Search

Khotbah-Khotbah

ርዕስ 3፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል

[3-2] የኢየሱስ ጥምቀትና የሐጢያቶች ስርየት፡፡ ‹‹ ማቴዎስ 3፡13-17 ››

የኢየሱስ ጥምቀትና የሐጢያቶች ስርየት፡፡
‹‹ ማቴዎስ 3፡13-17 ››
‹‹ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ ዮሐንስ ግን፡- እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር፡፡ ኢየሱስም መልሶ፡- አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው፡፡ ያን ጊዜ ፈቀደለት፡፡ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃው ወጣ፡፡ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ፡፡ የእግዚአብሄርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፡፡ እነሆም በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡››    
 
 
አሁንም ድረስ በሐጢያት የሚሰቃይ ይኖራልን? 
 
የሐጢያት ባርነታችን አብቅቷልን?
አዎን፡፡

እግዚአብሄር አምላካችን የሐጢያትን እግር ብረቶች ከሰዎች ሁሉ ላይ ቆርጦዋል፡፡ ከሐጢያት በታች ሆነው የተጨቆኑ ሰዎች ሁሉ የሐጢያት ባሮች ናቸው፡፡ ጌታችን ግን በቤዛነቱ ፈጽሞ ነጻ አወጣቸው፡፡ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ አስወገደ፡፡ አሁንም ድረስ በሐጢያት የሚሰቃይ ሰው አለን?
ከሐጢያት ጋር ያለን ጦርነት እንዳበቃ መረዳት ይኖርብናል፡፡ ዳግመኛ በፍጹም በሐጢያት አንሰቃይም፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱና በደሙ በዋጀን ጊዜ የሐጢያት ባርነታችን አከተመ፡፡ ሐጢያቶቻችን በሙሉ ያን ጊዜና እዚያው አከተሙ፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ አስተሰርዮዋል፡፡ እግዚአብሄር ለዘላለም ነጻ ባወጣን በኢየሱስ አማካይነት ለሐጢያቶቻችን ከፈለ፡፡  
ምን ያህል ሰዎች በሐጢያቶቸቸው እንደሚሰቃዩ ታውቃላችሁን? ይህ የጀመረው በአዳምና በሔዋን ዘመን ነው፡፡ የሰው ዘር ከአዳም በወረሳቸው ሐጢያቶች ይሰቃያል፡፡  
አምላካችን ግን በዘፍጥረት 3፡15 ላይ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አደረገ፡፡ ቃል ኪዳኑም ሐጢያተኞችን በሙሉ የሚያድን መሆኑ ነበር፡፡ እርሱ ሰዎች በውሃና በመንፈስ በኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕትነት በኩል እንደሚዋጁ ተናገረ፡፡ ጊዜው ሲደርስም እግዚአብሄር በመካከላችን ይኖር ዘንድ አዳኛችንን ኢየሱስን ላከው፡፡  
እርሱ አጥማቂውን ዮሐንስንም ከኢየሱስ በፊት እንደሚልከው ቃል ገባና ቃሉን ጠበቀ፡፡  
ማርቆስ 1፡1-8 እንዲህ ይላል፡- ‹‹የእግዚአብሄር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፡፡ እነሆ መንገድን የሚጠርግ መልዕክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፡፡ የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምጽ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደተጻፈ ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንሥሐንም ጥምቀት ለሐጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ፡፡ የይሁዳም አገር ሁሉ የኢየሩሳሌምም ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፡፡ ሐጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር፡፡ ዮሐንስም የግመል ጠጉር ለብሶ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፡፡ አንበጣና የበረሃ ማርም ይበላ ነበር፡፡ ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል፡፡ እኔ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል እያለ ይሰብክ ነበር፡፡››       
 
 

አጥማቂው ዮሐንስ የወንጌል ፋና ወጊና መስካሪ፡፡ 

 
አጥማቂው ዮሐንስ ማነው?
የመጨረሻው ሊቀ ካህንና የሰው ዘር ሁሉ ወኪል ነው፡፡ 

በግሪክ ‹ባፕቲዞ› የሚባለው ጥምቀት በመሰረቱ ‹መስረግ› ማለት ነው፡፡ ‹መታጠብን፣ መቀበርን፣ መጥለምን፣ ወይም ማስተላለፍን› ደግሞ ያመለክታል፡፡ ኢየሱስ ሲጠመቅ የእግዚአብሄር ጽድቅ ተፈጸመ፡፡ ‹ጽድቅ› በግሪክ ‹ዲካዮሱኔ› ነው፡፡ ትርጓሜው ‹ጻድቅ መሆን› ማለት ነው፡፡ ‹በጣም ተገቢ› ‹በጣም ተስማሚ› ወይም ‹እጅግ ያማረ ሁኔታ› ማለትም ጭምር ነው፡፡
ኢየሱስ የተጠመቀው እጅግ ተስማሚና ተገቢ በሆነ ሁኔታ አዳኝ መሆን ይችል ዘንድ ነው፡፡ ስለዚህ በኢየሱስ ጥምቀትና መስቀል የሚያምኑ ሰዎች ከእግዚአብሄር ዘንድ የቤዛነትን ስጦታ ይቀበላሉ፡፡  
በአዲስ ኪዳን አጥማቂው ዮሐንስ የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ሊቀ ካህን ነበር፡፡ ማቴዎስ 11፡10-11ን እንመልከት፡፡ ጥቅሱ አጥማቂው ዮሐንስ የሰው ዘር ወኪል እንደሆነ ይናገራል፡፡ በአዲስ ኪዳን ዘመን ሊቀ ካህን በመሆኑ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ አስተላለፈ፡፡ በዚህም የብሉይ ኪዳንን ክህነት አገለገለ፡፡   
ኢየሱስ ራሱ ስለ ዮሐንስ መሰከረ፡፡ በማቴዎስ 11፡13-14 ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፡፡ ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው፡፡›› ስለዚህ ኢየሱስን ያጠመቀው አጥማቂው ዮሐንስ የሊቀ ካህኑ አሮን ዘርና የመጨረሻው ሊቀ ካህን ነበር፡፡ (ሉቃስ 1፡5፤1ኛ ዜና 24፡10)  
ታዲያ ዮሐንስ ከግመል ጠጉር የተሰራ ልብስ ለብሶ ብቻውን በምድረ በዳ የኖረው ለምንድነው? ሊቀ ክህነትን ለመቀበል ነበር፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ የሰው ዘር ሁሉ ወኪል በመሆኑ በሰዎች መካከል መኖር አልቻለም፡፡ ስለዚህ ለሕዝቡ ‹‹እናንተ የእፉኝት ልጆች ንስሐ ግቡ›› በማለት ጮኸ፡፡ ሰዎችን ሐጢያቶቻቸውን ወደሚወስድላቸው ኢየሱስ ለመመለስም የንስሐ ፍሬ እንዲሆንላቸው አጠመቃቸው፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ እጆቹን በኢየሱስ ራስ ላይ በጫነ ጊዜ የዓለምን ሐጢያቶች ወደ ኢየሱስ አስተላልፎዋል፡፡     
 
 
ሁለት አይነት ጥምቀቶች፡፡ 
 
አጥማቂው ዮሐንስ ሰዎችን ያጠምቅ የነበረው ለምን ነበር? 
ሰዎች ለሐጢያቶቻቸው ሁሉ ንስሐ እንዲገቡና ለደህንነታቸውም በኢየሱስ ጥምቀት እንዲያምኑ ለመምራት ነው፡፡ 

አጥማቂው ዮሐንስ ሰዎችን አጠመቀ፡፡ ከዚያም ኢየሱስን አጠመቀው፡፡ የመጀመሪያው ሐጢያተኞች ወደ እግዚአብሄር እንዲመለሱ የሚጠራ ‹የንስሐ ጥምቀት› ነበር፡፡ በዮሐንስ በኩል የእግዚአብሄርን ቃሎች የሰሙ ብዙ ሰዎች ጣዖቶቻቸውን ትተው ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ፡፡   
ሁለተኛው ጥምቀት ማለትም የኢየሱስ ጥምቀት የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ የተላለፉበት ጥምቀት ነበር፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ይፈጽም ዘንድ አጠመቀው፡፡ በሌላ አነጋገር ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ የተጠመቀው ሰዎችን ሁሉ ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን ነበር፡፡ (ማቴዎስ 3፡15) 
ዮሐንስ ኢየሱስን ለምን አጠመቀው? እግዚአብሄር በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች ይድኑ ዘንድ የዓለምን ሐጢያቶች ለመደምሰስ ሲል ዮሐንስ ሐጢያቶችን በሙሉ ወደ ኢየሱስ እንዲያስተላልፍ ፈቀደ፡፡
አጥማቂው ዮሐንስ የሰው ዘር በሙሉ በቤዛነት ወንጌል በማመን ንስሐ እንዲገባና ከሐጢያቶቹ ሁሉ እንዲነጻ በጥምቀት አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ የማስተላለፍና ስለ ኢየሱስ የመመስከር ተልዕኮ የተሰጠው የእግዚአብሄር ባርያ ነበር፡፡ ስለዚህ ዮሐንስ ብቻውን በምድረ በዳ መኖር ነበረበት፡፡ በአጥማቂው ዮሐንስ ዘመን የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ተበላሽቶና እስከ ታች ድረስ በስብሶ ነበር፡፡  
ስለዚህ እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳን በሚልክያስ 4፡5-6 ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹እነሆ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሄር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ፡፡ መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል፡፡››  
በእግዚአብሄር ዓይን ከዚህ ቀደም የሆዋን ሲያመልኩ የነበሩ የእስራኤል ሕዝቦች በሙሉ ተበላሽተው ነበር፡፡ በእርሱ ፊት ጻድቅ ሰው አልነበረም፡፡ ለምሳሌ የመቅደሱ የሐይማኖት መሪዎች፣ ካህናት፣ ሕግ አዋቂዎችና ጸሐፍቶች በተለይ እስከ ታች ድረስ በስብሰው ነበር፡፡ እስራኤሎችና ካህናቶቻቸው በእግዚአብሄር ሕግ መሰረት ተገቢ መስዋዕቶችን አላቀረቡም፡፡ 
ካህናት እግዚአብሄር ለሐጢያቶቻቸው ስርየት የሰጣቸውን እጆችን የመጫንና ደምን የማቅረብ ስርዓት ትተውት ነበር፡፡ በሚልክያስ ዘመን የነበሩት ካህናት ተገቢውን የመስዋዕት ስርዓት፣ እጆችን መጫንና የመስዋዕቱን እንስሳ ደም ማቅረብ ትተው እንደነበር ተጽፎዋል፡፡   
ስለዚህ አጥማቂው ዮሐንስ ከእነርሱ ጋር መቆየት አልቻለም፡፡ ወደ ምድረ በዳ ሄዶ ጮኸ፡፡ እርሱ ምን አለ?
የነቢዩን የኢየሱስን ቃሎች በመጥቀስ በማርቆስ 1፡2-3 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡፡ ‹‹እነሆ መንገድን የሚጠርግ መልዕክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፡፡ የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምጽ፡፡›› 
የምድረ በዳው ድምጽ ሰዎች የንስሐ ጥምቀት እንዲቀበሉ ነገራቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ‹‹የንስሐ ጥምቀት›› ምንድነው? አጥማቂው ዮሐንስ የጮኸለት ጥምቀት ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ በሚወስድላቸው በእርሱ አምነው ይድኑ ዘንድ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ የሚመልስ ጥምቀት ነበር፡፡ ወደ ደህንነት የሚመራቸው የንስሐ ጥምቀት ነበር፡፡ 
‹‹ንስሐ ግቡ፤ ተጠመቁም፡፡ አዳኛችን ኢየሱስም ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ ለመውሰድ በተመሳሳይ መንገድ ይጠመቃል፡፡›› የአጥማቂው ዮሐንስ ጩኸት ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች እንደሚወስድና ሰዎች ሁሉ ወደ እግዚአብሄር ተመልሰው እንዲድኑ በመስቀል ላይ የሚኮነን መሆኑን የሚያውጅ ጩኸት ነበር፡፡   
‹‹እኔ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል፡፡›› ‹በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል› ማለት ሐጢያቶቻችሁን ሁሉ ማንጻት ማለት ነው፡፡ ማጥመቅ ማለት ‹ማጠብ› ማለት ነው፡፡ በዮርዳኖስ ወንዝ የሆነው የኢየሱስ ጥምቀት የእግዚአብሄር ልጅ እኛን ለማዳን እንደተጠመቀና ሐጢያቶቻችንን ሁሉ እንደወሰደ ይነግረናል፡፡  
ስለዚህ ከሐጢያተኛ ኑሮዋችን መመለስና በእርሱ ማመን አለብን፡፡ እርሱ የዓለምን ሐጢያቶች የወሰደ የእግዚአብሄር በግ ነው፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ የመሰከረለት የቤዛነት ወንጌል ይህ ነው፡፡ 
 
