Search

FAQ over het Christelijke Geloof

Onderwerp 3: Openbaring

3-4. ባቢሎን ምንድነች? 

ባቢሎን የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው ከእግዚአብሄር የተለየውን ይህንን ዓለም ለማመልከት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ‹‹የባቤል ግንብ›› ታሪክ ሊገኝ ይችላል፡፡ ሰዎች ጉልበታቸውን አስተባብረው እግዚአብሄርንም ትተው የባቤልን ግንብ ለመገንባት በፈለጉ ጊዜ እግዚአብሄር ግንቡን እንዳይገነቡ ከለከላቸው፡፡ ግንቡንም አፈረሰው፡፡ ቋንቋቸውንም ደባለቀው፤ እነርሱንም በተናቸው፡፡ 
ይህም ዓለም ልክ እንደ ባቤል ግንብ ዘመን ነው፡፡ የምድር ነገሥታት አመንዝረዋል፡፡ በዚህ ዓለም ነገሮችም በቅምጥልነት ኖረዋል፡፡ ነጋዴዎችም ሁሉ እርሱ የሰጣቸውን ነገር በመሸጥና በመግዛት በጣም ባተሌ ሆነው በሕይወታቸው ውስጥ እግዚአብሄርን ቸል ብለውታል፡፡ ሐሰተኛ ነቢያቶችም ሐይማኖትን በመጠቀም ብዙ እያወሩ ሕይወታቸውን ኖረዋል፡፡ የሰዎችን ነፍሳት የሚሸጡ ነጋዴዎችም ሆነው የዚህን ዓለም ቁሳዊ ሐብቶች በመሰብሰብ አዱኛን አከማችተዋል፡፡ የሰው ዘር እስከ አሁን ድረስ ከሰራው ዓለም ሁሉ የአሁኑን ዓለም የሚወዳደር ዓለም አልተገነባም በማለት ዓለምን ወድደዋል፡፡    
ልክ እንደዚሁ የመጨረሻው ዘመን ሲመጣ ይህ ዓለም በእግዚአብሄር ፊት ስለሚረክስና ሐጢያትም እጅግ ስለሚበዛ እግዚአብሄር ራሱ የፈጠረውን ዓለም ከማጥፋት በቀር ምርጫ አይኖረውም፡፡ የዚህ ዓለም ሰዎች ዓለምን አብዝተው ስለሚወዱ አምላካቸው እንደሆነ በመቁጠር ያምኑበታል፤ ይከተሉታልም፡፡ ከዚህ የተነሳ ይህ ዓለም የሐጢያት ምንጭ ሆንዋል፡፡ በዚህ የሐጢያት ምንጭ ውስጥ የሚኖረው ሕዝብም ሁሉንም ዓይነት ሐጢያት ጠጥቶዋል፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሐጢያቶች የዓለም ውድቀት ሆነዋል፡፡ ከዚህ የተነሳም ምድር እግዚአብሄር በሚያወርዳቸው የሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶች የመጨረሻ ጥፋትዋን ትጋፈጣለች፡፡ 
ይህ ዓለም ከእግዚአብሄር ዘንድ የሚወርዱትን የሰባቱን ጽዋዎች መቅሰፍቶች የሚጋፈጠው በውስጡ የሚኖረው ሕዝብ ዓለምን በመውደድ የሰይጣንና የጸረ ክርስቶስ አገልጋዮች በመሆን ጥረታቸውን ከጸረ ክርስቶስ ጋር አቆራኝተው ጌታ በሰጠው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ዳግመኛ የተወለዱ ቅዱሳኖችን በመግደላቸው ነው፡፡ 
የመጨረሻው ዘመን ሲመጣ ሰዎች ለጸረ ክርስቶስ በማጎብደድ እርሱ የሰጠውን የሰይጣንን ምልክት ተቀብለው የክፉው አገልጋዮች ይሆናሉ፡፡ ከጸረ ክርስቶስ ጋር የሚያሴሩት የዚህ ዓለም ሕዝቦች እግዚአብሄርን ስለተቃወሙና ቅዱሳኖቹን ስለገደሉ እግዚአብሄር በቅዱሳኖች ላይ ስደትን፣ መከራን፣ ችግርንና ሞትን እንዳመጡ ሁሉ እንደዚያው ይከፍላቸዋል፡፡