Search

FAQ over het Christelijke Geloof

Onderwerp 1: Wedergeboren zijn uit het water en de Geest

1-26. የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ማብራሪያ ልታቀርብልኝ ትችላለህ?

መርፌ ውጭ አንድ ቦታ ላይ ቢወድቅብን ምናልባትም በጠፋበት አካባቢ እንፈልገው ይሆናል። ነገር ግን ውስጥ ብሩህ ስለሆነ ብቻ በቤት ውስጥ የጠፋውን ነገር ለመፈለግ መሞከር ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው። በዘመኑ ቤተክርስቲያኖች ውስጥም እንዲሁ ያሉ ግራ የሚያጋቡ አንዳንድ ሰዎች አገኛለሁ። ስለ ምዕመናን የውሃ ጥምቀት ፍጻሜ በሌላቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክርክሮች ውስጥ በቀላሉ ተሳትፈው እያሉ “ኢየሱስ ለምን በመጥምቁ ዮሐንስ ተጠመቀ” የሚለውን ይህንን አስፈላጊ ጥያቄ ፈጽሞ አይጠይቁም። እንዲህ ካለው ዝንባሌ የተነሳ በዛሬው የክርስቲያን ማህበረሰብ ውስጥ ብዙ የቤተክርስቲያን ክፍልፋዮችና ሃይማኖታዊ ቡድኖች አሉ።
እነዚህን ማብቂያ የሌላቸውን ክርክሮች ወደ ፍጻሜ ለማምጣት ራሳችንን ከግርግሩ መንደር ማውጣትና መርፌያችንን ወደጣልንበት ሥፍራ መመለስ ይገባናል። እውነትን ከልባችን የምንሻ ከሆንን ከአመለካከት ዓይነተኛነት መላቀቅ አለብን፣ ምክንያቱም ይህንን በሐይማኖት መንደር ውስጥ ልናገኘው አንችልምና። ሐዋርያት በኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ላይ ብዙ ትኩረት ያደረጉት ለምንድነው?
ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም” (ዮሐንስ 3፡5)። መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ከኃጢአቶቻችን ሁሉ ሊያድነን በውሃና በደም እንደመጣ ይነግረናል (1ኛ ዮሐንስ 5፡6)። የደሙ ትርጉም በመስቀል ላይ የሞተው ሞቱ ነው። ታዲያ ‘ውሃ’ ስትል ምን ማለትህ ነው? መጥምቁ ዮሐንስ ለምን ኢየሱስን አጠመቀው? ከጥምቀቱ በፊትስ ለምን “አሁንስ ፍቀድልኝ፥ እንደዚህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው” (ማቴዎስ 3፡15) ብሎ አወጀ?
የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በተለይም የኢየሱስን ጥምቀት እንደተረዳህና እንደምታምን ከልቤ ተስፋ አደርጋለሁ። እርሱ ለደቀ መዛሙርቱ ስለሰጣቸው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አንዳንድ አጫጭር ማብራሪያዎች እነሆ። ሐዋርያት ወንጌልን በሰበኩ ጊዜ በኢየሱስ ጥምቀት ላይ እጅግ ታላቅ ትኩረት አድርገዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ አለ፦ “እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ” (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡3-4)።
“መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ” ምን ማለት ነው? ይህ ማለት የእርሱ ሞት በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በሰጠው ዘዴ መሠረት ኃጢአቶቻችንን በሙሉ አስተሰርዮዋል ማለት ነው። እርሱ በብሉይ ኪዳን መገለጥና ቃል ኪዳን መሠረት ስለእኛ ሞተ። ዕብራውያን 10፡1 እንዲህ ይላል፦ “ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና።” በዘሌዋውያን 1፡3-5 ላይ ያለውን ዓይነተኛ መስዋዕት እንመልከት። ኃጢአተኛው የኃጢአቶቹን ስርየት ለማግኘት የሚቃጠለውን መሥዋዕቱ ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይገባዋል።
1) ነውር የሌለበት መሥዋዕት ማቅረብ ነበረበት (ዘሌዋውያን 1፡3)።
