Search

คำสอน

ርዕስ 11፡ የመገናኛው ድንኳን

[11-26] የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ጌጠኛ ጉብጉቦች፡፡ ‹‹ዘጸዓት 25፡31-40››

የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ጌጠኛ ጉብጉቦች፡፡
‹‹ዘጸዓት 25፡31-40›› 
‹‹መቅረዝንም ከጥሩ ወርቅ አድርግ፤ መቅረዙ ከእግሩና ከአገዳው ጋር በተቀጠቀጠ ሥራ ይደረግ፡፡ ጽዋዎቹም፣ ጉብጉቦቹም፣ አበቦቹም፣ በአንድነት በእርሱ ይደረጉበት፡፡ በስተጎኑ ስድስት ቅርንጫፎች ይውጡለት፡፡ ሦስቱ የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን ሦስትም የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ ወገን ይውጡ፡፡ በአንደኛውም ቅርንጫፍ ጉብጉብና አበባ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፣ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ ጉብጉብና አበባ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች እንዲሁም ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አድርግ፡፡ በመቅረዙም ጉብጉቦቹንና አበቦቹን አራትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች አድርግ፡፡ ከመቅረዙም ለሚወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጉብጉብ፣ ከሁለትም ቅርነጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሰራ አንድ ጉብጉብ ደግሞ ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጉብጉብ ይሁን፡፡ ጉብጉቦቹና ቅርንጫፎቹ ሁሉ ከእርሱ ጋር አንድ ይሁኑ፤ ሁሉም አንድ ሆኖ ከተቀረጸ ከጥሩ ወርቅ ይደረግ፡፡ ሰባቱንም መብራቶች ሥራ፤ በፊቱ ያበሩ ዘንድ መብራቶቹን ያቀጣጥሉአቸዋል፡፡ መኮስተሪያዎችዋን፣ የኩስታሪ ማድረጊያዎችዋንም፣ ከጥሩ ወርቅ አድርግ፡፡ መቅረዙም ዕቃውም ሁሉ ከአንድ መክሊት ጥሩ ወርቅ ይሠሩ፡፡ በተራራ ላይ እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንድትሠራ ተጠንቀቅ፡፡›› 


ይህ ምንበብ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያለውን መቅረዝ ይገልጠል፡፡ ዛሬ የጌጠኛ ጉብጉቦቹን፣ የአበቦቹንና የመብራቶቹን መንፈሳዊ ትርጉም ላብራራ እወዳለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን በቅድሚያ ከአንድ መክሊት ወርቅ የመብራቱን አገዳ እንዲሠራ ነገረው፡፡ ስለዚህ በመጀመሪያ አገዳው ተሠራ፡፡ ከዚያም ከዚህ አገዳ ቅርንጫፎች ተቀጥቅጠው ተሠሩ፡፡ በመቅረዙ በእያንዳንዱ ወገን ሦስት ቅርንጫፎች ተደረጉ፡፡ በእያንዳንዱ ቅርንጫፍ ላይም የለውዝ አበባ የሚመስሉ ጽዋዎች ተደረጉ፡፡ ከዚያም ጌጠኛ ጉብጉቦችና አበባዎች ተደረጉ፡፡ በቅርንጫፎቹ ላይም ሰባት መብራቶች ተደረጉባቸው፡፡ ከዚያም ብርሃን ይሰጡ ዘንድ በእነዚህ መብራቶች ውስጥ ዘይት ተጨመረባቸው፡፡ በዚህ ሁኔታ መቅረዙ ለውስጠኛው ቅድስት ስፍራና ለዕቃዎቹ ሁሉ ብሩሀ የሆነ ብርሃን ሰጠ፡፡
የመንግሥተ ሰማይ ንጉሥ የሆነው ጌታችን ለእናንተና ለእኔ ሲል ራሱን ዝቅ ባደረገ ሰው ምሳሌ ሆኖ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ በዚህ ምድር ላይም ኢየሱስ በሰማያዊውና በቀዩ ማግ የተገለጡትን የደህንነት ሥራዎች አከናወነ፡፡ እነዚህ የደህንነት ሥራዎች የተፈጸሙት ወደዚህ ምድር በተወለደው፣ በ30 ዓመቱ በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀውና ከዚያም በመስቀል ላይ በተኮነነው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ኢየሱስ ‹‹እንዲህ›› በእጆች መጫን መልክ በመጠመቅ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፡፡ (ማቴዎስ 3፡15) ሰው የሆነው ኢየሱስ በጥምቀቱ የሰውን ዘር ሐጢያቶች ወሰደ፤ ተሰቀለ፤ ደሙንም አፈሰሰ፤ በዚህም በሰማያዊውና በቀዩ ማግ የተገለጡትን የደህንነት ተግባራት አከናወነ፡፡ የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን የተመሠረተችበት እውነት ይህ ነው፡፡
ጌታችን የቤተክርስቲያን ጌጠኛ ጉብጉብ ሆንዋል፡፡ እግዚአብሄር የሐጢያቶችን ስርየት ለተቀበልነው ለእናንተና ለእኔ የደህንነት መሠረት ሆነ፡፡ ስለዚህ እናንተና እኔ ጌታ በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ በተገለጡት የደህንነት ሥራዎች ከሐጢያቶቻችን ሁሉ እንዳዳነን በማመን የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን አባል ሆነናል፡፡ እኛ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት የእግዚአብሄርን ጸጋ ለብሰናል፡፡ ‹‹ቤተክርስቲያን›› የሚለው ቃል በግሪክ "έκκλησία" (ኤክሌዥያ) ማለት ሲሆን ትርጓሜውም ‹‹ከሐጢያተኛው ዓለም ተጠርተው የወጡ ስብስብ›› ማለት ነው፡፡
የዚህን ዓለም ሰዎች ከሐጢያት በማዳን ሐጢያትን እንዲያመልጡ ያስቻላቸው ሌላ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እርሱ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በመምጣት የሐጢያተኞችን ሁሉ ሐጢያቶች ያስወገደ ጌታ ነው፡፡ እኛ በጌታ ጥምቀትና ባፈሰሰው ደሙ በማመን ከሐጢያት ድነን ፈጽሞ ጻድቃን ሆነናል፡፡ ጌታ ጻድቃን ያደረገን እርሱ ወደዚህ ምድር መጥቶ በሰማያዊውና በሐምራዊው ማግ የተገለጡትን የደህንነት ሥራዎች በሙሉ እንደፈጸመ በማመናችን ነው፡፡ በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ የተገለጠው እምነት ይህ ነው፡፡
ኢየሱስ ወደዚህ ምድር መጥቶ በዮሐንስ በመጠመቅ (ማቴዎስ 3፡13-17) ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደ፡፡ በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ የተገለጠው እውነትና እምነት ይህ ነው፡፡ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ ከተጠመቀ በኋላ ለዓለም ሐጢያቶች በመስቀል ላይ ስለተኮነነ ሐጢያቶቻችንን ለአንዴና ለመጨረሻ ደምስሶዋል፡፡ በሌላ አነጋገር ሐጢያቶቻችንን ሁሉ የተሸከመው ኢየሱስ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ አድኖናል፡፡ ጌታ በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ በተገለጡት በእነዚህ የደህንነት ሥራዎች ከዓለም ሐጢያቶች ሁሉ አዳነን፡፡ እውነተኛውን ደህንነት ማወቅ ማለት በዚህ እውነት በትክክል ማመን ማለት ነው፡፡
ከሐጢያቶቻችን ሁሉ በእምነት ስላዳነን ከሐጢያት መዳን የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፡፡ ደህንነታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የታቀደው በተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ከዓለም ፍጥረት በፊት ነው፡፡ ይህች ፕላኔት ከመፈጠርዋ በፊት፣ የሰው ዘር የጋራ ቅድመ ወላጆች የሆኑት አዳምና ሔዋን ከመፈጠራቸው በፊት እግዚአብሄር አብ በኢየሱስ ክርስቶስና በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሐጢያተኞችን ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን አቀደ፡፡ ጊዜው ሲደርስም በጥምቀቱና ደሙን በማፍሰስ ይህንን ደህንነት ለመፈጸም ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ የሰውን ዘር የፈጠረው አምላካችን ቃል በገባላቸው መሠረት ለሰብዓዊ ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ስርየትን ፈጸመ፡፡ እነዚህ የእግዚአብሄር ተስፋዎች የተፈጸሙት ኢየሱስ በዮሐንስ በመጠመቁና ደሙን በማፍሰሱ ነው፡፡ እግዚአብሄር በዚህ ለሚያምኑት ሁሉ ከመላው ዓለም ሐጢያቶች የሚያድናቸወንና የሐጢያቶቻቸውን ስርየትና የዘላለም ሕይወት የሚቀበሉበትን የደህንነት ስጦታ ሰጥቶዋቸዋል፡፡ በዚህ እውነት የሚያምኑ ሰዎች የራሱ የእግዚአብሄር ልጆች ሆነው ፈጽመው ድነዋል፡፡ ይህ እውነት በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ የተገለጠው የደህንነት እውነት ነው፡፡
 


የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የመቅረዙ አገዳ ነው፡፡


ኢየሱስ ለሰው ዘር ሁሉ የደህንነት የማዕዘን ድንጋይ፣ አስፈላጊ የደህንነት የማዕዘን ድንጋይ ሆንዋል፡፡ ኢየሱስ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ደህንነትን አጠናቆ ለእኛ የደህንነት መሰረት ሆነልን፡፡ የእግዚአብሄር መቅረዝ የለውዝ አበቦች የሚመስሉ ጽዋዎች፣ ጌጠኛ ጉብጉቦችና አበቦች ነበሩበት፤ አገዳም ነበረበት፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የደህንነት አበባም ሆንዋል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የደህንነት እውነት አበባ ከሆነ ጌጠኛ ጉብጉቦቹ ምን ሊሆኑ ይችላሉ? እነርሱ በእርግጥም የእግዚአብሄር ባሮችና የሐጢያቶችን ስርየት የተቀበሉ ሰዎች ሁሉ ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር አበባው ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን አበቦቹን የሚደግፉት ጌጠኛ ጉብጉቦች ደግሞ እኛ ነን፡፡ 
ጌታችን ከሐጢያቶቻችንን ካዳነን በኋላ ሁላችንንም የወንጌል ጌጠኛ ጉብጉቦች አድርጎናል፡፡ ይህንን እውነት አውቃችሁ ታምኑበታላችሁን? መጋቢዎቻችን፣ ሽማግሌዎቻችን፣ ወንድሞችና እህቶች ሁሉ ጌጠኛ ጉብጉቦች ናቸው፡፡ የሐጢያቶቹን ስርየት የተቀበለ ማንኛውምም ሰው ጌጠኛ ጉበጉብ ነው፡፡ ጌታ በቅድሚያ የደህንነትን አገዳ በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ማግ ሠራ፡፡ ከዚያም በመጀመሪያ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አዳነንና የወንጌል አበቦች ያብቡ ዘንድ የሚደገፉዋቸውን ጌጠኛ ጉብጉቦች አደረገን፡፡ ሐጢያተኞች ከሐጢያቶቻቸው መዳን የሚችሉት ሁላችንም ጌጠኛ ጉብጉቦች ስንሆን ብቻ ነው፡፡ ብቸኛው ልዩነት መጠን ነው፡፡ አንዳንዶቹ ጌጠኛ ጉብጉቦች ትልቅ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ትንሽ ይሆኑ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሁላችንም የወንጌል ጌጠኛ ጉብጉቦች የመሆናችን እውነት አይለወጥም፡፡ 
ሰይጣን ሁልጊዜም እግዚአብሄርን ስለሚቃወም ሁላችን ከሐጢያቶቻችን ነጻ እንዳንወጣ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ከማመን ሊያግደን ይሻል፡፡ ነገር ግን አበቦች ማዕበል በሚያልፍበት ቆሻሻ ሜዳ ላይ እንደሚያብቡ ሁሉ እያንዳንዱም ሐጢያተኛ የደህንነት ወንጌል የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማድመጥ ከሐጢያቱ መዳን ይችላል፡፡ ጌታ የጠፉትን ነፍሳት ከሐጢያት ሊያድን ይፈልጋል፡፡ በሌላ አነጋገር እርሱ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እውነት በዚህ በመላው ዓለም ማሰራጨት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄርም ቤተክርስቲያን የምታከናውነው ይህንኑ ዓላማ ነው፡፡
አገልጋዮች በሚያገለግሉባቸው ቤተክርስቲያን ውስጥ ራሳቸውን ጌጠኛ ጉብጉቦች አድርገው በማመን ቤተክርስቲያኖቻቸውን የሚያገለግሉ ካልሆኑ እነዚህ ቤተክርስቲያኖች አንዳች የደህንነት ፍሬ ማፍራት አይችሉም፡፡ ማንኛውም አገልጋይ የሚፈልገው በጉባኤው መገልገል ብቻ ከሆነ እርሱ ያማረው ወንጌል ደጋፊ ከመሆን ይልቅ እንቅፋት ነው፡፡
ሰይጣን ቀድሞ የመጣበት ምክንያት ሕይወታችንን ለመስረቅና እኛን ለመግደል ነው፡፡ ጌታችን የመጣው ግን ለበጎቹ የተትረፈረፈ ሕይወት ለመስጠት ነው፡፡ (ዮሐንስ 10፡10) ያለውን ሁሌም ለእነርሱ በመስጠትም አድኖዋቸዋል፡፡ ለውሃውና ለመንፈሱ ወንጌል የሚጠቅም አንዳች ነገር ከተገኘ ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢመስልም ያንን ከማድረግ ማመንታት የለብንም፡፡ እንደዚህ ያለው አስተሳሰብ የወንጌል ጌጠኛ ጉብጉቦች ያደርገናል፡፡ መጋቢዎች ወንጌልን ለማገልገል ሲባል የጉልበት ሠራተኞች ቢሆኑ ተገቢ ነው፡፡ መጋቢዎቻችን በምታቃጥለው ጸሐይ ውስጥ እየሠሩ ያሉት ለዚህ ነው፡፡ በምታቃጥለው ጸሐይ ውስጥ ሆነው የጌጠኛዎቹን ጉብጉቦች ሚና በመፈጸማቸው አንድ ነፍስ እንኳን መዳን ቢችል ይህንን በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ይሠሩታል፡፡ አገልጋዮች የእግዚአብሄር ወንጌል አበባ እንዲያብብ ለማድረግ ማንኛውንም ነገር ለመሥራት ፈቃደኛ የሚያደርጋቸው እምነት ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ አንዲት የወንጌል አበባ እንድታብብ ምን ያህል ጥረትና መሥዋዕት እንደሚያስፈልግ መገንዘብ ያስፈልጋችኋል፡፡ እናንተና እኔ የሐጢያቶቻችንን ስርየት ማግኘት የቻልነው የእግዚአብሄርን ቃል ጠብቀው ለማቆየት ሲሉ ሰማዕት በሆኑት የቀድሞ የእምነት አባቶቻችን አማካይነት ነው፡፡
በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያሉት ሰባቱ መብራቶች የእግዚአብሄር ክቡር ዘይት ይፈስባቸው ነበር፡፡ እኛም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ባለን እምነታችን ይህንን ክቡር ዘይት ተቀብለን ልንደሰትበት ችለናል፡፡ በእግዚአብሄር ጸጋም የወንጌል ጌጠኛ ጉብጉቦች ሆነናል፡፡ ወንጌልን ስናገለግል ብዙ የሚከናወኑ ነገሮች እንዳሉ ወደ መረዳት እንመጣለን፡፡ አንዱ ተጠናቆ ወደ ሌላው ሲታለፍ መደረግ የሚያስፈልገው ነገር ማለቂያ የለውም፡፡ የወንጌል መጽሐፎቻችንን ማተም፣ አገልጋዮች ቃሉን በበቂ ሁኔታ ይሰብኩ ዘንድ መዋዕለ ንዋይ ማግኘት፣ ለመጸለይና ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን ለመምራት፣ ወንድሞችና እህቶችም ወንጌልን እንዲያገለግሉ ማድረግ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ወንጌልን የሚያገለግሉት የጌጠኛ ጉብጉቦችን ሚና ለመፈጸም ሲባል መከናወን አለባቸው፡፡ እግዚአብሄር የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አበባ ማበብ ይችል ዘንድ እኛን ጻድቃኖችን እንደ እነዚህ ጌጠኛ ጉብጉቦች እየተጠቀመብን የመሆኑን እውነታ ፈጽሞ እንደማትረሱት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡


