››
 
ምዕራፍ 15 ቅዱሳኖች እግዚአብሄርን በተቃወሙት ጠላቶቹ ላይ የሚወርዱትን የሰባቱን ጽዋዎች መቅሰፍቶች ያብራራል፡፡ በራዕይ ውስጥ በተለምዶ የሚታየው እንደ ሰባቱ ማህተሞች፣ ሰባቱ መለከቶችና ሰባቱ ጽዋዎች ያሉትን የያዘው ‹‹ሰባት›› ቁጥር የእግዚአብሄርን ፍጽምናና ሁሉን የሚገዛውን ሐይሉን ያመላክታል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን የሚያውቅና ሁሉን የሚችል አምላክ ነው፡፡ ኢየሱስ ለእኛ ሁሉን አዋቂና ሁሉን ቻይ አምላክ መሆኑ ጌታችን ምንም ነገር የማይሳነው ሁሉን የሚገዛ አምላክ መሆኑን ያሳያል፡፡ ጌታችን ሁሉን ነገር ያቀደና ሁሉን መፈጸም የሚችል ራሱ አምላክ ነው፡፡
 
ስለዚህ ቅዱሳን በዚህ ዓለም ላይ በሚያወርዳቸው የሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶች አማካይነት ስለሚገለጠው ሁሉን አዋቂና ሁሉን ቻይ ሐይሉ ጌታን ማመስገን አለባቸው፡፡ እንዲህ ያለ ፍርድ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው በእርሱ ሁሉን አዋቂነትና ሁሉን ቻይነት ስለመሆኑ እውነታ ጌታችንን እናመሰግነዋለን፡፡ ጌታ በሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶችና በዘላለማዊ የሲዖል ስቃይ ጠላቶቹን የሚበቀል መሆኑ ቅዱሳን አመስጋኞች ሊሆኑ የሚችሉበትና እጅግ ተገቢም ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ቅዱሳን ጌታን ከማመስገን በቀር ምንም ሊያደርጉ አይችሉም፡፡ ሐሌሉያ!
 
የሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶች የሚወርዱት የሰባቱ ዓመት ታላቅ መከራ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመታት ተኩል ጥቂት እንዳለፉ ነው፡፡ ከእነዚህ የሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶች የተነሳ የእግዚአብሄር ጠላቶች ልብ ይሸበራል፡፡ ጌታችን ሁሉን የሚገዛ አምላክ መሆኑን ሲያውቁ ይፈሩታል፡፡
 
በቁጥር 1 ላይ ተጠቀሰው ‹‹ታላቅና ድንቅ የሰማይ ምልክት›› የሚያመለክተው በዚህ ዓለም ላይ የሚወርዱትን የመጨረሻ መቅሰፍቶች ማለትም የሰባቱን ጽዋዎች መቅሰፍቶች ነው፡፡ በሌላ በኩል ‹‹ታላቅና ድንቅ›› የሚለው ሐረግ ሦስት ነገሮችን ይነግረናል፡፡ መጀመሪያ ቅዱሳን በትንቢት ቃል አማካይነት አስቀድመው በዚህች ዓለም ላይ ስለሚወርዱት መቅሰፍቶች ሁሉ ያውቃሉ፡፡ ሁለተኛ ቅዱሳን ከሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶች ነጻ ይሆናሉ፡፡ ሦስተኛ ጌታ የሚያወርዳቸው የእነዚህ የሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶች ሐይል ዓለም ዓቀፋዊና ክፉኛም አውዳሚ ይሆናል፡፡
 
በሌላ በኩል የተዋጁትና የተነጠቁት ቅዱሳን በአየር ላይ ‹‹የእግዚአብሄርን ባርያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ›› ይዘምራሉ፡፡ ከዘጸዓት 15፡1-8 እንደሚታየው የዚህ ቅኔ ምንጩ እስራኤሎች በሙሴ ተመርተው ቀይ ባህርን ከተሻገሩ በኋላ ጌታን ስለ ሐይሉና ሥልጣኑ ያመሰገኑበት መዝሙር ነው፡፡ እነርሱ በግብጻውያን ጭፍሮች እየተሳደዱ ባለበት ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ጌታ በሐይሉና በሥልጣኑ ስላዳናቸው እርሱን ከማመስገን በቀር ምንም ማድረግ አልቻሉም ነበር፡፡
 
ልክ እንደዚሁ የአዲስ ኪዳን ቅዱሳኖችም ኢየሱስ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ተፈጽሞ በተገኘው የሐጢያት ስርየት አማካይነት ዘላለማዊ ደህንነትን በማግኘታቸው ጌታን ከማመስገን በቀር ምንም ማድረግ አይችሉም፡፡ የመጨረሻው ዘመን ሲመጣ የእግዚአብሄር ሕዝብ እንደገና ጌታን በማመስን ስለ ሰማዕትነታቸው፣ ትንሳኤያቸው፣ ንጥቀታቸውና የዘላለም ሕይወት ያወድሱታል፡፡ ይህ ሁሉ የተቻለው ከጠላቶቻቸውና ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ባዳናቸው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ነው፡፡
 
