Search

คำสอน

ርዕስ 7፡ በቅድመ ውሳኔና የመለኮት ምርጫ ጽንሰ አሳብ ውስጥ ያለው ስሁትነት

[7-1] አስቀድሞ በመወሰንና በመለኮት ምርጫ ጽንሰ ሐሳብ ውስጥ ያለው ስህተት፡፡ ‹‹ ሮሜ 8፡28-30 ››

አስቀድሞ በመወሰንና በመለኮት ምርጫ ጽንሰ ሐሳብ ውስጥ ያለው ስህተት፡፡
‹‹ ሮሜ 8፡28-30 ›› 
‹‹እግዚአብሄርን ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን፡፡ ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፡፡ አስቀድሞ የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፡፡ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው፡፡›› 
 
 
እግዚአብሄር በእርግጥ የመረጠን አንዳንዶቻችን ብቻ ነውን?
አይደለም፡፡ እርሱ ሁላችንንም በኢየሱስ ክርስቶስ መረጠን፡፡ 
 
የክርስቲያንን ትምህርት ካዋቀሩት መሰረታዊ የነገረ መለኮት ትምህርቶች አንዱ የሆነው አስቀድሞ የመወሰንና የመለኮት ምርጫ ነገረ መለኮታዊ ጽንሰ ሐሳብ በኢየሱስ ማመን የሚፈልጉ ብዙዎች ቃለ እግዚአብሄርን በተሳሳተ መንገድ እንዲያስተውሉ መርቶዋቸዋል፡፡ ይህ የተዛባ ጽንሰ ሐሳብ ብዙ ግራ መጋባትን ፈጥሮዋል፡፡   
እውነት ያልሆኑ የነገረ መለኮት ትምህርቶች አስቀድሞ ስለ መወሰን እግዚአብሄር የሚወዳጨውን ሲመርጥ የሚጠላቸውን ይኮንናቸዋል ይላሉ፡፡  የተመረጡት አንዳንዶች ከውሃና ከመንፈስ ዳም የተወለዱና ሰማይ የሚቀበላቸው ሲሆኑ ያልተመረጡት ሌሎቹ ደግሞ መጨረሻቸው በሲዖል ለመቃጠል የደረሱ ናቸው ማለት ነው፡፡ 
በእርግጥ እግዚአብሄር አንዳንዶቻችንን ብቻ የሚመርጥ ከሆነ ‹‹እኔ ለደህንነት ተመርጬአለሁን?›› በሚል ጥያቄ ከመጨነቅ በቀር ማድረግ የምንችለው ነገር አይኖርም፡፡ ካልተመረጥን በኢየሱስ ማመናችንም ጥቅም ባልኖረው ነበር፡፡ ስለዚህ ይህ ጽንሰ ሐሳብ ብዙዎችን ራሱን እምነትን ከማሰብ ይልቅ በእግዚአብሄር ተመርጠው ስለመሆኑ ይበልጥ እንዲሰጉ አድርጎዋቸዋል፡፡   
ይህንን የምናምን ከሆነ እንዴት ከጥርጣሬዎች ነጻ መውጣትና በእግዚአብሄር ብቻ ማመን እንችላለን? እግዚአብሄርስ በእርግጥ እኛን እንደመረጠን በምን እናረጋግጣለን? እንደዚያ ከሆነ ‹‹ወይስ እግዚአብሄር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ አምላክ አይደለምን? አዎን ለተገረዝን ሁሉ አምላክ ነው›› (ሮሜ 3፡29) ቢልም አምላክነቱ ለተመረጡት ሰዎች ብቻ ይሆን ነበር፡፡  
ብዙ ሰዎች አስቀድሞ የመወሰንንና የመለኮት ምርጫን ትርጉም በተሳሳተ መንገድ ስለሚያስተውሉት በኢየሱስ ቢያምኑም እንደሚጠፉ ይፈራሉ፡፡
ኤፌሶን 1፡3-5 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከእግዚአብሄር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን፡፡ ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ሐጢአታችን ራሱን ሰጠ፡፡ ለአብ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን አሜን፡፡››
ስለዚህ አስቀድሞ ስለመወሰንና ስለ መለኮታዊ ምርጫ ያለንን ቃለ እግዚአብሄራዊ እሳቤ መመርመር ይኖርብናል፡፡ በመጀመሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አስቀድሞ መወሰንና ስለ መለኮት ምርጫ ምን እንደሚል መረዳትና በውሃውና በመንፈሱ አማካይነት በደህንነት ላይ ያለንን እምነታችነን ማጠንከር አለብን፡፡ 
ሮሜ የሚነግረን ምንድነው? አንዳንድ የቃለ እግዚአብሄር ምሁራን መሰረት የሌለውን ‹‹በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ምርጫ››ን ፈጠሩ፡፡ ታዲያ ነገረ መለኮት እግዚአብሄር ነውን? ነገረ መለኮት ራሱ እግዚአብሄር አይደለም፡፡
እግዚአብሄር ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እንኳን የሰውን ዘር ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ መርጦ ጻድቃን በማድረግ ሁላችንንም ለማዳን አእምሮውን አዘጋጀ፡፡ ኢየሱስ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይወደናል፡፡ አላማኒዎች በራሳቸው አስተሳሰቦች እምነት አላቸው፤ ምዕመናን ግን የእምነታቸውን መሰረት በተጻፈው የእግዚአብሄር ቃል ላይ ያደርጋሉ፡፡ 
 


መለኮታዊ ምርጫ በብሉይ ኪዳን፡፡ 

 
በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የምርጫ ጽንሰ  ሐሳብ እውነት ነውን? 
አይደለም፡፡ ጌታችን ጠባብ አስተሳሰብ ያለው አምላክ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የተመረጡ ጥቂቶችን ሳይሆን ሐጢያተኞችን በሙሉ በኢየሱስ መረጠ፡፡
  
በዘፍጥረት 25፡21-26 ስለ ሁለቱ የይስሐቅ ልጆች ስለ ኤሳውና ስለ ያዕቆብ እናነባለን፡፡ ሁለቱም ልጆች ገና በእናታቸው ማህጸን እያሉ እግዚአብሄር ያዕቆብን መረጠ፡፡ 
የእግዚአብሄርን ቃል በትክክል ያልተረዱ ሰዎች ይህንን በሁኔታ ላይ ላልተመሰረተ የምርጫ ጽንሰ ሐሳብ እንደ መሰረት ይወስዱታል፡፡ ይህ ደግሞ የዕጣ ፈንታን አምላክ ከክርስትና ጋር እንደ መቀላቀል ነው፡፡ 
እግዚአብሄር የመረጠን በኢየሱስ ክርስቶስ ሳይሆን ‹‹በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ምርጫ›› መሆኑን የምናምን ከሆነ እምነታችን የዕጣ ፈንታ አምላክንና ጣዖታትን ከማምለክ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ እግዚአብሄር የዕጣ ፈንታ አምላክ አይደለም፡፡ በዕጣ ፈንታ አምላክ የምናምን ከሆነ እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን ዕቅድ እየካድንና በሰይጣን ወጥመድ ውስጥ እየወደቅን ነው፡፡     
ሰዎች ለእግዚአብሄር ፈቃድ የማይታዘዙ ከሆኑ እንደሚጠፉ እንስሶች ከመምሰል በምንም አይለዩም፡፡ እኛ እንደሚጠፉ እንስሶች ስላልሆንን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን እውነት የሚያነቡና የሚያምኑ እውነተኛ ምዕመናን መሆን ይገባናል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን እውነት አስቀድሞ አለማሰብ ራስን ለሰይጣን አሳልፎ መስጠት ነው፡፡    
እውነተኛ እምነት ይኖረን ዘንድ በመጀመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጻፈው እውነት ማሰብና በክርስቶስ ዳግም የተወለዱትን ሰዎች እምነት መከተል አለብን፡፡ 
የካልቪን እምነት ውሱን በሆነው ቤዛነት ላይ ያተኩራል፡፡ ይህም የእግዚአብሄር ፍቅርና የጌታ ቤዛነት አንዳንዶችን እንደማይመለከት የሚጠቁም ነው፡፡ ይህ እውነት ሊሆን ይችላልን? 
መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ሰዎች ሁሉ ሊድኑ እግዚአብሄር ይወዳል›› ይላል፡፡ (1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡4) የንስሐ በረከት የሚደርሳቸው ጥቂቶች ብቻ ከሆኑ ብዙ አማኞች በኢየሱስ ማመናቸውን ይተዉ ነበር፡፡ እንዲያውስ በእንደዚህ አይነቱ ጠባብ አምላክ ማመን የሚፈልግ ማነው?
አምላካችን ጠባብ አስተሳሰብ ያለው ላለመሆኑ ሙሉ በሙሉ እርግጠኞች ልንሆን ይገባናል፡፡ እርሱ የእውነት፣ የፍቅርና  የፍትህ አምላክ ነው፡፡ በኢየሱስና በውሃውና በመንፈሱ ዳግም የመወለድ ወንጌል ማመንና  ከሐጢያቶቻችን ሁሉ መዳን ይኖርብናል፡፡ ኢየሱስ ከውሃና ከመንፈሱ ዳግም ለተወለዱት ሁሉ አዳኝ ነው፡፡
በካልቪን ትምህርት መሰረት አስር ሰዎች ቢኖሩ የተወሰኑት በእግዚአብሄር ይድኑና የተቀሩት በሲዖል እሳቶች ይቃጠላሉ፡፡ ይህ ውሸት ነው፡፡
እግዚአብሄር የተወሰኑትን ወዶ የተቀሩትን ይጠላል ማለት ስሜት የማይሰጥ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ዛሬ እዚህ  ከእኛ ጋር እንዳለ እናስብ፡፡ በስተቀኝ በኩል የተቀመጡትን በሙሉ ለመምረጥ ቢወስንና በስተግራ በኩል የተቀመጡትን በሙሉ ወደ ሲዖል ለመጣል ቢያስብ እርሱን አምላክ ነው ብለን እንቀበለዋለን? 
ተቀባይነት ያጡት ሰዎች የተቃውሞ ድምጾቻቸውን አያሰሙምን? ሁሉም ፍጥረታት ‹‹እግዚአብሄር እንዴት እንደዚህ ያዳላል?›› በማለት ይጮሁ ነበር፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ዘር ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለመረጠ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ምርጫ ውሸት ነው፡፡  
ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእግዚአብሄር የተጠራ ሁሉ የተመረጠ ነው፡፡ ታዲያ እግዚአብሄር ወደ ራሱ የሚጠራው ማንን ነው? እርሱ የሚጠራው ጻድቃንን ሳይሆን ሐጢያተኞችን ነው፡፡ እግዚአብሄር ራሳቸውን እንደ ጻድቃን የሚቆጠሩትን አይጠራም፡፡
የእግዚአብሄር የቤዛነት በረከት ለሐጢያተኞችና ለሲዖል ለተኮነኑት የተሰጠ ነው፡፡ ምርጫ ማለት እግዚአብሄር ጻድቅ ልጆቹ ያደርጋቸው ዘንድ ሐጢያተኞችን በሙሉ ይጠራል ማለት ነው፡፡
 


እግዚአብ0ሄር ጻድቅ ነው፡፡  

 
እግዚአብሄር የሚወደው የተመረጡ ጥቂቶችን ብቻ ነውን? 
አይደለም፡፡ ጌታ እንዲህ ጠባብ አስተሳሰብ ያለው አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ፍጹም ነው፡፡ 
 
እግዚአብሄር ጻድቅ ነው፡፡ እርሱ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የተመረጡትን ብቻ የሚወድ አምላክ አይደለም፡፡ እርሱ ሐጢያተኞችን በክርስቶስ ስም ይጠራቸዋል፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነትና እርሱ በሚሰጠው የሐጢያቶች ይቅርታ አማካይነት ከሚገኘው ደህንነት ውጪ የእግዚአብሄርን ፍቅርና ደህንነት እንዴት እናውቃለን? እርሱን በጭራሽ ቅንነት የጎደለው አምላክ አታድርጉት፡፡    
ኤፌሶን 1፡3-5ን ስታነቡ ምን እንደተሳተ ለማግኘት ሞከሩ፡፡ ‹‹በክርስቶስ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፡፡ ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን፡፡ በበጎ ፈቃዱ እንደወደደ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን፡፡›› የተሳተው ነገር ምንድነው? የተሳተው ቃል ‹‹በኢየሱስ ክርስቶስ›› የሚለው ነው፡፡
በካልቪኒዝም ትምህርት ውስጥ ያለው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተው ምርጫ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ጋር አይጣጣምም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን›› ይለናል፡፡    
እግዚአብሄር የሰውን ዘር በሙሉ ከመንፈስና ከእውነት ይወለዱ ዘንድ በክርስቶስ መረጠ፡፡ እነዚያ ሐጢያተኞች ሆነው የተወለዱትና ሐጢያትን ከማድረግ ውጭ ሌላ ምንም ማድረግ የማይችሉት ከሐጢያት ሊድኑና የእርሱ ልጆች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እርሱ የሰውን ዘር በሙሉ በኢየሱስ ክርስቶስ በዳኑትና በተመረጡት ዝርዝር ውስጥ አካተተ፡፡  
በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ምርጫ ላይ ሙጭጭ ያሉ በርካታ የቃለ እግዚአብሄር ምሁራን የተመረጡት አንዳንዶች ብቻ ናቸው በማለታቸው ብዙ ሰዎች ሙሉ በሙሉ ሚዛናዊ ባልሆኑ ትምህርቶች የእምነት ሁካታ ውስጥ ተጠምደዋል፡፡ እነዚህ ሐሰተኛ የቃለ እግዚአብሄር ምሁራን እግዚአብሄር አንዳንዶችን መርጦ ሌሎችን በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ምርጫ አማካይነት አስወግዶዋቸዋል ይላሉ፡፡ የቃሉ እውነት ግን እግዚአብሄር ሐጢያተኞችን ሁሉ በኢየሱስ እንደመረጠ ይናገራል፡፡ ብዙ ሰዎች አፈ ታሪካዊ አመኔታዎችን በማመናቸው እውነት ላልሆነው ትምህርት ሰለባ ሆኑ፡፡      
እኛ እግዚአብሄር የሰውን ዘር በሙሉ ለማዳን መወሰኑንና የሐጢያት ስርየትም በኢየሱስ ለሚያምን ለእያንዳንዱ ሰው መስጠቱን መገንዘባችንን ማወቅ አለብን፡፡ ይህንን በማድረግ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ መዳን፣ የእግዚአብሄር ልጆች መሆን፣ ጻድቅ ሕዝብ መሆን፣ የዘላለም ሕይወትም መያዝና እግዚአብሄርም ጻድቅ ለመሆኑ እርግጠኞች መሆን እንችላለን፡፡
 


በያዕቆብና በኤሳው ታሪክ ውስጥ ያለው የመለኮት ምርጫ፡፡  

 
እግዚአብሄር የመረጠው ማንን ነው? የተመረጡትን ብቻ ነውን? 
አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የሰው ዘርን በሙሉ በክርስቶስ መረጠ፡፡ ስለዚህ በክርስቶስ የሚያምንና በኢየሱስ ጥምቀት አማካይነት ሐጢያት የሌለበት ሁሉ የተመረጠ ነው፡፡
 