አዳዲስ ምዕመናንን በሚገባ መንከባከብም እንደዚሁ የእግዚአብሄርን ሥራ መሥራት ነው፡፡ 

በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ እጅግ የሚወደዱትና እጅግም የሚፈሩት የሐጢያቶችን ስርየት በቅርቡ የተቀበሉ ወንድሞችና እህቶች ናቸው፡፡ በእነርሱ ፊት መጋቢዎች እንኳን ትሁት ሊሆኑና ባሉበት መንፈሳዊ አስተውሎታቸው ደረጃ ሊገናኙዋቸው ይገባል፡፡ ለምን? የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ቢቀበሉም የውሳኔ መለኪያቸው አሁንም ቢሆን በስጋቸው ላይ ወደ መመሥረቱ ያዘነበለ ነው፡፡ ስለዚህ ቀድሞ ያመኑ የእምነት ቀደምቶች የእነርሱን ዱካዎች በመከተል ላይ ያሉትን እነዚያን ወጣት ምዕመናን የሚያገለግሉ ጌጠኛ ጉብጉቦች መሆን አለባቸው፡፡ እነዚህ አዲስ ምዕመናን በእምነታቸው ሲያድጉ በእምነታቸው ገና ጨቅላ ሳሉ እንዴት እንክብካቤ እንደተደረገላቸው ወደ መረዳቱ እንዲመጡ አዳዲስ ምዕመናንን ማገልገል ይገባቸዋል፡፡ በግላቸው ለተደረገላቸው ደግነትም አመስጋኝ ይሆናሉ፡፡ በእምነታቸውም እነርሱም በፋንታቸው ወደ ቤተክርስቲያን ለሚመጡት አዳዲስ ቅዱሳኖች ይህንን ደግነት ይሰጣሉ፡፡
ሆኖም ከመጠን በላይ በደግነት ልትንከባከቡዋቸው አይገባችሁም፡፡ ለአንድ ሰው በስጋ ከመጠን በላይ ደግ መሆን የግድ የዚህን ግለሰብ ነፍስ ያሳድጋል ወይም ያበለጥጋል ማለት አይደለም፡፡ ሰዎችን ወደ መንፈሳዊ ጤናማነት መምራት ማለት በእምነት በእግዚአብሄር ፈቃድ መሠረት እንዲኖሩ መምራት ማለት ነው፡፡ በደፈናው በስጋ ብቻ ጥሩ የምንሆንላቸው ከሆነ ይህ እነርሱን ከመርዳት ይልቅ ሊያበላሻቸው ይችላል፡፡ አንዳንድ ወንድሞችና እህቶች ቤተክርስቲያንን ለቀው የሚወጡት ለምን እንደሆነ ታወቃላችሁን? ትተው የሚወጡት በእምነት ወደ መንፈሳዊ አቅጣጫ ስላልተመሩ ነው፡፡ መቅረዙ የተሠራ የተድቦለቦለውን ንጹህ ወርቅ በመቀጥቀጥ እንደሆነ ሁሉ መቅረዝና ጌጠኛ ጉብጉቦች የሚሆኑትም እንደዚሁ የስጋ አሳቦቻቸውንና ጽድቃቸውን መካድ አለባቸው፡፡ ልቦቻቸውን መቀጥቀጥና በእግዚአብሄር ፈቃድ መሠረት ማስገዛት አለባቸው፡፡ እንደሚገባው ለእግዚአብሄር ለመገዛት ራሳቸውን በመቀጥቀጥ የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ሠራተኞች መሆን አለባቸው፡፡
የማህበረሰብ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ሰዎችን እንዴት በተሻለ ሁኔታ ማገልገል እንዳለባቸው ያስባሉ፡፡ ትክክለኛው የድርጊት አቅጣጫ ምንድነው? ለለማኞች ገንዘብን መስጠት ወይስ ከጥገኝነት ለማላቀቅ እነርሱን መርዳት? ብዙውን ጊዜ ብዙ ሰዎች ገንዘብና ምግብ ይሰጡዋቸዋል፡፡ ነገር ግን ስለ ማህበራዊ ሥራዎች አንዳንድ ዕውቀት ያላቸው ሰዎች ፈጽሞ ገንዘብ አይሰጡም፡፡ በምትኩ ራሳቸውን ከጥገኝነት አላቀው ሕይወታቸውን መኖር ይችሉ ዘንድ በችግረኞች ውስጥ መነሳሳትንና ራስን መቻልን የሚተክል ዕርዳታ ይሰጡዋቸዋል፡፡ በትክክል የሚረዳቸው ይህ ነው፡፡ ስለዚህ ሌሎችን መርዳትም እንደዚሁ አንዳንድ ውስብስብ የሆኑ ቴክኒካዊ ክህሎቶችን ይጠይቃል፡፡
የወንጌል ስብከት አገልግሎት የሚባለውም ይህ ነገር እንደዚሁ የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፡፡ ምክንያቱም ስጋቸውና መንፈሳቸው ተስማምቶ ያድግ ዘንድ ነፍሳቶችን በእግዚአብሄር ቃል የሚያጠጣና እነርሱን የሚያገለግል ሰው ያስፈልገዋልና፡፡ በሌላ አነጋገር አገልጋዮች ነፍሳቶችን መምራትና ወደ ጌታ ማምጣት አለባቸው፡፡ በእምነት ሕይወታቸውም እንዲያቃናላቸው በስጋ ጉዳዮችም ውስጥ እንደዚሁ ሊያግዙዋቸው ይገባል፡፡ አገልጋዮች ሁልጊዜም ንቁዎች መሆን አለባቸው፡፡ ዳግመኛ የተወለደው የእምነት ሕይወታችን ዓላማው በየቀኑ በተለያዩ መስኮችና አጋጣሚዎች ውስጥ የጌጠኛዎቹን ጉብጉቦች ሚና መፈጸም ነው፡፡ የእኛ ግዴታ ወደ እግዚአብሄር ከመሄዳችን በፊት በሕይወት ዘመናችን ሁሉ የወንጌል ጌጠኛ ጉብጉቦች ሆነን መኖር ነው፡፡
እግዚአብሄር እኛን ካዳነን በኋላ ጌጠኛ ጉብጉቦች አድርጎ የወንጌልን አበባ ወደ ሙሉ ማበብ እንድናደርስ ማገልገል እንችል ዘንድ ተገቢ የሆኑ ሐላፊነቶችን በአደራ ሰጥቶናል፡፡ ዳግመኛ ባልተወለዱ የዚህ ዓለም ሰዎች ማን አለብኝ ባዮች፣ አስመሳዮች፣ ዕብሪተኞችና ሁልጊዜም በሌሎች ምዕመናን መገልገል የሚፈልጉ ናቸው፡ ነገር ግን ዳግመኛ በተወለደችው ቤተክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሄር አገልጋዮች አድርጎ የሾማቸው ባሮች የእርሱን ፈቃድ በሚገባ የሚያውቁና ጌጠኛ የወንጌል ጉብጉቦች እንደመሆናቸው የተመደበላቸውን በታማኝነት የሚያከናውኑ ናቸው፡፡ አገልጋዮች የእነዚህን ጌጠኛ ጉብጉቦች ሚና መጫወት የሚገባቸው መሆኑ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችንን እንዲህ አለ፡- ‹‹ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 20፡35) ይህ መላ ምታዊ እሳቤ ሳይሆን የእምነትና የትክክለኛ ሕይወት መርህ ነው፡፡ በእርግጥም የሚሰጡ ከሚቀበሉ ይልቅ የተባረኩ ናቸው፡፡ በዚህ ጉዳይ ተሞክሮ አላችሁን?
አንድ ታሪክ ልንገራችሁ፡፡ በዕድሜያቸው መገባደጃ ላይ ልጅ ያገኙ ጥንዶች ይህ ልጅ ተፈቃሪ ሆኖ እንዲያድግ ጸለዩ፡፡ እንደጸለዩትም ልጁ በእርግጥም ሁልጊዜ ተፈቃሪ እንደሆነ አደገ፡፡ ነገር ግን ጊዜ እየነጎደ በሄደ ቁጥር ተፈቃሪ እንደሆነ ያሰቡት ልጃቸው ከራሱ በስተቀር ለሌላ የማያስብ ራስ ወዳድ ሆኖ እንዳደገ ተገነዘቡ፡፡ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ያደረጉት ነገር ልጁን ፈጽሞ አልጠቀመውም፡፡ በየጊዜው መቀበልን ብቻ ስለተለማመደ የሚያውቀው መቀበልን ብቻ እንጂ መስጠትን አይደለም፡፡ ይህም በስስትና በራስ ወዳድነት የተሞላ ልጅ አደረገው፡፡ እነዚያ በዕድሜ የገፉ ባለትዳሮች ልጃቸውን ሌሎችን መውደድ የሚያውቅ ሰው ወደ መሆን እንዲለወጥ እንደገና ጸለዩ፡፡ 
መስጠት ከመቀበል ይልቅ ይበልጥ ያማረ ነው፡፡ ጌታን ማገልገል ምን ያህል አስደሳች ነው? ምን ያህል የሚያረካ ነው? ወንጌልን በእምነት በማገለግልበት ጊዜ ሁሉ አንድ ነፍስ የሐጢያቶችን ስርየት እንደሚቀበል ሳስብ እደሰታለሁ፤ እረካለሁም፡፡ ጻደቃን ምዕመናን ወንጌልን ለብዙ ነፍሳቶች መስበክ ይወዳሉ፡፡ በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ የወንጌል ጌጠኛ ጉብጉቦች ሚና በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እናንተና እኔ እግዚአብሄር ጌጠኛ ጉብጉቦች አድርጎ በየትኞቹ ቦታዎች እንዳስቀመጠን መገንዘብ አለብን፡፡ በእነዚህ ጌጠኛ ጉብጉቦች ስፍራዎች ላይ በመሆንም ሚናዎቻችንን በእምነት መፈጸም አለብን፡፡ ወንጌልን በስጋ ችሎታዎቻችንና ኩራቶቻችን ሳይሆን በእግዚአብሄር ላይ ባለን እምነት ስናገለግል የደህንነት አበቦች ሙሉ በሙሉ እንዲያብቡ ያደርጋል፡፡ የወንጌል አበቦች የሚያብቡት የወንጌል ጌጠኛ ጉብጉቦች ስንሆን ነው፡፡ ብዙዎች የሚባረኩትም በእነዚህ አበቦች አማካይነት ነው፡፡ 
 


