Search

FAQ sur la Foi Chrétienne

Sujet 3 : La Révélation

3-10. የቅዱሳኖች ንጥቀት የሚመጣው ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ከነፋ በኋላ ነው ስትል የንጥቀትን ቀንና ሰዓት ማንም ጌታም ራሱ እንኳን እንደማያውቀው ጌታ የተናገረውን እየተቃረንህ አይደለምን?  

በፍጹም! ጌታችን የነገረን የቅዱሳኖችን ንጥቀት ትክክለኛ ቀንና ሰዓት ሳይሆን ወደዚህ አስደናቂ ሁነት የሚመሩትን ሁኔታዎችና ምልክቶች ነው፡፡ ጌታን የሚወዱ ቅዱሳን እምነታቸውን ማዘጋጀት የሚችሉት ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ጊዜው ሲመጣም ጸረ ክርስቶስን ተዋግተው ሰማዕትነታቸውን በመቀበል በንጥቀት ውስጥ ሊሳተፉ የሚችሉት ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡   
እግዚአብሄር በመገለጡ አማካይነት በወቅቱ በፍጥሞ ደሴት ተሰዶ ለነበረው ለሐዋርያው ዮሐንሰ በዚህ ዓለም የመጨረሻ ዘመን የሚሆነውን ነገር ሁሉ አሳይቶታል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ሲያቅድና ሥራዎቹን ሁሉ ሲፈጽም ባሮቹ ማወቃቸውን ያረጋግጣል፡፡ 
ከእግዚአብሄር ቃል ሁሉ በተለይ የራዕይ መጽሐፍ የተጻፈው በብዙ ተምሳሌታዊ መግለጫዎች ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ እነዚህን ተምሳሌቶች መፍታትና ለሕዝቡ ማብራራት የሚችሉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ የዳኑና በልባቸው ውስጥም መንፈስ ቅዱስ የሚኖርባቸው ባርያዎች ብቻ ናቸው፡፡ የራዕይ ቃል ለእግዚአብሄር ባሮችና ቅዱሳን ስለ ሰባቱ መለከቶች መቅሰፍቶች፣ ስለ ጸረ ክርስቶስ መገለጥ፣ ስለ ቅዱሳን ሰማዕትነት፣ ስለ ትንሳኤያቸውና ንጥቀታቸው፣ ስለ ክርስቶስ የሺህ ዓመት መንግሥትና ስለ አዲስ ሰማይና ምድር ሁሉንም በዝርዝር ገልጦላቸዋል፡፡ 
የቅዱሳን ንጥቀት ከሰማዕትነታቸው ጋር በሚገባ ተቆራኝቷል፡፡ ዮሐንስ ራዕይ 11፡10-12 ስለ ሁለቱ ነቢያቶቹ ሞት፣ በሦስት ቀን ተኩል ውስጥ ስለሚሆነው ትንሳኤያቸውና ንጥቀታቸው ይነግረናል፡፡ እነዚህ ሁለት ምስክሮች በጸረ ክርስቶስ ይገደሉና በሦስት ቀን ተኩል ውስጥ ከሙታን ይነሳሉ፡፡ ከዚህ ታሪክ መረዳት የምንችለው ነገር ቢኖር ጸረ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ሲገለጥና ሰዎችም ምልክቱን በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው እንዲቀበሉ ሲያደርግ ቅዱሳን ከጸረ ክርስቶስ ጋር ተዋግተው በእምነታቸው ይሰዋሉ፡፡ ነገር ግን ወዲያውኑ ያንን ተከትሎ ጌታ ሲመጣ የመጀመሪያውን ትንሳኤ አግኝተው ይነጠቃሉ፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16-17 ላይ እንዲህ ተናግሮዋል፡- ‹‹ጌታ ራሱ በትዕዛዝ፣ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሄርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፡፡ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሳሉ፡፡ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፡፡ ሁልጊዜም ከጌታ ጋር እንሆናለን፡፡›› በሌላ አነጋገር ሐዋርያው ጳውሎስ የንጥቀት ጊዜ የሚመጣው የቅዱሳን ሰማዕትነት ከሆነ በኋላና ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ሲነፋ እንደሆነ ነግሮናል፡፡ 
ጸረ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ላይ መንገስ ሲጀምር ምልክቱን እንድንቀበልም ሊያስገድደን ሲሞክርና ልክ እንደ አምላክ እንዲሰገድለት ሲጠይቅ እኛ ቅዱሳን ሰማዕት የምንሆንበት ጊዜ እንደቀረበ መገንዘብ አለብን፡፡ ሰማዕትነታችንን ከተቀበልን በኋላ ወዲያውኑ ትንሳኤያችንና ንጥቀታችን እንደሚመጣም እንደዚሁ መረዳት አለብን፡፡ ይህ በየትኛው ወርና ቀን እንደሚሆን በትክክል አናውቅም፡፡ ነገር ግን ለእኛ ግልጽ የሆነ ነገር ቢኖር የቅዱሳን ንጥቀት ሰባተኛው መልአክ መለከቱን በሚነፋበት ጊዜ የሚሆን መሆኑ ነው፡፡ ቅዱሳን ሁሉ ይህንን እውነት በማመን የጌታን ቀን ለመቀበል መዘጋጀት አለባቸው፡፡