በዘፍጥረት 25፡19-28 ላይ ኤሳውና ያዕቆብ በእናታቸው ማህጸን ውስጥ ሆነው ይታገሉ ነበር፡፡ እግዚአብሄር በዘፍጥረት 25፡23 ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹ሁለት ወገኖች በማህጸንሽ ናቸው፡፡ ሁለትም ሕዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ፡፡ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፡፡ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል፡፡›› 
ሐጢያተኞች እነዚህን ቃሎች በነገረ መለኮታዊ አስቀድሞ የመወሰንና የመለኮት ምርጫ ጽንሰ ሐሳብ በመለወጥ በኢየሱስ የሚያምኑ ብዙዎች መመረጥ አለመመረጣቸውን በሚመለከት ግራ እንዲጋቡ አድርጎዋቸዋል! የተመረጥን ነን ብለው ሲያስቡ እንደዳኑ ስለሚያስቡ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም የመወለድ ፍላጎት ያጣሉ፡፡
በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የምርጫ ጽንሰ ሐሳብ በኢየሱስ የሚያምኑ ብዙ ሰዎችን ከቤዛነት ጎዳና አርቆዋቸው ለሲዖል እንዲኮነኑ አድርጓቸዋል፡፡ ይህ እግዚአብሄርን ኢፍትሃዊ መስሎ እንዲታይ አድርጎታል፡፡ 
በርካታ የነገረ መለኮት ምሁራን ከራሳቸው አስተሳሰቦች የመነጨ የሐሰት ትምህርት ስለሚያስተምሩ በኢየሱስ የሚያምኑ ብዙዎች የተመረጡ ስለመሆናቸው ወይም ቤዛነታቸው አስቀድሞ የተወሰነ ስለመሆኑ እርግጠኞች ባለመሆናቸው ይጠይቃሉ፡፡ 
ከያዕቆብና ከኤሳው እግዚአብሄር የመረጠው ማንን ነው? እርሱ ያዕቆብን በኢየሱስ ክርስቶስ መረጠው፡፡ በሮሜ 9፡10-11 ላይ ገና በአንድ ሰው ቢጸነሱም ሳይወለዱ፤ መልካም ወይም ክፉ ሳያደርጉ እግዚአብሄር ከወንድሙ ይልቅ ያዕቆብን እንደመረጠ ተነግሮዋል፡፡  
የእግዚአብሄር አላማ ያዕቆብን ከሥራዎቹ የተነሳ ሳይሆን ከምርጫው የተነሳ መምረጥ ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ የመጣው ትክክለኛ ሕይወትን የኖሩትን ብቻ ሳይሆን ሐጢያተኞችን ለመጥራት እንደሆነ ይነግረናል፡፡ 
ሰዎች በሙሉ የአዳም ዘሮች እስከሆኑ ድረስ ሐጢያተኞች ሆነው የተወለዱ ናቸው፡፡ ዳዊት በእናቱ ማህጸን ውስጥ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ ሐጢያተኛ እንደነበርና በዓመጻም እንደተወለደ ተናገረ፡፡ ‹‹እነሆ በዓመጻ ተጸነስሁ፤ እናቴም በሐጢአት ወለደችኝ፡፡›› (መዝሙር 51፡5)   
ሰዎች ሁሉ በቅድመ አያቶቻቸው ሐጢያቶች ምክንያት ሐጢያተኞች ሆነው የተወለዱ ናቸው፡፡ ስለዚህ በዚህ ዓለም የተወለደ እያንዳንዱ ሰው ሐጢያተኛ ይሆናል፡፡ እንደ ሐጢያተኛ ይንቀሳቀሳል፡፡ የሐጢያትን ፍሬዎችም ያፈራል፡፡   
ገና ምንም ሐጢያት ያልሰራ ሕጻን የሐጢያትን ዘር ይዞ ስለተወለደ ቀድሞውኑም ሐጢያተኛ ነው፡፡ በልቡ ውስጥ ክፉ አሳቦች፣ ዝሙት፣ አመንዝራነትና ነፍሰ ገዳይነት አሉ፡፡ የቅድመ አያቶቹን ሐጢያቶች ይዞ ተወልዶዋል፡፡ ሰዎች ሁሉ ገና ከመወለዳቸው በፊትም እንኳን ሐጢያተኞች ናቸው፡፡ 
እግዚአብሄር እኛን ደካሞች አድርጎ የፈጠረበት ምክንያቱ ከዚህ እንደሚከተለው ነው፡፡ የሰው ዘር የእግዚአብሄር ፍጥረት ነው፡፡ ነገር ግን ጌታ እኛን ከሐጢያት በማዳን የእርሱ ልጆች ሊያደርገን እቅድ ነበረው፡፡ አዳምንም ሐጢያት እንዲሰራ የፈቀደለት ለዚህ ነው፡፡  
በዚህ ምክንያት ሐጢያተኞች በሆንን ጊዜ እግዚአብሄር አንድያ ልጁን ኢየሱስን ወደዚህ ዓለም በመላክ በጥምቀቱ አማካይነት የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ እንዲወስድ ፈቀደ፡፡  
የእግዚአብሄር አሳብ የሰውን ዘር በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ ደም እንዲያምኑና በኢየሱስ በማመን ሐይልም የእርሱ ልጆች እንዲሆኑ  ሥልጣን መስጠት ነው፡፡ ሐጢያትን በሙሉ በክርስቶስ እንደሚያነጻ ተስፋ በመስጠት አዳም ሐጢያት እንዲሰራ ፈቀደ፡፡ 
በሐሰት ትምህርት የሚያምኑ ሐጢያተኞች ‹‹ያዕቆብና ኤሳውን ተመልከቱ፡፡ እርሱ አንዱን መርጦ አንዱን ደግሞ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ትቶታል›› ይላሉ፡፡ እግዚአብሄር ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አልመረጠንም፤ ነገር ግን እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ መረጠን፡፡ እኛ መመልከት ያለብን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን ቃሎች ብቻ ነው፡፡ ሮሜ 9፡10-12 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ይህ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ርብቃ ደግሞ ከአንዱ ከአባታችን ከይስሐቅ በጸነሰች ጊዜ ልጆቹ ገና ሳይወለዱ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ ከጠሪው እንጂ ከሥራ ሳይሆን በምርጫ የሚሆን የእግዚአብሄር አሳብ ይጸና ዘንድ ለእርስዋ ታናሹ ለታላቁ ይገዛል ተባለላት፡፡››  
እግዚአብሄር ያዕቆብን በኢየሱስ መረጠው፡፡ ያዕቆብ ብቁዓን ያልሆኑና የራሳቸውን ጽድቅ የተነጠቁ ሰዎች ምሳሌ ነበር፡፡ በኤፌሶን 1፡4 ላይ እግዚአብሄር በእርሱ በኩል እንደመረጠን ይናገራል፡፡ 
እግዚአብሄር የጠራው ማንን ነው? እግዚአብሄር ያዕቆብን የጠራው እርሱ በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያተኛና ጻድቅ ያልሆነ ነገር ግን በእግዚአብሄር የሚተማመን መሆኑን ያውቅ ስለነበር ነው፡፡ እግዚአብሄር ያዕቆብን ልጁ ያደርገው ዘንድ በልጁ በኢየሱስ ስም ጠራውና በኋላ በውሃውና በደሙ ወንጌል ቤዘነትን ሰጠው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ያዕቆብን ጠራውና በቤዛነት ባረከው፡፡
እርሱ በኢየሱስ ቤዛነት ሐጢያተኞችን ጻድቃን ለማድረግ ጠራ፡፡ ያ የእግዚአብሄር እቅድ ነው፡፡
 


ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የመመረጥ ሐሰተኛ ትምህርት፡፡ 

 
እግዚአብሄር ያዕቆብን የወደደው ለምንድነው? 
ያዕቆብ ዓመጸኝነቱን ያውቅ ስለነበር ነው፡፡
 
በቅርቡ አንድ በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ምርጫ ላይ የተመረኮዘ ታሪክ ያለውን መጽሐፍ አነበብሁ፡፡ አንድ ወጣት ሰው ሕልም ያልማል፡፡ በሕልሙም አንዲት አሮጊት ሴት ትገለጥለትና ወደ አንድ ቦታ እንዲመጣ ትነግረዋለች፡፡ እርሱም ይሄዳል፡፡ ከዚያም አሮጊቷ ሴት በእግዚአብሄር እንደተመረጠ ትነግረዋለች፡፡  
እርሱ በእግዚአብሄር እንኳን ሳያምን እንዴት እግዚአብሄር ሊመርጠው እንደቻለ አሮጊቷን ጠየቃት፡፡ አሮጊቷም እምነተ ጎዶሎ ቢሆንም እግዚአብሄር ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንደመረጠው ትነግረዋለች፡፡  
ይህ እውነት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር እንዴት በዘፈቀደ አንዳንድ ሰዎችን ለሲዖል ሲኮንን ሌሎችን ለደህንነት ይመርጣል? እግዚአብሄር እያንዳንዱን ሰው በኢየሱስ በኩል መረጠው፡፡  
ኢየሱስን የሚያገልል የነገረ መለኮት የምርጫ ጽንሰ ሐሳብ ውሸት ነው፡፡ እውነት አይደለም፡፡ ነገር ግን ብዙ የነገረ መለኮት ምሁራን እግዚአብሄር የመረጠው አንዳንዶቻችንን ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ያ እውነት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በኢየሱስ በኩል እያንዳንዱን ሰው ማዳን ይፈልጋል፡፡ የማይድኑት በኢየሱስ በኩል በሆነው የውሃና የመንፈስ ቤዛነት የማያምኑት ብቻ ናቸው፡፡ 
እግዚአብሄር ከዓለም ፍጥረት በፊት እንኳን የሰውን ዘር በሙሉ በልጁ በኢየሱስ በኩል ለደህንነት አስቀድሞ ወሰነና ልጆቹ ሊያደርገን አቀደ፡፡ እርሱ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት በኩል የሰውን ዘር ከዓለም ሐጢያቶች ሁሉ ለማዳን አቀደ፡፡ ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈው እውነት ነው፡፡  
በክርስቶስ ዳግም የተወለዱ ጻድቃን ምርጦች ናቸው፡፡ ነገር ግን የነገረ መለኮት ምሁራን እግዚአብሄር የመረጠው አንዳንዶቻችንን ብቻ ነው በማለት ሙጭጭ ይላሉ፡፡ ለምሳሌ የቡዲስት መነኮሳት እግዚአብሄር ካልመረጣቸው መካከል ናቸው ይላሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር እነርሱንም በኢየሱስ መረጣቸው፡፡ 
እግዚአብሄር የሚመርጠው ያለ ምንም መስፈርት ማንንም ከሆነ እኛም ወንጌልን መስበክ ባላስፈለገን ነበር፡፡ እግዚአብሄር ያለ ኢየሱስ የሆነን አንድን ሰው ለመምረጥ አቅዶ ከነበረ ሐጢያተኞችም በኢየሱስ ማመን አያስፈልጋቸውም ነበር፡፡ ታዲያ የፍቅር፣ የእውነትና የደህንነት ቃሎች እንዴት ሊፈጸሙ ይችላሉ?   
የእግዚአብሄር አገልጋዮችስ ወንጌልን በዚህ ምድር ላይ ለመስበክ የሚያስፈልጋቸው አንዳች ምክንያት ይኖራቸው ነበርን? እግዚአብሄር ቤዛነትን ያገኙትንና ያለ ኢየሱስ የተኮነኑትን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ቀድሞውንም ከመረጣቸው ይህ ስሜት ይሰጣልን?    
እግዚአብሄር ያዕቆብን በኢየሱስ የመረጠበት ምክንያትና ያዕቆብን ወድዶ ኤሳውን የጠላበት ምክንያት ከመፈጠራቸው በፊት ያዕቆብ በኢየሱስ እንደሚያምንና ኤሳው ግን በኢየሱስ እንደማያምን ያውቅ ስለነበር ነው፡፡     
እግዚአብሄር ያዕቆብን የወደደው ለምንድነው? ያዕቆብ ሐጢያተኛ ስለነበርና ከንቱነቱን ስላወቀ ነበር፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያተኛ መሆኑን አመነና የአምላክን ጸጋ ለመነ፡፡ እግዚአብሄር ያዕቆብን ያዳነው ለዚህ ነው፡፡ 
ኤሳው ግን በጌታ ከመደገፍ ይልቅ ይበልጥ በራሱ ተደገፈ፡፡ የእግዚአብሄርንም ጸጋ አልተራበም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ያዕቆብን እንደወደደና ኤሳውን እንደጠላ ተናገረ፡፡ ይህ የእውነት ቃል ነው፡፡   
እግዚአብሄር ሁላችንንም በኢየሱስ ለደህንነት አስቀድሞ ወሰነን፡፡ ሐጢያተኞች በሙሉ ማድረግ የሚጠበቅባቸው በኢየሱስ ማመን ብቻ ነው፡፡ በዚህም የእግዚአብሄር እውነትና ፍትህ በልቦቻቸው ውስጥ ይቀረጻል፡፡ እኛ ሐጢያተኞች ማድረግ የምንችለው ብቸኛ ነገር ቢኖር በኢየሱስ በኩል በመቤዠት ማመን ነው፡፡ 
 


ሐሰተኛው የቀስ በቀስ ቅድስና ጽንሰ ሐሳብ፡፡  

 
ሐጢያተኛ ቀስ በቀስ ጻድቅ ሊሆን መቻሉ እውነት ነውን? 
አይደለም፡፡ ይህ አይቻልም፡፡ እግዚአብሄር ሐጢያተኞችን በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ በጥምቀቱ ቤዛነትና በመስቀል ላይ ሞቱ አማካይነት ጻድቃንና እንከን የለሽ  አደረጋቸው፡፡
 