 
ለሐጢያቶች ስርየት የሊቀ ካህኑ ተግባር፡፡ 
 
የደህንነትን መንገድ የጠረገው ማነው?
አጥማቂው ዮሐንስ፡፡

ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ተንብዮ ነበር፡፡ ‹‹ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፡፡ የተቀጠረችበት ወራት እንደተፈጸመ፣ ሐጢአትዋም እንደተሰረየ፣ ከእግዚአብሄርም እጅ ስለ ሐጢአትዋ ሁሉ ሁለት ዕጥፍ እንደተቀበለች ወደ እርስዋ ጩሁ፡፡›› (ኢሳይያስ 40፡2)  
ኢየሱስ ክርስቶስ ምንም ሳያስቀር ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደ፡፡ የአዳም ሐጢያት፣ አሁን ያሉት ሐጢያቶችና ወደፊት የሚሆኑት ሐጢያቶችም እንደዚሁ በእርሱ ጥምቀት ታጥበው ነጹ፡፡ እርሱ ሁላችንንም ዋጀን፡፡ ሁላችንም ስለ እግዚአብሄር ቤዛነት ማወቅ ይገባናል፡፡   
ከሐጢያቶቻችን ለመዳን አጥማቂው ዮሐንስ በጥምቀት ዘዴ አማካይነት ሐጢያቶችን በሙሉ ወደ ኢየሱስ እንዳስተላለፈ በሚናገረው ወንጌል ማመን አለብን፡፡
‹‹እግዚአብሄር ፍቅር ስለሆነ በልቦቻችን ውስጥ ሐጢያት ቢኖርም በኢየሱስ በማመን ብቻ መንግሥተ ሰማይ መግባት እንችላለን›› ብለን በማሰብ የተሳሳተ መረዳት መያዝ አይገባንም፡፡    
ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ቤዛነትን ለማግኘት አጥማቂው ዮሐንስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ ባስተላለፈበት ጥምቀትና መስቀል ማመን ይገባናል፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ ያስተላለፈው ‹በውሃ› ነው፡፡   
እግዚአብሄር እኛን ለማዳን ያደረገው የመጀመሪያው ነገር ዮሐንስን ወደዚህ ዓለም መላክ ነበር፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ የእግዚአብሄር መልዕክተኛ ስለሆነ በጥምቀቱ አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ያስተላለፈ የንጉስ አምባሳደር ሆኖ ተላከ፡፡ የሰው ዘር ሊቀ ካህን በመሆንም አገለገለ፡፡  
እግዚአብሄር መልዕክተኛውን አጥማቂውን ዮሐንስን እንደላከልን ነግሮናል፡፡ ‹‹በፊትህ መልዕክተኛዬን እልካለሁ፡፡›› በፊትህ ማለት በኢየሱስ ፊት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ዮሐንስን ከኢየሱስ በፊት ለምን ላከው? በጥምቀት አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ የእግዚአብሄር ልጅ ወደሆነው ወደ ኢየሱስ ለማስተላለፍ ነበር፡፡ ‹‹መንገድን በፊትህ ያዘጋጃል፡፡›› የምንባቡ ትክክለኛ ትርጉም ይህ ነው፡፡  
እኛ ድነን ሰማይ መሄድ እንችል ዘንድ መንገዱን የጠረገው ማነው? አጥማቂው ዮሐንስ ነው፡፡ ‹በአንተ› ማለት ኢየሱስ ሲሆን ‹የእኔ› ማለት ደግሞ እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹መልዕክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፤ እርሱም መንገድን በፊትህ ያዘጋጃል›› ሲል ምን ማለቱ ነው?   
ሰማይ እንገባ ዘንድ መንገዳችንን የሚጠርገው ማነው? ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንዳነጻቸው እንድናምን አጥማቂው ዮሐንስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወደ ኢየሱስ አስተላለፈ፡፡ የእርሱ ተግባር ኢየሱስ ክርስቶስን በማጥመቅ ሐጢያቶቻችንን ወደ ኢየሱስ ማስተላለፍ ነበር፡፡ በእውነት እንድናምንና እንድንድን ያስቻሉት ኢየሱስና ዮሐንስ ነበሩ፡፡  
ደህንነታችን የተመሰረተው ምን ላይ ነው? የእግዚአብሄር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሰራቸው የጽድቅ ሥራዎችና የእግዚአብሄር መልዕክተኛ የሆነው አጥማቂው ዮሐንስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ ያስተላለፈ በመሆኑ እውነታ በማመን ወይም አለማመናችን ላይ ነው፡፡ እግዚአብሄር አብ ልጁን የሚያጠምቀውን መልዕክተኛውን አስቀድሞ በመላክ የሰው ዘር ወኪል አደረገው፡፡ በዚህም ለእኛ የቤዛነትን ሥራ ፈጸመ፡፡  
እግዚአብሄር በኢየሱስ ላመኑ ሰዎች የደህንነትን መንገድ ያዘጋጅላቸው ዘንድ ልጁን እንዲያጠምቅለት አጥማቂውን ዮሐንስን ላከው፡፡ ዮሐንስ ኢየሱስን ያጠመቀበት ምክንያት ይህ ነው፡፡ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ መጠመቁ ሰዎች ሁሉ በኢየሱስ አምነው ሰማይ ይገቡ ዘንድ የሰው ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ የተላለፉበት የእግዚአብሄር ቤዛነት ፍጻሜ ነበር፡፡  
ሰዎች ወደፊት የሚሰሩዋቸው ሐጢያቶችም እንደዚሁ በጥምቀቱ አማካይነት ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል፡፡  ኢየሱስና አጥማቂው ዮሐንስ አብረው ሁላችንም ሰማይ የምንገባበትን መንገድ አዘጋጁልን፡፡ እግዚአብሄር በዚህ መንገድ በአጥማቂው ዮሐንስ በኩል የቤዛነትን ምስጢር ገለጠ፡፡  
ዮሐንስ የሰው ዘር ወኪል በመሆን ቤዛነታችን አምነን ሰማይ እንገባ ዘንድ ኢየሱስን አጠመቀው፡፡ በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶችን በሙሉ ወደ ኢየሱስ አስተላለፈ፡፡ የቤዛነት ዜና ማለትም ወንጌል ይህ ነው፡፡ 
 
 
አጥማቂው ዮሐንስ ለምን ተወለደ? 
 
በኢየሱስ ልናምን የምንችለው በማን በኩል ነው?
በአጥማቂው ዮሐንስ፡፡ 

በሚልክያስ 3፡1 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹እነሆ መልዕክተኛዬን እልካለሁ እርሱም መንገድን በፊቴ ያስተካክላል፡፡›› መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ ማንበብ ይኖርባችኋል፡፡ እግዚአብሄር መልዕክተኛውን ከኢየሱስ ፊት ለምን ላከው? አጥማቂው ዮሐንስ ከኢየሱስ 6 ወር ቀደም ብሎ ለምን ተወለደ? መጽሐፍ ቅዱስ ስለምን እንደሚናገር መረዳት ይገባናል፡፡ ብሉይ ኪዳን የሊቀ ካህኑን የአሮንን ተግባር ያትታል፡፡ አሮን የሙሴ ታላቅ ወንድም ነበር፡፡ እግዚአብሄርም እርሱንና ልጆቹን ካህናት አድርጎ ቀባቸው፡፡ ሌሎቹ ሌዋውያን ዕቃዎችን በማሰናዳት፣ ሕብስትን በመጋገር፣ ዱቄትን በመለወስ ከእነርሱ በታች ሆነው ሰሩ፡፡ የአሮን ልጆች ደግሞ በተቀደሰው ድንኳን ውስጥ መስዋዕትን ያቀርቡ ነበር፡፡  
የአሮን ልጆች የተቀቡት በመካከላቸው እኩል የሥራ ድርሻ እንዲኖራቸው ነው፡፡ ነገር ግን የስርየት ቀን በሆነው በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን የሕዝቡን ዓመታዊ ሐጢያቶች ለማስተሰረይ የሚቀርበውን መስዋዕት የሚያቀርበው ግን ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር፡፡  
በሉቃስ 1፡5 ላይ ስለ አጥማቂው ዮሐንስ ሐረግ የተጻፈ ታሪክ አለ፡፡ ኢየሱስን በትክክል ለመረዳት ይህንን የእግዚአብሄር መልዕክተኛ በትክክል ማስተዋል ይኖርብናል፡፡ ስለ ኢየሱስ ብዙ የማሰብ አዝማሚያ አለን፡፡ ነገር ግን ከእርሱ በፊት ስለመጣው አጥማቂው ዮሐንስ ብዙ ቸል እንላለን፡፡ እንድታስተውሉ ልረዳችሁ እወዳለሁ፡፡ 
‹‹የእግዚአብሄር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፡፡ እነሆ መንገድህን የሚጠርግ መልዕክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፡፡›› (ማርቆስ 1፡1-2) የሰማይ ወንጌል ሁሌም የሚጀምረው በአጥማቂው ዮሐንስ ነው፡፡  
ስለ አጥማቂው ዮሐንስ በሚገባ ስንማር የኢየሱስን የቤዛነት ወንጌል በግልጽ መረዳትና ማመን እንችላለን፡፡ ይህ የአገሮችን ሁኔታዎች ለመረዳት በመላው አለም የላክናቸውን አምባሳደሮች ከመስማት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ስለ አጥማቂው ዮሐንስ ስናውቅ የእግዚአብሄርን ቤዛነት በሚገባ መረዳት እንችላለን፡፡ 
ሆኖም በዚህ ዘመን በጣም ብዙ ክርስቲያኖች የዮሐንስን አስፈላጊነት አለማየታቸው ምንኛ ያሳዝናል! እግዚአብሄር አጥማቂውን ዮሐንስን የላከው ስለተሰላቸና የሚያደርገው ሌላ ነገር ስላጣ አይደለም፡፡ የአዲስ ኪዳን አራቱም ወንጌሎች በሙሉ ስለ ኢየሱስ ቤዛነት ከመናገራቸው በፊት ስለ አጥማቂው ዮሐንስ ይናገራሉ፡፡ 
የዘመኑ ወንጌላውያን ግን እርሱን ፈጽሞ ችላ ብለውት ለመዳን በኢየሱስ ማመን ብቻ በቂ እንደሆነ ለሰዎች ይናገራሉ፡፡ እነርሱ ሰዎችን በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ሐጢያተኞች ሆነው እንዲኖሩና በመጨረሻም ሲዖል እንዲወርዱ እየነዱዋቸው ነው፡፡ ክርስቲያኖች በሙሉ የአጥማቂውን ዮሐንስን ሚና ሳይረዱ በኢየሱስ ብቻ ቢያምኑ ክርስትና ወደ ዓለም ሐይማኖትነት ይዘቅጥ ነበር፡፡ እውነትን የማታውቁ ከሆነ እንዴት ከሐጢያቶቻቸው መዳን ትችላላችሁ? የማይቻል ነው፡፡   
የቤዛነት ወንጌል ያን ያህል ቀላል ያን ያህልም መናኛ አይደለም፡፡ በጣም ብዙ ሰዎች ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለእኛ ስለሞተ ቤዛነት ያረፈው በመስቀሉ ላይ ባለን እምነት እንደሆነ ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ሐጢያቶችን የማስተላለፉን የተሟላ እውነት ሳታውቁ በስቅለቱ ብቻ የምታምኑ ከሆነ እምነታችሁ ምንም ያህል ብርቱ ቢሆንም የዚህ ዓይነቱ እምነት ወደ ምሉዕ ደህንነት አያደርሳችሁም፡፡ 
እግዚአብሄር አጥማቂውን ዮሐንስን የላከው ቤዛነት እንዴት እንደደተፈጸመና ኢየሱስም የዓለምን ሐጢያቶች እንዴት እንደሚወስድ ዓለም ያውቅ ዘንድ ነው፡፡ ኢየሱስ በራሱ ላይ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ የወሰደ የእግዚአብሄር ልጅ መሆኑን የምንረዳው ሙሉውን እውነት ስናውቅ ብቻ ነው፡፡  
አጥማቂው ዮሐንስ ስለ ቤዛነት እውነት ነገረን፡፡ ኢየሱስ አምላክና እውነተኛ ብርሃን እንደሆነ ነገረን፡፡ እርሱ ያ ብርሃን እንዳልሆነ ነገር ግን እርሱ የብርሃን ምስክር እንደሆነ በግልጽ ተናገረ፡፡ በዮሐንስ 1 ላይም ኢየሱስ ክርስቶስን በማጥመቅ የቤዛነትን ወንጌል ያዘጋጀው እርሱ እንደነበረም መሰከረ፡፡   
አጥማቂው ዮሐንስ ስለ ቤዛነት የመሰከረው ምስክርነት ባይኖረን ኖሮ እንዴት በኢየሱስ ማመን እንችል ነበር? እኛ ኢየሱስን ፈጽሞ አላየነውም፡፡ የመጣነው ከተለያዩ ባህሎችና ሐይማኖቶች በመሆኑ የሆዋን አምላካችን አድርገን ማመኑ እንዴት ይቻል ነበር?  
በመላው ዓለም ላይ እንዲህ ያሉ የተለያዩ ሐይማኖቶች ያሉ በመሆናቸው ኢየሱስን እንዴት ማወቅ ይቻለን ነበር? ኢየሱስ በእርግጥም የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ በመውሰድ ያዳነን የእግዚአብሄር ልጅ መሆኑን እንዴት ማወቅ ይቻለን ነበር? 
ከመጀመሪያው የቤዛነትን ቃሎች ለማግኘትና ኢየሱስ አዳኛችን መሆኑን ለማወቅ ብሉይ ኪዳንን መመልከት ይኖርብናል፡፡ ትክክለኛ እምነት እንዲኖረን ትክክለኛ እውቀት ማግኘት ይኖርብናል፡፡ በኢየሱስ አምነን ለመዳን አጥማቂው ዮሐንስ የመሰከረለትን የቤዛነት ወንጌልና እርሱም በዚያ ውስጥ ያለውን ሚና ማወቅ ይኖርብናል፡፡ በኢየሱስ የተሟላ እምነት እንዲኖረን ስለ ቤዛነት እውነቱን ማወቅ ይኖርብናል፡፡  
ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- ‹‹እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፡፡›› በኢየሱስ ውስጥ ያለውን የቤዛነት እውነት ማወቅ ይኖርብናል፡፡ 
 
 
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ማስረጃዎች፡፡ 
 
አራቱ ወንጌሎች የሚጀምሩት ከምን ነጥብ ነው? 
ከመጥምቁ ዮሐንስ መምጣት ነው፡፡ 

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን ማስረጃዎች በሙሉ ለመመርመር ወደፊት እንግፋ፡፡ አራቱ ወንጌሎች ስለ አጥማቂው ዮሐንስ፣ ስለ ማንነቱ፣ ለምን ‹የሰው ዘር ወኪል› ወይም ‹ሊቀ ካህን› ተብሎ እንደተጠራ፣ በእርሱ በኩልም የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ እንዴት ወደ ኢየሱስ እንደተላለፉና ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ ወስዶ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ የሚናገሩትን እንመልከት፡፡     
አራቱም ወንጌሎች የሚጀምሩት በአጥማቂው ዮሐንስ በመሆኑ እውነታ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባናል፡፡ ዮሐንስ 1፡6 በወንጌል ውስጥ ከሚገኙት እጅግ ጠቃሚ እውነታዎች አንዱን ይጠቅሳል፡፡ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ የማስተላለፉን ተግባር ማን እንደፈጸመው ይነግረናል፡፡ ‹‹ከእግዚአብሄር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበር፡፡ ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ፡፡›› (ዮሐንስ 1፡6-7)   
ቃሉ እንዲህ ይላል፡- ‹ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ፡፡› እርሱ ‹ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ› መጣ፡፡ ብርሃኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህ ማለት ሁሉ በእርሱ ያምኑ ዘንድ ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ መመስከር ነበረበት ማለት ነው፡፡ አሁን እስቲ ማቴዎስ ምዕራፍ 3ን በቅርበት እንመልከት፡፡   
ማቴዎስ 3፡13-17 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ ዮሐንስ ግን፡- እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር፡፡ ኢየሱስም መልሶ፡- አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው፡፡ ያን ጊዜ ፈቀደለት፡፡ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃው ወጣ፡፡ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ፡፡ የእግዚአብሄርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፡፡ እነሆም በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡››    
 
