Search

ЧЗВ за Християнската Вяра

Тема 1: Новорождението от водата и Духа

1-28. አንተ ብዙውን ጊዜ የሚተወውን የኢየሱስን ጥምቀት በተለይ ካላጎላህ በስተቀር፣ ይህ እኔ ቀድሞውንም አምኜበትና አስተምሬው የነበረ ነገር ነው። እንደዚህ ከሆነ፣ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በትክክል ልዩ የሚያደርገው ምንድነው?

“መዳን” ማለት ከኃጢአቶች ሁሉ ፍጹም መነጻት ማለት ነው። ይህም ደግሞ ዳግመኛ መወለድ ማለት ነው። አንድ ኃጢአተኛ በሕይወት ወንጌል በማመን ጻድቅ ሲሆን “እርሱ/እርስዋ በኢየሱስ መዳን አማካይነት ከውሃና ከመንፈስ ተወለደ/ች” እንላለን። መንፈስ ቅዱስ በተዋጁትና ዳግም በተወለዱት ላይ ይወርድና የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆኑ ይመሰክራል። ስለዚህ ሁሉም ተመሳሳይ ነው፤ ከኃጢአቶች ሁሉ ፍጹም መነጻት፣ መንፈስ ቅዱስን መቀበል፣ መዳን፣ ዳግም መወለድ፣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንና ጻድቅ ሰው መሆን ተመሳሳይ ነገሮች ናቸው።
ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ። በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሐንስ 14፡6)፣ ይህ የሚያመላክተው እኛ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት የምንችለው የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ በሆነው በኢየሱስ ብቻ መሆኑን ነው። ስለዚህ ኢየሱስ እንዴት ኃጢአቶቻችንን ሁሉ እንዳጠበና ወደ እርሱ መንግሥት መግባት የሚገባን የእርሱ ሕዝቦች አድርጎ እንደቆጠረን ማወቅ ይኖርብናል።
ሆኖም አብዛኞቹ ክርስቲያኖች የእርሱን ስም መጥራት ብቻ ሊያድናቸው እንደሚችል አሁንም ያስባሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ሳይከፍቱ ወይም ሳያነቡ፣ ከኃጢአቶቻችን ሁሉ ሊያድነን ያደረገውን ነገር ሳያውቁ በኢየሱስ ያምናሉ። እግዚአብሔር ለውጥ ወይም መዛወር የሌለበት መንፈስና ቅዱስ ነው፤ እኛ ግን የምንኖረው ኃጢአተኛ ሕይወትን ነው። ወደ ጌታ መንግሥት መግባት የሚቻለው በኢየሱስ አማካይነት ብቻ ነው ‘በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ’ (ሮሜ 8፡2) እምነት አማካይነት በእርሱ ማመን እንችላለን።
ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ለመዳናችን ምን እንዳደረገ እንኳን አያውቁም፤ በፋንታው “ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ” በማለት ዕውር ሆነው በከንቱ በእርሱ ያምናሉ። የዳኑ እንደሆኑም ያስባሉ፣ ነገር ግን በልባቸው ውስጥ አሁንም ኃጢአቶች አሉባቸው። በኢየሱስ ላይ እምነት ቢኖራችሁም በልባችሁ ውስጥ አሁንም ኃጢአት ካለ ታዲያ የዳናችሁት ከምንድነው? አንድ ሰው “ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን እንዴት አጠበ?” ብሎ ቢጠይቅ ብዙ ሰዎች “ምናልባትም በመስቀል ላይ ሳያነጻቸው አይቀርም” ብለው ይመልሳሉ። ከዚያም ለሌላ ጥያቄ፣ “በልባችሁ ውስጥ ኃጢአት አለን?” ለሚለው ጥያቄም “በእርግጠኝነት። በዚህ ምድር ላይ ፈጽሞ ከኃጢአት ነጻ መሆን የሚችል ማን ነው?” ይላሉ።
የኢየሱስ ስም “ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና” (ማቴዎስ 1፡21) ማለት ነው። ከኃጢአት ለመዳን በኢየሱስ እናምናለን።