ሰይጣን ሐጢያተኞች ከሐጢያቶቻቸው መዳን እንዳይችሉ ቀስ በቀስ በመቀደስ ጽንሰ ሐሳብ አታለላቸው፡፡ ቀስ በቀስ መቀደስ ማለት ሐጢያተኞች በኢየሱስ ካመኑ በኋላ ቅዱስ የሚሆኑት ቀስ በቀስ ነው ማለት ነው፡፡ 
ጽንሰ ሐሳቡ እንደሚከተለው ነው፡፡ ሐጢያተኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጻድቅ አይሆኑም፤ ነገር ግን በኢየሱስ ሲያምኑ የሚድኑት ከአዳም ሐጢያት ብቻ ነው፤ በተግባር የተሰሩ ሐጢያቶች የሚወገዱት በየቀኑ የንስሐ ጸሎትን በማድረግ ነው፡፡ ሰዎችም ቀስ በቀስ ይቀደሳሉ፡፡  
የዚህ ጽንሰ ሐሳብ ፋይዳ የቀስ በቀስ ቅድስና ነው፡፡ ሰው በኢየሱስ ማመኑና ቀስ በቀስ ቅዱስ ክርስቲያን መሆኑ ትልቅ ነገር ይመስላል፡፡ ይህ ጽንሰ ሐሳብ በርካታ ክርስቲያኖችን ለዓመታት በማሳት አዘናግቶዋቸዋል፡፡ በክርስትና ውስጥ ከአንተ ይበልጥ ቅዱስ ነኝ የሚሉ ክርስቲያኖች የበዙት ለዚህ ነው፡፡
እነርሱ አንድ ቀን እንደሚለወጡና ሐጢያት መስራት እንደሚያቆሙ ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ሕይወታቸውን ሐጢያተኞች ሆነው ይኖሩታል፡፡ ከሞቱ በኋላም በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያተኞች ሆነው ይፈረድባቸዋል፡፡ 
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን እውነተኛ ቃል አንብቡ፡፡ ሮሜ 8፡30 እንዲህ ይላል፡- ‹‹አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፡፡ የጠራቸውን እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፡፡ ያጸደቃቸውን እንዚህን ደግሞ አከበራቸው፡፡››  
ቁጥር 29 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፡፡›› በመጀመሪያ ዕይታ ጻድቅ ለመሆን ደረጃዎች ያሉ ይመስላል፡፡ ነገር ግን ቃሉ ጽድቅ ለአንዴና ለመጨረሻ እንደተሰጠ ይነግረናል፡፡
‹‹የጠራቸውን ደግሞ አጸደቃቸው፡፡›› ኢየሱስ ሐጢያተኞችን ጠራቸውና በዮርዳኖስ ባደረገው ጥምቀቱና በመስቀል ላይ ሞቱ አጸደቃቸው፡፡  
ስለዚህ በኢየሱስ ቤዛነት የሚያምን ሰው የከበረ የእግዚአብሄር ልጅ ይሆናል፡፡ ሐጢያተኞችን መቤዠትና በዚህ ስም እነርሱን ማክበር የእግዚአብሄር ጸጋ ነው፡፡  
ይህ እግዚአብሄር የሚነግረን ነው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ክርስቲያኖች ሮሜ 8፡30ን እንድንመለከት ይነግሩናል፡፡ ‹‹ለመቀደስ ደረጃዎች አሉ፡፡ ያ ማለት ቀስ በቀስ እንለወጣለን ማለት አይደለምን?›› የተታለሉት እንዲህ ነው፡፡ ሐጢያተኛ በጊዜ ሒደት ውስጥ ጻድቅ እንደሚሆን ለሰዎች በወደፊት የግስ ጊዜ ይነግሩዋቸዋል፡፡  
ነገር ግን እኛ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጻድቅን እንደሆንን መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን በወደፊት ጊዜ ሳይሆን ተፍጻሜትን በሚያሳይ ሐላፊ ጊዜ ነው፡፡ በወደፊት እሳቤና በተፍጻሜታዊ ሐላፊ ጊዜ እሳቤ መካከል ግልጽ ልዩነት አለ፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ በሚገባ ማመን ይገባናል፡፡ በተጻፈው መሰረት ለአንዴና ለመጨረሻ የእግዚአብሄር ልጆች መሆን እንችላለን፡፡ ይህ ከቀስ በቀስ ቅድስና ጽንሰ ሐሳብ ፈጽሞ የተለየ ነው፡፡ 
የቀስ በቀስ ቅድስና ጽንሰ አሳብ በኢየሱስ ስናምን ይቅር የተባልነው የአዳምን ሐጢያት ብቻ ነው ይላል፡፡ ይህም የሚጠቁመው በእግዚአብሄር ፊት ስንቆም ጻድቅ እንሆን ዘንድ ሃይማኖታዊ ሕይወትን መኖርና በየቀኑም ከሐጢያቶቻቸን ንስሐ መግባት ያለብን መሆኑን ነው፡፡   
ብዙ ሰዎች በዚህ ጽንሰ ሐሳብ ስለሚያምኑ በኢየሱስ ማመን ከጀመሩ በኋላም እንኳን አሁንም ድረስ ሐጢያተኞች ናቸው፡፡ የቀስ በቀስ ቅድስና ጽንሰ ሐሳብ እውነት ያልሆነው ለዚህ ነው፡፡ 
መጽሐፍ ቅዱስ ጻድቃንና የእግዚአብሄር ልጆች ልንሆን የምንችለው በእምነት መሆኑን ይነግረናል፡፡ ልክ ሕጻናት ወደዚህች ምድር በሚመጡበት አኳኋን የእግዚአብሄር ልጆችም የኢየሱስን ቤዛነት ሲገነዘቡና ሲያምኑ ወዲያውኑ ይቀደሳሉ፡፡ ሐሰተኛው የቀስ በቀስ ቅድስና ጽንሰ ሐሳብ ከውሸት የፈለቀ ነው፡፡
 

ከሐጢያቶች ሁሉ የተሟላ መዳን፡፡ 
 
ሙሉ በሙሉ ለመቀደስ ማድረግ ያለብን ምንድነው? 
በውሃውና በመንፈሱ ቤዛነት ማመን አለብን፡፡
 
ሮሜ 8፡1-2 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከሐጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና፡፡›› ይህ እግዚአብሄር ሐጢያተኞችን በሙሉ ጻድቅ እንዳደረጋቸውና ወደ ኢየሱስ የመጡትንም ከሐጢያትና ከሞት እንዳዳናቸው ይነግረናል፡፡  
መጽሐፍ ቅዱስ በዕብራውያን 9፡12 ላይ ስለ ሙሉ ቤዛነት ይነግረናል፡፡ ‹‹የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም፡፡›› ይህ ማለት እኛ በኢየሱስ ያመንን ቤዛነትን አግኝተን ሰማይ መግባት ተፈቅዶልናል ማለት ነው፡፡  
እኛ በክርስቶስ ኢየሱስ የውሃና የመንፈስ ቤዛነትን ወንጌል ሰምተንና አምነን ለሐጢያቶቻችን ሁሉ ይቅርታን አግኝተናል፡፡ ነገር ግን ይቅርታን ያገኙት ለአዳም ሐጢያት ብቻ መሆኑን የሚያምኑ ሐጢያተኞች በእርግጥ ሊድኑ አይችሉም፡፡ እነርሱ በኢየሱስ ካመኑ በኋላ ከፈጸሙዋቸው ሐጢያቶች ለመቀደስ ሲሉ በየቀኑ ንስሐ መግባት እንዳለባቸው ይሰማቸዋል፡፡    
የተዛባው እምነታቸው ወደ ሲዖል ይነዳቸዋል፡፡ የተሳሳቱት አመኔታዎቻቸውም ራሳቸውን ከበደሎቻቸው ሁሉ ነጻ ለማውጣት በየቀኑ ንስሐ እንዲገቡ ያደርጉዋቸዋል፡፡ ከሲዖል የሚያድነን እውነተኛ እምነት ይህ አይደለም፡፡  
እነርሱ በኢየሱስ አምነውና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ቤዛነትን አግኝተው ቢሆን ኖሮ ጻድቃንና የእግዚአብሄር ልጆች ይሆኑ ነበር፡፡ እውነተኛ ቤዛነት ምዕመናንን ጻድቃን በማድረግ ለአንዴና ለመጨረሻ ወደ እግዚአብሄር ልጅነት ይለውጣቸዋል፡፡  
ምንም እንኳን አማኞች ከዓለም ሐጢያቶቻቸው ለዘላለም የዳኑ ቢሆኑም ሥጋቸው ግን እስከሚሞቱበት ቀን ድረስ ሐጢያትን ከመስራት አይታቀብም፡፡ ነገር ግን ልቦቻቸው በእግዚአብሄር ጽድቅ የተሞሉ ናቸው፡፡ ይህንን እውነት መቼም ቢሆን በተሳሳተ መንገድ ልናስተውለው አይገባንም፡፡ 
መጽሐፍ ቅዱስ በወንጌል ስናምን እንደተቀደስንና እንደጸደቅን ይነግረናል፡፡ 
እውነተኛውን ወንጌል ለማየት ዕብራውያን 10፡9-14ን እንመልከት፡- ‹‹ቀጥሎ እነሆ አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ላደርግ መጥቻለሁ፡፡ ሁለተኛውንም ሊያቆም የፊተኛውን ይሽራል፡፡ በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ በማቅረብ ተቀድሰናል፡፡ ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ሐጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መስዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞዋል፡፡ እርሱ ግን ስለ ሐጢአት አንድን መስዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደፊት ይጠብቃል፡፡ አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና፡፡››   
‹‹በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል፡፡›› ይህ የተጻፈው ተፍጻሜትን በሚያሳይ የአሁን ጊዜ አመላካች በሆነ ግስ እንጂ የወደፊት ጊዜን አመላካች በሆነ ግስ አለመሆኑን ልብ በሉ፡፡  
ፈጽመን ለመቀደስ ሁላችንም ኢየሱስ በሰጠን የውሃና የመንፈስ ቤዛነት ማመን አለብን፡፡ 
 


ኢየሱስ ለአንዴና ለመጨረሻ የዘላለምን ቤዛነት ሰጠ፡፡ 

 
ሰው ሁሌም ለመደሰት የተመደበው ለምንድነው? (1ኛ ተሰሎንቄ 5፡16)
ምክንያቱም ኢየሱስ ሐጢያቶቹን በሙሉ ስለወሰደለትበእርሱ ፊት ትሁት ከመሆንና ጸጋውን ከማመስገን በስተቀር ምንም ሌላ ነገር ማድረግ ስለማይችል ነው፡፡
 
በኢየሱስ ዘላለማዊ ቤዛነት የምናምን ከሆነ ሁላችንም በአንድ ጊዜ ጻድቃን እንሆናለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹በሁሉ አመስግኑ፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና፡፡›› (1ኛ ተሰሎንቄ 5፡16-18) 
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፡፡ ሁልጊዜ መደሰት የምንችለው እንዴት ነው? እነዚያ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዘላለማዊ ቤዛነትን ያገኙ ያለ ልክ ሊደሰቱ ይችላሉ፡፡ ከሐጢያት ነጻ ስለሆኑ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ በመውሰዱ እውቀት የተደላደሉ ናቸው፡፡ በእርሱ ፊትም ትሁታን፣ ለጸጋውም አመስጋኞች ናቸው፡፡ ከዚህ የተነሳ ያለ ማቋረጥ ይደሰታሉ፡፡    
‹‹ዓመጻቸው የተሰረየላቸው ሐጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው፡፡ ጌታ ሐጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ብፁዕ ነው፡፡›› (ሮሜ 4፡7) ይህ ማለት ሐጢያቶቻችን ገናም በልባችን ውስጥ እያሉ ተሸፍነዋል ማለት አይደለም፡፡ ልባችን ነጽተዋል፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ፈጽሞ አነጻና ለአንዴና ለመጨረሻ አዳነን፡፡    
ይህ ዘላለማዊ ቤዛነት በአዲስ ኪዳንም ተጠቅሶዋል፡፡ ኢየሱስ በሚጠመቅበት ጊዜ ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና›› አለ፡፡ (ማቴዎስ 3፡15)
በብሉይ ኪዳን በጎች ወይም ፍየሎች በእጆች መጫን አማካይነት የሕዝቡን ሐጢያቶች ይወስዱ እንደነበረ ሁሉ ኢየሱስም የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደና የሰውን ዘር እጅግ ተገቢና ተስማሚ በሆነ መንገድ አነጻ፡፡ 
ኢየሱስ ‹‹ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና›› አለ፡፡ ኢየሱስ እጅግ ተገቢ በሆነ መንገድ ተጠመቀና የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ በመውሰድ አዳነን፡፡ 
በማቴዎስ 3፡15 ላይ ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ መውሰዱ ተጽፎዋል፡፡ የእግዚአብሄር ፍትህ ተጠናቀቀ፡፡ ይህንን ዘላለማዊ ቤዛነት ለማስተዋል መሞከር አይገባንም፡፡ ይህንን የእርሱ የደህንነት ቃል አድርገን ልንወስደው ይገባናል፡፡ ‹‹መተላለፉ የቀረችለት ሐጢአቱም የተከደነችለት ምስጉን ነው፡፡›› (መዝሙረ ዳዊት 32፡1) 
ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የሰውን ዘር የልብና የሥጋ ሐጢያቶች በሙሉ አነጻ፡፡ በዚህ በተበላሸና በዘቀጠ ዓለም ውስጥ ለምንሰራቸው ሐጢያቶች ተኮነነ፡፡ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ከወሰደ በኋላ በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ 
በዚህ የሐጢያት ቤዛነት የሚያምን ማንኛውም ሰው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጻድቅና ያለ ነቀፋ ሊሆን ይችላል፡፡ ኢየሱስ ለዘላለም ስለሚኖር በክርስቶስ ቤዛነት የሚያምን ማንኛውም ሰው ጻድቅ ሆኖ ይቀራል፡፡   
አሁን እኛም በእግዚአብሄር ፊት በድፍረት ቆመን ‹‹እንደምን ነህ ጌታዬ? በአንተ አንድያ ልጅ በክርስቶስ ኢየሱስ አምናለሁ፡፡ እኔ ያንተ ልጅ ነኝ፡፡ ይህን ያገኘሁት በሥራዬ ሳይሆን በኢየሱስ የውሃና የመንፈስ ወንጌል ላይ ባለኝ እምነትና ዳግም መወለድ ነው፡፡ ከዓለም ሐጢያቶች በሙሉ አድነኸኛል፡፡ ‹‹ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና (ማቴዎስ 3፡15) ባልከውም አምናለሁ፡፡ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ እኔ ልጅ ለመሆን በቅቻለሁ፡፡ ለዚህም በጣም አመሰግንሃለሁ›› ማለት እንችላለን፡፡   
ኢየሱስ ሐጢያቶቻችሁን ሁሉ አንጽቷልን? ለኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ለሆነው ሞቱ ምስጋና ይድረሰውና ሐጢያተኞች በዚህ በማመን ብቻ ሊቀደሱ ይችላሉ፡፡ 
 


በኢየሱስ ጥምቀትና በቤዛነት መካከል ያለው ዝምድና፡፡ 

 
በኢየሱስ ጥምቀትና በቤዛነቱ መካከል ያለው ዝምድና ምንድነው? 
የኢየሱስ ጥምቀት በብሉይ ኪዳን ውስጥ በእጆች መጫን አማካይነት የተተነበየው ቤዛነት ተምሳሌት ነው፡፡
 
