Search

FAQ sur la Foi Chrétienne

Sujet 3 : La Révélation

3-1. በምዕራፍ 7 ላይ የተጠቀሰው 144,000 የሚለው ቁጥር የሚድኑት የእስራኤል ሕዝቦች ትክክለኛ ቁጥር ነው ወይስ ተምሳሌታዊ አሃዝ?  

በምዕራፍ 7 ላይ የተጠቀሰው 144,000 የሚለው ቁጥር በመጨረሻው ዘመን ከእስራኤላውያን በትክክል ምን ያህል ሕዝቦች እንደሚድኑ ይነግረናል፡፡ ከአስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ከእያንዳንዳቸው 12,000 ተወስዶ በጠቅላላው 144,000 ይድናሉ፡፡ ይህም በእግዚአብሄር ልዩ ቸርነት የሚፈጸም ነው፡፡ እግዚአብሄር ከወደዳቸው የአብርሃም ዘሮች አንዳንዶቹ ይድናሉ፡፡ እግዚአብሄር ለአብርሃም የሰጠውን ተስፋ ያስባል፡፡ ይህንን ተስፋ ለመፈጸምም አሁን የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ለአሕዛቦች ብቻ ሳይሆን በሥጋ የአብርሃም ዘሮች ለሆኑት የእስራኤል ሕዝቦች እንዲሰራጭ ፈቅዶዋል፡፡ 
ስለዚህ እግዚአብሄር በመጨረሻው ዘመን መከራዎችና በተለየ መንገድ ለእስራኤሎች በሚያስነሳቸው ሁለት ምስክሮች አማካይነት እነርሱ ያሳደዱትና የሰቀሉት ኢየሱስ ክርስቶስ በእርግጥም የእነርሱ እውነተኛ አዳኝ መሆኑን ወደ ማመን እንዲመጡ ወስኖዋል፡፡ እስራኤሎችም በእግዚአብሄርና በአብርሃም እምነት አማካይነት የእግዚአብሄር ልዩ ፍቅር ተቀባዮች ይሆናሉ፡፡ 
እግዚአብሄር ከአስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ከእያንዳንዳቸው 12,000ዎችን በተለየ መንገድ ከሐጢያቶቻቸውና ከጥፋት አድኖ በመልአኩ አማካይነት በእግዚአብሄር ማህተም ሊያትማቸው ወስኖዋል፡፡ ስለዚህ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል 144,000ዎች የእግዚአብሄር ሕዝብ መሆናቸውን የሚያሳይ ምልክት ይቀበላሉ፡፡ ይህ ቁጥር በአስራ ሁለቱ ነገዶች መካከል እኩል የተከፋፈለ ነው፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሄር ለእነርሱ ያለው ፍቅር ለአንድ የተለየ ነገድ በማድላት ላይ የተመሰረተ አይደለምና፡፡ ነገር ግን ለሁሉም ሕዝቡ የሚሆኑበትን ጸጋ ያለብሳቸዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ስሜታቸው ውሳኔያቸውን እንዲጋርድ ቢፈቅዱም እግዘአብሄር ፍጹም በሆነ ፍትህና እኩልነት በነገሮች ሁሉ ውስጥ ይሰራል፡፡ 
እግዚአብሄር 144,000 እስራኤሎችን በደህንነት ማህተም አትሞ ሲያበቃ በዚህ ምድር ላይ ታላላቆቹን መቅሰፍቶች ያወርዳል፡፡ እግዚአብሄር ከአስራ ሁለቱ ነገዶች ከእያንዳንዳቸው-- ከይሁዳ፣ ከሮቤል፣ ከጋድ፣ ከአሴር፣ ከንፍታሌም፣ ከምናሴ፣ ከስምዖን፣ ከሌዊ፣ ከይሳኮር፣ ከዛብሎን፣ ከዮሴፍና ከብንያም ነገዶች 12,000 ወስዶ በጠቅላላው 144,000 እስራኤሎችን ሕዝቡ አድርጎዋቸዋል፡፡ ይህንን ያደረገው እግዚአብሄር አምላካቸው እንደሚሆን ለአብርሃምና ለዘሮቹ የገባውን ተስፋ ለመፈጸም ነው፡፡ 
እግዚአብሄር በዚህ ሁኔታ 144,000 እስራኤሎችን ለማዳን ወሰነ፡፡ እዚህ ላይ 14 ቁጥር በማቴዎስ 1፡17 ላይ እንደሚታየው ለእኛ የተለየ ትርጉም ያለው ሲሆን እግዚአብሄር በእስራኤሎች መካከል አዲስ ሥራ እንደሚጀምር ይነግረናል፡፡ ይህ ቁጥር አሁን በዚህ ምድር ላይ የመጀመሪያውን ዓለም ታሪክ በመደምደም የዳኑት እስራኤሎች በአዲስ ሰማይና ምድር እንዲኖሩ የሚያደርግበትን የእግዚአብሄር ፈቃድ ይዞዋል፡፡ 
ከአብርሃም እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ድረስ ያለውን የዘር ግንድ መስመር ስንመለከት ከአብርሃም እስከ ዳዊት 14 ትውልዶች፣ ከባቢሎን ምርኮ እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ድረስም 14 ትውልዶች እንዳሉ መረዳት እንችላለን፡፡ በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር በእያንዳንዱ 14 ትውልዶች ውስጥ አዲስ ሥራውን እንደሚጀምር መረዳት እንችላለን፡፡ እግዚአብሄር 144,000 እስራኤሎችን ያተመው በዚህ በአሁኑ ዓለም ሳይሆን በእግዚአብሄር መንግሥት ውስጥ አዲስ ሕይወትን እንዲኖሩ ባፈው ፈቃዱ ነው፡፡ ማየት እንደሚቻለው እግዚአብሄር በአንድ ወቅት ለሰው ዘር የገባውንና የመሰረተውን ተስፋ በተጨባጭ የሚፈጽም ታማኝ አምላክ ነው፡፡