Search

คำถามที่พบบ่อยเกี่ยวกับความเชื่อของคริสเตียน

เรื่องที่ 1 : การเกิดใหม่โดยน้ำและพระวิญญาณ

1-16. የሐጢያት ደመወዝ ምንድነው? 

የሐጢያት ደመወዝ ሞት ነው፡፡ ይህ ምንም ይሁን እያንዳንዱ ሐጢያት በእግዚአብሄር ፊት መኮነን አለበት፡፡  ለአንዲት ሐጢያት እንኳን ፍርዱ ሞት ነው፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ሐጢያቶቻቸውን ለማስተሰረይ ነውር የሌለበትን በግ ማቅረብ ነበረባቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህ መስዋዕቶች ሐጢያቶቻቸውን ለዘላለም ማንጻት የሚችሉ አልነበሩም፡፡ ‹‹የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ሐጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና፡፡›› (ዕብራውያን 10፡4)    
ስለዚህ እግዚአብሄር ሕዝቡን ሁሉ ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን ጠቦትን አዘጋጀ፡፡ እያንዳንዱ የመስዋዕት እንስሳ ሐጢያትን ሁሉ ለመውሰድና ከዚያም በእነርሱ ምትክ ለመሞት እጆች ሊጫኑበት ይገባ ነበር፡፡ 
በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ የእግዚአብሄር በግ ሆኖ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በመውሰድ ስለ እኛ ሞቷል፡፡ ‹‹የሐጢአት ደመወዝ ሞት ነው፡፡ የእግዚአብሄር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው፡፡›› (ሮሜ 6፡23)    
የሐጢያት ደመወዝ ሞት ነው፡፡ ኢየሱስ ግን በእኛ ፋንታ በመሞትና ለዓለም ሐጢያተኞች በሙሉ የዘላለም ሕይወት ስጦታን በማዘጋጀት ፍቅሩን ገለጠ፡፡