በኢየሱስ እያመነና በቤተክርስቲያን ውስጥ ‹‹አቤቱ ባለፈው ሳምንት የሰራኋቸውን ሐጢያቶች እባክህ ይቅር በለኝ፡፡ ባለፉት ሦስት ቀናቶች የሰራኋቸውን ሐጢያቶች ይቅር በለኝ፡፡ ጌታ ሆይ ዛሬ የሰራኋቸውንም ሐጢያቶች ይቅር በለኝ፡፡ በኢየሱስ አምናለሁ›› ብሎ እየጸለየ ሐጢያተኛ ሆኖ የሚኖርን ሰውን አስቡ፡፡  
ይህ ሰው በዚያ ጸሎት የዘወትር ሐጢያቶቹ በሙሉ ይቅር ተባሉለት ብለን እናስብ፡፡ በኋላ ግን ወደ ቀን ተቀን ሕይወቱ ይመለስና እንደገና ሐጢያትን ይሰራል፡፡ እንደገናም ሐጢያተኛ ይሆናል፡፡ 
ኢየሱስ የእግዚአብሄር በግ ሆነና የሐጢያተኞችን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ አማካይነት ወሰደና በመስቀል ተሰቅሎ ተቤዣቸው፡፡ ሐጢያተኞች ቤዛነትን ለማግኘት የሚከተለውን ማመን አለባቸው፡፡    
ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ሐጢያት በሙሉ ተወሰደና የእግዚአብሄር ጽድቅ ተፈጸመ፡፡ የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ነጸተዋል፡፡ በዚህ እውነት ያመነ ሁሉ ነጻ ወጥቶዋል፡፡ በማቴዎስ 3፡13-17 ላይ እንደተጻፈው ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ የተጠመቀውና የምዕመናን ሁሉ አዳኝ የሆነው ‹‹እንዲህ›› ነው፡፡  
የወንጌል እውነት ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ማንጻቱን ይናገራል፡፡ ነገር ግን የሐሰት ነገረ መለኮት በየቀኑ ቤዛነትን እንደምናገኝ ይነግረናል፡፡ ማመን የሚገባን የትኛውን ነው? ለአንዴና ለመጨረሻ ቤዛነትን አግኝተናል ወይስ ቤዛነትን የምናገኘው በየቀኑ ነው? 
ኢየሱስ ለአንዴና ለመጨረሻ እንዳዳነን ግልጽ ነው፡፡ እውነተኛው አመኔታ ለአንዴና ለመጨረሻ በተሰጠው የውሃና የመንፈስ ቤዛነት ማመን ነው፡፡ በየቀኑ መዳን እንዳለብን የሚያምኑ በጭራሽ አይድኑም፡፡  
እነርሱ እውነተኛ ቤዛነት ሊመጣ የሚችለው ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ሞቱ ለአንዴና ለመጨረሻ እንዳዳነን ከማመን መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው ነገር እግዚአብሄርን ማመስገንና በዚህ በእውነተኛው ወንጌል ማመን ነው፡፡
ነገር ግን በእምነታቸው ትክክለኛውን ምሪት ያልያዙ ሰዎች የዳንነው ከአዳም ሐጢያት ብቻ እንደሆነ፣ በተግባር ከምንሰራቸው ሐጢያቶቻችን በየቀኑ ቤዛነትን ማግኘት እንደሚገባንና ‹‹ቀስ በቀስ›› ቅዱስ መሆን እንደምንችል ይናገራሉ፡፡ ያ ስህተት ነው፡፡ 
የኢየሱስ ጥምቀትና የመስቀል ላይ ሞቱ ለአንዴና ለመጨረሻ የሐጢያት ይቅርታን ከወነ፡፡ ይህ እውነት ነው፡፡ እኛ እንድን ዘንድ ሐጢያቶቻችን በሙሉ በጥምቀቱ አማካይነት ወደ ኢየሱስ መተላለፍና እርሱም በመስቀል ላይ  መሞት ነበረበት፡፡   
ሐጢያትን ከሰራን በኋላ ‹‹ይቅር በለኝ›› ማለት ከእግዚአብሄር ፍትህ ጋር አይጣጣምም፡፡ የእግዚአብሄር ሕግ የሐጢያት ደመወዝ ሞት መሆኑን ይናገራል፡፡ እግዚአብሄር ፍጹምና ቅዱስ መሆኑን ማወቅ ይገባናል፡፡  
ሐጢያት ከሰሩ በኋላ ‹‹አዝናለሁ፤ እባክህ ይቅር በለኝ›› ብለው ወደ እግዚአብሄር የሚጸልዩ የእግዚአብሄርን ፍትህ አያውቁም፡፡ እነርሱ ይቅርታን ለማግኘት ቢጸልዩም አላማቸው ግን ሕሊናቸውን ማረጋጋት ነው፡፡ አንድ ሰው በየቀኑ ሐጢያትን መስራቱና ለመተላለፎቹ በተደጋጋሚ ንስሐ በመግባት ሕሊናውን ማጽናናቱ ትክክል ነውን? ለመዳን ብቸኛው መንገድ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ ላይ ደም ማመን ነው፡፡ ይህንን በልቦቻችን ልናምነው ይገባናል፡፡ የእግዚአብሄርን ፍርድ ማስወገድ የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነው፡፡     
ከሐጢያት ነጻ ስለ መውጣት ጨምረን እናስብ፡፡ በዕብራውያን 9፡22 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ሁሉም በደም ይነጻል፡፡ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም፡፡››   
በእግዚአብሄር ፍጹም ሕግ መሰረት ሐጢያቶች መንጻት ያለባቸው በደም ነው፡፡ ደም ሳይፈስ ስርየት የለም፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ቅን ሕግ ነው፡፡ የሐጢያት ደመወዝ ሳይከፈል ፈጽሞ ስርየት ሊኖር አይችልም፡፡ 
የእግዚአብሄር ሕግ ቅን ነው፡፡ ኢየሱስ እኛን ሐጢያተኞችን ለማዳን በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀና በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰ፡፡ በጥምቀቱ አማካይነት መተላለፎቻችንን በሙሉ አነጻና ለሐጢያቶቻችን ሁሉ ዋጋ ለመክፈል በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰ፡፡ የሐጢያትን ደመወዝ ለሁላችንም ከፈለ፡፡  
 
ቤዛነት ለአንዴና ለመጨረሻ ተሰጥቷል ወይስ በየቀኑ ይሰጣል? 
ለአንዴና ለመጨረሻ ነው፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት የሐጢያተኞችን ሁሉ ሐጢያቶች አነጻ፡፡
 
በማቴዎስ 3፡15 ላይ ኢየሱስ በጣም ተገቢ በሆነ መንገድ  የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ አማካይነት አነጻና እኛን ከዓለም ሐጢያቶች ሁሉ ለማዳን በመስቀል ላይ ሞተ፡፡   
በየቀኑ ይቅርታን መጠየቅ እንደገና ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንዲወስድና እንዲሞት መጠየቅ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ጻድቅ ሕግ በትክክል መረዳት ይኖርብናል፡፡ ኢየሱስ እኛን ከሐጢያት ለማንጻት በተደጋጋሚ መሞት የለበትም፡፡  
እግዚአብሄር በኢየሱስ አምነው ለሰሩዋቸው ሐጢያቶች ደጋግመው ይቅርታ የሚጠይቁትን እጅግ ስዶች እንደሆኑ አድርጎ ይቆጥራቸዋል፡፡ ‹‹እነዚህ ስድ ሞኞች! ልጄ ኢየሱስ ለሁለተኛ ጊዜ እንዲጠመቅና እንደገና በመስቀል ላይ እንዲሞት እየጠየቁ ነው! በኢየሱስ ቤዛነት እያመኑ ገናም ራሳቸውን ሐጢያተኞች ብለው ይጠራሉ! ቅን በሆነው ሕጌ እፈርድባቸውና ሁሉንም ወደሚነደው የሲዖል ጉድጓድ እልካቸዋለሁ፡፡ ብቸኛ ልጃችሁን ዳግም ለመግደል ፈቃደኞቹ ትሆናላችሁን? እናንተም በተግባር ለምትሰሩዋቸው ሐጢያቶች ልጄን ለሁለተኛ ጊዜ እንድገድለው እየጠየቃችሁኝ ነው፡፡ የምትሰሩዋቸውን ሐጢያቶች በተደጋጋሚ ይቅር እንድል በመጠየቅ ቁጣዬን አትቀስቅሱብኝ፡፡ በውሃውና በመንፈሱ የቤዛነት ወንጌል ብቻ እመኑ፡፡››
ኢየሱስ ሐጢያተኛ ሆነው ለቀሩት እውነተኛ ወንጌል ወደሚሰበክበት ቤተክርስቲያን መሄድ፣ የሐሰት እምነትን መተው፣ ሐሰትን በእምነት በማሸነፍ ቤዛነትን መቀበል እንደሚገባቸው ይነግራቸዋል፡፡  
አሁን እናንተም በልባችሁ በማመን የምትድኑበት ጊዜ ነው፡፡ ታምናላችሁን? 
 

በእውነት ላይ ሳይሆን በሥራዎች ላይ የተመሰረተ እምነት ውጤቱ፡፡ 
 
ብዙ ክርስቲያኖች አንድ ወጥ የሆነ የታመነ ሕይወት መምራት የተሳናቸው ለምንድነው? 
ምክንያቱም በሥራዎቻቸው ስለሚደገፉ ነው፡፡
 
በኢየሱስ የሚያምኑ ነገር ግን ነጻ ያልወጡ ሐጢያተኞች እንኳን ከ3-5 ዓመታት ብሩህ ሆነው ሊያበሩ ይችላሉ፡፡ በመጀመሪያ ግለት ይታይባቸዋል፡፡ ነገር ግን እምነታቸው ከጊዜ ጋር ይደበዝዛል፡፡ በኢየሱስ የምታምኑት በሥራዎቻችሁ አማካይነት ከሆነ ግለታችሁ ፈጥኖ ይጠፋል፡፡ 
የታወረ ሊያይ አይችልም፡፡ ስለዚህ በሌሎች ስሜቶቻቸው ላይ ይደገፉና በዚህ መንገድ እውቀትን ያከማቻሉ፡፡ አይኖቻቸው እንባን ሲያቀሩ ይህን የሐጢያቶቻቸው ማስተሰርያ አድርገው በስህተት ይወስዱታል፡፡ እውነተኛ ስርየት ስሜት አይደለም፡፡ 
በመንፈስ የታወሩ ሰዎች የተለያዩ የመነቃቃት ስብሰባዎችን በመካፈል የመጀመሪያውን ፍቅራቸውን ለመመለስ ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ስሜታቸውን ሊመልሱት አይችሉም፡፡ የሐጢያትን ስርየት ማግኘትም እንዲሁ የሚቻል ነገር አይደለም፡፡ ከመጀመሪያው ጀምሮ በትክክል አምነው ከነበረ ቀናት በተቆጠሩ ጊዜ ስርየትና የእርሱ ጸጋ ይበልጥ ፊታቸውን ብሩህ አድርጎ ባበራው ነበር፡፡  
ነገር ግን የሐሰት ስርየት መጀመሪያ ላይ ደምቆ ከዚያ በኋላ ድምቀቱን ያጣል፡፡ የስሜቱ ግለት ፈጽሞ ይበርዳል፡፡ ምክንያቱም በመንፈሳዊ ሁኔታቸው የታወሩ ከመጀመሪያውም እውነተኛ የሆነውን ወንጌል መስማት ተስኖዋቸዋልና፡፡  
ግብዝ የሆኑ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ቅዱሳት መጽሐፍቶችን በእጆቻቸው ይይዛሉ፤ የጌታን ጸሎትና የሐዋርያትን የእምነት ስርዓተ ደንብ ያነበንባሉ፡፡ ሁልጊዜም ይጸልያሉ፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሹመትን ያገኛሉ፡፡ በስሜትም ይሞላሉ፡፡ ነገር ግን ሐጢያቶቻቸው ይከማቻሉ፡፡ በመጨረሻ እግዚአብሄር ያባርራቸዋል፡፡ በስተ ውጪ በሃይማኖታዊ ግለት ኖራ ተለስነዋል፡፡ በስተ ውስጥ ግን ልቦናቸው በሐጢያት በስብሶዋል፡፡ ይህ በእውነት ላይ የተመሰረተ እምነት ውጤት ሳይሆን በሥራዎች ላይ የተመሰረተ ሃይማኖት ውጤት ነው፡፡ 
 


በእምነት ጻድቃን እንሆናለን፡፡ 

 
ለዚህ ዓለም ሐጢያት ሁሉ ቤዛነት አስቀድሞ ተፈጽሞዋልን? 
አዎን፡፡ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ሞቱ  አማካይነት ተፈጽሞዋል፡፡
 