የዮሐንስን የዘር ሐረግ መረዳት የሚኖርብንለምንድነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ የሰው ዘር ሁሉ ሊቀ ካህን መሆኑን ስለሚነግረን ነው፡፡  

አጥማቂው ዮሐንስ በዓለም ላይ ያሉትን ሐጢያቶች ስርየት በሙሉ ለመፈጸም ኢየሱስን አጠመቀው፡፡ ኢየሱስ ከዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀት ለደህንነታችን እጅግ አስፈላጊ ኩነት ነበር፡፡ ነገር ግን ሙሉውን እውነት በሚገባ ለመረዳት በመጀመሪያ አጥማቂውን ዮሐንስን በጥልቀት ማጥናት ይኖርብናል፡፡ 
ሉቃስ 1፡1-14 እንዲህ ይላል፡- ‹‹የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ ከመጀመሪያ በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን በእኛ ዘንድ ስለተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለሞከሩ እኔ ደግሞ ስለተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ተከትዬ በየተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ፡፡ በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፡፡ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፤ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ፡፡ ሁለቱም በጌታ ትዕዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ  በእግዚአብሄር ፊት ጻድቃን ነበሩ፡፡ ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ አልነበራቸውም፡፡ ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር፡፡ እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሄር ፊት ሲያገለግል እንደ ካህናት ስርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት፡፡ በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይፀልዩ ነበር፡፡ የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው፡፡ ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ ፍርሃትም ወደቀበት፡፡ መልአኩም እንዲህ አለው፡- ዘካርያስ ሆይ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ፡፡ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፡፡ ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፡፡ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፡፡››    
እዚህ ላይ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የሆነው ሉቃስ የዮሐንስን የዘር ሐረግ በዝርዝር ይነግረናል፡፡ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የሆነው ሉቃስ የዮሐንስን የዘር ሐረግ ከመጀመሪያው ጀምሮ አብራርቷል፡፡ ሉቃስ ባህሉ ሌላ ለሆነውና ስለ ጌታ ለማያውቀው ቴዎፍሎስ ለተባለ ሰው ወንጌልን አስተምሮት ነበር፡፡   
ስለዚህ የሐጢያተኞች አዳኝ ስለሆነው ኢየሱስ ያስተምረው ዘንድ ሉቃስ የአጥማቂውን ዮሐንስን የዘር ሐረግ በስፋት ሊያብራራለት እንደሚያስፈልገው አሰበ፡፡ እኛም ደግሞ ከተለያዩ ዘሮች የመጣን አሕዛቦች ስለሆንን ደረጃ በደረጃ በተለየ መንገድ ካልተብራራልን የኢየሱስን ደህንነት መረዳት አንችልም፡፡ ዝርዝሮቹ ምን እንደሆኑ ፈልገን እናግኝ፡፡   
ሉቃስ 1፡5-9 እንዲህ ይተርካል፡- ‹‹በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፡፡ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፤ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ፡፡ ሁለቱም በጌታ ትዕዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ  በእግዚአብሄር ፊት ጻድቃን ነበሩ፡፡ ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ አልነበራቸውም፡፡ ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር፡፡ እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሄር ፊት ሲያገለግል እንደ ካህናት ስርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት፡፡››  
እዚህ ላይ ዘካርያስ በክህነቱ ስርዓት መሰረት እግዚአብሄርን እያገለገለ ሳለ አንድ ኩነት ተከሰተ፡፡ ሉቃስ ዘካርያስ የአሮን ዘር እንደነበር በግልጽ መስክሮአል፡፡ ዘካርያስ በየትኛው ክፍል ተራ ውስጥ ነበር? ይህ በጣም ወሳኝ ነጥብ ነው፡፡ 
እርሱ እንዲህ አብራራ፡፡ ‹‹እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሄር ፊት ሲያገለግል፡፡›› ሉቃስ ስለ ዘካርያስ በሚገባ ያውቅ ስለነበር ዘካርያስንና ኤልሳቤጥን በመጥቀስ የቤዛነቱን ወንጌል እንዳብራራ ማየት እንችላለን፡፡  
አጥማቂው ዮሐንስ ለዘካርያስና ከአሮን ሴት ልጆች አንዷ ለነበረችው ለሚስቱ ለኤልሳቤጥ ተወለደ፡፡ አሁን የዮሐንስን አባት የዘካርያስን የዘር ሐረግ እንመልከት፡፡ 
 
 
የአጥማቂው ዮሐንስ የዘር ሐረግ፡፡ 
 
አጥማቂው ዮሐንስ የማን ዘር ነበር?
የሊቀ ካህኑ የአሮን ነው፡፡

የአጥማቂውን የዮሐንስን የዘር ሐረግ ለመረዳት ከብሉይ ኪዳን 1ኛ ዜና 24፡1-19ን ማንበብ ይኖርብናል፡፡ 
‹‹የአሮንም ልጆች ሰሞን ይህ ነው፡፡ የአሮን ልጆች ናዳብ፣ አብዩድ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር ነበሩ፡፡ ናዳብና አብዩድ ግን ልጆች ሳይወልዱ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፡፡ አልዓዛርና ኢታምርም ካህናት ሆኑ፡፡ ዳዊትም ከአልዓዛር ልጆች ከሳዶቅ ጋር፤ ከኢታምርም ልጆች ከአቤሜሌክ ጋር ሆኖ እንደ አገልግሎታቸው ሥርዓት ከፍሎ መደባቸው፡፡ የአልዓዛርም ልጆች ከአለቆች ከኢታምር ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፡፡ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች አሥራ ስድስት፤ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው አሥራ ስምንት አለቆች ነበሩ፡፡ ከአልዓዛርና ከኢታምርም ልጆች መካከል የመቅደሱና የእግዚአብሄር አለቆች ነበሩና፡፡ እነዚህና እነዚያ እንዲህ በዕጣ ተመደቡ፡፡ ከሌዋውያንም ወገን የነበረው የናትናኤል ልጅ ጸሐፊው ሸማያ በንጉሡና በአለቆቹ ፊት በካህኑ በሳዶቅና በአብያታርም ልጅ በአቤሜሌክ ፊት ጻፋቸው፡፡ አንዱንም የአባት ቤት ለአልዓዛር አንዱንም ለኢታምር ጻፈ፡፡ 
መጀመሪያውም ዕጣ ለዩአሪብ ወጣ፡፡ ሁለተኛው ለዮዳኤ፣ ሦስተኛው ለካሪም፣ አራተኛው ለሥዖሪም፣ አምስተኛው ለመልክያ፣ ስድስተኛው ለሚያሚን፣ ሰባተኛው ለአቆስ፣ ስምንተኛው ለአብያ፣ ዘጠነኛው ለኢያሱ፣ አሥረኛው ለሴኬንያ፣ አሥራ አንደኛው ለኤልያሴብ፣ አሥራ ሁለተኛው ለያቂም፣ አሥራ ሦስተኛው ለኦፓ፣ አሥራ አራተኛው ለየሼአብ፣ አሥራ አምስተኛው ለቢልጋ፣ አሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፣ አስራ ሰባተኛው ለኤዚር፣ አሥራ ስምንተኛው ለሃፊጼጽ፣ አስራ ዘጠነኛው ለፈታያ፣ ሃያኛው ለኤዜቄል፣ ሃያ አንደኛው ለያኪን፣ ሃያ ሁለተኛው ለጋሙል፣ ሃያ ሦስተኛው ለድላያ፣ ሃያ አራተኛው ለመዓዝያ፡፡ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሄር እንዳዘዘ አባታቸው አሮን እንደሰጣቸው ሥርዓት ወደ እግዚአብሄር ቤት የሚገቡበት የአገልግሎታቸው ሥርዓት ይህ ነበር፡፡››
ቁጥር 10ን እንደገና እናንብብ፡፡ ‹‹ሰባተኛው ለአቆስ ስምንተኛ ለአብያ፡፡›› በንጉሥ ዳዊት ዘመን በጣም ብዙ ካህናት ስለነበሩ ስርዓቱን ተከትሎ ለሚከናወኑት አገልግሎቶች ስርዓተ ደንብ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነበር፡፡ ስለዚህ መስዋዕቱ በስርዓት ይቀርብ ዘንድ ዳዊት ለአሮን ልጆች ለእያንዳንዳቸው ክፍለ ተራዎችን መደበ፡፡ (ሁላችሁም እንደምታውቁት አሮን የሙሴ ታላቅ ወንድም ነበር፡፡ እግዚአብሄር በእስራኤል ሕዝብ ፊት ሙሴን ወኪሉ፤ አሮንን ደግሞ የተቀደሰው ድንኳን ሊቀ ካህን አድርጎ ሾማቸው፡፡)      
ሌሎቹ ሌዋውያን በሙሉ ከካህናቱና ከአሮን በታች ነበሩ፡፡ ካህናት የሆኑት ልጆቹም በእግዚአብሄር ፊት በመስዋዕቶቹ ሁሉ ላይ ተሹመው ነበር፡፡ ዳዊት ክፍለ ተራዎችን ከመመደቡ በፊት የአሮን ዘሮች የነበሩት ካህናት በየጊዜው ዕጣዎችን መጣል ነበረባቸው፡፡ ይህም ብዙ ግራ መጋባትን ፈጥሮ ነበር፡፡ 
ስለዚህ ዳዊት እያንዳንዱን ሰሞን ስርዓት በማስያዝ አንድ ተራ ክፍል አዘጋጀ፡፡ በአንድ ክፍለ ተራ ውስጥ ከአሮን የልጅ ልጆች የሚጀምሩ ሃያ አራት ሰሞኖች የነበሩ ሲሆን ስምንተኛው አብያ ነበር፡፡ ቃሉ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከአብያ ወገን የሆነ ዘካርያስ የሚባል ካህን ነበረ፡፡›› ስለዚህ ዘካርያስ ከአብያ ክፍል የሆነ ካህን ነበር፡፡ እነርሱ ሁለቱም የሊቀ ካህኑ የአሮን ዘሮች ነበሩ፡፡   
የአጥማቂው ዮሐንስ አባት ከአብያ ክፍል የሆነው ካህኑ ዘካርያስ ነበር፡፡ እነርሱ የሚጋቡት ከቤተሰቦቻቸው አባሎች ጋር እንደነበር ከመጽሐፍ ቅዱስ እናውቃለን፡፡ 
ያዕቆብም ያገባው ከእናቱ ወገን የአጎቱን ሴት ልጅ ነበር፡፡ ይህ ማብራሪያ ጥልቅ ጠቀሜታ ያለው የዘር ሐረግ ነው፡፡ ‹‹ከአብያ ወገን የሆነ ዘካርያስ የሚባል ካህን ነበር›› ይላል፡፡ 
ስለዚህ እርሱ በእርግጥም የአሮን ዘር ነበር፡፡ ማን? የአጥማቂው ዮሐንስ አባት ዘካርያስ፡፡ ይህ የኢየሱስን ቤዛነት፣ የአጥማቂውን ዮሐንስን አገልግሎትና የዓለም ሐጢያቶች ወደ ኢየሱስ መተላለፋቸውን የሚያብራራ ጠቃሚ እውነት ነው፡፡  
 
