The New Life Mission

መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች፤

ቋንቋ፤

አጋር ሠራተኛ ከሆንክና "መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች" በሚለው ላይ መልዕክትና ፎቶዎችን መለጠፍ የምትወድ ከሆነ "መልዕክት ለጥፍ" የሚለውን ቁልፍ ጠቅ አድርግና ግባ፡፡ ልጥፍህ የሚታየው የእኛን ይሁንታ ሲያገኝ ብቻ ይሆናል፡፡

መልዕክት ለጥፍ
ጠቅላላ፤ 6
 • ቁ.6 ወንጌልን ስንሰብክ በጥበብ ይሁን!

  ወንጌልን ስንሰብክ በጥበብ መስበክ እንዳለብን የእምነት አባቶቻችን ይመክሩናል! ያ እጅግ በጣም ድንቅ ምክር ነው! ወንጌልን በጥበብ መስበክ ማለት ከዕለት ዕለት ህይወትችን ስንነሳ ዳግም ካልተወለዱ ሰዎች ጋር በሚኖሩን የተለያዩ ግንኙነቶቻችን መልካም ግንኙነቶችን ማድረግ ይኖርብናል! ያም ወንጌልን በምንሰብካቸው ሰዓት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርልናል! ሌላው ለዓለም ህጎችም መገዛት ይኖርብናል ምክንያቱም የዓለም ህጎችን ተላልፈን ወንጌልን መስበክ አይቻልምና! የዓለም ህጎችን መታዘዝ ስንል ግን ሁሉንም ህጎች መቀበል ማለት አይደለም! መታዘዝ ያለብን እምነታችንን የማይነኩ ሲሆኑ ብቻና ብቻ መሆን አለበት! የእምነት አባቶቻችን እምነታቸውን የሚነኩ የዓለም ህጎችን አንቀበልም በማለት ሰማዕት ሆነዋል! እኛም የዛሬዎቹ ጻድቃን በእምነታችን የሚመጣብንን ማንኛውንም ነገር መታዘዝም ሆነ መቀበል የለብንም! በሌላ በኩል ወንጌልን በጥበብ መስበክ ማለት ባገኘናቸው የወንጌል በሮች ሁሉ በመጠቀም ወንጌልን መስበክ አለብን ማለት ነው! በሌላ አነጋገር አቅማችን በፈቀደው ሁሉ ወንጌልን መስበክ አለብን ማለትም ነው! ሁላችንም እዚጋ አንድ ማስታዋል ያለብን ነገር ወንጌልን በየትኛው ዘርፍ መስበክ እንዳለብን ማወቅ አለብን ያም ማለት የትኛው ዘርፍ ወንጌልን ለመስበክ እንደሚቀርበን መገንዘብ ማለት ነው! በቸርች ውስጥ ወንጌልን በማሰራጨት ሂደት ላይ ከትናንሽ ሀላፊነቶች ጀምሮ እስከ ትላልቅ ሀላፊነቶች አሉ! ለምሳሌ ቤ/ክንን ማጽዳት, ለወንጌል ስርጭት መውጣት, የተለያዩ የጉልበት ስራዎችን መስራት, ለቅዱሳን ምግብ ማብሰል, ስብከቶችን መስበክ, ዝማሬዎችን ማዘጋጀት ሌሎችም የመሳሰሉ ስራዎች ይኖራሉ! አንድ ጻድቅ ሁሉንም ሀላፊነቶች ብቻውን መወጣት በፍጽም አይችልም ሁላችንም ግን የየራሳችንን ሀላፊነቶች ስናውቅ ሀላፊነቶቻችንን በአግባቡ መወጣት እንችላለን እዚጋ ዋናው መልዕክት አንዳችን ያለአንዳችን በጋራ ካልሆነ በቀር በግላችን በፍጥነት መራመድ አለመቻላችን ነው! እኛ ቅዱሳን ባለንበት ውስብስብ ዓለም ውስጥ የውሀውንና የመንፈሱን ወንጌልን በአራቱም ማዕዘናት የማሰራጨት ሃላፊነት