ዕብራውያን 10፡16-18ን እናንብብ፡፡ ‹‹ከዚያም ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፡፡ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ፤ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ ብሎ ከተናገረ በኋላ ሐጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል፡፡ የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ ከዚህ ወዲህ ስለ ሐጢአት ማቅረብ የለም፡፡››   
አሁን እኛ በኢየሱስ የጥምቀት ውሃና በመስቀሉ ደም  ቤዛነትን ስላገኘን ከዚህ በኋላ የሐጢያት ስርየት አያስፈልገንም፡፡ ይህ መጀመሪያ ላይ ስትሰሙት የሚታመን ነገር ላይመስላችሁ ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ጋር የሚስማማ ነው፡፡ እነዚያ የሰው ቃሎች ናቸውን? መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉም ነገር የሚለካበት መለኪያና ቱምቢ ነው፡፡   
‹‹ከዚያም ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፡፡ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ፤ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ፡፡›› ቤዛነትን ካገኛችሁ በኋላ የሚሰማችሁ ስሜት ምንድነው? አሁን ልባችሁ ከሐጢያት ነጻ ስለሆነ ታድሳችኋል፤ ጻድቅ ሰው ሆናችኋል፡፡ በብርሃን መኖርም ትችላላችሁ፡፡  
ጌታ በዕብራውያን 10፡17 ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹ሐጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም፡፡›› እርሱ ቤዛነትን ያገኙትን ሐጢያቶችና ዓመጾች እንደማያስታውስ ነገረን፡፡ ለምን? ምክንያቱም ኢየሱስ እጅግ ተስማሚ በሆነ መንገድ ‹‹እንዲህ›› ተጠምቋልና፡፡ ኢየሱስ ሐጢያትን በሙሉ ከወሰደ በኋላ በእርሱ በሚያምኑት ምትክ ተፈረደበት፡፡   
አሁን እርሱ ለሐጢያቶቻችን በሙሉ ዋጋ ስለከፈለ ሐጢያቶቻችንን ልናስታውስ ብንችልም ስለ እነርሱ የጥፋተኝነት ስሜት አይሰማንም፡፡ ኢየሱስ ሐጢያትን ሁሉ ስላነጻና ስለ እኛም በመስቀል ላይ ስለደማ ዳግመኛ ለሐጢያቶቻችን አንሞትም፡፡ 
ዕብራውያን 10፡18 እንዲህ ይላል፡- ‹‹የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ ከዚህ ወዲህ ስለ ሐጢአት ማቅረብ የለም፡፡›› ይህ ማለት እርሱ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ደመሰሰ ማለት ነው፡፡ በኢየሱስ ዳግም የተወለዱትም ዳግመኛ ምንም አይነት የሐጢያት ቁርባን ማቅረብ አያስፈልጋቸውም፡፡
‹‹ኦ አምላኬ እባክህ ይቅር በለኝ፡፡ በኢየሱስ ባምንም አሁንም ድረስ በጉሰቁልና ውስጥ የምኖረው ገና ቤዛነትን ስላላገኙ ነው፡፡ ክርስቲያን ነኝ፤ አእምሮዬ ግን ሙሉ በሙሉ በሐጢያት በስብሶል፡፡›› እንዲህ ብለን መጸለይ አያስፈልገንም፡፡    
ሐጢያተኞች ሐጢያትን የሚሰሩት እያወቁ አይደለም፡፡ ሐጢያት ምን እንደሆነ የማያውቁት የእግዚአብሄርን የእውነት ሕግ ስለማያውቁ ነው፡፡ እነርሱ የሚያውቁት በሕሊናቸው ሐጢያት መስራት እንደሌለባቸው ነው፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት ማድረግ ምን እንደሆነ አያውቁም፡፡ እግዚአብሄር በኢየሱስ አለማመን ትልቅ ሐጢያት መሆኑን ጠቆመን፡፡ 
ዮሐንስ 16፡9 በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት ማለት ምን እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ‹‹ስለ ሐጢአት በእኔ ስለማያምኑ ነው፡፡›› በእርሱ አለማመን በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት ነው፡፡ ዮሐንስ 16፡10 ጽድቅ ምን እንደሆነ ይናገራል፡፡ ‹‹ስለ ጽድቅም ወደ አብ ስለምሄድ ከዚህ በኋላ ስለማታዩኝ ነው፡፡›› በሌላ አነጋገር ኢየሱስ ይህንን ዓለም ከሐጢያት ሁሉ ነጻ ስላወጣ ለሁለተኛ ጊዜ በመጠመቅና በመስቀል ላይ በመሞት ዳግመኛ ነጻ ሊያወጣን አያስፈልገውም፡፡      
በቤዛነት ያመኑትን ሊቀድሳቸውና ሊያጸድቃቸው ጠራቸው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ቤዛነት በእርሱ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ሞቱ አማካይነት ተጠናቋል፡፡ ሐጢያተኞችን ነጻ ለማውጣት ሌላ ቤዛነት አያስፈልግም፡፡   
‹‹መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 4፡12) ኢየሱስ ሐጢያተኞችን በሙሉ ለማዳን ወደዚህ ዓለም ወረደ፡፡ በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ በመስቀል ላይም ደማ፡፡ ይህንን በልባችሁ እመኑና ዳኑ፡፡ ኢየሱስ በውሃ በመንፈስ ቀደሳችሁ፡፡  
ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በውሃውና በመንፈሱ አማካይነት ከሥጋችን ጠርጎ አስወገደ፡፡ እኛ በእምነት የዳንን ሰዎች ነን፡፡ እውነቱን ብናምን፤ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በወንጌል ብናምን ለአንዴና ለመጨረሻ ጻድቃን እንሆናለን፡፡ የኢየሱስ ጥምቀትና የመስቀል ላይ ሞቱ፤ እነዚህ ሁለቱ ፍሬ ነገሮች መሰረታዊውን እውነት ያዋቅራሉ፡፡  
 

ሐጢያተኞች እንደ መከለያ የሚጠቀሙባቸው ጥቅሶች፡፡ 
 
ቤዛነትን የምናገኘው ሐጢቶቻችንን ስንናዘዝ ነው ወይስ አስቀድሞም ቤዛነትን አግኝተናል? 
እግዚአብሄር ለአንዴና ለመጨረሻ ከሐጢያት ቤዛነትን ሰጠን፡፡
 
1ኛ ዮሐንስ 1፡9 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በሐጢአታችን ብንናዘዝ ሐጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው፡፡›› 
ይቅር ለመባል የሚያስፈልገን ሐጢያቶቻችንን መናዘዝ ብቻ ቢሆን ኖሮ ጥሩ በሆነ ነበር፡፡ ይህንን በአእምሮዋችን ይዘን አንዳንድ የቃለ እግዚአብሄር ምሁራን አዲስ ትምህርት ይዘው ቀርበዋል፡፡ አንድ ሰው ሐጢያቶቹን በሚናዘዝበት ጊዜ ሁሉ ይቅርታን ሊያገኝ ይችላል ብለው ሙጭጭ ይላሉ፡፡ ይህ ምቹ አይደለምን? ነገር ግን ኢየሱስ ራሳችንን ለእግዚአብሄር በምንናዘዝበት ጊዜ ሁሉ በጭራሽ ሐጢያቶቻችን ይሰረያሉ አላለም፡፡ 
ሐጢያቶቻችንን በመናዘዝ ብቻ በእርግጥ ይቅርታን ልናገኝ እንችላለን ወይስ አስቀድሞ ቤዛነትን አግኝተናል? የምታምኑት የትኛውን ነው? ይህንን ሐሰተኛ ትምህርት የሚደግፉ ሰዎች ሐጢያቶቻቸውን በሚናዘዙበት ጊዜ ሁሉ ይቅርታን እንደሚያገኙ ያምናሉ፡፡ ነገር ግን የቤዛነትን እውነተኛ ቃሎች ስለማያውቁ ሐጢያት በልቦቻቸው ውስጥ ይቀራል፡፡ በኢየሱስ የሚያምኑ ሐጢያተኞች በተግባር ለሰሩዋቸው ሐጢያቶች ይቅርታን ለማግኘት በሚጸልዩበት ጊዜ ሁሉ ይቅርታን የሚያገኙ መሆናቸው ትርጉም አይሰጥም፡፡ 
ከዚህ የተነሳ በመቤዠት ላይ የተናገራቸውን የእርሱን ቃሎች መቀበልና የተነገረን ምንም ይሁን በእውነትና በሐሰት መካከል መለየት ይኖርብናል፡፡
ሐጢያተኞች 1ኛ ዮሐንስ 1፡9ን በተሳሳተ መንገድ ይረዱታል፡፡ ጥቅሱ የሚመለከተው በየቀኑ ለሚሰሩ ሐጢያቶች የሚሰጠውን ይቅርታ እንደሆነ በተሳሳተ መንገድ ያስባሉ፡፡ አስተምህሮቶቹን በጥንቃቄ እናንብባቸው፡- ‹‹በሐጢአታችን ብንናዘዝ ሐጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው፡፡›› የዳንነው ከአዳም ሐጢያት ብቻ ስለሆነ የታመነና ጻድቅ ሆኖ ይቅር ይለን ዘንድ በተግባር የሰራናቸውን ሐጢያቶች መናዘዝ አለብን ብላችሁ ታስባላችሁን? እነዚህ ከሥጋችን ድካም የመነጩ የተዛቡ አስተሳሰቦች ናቸው፡፡  
በኢየሱስ ጥምቀትና ደም በምናምንበት ወቅት ይህ እውነት እንዳልሆነ እንረዳለን፡፡ ሐጢያት በሙሉ ቀድሞውኑም ከረጅም በፊት በጥምቀቱና በመስቀሉ ደም ነጽቶዋል፡፡   
በመንፈሱ መሰረት ማመንና በተዛቡ አስተሳሰቦች መሰረት ማመን ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ በራሳቸው አስተሳሰቦች መሰረት የሚያምኑ በየቀኑ ስለ ሐጢያቶቻቸው መታጠብ እንደሚያስፈልጋቸው ይሰማቸዋል፡፡ ነገር ግን በውሃውና በደሙ ቤዛነት የሚያምኑ በኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትና ደም አማካይነት ለአንዴና ለመጨረሻ ነጻ ወጥተዋል፡፡    
በአዲስ መልክ ቤዛነትን ለማግኘት በየቀኑ መናዘዝ እንዳለባቸው የሚያምኑ ሰዎች በኢየሱስ ጥምቀትና ደም አማካይነት የተገኘውን ቤዛነት ያለ ማመን ሐጢያት እየሰሩ ነው፡፡ 
በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ አማካይነት ለአንዴና ለመጨረሻ ቤዛነትን አግኝታችኋልን? ቤዛነትን ያላገኙ ሐጢያቶቻቸውን በየቀኑ በመናዘዝ ደህንነትን ለማግኘት ይሞክራሉ፡፡ ይህ ወደፊት የሚሰሩዋቸውን የተግባር ሐጢያቶች በሚመለከት ያለውን ችግር አያቃልልም፡፡ 
እነርሱ ወደፊት ለሚሰሩዋቸው ሐጢያቶች አስቀድመው ለመናዘዝ ይሞክሩ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እንዲህ በማድረጋቸው በኢየሱስ ላይ ያላቸው እምነት ጎዶሎ መሆኑን ያሳያሉ፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱና በደሙ ፍርድን በራሱ ላይ በመውሰድ ለአንዴና ለመጨረሻ ከሐጢያት ነጻ አወጣን፡፡ እኛ በእርሱ በማመናችን ብቻ ነጻ ወጥተናል፡፡    
ለመዳን የወደፊት ሐጢያቶቻችሁን እንኳን መናዘዝ እንዳለባችሁ የምታስቡ ከሆነ ከውሃና መንፈስ ዳግም ስለ መወለድ አንዳች ነገር ከማያውቁት አላማኒዎች የተለያችሁ አትሆኑም፡፡ ሐጢያተኞች በኑዛዜ አማካይነት ቤዛነትን ሊያገኙ አይችሉም፡፡  
ስለዚህ ‹‹እኔ ገና ቤዛነትን ያላገኘሁ ሐጢያተኛ ነኝ›› ብላችሁ በቅንነት ተናዛችሁ የእርሱን ጥምቀትና የመስቀል ላይ ሞት ወንጌል የምታደምጡና የምታምኑ ከሆነ እግዚአብሄር ከሐጢያቶቻችሁ ሁሉ ነጻ ያወጣችኋል፡፡    
ነገር ግን በቤዛነቱ ወንጌል ካላመናችሁና በንስሐ ጸሎት ስር የምትደበቁ ከሆናችሁ ኢየሱስ ጻድቅ ፈራጅ ሆኖ ዳግመኛ ወደዚህ ዓለም በሚመጣበት ጊዜ አስከፊ ፍርድ ይጠብቃችኋል፡፡   
በውሃውና በመንፈሱ የቤዛነት ወንጌል የማያምኑ ይፈረድባቸዋል፡፡ ከኑዛዜዎቻቸው ጀርባ ቢደበቁም ፍርድ ይገጥማቸዋል፡፡ ስለዚህ የፍርዱን ቀን አትጠብቁ፡፡ አሁኑኑ በተባረከው የውሃና የመንፈስ ወንጌል እመኑ፡፡ 
 


ተገቢው ኑዛዜና እውነተኛው እምነት፡፡   

 
ለሐጢያተኛ ተገቢው ኑዛዜ ምንድነው? 
በእውነተኛው ወንጌል እስካላመነ ድረስ አሁንም ድረስ ሐጢያት ያለበትና ሲዖል የሚሄድ መሆኑን መናዘዝ ነው፡፡
 
እግዚአብሄር ለአንዴና ለመጨረሻ ተቤዠን፡፡ እኔ ለማለት እየሞከርሁ ያለሁትን የሚያብራራ አንድ እውነተኛ የሕይወት ምሳሌ ይኸውላችሁ፡፡ የሰሜን ኮርያ ሰላይ ወደ ደቡብ ኮርያ መጣ እንበል፡፡ በዚህ ጊዜ እኛ ምን ያህል እንደበለጸግን ሲመለከት መታለሉን ስለተረዳ ራሱን ለማጋለጥ ወሰነ፡፡  
በአቅራቢያው ወደሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ ከሄደ በኋላ ‹‹እኔ ከሰሜን የመጣሁ ሰላይ ነኝ፡፡›› ወይም ‹‹ወደ ደቡብ የመጣሁት እከሌንና እከሌን ለመግደልና ያንንና ይህንን ለማፈንዳት ነው፡፡ ቀደም ብዬ ይህንን አፈንድቻለሁ፡፡ አሁን ግን እጄን እሰጣለሁ፡፡ ስለዚህ ከእንግዲህ ሰላይ አይደለሁም›› በማለት ሊናዘዝ ይችላል፡፡   
ይህ ትክክለኛ ኑዛዜ ነውን? ለመናዘዝ ከፈለገ ማለት ያለበት ነገር ቢኖር ‹‹እኔ ሰላይ ነኝ›› ብቻ ነው፡፡ ይህ ቀላል ዓረፍተ ነገር ግለሰቡ መጥፎ ሰው እንደሆነና ሊፈረድበት እንደሚገባ ሁሉን ነገር ይጠቁማል፡፡ ከዚህ ቀላል አረፍተ ነገር አንጻር እርሱ የተሰጠው ተልዕኮ ምንም ቢሆን ይቅርታን ያገኛል፡፡ 
ልክ እንደዚያ ሁሉ አንድ ሐጢያተኛ በእግዚአብሄር ፊት ‹‹እኔ ቤዛነትን ያላገኘሁ ሐጢያተኛ ነኝ፡፡ ወደ ሲዖል ልወረወርና ሊፈረድብኝ የሚገባኝ ነኝ፡፡ እባክህ አድነኝ›› ቢልና በኢየሱስ ቢያምን ቤዛነትን ያገኛል፡፡ ኢየሱስ ስለ እኛ ተጠመቀና ደሙን አፈሰሰ፡፡ እኛ ማድረግ ያለብን ለመዳን በእርሱ አማካይነት ለደህንነት ማመን ነው፡፡ 
ዮሐንስ ራዕይ 2፡17 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎዋል፡፡›› መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን ስም የሚያውቀው እውነተኛውን ወንጌል ያገኘ ብቻ መሆኑ ይነግረናል፡፡ ጻድቅ የመሆንን ምስጢር የሚያውቀው ለአንዴና ለመጨረሻ ቤዛነትን ያገኘ ብቻ ነው፡፡  
ይህንን የማያውቁ በየቀኑ የንስሐ ጸሎቶችን ቢጸልዩም አሁንም ሐጢያተኞች ይሆናሉ፡፡ መናዘዝ ማለት በየቀኑ ለይቅርታ መጸለይ ማለት አይደለም፡፡ ምንም እንኳን አንድ ሰው ለ10 ዓመት ክርስቲያን ሆኖ ቢቆይም በየቀኑ የእግዚአብሄርን ይቅርታ የጠየቀ ሰው አሁንም ሐጢያተኛ ነው፡፡ አሁንም የእግዚአብሄር ልጅ አልሆነም፡፡   
እነርሱ ለመዳን ሐጢያተኞች መሆናቸውን መናዘዝና በኢየሱስ ቤዛነት ማመን ይኖርባቸዋል፡፡ እውነተኛው እምነት ይህ ነው፡፡  
 

1ኛ ዮሐንስ 1፡9 ስለ ኑዛዜ የሚነግረን የአንድን ሰው ሐጢያቶች ስለ መዘርዘር አይደለም፡፡  
 
ለመዳን ሐጢያቶቻችንን መናዘዝ ያለብን አንድ ጊዜ ነው ወይስ በየቀኑ? 
አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
 