 
ካህናት ሆነው ሊያገለግሉ የሚችሉት የአሮን ልጆች ብቻ ናቸው፡፡ 
 
በብሉይ ኪዳን ዘመን ሊቀ ካህናት ሆኖ ማገልገል የቻለው ማን ነበር? 
አሮንና የእርሱ የተሾሙ ዝርያዎች ብቻ ነበሩ፡፡ 

ታዲያ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የአሮን ልጆች ካህናት ሆነው ማገልገል እንደሚገባቸው የተዘረዘረው የት ቦታ ነው? እስቲ እንመልከተው፡፡ 
ዘሁልቁ 20፡22-29 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከቃዴስም ተጓዙ፡፡ የእስራኤልም ልጆች ማህበር ሁሉ ወደ ሖር ተራራ መጡ፡፡ እግዚአብሄርም ሙሴንና አሮንን በኤዶምያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፡- አሮን ወደ ወገኑ ይከማች፡፡ በመሪባ ውሃ ዘንድ በቃሌ ላይ ስላመጻችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደ ሰጠኋት ምድር አይገባም፡፡ አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሖር ተራራ ላይ አምጣቸው፡፡ ከአሮንም ልብሱን አውጣ፡፡ ልጁንም አልዓዛርን አለበሰው፡፡ አሮንም በዚያ በተራራው ራስ ላይ ሞተ፡፡ ሙሴና አልዓዛርም ከተራራው ወረዱ፡፡ ማህበሩም ሁሉ አሮን እንደሞተ ባየ ጊዜ የእስራኤል ቤት ሁሉ ለአሮን ሠላሳ ቀን አለቀሱ፡፡››  
በዘጸአት ውስጥ የእግዚአብሄር ቃል የሊቀ ካህኑ የአሮን ልጆች ክህነቱን መውሰድ እንደሚገባው፤ የተሾመውም ልጅ አባቱ እንዳደረገው 30 አመት ሲሆነው ሊቀ ክህነቱን መውሰድ እንደነበረበት በመናገር የመዘገበው ነገር አለ፡፡  
ዘጸአት 28፡1-5 እንዲህ ይላል፡- ‹‹አንተም ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ ካህናት ይሆኑልኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅርብ፡፡ አሮንን፤ የአሮንንም ልጆች ናዳብን፣ አብዩድንም፣ አልዓዛርንም፣ ኢታምርንም አቅርብ፡፡ የተቀደሰውንም ልብስ ለክብርና ለጌጥ እንዲሆን ለወንድምህ ለአሮን ሥራለት፡፡ አንተም ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ አሮን ቅዱስ ይሆን ዘንድ ልብስ እንዲሰሩለት የጥበብ መንፈስ ለሞላሁባቸው፣ በልባቸው ጥበበኞች ለሆኑት ሁሉ ተናገር፡፡ የሚሰሩአቸውም ልብሶች እነዚህ ናቸው፡፡ የደረት ኪስ፣ ኤፉድም፣ ቀሚስም፣ ዝንጉርጉር ሸሚዝም፣ መጠምጠሚያም፣ መታጠቂያም፡፡ እነዚህም ካህናት ይሆኑልኝ ዘንድ ለወንድምህ ለአሮን ለልጆቹም የተቀደሰ ልብስ ያድርጉ፡፡ ወርቅንም፣ ሰማያዊና ሐምራዊ፣ ቀይም ግምጃ፣ ጥሩ በፍታም ይውሰዱ፡፡››   
እግዚአብሄር የሙሴን ወንድም አሮንን ሊቀ ክህነት ውስጥ መደበው፡፡ ክህነት ለሌላ ለማንም ሰው ክፍት አልነበረም፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን አሮንን ሊቀ ካህን አድርጎ እንዲሾመውና እርሱ በገለጠው መሰረትም ትክክለኛ ልብስ እንዲያዘጋጅለት አዘዘው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ፈጽሞ መዘንጋት የለብንም፡፡    
በዘጸአት 29፡1-9 ላይም እንዲህ ይላል፡- ‹‹እኔንም በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀድሳቸው ዘንድ የምታደርግባቸው ነገር ይህ ነው፡፡ ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች ትወስዳለህ፡፡ ቂጣ እንጀራ፣ በዘይትም የተለወሰ የቂጣ እንጎቻ፣ በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ ከመልካም ስንዴ ታደርጋለህ፡፡ በአንድ ሌማትም ታደርጋቸዋለህ፡፡ ከወይፈኑና ከሁለቱ አውራ በጎች ጋር በሌማቱ  ታቀርባቸዋለህ፡፡ አሮንንና ልጆቹንም ወደ መገናኛው ድንኳን ታቀርባቸዋለህ፡፡ በውሃም ታጥባቸዋለህ፡፡ ልብሶችን ወስደህ ለአሮን ሸሚዝና የኤፉድ ቀሚስ ኤፉድም የደረት ኪስም ታለብሰዋለህ፡፡ በብልሃትም በተጠለፈ ቋድ ታስታጥቀዋለህ፡፡ መጠምጠሚያውንም በራሱ ላይ ታደርጋለህ፡፡ የተቀደሰውንም አክሊል በመጠምጠሚያው ላይ ታኖራለህ፡፡ የቅብዓትንም ዘይት ወስደህ በራሱ ላይ ታፈሰዋለህ ትቀባውማለህ፡፡ ልጆቹንም ታቀርባቸዋለህ፤ ሸሚዞችንም ታለብሳቸዋለህ፡፡ አሮንንና ልጆቹንም በመታጠቂያ ታስታጥቃቸዋለህ፡፡ ቆብንም ታለብሳቸዋለህ፡፡ ለዘላለም ሥርዓትም ክህነት ይሆንላቸዋል፡፡ እንዲሁም አሮንንና ልጆቹን ትክናቸዋለህ፡፡››     
አሮንንና ልጆቹን በመታጠቂያ ታስታጥቃቸዋለህ፡፡ በራሳቸውም ላይ ቆቦችን ታደርግላቸዋለህ፡፡…ክህነቱም በዘላለም ስርዓት የእነርሱ ነው፡፡ አሮንንና ልጆቹን ትቀድሳቸዋለህ፡፡…እግዚአብሄር ክህነቱን ለዘላለም ለማገልገል የሚቀድሱት አሮንና ልጆቹ እንደሆኑ በግልጽ ተናግሮዋል፡፡ ‹‹ለዘላለም ስርዓት›› ብሎ በግልጽ ሲናገር ክህነቱ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም ከመጣ በኋላ እንኳን ይሰራል ማለት ነው፡፡ 
ሉቃስ ዘካርያስ የሊቀ ካህኑ የአሮን ዘር እንደነበር በስፋት አብራራ፡፡ ዘካርያስ በጌታ መቅደስ ውስጥ በእግዚአብሄር ፊት ካህን ሆኖ እያገለገለ ሳለ መልአክ ተገልጦ ጸሎቱ እንደተሰማለትና ሚስቱም ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ እንደምትወልድለት ነገረው፡፡  
ዘካርያስ ይህንን ማመን ስላዳገተው ‹‹ምስቴ በዕድሜዋ አርጅታለችና እንዴት ልጅ መውለድ ትችላለች?›› አለ፡፡ በጥርጣሬው ምክንያትም እግዚአብሄር ቃሎቹ እንደሚፈጸሙ ሊያሳየው ዲዳ አደረገው፡፡ 
ጊዜውን ጠብቆም ሚስቱ አረገዘች፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ድንግሊቱ ማርያምም ደግሞ እንደዚሁ አረገዘች፡፡ ሁለቱም ክስተቶች እግዚአብሄር ለደህንነታችን ያዘጋጃቸው ሥራዎች ነበሩ፡፡ እርሱ ጎስቋላውን የሰው ዘር ለማዳን ባሪያውን ዮሐንስንና አንድያ ልጁን ኢየሱስን ወደዚህ ዓለም መላክ ነበረበት፡፡  
ስለዚህ እግዚአብሄር በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች ይድኑ ዘንድ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለማስተላለፍ ልጁ በዮሐንስ እንዲጠመቅ አደረገው፡፡ 
 
 
የእግዚአብሄር ልዩ ችሮታ!
 
ለቤዛነት ሥራው እግዚአብሄር ከኢየሱስ በፊት ያዘጋጀው ማንን ነበር? 
አጥማቂውን ዮሐንስን፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ሥጋ የተወለደ አዳኝ ነበር፡፡ ማርያም ከይሁዳ ነገድ ለሆነው ለዮሴፍ ታጭታ ነበር፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ ከሊቀ ካህኑ ከአሮን ቤት መወለድ እንደነበረበት ሁሉ ኢየሱስም የእግዚአብሄርን ቃል ኪዳን ለመፈጸም በይሁዳ ዘር በኩል መወለድ ነበረበት፡፡  
እግዚአብሄር እነዚህ ሁለቱ በዚህ ዓለም እንዲወለዱ አደረገ፡፡ በዚያ ቅደም ተከተል መሰረትም ዮሐንስ ከኢየሱስ በፊት ተወለደ፡፡ ዮሐንስ የተወለደው ኢየሱስን ለማጥመቅና የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ ለማስተላለፍ ነበር፡፡ የሊቀ ካህን ዘርም በብሉይና በአዲስ ኪዳናት ላይ የተገባውን የእግዚአብሄር ቃል ኪዳን ለመፈጸም የስርየት መስዋዕትን ማቅረብ ነበረበት፡፡ ሰዎች ሁሉ ይድኑ ዘንድ የኢየሱስ የቤዛነት ወንጌል በትክክል ተግባራዊ መደረግ ነበረበት፡፡  
በዘጸአት ውስጥ እግዚአብሄር ለእስራኤሎች ሕጉንና ኪዳኖቹን ሰጣቸው፡፡ የእግዚአብሄር ሕጎችና የመገናኛው ድንኳን ስርዓተ መስዋዕት፣ የካህናቶች ልብሶችና ወደ ካህናት ልጆች የሚተላለፈው የክህነት መተኪያም እንደዚሁ ተሰጥተዋቸው ነበር፡፡ እግዚአብሄር አሮንንና ዘሮቹን ለዘላለም ሊቀ ካህናት አድርጎ ሾማቸው፡፡ 
ስለዚህ የአሮን ዘሮች በሙሉ መስዋዕቶችን ማቅረብ ይችሉ ነበር፡፡ ሊቀ ካህናትም የሚወጡት ከአሮን ቤት ብቻ ነበር፡፡ ይህ ለምን እንደሆነ ታያላችሁን? 
እግዚአብሄር ከብዙዎቹ የአሮን ዘሮች መካከል ዘካርያስ የተባለን አንድ ካህንና ሚስቱን ኤልሳቤጥን መረጠ፡፡ እርሱ እንዲህ አለ፡- ‹‹እነሆ በፊትህ መልዕክተኛዬን እልካለሁ፡፡›› እግዚአብሄር ለዘካርያስ ኤልሳቤጥ ልጅ ይኖራት ዘንድ እንደሚያስችላትና ስሙንም ዮሐንስ ብሎ እንደሚሰይመው ነገረው፡፡ ልጁ እስከሚወለድና ስም እስኪሰጠው ድረስ በእርሱ ትዕዛዝ ዲዳ በመሆኑም በጣም ተገርሞ ነበር፡፡
በእርግጥም በቤቱ ውስጥ ወንድ ልጅ ተወለደ፡፡ በእስራኤል ልማድ መሰረት ለልጁ ስም የሚሰየምበት ጊዜ ሲደርስ ልጁ በአባቱ ወይም ከዘመዶቹ በአንዱ ሰው ስም ይሰየም ነበር፡፡ 
‹‹የኤልሳቤጥ የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ፡፡ ወንድ ልጅም ወለደች፡፡ ጎረቤቶችዋም ዘመዶችዋም ጌታ ምሕረቱን እንዳገነነላት ሰምተው ከእርስዋ ጋር ደስ አላቸው፡፡ በስምንተኛውም ቀን ሕጻኑን ሊገርዙት መጡ፡፡ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ወደዱ፡፡ እናቱ ግን መልሳ አይሆንም ዮሐንስ ይባል እንጂ አለች፡፡ እነርሱም ከወገንሽ ማንም በዚህ ስም የተጠራ የለም አሉአት፡፡ አባቱንም ማን ሊባል እንዲወድ ጠቀሱት፡፡ ብራናም ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ፡፡ ሁሉም አደነቁ፡፡ ያን ጊዜ አፉ ተከፈተ፤ መላሱም ተፈታ፡፡ እግዚአብሄርንም እየባረከ ተናገረ፡፡ ለጎረቤቶቻቸውም ሁሉ ፍርሃት ሆነ፡፡ ይህም ሁሉ ነገር በይሁዳ በተራራማው አገር ሁሉ ተወራ፡፡ የሰሙትም ሁሉ፡- እንኪያ ይህ ሕጻን ምን ይሆን? እያሉ በልባቸው አኖሩት፡፡ የጌታ እጅ ከእርሱ ጋር ነበረችና፡፡›› (ሉቃስ 1፡57-66)
ልጁ በተወለደ ጊዜ ዘካርያስ ገናም ዲዳ ነበር፡፡ ለልጁ ስም የመሰየም ጊዜ ሲደርስ ዘመዶቹ ልጁ ዘካርያስ ተብሎ መጠራት እንደሚገባው አሳብ አቀረቡ፡፡ እናቱ ግን ስሙ ዮሐንስ መሆን እንዳለበት ተሟገተች፡፡ በዚህ ጊዜ ዘመዶች የሆኑት በቤተሰቡ ውስጥ በዚያ ስም የተጠራ ሰው ስለሌለ ልጁ በአባቱ ስም መጠራት እንዳለበት ተናገሩ፡፡
ኤልሳቤጥ ስሙን በሚመለከት በተሟገተች ጊዜ ዘመዶች የሆኑት ወደ ዘካርያስ ሄደው የሕፃኑ ስም ማን መሆን እንዳለበት ጠየቁት፡፡ ዘካርያስ ገናም ዲዳ ስለነበር መጸፊያ ብራና ለምኖ ‹ዮሐንስ› ብሎ ጻፈ፡፡ ዘመዶች የሆኑት ሁሉ በዚህ ያልተለመደ የስም ምርጫ ተገረሙ፡፡
ከስም አወጣጡ በኋላ ግን የዘካርያስ አንደበት ወዲያውኑ ተከፈተ፡፡ እርሱም እግዚአብሄርን አመሰገነ፡፡ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ትንቢት ተናገረ፡፡ በዚህም ሉቃስ በዘካርያስ ቤት ስለተወለደው አጥማቂው ዮሐንስ ይነግረናል፡፡ ‹‹ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፡፡›› በእግዚአብሄር ልዩ ችሮታ የሰው ዘር ወኪል የአሮን ዘር ለሆነው ለዘካርያስ ተወለደለት፡፡
እግዚአብሄር በአጥማቂው ዮሐንስና በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሰውን ዘር ደህንነት ፈጸመ፡፡ እኛ በዮሐንስና በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በተፈጸመው የቤዛነት ሥራ በማመን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ድነናል፡፡ 
 
 

የኢየሱስ ጥምቀት፡፡ 

 
ኢየሱስ በዮሐንስ የተጠመቀው ለምን ነበር? 
የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድ ነው፡፡  

አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደነበርና ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደ መሰከረ፡፡ የእግዚአብሄርን ማዳን ለመመስከር የተላከው የእግዚአብሄር ባርያ የሆነው አጥማቂው ዮሐንስ ነበር፡፡ ይህ ማለት እግዚአብሄር አዳኛችን እንደሆነ ራሱ አይነግረንም ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በቤተክርስቲያን ውስጥ በባሪያዎቹና በዳኑት ሕዝቦቹ አንደበት ሁሉ ይሰራል፡፡
እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡- ‹‹ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፡፡ የተቀጠረችበት ወራት እንደተፈጸመ ሐጢአትዋም እንደተሰረየ ከእግዚአብሄርም እጅ ስለ ሐጢአትዋ ሁለት እጥፍ እንደተቀበለች ወደ እርስዋ ጩሁ፡፡ ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፡፡ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች፡፡›› (ኢሳይያስ 40፡2,8) 
እግዚአብሄር ክርስቶስ ከመወለዱ ከሰባት መቶ አመታት በፊት አስቀድሞ ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ሐጢያተኞች አይደላችሁም፡፡ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ ይቅር ብያለሁ፡፡ ጦርነቱም አብቅቷል›› በማለት ቃል ገብቷል፡፡ ስለዚህ የቤዛነት ወንጌል ድምጽ ለእኛ መጮሁን ቀጥሎዋል፡፡ የመዘጋጀት ወንጌል ተብሎ የሚጠራው ይህ ነው፡፡ 
የአጥማቂውን ዮሐንስን ሥራዎች ስናስተውልና የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ በአጥማቂው ዮሐንስ አማካይነት ወደ ኢየሱስ እንደተላለፉ በተጨባጭ ስንረዳ ሁላችንም ከሐጢያቶቻችን ነጻ መውጣት እንችላለን፡፡  
አራቱም ወንጌሎች በሙሉ ስለ አጥማቂው ዮሐንስ ይነግሩናል፡፡ የመጨረሻው የብሉይ ኪዳን ነቢይ ሚልክያስም አጥማቂው ዮሐንስ እግዚአብሄር ያዘጋጀው ነቢይ እንደነበር መሰከረ፡፡ አዲስ ኪዳን የሚጀምረው በአጥማቂው ዮሐንስ ውልደትና በእርሱ አማካይነት በተላለፈው ሐጢያት ነው፡፡ 
ታዲያ ለምን አጥማቂው ዮሐንስ ብለን እንጠራዋለን? እንደዚያ የምንጠራው ኢየሱስን ስላጠመቀው ነው፡፡ ጥምቀት ማለት ምን ማለት ነው? ጥምቀት ማለት ‹ማስተላለፍ፣ መቀበር፣ መታጠብ› ማለት ነው፡፡ ከብሉይ ኪዳን ‹እጆችን መጫን› ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ 
በብሉይ ኪዳን አንድ ሰው ሐጢያት ሲሰራ እጆቹን በራሱ ላይ በመጫን ሐጢያቶቹን ነውር በሌለው የመስዋዕት እንስሳ ላይ ያስተላልፋል፡፡ መስዋዕቱም እነዚያን ሐጢያቶች ይዞ ይሞታል፡፡ ‹እጆችን መጫን› ማለት ‹ማስተላለፍ› ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ‹እጆችን መጫን› እና ‹ጥምቀት› በግልጽ የተለያዩ ቢሆኑም ተመሳሳይ አንደምታዎች አሉዋቸው፡፡ 
ታዲያ የኢየሱስ ጥምቀት ትርጉም ምንድነው? የእርሱ ጥምቀት የሐጢያት ስርየታችንን የምንቀበልበት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሐጢያት ‹በእጆች መጫን› አማካይነት ወደ መስዋዕቱ የሚተላለፍበትም ሕግ አዘጋጅቷል፡፡ ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሐጢያተኞች ሐጢያቶቻቸውን በራሱ ላይ ለማስተላለፍ እጆቻቸውን በመስዋዕቱ ራስ ላይ መጫን ነበረባቸው፡፡ ከዚያም ጉሮሮውን ማረድ ነበረባቸው፡፡ ካህናቱም ደሙን በሚቃጠለው መስዋዕት መሰዊያ ቀንዶች ላይ መቀባት ነበረባቸው፡፡ በየቀኑ የሚሰሩት ሐጢያቶች ስርየት የሚያገኙት በዚህ መልኩ ነው፡፡
ለአመታዊዎቹ ሐጢያቶቻቸውስ ስርየትን የሚያገኙት እንዴት ነበር? 
ይህንን በሚመለከት ሊቀ ካህኑ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ መስዋዕትን ያቀርባል፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ የተወለደው ከአሮን ቤት በመሆኑ ሊቀ ካህን መሆኑ ትክክል ነበር፡፡ እግዚአብሄርም በገባው የቤዛነት ተስፋው መሰረት የመጨረሻው ሊቀ ካህን ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ወሰነው፡፡
አጥማቂው ዮሐንስ የሰው ዘር ሁሉ ወኪልና የመጨረሻው ሊቀ ካህን የሆነው አዲስ ኪዳን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ በመጠናቀቁ ነው፡፡ አሮን በብሉይ ኪዳን የሕዝቡን ሐጢያቶች እንዳስተሰረየ ሁሉ በአዲስ ኪዳን የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ ማስተላለፍ የቻለ ከአጥማቂው ዮሐንስ ሌላ ማነው? አጥማቂው ዮሐንስ የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ሊቀ ካህንና የሰው ዘር ወኪል በመሆኑ ኢየሱስን ባጠመቀው ጊዜ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ አስተላለፈ፡፡  
ዮሐንስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ ስላስተላለፈ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን ሊያድነን ይችላል፡፡ ኢየሱስ ሐጢያተኞችን በሙሉ ለማዳን በግ ሆነ፡፡ በዚህም እግዚአብሄር እንዳቀደው የቤዛነትን ሥራ ፈጸመ፡፡ ኢየሱስ አጥማቂው ዮሐንስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ ያስተላለፈ የመጨረሻው ሊቀ ካህን እንደሆነ ነግሮናል፡፡  
ኢየሱስ ራሱ ይህንን ማድረግ ያልቻለው ለምንድነው? ለምን አጥማቂው ዮሐንስ አስፈለገው? አጥማቂው ዮሐንስ በስድስት ወራት ቀድሞ የተወለደበት ምክንያት አለ፡፡ ይህም የብሉይ ኪዳንን ሕግና ተስፋዎቹን ለመፈጸም ነበር፡፡ 
ኢየሱስ ከድንግል ማርያም ተወለደ፡፡ አጥማቂው ዮሐንስም ኤልሳቤጥ ከተባለች ያረጀችና መካን ሴት ተወለደ፡፡ 
እነዚህ የእግዚአብሄር ሥራዎች ነበሩ፡፡ ያቀዳቸውም ሐጢያተኞችን በሙሉ ለማዳን ነበር፡፡ እርሱ እኛን ከሐጢያት ጋር ከሚደረግ የዘላለም ጦርነትና በሐጢያተኛ ተፈጥሮዋችን ከሚገጥሙን መከራዎች ሊያድነን ባርያውን ዮሐንስን ከዚያም ልጁን ኢየሱስን ላከ፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ የተላከው የሰው ዘር ወኪል፤ የመጨረሻው ሊቀካሀን ሆኖ ነበር፡፡ 
 
 
ከሴቶች የተወለደ እጅግ ታላቁ ሰው፡፡ 
 
በምድር ላይ እጅግ ታላቁ ሰው ማን ነበር? 
አጥማቂው ዮሐንስ፡፡:

ማቴዎስ 11፡7-14ን እንመልከት፡- ‹‹እነዚያም ሲሄዱ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ፡፡ እንዲህም አለ፡- ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ? ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸንበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ፡፡ ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን፡፡ እነሆ መንገድህን   በፊትህ የሚጠርግ መልዕክተኛዬን እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና፡፡ እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም፡፡ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል፡፡ ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፤ ግፈኞችም ይናጠቋታል፡፡ ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፡፡ ልትቀበሉትስ ብትወዱ ሊመጣ ያለው ኤልያስ ይህ ነው፡፡››   
ሰዎች ‹‹እናንተ የእፉኝት ልጆች ንስሐ ግቡ!›› እያለ የሚጮኸውን አጥማቂውን ዮሐንስን ለማየት ወደ ምድረ በዳ ወጡ፡፡ ኢየሱስም እንዲህ አለ፡- ‹‹ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ፡፡››  
ኢየሱስም ራሱ የዮሐንስን ታላቅነት መሰከረ፡፡ ኢየሱስ ‹‹ምን ልታዩ ወጣችሁ? የግመል ጠጉር የለበሰንና ላንቃው እስኪሰነጠቅ ድረስ የሚጮህን ሰው? እርሱ የግመል ጠጉር መልበስ አለበት፡፡ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰን ሰው? እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ፡፡ እርሱ ግን ከንጉሥም ይበልጣል›› በማለት መሰከረ፡፡ ‹‹እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ፡፡ ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን፡፡››   
በጥንት ዘመን ነቢያት ከነገስታቶች የሚበልጡ ሆነው ይቆጠሩ ነበር፡፡ አጥማቂው ዮሐንስም ከንጉሥ የሚበልጥ ከነቢይም የላቀ ነበር፡፡ እርሱ ከብሉይ ኪዳን ነቢያቶችም ሁሉ የሚበልጥ ነበር፡፡ እንዲያውም የመጨረሻው ሊቀ ካህንና የሰው ዘር ወኪል የሆነው ዮሐንስ ከመጀመሪያው ሊቀ ካህን ከአሮንም የበለጠ ጠቃሚ ሰው ነበር፡፡ ኢየሱስ ራሱ ዮሐንስ እንደዚህ አይነት ሰው እንደነበር መሰከረ፡፡   
የሰው ዘር ወኪል ማነው? ከራሱ ከክርስቶስ ውጪ በምድር ላይ እጅግ ታላቁ ሰው ማነው? አጥማቂው ዮሐንስ ነው፡፡ ‹‹አዎን እላችኋለሁ ከነብይም የሚበልጠውን፡፡ እነሆ መልዕክተኛዬን እልካለሁ፡፡ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፡፡››  
አጥማቂው ዮሐንስ ከሐጢያት ጋር የሚደረገው ጦርነት እንዳበቃ መሰከረ፡፡ ‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢያት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ፡፡›› ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች እንደወሰደ የመሰከረው አጥማቂው ዮሐንስ ነበር፡፡ 
በማቴዎስ 11፡11 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹እውነት እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም፡፡›› ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከአጥማቂው ዮሐንስ የሚበልጥ ተገኘቶ ነበርን?  
‹ከሴቶች መወለድ› ማለት ምን ማለት ነው? ይህ የሚያመላክተው የሰውን ዘር ሁሉ ነው፡፡ ከአዳምና ከሔዋን በስተቀር ሰዎች ሁሉ ከሴቶች የተወለዱ ናቸው፡፡ አዎ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከአጥማቂው ዮሐንስ የሚበልጥ ሰው አልተነሳም፡፡ ስለዚህ እርሱ የመጨረሻው ሊቀ ካህንና የሰው ዘር ወኪል ነው፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ ሊቀ ካህን፣ ነቢይና የሰው ዘር ሁሉ ወኪል ነበር፡፡   
በብሉይ ኪዳን አሮንና ልጆቹ ለዘላለም እንዲያገለግሉ በእግዚአብሄር ተሹመው ነበር፡፡ ሐጢያቶች በሙሉ በአሮንና በልጆቹ አማካይነት መንጻት ነበረባቸው፡፡ ይህም እግዚአብሄር ባዘዘው መሰረት ነበር፡፡ 
አንዳንድ ሌሎች ሌዋውያን ቀርበው በእነርሱ ክህነት ውስጥ ጣልቃ ለመግባት ቢደፍሩ በእርግጥም ይሞታሉ፡፡ እነርሱ ማድረግ ያለባቸው በመሰዊያው ላይ ለሚነደው እሳት ማገዶ መሰብሰብ፣ የእንሰሶችን ቆዳ መግፈፍ፣ ስቡን መለየት፣ አንጀቶችን ማጽዳት፣ ቆሻሻውን ከሰፈሩ ውጪ መጣል ነው፡፡ የካህናትን ሥራ ለመስራት ቢደፍሩ ይሞታሉ፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ሕግ ነው፡፡ መስመሩን ማለፍ አይችሉም፡፡     
በምድር ላይ ከአጥማቂው ዮሐንስ የሚበልጥ ሰው አልተነሳም፡፡ እርሱ ከሟች ሰዎች መካከል እጅግ ታላቅ ሰው ነው፡፡ ‹‹ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፡፡ ግፈኞችም ይናጠቋታል፡፡›› 
የሰው ዘር ቤዛነት የተፈጸመው አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስን ባጠመቀው ጊዜ ነበር፡፡ በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎችም በእምነት ጻድቃን ስለሆኑ መንግሥተ ሰማይ መግባት ይችላሉ፡፡ 
አሁን የዮሐንስ አባት ስለ ልጁ የመሰከረውን እንመልከት፡፡ 
 
 
የዮሐንስ አባት የዘካርያስ ምስክርነት፡፡ 
 
ዘካርያስ ስለ ልጁ የተነበየው ምን ነበር? 
ዮሐንስ ለሕዝቡ የደህንነትን እውቀት በመስጠት የጌታን መንገድ ያዘጋጃል፡፡ 

ሉቃስ 1፡67-80ን እናንብብ፡- ‹‹አባቱ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ ሞላበትና ትንቢት ተናገረ፡፡ እንዲህም አለ፡- የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፤ ጎብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፡፡ ከጥንት ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያት አፍ እንደተናገረ በብላቴናው በዳዊት ቤት የመዳን ቀንድን አሥነስቶልናል፡፡ ማዳኑም ከወደረኞቻችንና ከሚጠሉን ሁሉ እጅ ነው፡፡ እንደዚህ ለአባቶቻችን ምሕረት አደረገ፡፡ ለአባታችን ለአብርሃምም የማለውን መሐላውን ቅዱሱን ኪዳን አሰበ፡፡ በእርሱም ከጠላቶቻችን እጅ ድነን በዘመናችን ሁሉ ያለ ፍርሃት በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገለግለው ሰጠን፡፡ ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፡፡ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሄዳለህና፡፡ እንደዚህም የሐጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፡፡ ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጎበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርህራሄ ምክንያት ነው፡፡ ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል፡፡ እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል፡፡ ሕጻኑም አደገ፤ ለእስራኤልም እስከታየበት ቀን ድረስ በምድረ በዳ ኖረ፡፡››    
ዘካርያስ ሁለት ነገሮችን ተነበየ፡፡ እርሱ ከቁጥር 68 እስከ 73 ድረስ እግዚአብሄር ተስፋዎቹን እንዳልረሳ ኢየሱስም እግዚአብሄር ለአብርሃም በገባው ቃል መሰረት ዘሮቹን ከወደረኞቻቸው እጅ ለማዳን ከድንግል ማርያም እንደተወለደ ተነበየ፡፡ 
ከቁጥር 74 በኋላ ደግሞ ‹‹በእርሱም ከጠላቶቻችን እጅ ድነን በዘመናችን ሁሉ ያለ ፍርሃት በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገለግለው ሰጠን፡፡›› ይላል፡፡ ይህ እግዚአብሄር ለአብርሃምና ለእስራኤል ሕዝብ የገባውን የተስፋ ቃል የሚያስታውስ ነው፡፡ ‹‹ያለ ፍርሃት እንድናገለግለው ሰጠን›› በማለትም ተነበየ፡፡      
በመቀጠልም ከቁጥር 76 ጀምሮ ስለ ልጁ ተነበየ፡፡ ‹‹ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፡፡ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሄዳለህና፡፡ እንደዚህም የሐጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፡፡ ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጎበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርህራሄ ምክንያት ነው፡፡ ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል፡፡ እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል፡፡›› 
እዚህ ላይ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹እንደዚህም የሐጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፡፡›› የደህንነት እውቀት የሚሰጠው በማን እንደሆነ ተናገረ? በአጥማቂው ዮሐንስ፡፡ ይህንን ሁሉ ማየት ትችላላችሁን? አጥማቂው ዮሐንስ በእግዚአብሄር ቃሎች አማካይነት ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች የሚወስድ የእግዚአብሄር ልጅ የመሆኑን እውቀት ሊሰጠን ይገባ ነበር፡፡     
አሁን ማርቆስ 1ን እንመልከት፡- ‹‹የእግዚአብሄር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፡፡ እነሆ መንገድን የሚጠርግ መልዕክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፡፡ የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምጽ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደተጻፈ ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለሐጢያት ስርየት እየሰበከ መጣ፡፡ የይሁዳም አገር ሁሉ የኢየሩሳሌምም ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፡፡ ሐጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ ይጠመቁ ነበር፡፡›› (ማርቆስ 1፡1-5) 
እስራኤሎች አጥማቂውን ዮሐንስን በሰሙት ጊዜ የአሕዛቦችን ጣዖታት ከማምለክ ተመልሰው በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቁ፡፡ ዮሐንስ ግን እንዲህ ሲል መሰከረ፡- ‹‹እኔ ወደ እግዚአብሄር ትመለሱ ዘንድ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፡፡ ነገር ግን ሐጢያቶቻችሁ በሙሉ ወደ እርሱ ይተላለፉ ዘንድ የእግዚአብሄር ልጅ መጥቶ በዚሁ ተመሳሳይ ሁኔታ ይጠመቃል፡፡ እናንተ እንደተጠመቃችሁት በእርሱ ጥምቀት ብታምኑ በብሉይ ኪዳን በእጆች መጫን አማካይነት ሐጢያቶች እንደተላለፉ ሁሉ የእናንተም ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ ይተላለፋሉ፡፡›› ዮሐንስ የመሰከረው ያንን ነበር፡፡   
ኢየሱስ በዮርዳኖስ ተጠመቀ ማለት በሞት ወንዝ ውስጥ ተጠመቀ ማለት ነው፡፡ እኛ በቀብር ጊዜ እንዲህ እያልን እንዘምራለን፡- ‹‹♪በጣፋጩ ባማረው በዚያ የባህር ዳር እንገናኛለን ♪›› ስንሞት የዮርዳኖስን ወንዝ እንሻገራለን፡፡ የዮርዳኖስ ወንዝ የሞት ወንዝ ነው፡፡ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በዚያ ስለወሰደ ኢየሱስ በዚህ የሞት ወንዝ ውስጥ ተጠመቀ፡፡ ‹‹የሐጢአት ደመወዝ ሞት ነው፡፡››   
 