ነገር ግን በኢየሱስ ብናምንም አሁንም ድረስ በልቦቻችን ውስጥ ኃጢአት ካለ አሁንም ለኃጢአት ባርነት የተሸጥንና በዚያው መሠረትም የምንፈረድ ኃጢአተኞች ነን። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ብሎዋል፦ “እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም” (ሮሜ 8፡1)። ስለዚህ በልቡ ኃጢአት ያለበት ሰው ገናም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ አልሆነም። አሁንም ድረስ በኢየሱስ ቢያምኑም ያልተዋጁና ከመዳን የራቁ ኃጢአተኞች ሆነው ለምን ይቀራሉ? በኢየሱስ ጥምቀት ኃጢአቶቻቸውን በእርሱ ላይ ሳያስቀምጡ በመስቀሉ ደም ብቻ ስለሚያምኑ ነው። ስለዚህ አሁንም ድረስ በልባቸው ውስጥ ኃጢአት አለ፣ ኢየሱስም ኃጢአቶቻቸው ምንም ቢሆን በመስቀል ላይ ሞቷል።
በኢየሱስ ጥምቀት በሚያምኑ ክርስቲያኖችና በእርሱ በማያምኑ ሰዎች መካከል አቢይ የሆነ ልዩነት አለ። አንዳንዶች በኢየሱስ ጥምቀት ላይ እምነትን ይዘው ቤዛነትን አግኝተው ጻድቃን ሲሆኑ ሌሎች ግን አሁንም ድረስ በዚህ ላይ እምነት ሳይኖራቸው አሁንም ደረስ ኃጢአተኞች ሆነው ቀርተዋል። መንፈስ ቅዱስ በኃጢአተኛ ላይ አይመጣም፣ እርሱ የሚመጣው በውሃውና በመንፈሱ ዳግም በተወለደ ጻድቅ ሰው ላይ ብቻ ነው።
ስለዚህም ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ አለ፦ “ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?” (ሮሜ 6፡3)። ብዙ ሰዎች ኢየሱስ በመስቀል ላይ ኃጢአቶቻችንን እንደወሰደ ያምናሉ፣ ነገር ግን በኢየሱስ ጥምቀት ካላመንን ኃጢአት አልባ የሆነ ልብ እንዳለን መመስከር በፍጹም አንችልም። እንደዚያ ብናደርግ ከሕሊናችን ጋር የሚጋጭ ውሸት ለእግዚአብሔር እየነገርነው ነው።
በእርሱ ጥምቀት በማመን ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ወደ ኢየሱስ ካላስተላለፍን አሁንም ድረስ በልቦቻችን ውስጥ ኃጢአት አለ። የኢየሱስን ጥምቀትና መስቀል ወንጌል የማያምኑ ሰዎች ሕግ አክራሪነት ውስጥ ወደ መውደቅ ያዘነብላሉ፣ የከፉ ኃጢአተኞችም ይሆናሉ። ስለዚህ ምንም ነገር ቢያደርጉም፣ ጥልቅ ተራሮች ላይ ሄደው ቢጸልዩ ወይም በጸሎት ስብሰባዎች ላይ ይቅርታን ለማግኘት ከልባቸው ቢጸልዩም፣ አሁንም ድረስ በልባቸው ውስጥ የቀሩ ኃጢአቶችን ያገኛሉ።
ኢየሱስ እንዲህ ብሎዋል፦ “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ” (ማቴዎስ 7፡21-23)።
“እናንተ ዓመፀኞች” የሚለው የሚያመለክተው ማንን ነው? ይህ የሚያመላክተው በመስቀሉ ብቻ ስላመኑ በልባቸው ውስጥ ፍጹም የሆነውን ቤዛነት ያልተቀበሉትን ሰዎች ነው። ያ ከእግዚአብሔር ያልሆነ በፈቃደኝነት የተመሰረተ እምነት ነው። ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀሉ አማካይነት እንዳዳነን እውነቱን ካላመንን ዓመፀኞች ነን። የኢየሱስን ጥምቀትና መስቀል ከማወቃችንና ከማመናችን በፊት ትክክለኛ እምነት አለን ማለት አንችልም።
ኢየሱስ ሰዎች ዳግም መወለድ የሚፈልጉ ከሆነ ያ የሚቻለው በውሃና በመንፈስ አማካይነት ብቻ እንደሆነ ተናግሮዋል። እንደ ኖህ ዘመን ሰዎች ከጥፋት ውሃ መዳን የቻሉት በመርከብ ውስጥ ገብተው ብቻ እንደነበረ ሁሉ፣ እናንተም ከኃጢአቶቻችሁ ሁሉ መዳን መቀበልና እውነተኛ የታመነ ሕይወት መኖር የምትችሉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ስታምኑ ብቻ ነው።

ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ውጭ ከኃጢአቶቻችሁ ሁሉ መዳንም ሆነ የእግዚአብሔር ልጆች መሆን አትችሉም።