ቤተክርስቲያን ይህንን ዓለም በደህንነት ብርሃን የምታበራ መቅረዝ ናት፡፡ 


ጻድቃን አብረው በመሰባሰብ የወንጌል መቅረዝ ይሆኑና ይህንን ዓለም ያበራሉ፡፡ ጻድቃን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ብርሃን ያበራሉ፡፡ ሕይወትም ይህንን ጨለማ ዓለም ብሩህ በሆነው የእውነት ብርሃን የሚያበራ መቅረዝ ነው፡፡ ኑሮዋችን ይህ ነው፡፡ የእምነት አበቦች በዚህ ዓለም ላይ በሚገባ የሚያብቡት የሐጢያቶችን ስርየት የተቀበሉት ጻድቃን የወንጌል ጌጠኛ ጉብጉቦች ሲሆኑ ነው፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ለመላው ዓለም የሚሰበከው ይህ ሲሆን ነው፡፡ ከእነዚህ ጌጠኛ ጉብጉቦች ውጪ አበቦችም መብራትም ሊኖር አይችልም፡፡ የመቅረዙ አገዳ የለውዝ አበቦች የሚመስሉ ጽዋዎች ያሉት ሲሆን እያንዳንዱም ጽዋ ጌጠኛ ጉበጉብና አበቦች ነበሩበት፡፡ የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን በየቦታው ብቅ ማለትና ብዙ ነፍሳቶችም ከሐጢያቶቻቸው መዳን የሚችሉት እንዲህ ያለን ጌጠኛ ጉብጉቦች ስንሆንና ለእያንዳንዳችን የተሰጠንን ሚና ስንፈጽም ነው፡፡ መቅረዙን ስንመለከት በአንዱ ጌጠኛ ጉብጉብ ላይ ሌላ ጉብጉብ እንዳለ እንመለከታለን፡፡ ከዚህ ጉብጉብ በላይም እንደገና በአገዳው አጠገብ ሌላ ጉብጉብ አለ፡፡ ልክ እንደዚሁ ወንጌልን በማገልገላችሁ የወንጌል አበቦች አሁንም ድረስ እያበቡ ነው፡፡ ወንጌል በዚህ ዓለም በሙሉ ይሰበካል፡፡ እነዚህ ጌጠኛ ጉብጉቦች እናንተና እኔ ነን፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሰምተን እስከዚህ ቀን ድረስ ይህንን ወንጌል በመላው ዓለም በማሰራጨታችን ጌጠኛ ጉብጉቦች ሆነን እጅግ ብዙ ሥራዎችን ሠርተናል፡፡ የሐጢያቶቻችሁን ስርየት መቀበልና ይህንንም ለሌሎች ማሰራጨት የምትችሉት በዚህ መንገድ ነው፡፡
እነዚህን ጌጠኛ ጉብጉቦች በመሆን ሚናዎቻችንን ለመፈጸም የተለያዩ ሥራዎችን ሠርተናል፡፡ ለምሳሌ ደቀ መዛሙርትን ለማሰልጠንና ለመንፈሳዊ ዕፎይታ እንዲያገለግል ብለን ይህንን ቻፕል የሠራነው ከሁለት ዓመታት በፊት ነው፡፡ ይህንን ቅልብጭ ያለ ሕንጻ ለመገንባት አንድ ወር ፈጅቶብናል፡፡ በእምነት ስንገነባ ‹‹ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መንፈሳዊ ዕፎይታን ለማግኘት ወደዚህ ስፍራ ይመጣሉ፡፡ ብዙ የጠፉ ነፍሳቶችም ወደ ወንጌል ትምህርት ክፍሎቻችን መጥተው ቃሉን ይሰማሉ፡፡ የሐጢያቶችንም ይቅርታ ያገኛሉ›› ብለን አሰብን፡፡ ይህንን ሕንጻ ስንገነባ ብዙ ችግሮች ቢገጥሙንም ሁልጊዜም ይህንን አሳብ በአእምሮዋችን በመያዝ እነዚህን ችግሮች ጥሰን በማለፍ በተስፋ በታማኝነት እየሠራን ነው፡፡ ይህ የደቀ መዛሙርት ማሰልጠኛ ጣቢያ የተገነባውና እኛም በዚህ ሞቅ ባለና አመቺ በሆነ ስፍራ ውስጥ ማምለክ የቻልነው በዚህ መንገድ ነው፡፡ ይህ ተግባራዊ የሆነው የእያንዳንዱን ጌጠኛ ጉብጉብ ሚና በፈጸሙት ሰዎችም ጭምር ነው፡፡ በዚህ ቀዝቃዛ የአየር ጠባይ ውስጥ ሞቅ ብሎን እያመለክን ያለነው እናንተና እኔ ጌጠኛ ጉብጉቦች ስለሆንን ነው፡፡ ጌጠኛ ጉብጉብ ባይኖር ኖሮ እነዚህ ቀላል ኩነቶች በጭራሽ ተግባራዊ አይሆኑም ነበር፡፡ ይህ ቻፕል ከመገንባቱ በፊት ይህ ስፍራ የፈራረሰ ምድረ በዳ ነበር፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ለመስማት እንደዚህ ባለ የማይስብ ስፍራ ላይ የምንሰበሰብ ቢሆን ኖሮ የመምጣት ፍላጎት ይኖራችሁ ነበር? ለአምልኮ አገልግሎት በጣም ስለሚቀዘቅዝ ምናልባትም ተመልሳችሁ ወደ ቤታችሁ ትሄዱ ነበር፡፡
የወንጌል አበባ እስከዚህ ቀን ድረስ ማበብ እንዲችል ብቻ ሳይሆን ወደፊትም ይህንኑ በማድረግ እንድንቀጥል የሆነው እነዚህ ጌጠኛ ጉብጉቦች በስፍራቸው ስላሉ ነው፡፡ ‹‹በክሪሳንዝመም አጠገብ›› የሚል ርዕስ ያለው አንድ የታወቀ ሥነ ግጥም አለ፡፡ እንዲህ ይላል፡- 
‹‹አንድ ክሪሳንዝመም እንዲያብብ
የምሽት አበባ ከጸደይ ጀምራ እንደዚያ ማልቀስ አለባት፡፡
አንድ ክሪሳንዝመም እንዲያብብ
ነጎድጓዱ ጸጥ ባሉት ደመናት ላይ ማንጎዳጎድ አለበት…፡፡›› 
በእርግጥም ብዙዎቹ የእግዚአብሄር ባሮችና ብዙ ቅዱሳኖች ጌጠኛ ጉብጉቦች በወንጌል ዛፍ ላይ ተንጠልጥለዋል፡፡ የውሃና የመንፈስ ወንጌል ያብብ ዘንድ የእነዚህን ጌጠኛ ጉብጉቦች ሚና የሚፈጽሙ ሠራተኞች በየቀኑ ለፍተዋል፡፡ ይህንን የጌጠኛ ጉብጉቦችን ሚና በሚገባ መፈጸም እንድንችል ጌታ ከእነዚህ ጌጠኛ ጉብጉቦች በታች የለውዝ አበባ የሚመስሉ ተጨማሪ ጽዋዎችን አድርጓል፡፡ እግዚአብሄር በራሱ ጊዜ ለሰባቱ መብራቶች ዘይትን በመስጠት ጸጋውን ለግሶናል፡፡ ጌታችን በራሳችን ብርታት አንዳች ነገር ማድረግ እንደማንችል ስለሚያውቅ ወንጌልን ለማገልገል የጌጠኛዎቹን ጉብጉቦች ሚና መፈጸም እንችል ዘንድ በቤተክርስቲያን አማካይነት ጸጋውን አለበሰን፡፡ ስለዚህ እነዚህን ጌጠኛ ጉበጉቦች መሆን ማለት ወንጌልን በራሳችን ብርታት ብቻ ማሰራጨት እንችላለን ማለት እንዳይደለ መረዳት አለብን፡፡ በፋንታው ሁላችንም እነዚህን ጌጠኛ ጉብጉቦች ለመሆን ክብር ያገኘነው በእግዚአብሄር ጸጋ ብቻ ነው፡፡
የሐጢያት ስርየትን አሁን የተቀበሉና ከቅርብ ጊዜ በፊት የተቀበሉ ሁለቱም ወንጌልን ለማገልገል ተመሳሳይ ጌጠኛ ጉብጉቦች ናቸው፡፡ የተለያዩ መንፈሳዊ ደረጃዎች ያሉዋቸው ሆነው ሳሉ ሁሉም ተመሳሳይ የሆኑበት ምክንያት ሁሉም ጌጠኛ ጉብጉቦች ለመሆን ስለተጠሩ ነወ፡፡ እያንዳንዳችን ያለ ምንም አድልዎ ጌጠኛ ጉብጉብ ነን፡፡ ሌሎች ሥራዎችን ለመሥራት ጣቶቻችንን እንኳን ሳናነሳ ቃሉን በመንፈሳዊ መልኩ መስበክ ብቻ ትክክለኛ መንፈሳዊ ሕይወት አይደለም፡፡ ከልባቸው መንፈሳዊ የሆኑ ሰዎች ወንጌልን የሚጠቅም እስከሆነ ድረስ ማንኛውንም ነገር ያደርጋሉ፡፡ ‹‹የቤተክርስቲያኔ አቋም ይህ ነው፡፡ ስለዚህ የምሠራው እነዚህን ነገሮች ብቻ ነው፡፡ አንተ የሐጢያቶችን ስርየት የተቀበልከው አሁን ስለሆነ እኔ የራሴን ስሠራ አንተ ደግሞ ሌሎች ነገሮችን ልትሠራ አይገባህምን?›› ይህ ትክክል አይደለም፡፡ ወንጌልን ወደ ማገልገል ስንመጣ ማንም ከሌላው ሰው አይበልጥም አያንስምም፡፡ ሁላችንም ወንጌል እንዲያብብና እንዲለመልም መተባበርና ማዳበሪያ መሆን አለብን፡፡
 