አለብን ይሄን ስል የእኔ ሃላፊነት ምንድነው በየትኛውስ ዘርፍ ነው ማገልገል ምችለው? ጥያቄውን ለራሳችን እየመልስን በምንችለው ሁሉ ወንጌልን መስበክ ይኖርብናል! ሁላችንም ባለን አቅም በትጋት ወንጌልን የምንሰብክ ከሆነ በዛም ድንቅ ስራ እስከመጨረሻው የምንጸና ከሆነ ወንጌላችን በመላው ዓለም ይደረሳል ከዛም በእርግጥም ኢየሱስ ይመጣል የተስፋውንም ቃል ይጠብቃል! ከበደላችን ሁሉ ያነጻን እስካለንበት ጊዜ ድረስ በእምነት ያቆመን እግዚአብሔር ይመስገን እስከሞት ድረስት በሚታመን እምነትም ይባርከን! ወንድማችሁ Teferi Oshine Tanto Ethiopia/Hawassa

  • Teferi Oshine
  • Ethiopia
  • 05/10/2022 17
 • ቁ.5 የእምነት ምስክርነት

  ሰላም ቅዱሳን ጸጋው የበዛላችሁ ከእግዚአብሔር የተሰጠን እውነተኛው ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን! ዛሬ ከእምነት ምስክርነታችን እንድንማማር የእምነት ምስክርነቴን ልጽፍላችሁ ወደድኩ! እግዚአብሔር ቢፈቅድ በእምነት ህይወቴ የሚገጥሙኝን መልካምና ክፉ ገጠመኞቼን እንድንማርባቸው በቀጣይ ጊዜያት ልጽፍ እመኛለው!!! ዳግም መቼ እንደተወለድኩ ትክክለኛ ቀኑን ወሩንና አመቱን አላስታውስም!  ግን ጻድቅ ያደረገኝ እግዚአብሔር ይመስገን! እንዴት ዳግም እንደተወለድኩ ማብራራት እችላለው!  ከ6 አመቴ ጀምሮ እስከ 14 አመቴ ድረስ ያደኩት በፕሮቴስታንት ሀይማኖት ውስጥ ነበር! የውሃውን እና የመንፈሱን ወንጌል ለመጀመሪያ ጊዜ ከጎረቤት የሚኖር የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አርበኛ ስራውን ሊሰራ የመንደሩን ህጻናት ሰበሰበ በሰዓቱ እኔ የ10 አመት ልጅ ነበርኩ!  ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ 14 አመቴ በመንደራችን ከህጻናቱ ጋር ከአርበኛው የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እየሰማውና ቤተሰብ ከሚልከኝ ሀይማኖት ቤት በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ስላሉ ነብያት ታሪክ እየተማርኩ ቀጠልኩ በ11 እና 12 ዓመቴ፣ የክርስቶስን ጽድቅ መሰረታዊ የድነት እውቀት እየለየው መጣው!  ያም የክርስቶስ ጽድቅ በልቤ እንዲታተም አደረገ ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ!!!  13 እና 14 አመት ሲሆነኝ የክርስቶስ ፅድቅ በልቤ ሲያብብ አየሁ!  ስለ ሰው ማንነት፣ ስለ ሕግ፣ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ፣ ስለ ብሉይ ኪዳንኑና ስለ አዲስ ኪዳኑ የስርየት ሥርየት፣ ስለ ውኃ ደም መንፈስ መሠረታዊ የደኅነት እውቀትና በአጠቃላይ ስለ መንፈስ ቅዱስ ወንጌል የበለጠ ተረዳው።  