 
ሐጢያቶቻችንን ያስተላለፈ ጥምቀት፡፡
 
በአዲስ ኪዳን የእጆች መጫን ተምሳሌት ምንድነው?
የኢየሱስ ጥምቀት፡፡ 

በማቴዎስ 3፡13-17 ይህንን እናነባለን፡- ‹‹ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ ዮሐንስ ግን፡- እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር፡፡ ኢየሱስም መልሶ፡- አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው፡፡ ያን ጊዜ ፈቀደለት፡፡ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃው ወጣ፡፡ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ፡፡ የእግዚአብሄርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፡፡ እነሆም በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡››      
ኢየሱስ ወደ ዮርዳኖስ ሄዶ በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ ዮሐንስንም ‹‹አጥምቀኝ›› ብሎ አዘዘው፡፡ ዮሐንስም ‹‹እኔ በአንተ መጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?›› አለው፡፡ የሰማይና የምድር ሊቀ ካህናት በአንድ ላይ ተገናኙ፡፡ 
በዕብራውያን ላይ እንደተወሳው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ መልከጼዴቅ ስርዓት ለዘላለም ሊቀ ካህን ነው፡፡ ይህ ማለት ኢየሱስ የሰብአዊ ዘር ግንድ የለውም ማለት ነው፡፡ እርሱ የአሮን ወይም በምድር ላይ ያለ የማንም ዘር አልነበረም፡፡ እርሱ ፈጣሪያችን የእግዚአብሄር ልጅ ነው፡፡ እርሱ ያለና የሚኖር ነው፡፡ ስለዚህ የዘር ግንድ የለውም፡፡ ኢየሱስ የሰማይን ክብር አውልቆ ሕዝቡን ለማዳን ወደዚህ ምድር መጣ፡፡      
እርሱ ወደዚህ ምድር የወረደበት ምክንያት በሰይጣን ማታለያ የተሰቃዩትን ሐጢያተኞች በሙሉ ለማዳን ነው፡፡ በተጨማሪም በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፡፡ ‹‹ኢየሱስም መልሶ፡- አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው፡፡ ያን ጊዜ ፈቀደለት፡፡›› 
‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ፡፡›› ፍቀድልኝ! ኢየሱስ የሰው ዘር ሁሉ ወኪል የሆነውን አዘዘውና ለመጠመቅ ራሱን አጎነበሰ፡፡ በብሉይ ኪዳን ለእግዚአብሄር መስዋዕት ሲቀርብ ሐጢያተኛው ወይም ሊቀ ካህኑ በራሱ ላይ እጆቹን በመጫን ሐጢያቶችን ያስተላልፋል፡፡ ‹የአንድን ሰው እጅ መጫን› ማለት ‹ማስተላለፍ› ማለት ነው፡፡  
አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስን አጠመቀው፡፡ ይህ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከሚደረገው እጆችን መጫን ጋር ተመሳሳይ ነበር፡፡ ‹ማስተላለፍ› ‹መቀበር› እና ‹መስዋዕት ማድረግ› እንደዚሁ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ብሉይ ኪዳን ጥላው ሲሆን አዲስ ኪዳን አካል ነው፡፡ 
በብሉይ ኪዳን አንድ ሐጢያተኛ እጆቹን በጠቦቱ ላይ ሲጭን ሐጢያቱ ወደ ጠቦቱ ይተላለፋል፡፡ ጠቦቱም ይታረዳል፡፡ ጠቦቱ ሲሞት ይቀበራል፡፡ እጆቹን በጠቦቱ ላይ የጫነው ሰው ሐጢያቶች ወደ መስዋዕቱ እንስሳ ስለተላለፉ በሐጢያቶች ምክንያት ጠቦቱ መታረድ ነበረበት! ሐጢያቶቹ ወደ ጠቦቱ ከተላለፉ በስርዓተ መስዋዕቱ መሰረት ጠቦቱን ያቀረበው ሰው ያለ ሐጢያት መሆን ይቻለዋል? አዎ፡፡    
ይህ መሐረብ ሐጢያት ይህ ማይክራፎን ደግሞ ጠቦት ነው እንበል፡፡ እጆቼን በዚህ ማይክራፎን ላይ ስጭን ይህ ሐጢያት ወደ ማይክራፎኑ ማለትም ወደ ጠቦቱ ይተላለፋል፡፡ እንዲህ እንዲሆን የወሰነው እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡ ‹‹እጆችህን ጫን፡፡›› በብሉይ ኪዳን ዘመን አንድ ሰው ከሐጢያቶች ለመዳን እጆቹን በመስዋዕቱ ራስ ላይ መጫን ነበረበት፡፡ ከዚያ በኋላ ያለ ሐጢያት መሆን  ሐጢያቶች ማንጻት፣ መቀበርና ወደ እርሱ ማስተላለፍ ነበረበት፡፡ ትክክለኛው ነገር ይህ ነው፡፡  
 
ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ማለት ምን ማለት ነው?
ሐጢያቶችን ወደ ኢየሱስ በማስተላለፍ ሐጢያቶችን ሁሉ ማንጻት ማለት ነው:: 

ስለዚህ ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድ በተጠመቀ ጊዜ በእርግጥ ሁሉም ወደ እርሱ ተላልፈው ነበርን? የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል፡፡ ሰዎችም ሁሉ ተዋጅተዋል፡፡ ይህም በብሉይ ኪዳን ሐጢያቶችን ወደ መስዋዕቶች ከማስተላለፍ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ኢየሱስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጥቶ ዮሐንስን እንዲህ አለው፡- ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና፡፡›› (ማቴዎስ 3፡15) 
ከዚያም ዮሐንስ ኢየሱስን አጠመቀው፡፡ በእርሱ ጥምቀት ጽድቅን ሁሉ መፈጸም እንደሚገባቸው ለዮሐንስ ነገረው፡፡ ‹ጽድቅን ሁሉ› ማለት ‹እጅግ ተገቢና ተስማሚ› ማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ‹እንዲህ› በጥምቀት አማካይነት ጽድቅ ሁሉ ተፈጸመ፡፡ ይህ ማለት ዮሐንስ ኢየሱስን ማጥመቁና የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ ለማስተላለፍም ኢየሱስ በዮሐንስ መጠመቁ ትክክል ነበር ማለት ነው፡፡  
እግዚአብሄር ቤዛነትን የሚሰጠው በኢየሱስ ጥምቀት፣ በመስቀል ላይ መስዋዕቱና በእኛ እምነቶች ላይ ተመስርቶ ነው፡፡ ‹‹ሰዎች ሁሉ በሐጢያት ተቸግረዋል፡፡ በሐጢያቶቻቸውም ምክንያት በዲያብሎስ ተሰቃይተዋል፡፤ ስለዚህ እነርሱ እንዲድኑና ሰማይ እንዲገቡ አንተ የሰው ዘር ወኪልና የአሮን ዘር በመሆንህ ለሕዝቡ ሁሉ ልታጠምቀኝ ይገባል፡፡ እኔም በአንተ እጠመቃለሁ፡፡ ያን ጊዜ የቤዛነት ሥራ ይጠናቀቃል፡፡››
ዮሐንስም ‹‹ገባኝ›› ብሎ መለሰ፡፡  
ስለዚህ ዮሐንስ ኢየሱስን አጠመቀው፡፡ በኢየሱስ ራስ ላይ እጆቹን ጭኖ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ አስተላለፈ፡፡ በዚህም ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ያነጻ አዳኝ ሆነ፡፡ አሁን በእርሱ ቤዛነት ማመን ሊያድነን ይችላል፡፡ ታምናላችሁን? 
ኢየሱስ በሰው ዘር ሁሉ ወኪል እጆች አማካይነት በዮርዳኖስ ከተጠመቀ በኋላ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በሰውነቱ ተሸክሞ በአገልግሎቱ ውስጥ የመጀመሪያው ይፋ ሥራዎች አድርጎ እየተጓዘ ለሦስት ዓመት ተኩል ወንጌልን ሰበከ፡፡ 
በምንዝር ለተያዘችው ሴት እንዲህ አላት፡- ‹‹እኔም አልፈርድብሽም፡፡›› ሊፈርድባት ያልቻለው ሐጢያቶችዋን በሙሉ በራሱ ላይ ስለወሰደና ለእነርሱም በመስቀል ላይ ለመሞት ስለተዘጋጀ ነበር፡፡ ጌቴሴማኔ በተባለ ስፍራ ሲጸልይ የአምላክ የፍርድ ጽዋ ከእርሱ እንዲያልፍ ይፈቅድ ዘንድ አብን በመለመን ሦስት ጊዜ ጸለየ፡፡ ነገር ግን ወዲያውኑ ይህንን ትቶ ‹‹እኔ እንደምፈቅድ ሳይሆን አንተ እንደምትፈቅድ ይሁን›› አለ፡፡   
 
 
‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ!›› 
 
ኢየሱስ የወሰደው ምን ያህሉን ሐጢያት ነው? 
የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ነው፡፡ 

ዮሐንስ 1፡29 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፡- እነሆ የዓለምን ሐጢያት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ፡፡›› አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስን አጠመቀው፡፡ በነገውም ኢየሱስ ወደ እርሱ መጣ፡፡ ስለዚህ ለሕዝቡ ‹‹የእግዚአብሄር በግ›› በማለት ነገራቸው፡፡ ይህ የእርሱ ምስክርነት ነበር፡፡
የእግዚአብሄር ልጅ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ሐጢያቶቹን ሁሉ ወሰደ፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ እንደገናም መሰከረ፡፡ ዮሐንስ 1፡35-36 ‹‹በነገው ደግሞ ዮሐንስ ከደቀ መዛሙርቱም ሁለቱ ቆመው ነበር፡፡ ኢየሱስም ሲሄድ ተመልክቶ፡- እነሆ የእግዚአብሄር በግ አለ፡፡››
የእግዚአብሄር በግ የሚያመላክተው ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ለእስራኤል ሐጢያቶች እንደሞተ የተጠቀሰው እውነተኛና ትክክለኛ የመስዋዕት እንስሳ የመሆኑን እውነታ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ልጅና ፈጣሪያችን ሐጢያቶቻችንን ከዓለም ፍጥረት እስከ ፍጻሜው ድረስ ያሉትን ሐጢያቶች፣ በሙሉ ከአዳም ሐጢያት ጀምሮ እኛ እስከሰራናቸው በደሎች ድረስ ያሉትን፣ ከድካሞቻችን እስከ ስህተቶቻችን ድረስ ያሉትን ሐጢያቶች ለመውሰድ ለእናንተና ለእኔ ወደ ዓለም መጣ፡፡ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ሁላችንንም አዳነን፡፡    
ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደና ለእኛ ለምዕመናኖች ፍጹም ቤዛነትን ሰጠን፡፡ ይህንን አስተዋላችሁን? ‹‹የዓለምን ሐጢአት ሁሉ የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ፡፡›› 
እርሱ በዚህ ምድር ላይ ከተወለደ 2,000 አመታት አልፈዋል፡፡ በ30 አ.ም ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደ፡፡ 1 አ.ም ኢየሱስ የተወለደበት ዓመት ነበር፡፡ ከክርሰቶስ በፊት ያለውን ዘመን ዓመተ ዓለም ብለን እንጠራዋለን፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም ከመጣ ወደ 2,000 አመታት ያህል አልፈዋል፡፡ 
በ30 ዓ.ም አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስን አጠመቀው፡፡ በቀጣዩም ቀን ዮሐንስ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል ጮኸ፡፡ ‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ፡፡›› ‹‹እነሆ!›› ሰዎች ሐጢያቶቻቸውን ሁሉ በወሰደው በኢየሱስ እንዲያምኑ ነገራቸው፡፡ ኢየሱስ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ያዳነን የእግዚአብሄር በግ እንደነበር መሰከረ፡፡
ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደ፡፡ ከሐጢያት ጋር የምናደርገው ዘላቂ ጦርነት አበቃ፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ ስለወሰዳቸው እኛ አሁን ያለ ሐጢያት ነን፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ማለትም የእናንተንና የእኔን ሐጢያቶች እንደወሰደ መሰከረ፡፡‹‹ሁሉ በእርሱ (ዮሐንስ) በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ፡፡›› (ዮሐንስ 1፡7)
ያለ ዮሐንስ ምስክርነት ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደ እንዴት ማወቅ እንችል ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ ብዙውን ጊዜ እርሱ ስለ እኛ እንደሞተ ይነግረናል፡፡ ነገር ግን ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደ በግልጽ የመሰከረው አጥማቂው ዮሐንስ ብቻ ነው፡፡ 
 
ለም ሐጢያት ምን ያህል ሐጢያት ነው? 
ከዓለም መጀመሪያ እስከ መጨረሻው ድረስ ያሉት የሰዎች ሁሉ ሐጢያቶች ናቸው፡፡  

ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ብዙዎች እውነቱን መሰከሩ፡፡ በሕይወት ሳለ ግን የመሰከረው ዮሐንስ ብቻ ነው፡፡ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርትም የኢየሱስን ቤዛነት መመስከራቸው እርግጥ ነው፡፡ እነርሱ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን እንደወሰደና አዳኛችን እንደሆነ መስክረዋል፡፡  
ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች ወሰደ፡፡ አሁን አንባቢ ሆይ ገና 100 አመት አልሆነህም፤ ሆኖሃል እንዴ? ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች የወሰደው በ30 አመቱ ነበር፡፡ ይህንን ስዕላዊ መግለጫ ተመልከቱ፡፡                           
           