አንድ ሌባና ወንጀለኛ ምግባሮቻቸውን በመናዘዝ ብቻ ቤዛነትን ሊያገኙ ይችላሉን? ሐጢያተኞች ሐጢያቶቻቸውን በመናዘዛቸው ብቻ ሊድኑ አይችሉም፡፡ እነርሱ ሊድኑ የሚችሉት በተባረከው የኢየሱስ የውሃና የመንፈስ ወንጌል በማመን ብቻ ነው፡፡ አንዳንድ የተሳሳቱ ክርስቲያኖች እንዲህ በማለት ኑዛዜዎችን ያደርጋሉ፡፡ 
‹‹ውድ እግዚአብሄር ዛሬም እንደገና ከአንድ ሰው ጋር ተጣላሁ፡፡ ሐጢያትን ሰራሁ፡፡ አንድን ሰው አታለልሁ፡፡ የሆነ ነገር ሰረቅሁ፡፡›› 
እንደዚያ የሚቀጥሉ ከሆነ እግዚአብሄር ‹‹አንተ ሐጢያተኛ ዝም በል! እና ምን ይሁን?›› ይለዋል፡፡
‹‹እግዚአብሄር ሆይ እባክህ አድምጠኝ፡፡ ሐጢያቶቻችንን እንድንናዘዝ ነግረኸናል፡፡ ምህረትህንም እለምናለሁ፡፡›› 
እግዚአብሄር ሊሰማው የሚፈልገው የዚህ አይነት ጸሎት አይደለም፡፡ እርሱ ሊሰማው የሚፈልገው በውሃውና በመንፈሱ ቤዛነት የሚያምኑትን፤ ሐጢያቶቻቸውን አምነው የሚቀበሉትንና ዳግም በመወለድ ወንጌል በእርግጠኝነት የሚያምኑ ሰዎችን ጸሎት ነው፡፡ 
አውግስጦስ የእናቱን ጡት ከሚጠባበት ጊዜ ጀምሮ ንስሐ እንደገባ ተናገረ፡፡ እርሱ እንደዚያ አይነት ኑዛዜ መንግሥተ ሰማይ እንደሚያስገባው አሰበ፡፡ በዚህ ከመሳቅ ሌላ ምንም አናደርግም፡፡ የራስን ሐጢያቶች መናዘዝ ብቻውን ምንም አይፈይድም፡፡  
እግዚአብሄር ‹‹ዝም በል! ሐጢአት መስራትህን ብቻ ንገረኝ፤ ከዚያም ስለ እርሱ መናገርህን አቁም፡፡ እስካሁን ድረስ በስህተት አምነሃል፡፡ ስለዚህ እውነተኛው ወንጌል ወደተስተማረበት ቤተክርስቲያን ሂድ፡፡ በተገቢው መንገድ በቤዛነት ወንጌል እመንና ቤዛነትን አግኝ፡፡ ካልሆነ መጥቼ እፈርድብሃለሁ›› ይለዋል፡፡ 
የሐጢያት ይቅርታን ለማግኘት የሚጸልዩ የንስሐ ጸሎቶችና በኑዛዜ አማካይነት ለመዳን የሚደረጉ ማናቸውም ሌሎች ሙከራዎች የተዛባና እውነተኛ ያልሆነ እምነትን ይጠቁማል፡፡   
ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ስናምን የውሃውና የደሙ ወንጌል ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ነጻ እንደሚያወጣን በ1ኛ ዮሐንስ 1፡9 ላይ ተጽፎዋል፡፡ 
 

‹‹ከእኔ ራቁ፡፡››  
 
ዓመጻን ማድረግ ምን ማለት ነው?
ይህ ማለት በሰው ውስጥ ሐጢያትን በልብ ይዞ በኢየሱስ ማመን ማለት ነው፡፡
 
ክርስቲያን የሆኑ ሐጢያተኞች የተዛባ እምነት ስላላቸው በኢየሱስ ፊት ዓመጻን ያደርጋሉ፡፡ ‹‹በዚያን ቀን ብዙዎች፡- ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ተዓምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል፡፡ የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ፡፡›› (ማቴዎስ 7፡22-23)   
አንድ በስህተት የሚያምን ሰው ሞተና በእግዚአብሄር ፊት ቆሞ ‹‹ጌታ ሆይ እንደምን ሰንብተሃል? እዚያ ሆኜ ስለ አንተ ሳስብ በጣም ውብ መሰልከኝ፡፡ እዚህ ግን ይበልጥ ውብ ነህ፡፡ አመሰግንሃለሁ ጌታዬ፡፡ አዳንከኝ፡፡ ምንም እንኳን በልቤ ውስጥ ሐጢያት ቢኖርም ሐጢያት አልባ አድርገህ እንደምትመለከተኝ አምናለሁ፡፡ እዚህ የመጣሁትም አንተ ሰማይ እንደምትወስደኝ ቃል ስለገባህልኝ ነው፡፡ አሁን አበቦች ሁሌም ወደሚፈኩበት ወደዚያ እሄዳለሁ፡፡ በል ቻዎ እንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለሁ›› ሲል አስቡ፡፡     
ወደ አትክልቱ ስፍራ መንቀሳቀስ ሲጀምር ኢየሱስ ያስቆመዋል፡፡ ‹‹ቆይ እስቲ ይህ ሰው በልቡ ሐጢያት እንዳለበት እንይ፡፡ ሐጢያተኛ ነህን?››  
‹‹በእርግጥ ሐጢያት አለብኝ፡፡ ነገር ግን በአንተ አላመንሁምን?›› 
‹‹በእኔ ብታምንም ሐጢያት አለብህን?›› 
‹‹አዎን በእርግጥ ሐጢያት አለብኝ፡፡›› 
‹‹ምን? ሐጢያት አለብህ? የሕይወትን መጽሐፍ አምጡልኝ፡፡ የሥራዎችን መጽሐፍም አምጡልኝ፡፡ ስሙንም ተመልከቱ፡፡ ስሙም የትኛው መጽሐፍ ላይ እንደተጻፈ ተመልከቱ፡፡›› 
እርግጠኛ ለመሆንም ስሙ በሥራዎች መጽሐፍ ላይ ተመዝግቦዋል፡፡ 
‹‹አሁን በምድር ላይ የሰራሃቸውን ሐጢያቶች በሙሉ ተናዘዝ፡፡››  
ሰውየው ያንን ለማደረግ ባይሞክርም እግዚአብሄር አፉን ከፍቶ ሐጢያቶቹን እንዲናዘዝ አስገደደው፡፡ 
‹‹አዎ እንዲህና እንዲህ ያሉትን ሐጢያቶች ሰርቻለሁ፡፡…››  
በጣም ግራ ተጋባ፤ አፉን መክደን አልቻለም፡፡ 
‹‹እሺ አሁን ይበቃል! እርሱ ሲዖል ለመግባት የሚያስፈልገውን ያህል ሐጢያት ሰርቷል፡፡ እርሱ ብቁ ከመሆንም በላይ ነው! ስለዚህ ወደዚያ የመቃጠያ ስፍራ ላኩት!›› ተብሎ ይፈረድበታል፡፡  
ይህ ሰው አበቦች ወደሚፈኩበት ስፍራ አልተላከም፡፡ ነገር ግን እሳትና ዲን ወደተሞላ ስፍራ ተላከ፡፡ ወደ ሲዖል በሚወሰድበት ጊዜ ጥርሱን በንዴት ያፋጭ ነበር፡፡ 
‹‹እኔ በአንተ አመንሁ፡፡ በስምህ  ተነበይሁ፡፡ በስምህም ሰበክሁ፡፡ አንተን ለማገልገልም ቤቴን ሸጥሁ፡፡ ዕጓለ ሙታኖችን ረዳሁ፡፡ በስምህ ታገስሁ፡፡ ንጋት ላይ ጸለይሁ፡፡ ሕሙማንን ተንከባከብሁ፡፡… የሚገባኝ  መንግሥተ ሰማይ ነው›› በማለት ቅሬታውን ያቀርባል፡፡ 
ጥርሶቹን ከመጠን በላይ ስላፋጫቸው ከጥቅም ውጪ አደረጋቸው፡፡ ሲዖል በደረሰ ጊዜ በኢየሱስ ያለውን እውነተኛ የቤዛነት ትርጉም የማያውቁ ክርስቲያኖችን ሁሉ ያገኛል፡፡ የቤዛነትን ወንጌል በተሳሳተ መንገድ የሚያስተውሉ ሁሉ በእርሱ ተቀባይነትን ያጣሉ፡፡  
 

የሐሰተኛ ምዕመናን ሐጢያቶች በሥራዎች መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግበዋል፡፡ 
 
የሐጢያተኞች ሐጢያቶች በሙሉ የሚመዘገበው የት ነው?
የሚመዘገቡት በልቦቻቸውና በሥራዎች መጽሐፍ ላይ ነው፡፡
  
በኢየሱስ ብናምንም ባናምንም እግዚአብሄር በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያት ያለባቸውን ሁሉ ያጠፋቸዋል፡፡ እርሱ በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ቅንጣት ታህል ሐጢያት እንኳን ቢያገኝ ያ ሰው በፍርድ ቀን የሚገባው ወደ ሲዖል ነው፡፡ እግዚአብሄር ገና ቤዛነትን ያላገኙ ሐጢያተኞች ቤዛነትን ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ነጻ ያልወጡ መሆናቸውን እንዲናዘዙ ይነግራቸዋል፡፡
የሐጢያተኛ ሐጢያቶች የተመዘገቡት በልቡ ውስጥ ነው፡፡ ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ዳግም የተወለዱ ሰዎች ሐጢያቶቻቸውን ያስታውሱ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከልቦቻቸው ተሰርዘዋል፡፡ እነርሱ ጻድቃን ናቸው፡፡   
ነገር ግን ዳግም ያልተወለዱ ሰዎች በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያት አለባቸው፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያተኞች ናቸው፡፡ ለመጸለይ በሚንበረከኩበት ጊዜ ሁሉ ሐጢያቶቻቸው ከእግዚአብሄር ይለዩዋቸውና ጸሎቶቻቸውንም እንዳይሰማ  ይከለክሉታል፡፡ እነርሱ ለዚህም ለዚያም ይጸልያሉ፤ ሐጢያቶቻቸው ግን አሁንም እዚያው ናቸው፡፡ ከ10 አመት በፊት፣ ከ11 አመት በፊት፣ ከ20 አመት በፊት ሳይቀር ለፈጸሙዋቸው መተላለፎቻቸው ንስሐ በመግባት ሐጢያቶቻቸውን በመናዘዝ ዕድሜያቸውን ይፈጃሉ፡፡   
በጸሎታቸው በተደጋጋሚ ንስሐ መግባት ይኖርባቸዋልን? ይህንን የሚያደርጉትስ ለምንድነው? ይህንን ማድረግ አይፈልጉም፡፡ ነገር ግን መጸለይ ሲጀምሩ በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያተኞች መሆናቸውን ያስታውሳሉ፡፡ ከዚህ የተነሳ ከልባቸው ከመጸለያቸው በፊት ለሐጢያቶቻቸው ስርየት ማግኘት እንደሚኖርባቸው ይሰማቸዋል፡፡  
እግዚአብሄር ሐጢያቶቻቸውን በልቦቻቸው ገበታዎች ላይ በብረት ብርዕ ስለጻፈው ሐጢያቶቻቸው በጭራሽ ሊፋቁ አይችሉም፡፡ ከዚህ የተነሳ ወደ እግዚአብሄር በሚቀርቡበት ጊዜ ሁሉ ሐጢያቶቻቸውን መናዘዝ እንደሚኖርባቸው ይሰማቸዋል፡፡ ስለዚህ ምሉዕ ከሆነው የኢየሱስ ወንጌል ገሚሱን ብቻ የሚያምኑ ሐጢያተኞች ሆነው በጉስቁልና ይኖሩና ፍጻሜያቸው ሲዖል ይሆናል፡፡     
በኤርምያስ 17፡1 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹የይሁዳ ሐጢአት በብረት ብዕርና በተሾለ ዕብነ አልማዝ ተጽፎአል፡፡ በልባቸው ጽላትና በመሠዊያቸው ቀንዶች ተቀርጾአል፡፡››   
ይሁዳ የእስራኤል ሕዝብ ንጉሳዊ ነገድ ስም ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይሁዳ የሰውን ዘር ሁሉ እንዲወክል ስላስቀመጠው ይሁዳ ማለት ሁሉም ሕዝብ ማለት ነው፡፡ 
የይሁዳ ሐጢያት የተጻፈው በብረት ብዕርና ብረትን በሚቆርጠው ዕብነ አልማዝ ቁስ ነው፡፡ አልማዝ በምድር ላይ ጠንካራው ቁስ ነው፡፡ ሐጢያቶቻችን በብረት ብዕርና በተሾለ ዕብነ አልማዝ ተመዝግበዋል፡፡    
አንዴ ከተቀረጹ በኋላ መቼም ቢሆን አይጠፉም፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እስካላመንን ድረስ ሊጠፉ አይችሉም፡፡  
አስተሳሰቦቻቸው ቤዛነትን ማግኘት፣ በክርስትና ትምህርቶች ማመን፣ ቃለ እግዚአብሄርን ማስታወስና ራሳቸውን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት መስጠት ሐጢያት በልቦቻቸው ውስጥ እስካለ ድረስ ፋይዳ የለውም፡፡  
ሐጢያቶቻቸው ያለ ኢየሱስ ጥምቀት ፈጽሞ ስለማይፋቁ ሐጢያተኞች ሐጢያቶቻቸውን በማስታወስ በሚጸልዩበት ጊዜ ሁሉ ‹‹አቤቱ እኔ ሐጢያተኛ ነኝ›› ይላሉ፡፡ ምንም ያህል ከእግዚአብሄር ጋር አብዝተው ሕብረት ለማድረግ ቢሞክሩ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥም ብዙ ሐላፊነትን ቢሸከሙ፣ የስነ መለኮት ትምህርትን ቢማሩ በልቦቻቸው ውስጥ አሁንም ሐጢያት አለ፡፡  
ስለዚህ ወደ ተራሮች ይወጣሉ፡፡ በልሳን ለመናገርም ከንቱ ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ የሚንቀለቀል የእሳት ነበልባል ራዕዮችንም ማየት ይሻሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ፋይዳ የለውም፡፡ ሐጢያት በልባችሁ ውስጥ እስካለ ድረስ ፈጽሞ ሰላም አይኖራችሁም፡፡   
በኤርምያስ 17፡1 ላይ እንደተጻፈው ሐጢያቶቻችን በመሠዊያዎቻችን ቀንዶች ላይ ተጽፎዋል፡፡ በሰማይ የሕይወትና የሥራ መጽሐፎች አሉ፡፡ የሐጢያተኞች ሐጢያቶች በስራዎች መጽሐፎች ላይ ተመዝግበዋል፡፡ ከዚህ የተነሳ ሰዎች ከመተላለፎቻቸው በጭራሽ ማምለጥ አይችሉም፡፡ እግዚአብሄር ሐጢያቶቻችንን በሥራዎች መጽሐፎችና በሕሊናዎቻችን ጽላቶች ይመዘግባቸውና በሕጉ አማካይነት ለእኛ ያሳየናል፡፡   
በኢየሱስ ጥምቀትና እርሱ ለእኛ ሲል በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም በማመን እነዚህን ዘገባዎች ጠራርገን ማስወገድና መዳን አለብን፡፡ ያን ጊዜ ለዘላለም ሕይወት ዝግጁ እንሆናለን፡፡ ስሞቻችንም በሕይወት መጽሐፍ ላይ ይጻፋሉ፡፡  
 

ስማችሁ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ አለ? 
 