ሳላስበው ወንጌልን ስሰብክ እና ውሸታሞችን እየተቃወምኩ የሬቨረንድ ፓውልሲ ጆንግን መጽሃፍ የማሰራጭ ሆኜ እያገለገልኩ መጣው!  ሀዋሪያው ጳውሎስ "እኔ ከሰበኩላችሁ ወንጌል ውጭ ማንም በሰብካችሁ የተረገመ ይሁን" ገላቲያ 1፥7-9  እንዳለው እኔም ከአውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ውጭ ሌላ ወንጌል ሁሉ ከሰይጣን መሆኑን የውሃውንና የመንፈሱ ወንጌል በመስበክ አረጋግጣለው! ወንጌላችን ሌላ አደለም (ኢየሱስ እንደመስዎዕቱ በግ ያለነውር ከሰማይ መቷል በእጆች መጫን ስርዓት በጥምቀቱ የዓለምን ሁሉ ሀጢአት ወስዷል ሰለሀጢአትም ዋጋን ሁሉ ከፍሏል በእርግጥም ሞቷል በሶስተኛውም ቀን ከሞት ተነስቷል የሚል ነው ሀሌሉያ!) በሚገርም ሁኔታ እዚሁ 14ኛ አመቴ ላይ እያለው ጥምቀት ምን ማለት እንደሆነ በደንብ ከተረዳው በኋላ ፕሮቴስታንቶች እድሜክ 14 ደርሷል ብለው የጥምቀት ትምህርት እንድጀምር ተነገረኝ! መንፈስ ቅዱስ ወደ ውቡ ወንጌል (የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል) ጠቅልሎ ሊወስደኝ ሲወድ ያንን አደረገ! እኔ ባህሪዬ ዝምተኛና አይንአፋር ነኝ¡ የዛን ቀን ግን በሙሉ ድፍረት የተለያዩ ጥያቄዎችንና ንግግሮችን ሳደርግ እንደነበር አስታውሳለው ከጥያቄዎቼ አንዱ ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ? የሚል ነበር ምንም እንኳን ብዙ እና ከእኔ ትላልቅ ቢሆኑም ኢየሱስ ለምን እንደተጠመቀ አያውቁም ነበር በተዋቡ ቃላት የተሳሳቱ መልሶችን ብቻ ይመልሳሉ! በንግግራቸው ሁሉም እንደህጻናት ይታዩኝ ጀመር! ከዛን ጊዜ ጀምሮ በእኔ ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን ማድረስ ጀመሩ ለጓደኞቼ በሙሉ ተፈሪ የስዕተት አስተምህሮት ውስጥ ገብቷል እርሱን እንዳትሰሙት የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጡ! በዚህ ሁሉ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ድፍረት ሲሆነኝ እምነትን ሲሰጠኝ አንደበቶቼን ሲዳስስ እንደነበር አያለው፡ በመጨረሻም የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አሸንፎ ሙሉ እኔነቴን ለውሃውና ለመንፈሱ ወንጌል አቅርብያለው በድጋሚ ምስጋን ለመንፈስ ቅዱስ ይሁን!!! ከዛን ጌዜ ጀምሮ ሳልቀላቅል ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ውሃ ጣፍጦኝ እየጠጣው ነው! ውቡ ወንጌላችን በዓለም ሁሉ ይድረስ!!! ሁላችንም እስከሞት ድረስ በእምነታችን እንድንጸና አባታችን ኢየሱስ በነገር ሁሉ ይርዳን! ወዳችኋለው ተባረኩ! ወንድማችሁ ተፈሪ ኦሺኔ ታንቶ Ethiopia/Hawassa