 
ሰው የተፈጠረው ኢየሱስ ከመምጣቱ ከ4,000 አመታት በፊት ነው እንበል፡፡ ኢየሱስ ከመጣ ከ2,000 አመታት ጥቂት አልፎዋል እንበል፡፡ ዓለም እስከ መቼ ድረስ እንደሚቆይ አናውቅም፡፡ መጨረሻው ግን እንደሚመጣ የተረጋገጠ ነው፡፡ እርሱ እንዲህ ይላል፡- ‹‹አልፋና ዖሜጋ ፊተኛውና ኋለኛው መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ፡፡›› (ዮሐንስ ራዕይ 22፡13)  
ስለዚህ መጨረሻ እንዳለ የተረጋገጠ ነው፡፡ አሁን እኛ ያለነው 2002 ዓመት በሚለው ጠቋሚ ላይ ነው፡፡ ክርስቶስ በ30 ዓ.ም ሐጢያቶቻችንን ወሰደ፡፡ ይህም በመስቀል ላይ ከመሞቱ ከ3 ዓመት በፊት ነው፡፡  
‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ፡፡›› እርሱ የዓለምን ሐጢያቶች ማለትም የእናንተንና የእኔን ሐጢያቶች ወሰደ፡፡ እኛ ከክርስቶስ ልደት 2000 አመታት ርቀን ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን ከወሰደ ከ2000 አመታት በኋላ ሕይወታቸንን እየኖርን ነው፡፡ አሁንም ድረስ እየኖርንና ቀንና ሌሊት ሐጢያቶችን እየሰራን ነው፡፡ ሆኖም ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች አስቀድሞ የወሰደ የእግዚአብሄር በግ ነው፡፡  
ከተወለድንበት ቅጽበት ጀምሮ መኖርና ሐጢያት መስራት እንጀምራለን፡፡ ከተወለድንበት ቅጽበት ጀምሮ ሁላችንም ሐጢያት እንሰራለን ወይስ አንሰራም?--እንሰራለን፡፡-- እስቲ ሒደቱን ሁሉ እንለፍበት፡፡ ከተወለድንበት ቀን ጀምሮ 10 ዓመት እስኪሆነን ድረስ ሐጢያት እንሰራለን ወይስ አንሰራም? --እንሰራለን፡፡-- ታዲያ እነዚህ ሐጢያቶች ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል ወይስ አልተላለፉም? --ተላልፈዋል፡፡-- ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ ስለተላለፉ እርሱ አዳኛችን ነው፡፡ እንደዚያ ካልሆነ እንዴት አዳኛችን ሊሆን ይችላል? ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል፡፡    
ከ11 እስከ 20 ዓመት ድረስ ሐጢያት እንሰራለን ወይስ አንሰራም? በልቦቻችንና በምግባሮቻችን ሐጢያት እንሰራለን፡፡…ሐጢያት በመስራት የተዋጣልን ነን፡፡ ሐጢያት እንዳንሰራ ተምረናል፡፡ ነገር ግን በተፈጥሮ ሐጢያቶች ለመስራት እናዘነብላለን፡፡  
እግዚአብሄር እነዚያ ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ እንደተላለፉ ነገረን፡፡ ሐጢያተኞች እንደሆንን ስላወቀ እነዚያን ሐጢያቶች በሙሉ አስቀድሞ ወሰደ፡፡ 
በዚህ ዓለም ላይ በተለምዶ የምንኖረው ምን ያህል ነው? 70 ዓመት አካባቢ ነው እንበል፡፡ በእነዚያ 70 ዓመታቶች የሰራናቸውን ሐጢያቶች በሙሉ ብንጨምር ሸክማችን ምን ያህል ከባድ ይሆናል? 8 ቶን በሚጭኑ የጭነት መኪኖች ውስጥ ብንጠቀጥቃቸው ምናልባትም ከ100 በላይ የጭነት መኪኖች ያስፈልጉን ነበር፡፡
በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ምን ያህል ሐጢያት እንደምንሰራ ለማሰብ ሞክሩ፡፡ እነዚያ የዓለም ሐጢያቶች ናቸው ወይስ አይደሉም? የዓለም ሐጢያቶች ክፍል ናቸው፡፡ ከተወለድንበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 10፣ ከ10 እስከ 20፣ ከ20 እስከ 30 አመታችን…እስክንሞት ድረስ ሐጢያት እንሰራለን፡፡ እነዚያ ሐጢያቶች በሙሉ ግን በጥምቀቱ አማካይነት ቀድሞውኑም ወደ ኢየሱስ በተላለፉት የዓለም ሐጢያቶች ውስጥ ተጨምረዋል፡፡    
 
 
የሰው አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ 
 
ኢየሱስ ያስወገደልን ምን ያህሉን ሐጢያት ነው? 
የአያቶቻችን፣ የእኛን፣ የዘሮቻችንን እንዲሁም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ያሉ ሐጢያቶችን በሙሉ ነው፡፡  

ኢየሱስ እነዚያን ሐጢያቶች በሙሉ ለማንጻት በሥጋ እንደመጣ ነገረን፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ራሱን ማጥመቅ ስላልቻለ እግዚአብሄር የሰዎች ሁሉ የተመረጠ ወኪል የሆነውን ባርያውን ዮሐንስን አስቀድሞ ላከው፡፡ እንዲህ ተብሎዋል፡- ‹‹ስሙም ድንቅ መካር ሐያል አምላክ ይባላል፡፡›› እርሱ በራሱ በጥበቡና በምክሩ የሰውን ዘር ወኪል አስቀድሞ ላከ፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ የሆነው ራሱ ኢየሱስም የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድ በሥጋ መጣ፡፡ ይህ የእግዚአብሄርን ጥልቅ ችሮታ የሚያሳይ ድንቅ ደህንነት አይደለምን?  
ይህ ድንቅ ነው አይደል? ስለዚህ እርሱ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ ብቻ በመላው ዓለም የሚኖሩትን የሰው ዘር ሐጢያቶች በሙሉ አንጽቶ ለአንዴና ለመጨረሻ በመሰቀል እያንዳንዱን ሰው ከሐጢያት አድኖዋል፡፡ ስለዚህ ነገር አስቡ፡፡ ከ20 እስከ 30፤ ከ30 እስከ 40፤ ከ40 እስከ 60፤ እስከ 70፤ እስከ 100 ዓመት ድረስ ያሉትን የእናንተን ሐጢያቶችና የልጆቻችሁንም ሐጢያቶች በሙሉ ተመልከቱ፡፡ እርሱ እነዚህን ሐጢያቶች በሙሉ ደምስሶዋል ወይስ አልደመሰሰም? አዎ ደምስሶዋል፡፡ እርሱ የሰው ዘር አዳኝ ኢየሱስ ነው፡፡ 
አጥማቂው ዮሐንስ ሐጢያቶችን በሙሉ ወደ ኢየሱስ ስላስተላለፈና እግዚአብሄርም እንዲህ እንዲሆን ስላቀደ በእርሱ በማመን መዳን እንችላለን፡፡ እናንተና እኔ ሐጢያተኞች ነን? ሐጢያቶቻችን በሙሉ ወደ ኢየሱስ ስለተላለፉ እኛ ከእንግዲህ ወዲያ ሐጢያተኞች አይደለንም፡፡ 
በዚህ ዓለም ላይ ሐጢያት አለ ብሎ ለመናገር የሚደፍር ማነው? ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፡፡ እርሱ ሐጢያት እንደምንሰራ ስላወቀ የወደፊት ሐጢያቶችንም ሁሉ ወሰደ፡፡ አንዳንዶቻችን ገና 50 አመት አልሆነንም፡፡ አንዳንዶቻችን የዕድሜያችንን ግማሽ እንኳን አልኖርንም፡፡ አንዳንዶቻችን ግን እኔንም ጨምሮ ለዘላለም የምንኖር ይመስል ስለ ራሳችን እናወራለን፡፡ 
አስቸጋሪ ሕይወት የምንኖር ብዙዎች አሉን፡፡ ይህንን በዚህ መንገድ ላብራራው፡፡ የአንዲት እሳት ራት አጋማሽ የዕድሜ ርዝመት ምን ያህል ነው? 12 ሰዓት አካባቢ ነው፡፡  
‹‹ኦ አምላኬ! የዝንብ መግደያ ገጥሞኝ ደቅቄ ልሞት ነበር፡፡ በተጋመሰው ሕይወቴ እንዲህ ያለ ጨካኝ ሰው ገጥሞኝ አያውቅም፡፡ የኖርሁት 12 ሰዓት ብቻ ነበር፡፡›› ነገር ግን መለፍለፍዋን ማቆም አልቻለችም፡፡ ቀድሞውኑም የዕድሜዋ ግማሽ አልፎዋል፡፡   
ምሽት 1 ወይም 2 ሰዓት ላይ የሕይወቷን ማምሻ አልፋለች፡፡ በቅርቡም ትሞታለች፡፡ አንዳንድ የእሳት ራቶች 20 ሰዓት፣ አንዳንዶቹም 21፣ አንዳንዶቹም ሽምግልና ሊባል በሚችል መልኩ 24 ሰዓት ይኖራሉ፡፡ እነርሱ ስለ ዕድሜ ልምምዶቻቸው ያወሩ ይሆናል፡፡ ይህ ግን ለእኛ ምን ይመስለናል? እኛ 70 ወይም 80 ዓመት ስለምንኖር ‹‹አታስቁኝ›› እንል ይሆናል፡፡ የእነርሱ ልምምድ በአይኖቻችን ፊት ምንም ማለት ናቸው፡፡  
ይህንን ምሳሌ በእግዚአብሄርና በእኛ መካከል ባለው ግንኙነት ላይ እናውለው፡፡ እግዚአብሄር ዘላለማዊ ነው፡፡ በዘላለማዊነት ውስጥ ይኖራል፡፡ እርሱ የዓለምን መጀመሪያና መጨረሻ ይወስናል፡፡ እርሱ ከዘላለም የጊዜ ክልል ውጭ ለዘላለም ይኖራል፡፡ እኛን የሚመለከተን ከዘላለማዊነቱ ስፍራ አንጻር ነው፡፡ 
በአንድ ወቅት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፡፡ በመስቀል ላይም ሞተ፡፡ ‹‹ተፈጸመ›› አለ፡፤ በሶስተኛው ቀን ተነሳ፡፡ ወደ ሰማይም አረገ፡፡ አሁን በዘላለማዊነት ውስጥ ይኖራል፡፡ አሁን ሁላችንንም ከላይ ሆኖ ወደታች ይመለከተናል፡፡  
አንድ ሰው ‹‹ኦ ብዙ ሐጢያት ሰርቻለሁ፡፡›› ‹‹የኖርሁት 20 አመት ብቻ ቢሆንም ብዙ ሐጢያት ሰርቻለሁ፡፡›› ‹‹30 አመት ኖሬ በጣም ብዙ ሐጢያት ሰርቻለሁ፡፡ በጣም ብዙ ነው፡፡ እንዴት ያለ ሐጢያቶች መኖር እችላለሁ?›› ይል ይሆናል፡፡  
በዘላለማዊነቱ ውስጥ ያለው ጌታችን ግን ‹‹አታስቀኝ፤ እስከ አሁን ድረስ የአንተን ሐጢያቶች ብቻ ሳይሆን አንተ ከመወለድህ በፊት የነበሩትን የቅድመ አያቶችህን ሐጢያቶች፣ አንተ ከሞትህ በኋላ የሚኖሩትን የዘሮችህን ትውልድ ሐጢያቶች በሙሉ ዋጅቻለሁ›› ይላል፡፡ እርሱ ይህንን የሚነግራችሁ ከዘላለም የጊዜ ፋይዳ አንጻር ነው፡፡ ይህንን ታምናላችሁን? እመኑትና በነጻ የተሰጣችሁን የደህንነት ስጦታ ተቀበሉ፡፡ መንግሥተ ሰማይም ግቡ፡፡ 
በራሳችሁ አስተሳሰቦች ራሳችሁን አትሰሩ፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሄር ቃሎች እመኑ፡፡ ‹ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና፡፡› የዓለምን ሐጢያቶች የወሰደው የእግዚአብሄር በግ ቀድሞውኑም ጽድቅን ሁሉ ፈጸመ፡፡ ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፡፡ ወሰደ ወይስ አልወሰደም? ወሰደ፡፡  
 
ኢየሱስ በመስቀል ላይ የመጨረሻውን እስትንፋሱን ከመስጠቱ በፊት ያለው ምን ነበር? 
‹‹ተፈጸመ፡፡››

ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፡፡ በጴንጤናዊው ጲላጦስ ችሎትም ሞት ተፈረደበትና በመስቀል ላይ ተሰቀለ፡፡ 
‹‹መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ፡፡ በዚያም ሰቀሉት፡፡ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉት፡፡ ጴላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፡፡ ጽሕፈቱም፡- የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሚል ነበር፡፡ ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበርና ከአይሁድ ብዙዎች ይህንን ጽሕፈት አነበቡት፡፡ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር፡፡›› (ዮሐንስ 19፡17-20) 
እርሱ በመስቀል ላይ ከተሰቀለ በኋላ ምን እንደተፈጠረ እንመልከት፡- ‹‹ከዚህም በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ተጠማሁ አለ፡፡›› እርሱ በመጽሐፍ እንደተጻፈው ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደ፡፡ ‹‹ከዚህም በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ተጠማሁ አለ፡፡ በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፡፡ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት፡፡ ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ ተፈጸመ አለ፡፡ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ፡፡›› (ዮሐንስ 19፡28-30)   
ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ ‹‹ተፈጸመ!›› በማለት ጮኸ፡፡ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ፡፡ በእርግጥም ሞቶ ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን ተነስቶ ወደ ሰማይ አረገ፡፡ 
ወደ ዕብራውያን 10፡1-9 እንመለስ፡- ‹‹ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፤ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር የሚያቀርቡት በዚያ መስዋዕት የሚቀርቡትን ሊፈጽም ከቶ አይችልም፡፡ እንደዚህማ ባይሆን የሚያመልኩት አንድ ጊዜ ነጽተው ከዚያ በኋላ በሕሊናቸው ሐጢአትን ስላላወቁ ማቅረብን በተዉ አልነበረምን? ነገር ግን በዚያ መሥዋዕት በየዓመቱ የሐጢአት መታሰቢያ አለ፡፡ የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ሐጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና፡፡ ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ፡- መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም፤ ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፡፡ በሙሉ በሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ሐጢአት በሚሰዋ መሥዋዕት ደስ አላለህም፡፡ በዚያን ጊዜ፡- እነሆ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደተጻፈ አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ላደርግ መጥቻለሁ ይላል፡፡ በዚህ ላይ መሥዋዕትንና መባን፣ በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንም፣ ስለ ሐጢአትም የሚሰዋ መሥዋዕትን አልወደድህም፤ በእነርሱም ደስ አላለህም ብሎ እነዚህም እንደ ሕግ የሚቀርቡት ናቸው፡፡ ቀጥሎ፡- እነሆ አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ ብሎአል፡፡ ሁለተኛውን ሊያቆም የፊተኛውን ይሸራል፡፡›› (ዕብራውያን 10፡1-9) 
 