ዳግመኛ የተወለዱ ቅዱሳኖች ስጋን የሚከተሉት እንዴት ነው? 


‹‹አሁን ሐጢያቶቼ በመወገዳቸውና ሐጢያት አልባ በመሆኔ በጣም ተደስቻለሁ፡፡ ሐብታም ብሆን ደግሞ በጣም እደሰት ነበር፡፡ በመጨረሻ ባለጠጋ ሆኜ ብኖር በጣም ግሩም አይደለምን?›› መንፈሳዊ ችግሮቹ እንዲፈቱለት በስጋ እንዲሳካለት የሚፈልግ አንዳች ሰው አለ? እኔ ጌታን ለመጀመሪያ ጊዜ ሳገኝ ያዳነኝ ለወንጌል ፍጹም የሆንሁ ጌጠኛ ጉብጉብ እሆን ዘንድ መሆኑን ስለማላውቅ ይህንን ሚና የምፈጽመው በንግድ ዓለም በመሰማራትና ገንዘብ በማግኘት ነው በማለት አሰብሁ፡፡ በየቀኑ ወደ ቤተክርስቲያን እሄዳለሁ፤ የሰንበት ትምህርት አስተምራለሁ፤ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለልጆች አሰራጫለሁ፤ አነስተኛ ንግድ አካሂዳለሁ፤ በቀን ውስጥ ለጥቂት ሰዓታት እሠራለሁ፤ በየቀኑ የማገኘውን ገቢም ለቤተክርስቲያን እሰጣለሁ፤ በዚህ መንገድ በቁሳ ቁስ በማገልገልም ቤተክርስቲያን እንዲሠራ አግዛለሁ ብዬ አሰብሁ፡፡ ያሰብኋቸው አሳቦች ምንም ይሁኑ ጌጠኛ ጉብጉብ ሆኜ መፈጸም የሚገባኝ ሚና ምን እንደሆነ ጌታን ስጠይቀው ይህንን ሚና ገንዘብ በማከማቸት ልፈጽመው አልፈለገም፡፡
በወቅቱ አሳቦቼ የተሳሳቱ ነበሩ፡፡ ጌታ ይህንን እንዳደርግ አልፈቀደም፡፡ ስለዚህ አሁን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለሚያሰራጨው አገልግሎቴ ራሴን ቀድሼ በመስጠት ትክክለኛ ጌጠኛ ጉብጉብ በመሆን ሚናዬን እየፈጸምሁ ነው፡፡ ሁላችንም እግዚአብሄር የሚደሰትበትን ማንኛውንም ነገር ማድረግ አለብን፡፡ ተራራን እንድንንድ ከነገረን ልንንደው ይገባናል፡፡ የተሰጠን ማንኛውም ሥራ ፈጽሞ የማይቻልና ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ቢመስል እንኳን እግዚአብሄር በእምነት እንድናደርገው ከነገረንና በመንፈሳዊ ረገድ ጠቃሚ ከሆነ በእርግጥ እንደሚሳካ ማመን አለብን፡፡ ተራራውን በዶማ በምንቆፍርበት ጊዜ ጅማሬያችን ደካማ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በጊዜው ተራራውን በድማሚት እናፈነዳውና ፍርስራሹን በቡልደዘር እንጠርገዋለን፡፡ ያን ጊዜ ተራራው ይጠፋል፡፡ በሌላ አነጋገር የምንከተለው የእግዚአብሄርን ፈቃድ እንጂ ሰው ሰራሽ አስተሳሰቦቻችንን ስላልሆነ ሁልጊዜም ለእግዚአብሄር ወንጌል የጌጠኛውን ጉብጉቦች ሚና በእምነት እንፈጽማለን፡፡
ጌታ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያስቀመጠን ለወንጌል ስርጭት ጌጠኛ ጉብጉቦች እንድንሆን ነው፡፡ ብቸኛው ልዩነት ጌጠኛ ጉብጉቦች ሆነን የተቀመጥንበት ስፍራ ነው፡፡ የወንጌልን ስርጭት በሚመለከት ከሌላው የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ጠቀሜታ ያለው ስፍራ በጭራሽ የለም፡፡ ቅደም ተከተሉን ብንመረምር ጌታ ኢየሱስ እንዳለው ፊተኛው ኋለኛ ይሆናል፡፡ ‹‹ሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን፡፡›› (ማርቆስ 9፡35) ጌታ የጌጠኛውን ጉብጉብ ሚና እንድንፈጽም ሲጠራን ራሳችንን በማስቀደም እንዳንኩራራ መሆኑ እውነት አይደለምን? የጌጠኛውን ጉብጉብ ሚና በሚገባ ስንፈጽም ድንቅ የሆኑት የጌታችን ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡ ምክንያቱም በመቅረዙ ላይ ያሉት ሰባቱ መብራቶች የሚያበሩት ብርሃን ቅድስቱን ክፍል ወለል አድርጎ ያበራዋልና፡፡
በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹መኮስተሪያዎችዋን፣ የኩስታሪ ማድረጊያዎችዋንም፣ ከጥሩ ወርቅ አድርግ፡፡ መቅረዙም ዕቃውም ሁሉ ከአንድ መክሊት ጥሩ ወርቅ ይሠሩ፡፡ በተራራ ላይ እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንድትሠራ ተጠንቀቅ፡፡›› (ዘጸዓት 25፡38-40) ከመቅረዙ ዕቃዎች መካከል መኮስተሪያዎቹ ይገኛሉ፡፡ ዘይት ይጨመርና በመቅረዙ ጫፍ ላይ ባሉት መብራቶች ላይ ጧፎች ይደረጋሉ፡፡ ጧፎቹ ሲነዱ ብልጭታዎች ስለሚበኑ መኮስተሪያዎቹ እነዚህን ብልጭታዎች ለማንሳት ያገለግሉ ነበር፡፡ እነዚህ መኮስተሪያዎችም የተሠሩት ከወርቅ ነበር፡፡ ካህናቶች የነደዱትን ጧፎች በእነዚህ መኮስተሪያዎች ይኮሰትሩዋቸውና በሳህኖች ላይ ያስቀምጡዋቸዋል፡፡ እነዚህ ዕቃዎች ብዙውን ጊዜ የሚያገለግሉት በቅድስቱ ስፍራ ውስጥ ነበር፡፡
የሐጢያቶቻችንን ስርየት ከተቀበልን በኋላ የጌጠኛውን ጉብጉብ ሚና ስንፈጽም ራሳችንን በአንድ ሥራ ባተሌ አድርገን በማጥመዳችን የተነሳ ልቦቻችን የሚደነድኑበት ወቅት አለ፡፡ ስለዚህ በሐላፊነት የተሰጡንን ሥራዎች በተለምዶ ወይም ያለ ሙሉ ልብ የምንሠራበት ጊዜ አለ፡፡ በዚህ ወቅት የእግዚአብሄር ባሮች የመቅረዙን ጧፎች መቀየር ያስፈልጋቸዋል፡፡ የነደዱት ጧፎች እንደሚታደሱ ሁሉ የእግዚአብሄር ባሮችም የተሰጡንን ሐላፊነቶች በመቀያየር ልቦቻችንን ያድሱዋቸዋል፡፡ ጌታችን ‹‹አሮጌው ነገር አልፎዋል፤ እነሆም ሁሉም አዲስ ሆንዋል›› (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17) ተብሎ እንደተጻፈ ወንጌልን በታደሱት ልቦቻችን ማገልገላችንን እንቀጥል ዘንድ የልቦቻችንን አመድ ያስወግዳል፡፡ በዚህ አማካይነት ሠራተኞች ዳግመኛ አዲስ በሆኑት ልቦቻቸው ወንጌልን ያገለግላሉ፡፡
በቅድስቱ ስፍራ ውስጥ ያለው ንጹህ ወርቅ ብቻ እንደሆነ ታስታውሳላችሁን? በእምነት ታማኝ ጌጠኛ ጉብጉብ ለመሆን ያለ መታከት አዳዲስ የጌታ ሥራዎችን መሻት አለባችሁ፡፡ ሁልጊዜም በእምነት መኖር የምንችለው ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ዛሬን በእምነት መኖር ይገባናል፡፡ ነገንም እንደዚሁ በእምነት ልንኖር ይገባናል፡፡ በየቀኑ የጌጠኛውን ጉብጉብ አዳዲስ ሚናዎች በእምነት እንፈጽማለን፡፡ እኛ የእግዚአብሄር ወንጌል ሠራተኞች በመኮስተሪያዎቹ አመዱን ሁሉ ከጧፎቹ ማስወገድ፣ መብራቶቹን ማስተካከል፣ ብሩህ ሆነው እንዲበሩና ብርሃናቸውም ፈጽሞ እንዳይጠፋ ማድረግ አለብን፡፡ 
የቅድስቱ ስፍራ ውስጠኛው ክፍል የከበረ ነው፡፡ ጌታ የሐጢያቶችን ስርየት ወንጌል የሚያሰራጭ መቅረዝ ይሆኑ ዘንድ ጻድቃኖችን ጠርቶ በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰብስቦዋቸዋል፡፡ በቤተክርስቲያኑ ውስጥም እግዚአብሄር መሪዎችን አስቀምጦዋል፡፡ ወንጌልን ለማገልገል የሚያስችላቸውንም ሥጦታዎቹን ለጻድቃኖቹ ሁሉ ሰጥቷል፡፡ እያንዳንዳችን በተመደብንበት ስፍራ የወንጌል አበቦች እንዲያብቡ የሚያደርገውን ጌጠኛ ጉብጉብ በመሆን ጌታን እናገለግለው ዘንድ ጠርቶናል፡፡ በዚህም እግዚአብሄር ወንጌልን በመላው ዓለም ለሚገኙ ሐጢያተኞች በሙሉ እንድናሰራጭ ፈቅዶልናል፡፡ ይህች የተለየች ‹‹ኤክሌዥያ›› የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ነች፡፡ በሌላ አነጋገር እኛ ተጠርተው የወጡና የዳኑ በአንድ ላይ የተሰባሰቡባት የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ሕዝብ ነን፡፡ አምላካችን ከሐጢያቶቻችንና ከበደሎቻችን ሁሉ ነጻ አውጥቶ ከሐጢያት አድኖናል፡፡ እግዚአብሄር በጌታችን ማዳን አማካይነት በኢየሰስ እንድናምን በማድረግ አድኖናል፡፡ አብረን በመስማማትም ወንጌልን እናገለግል ዘንድ ይህችን ቤተክርስቲያን መሥርቷል፡፡ ቅዱሳኖችን ያሰባሰበው ይህ እውነት ነው፡፡

 
የቤተክርስቲያን መኖር ምክንያቱ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ብርሃን ማብራት ነው፡፡ 