  • Teferi Oshine
  • Ethiopia
  • 11/19/2021 84
 • ቁ.4 አሁን ግን ከዚህ የዲያብሎስ ሽንገላ ነጻ የሚያወጡበትና ከኃጢአት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚድኑበት ዘመን መጥቷል። 

  አያሌ ክርስቲያኖች ክርስቶስ በመስቀል ላይ እንደሞተላቸው ቢያምኑም፣ ግን ኃጢአተኞች ናቸው። ኢየሱስ የአዳምን ወይም የውርስ ኃጢአት ብቻ እንዳስወገደ ስለሚያምኑ፣ በየዕለቱ ለሚሰሩት ኃጢአት ስርየትን ለማግኘት በእ/ር ፊት ያለቅሳሉ። በክርስቶስ ቢያምኑም ኃጢአተኞች እንደሆኑ ያስባሉ። አሁን ግን ከዚህ የዲያብሎስ ሽንገላ ነጻ የሚያወጡበትና ከኃጢአት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚድኑበት ዘመን መጥቷል።  Bereket Make Mara, Ethiopia

  • Bereket Make Mara
  • Ethiopia
  • 11/02/2021 34
 • ቁ.3 የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ከሐጢያት አድኖኛል፡፡

  ከዓመታት በፊት በአንድ ቢሮ ውስጥ እየሰራሁ አንድ ወጣት ባለ ጉዳይ ወደ ቢሮዬ መጣ፡፡ በእጁ ‹‹Have You Truly Been Born Again of Water and The Spirit?›› የሚል በእንግሊዝኛ የተጻፈ መጽሐፍ ይዞ ነበር፡፡ ርዕሱ ትንሽ እንግዳ ስለሆነብኝ ወጣቱ የሚፈልገውን ካሰተናገድሁት በኋላ መጽሐፉን አየው ዘንድ ቢፈቅድልኝ ብዬ ጠየቅሁት፡፡ ወጣቱም ‹‹እንዲያውም ትርፍ ስላለኝ ውሰደውና አንብበው›› በማለት ሰጠኝ፡፡ በአክብሮት ተቀበልኩት፡፡ ወደ ቤት ከተመለስሁ በኋላ በመደርደሪያዬ ላይ አስቀመጥሁት፡፡ ለአንድ ሳምንት ያህል አላየሁትም፡፡     አንድ ቀን ሌላ መጽሐፍ ስፈልግ ዓይኖቼ በዚህ መጽሐፍ ላይ አረፉ፡፡ የምፈልገውን መጽሐፍ ትቼ ይህንን መጽሐፍ ከመደርደሪያው ላይ ሳብ አድርጌ እንደ ነገሩ ማገላበጥ ጀመርሁ፡፡ የአንድ መጽሐፍ ምንነት የሚታወቀው መቅድሙን በማንበብ እንደሆነ ስለማውቅ የዚህን መጽሐፍ መቅድም ማንበብ ጀመርሁ፡፡ ምንም እንኳን በሃይማኖት ቤት ለረጅም ጊዜ ባሳልፍም የኢየሱስ ጥምቀት ከደህንነቴ ጋር ይገናኛል ብዬ አንዴም እንኳን አስቤ አላውቅም ነበር፡፡   በእጄ ላይ ያለው መጽሐፍ ፈጽሞ አዲስ የደህንነት እሳቤን አሳየኝ፡፡ የኢየሱስ ጥምቀትና ዳግመኛ ከውሃና ከመንፈስ መወለድ ለእኔ ፈጽሞ አዲስ መገለጦች ነበሩ፡፡ ይህንን መጽሐፍ በታላቅ ጉጉትና አውቆ ለመዳን በተከፈተ ልብ ማንበቤን ተያያዘሁት፡፡ የብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት ስርዓት፤ የእጆች መጫን፤ የመሥዋዕቶችን ደም የማፍሰስ ስርዓት በአዲስ ኪዳን ከኢየሱስ ጥምቀትና ሞት ጋር ያላቸውን ቁርኝት በሰፋት በተረዳሁ ጊዜ፤ ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን የእግዚአብሄር በግ ሆኖ ወደዚሀ ምድር በመምጣት የሰው ዘር ወኪል (ዮሐንስ 11፡11) በሆነው በአጥማቂው ዮሐንስ አማካይነት ሐጢያቶቼን በሙሉ በራሱ ላይ በጥምቀቱ መወሰዱን ሳውቅና ይህም በጥላው ለመስዋዕቶች በሚቀርቡት እንስሶች ላይ በሚደረገው የእጆች መጫን ስርዓት አማካይነት ከሚተላለፉት የሐጢያተኛው ሐጢያቶች ጋር መሳ ለመሳ እንደሚመሳሰል ስረዳ ለዚህ ትልቅ የመዳን ዕውቀት እጄን ወደላይ አንስቼ ከመማረክ በቀር ላደርገው የምችለው ነገር አልነበረም፡፡  ይህ የእውነት ብርሃን በልቤ ላይ በራ፡፡ ሐጢያት አልባ ያደረገኝ የኢየሱስ ጥምቀትና የመስቀል ላይ ሞቱ ነፍሴን በሐሴት ሞላት፡፡ ኢየሱስ ተጠምቆ ‹‹ጽድቅን ሁሉ በመፈጸም›› (ማቴዎስ 3፡15) የዘላለም ጽድቁን ስላወረሰኝ አሁን ጻድቅ ነኝ፡፡ ዳግመኛ ከተወለድሁም 18 ዓመት አልፎኛል፡፡ አሁን የ18 ዓመት መንፈሳዊ ወጣት ነኝ፡፡ ይህንን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ገናም በሐጢያት እስራት ውስጥ ላሉና በጨለማ ውስጥ ለሚዳክሩ መስበኬን አላቋረጥሁም፡፡  ክብር በውሃ፣ በደምና በመንፈስ (1ኛ ዮሐንስ 5፡6) ለመጣው፣ ሐጢያቴን ከላዬ ላይ እንዳረጀ  ልብስ ገፎ ለጣለውና አዲሱን የጽድቅ ልብስ ላለበሰኝ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን! አሜን!!  ካሳሁን አየለ, Ethiopia

  • Kassahun Ayele
  • Ethiopia
  • 10/31/2021 21
 • ቁ.2 ከእኔ ሕይወት ትማሩ ዘንድ የደህንነት ምስክርነቴን እንደሚከተለው አቀርባለሁ ።

  ሰላም! ዳንኤል ተስፋዬ እባላለሁ። ከእኔ ሕይወት ትማሩ ዘንድ የደህንነት ምስክርነቴን እንደሚከተለው አቀርባለሁ ። ተወልጄ ያደኩት  በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ ነው።አባቴ የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ሲሆን ከአንድም ሁለት ቦታ የመሠረተ ክርስቶስ ቤ/ክ በሌሉባቸው ቦታዎች ቤ/ክ በመትከል ብዙ ሰዎችን ጴንጤ አድርጉዋል።በቤተሰባችን ውስጥም ቋሚ የሆነ የማለዳ ፣የቀትርና የማታ ፕሮግራሞች ይደረጋሉ።ራሴን ወደ ማወቅ ደረጃ ላይ ስደርስ (የ7ተኛ ክፍል ተማሪ እያለው ነው) አንድ ቀን የምሽት ፕሮግራማችን ላይ አባቴ "ዳንኤል" ብሎ ሲጠራኝ "አቤት አባባ" አልኩኝ።"