Search

คำถามที่พบบ่อยเกี่ยวกับความเชื่อของคริสเตียน

เรื่องที่ 4: คำถามที่พบบ่อยจากผู้อ่านหนังสือของเรา

4-10. ‹‹የእውነትን እውነት ከተቀበልን በኋላ ወደን ሐጢአትን ብናደርግ›› (ዕብራውያን 10፡26) ማለት ምን ማለት ነው?

የጠቀስከው ምንባብ ትርጓሜ ይኸውልህ፡፡
‹‹የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ሐጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ሐጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፡፡ የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ፡፡››     
አሁን በእውነት እውቀት ማለትም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ እምነት ሊኖርህ ይችላል፡፡ 
ታዲያ ‹‹ወዶ ሐጢያት ማድረግ›› ምን ማለት ነው? 
ሐጢያት በሁለት መደቦች ሊከፈል እንደሚችል ማወቅ አለብን፡፡ ‹‹ሞት የሚገባው ሐጢያት›› እና ‹‹ሞት የማይገባው ሐጢያት፡፡›› (1ኛ ዮሐንስ 5፡16)   
ነገር ግን ‹‹ሞት የሚገባው ሐጢያት›› መንፈስ ቅዱስን የመሳደብ ሐጢያት ነው፡፡ 
‹‹ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ሐጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም፡፡›› (ማቴዎስ 12፡31) መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ እውነተኛ አዳኝ እንደሆነ ይመሰክራል፤ ዳግመኛ በተወለዱ ቅዱሳኖች አማካይነትም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ይመሰክራል፡፡ 
በአጭሩ ሰው መላውን ይዘቶቹን ከሰማ በኋላ እውነተኛውን ወንጌል የሚክድ ከሆነ ያን ጊዜ ይህ ሰው መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሐጢያት እየሰራ ነው፡፡ የሚያሳዝነው በወንጌል ምክንያት አንዳንድ ችግሮች በሚገጥሙዋቸው ጊዜ ወንጌልን የሚክዱ ሰዎች ያሉ መሆናቸው ነው፡፡
ሰው እውነት መሆኑን እያወቀ እውነተኛውን ወንጌል በውዴታ የሚክድ ከሆነ እግዚአብሄር የዚህን ሰው እንዲህ ያለ ሐጢያት ይቅር ሊለው ይችላልን? እግዚአብሄር እንዲህ ባለ ሐጢያት ላይ በግልጥ ዘላለማዊ ኩነኔን ያውጃል፡፡