2) እጆቹን በመሥዋዕቱ ራስ ላይ መጫን ነበረበት (ዘሌዋውያን 1፡4)። እዚህ ላይ የእግዚአብሔርን ሕግ ግልጽ ማድረግ ይገባናል፦ በመሥዋዕቱ ራስ ላይ እጆችን መጫን ኃጢአቶቹን ወደ መሥዋዕቱ ለማስተላለፍ የእግዚአብሔር ሕግ ነው።
3) ኃጢአቱን ለማስተሰረይ መሥዋዕቱን መግደል ነበረበት (ዘሌዋውያን 1፡5)።
አሮን በማስተስረያ ቀን ሁለቱንም እጆቹን ሕያው በሆነው ፍየል ራስ ላይ ጭኖ፣ ኃጢአቶቻቸውን ሁሉ በሚመለከት የእስራኤልን ልጆች በደሎችና መተላለፎች ሁሉ በእርሱ ላይ ይናዘዛል፣ በፍየሉም ራስ ላይ ያኖራቸዋል (ዘሌዋውያን 16፡21)። በዚያን ዘመን አሮን የእስራኤል ተወካይ ነበር። እጆቹን በፍየሉ ራስ ላይ የሚጭነው እርሱ ብቻ ነው፣ የእስራኤሎች (ወደ 2-3 ሚሊዮን አካባቢ) ዓመታዊ ኃጢአቶች በሙሉ ወደ እርሱ ይተላለፉ ነበር። የብሉይ ኪዳን መሥዋዕት ሊመጡ ያሉ በጎ ነገሮች ጥላ ነበር። ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት እኛን ሊቀድስ በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ።
በመጀመሪያ ኢየሱስ ነውር የሌለበት የእግዚአብሔር በግ ለመሆን የሰው ሥጋ ለብሶ መጣ። እርሱ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅና “የባሕርዩ ምሳሌ” (ዕብራውያን 1፡3) ነው። ስለዚህ ለሰው ዘር ሁሉ የሚሆን የኃጢአት መሥዋዕት ለመሆን ተገቢ ነው።
ሁለተኛ መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን በዮርዳኖስ አጠመቀው። ጥምቀት የተሰጠው “እጆችን በመጫን” መልክ ሲሆን፣ መጥምቁ ዮሐንስም የአሮን ዘርና የሰው ዘር ሁሉ ተወካይ ነው። ዮሐንስ በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ እጆቹን በጫነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር በደነገገው ሕግ መሠረት የዓለም ኃጢአቶች በሙሉ ወደ እርሱ ተላለፉ። ኢየሱስ ዮሐንስን “አሁንስ ፍቀድልኝ፥ እንደዚህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና” ከዚያም ዮሐንስ አጠመቀው። በመጨረሻ ኃጢአቶቻችን በሙሉ ወደ እርሱ ተላለፉ። በማግስቱ ዮሐንስ እንዲህ ብሎ ጮኸ፦ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ዮሐንስ 1፡29)።
ሦስተኛ ኢየሱስ “ተፈጸመ” (ዮሐንስ 19፡30) በማለት ኃጢአቶቻችን ሁሉን ለማጥፋት በመስቀል ላይ ሞተ። በእግዚአብሔርም ፊት እኛን ጻድቃን ለማድረግ ከሙታን ተነሣ። ኃጢአትን ለማጥፋት የኃጢአት መሥዋዕት እንደሚቀርብ አስታውሱ። አንድ ኃጢአተኛ መሥዋዕቱን ከመግደሉ በፊት እጆቹን በመሥዋዕቱ ራስ ላይ መጫን ነበረበት። አንዲት ደረጃ ቢረሳ፣ ማለትም እጆቹን በመሥዋዕቱ እንስሳ ራስ ላይ ማኖሩን ቢገድፍ ዓመጽን በመፈጸሙ ምክንያት መዳን አይችልም ነበር። አንድ ክርስቲያን የኢየሱስ ጥምቀት ምን ማለት እንደሆነ የማያውቅ ከሆነ ይህ ሰው በልቡ ውስጥ ኃጢአቶች ያሉበት በመሆኑ በራሱ እምነት ብቻ መዳን አይችልም።
አብዛኞቹ ክርስቲያኖች የሚያውቁት የእርሱን የጽድቅ ምግባር ግማሽ ብቻ ነው። ሐዋርያው ዮሐንስ በመጀመሪያው መልዕክቱ ውስጥ ወንጌልን ግልጽ አድርጎታል፦ “በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም። መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው” (1ኛ ዮሐንስ 5፡6-7)። የእርሱ ጥምቀት ለመዳናችን ያለውን የጽድቅ ምግባሩን ለማጠናቀቅ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የሚደግፉ ብዙ ምንባቦች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ።

ክርስቲያኖች ሁሉ ወደ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል መመለስ ይገባቸዋል።