ጌታን መቀበል ትፈልጋለህ?" ሲለኝ ፣ ጥያቄው እንግዳ ስለነበረብኝና እኔ ጌታን ተቀብያለው ብዬ አስብ ስለነበር ፈራ ተባ እያልኩ "እንዴ አባባ እስከዛሬ ጌታን አልተቀበልኩም ማለት ነው? ለማለት አስቤ ፊት ፊቱን ሳየው" ሃሳቤ ገባው መሰለኝ ሳልጠይቀው እንዲህ አለኝ። ይኸውልህ ልጄ ክርስትና የሚወረስ ነገር አይደለም።ወደህ አምነህ የምትከተለው ነገር ነው።ሲለኝ እንዴ አባባ እኔ እኮ ክርስቶስን የምከተለው ወድጄ ነው አልኩት።ከዛም በል እንግዲህ ወደህ የምትከተል ከሆነ ተነስና እጆችህን ወደላይ በማንሳት እኔ የምለውን ደግመህ በማለት ጌታን ተቀበል አለኝ እኔም በደስታ እጄን አንስቼ አባቴ የሚለውን በመከተል"አለምንና ሴጣንን ክጃለው፤ኃጢያትን ክጃለው፤ጌታ ሆይ ስሜን በህይወት መዝገብ ላይ ፃፈው..." ስል ጌታን ተቀበልኩ።ከዛም የተለያዩ ትምህርቶችን በመከታተል ተጠመኩ ፣ወደ አገልግሎት ውስጥ ተሰማራው።እያደኩ ስመጣም የታዋቂ ፓስተሮችንና ወንጌላውያንን አገልግሎት በሬድዮ (በተለይ የምስራች ድምጽን)፣በመፅሄት፣እንዲሁም ስብከቶቻቸውን በካሴት አጥብቄ እከታተል ነበር፤ የሃይስኩል ተማሪ እያለው ትዝ ይለኛል፤ሃጢያት ያስጨንቀኝ፤ቅጀት ያስጨንቀኝ ጀመረ።የምሰማቸው ስብከቾች ሁሉ ተቀደስ፤ኃጢያት አትስራ ነው፤የምሰማቸው መገለጦች ያሳቅቁኝ ነበሩ" አንድ ሴት አለሽ/አንድ ሰው አለህ በቅርቡ ይሄንና ያንን ሃጢያት ሰርተሃል..." የሚሉ አሳቃቂ መገለጦች። እኔ በወቅቱ በአፍላ እድሜዬ ላይ እንደመገኘቴ በየቀኑ በተግባር ባላመነዝርም ባሳብ ግን የምዳራቸው ሴቶች ነበሩ፤እናም "አንድ ሰው አለህ አመንዝረህ የመጣህ"የሚሉ መገለጦችን በሰማው ቁጥር በጣም እሳቀቅ ነበር፤ከዛም ያው አንድ በተግባር የሚያመነዝር ሰው ስለማይጠፋ ያ ሰው ብድግ ሲል ሁፈይ እኔን አደለም ማለት ነው ብዬ እፅናናለው።ነገር ግን ለጊዜው ነው፤ወዲያው ሃጢያቴ እንደጭጋግ ይከበኝና እጨነቃለው።በዛ ላይ ለሊት በጣም ያቃዠኛል።እፀልያለው።አፀልያለው። ነገር ግን ሁሌም ኃጢያት ያስጨንቀኛል።ስለ ኃጢያቶቼ የንስሃ ፀሎት ፀልያለው።ደስ ይለኛል።ግን ደሞ ወዲያው ተመልሼ ራሴን ኃጢያት ስሰራ አገኘዋለው።ያኔ በቃ እኔ መቀደስ የማልችል ሰው መሆኔ ገባኝ።ባህሪዬ ጥሩ ስላልሆነ መፅሀፍ ቅዱስ መያዝ ራሱ አፍራለው።የማፍረው በመፅሀፍ ቅዱስ ሳይሆን በራሴ ባህሪ ነው። አንዳንድ እኔ በደንብ የማውቃቸው ሴትና ወንድ ጓደኞቼ መፅሀፍ ቅዱስ ይዘው ሽር ብትን እያሉ ቸርች ሲሄዱ ሳይ በድፍረታቸው እደነቃለው።እኔ ግን ማስመሰልን እንደነሱ ስላልተካንኩበት ነው መሰለኝ የሃጢያቴን ብዛት ሳስብ ራሴን ለጌታ ያልተገባው አድርጌ አስብ ነበር። የ10ኛ ክፍል ውጤት መቶልኝ የፕሪፕ ተማሪ ስሆን፤የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ስለ እምነቴ ራሴንና የተለያዩ አገልጋዮችን መጠየቅ ጀመርኩ።ከዛም ማቴ7:21-23ን አንድ ቀን ሳነብ አንድ ነገር ግልፅ ሆነልኝ።