አንድ መክሊት ድቡልቡል ወርቅ በመቀጥቀጥ የተሠራው መቅረዝ ያስፈለገው የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ተባብራ የወንጌል አበቦች እንዲያብቡ ለማድረግ ነው፡፡ ይህ መቅረዝ የእግዚአብሄርን ቤተክርስቲያን ያመለክታል፡፡ ዓላማውም ጨለማውን ሁሉ ማብራት ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ሕያው የሆነችበት ዋናው ዓላማ ይህ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ዳግመኛ እንድንወለድ በማገልገል ቀዳሚዋ ጌጠኛ ጉብጉብ ሆናለች፡፡ አሁን ተራው የእኛ ነው፡፡ እናንተና እኔ እንደዚሁም የሐጢያቶችን ስርየት የተቀበልን ሁላችን እነዚህን ጌጠኛ ጉብጉቦች መሆን አለብን፡፡ የወንጌል አበቦች በሚገባ ያብቡ ዘንድም ጌጠኛ ጉብጉቦችና ማዳበሪያዎች ሆነን ሐላፊነቶቻችንን ተግባራዊ ማድረግ ይገባናል፡፡ ጻድቃን የሆንን ሁላችንና የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን የወንጌልን ብርሃን በመላው ዓለም የሚያሰራጨውን መቅረዝ ሚና መፈጸምና ጌታን ማገልገል አለብን፡፡
እኛ አዲስ የቤተክርስቲያን ድርጅት ለመመሥረት እየሞከርን አይደለም፡፡ የቤተክርስቲያን ድርጅታችንን ለመግለጥ የሚያስፈልገን ከሆነ የኢየሱስ ቤተክርስቲያን ነን፡፡ እኛ ጌታን ለማገልገል የተጠራን ጻድቃን ነን፡፡ የመቅረዙ ጌጠኛ ጉብጉቦች ስንሆንና ጌታን ስናገለግል እርሱም ጌጠኛ ጉብጉቦች በመሆናችን የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሁሉ እንደሚሰጠን ግንዛቤ ይኖረናል፡፡ ፍላጎቶቻችንን ለማሟላት አንዳች የተለየ ነገር ባንሞክርም እግዚአብሄር ራሱ ፍላጎቶቻችንን ሁሉ አትረፍርፎ ይሞላልናል፡፡ ጌታ እንዳለው ሁሉም ነገር በጊዜው ይሟላል፡፡ ‹‹አስቀድማችሁ የእግዚአብሄርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፤ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል፡፡›› (ማቴዎስ 6፡33) ጌታ ወንጌልን ለሚያገለግሉት ጻድቃን የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ይጨምርላቸዋል፡፡ የጌጠኛውን ጉብጉቦች ሚና የሚፈጽሙ ሠራተኞች ችግር ሲገጥማቸው ጌታ ‹‹እኔ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ደስ ይበላችሁ!›› በማለት ብርታትን ይሰጣቸዋል፡፡ ጌጠኛ ጉብጉቦቹ እምነት ከሌላቸው ‹‹ብርቱ እምነት ይኑራችሁ! ሐይልን በምሰጣችሁ በእኔ ሁሉን ትችላላችሁ›› በማለት እምነትን ይሰጣቸዋል፡፡ እግዚአብሄር የጽድቅ ሥራዎቹን ለመሥራት ጌጠኛ ጉብጉቦቹ አድርጎ ሊጠቀምብን ጌጠኛ ጉብጉቦች የሆንነውን እኛን ጻድቃኖች ባርኮናል፡፡
እኛ ጻድቃኖች ምንም ነገር ብናደርግ ወንጌል እንዲያብብ ጌጠኛ ጉብጉቦች ሆነን ማገልገል ይገባናል፡፡ ተማሪዎቻችንም እንደዚሁ የወንጌል ጌጠኛ ጉብጉቦች በመሆን የትምህርት ቤት ሕይወታቸውን በታማኝነት መኖር አለባቸው፡፡ በሥራ ገበታዎቻቸው ላይ ለእንጀራቸው የሚሠሩ ምዕመናኖቻችንም የወንጌል ጌጠኛ ጉብጉቦች ሆነው ይህንኑ ማድረግ አለባቸው፡፡ የምናደርገው ምንም ነገር ይሁን ሁላችንም የጌታ ወንጌል ጌጠኛ ጉብጉቦች ለመሆን ልናደርገው ይገባናል፡፡ እኛ ጻድቃኖች የወንጌልን ጌጠኛ ጉብጉቦች ሚና ለመፈጸም ስንል መኖር አለብን፡፡ የእምነት ሕይወታችንን በትክክል መኖር የሚገባን እንደዚህ ነው፡፡ የወንጌል አበቦች ያብቡ ዘንድ ጌጠኛ ጉብጉቦች በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡
እኛ ራሳችን አበቦች እንዳልሆንን ማስታወስ ያስፈልጋችኋል፡፡ የወንጌል አበባ ኢየሱስ ነው፡፡ እውነተኛው ብርሃንም እንደዚሁ ኢየሱስ ነው፡፡ እኛ ማድረግ የሚኖርብን በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ በተገለጠው የደህንነት እውነት በማመን ይህንን ኢየሱስ ክርስቶስ በእምነት በመላው ዓለም መስበክ ነው፡፡ በ1ኛ ቆሮንቶስ 10፡31 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሄር ክብር አድርጉት፡፡›› ሕይወታችን የጌጠኛውን ጉብጉብ ሚና በታማኝነት በመፈጸም ይህንን ወንጌል በማሰራጨት ላይ ያለመ ነው፡፡