በሕይወት መጽሐፍ ላይ የተመዘገበው የእነማን ስም ነው?
በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያት የሌለባቸው ሰዎች ስሞች በዚያ ላይ ተመዝግበዋል፡፡ 
 
በሕይወት መጽሐፍ ላይ ስማችሁ መመዝገቡ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ስማችሁ በዚያ መጽሐፍ ላይ ካልተመዘገበ በኢየሱስ የማመናችሁ ትርጉም ምንድነው? ቤዛነትን በተጨባጭ ለማግኘት ከውሃና ከመንፈስ ዳግም በመወለድ ማመን አለባችሁ፡፡ 
ኢየሱስ ወደዚህ ምድር መጥቶ ልክ 30 ዓመት እንደሆነው የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድ ተጠመቀ፡፡ እኛንም ከሐጢያት ያድነን ዘንድ በመስቀል ላይ ተሰቀለ፡፡ በማቴዎስ 3፡15 ላይ እንደተጻፈው ኢየሱስ ‹‹እንዲህ›› ተጠመቀና በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ ስሞቻችን በሕይወት መጽሐፍ ላይ እንዲመዘገቡ በዚህ ማመን አለብን፡፡  
ሰዎች ሞተው በእግዚአብሄር ፊት ሲቆሙ እግዚአብሄር እንዲህ ይላቸዋል፡- ‹‹የዚህ ሰው ስም በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ እንዳለ ይታይ፡፡››
‹‹ጌታ ሆይ አለ፡፡›› 
‹‹አዎን በምድር ላይ ስለ እኔ ተሰቃይተሃል፡፡ ዕንባዎችንም አፍስሰሃል፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ይህ መቼም እንዲደርስብህ አልፈቅድም፡፡›› 
ከዚያም እግዚአብሄር በዚህ ሰው ራስ ላይ የጽድቅን አክሊል ይጭንለታል፡፡ 
‹‹አመሰግንሃለሁ ጌታዬ፡፡ ለዘላለምም ሳወድስህ እኖራለሁ፡፡›› 
‹‹መላዕክት በዚህ ሰው ላይ አክሊልን ጫኑ፡፡›› 
‹‹ጌታ ሆይ አንተ እኔን ማዳንህ ከበቂም በላይ ነው፡፡ አክሊሉም ለእኔ ይበዛብኛል፡፡ አመሰግንሃለሁ፡፡ ስላዳንከኝም ለዘላለም አወድስሃለሁ፡፡ አንተ ባለህበት ለመኖር በመቻሌም ደስታዬ ወሰን የለሽ ነው፡፡›› 
‹‹መላዕክት ተንበርከኩና 10,000ኛ ልጄን በጀርባችሁ ተሸከሙት፡፡››
መላዕክቱም ‹‹እሺ ጌታዬ›› ብለው ይመልሱለታል፡፡ 
‹‹እባክህ ጀርባዬ ላይ ታዘል፡፡››  
‹‹በጣም የሚመች ነው፡፡ ይህንን በትክክል እያደረግሁት ነውን? እንሂድ፡፡››  
መልአኩ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ይራመዳል፡፡
‹‹መራመድ ትወዳለህን?››   
‹‹ዋው ይህ ቦታ በጣም ያምራል፡፡ እንዴትስ ትልቅ ነው›› 
ለብዙ ቢሊዮን ዓመታት የተንቀሳቀስሁበት ቢሆንም አሁንም ድረስ መጨረሻውን አላገኘሁትም፡፡›› 
‹‹እውነትህን ነው? መቼም ሳልከብድህ አልቀረሁም፡፡ አሁን መውረድ እችላለሁ፡፡››  
‹‹በዚህ መቼም ቢሆን አይደክመንም›› 
‹‹አመሰግናለሁ፡፡ መንግሥተ ሰማይ መሬት ላይ መቆም እፈልጋለሁ፡፡ ከእኔ በፊት እዚህ የደረሱት ጻድቃን ሁሉ የት አሉ?›› 
‹‹በዚያ በኩል ናቸው፡፡›› 
‹‹ወደዚያ እንሂድ፡፡›› 
ሃሌሉያ! እርስ በርሳቸው ተቃቀፉ፡፡ ፈገግም አሉ፡፡ ለዘላለምም በደስታ መኖር ቀጠሉ፡፡ 
በኢየሱስ አምኖ ነገር ግን ገናም ሐጢያተኛ ሆኖ ስለሞተና በእግዚአብሄር ፊት ስለቆመ ሰው አስቡ፡፡ እርሱም ደግሞ በኢየሱስ እንደሚያምንና ሐጢያተኛ መሆኑን እንደሚቀበል ይናገራል፡፡
እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡- ‹‹የዚህ ሰው ስም በሕይወት መጽሐፍ ተጽፎ እንደሆነ ይታይ፡፡›› 
‹‹ጌታ ሆይ ስሙ መጽሐፉ ውስጥ የለም፡፡›› 
‹‹እንግዲያውስ በሥራዎች መጽሐፍ ላይ ተመልከቱት፡፡››  
‹‹ስሙና ሐጢያቶቹ በዚህ አሉ፡፡›› 
‹‹ይህን ሰው ስለ ነዳጅ ዋጋ ወደማያስብበት ቦታ ላኩት፡፡ በዚያም ለዘላለም ይኑር፡፡›› 
‹‹ኦ ጌታዬ ይህ ትክክል አይደለም፡፡…›› 
እርሱ ትክክል እንዳልሆነ ይናገራል፡፡ እንዲህ በትጋት በኢየሱስ አምኖ ሳለ ለምን ወደ ሲዖል ተላከ? 
ለዚህ ምክንያቱ በሰይጣን በመታለሉና የወንጌሉን ከፊል እውነት ብቻ በማድመጡ ነው፡፡ የኢየሱስን ቤዛነት እውነተኛ ትርጉም በተሳሳተ መንገድ ከተረዳነው የእኛም መጨረሻ እንደዚሁ ሲዖል ይሆናል፡፡ 
ይህ ሰው በኢየሱስ አመነ፡፡ ሆኖም በሰይጣን ተታለለና ሐጢያተኛ እንደሆነ አሰበ፡፡ እውነተኛውን ወንጌል ሰምቶ ቢሆን ኖሮ እምነቱ ልክ አለመሆኑን ይገነዘብ ነበር፡፡ ነገር ግን ከተሳሳቱ አመኔታዎቹ ጋር ራስወዳድነታዊ ቁርኝት በመያዙ ማመን ተሳነው፡፡  
መንግሥት ሰማይ መሄድ የምትፈልጉ ከሆነ ከውሃና ከመንፈሱ ዳግም ስለ መወለድ በደንብ ማመን አለባችሁ፡፡ በማቴዎስ 3፡15 ላይ እንደተጻፈው ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ የወሰደው ‹‹እንዲህ›› ነው፡፡ በውሃውና በደሙ ደህንነት ማመን ይገባችኋል፡፡ 
 
በሥራዎች መጽሐፍ ላይ ስሞቻቸው የተጻፈው እነማን ናቸው?
በልባቸው ሐጢያት ያለባቸው ሰዎች ስሞች በዚያ ተጽፈዋል፡፡
 
የሌላውን ጥያቄ በጭራሽ እምቢ እንደማይል ጥሩ አይነት ሰው ማንኛውንም ነገር ማመን የምትመርጡ ከሆነ ፍጻሜያችሁ ሲዖል ይሆናል፡፡ በሲዖል በጣም ብዙ ጥሩ ሰዎች አሉ፡፡ በመንግሥተ ሰማይ ያሉት ግን ለሚያምኑት ነገር ሲታገሉ የነበሩ እውነተኛ ታጋዮች ናቸው፡፡ 
በሰማይ ያሉት ሐጢያተኞች እንደነበሩና መድረሻቸው ሲዖል እንደነበረ ያወቁ ነገር ግን ሐጢያቶቻቸው በኢየሱስ ጥምቀትና ደም አማካይነት መንጻቱን በምስጋና ያመኑ ናቸው፡፡ በሰማይ የጆሮዎችና የአፎች ክምር አለ ይባላል፡፡ ምክንያቱም ብዙ ሰዎች በኢየሱስ ቤዛነት የሚያምኑት በአፋቸው ወይም በጆሮዎቻቸው ብቻ ስለሆነ እግዚአብሄር ቀሪ አካሎቻቸውን በዲን ወደሚነዱ እሳቶች ይጥላል፡፡ 
አንድ በኢየሱስ የሚያምንና በልቡ ውስጥ ግን አሁንም ድረስ ሐጢያት ያለበት ሰው በእግዚአብሄር ፊት ቆሞ ‹‹ጌታ ሆይ በልቤ ውስጥ ምንም እንኳን ሐጢያት ቢኖርብኝም ሰዎች በኢየሱስ የማምን ስለሆነ ጻድቅ ብለው ይጠሩኛል፡፡ አንተም እኔን ሐጢያት እንደሌለብኝ አድርገህ እንደምትመለከተኝ አምናለሁ፡፡ የተማርሁትና ሳምነው የነበረው ይህንን ነው፡፡ ብዙዎች ያመኑትን አመንሁ፡፡ ይህ እኔ ከመጣሁበት ስፍራ እጅግ በሰፊው ተቀባይነት ያገኘ እምነት ነው›› ይላሉ፡፡
እግዚአብሄርም መለሰ፡፡ ‹‹በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ያለባቸውን ሰዎች ይቅር ማለት አልችልም፡፡ በውሃና በመንፈስ ዳግም የመወለድ በረከት ሐጢያቶችህን በሙሉ አነጻሁ፡፡ አንተ ግን በዚህ ለማመን እምቢተኛ ሆንህ፡፡ መላዕክቶች! ይህንን የማይረባ ሰው ወደ ሲዖል እሳቶች ወርውሩት፡፡›› 
በኢየሱስ አምናለሁ እያለ በልቡ ውስጥ ሐጢያት እንዳለ የሚያስብ ማንኛውም ሰው መጨረሻው ሲዖል ይሆናል፡፡ እውነተኛውን የቤዛነት ወንጌል አድምጡና ከሐጢያት ሁሉ ነጻ ውጡ፡፡ አለበለዚያ በሲዖል ትቃጠላላችሁ፡፡ 
በልባችሁ ውስጥ ሐጢያት እያለ ሐጢያት አልባ ነኝ ማለት እግዚአብሄርን ማታለል ነው፡፡ በስተ መጨረሻ በሐጢያተኞችና በጻድቃን መካከል ምን ያህል ልዩነት እንዳለ መመልከት እንችላለን፡፡ እኔ እናንተ ቤዛነትን እንድታገኙ ለምን እንደምወተውት ትረዳላችሁ፡፡   
ወደ ሲዖልና ወደ መንግሥተ ሰማይ በሚወስዱት መንታ መንገዶች ላይ በቆማችሁ ጊዜ ምሉዕ በሆነው ወንጌል (በኢየሱስ ጥምቀትና ሞት) በሚያምኑትና በሌሎቹ መካከል ያለውን ልዩነት ትረዳላችሁ፡፡ ይህ ትልቅ ልዩነትን ይፈጥራል፡፡ አንዳንዶች መንግሥተ ሰማይ ሲገቡ ሌሎች ግን ወደ ሲዖል ይወርዳሉ፡፡   
በኢየሱስ አምናችሁ አሁንም ገና ሐጢያተኞች ናችሁን? እንዲህ ከሆነ ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ዳግም መወለድ እንዳለባችሁ መገንዘብ ይገባችኋል፡፡ እግዚአብሄር በልባቸው ሐጢያት ያለባቸውን የሚልከው ወደ ሲዖል ነው፡፡ መንግሥተ ሰማይ መግባት የሚችሉት ምሉዕ በሆነው የሐጢያት ይቅርታ የሚያምኑ ብቻ ናቸው፡፡ 
ይህንን አሁኑኑ አድርጉት፡፡ ችላ ካላችሁት በጣም ሊረፍድ ይችላል፡፡ አስቀድማችሁ ተዘጋጁ፡፡ መጨረሻችሁ ሲዖል ከመሆኑ በፊት በውሃውና በመንፈሱ ቤዛነት እመኑና ተቀደሱ፡፡
ለጌታችን ኢየሱስ ክብር ይሁን! እኛን ሐጢያተኞቹን ጻድቅ በማድረጉ ረገድ ላደረገልን ቸርነቱ እናመሰግነዋለን! ሃሌሉያ!   
 

ኢየሱስ፡ የጻድቃን ጠበቃ፡፡  
 
ሐጢያቶቻችን በንስሐ ጸሎት ሊደመሰሱ ይችላሉን?
በፍጹም! ይህ የማይቻል ነው፡፡ ሰይጣን እኛን ከሚያታልልባቸው መንገዶች አንዱ ይህ ነው፡፡
 