ብዙ ሰዎች በኢየሱስ ስም አጋንንት አውጥተው፣በሽተኛ ፈውሰው፣ትንቢት ተናግረውና ብዙ ተሃምራትን አድርገ ገሃነም የሚገቡ ከሆነ እኔማ ብዬ መዳኔን100% እርግጠኛ ሆኜ መናገር እንደማልችል ገባኝ፤ከነዚህ ሰዎች አንዱ አለመሆኔን ማረጋግጥበት ነገር አልነበረም።በዛ ላይ ኃጢያት ያለበት ሰው በኢየሱስ ቢያምንም እንኳ መንግስተሰማይ መግባት እንደማይችል አውቃለው። የሚገርመው አንድ እንግዳ ሰው አግኝቶኝ በጌታ ነህ? ብሎ ቢጠይቀኝ "አዎ፤ተጠምቄያለው፤በክርስቶስ ፀድቂያለው" ብዬ መልሳለው።አዬ መፅደቅ እቴ?! ኃጢያት በሰራው ሰሃት ሁሉ ግን አለመፅደቄ ኃጢያት ያለብኝ ሰው መሆኔ ቁልጭ ብሎ ይታየኛል።ሰዎች ድኛለው በጌታ ነኝ የሚሉት ቃላት ሁሉ ባዶ ይሆንብኛል። ከዛም በቃ አምሮዬ ብዙ ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀመረ መፅደቅ ማለት ምን ማለት ነው? በአዳም የገባው ኃጢያት ሚባለው የትኛው ነው?  እኔ ብቻ ነኝ አጢያት መስራት ማቆም ያቃተኝ ወይስ ሁሉም ሰው እንደኔ ነው?....ብዙ ጥያቄዎች።በዚህ መሃል ኢንትራንስ ውጤት መጥቶልኝ አ.አ.ዩ ገባው።እውነት እኔ ድኛለው? የሚለው ጥያቄዬ ተጠናክሮ ከኔ ጋር ካንፓስ ገባ። ትንሽ ግን "ፌሎ አቴንድ" ሳደርግ፤በለስላሳ ሙዙቃ ታጅበን ስናመልክ ምናምን በቃ ሁሉን እረሳለው።ደስ ይለኛል።በእንባ ታጅቤ ያመለኳቸው ጊዜያቶችን አልረሳቸውም።የማልዋሻቹ ነገር ግን ከፌሎ እንደወጣው ሁሉን እረሳለው።"የኔን አምልኮ በእርግጥ እ/ር ይቀበለዋል?" ስል አስባለው።እንደ አብዛኞቹ የፌሎ ጓደኞቼ ሻይ ቡና ብዬ ዶርሜ ገባና ላይብረሪ ሄጄ ካጠናው ቡሃላ ብዙ ጊዜ ስለእምነቴ አስባለው።እንዲህ እንዲህ እያልኩ የመጀመሪያ አመት ፍሬሽ ማንነቴን ጨረስኩና ወደ ቤተሰብ ጋር ለመሄድ በተሰናዳሁበት ወቅት አንድ በጣም የምወደው ከክርስቲያን ቤተስብ የሆነ ዶርምሜቴ፤ዳኒ ወክ እናድርግ ብሎኝ 6 ኪሎን ለቀን ወደ ፬ ኪሎ ማዝገም ጀመርን፤ ድንገት ግን አራት ኪሎ ስንደርስ አንድ ወጣት መንፈሳዊ መፅሀፍ በሃያ አያ ብር ብቻ! ሲል ጓደኛዬ  "ዳኒ ክረምቱን እንድናነበው ለምን መንፈሳዊ መፅሀፉን አንገዛውም" አለኝ።በነገራችን ላይ ጓደኛዬ ከእኔ እጅጉን የተሻለ አንባቢ ነው።ለመንፈሳዊ ነገሮች ያለው ጥማት እኔን እራሱ ያስከነዳል። በቃ መፅሀፉን ገስተን ሁለታችንም ወደየቤተሰቦቻችን መረሽን።ክረምቱን እኔ ትንሽ እሱ በደንብ አንብቦ ሁለተኛ አመት ላይ ተገናኘን ። ከዛም አስቀድመን ተደዋውለን ስለነበር ለፌሎ እንዲመቸን ከሌሎች ክርስቲያን ተማሪዎች ጋር አንድ ዶርም ያዝን። ጓደኛዬ የኔንና የራሱን መፅሀፍ አንብቦ ጨረሰ።ሌላም ተጨማሪ ራሱ ፀሐፊው የፃፈውን ሁለት መፅሀፍ አነበበ። ከዛም ፌሎ እርግፍ አድርጎ ተወና ከትምህርቱ በላይ መፅሀፍ ቅዱስን ማጥናት ጀመረ። እኔና ሌሎች ዶርም ሜቶቹ ፌሎ እንዳይቀር መከርነው።