ሰዎች በወጣትነታቸው እጅግ የሚጨነቁት ስለ ወደፊት ሕይወታቸው ነው፡፡ ‹‹የወደፊት ሕይወቴ ምን ይሆናል? የምወዳትስ የት አለች? የወደፊት እጮኛዬስ ምን እያደረገች ነው?›› በማለት ይጨነቃሉ፡፡ የወደፊት እጮኛዬ ያለው የት ነው? እርሱ ያለው በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡ እርሱም ሌላ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ታዲያ እርሱ ምን ያደርጋል? ብርሃኑን ያበራል፡፡ እርሱ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ብርሃን ነው፡፡ እርሱ ጌታ ነው፡፡ እናንተ ሁላችሁም የእርሱ ሙሽሮች ናችሁ፡፡ ጌታ በቃሉ አማካይነት እዚሁ በእርሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደሚገናኛችሁ በመናገር ወደ ቤተክርስቲያኑ እንድትመጡ እየነገራችሁ ነው፡፡ በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ በተገለጠው እውነት ከሙሉ ልባችሁ በማመን ወደ እግዚአብሄር ስትጸልዩ እንደሚገናኛችሁ እየተናገረ ነው፡፡ በእርሱ ስታምኑ ወደ እናንተ እንደሚመጣና እንደሚገናኛችሁ ነግሮዋችኋል፡፡
ጻድቃን ሁልጊዜም በአስተሳሰቦቻቸው የነቁ መሆን አለባቸው፡፡ ልቦቻችሁን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ስትሞሉት መንፈስ ቅዱስ በየቀኑ ያነቃችኋል፡፡ ጻድቃን ማድረግ የሚኖርባቸው ነገር የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለማሰራጨት ሕይወታቸውን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት መሠረት መኖር ነው፡፡ ይህንን ስናደርግ ያን ጊዜ እኛው ራሳችን ስጋዊ አስተሳሰቦችን ከመንፈሳዊ አስተሳሰቦች ለይተን ማወቅ እንችላለን፡፡
ከዚህ ቀደም ምናልባት ሽንኩርት ልጣችሁ ይሆናል፡፡ በመጀመሪያ ውጫዊ ቆዳውን ትልጣላችሁ፡፡ ስትልጡት በመጠኑ ወደ አረንጓዴነት የሚያደላ ሌላ ሽፋን ብቅ ይላል፡፡ ይህንን ወደ አረንጓዴነት የሚያደላ ሽፋን ስትልጡት ከውስጥ ነጭ ሽፋን ይመጣል፡፡ ሽንኩርቱ በሙሉ አንዱ በሌላው ላይ ከተደራረቡ ነጭ ሽፋኖች የተሠራ ነው፡፡ ተልጦ ውስጠኛው ነጭ ሽፋን ብቅ ሲል ይህ ብቅ ያለው ሽፋን ከጊዜ በኋላ ወደ ቢጫ ቆዳ ይለወጣል፡፡ ነገር ግን ይህ ቆዳ ሲላጥ እንደገና ውስጣዊው ነጭ ሽፋን ብቅ ይላል፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላም ይህ ውስጠኛው ቆዳ እንደገና ወደ ውጫዊ ቆዳ ይለወጣል፡፡ ስለዚሀ ጠንከር ያለ ሽፋን ለማግኘት እንደገና ልትልጡት ያስፈልጋችኋል፡፡
የእኛም ስጋ ልክ እንደዚህ ሽንኩርት ሽፋኖች ነው፡፡ ስለዚህ በየቀኑ ስጋዊ አስተሳሰቦቻችንን ልጠን መጣል አለብን፡፡ ‹‹በዳንሁ ጊዜ ራሴን ክጃለሁ፤ የሐጢያቶችን ስርየት ከተቀበልሁ በኋላ እንኳ በተደጋጋሚ ራሴን መካድ ይኖርብኛልን? ባለፈው ዓመት ምን ያህል ጊዜ ራሴን እንደካድሁ ታውቃለህን? ልቤን መስበር በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ አሁን ደግሜ ላደርገው ያስፈልገኛልን? በጣም አዳጋች ነው!›› ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ወንድሞችና እህቶች በዚህ መንገድ የስጋ አስተሳሰቦቻችሁን ማስወገድ ትክክለኛ ነገር ነው፡፡ ልክ የሽንኩርትን ሽፋኖች እንደምንልጥ ሁሉ የስጋ አስተሳሰቦቻችንንም መላጥ የመርህ ጉዳይና ትክክለኛ ነገር እንደሆነ ጌታ እየነገረን ነው፡፡
ጌታችን በተጻፈው ቃሉ አማካይነት ሊገናኘን ይፈልጋል፡፡ በሕብስቱ ገበታ፣ በመቅረዙ፣ በዕጣኑ መሠውያና በስርየት መክደኛው ፊት ሊገናኘን ይፈልጋል፡፡ እዚህ ላይ ራሳችሁን ለመካድ መገደድና እምነት ሳይኖራችሁ እምነት እንዳላችሁ ማስመሰል ይኖርባችኋል ማለቴ አይደለም፡፡ ነገር ግን በእምነት ከልባችሁ ራሳችሁን መካድ ይገባችኋል ማለቴ ነው፡፡ አሁን ገባችሁ? ጌታ ራሳችሁን መካዳችሁ ይጠቅማችኋል ብሎ መጠቆሙ ብቻ ሳይሆን ያንኑ ማድረግ እንደሚገባችሁ እየተናገረ ነው፡፡ በልባችሁ ራሳችሁን መካድ እንዳለባችሁ በአእምሮዋችሁ ውስጥ ከጻፋችሁ ያን ጊዜ ራስን መካድ በራሱ ይመጣል፡፡ እናንተ ‹‹አሃ ለካ ራሴን መካድ የምችለው በዚህ መንገድ ነው›› ብላችሁ ሳትገነዘቡ በራሱ ይመጣል፡፡ ነገር ግን መሠረታዊ የሆኑት መርሆዎች ሳይስተማሩ ሰዎች ፈቃዳቸውን እንዲያጎብጡ የሚገደዱ ብቻ ከሆኑ እዚህ ላይ መድረስ የማይችሉ ከመሆናቸውም በላይ መጨረሻቸው እምነታቸውን ማጣት ሊሆን ይችላል፡፡
ልቦቻችን እንዲገዙ ስንነግራቸው ጌታ ይደሰታል፡፡ ይህ ጌታን የሚያስደስተው ከሆነ ስጋዊ አስተሳሰቦቻችንን ማስገዛት ይገባናል፡፡ በእርግጥ የምንደርስባቸወ የማይመስሉን አንዳንድ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ወደ እነርሱ ላይ ለመድረስ በርትተን መሞከራችንን እንቀጥላለን፡፡ ነገሩ እንዲህ አይደለምን? ጌታ ስላዳነንና ሠራተኞቹ ስላደረገን እኛ ልናደርገው የምንችለው ምንም ነገር የለም፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹ሐይልን በሚሰጠኝ በክርሰቶስ ሁሉን እችላለሁ፡፡›› (ፊልጵስዮስ 4፡13) ከዚህም በላይ የወንጌል አበቦች እንዲያብቡ ማድረግን በሚመለከት ከሁሉም እጅግ የምናንስ ጌጠኛ ጉብጉቦች ብንሆንም ያ ማበብ አሁንም ድረስ ዕፁብ ድንቅ ነው፡፡ ታዲያ እኛ ልናደርገው የማንችለው ምን ነገር አለ? እኛ ከጌጠኛ ጉብጉቦች ሁሉ የምናንስ ሆነን ሳለን እንኳን ጌታ የወንጌል አበቦች እንዲያብቡ የሚያደርግ ከሆነ እኛስ የእርሱ ጌጠኛ ጉብጉቦች መሆን አንችልም? በእርግጥ እንችላለን፡፡