በተጨማሪም የዚህ ቅኔ ጠቃሚው መለያው የእግዚአብሄርን ሁሉን ቻይነት፣ ግርማ ሞገስና ጽድቅ ማወደሱ ነው፡፡ ሰማዕትነት ጌታን ለሐይሉ፣ ከሐጢያት ለዳኑበት ጸጋቸውና ለዘላለም ሕይወት በረከት ከማመስገን በቀር ምንም ማድረግ አይችሉም፡፡
 
በቁጥር 5 ላይ ‹‹የምስክሩ ድንኳን መቅደስ›› የሚለው የሚያመለክተው እስራኤሎች ከግብጽ በወጡ ጊዜ ጌታን የማጀብ በረከት ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሄር የፈቀደላቸውን ድንኳን ነው፡፡
 
በቁጥር 6 ላይ የተጠቀሰው ‹‹ቀጭን የተልባ እግር›› የሚያመለክተው የእግዚአብሄርን ጽድቅ ነው፡፡ ይህም መላዕክቶች የጌታን ጽድቅ እንደሚለብሱና የትኛውም ጠላት ሊንቀው የማይችለውን የፍርድ ዓይነት ለመበየን ከእርሱ ዘንድ ሥልጣንን እንደሚቀበሉ ይነግረናል፡፡
 
ቁጥር 8 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከእግዚአብሄርም ክብርና ከሐይሉ ጢስ በመቅደሱ ሞላበት፡፡ የሰባቱም መላእክት ሰባት መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ አንድ ስንኳ ወደ መቅደሱ ይገባ ዘንድ አልቻለም፡፡›› እዚህ ላይ ሦስት ፍቺዎችን ማግኘት እንችላለን፡፡ የመጀመሪያው የእግዚአብሄር ቁጣ በጠላቶቹ ላይ ምን ያህል የተሟላ እንደሆነ ነው፡፡
 
ሁለተኛው ማንም ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትና በደሙ ሳያምን ወደ እግዚአብሄር መቅደስ መግባት እንደማይችል ይነግረናል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሄር ለሐጢያተኞች የሚሰጠው ደህንነት ፍጹም ነውና፡፡
ሦስተኛው የሰው በጎነት ማንንም ሰው የእግዚአብሄርን የጽድቅ ፍርድ ማስመለጥ እንደማይችልና ሰው በሐጢያተኞች ላይ ከሚወርደው የእግዚአብሄር ቁጣ ማምለጥ የሚችለው በኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትና በደሙ በማመን ብቻ እንደሆነ ያሳየናል፡፡
 
ስለዚህ ቅዱሳን ወንጌልን አጥብቀው መያዝና እስከ መጨረሻዋ ቅጽበት ድረስ መስበክ አለባቸው፡፡ እስከ አሁን ድረስ የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ያልተቀበሉትም የእግዚአብሄርን የጽድቅ ፍርድ ለመቀበል እንደታጩ መረዳትና በተቻለ ፍጥነት ጌታ ወደሰጠው የውሃና የመንፈስ ወንጌል መመለስ አለባቸው፡፡ እግዚአብሄር በሰባቱ ጽዋዎች ሰባት መቅሰፍቶች በጠላቶቹ ላይ የሚያወርደው ፍርድ ሁሉም ያየው ዘንድ እንከን የሌለበት ስለሚሆን ይህ የሐጢያት ፍርድ በሙሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ማንም ሊያቆመው እንደማይችል ምንባቡ ያሳያል፡፡
 
ዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 15 ጸረ ክርስቶስ፣ ሰይጣን፣ አጋንንቶችና በክርስቶስ ፍቅር የቀረበልንን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የሚቃወሙና የማያምኑ ሁሉ የጌታችን ጠላቶች ናቸው፡፡ ይፈርድባቸው ዘንድ በእግዚአብሄር ጠላቶች ላይ እነዚህን መቅሰፍቶች በማምጣቱ ጌታን አመሰግነዋለሁ፤ አወድሰውማለሁ፡፡ ቅዱሳን ጌታን በእግዚአብሄር ማደርያ በሙሴ ቅኔና በበጉ ቅኔ ማመስገናቸው ተገቢ ነው፡፡
 
የጌታን ጽድቅ፣ ሐይል፣ ግርማ ሞገስና እውነት ከማመስገን ሊያስቆመን የሚችል ማንም የለም፡፡ እንዲህ ያሉ በረከቶችን ስለሰጠን ጌታን አመሰግነዋለሁ፡፡ ሐሌሉያ!