አልሰማንም።ጭራሽ አንድ ቀን እኔ "እኛ በጌታ የሆንን ሰዎች" እያልኩ ሳወራ።"ዝም በል ባክህ አንተ አልዳንክም" ብሎ አስደነገጠኝ።"ኸረ ባኪህ እኔማ ድኛለው" አልኩት።"እኔም የዳንኩት አሁን ነው አትሸወድ" አለኝ።ኸረ ፍልስፍና ጀመርሽ? በማለትም ላልሰማው ጆሮዬን ደፍኜ ለአንድ ሴሚስተር ያህል ተከራከርኩት።ፌሎ ስሄድ ምሰማቸው ስብከቶች ማስተዋል ጀመርኩ፤የህግ ት/ት እና ምድራዊ ስኬትን ሚያራግቡ ናቸው። አንድ ቀን እስቲ ዝም ብዬ በጭፍን ከምቃወመው ላዳምጠው ብዬ የተረዳውን እንዲነግረኝ ጠየኩት እርሱም እንዲህ በማለት ዳግም የምወለድበትን እውነታ ነገረኝ፦  እኛ ሰዎች የምንድነው አስቀድመን ስለኃጢያቶቻችን ስናውቅ ነው።የምንወለደው 12 ኃጢያቶችን በልባችን ይዘን ነው (ማር7:20-23) ።አለኝ ክፍሉን አወጣውና አነበብኩት።እውነት ነው እኔ በዘመኔ ስሰራቸው የነበሩ ኃጢያቶች ናቸው።"እነዚህን ኃጢያቶች በልብህ እንዳሉ ታምናለህ?"ሲለኝ።"በሚገባ" አልኩት ። "እስከለተሞትህስ እንደምትሰራቸው ታምናለህ?" ሲለኝ አዎን አልኩት ። እኔ ግን በኢየሱስ አምናለሁ እኮ አልኩት። ታምናህ እኔም አምን ነበር ታውቃለህ ግን ዳግመኛ አልተወለድኩም ነበር ። አንተም ዳግመኛ አልተወለድክም ። ይህን ሲለኝ ትንሽ እንደመብሸቅ አልኩና " እንደውም ልንገርህ እኔ በስህተት መንገድ ከሆንኩ ኢየሱስ እንደጳውሎስ ተገልጦ ተመለስ ይበለኝ ። " አልኩት ያኔ እንዲህ አለኝ " እግዚአብሔር የሚናገረን እኛ በምንፈልገው መንገድ ሳይሆን እርሱ በፈለገው መንገድ ነው አለኝ ። ያኔ በልቤ ለማመን ወሰንኩ ። በዚህ ወቅት በዮሐንስ መልዕክት ላይ የተጻፈ አንድ የnlm መጽሐፍ አንብቤ ጨርሼ ነበር ። ስለብሉይ ኪዳን የስርየት ህግ ፣ስለህግ አላማ ፣ ስለኢየሱስ ጥምቀት ፣ ስለመስቀል ሞቱና ዘላለማዊ ስርየቱ ፣ ስለንስሃ ጸሎት አላስፈላጊነት፣ ስለሰው ጽድቅና የእግዚአብሔር ጽድቅ ልዩነት አወኩ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለየው ። ድኜ ቀረው ። ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ ኃጢአቶቼን ሙሉ በሙሉ እንደወሰደልኝ አውቄ በልቤ ስቀበል ፤ ኢየሱስ በመስቀል ተሰቅሎ በውኃና በደም በደሎቼን እንደደመሰሳቸው እንደተኮነነልኝ ሳምን ፤ኢየሱስ በትሣዬው አዲስ ፍጥረትና ኃጢአት አልባ እንዳደረገኝ በልቤ ሳምን ድኜ ቀረው ። አሁን ላዳነኝ ለዚህ ጌታ ከወንድሞቼና እህቶች  ጋር  በመሆን የወንጌልን ስራ እየሰራው አለው። ስለሁሉ ጌታ ኢየሱስ የተመሰገነ  ይሁን! ! Daniel Tesfaye Heramo, Ethiopia

  • Daniel Tesfaye Heramo
  • Ethiopia
  • 10/30/2021 26