1ኛ ዮሐንስ 2፡1-2ን እናንብብ፡- ‹‹ልጆቼ ሆይ ሐጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ፡፡ ማንም ከእናንተ ሐጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፡፡ እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እርሱም የሐጢአታችን ማስተሰርያ ነው፡፡ ለሐጢአታችንም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ሐጢአት እንጂ፡፡››   
እዚህ ላይ የተጻፈውን ማየት ትችላላችሁን? አሁንም ድረስ የሚያምን ነገር ግን በውስጡ ሐጢያት ያለበት አለ?   በልባችሁ ውስጥ ሐጢያት እያለ ለእግዚአብሄር እንደሌለባችሁ የምትናገሩ ከሆነ እናንተ እርሱን እያታለላችሁት ነው፡፡ ራሳችሁንም እያታለላችሁ ነው፡፡    
ነገር ግን ኢየሱስን በትክክል የምታስተውሉት ከሆነና ሐጢያቶችን በሙሉ በዮርዳኖስ ለማንጻት ምን እንዳደረገ የምታምኑ ከሆነ ሙሉ በሙሉ ከሐጢያት ነጻ ትሆናላችሁ፡፡ ያን ጊዜ ‹‹ጌታ ሆይ በአንተ ዳግም ከውሃና ከመንፈስ ተወለድሁ፡፡ ሐጢያት የለብኝም፡፡ በፊትህም ያለ ምንም ሐፍረት መቆም እችላለሁ›› ማለት ትችላላችሁ፡፡ 
ያን ጊዜ ጌታ መልስ ይሰጣል፡፡ ‹‹አዎ ትክክል ነህ፡፡ አብርሃም በእኔ እንዳመነና ጻደቅ እንደሆነ ሁሉ አንተም ጻድቅ ነህ፡፡ ምክንያቱም ሐጢያቶችህን በሙሉ አንጽቻለሁና፡፡››  
ነገር ግን በኢየሱስ ቢያምንም አሁንም ድረስ በልቡ ውስጥ ሐጢያት ያለበትን ሰው አስቡት፡፡ ‹‹በኢየሱስ ስለማምን በልቤ ውስጥ ትንሽ ሐጢያት ቢኖርም ሰማይ እገባለሁ›› ይላል፡፡  
እርሱ ሰማይ ለመግባት አብዝቶ ከመሻቱ የተነሳ በፍርድ ወንበር ፊት ቆሞ ሳለ ሊከራከር ይሞክራል፡፡ ነገር ግን መጨረሻው ሲዖል ነው፡፡ ለምን? ከውሃና ከመንፈስ ዳግም የመወለድን የተባረከ ወንጌል አላወቀም፡፡  
እያንዳንዱ ሰው በምድር ላይ በሚኖርበት ጊዜ ሐጢያተኛ መሆኑን መናዘዝ አለበት፡፡ ‹‹እኔ ሐጢያተኛ ነኝ፡፡ መድረሻዬም ሲዖል ነው፡፡ እባክህ አድነኝ›› በማለትም መጸለይ ይኖርበታል፡፡ ሐጢያተኛ በንስሐ ጸሎቶች ቤዛነትን አያገኝም፡፡ ይልቁንም ለመዳን ሐጢያተኛ መሆኑን ማመንና የውሃውንና የመንፈሱን ቤዛነት መቀበል ይኖርበታል፡፡ ጻድቅ ሊሆን የሚችለው በውሃውና በመንፈሱ ቤዛነት በኩል ብቻ ነው፡፡
በኢየሱስ ይቅርታን የሚያገኘው የአዳም ሐጢያት ብቻ ነው፤ እኛም ደህንነትን ለማግኘት ከእውነተኛ ሐጢያቶቻችን ንስሐ መግባት ይኖርብናል ብሎ ሙጭጭ ማለት ሐሰተኛ ወንጌል ነው፡፡ ይህ በቀጥታ የሚመራን ወደ ሲዖል ነው፡፡ እጅግ በርካታ ምዕመናን ይህንን የሐሰት ወንጌል በማመን ራሳቸውን ለሲዖል ዳርገዋል፡፡ ይህ ዝንባሌ በዘመናችን የበለጠ ገኖ ወጥቶዋል፡፡ 
ሐሰተኛ ወንጌል ውስጥ ብትወድቁ መውደቃችሁን ታውቁታላችሁን? ዕዳዎቻችሁን ከከፈላችሁ በኋላም እንኳን  ባለ ዕዳዎች ልትሆኑ ትችላላችሁን? እስቲ አስቡት፡፡ በኢየሱስ እያመናችሁም አሁንም ድረስ ራሳችሁን እንደ ሐጢያተኛ የምትቆጥሩ ከሆናችሁ በእርሱ በትክክል ታምናላችሁ ማለት ይቻላልን? እናንተ አማኝና ሐጢያተኛ ናችሁ ወይስ አማኝና ጻደቅ ሰው?  
ለራሳችሁ መምረጥ ትችላላችሁ፡፡ ወይ ሐጢያቶቻችሁ በሙሉ ይቅር መባላቸውን ልታምኑ ትችላላችሁ፤ አለበለዚያም በየቀኑ ለመተላለፎቻችሁ ንስሐ ልትገቡ ትችላላችሁ፡፡ ምርጫችሁ ወደ ሰማይ ወይም ወደ ሲዖል የምትሄዱ ለመሆናችሁ ይወስናል፡፡ እውነተኛውን ወንጌል የነገራችሁን ወንጌላዊ ልትሰሙት ይገባል፡፡  
በሐሰተኛ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች በእያንዳንዱ የማለዳ የጸሎት ስብሰባ፣ በእያንዳንዱ የረቡዕ አገልግሎት፣ በየአርቡ የሙሉ ሌሊት ጸሎት ገናም ለሐጢያቶቻቸው ይቅርታን ለማግኘት ይጸልያሉ፡፡  
‹‹ጌታ ሆይ ሐጢያትን ሰርቻለሁ፡፡ በዚህ ሳምንት ሐጢያትን አድርጌያለሁ›› ይላሉ፡፡ ከዚያም ከዓመታት በፊት የሰሩዋቸውን ሐጢያቶች በማስታወስ ለእነዚያም ይጸልያሉ፡፡ ይህ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም የመወለድን የተባረከ ወንጌል መጻረር ነው፡፡   
ሐጢያቶቻችን  በደም መከፈል አለባቸው፡፡ ዕብራውያን 9፡22 ‹‹ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም›› ይላል፡፡ ሐጢያት እንዳለባችሁ የምታስቡ ከሆነ እንደገና ስለ እናንተ እንዲደማላችሁ እየጠየቃችሁት ነውን? ምሉዕ በሆነው ቤዛነት የማያምኑ የኢየሱስን ቤዛነት ወደ ውሸት በመለወጣቸው ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ እንዲያውም ኢየሱስ ለአንዴና ለመጨረሻ እንዳላዳነንና ውሸታም እንደሆነ ያውጃሉ፡፡
በኢየሱስ ቤዛነትን ለማግኘት እናንተ በእውነተኛው የውሃና የመንፈስ ወንጌል ማመን አለባችሁ፡፡ በብዙ መቶዎች፣ ሺህዎችና ሚሊዮን ጸሎቶች ከሐጢያት ልትድኑ ትችላላችሁን? እውነተኛው ወንጌል ለአንዴና ለመጨረሻ ይቤዠናል፡፡ ጻድቃን ሁኑ፡፡ ወደ እግዚአብሄርም መንግሥት ግቡ፡፡ በዘመኑ ሁሉ የጽድቅን ሕይወት ኑሩ፡፡ 
♪በኢየሱስ አዲስ ሕይወትን እኖራለሁ፡፡ ያለፈው አልፎ አዲስ ፍጡር ሆኛለሁ፡፡ የባከነው ጊዜም አልፎዋል፡፡ ኦ! ኢየሱስ የእውነት ኑሮዬ ነው፡፡ በኢየሱስ አዲስ ሕይወትን እኖራለሁ፡፡ 
በኢየሱስ አዲስ ሕይወትን ትኖራላችሁ፡፡ እንደምትፈልጉት ውብ መስላችሁ ባትታዩም፣ በጣም አጭር ወይም ወፍራም ብትሆኑም ከውሃና ከመንፈስ ዳግም በመወለድ ወንጌል የተባረኩ የደስታ ኑሮ ይኖራሉ፡፡ አፍንጫችሁ ጥሩ ቅርጽ ባይኖረው ወይም አጭር ብትሆኑ ምን ፋይዳ አለው? ፍጹማን ስላልሆንን በኢየሱስ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም በመወለድ ድነናል፡፡ ነገር ግን ትዕቢተኞች ፍጻሜያቸው ሲዖል ይሆናል፡፡   
ጌታ ሆይ አመሰግንሃለሁ፡፡ ለጌታዬ ሁልጊዜም ምስጋናን አቀርባለሁ፡፡ በውሃና በመንፈስ ወንጌል በማመን ዳግም በመወለድ የምናምን ስለሆነ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት እንገባለን፡፡  
 

ሐሰት ወደ ሲዖል ይነዳናል፡፡  
 
በመጨረሻ የጽድቅን አክሊል የሚቀበለው ማነው? 
ሐሰትን ያሸነፈው ነው፡፡
 
ሐሰት ይቅርታን ለማግኘት በየቀኑ ንስሐ መግባት እንዳለብን ይነግረናል፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ግን ቀደም ብሎ ሙሉ በሙሉ ይቅርታ እንዳገኘንና ማድረግ የሚያስፈልገንም ይህንን ማመን ብቻ እንደሆነ ይነግረናል፡፡  
እውነቱ የቱ ነው? በየቀኑ ንስሐ መግባት አለብን? ወይስ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለማንጻት እጅግ ተስማሚ በሆነ መንገድ በተጠመቀ ጊዜ እንዳዳነን ማመን ትክክል ነው? እውነቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ሐጢያቶቻችንን መውሰዱና በዚህ ትክክለኛ መንገድ ደህንነት የሰጠን መሆኑ ነው፡፡   
በመንፈሳዊው ጦርነት ውስጥ ውሸትን ማሸነፍ ይኖርብናል፡፡ ብዙ ሰዎች ይህንን ውሸት ይከተላሉ፡፡ ‹‹በጴርጋሞን ወዳለው ቤተክርስቲያን እንዲህ ብለህ ጻፍ፡- በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያለው እንዲህ ይላል፤ የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፡፡ ስሜንም ትጠብቃለህ፡፡ ሰይጣንም በሚኖርበት በእናንተ ዘንድ የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም፡፡›› (ዮሐንስ ራዕይ 2፡12-13)
‹‹መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ፡፡ ድል ለነሳው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፡፡ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፡፡ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል፡፡›› (ዮሐንስ ራዕይ 2፡17)  
በርካታ ክፉ መናፍስቶች በሚኖሩበትና ሐሰትም እውነት ስለመሆኑ በሚያስመስልበት ቦታ ሰይጣን የብርሃን መልአክ መስሎ ይገለጣል፡፡ እግዚአብሄር ከውሃና ከመንፈስ የሆነውን የደህንነት እውነት ሰምቶ የተረዳን ነገር ግን በዚያ የማያምነን ማንኛውንም ሰው ሊያግዘው አይችልም፡፡ እንደዚህ ያለ ሰው በእርግጥም ፍጻሜው ሲዖል ይሆናል፡፡    
በኢየሱስ ደህንነት ያምን እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ እያንዳንዱ ሰው ለራሱ መወሰን ይኖርበታል፡፡ ማንም ከእግራችሁ ስር ተንበርክኮ ታምኑና ትድኑ ዘንድ የሚለምናችሁ አይኖርም፡፡  
ከሐጢያት ለመዳን የምትፈልጉ ከሆነ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እመኑ፡፡ በማዳን ፍቅሩና እኛን ባዳነበት ጸጋው ምስጋናን ተሞልታችሁ ከሆነ እመኑት፡፡ ወደ ሲዖል ለመግባት የተዘጋጃችሁ ሐጢያተኞች መሆናችሁን የምታውቁ ከሆነ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ ደም አምናችሁ ዳኑ፡፡ ያን ጊዜ ጻድቃን ትሆናላችሁ፡፡   
ሐጢያተኞች እንዳልሆናችሁ የምታስቡ ከሆነ በኢየሱስ በማመን ቤዛነት ማግኘት አያስፈልጋችሁም፡፡ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም የመወለድ ወንጌል ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ነጻ የሚወጡት ሐጢያተኞች ብቻ ናቸው፡፡ ኢየሱስ የሐጢያተኞች አዳኝና የችግረኞች አጽናኝ ነው፡፡ እርሱ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱ የፍቅር ባለቤት ነው፡፡   
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አምናችሁ ዳግም ትወለዱ ዘንድ ከልቤ እወተውታችኋለሁ፡፡ በዚህ እመኑ፡፡ ኢየሱስ የእናንተ አዳኝ፣ ወዳጅ፣ እረኛና አምላክ እንደሚሆን እርግጠኞች ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ ሐጢያተኞች በኢየሱስ ማመን አለባቸው፡፡ ፍጻሜያችሁ ሲዖል እንዲሆን ካልፈለጋችሁ ይህንን ልታምኑ ይገባል፡፡ እግዚአብሄር የደህንነትን ወንጌል እንድናምን አይለምነንም፡፡   
መንግሥተ ሰማይ መግባት ትፈልጋላችሁን? የምትፈልጉ ከሆነ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እመኑ፡፡ ኢየሱስ ‹‹እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ እመኑኝ›› ይላል፡፡ ሲዖል መጣል የሚፈልግ አለ? እንደዚህ ከሆነ በዚህ አትመኑ፡፡ ይህ ከሆነ እርሱ ለእናንተ በሲዖል ቦታ እንዳገኘላችሁ ይናገራል፡፡ 
እግዚአብሄር አይለምንም፡፡ ነጋዴ ደንበኞቹን አንዱን ከሌላው ሳይለይ የሚያባብለው ዕቃዎቹን ለመሸጥ ነው፡፡ እግዚአብሄር ግን መንግሥተ ሰማይን በነጻ የሚሰጠው ቤዛነትን ላገኙ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ጻድቅ ነው፡፡ 
ሰዎች የዓለም ፍጻሜ እንደቀረበ ይናገራሉ፡፡ አዎን እኔም የማስበው እንደዚያ ነው፡፡ በእውነተኛው ከውሃና ከመንፈስ ዳግም የመወለድ ወንጌል አለማመን ሞኝነት ነው፡፡ 
ከውሃና ከመንፈስ ዳግም በመወለድ የተባረከ ወንጌል እመኑ፡፡ መንግሥተ ሰማይም አብረን እንግባ፡፡ ኢየሱስ በሚኖርበት ቦታ ከእኔ ጋር መሄድ አትፈልጉምን? 
 
እናንተ ጻድቃን ናችሁ ወይስ ሐጢያተኞች? 
በልቡ ሐጢያት የሌለበት ጻድቅ ነን፡፡ 
 
ሮሜ 8፡1-2ን እናንብብ፡- ‹‹እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከሐጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና፡፡›› 
ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ሞቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደ፡፡ ለሐጢያቶቻቸው ፍርድን መቀበል የነበረባቸውን ሐጢያተኞች በሙሉ አዳነ፡፡ 
የእግዚአብሄር ደህንነት ሁለት ነገሮችን ይዞዋል፡፡ አንደኛው ሕጉ ሲሆን ሌላው ደግሞ ፍቅሩ ነው፡፡ ሕጉ ሐጢያተኞች መሆናችንን ያስተምረናል፡፡ በሕጉ መሰረት የሐጢያት ደመወዝ ሞት ነው፡፡ በሕጉ መዳን አንችልም፡፡ ሕጉ የእኛን ሐጢያተኛ ተፈጥሮና ዕጣ ፈንታችንን ያስተምረናል፡፡ እኛ ሐጢያተኞች መሆናችንን እንድናውቅ ይፈቅድልናል፡፡
ኢየሱስ የሐጢያትን ደመወዝ ለመክፈል ወደዚህ አለም ወረደ፤ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደ፤ እኛን ከፍርድ ለማዳንም በሕይወቱ ከፈለ፡፡ በእኛ ፋንታ የራሱን ሕይወት በመሰዋት ፍርድን ተቀበለ፡፡ ከሐጢያት ሁሉ ያዳነን የእግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ 
ወሸትን ማሸነፍ አለብን፡፡ እግዚአብሄር ውሸትን ለሚያሸንፍ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም የመወለድን በረከት ይሰጠዋል፡፡ 
እኛ በኢየሱስ በማመን ድነናል፡፡ ቃሎቹን በማመን ጽድቅን እናገኛለን፡፡ እውነትንም እናስተውላለን፡፡ 
በኢየሱስ በማመንም እንድናለን፡፡ የእርሱን ቃሎች በማመን ወደ ጽድቅና እውነትን ወደ መረዳት እንደርሳለን፡፡ በልቦቻችሁ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም በመወለድ እውነት እመኑ ትድኑማላችሁ፡፡