በልቦቻችን ውስጥ ያለውን እምነታችንን ለመቀበልም የተዘጋጀን መሆን አለብን፡፡ እኛ ማድረግ የሚኖርብን ‹‹አዎ ያ ትክክል ነው›› በማለት ትክክል የሆነውን እንደ ትክክል መቁጠርና ‹‹አይደለም አስተሳሰቦቼ ተሳስተዋል፤ ተሳስቼ ነበር›› በማለት ስህተቱን እንደ ስህተት መቀበል ነው፡፡ ጌታን መከተል ማለት ራስን መካድና የራስን ፈቃድ ማስገዛት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ስጋዊ ፍላጎቶቻችንን ስናስገዛ ጌታችን ይለውጠናል፡፡ ነገር ግን እኛ በራሳችን መንገድ ራሳችንን መለወጥ አንችልም፡፡ መንፈሳዊ ሰው መሆን በእኛ ጥረቶች የሚደረስበት አንዳች ነገር አይደለም፡፡ እኛ ማድረግ ያለብን ትክክል ወይም ስህተት እንደሆንን ለማየት ራሳችንን በእግዚአብሄር ቃል መስታወት ማየት ነው፡፡ ተሳስተን ከሆነ ማድረግ የሚኖርብን ነገር ቢኖር ‹‹አዎ ጌታ ሆይ! አንተ ብቻ ትክክል ነህ፤ የተሳሳትሁት እኔ ነኝ›› በማለት ማንነታችንን እንዳለ መቀበል ነው፡፡ ይህንን ወዲያውኑ ስናደርግ በልቦቻችን ውስጥ ያለው ጨለማ ይወገዳል፡፡ ጌታም እንዲህ ይለናል፡- ‹‹እናንተን የመሰለውን ፍጡር ሳይቀር ሐጢያቶቻችሁን ሁሉ ደምስሻለሁ፡፡›› ጌታችን ‹‹ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፡፡ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና›› (ኤፌሶን 5፡13) ይላል፡፡
እኛ በፈቃዳችን የምናደርገው ምንም ነገር የለም፡፡ እኛ ማድረግ የሚገባን ነገር ቢኖር በእምነት በቅድስቱ ስፍራ ውስጥ መኖር ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ በእምነት በቅድስቱ ስፍራ ውስጥ ስንኖር ጌታ በእኛ ይሠራል፡፡ እግዚአብሄር የከበርን ጌጠኛ ጉብጉቦች ሊያደርገን ብዙ ጸጋና ብዙ በረከቶች ለግሶናል፡፡ እግዚአብሄር በእውነት በእኛ አማካይነት የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለማሰራጨት ስለፈለገ ተጨማሪ በረከቶችን ሰጥቶናል፡፡ ሁላችሁም ይህንን እውነት እንደምታምኑ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ሁሉ እንደምታምኑ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ታምናላችሁን? ይህ ጥያቄ በሚጠየቅበት ጊዜ ሁሉ መልሳችሁ ‹‹አዎ›› ከሆነ እንግዲያውስ እምነታችሁ ያድጋል፡፡ የእምነት ግዛት እንደዚህ ስለሆነ ማንም በራሱ አንዳች ነገር ሊማር አይችልም፡፡
አገልጋዮች ጌጠኛ ጉብጉቦች ናቸው፡፡ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንም ሁሉ እንደዚሁ ናቸው፡፡ ‹‹አንተ አስቀያሚ ጌጠኛ ጉብጉብ ነህ፤ እኔ ግን ውብ ጉብጉብ ነኝ፡፡›› በእናንተ መካከል ያለ ሰው እንደዚህ እንደማያስብ አውቃለሁ፡፡ እንደዚህ ያሉ አስተሳሰቦች ወደ እናንተ ሲመጡ ከእግዚአብሄር አእምሮ ርቃችሁ በተቃራኒ አቅጣጫ እየተጓዛችሁ መሆናችሁን አውቃችሁ ዘወር ማለት አለባችሁ፡፡ ጌጠኛ ጉብጉቦች ሽልማትን ለማግኘት በሚደረግ ትርጉም አልባ የውበት ፉክክር ውስጥ መፎካከር ምን ይረባቸዋል? አንዳንድ ጌጠኛ ጉብጉቦች ምንም ያህል ጥሩ መስለው ቢታዩም ከእነርሱ ማናቸውም ከራሱ ከአበባው ይልቅ የተዋቡ መሆን ይችላሉን? ጌጠኛ ጉብጉቦች ከራሱ ከአበባው ይልቅ ይበልጥ የተዋቡ ከሆኑ አበባው ጥቅም የሌለውና የማይስብ ይሆናል፡፡ አንድን ግድግዳ ለመገንባት ታናናሽና ታላላቅ ጡቦች እንደሚያስፈልጉ ሁሉ ሁላችንም የተሻልንም እንሁን የከፋን የጌታ ወንጌል አበቦች እንዲያብቡ ለማድረግ ጌጠኛ ጉብጉቦች ሆነን እናስፈልጋለን፡፡
ስለዚህ በዕብሪተኝነታችን አንዳችን ሌላችንን ችላ አንበል፡፡ በፈንታው ሁላችንም የከበርን መሆናችንን በመገንዘብ አንዳችን ሌላችንን እናክብር፡፡ እያንዳንዱ ሰው ክቡር ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ተፈላጊ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን አንድ መክሊት ንጹህ ወርቅ ጠፍጥፎ መቅረዙን እንዲሠራ እንዳዘዘው እኛንም በደህንነት ሕጉ ጻድቃን አድርጎን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የሚያገለግሉ ጌጠኛ ጉብጉቦች አድርጎናል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር በእኛ አማካይነት ወንጌሉን ለማሰራጨት ተደስቷል፡፡ አሁንም ቢሆን እግዚአብሄር በቤተክርስቲያኑ አማካይነት የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለሰው ዘር ሁሉ እያሰራጨ ነው፡፡ እግዚአብሄር በዚህ ወንጌልና በጌጠኛ ጉብጉቦቹ ስርጭት አማካይነት መላውን ሰፊ ዓለም በእውነት ፍቅሩ ሊያበራ ይፈልጋል፡፡
ሐሌሉያ!