 
ዘላለማዊ ቤዛነት፡፡ 
 
በኢየሱስ ካመንን በኋላ በየዕለቱ የምንሰራቸውን ሐጢያቶች የምናስወግደው እንዴት ነው? 
ኢየሱስ በጥምቀቱ ቀድሞውኑም ሐጢያትን ሁሉ እንደደመሰሰ በማረጋገጥ ነው፡፡ 

በሌላ አነጋገር ሕጉ ማለትም የመስዋዕቱ ስርዓት ሊመጡ ያሉ ነገሮች ጥላ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን የበጎችና የፍየሎች መስዋዕቶች ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚመጣና ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለመደምሰስም በተመሳሳይ ሁኔታ ሐጢያቶቻችንን እንደሚወስድ ገለጡልን፡፡ 
የብሉይ ኪዳን ሰዎች ዳዊት፣ አብርሃምና ሌሎች ሁሉ የመስዋዕቱ ስርዓት ለእነርሱ ምን ማለት እንደሆነ አወቁና አመኑ፡፡ የመስዋዕቱ ስርዓት መሲሁ ክርስቶስ (ክርስቶስ ማለት ‹የተቀባ ንጉሥ› ማለት ነው) ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ ለማንጻት አንድ ቀን እንደሚመጣ ይገልጣል፡፡ እነርሱ በደህንነታቸው አምነው በእምነታቸው ዳኑ፡፡  
ሕጉ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ነበር፡፡ ለሐጢያቶቻቸው በየቀኑና በየዓመቱ መስዋዕቶችን ማቅረብ በጭራሽ  ፈጽሞ ሊቤዡዋቸው አልቻሉም፡፡ ስለዚህ እንከን የሌለበት ፍጹምና ዘላለማዊ ሕላዌ የሆነው የእግዚአብሄር ልጅ ወደ ምድር መምጣት ነበረበት፡፡
ኢየሱስ ስለ እርሱ በመጽሐፍ እንደተጻፈ የአባቱን ፈቃድ ለማድረግ መጣ፡፡ ‹‹እነሆ አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ ብሎአል፡፡ ሁለተኛውን ሊያቆም የፊተኛውን ይሸራል፡፡›› ኢየሱስ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ እንደተጻፈው ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ስለወሰደና እኛም በእርሱ ስለምናምን ከሐጢያቶቻችን ድነናል፡፡  
ዕብራውያን 10፡10ን እናንብብ፡- ‹‹በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ በማቅረብ አንድ ጊዜ ተቀድሰናል፡፡›› በዚያ ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ በማቅረብ አንድ ጊዜ ተቀድሰናል፡፡ ተቀድሰናል ወይስ አልተቀደስንም? --ተቀድሰናል፡፡--   
ይህ ምን ማለት ነው? እግዚአብሄር አብ ልጁን ላከ፡፡ ሐጢያቶቻችንንም በሙሉ በጥምቀቱ አማካይነት ወደ እርሱ አስተላለፈ፡፡ ተቀብሎትም በመስቀል ላይ ለዘላለም ተፈረደበት፡፡ ስለዚህ በሐጢያት ስንሰቃይ የነበርነውን ሁላችንን አዳነን፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድ ይህ ነበር፡፡
መቀደስ እንችል ዘንድ ኢየሱስ እኛን ለማዳን ራሱን የዘላለም መስዋዕት አድርጎ አቀረበ፡፡ ኢየሱስ ራሱ እንዳይፈረድብን ለሐጢያቶቻችን ሁሉ መስዋዕት ስለሆነና ስለሞተ ተቀድሰናል፡፡ 
የብሉይ ኪዳን መስዋዕት በየቀኑ የሚቀርበው በየቀኑ የሚሰሩት ሐጢያቶች በሙሉ ለመንጻት ሌላ መስዋዕት ያስፈልጋቸው ስለነበር ነው፡፡ 
 
 

ኢየሱስ የጴጥሮስን እግር የማጠቡ መንፈሳዊ ትርጉም፡፡ 

 
የንስሐ ጸሎቶች ልናቀርብለት የሚገባን አንዳች ሐጢያት አለ? 
የለም፡፡

በዮሐንስ 13 ላይ ኢየሱስ የጴጥሮስን እግር ያጠበበት ታሪክ አለ፡፡ እርሱ የጴጥሮስን እግር ያጠበው ጴጥሮስ ወደፊትም ሐጢያቶችን እንደሚሰራ ሊያሳየውና ቀድሞውኑም እነዚያን ሐጢያቶች በሙሉ እንደዋጃቸው ሊያስተምረው ነበር፡፡ ኢየሱስ ጴጥሮስ ወደፊትም ደግሞ ሐጢያት እንደሚሰራ አወቀ፡፡ ስለዚህ በመታጠቢያው ውስጥ ውሃ አፈሰሰና እግሮቹን አጠበ፡፡  
ጴጥሮስ አሻፈረኝ ለማለት ቢሞክርም ኢየሱስ ‹‹እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፤ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ›› አለው፡፡ ይህ ምንባብ ‹ከዚህ በኋላ እንደገና ሐጢያት ትሰራለህ፡፡ ሐጢያቶችህን በሙሉ ካነጻሁልህ በኋላ ትክደኛለህ፡፡ ዳግመኛም ሐጢያት ትሰራለህ፡፡ እኔ ወደ ሰማይ ካረግሁ በኋላም እንኳን ሐጢያትን ትሰራለህ፡፡ ስለዚህ አስቀድሞ የወደፊት ሐጢያቶችህንም እንኳን ስለወሰድሁ ሰይጣን እንዳይፈትንህ ለማስጠንቀቅ እግሮችህን አጥባለሁ፡፡›     
እርሱ የጴጥሮስን እግር ያጠበው እኛ በየቀኑ ንስሐ መግባት እንዳለብን ሊነግረን ይመስላችኋልን? አይደለም፡፡ ለመዳን በየቀኑ ንስሐ መግባት ቢኖርብን ኖሮ ያ ማለት ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ አልወስድም ማለት ይሆን ነበር፡፡ 
ኢየሱስ ግን ለዘላለም እንደቀደሰን ተናገረ፡፡ በየቀኑ ንስሐ መግባት ቢኖርብን ኖሮ ወደ ብሉይ ኪዳን ዘመን መመለስ ይገባን ነበር፡፡ ታዲያ ማን ሊጸድቅ ይችላል? ሙሉ በሙሉስ ማን ሊድን ይችላል? በእግዚአብሄር ብናምንም ማን ያለ ሐጢያት ሊኖር ይችላል? 
ንስሐ በመግባት ማን ሊቀደስ ይችላል? እኛ ያለ ማቋረጥ በየቀኑ ሐጢያት እንሰራለን፡፡ ስለዚህ ለእያንዳንዱ ሐጢያት ይቅርታ መጠየቅ የምንችለው እንዴት ነው? ቤዛነቶቻችንን ለማግኘት እንዲህ ግድ የለሾች የምንሆነውና እርሱን መነዝነዝ የምንችለው እንዴት ነው? ምሽት ላይ ማለዳ የሰራናቸውን ሐጢያቶች ወደ መርሳት እናዘነብላለን፡፡ ማታ የሰራናቸውን ሐጢያቶች ደግሞ ጠዋት እንረሳቸዋለን፡፡ ለሐጢያቶቻችን በሙሉ ፈጽሞ ንስሐ መግባት አይቻለንም፡፡    
ስለዚህ ኢየሱስ አንድ ጊዜ ተጠመቀ፡፡ ሁላችንም በአንድ ጊዜ እንቀደስ ዘንድም ራሱን አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ አቀረበ፡፡ ይህንን ማስተዋል ትችላላችሁን? እኛ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ተዋጅተናል፡፡ የምንዋጀው ንስሐ በምንገባበት ጊዜ ሁሉ አይደለም፡፡ 
ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን፤ የእናንተንና የእኔን ሐጢያቶች በሙሉ እንደወሰደ በማመን ከሐጢያቶቻችን ድነናል፡፡ 
‹‹ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ሐጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መስዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፡፡ እርሱ ግን ስለ ሐጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘለዓለም አቅርቦ በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደፊት ይጠብቃል፡፡ አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና፡፡ መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፡፡ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ፤ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ ብሎ ከተናገረ በኋላ ሐጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል፡፡ የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ ከእንግዲህ ወዲያ ስለ ሐጢአት ማቅረብ የለም፡፡›› (ዕብራውያን 10፡11-18)   
ከላይ በቁጥር 18 ላይ ‹‹የእነዚህ ስርየት ባለበት›› ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ማለት ሐጢያት ራሱ ማንኛውም ሐጢያት ምንም ሳይቀር ለዘላለም ስርየትን አግኝቷል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር እነርሱን ደመሰሰና ሁላችንንም ይቅር አለን፡፡ ይህንን ታምናላችሁን? ‹‹የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ ከዚህ ወዲህ ስለ ሐጢአት ማቅረብ የለም፡፡››   
እስከ አሁን ያለውን እያንዳንዱን ነገር እናጠቃለው፡፡ በሌላ አነጋገር አጥማቂው ዮሐንስ እጆቹን በኢየሱስ ላይ ባይጭንና ኢየሱስንም ባያጠምቀው ኖሮ መዳን እንችል ነበር? የለም ፈጽሞ አንችልም! ወደኋላ ተመልሰን እናስብ፡፡ ኢየሱስ አጥማቂው ዮሐንስ የሰዎች ሁሉ ወኪል አድርጎ ባይመርጠውና በእርሱ አማካይነትም ሐጢያት ሁሉ ባይወስድ ኖሮ እርሱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ማንጻት ይችል ነበር? አይችልም ነበር፡፡   
የእግዚአብሄር ሕግ ጻድቅና መልካምም ነው፡፡ እርሱ አዳኛችን እንደሆነና ሐጢያቶቻችንን ሁሉ እንደወሰደ ብቻ አልተናገረም፡፡ ሐጢያቶቻችንን በተግባር መውሰድ ነበረበት፡፡ አምላክ የሆነው ኢየሱስ በሥጋ ለምን ወደ እኛ መጣ? የመጣው የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ አማካይነት ለመወስድ ነው፡፡ ኢየሱስ የዘላለም መስዋዕት ሆኖ ለመቅረብ በሥጋ እስካልመጣ ድረስ የልባችንና የሥጋችን ሐጢያቶች በሙሉ ሊደመሰሱ እንደማይችሉ ያውቅ ነበር፡፡   
ኢየሱስ ባይጠመቅ ኖሮ ሐጢያቶቻችን አሁንም ድረስ ይኖሩ ነበር፡፡ በመጀመሪያው ሐጢያቶቻችንን ሳይወስድ ቢሰቀል ኖሮ ሞቱ ትርጉም አልባ ይሆን ነበር፡፡ ከእኛ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር አይኖረውም ነበር፡፡ ፈጽሞ ትርጉም የለሽ ይሆን ነበር፡፡ 
ስለዚህ ኢየሱስ በ30 ዓመቱ የአደባባይ አገልግሎቱን ሲጀምር ሊጠመቅ በዮርዳኖስ ወዳለው ወደ አጥማቂው ዮሐንስ ሄደ፡፡ የእርሱ የአደባባይ አገልግሎት የተጀመረው በ30 አመቱ ያበቃው ደግሞ በ33 ዓመቱ ነበር፡፡ 30 ዓመት ሲሆነው ሊጠመቅ ወደ አጠጥማቂው ዮሐንስ ሄደ፡፡ ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ፤ ሰዎች ሁሉ መዳንና ጻድቃን መሆን ይችሉ ዘንድ እንዲህ ማድረግ ይገባናልና፡፡ ለእኛ ይህንን ማድረግ ተገቢ ነገር ነው፡፡ አሁን አጥምቀኝ፡፡›› አዎ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰዎች ሁሉ ቤዛነት ተጠመቀ፡፡    
እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ ነገር ግን ልጁ እንዲሞት መፍቀድ ነበረበት፡፡ ስለዚህ ለሦስት ሰዓታት ያህል በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ነበር፡፡ ኢየሱስም ከመሞቱ ቀደም ብሎ ‹‹ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ?›› በማለት ጮኸ፡፡ ያም ማለት ‹‹አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?›› ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ተሸክሞ ስለ እኛ በመስቀል ላይ በይፋ ፍርድን ተቀበለ፡፡ በዚህም ሁላችንን አዳነን፡፡ ያለ ኢየሱስ ጥምቀት ሞቱ ትርጉም የለሽ ነው፡፡: 
 
ሐጢያተኛ ነህ ወይስ ጻድቅ ሰው? 
በልቤ ውስጥ አንዳች ሐጢያት የሌለብኝ ጻድቅ ሰው፡፡ 

ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ሳይወስድ በመስቀል ላይ ሞቶ ቢሆን ኖሮ ሞቱ ቤዛነትን አይፈጽምም ነበር፡፡ ኢየሱስ እኛን ፈጽሞ ለመዋጀት የሰዎች ሁሉ ወኪል በሆነው በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች ሁሉ ይድኑ ዘንድም በመስቀል ላይ ፍርድን ተቀበለ፡፡   
ስለዚህ ከአጥማቂው ዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ ስላስተላለፈ ሐጢያቶቻችን ስርየትን አግኝተዋል፡፡ አሁን እናንተና እኔ እግዚአብሄርን አባታችን ብለን መጥራትና በድፍረትም መንግሥተ ሰማይ መግባት እንችላለን፡፡  
ዕብራውያን 10፡18 እንዲህ ይላል፡- ‹‹የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ ከእንግዲህ ወዲያ ስለ ሐጢአት ማቅረብ የለም፡፡›› እናንተ አሁንም ሐጢያተኞች ናችሁን? ኢየሱስ ቀድሞውኑም ዕዳዎቻችሁን በመክፈሉ እናንተአሁንም ዕዳዎችን መክፈል ይኖርባችኋልን? 
ከልክ በላይ የመጠጣት አባዜው ከብዙ አበዳሪዎች እንዲበደር ያደረገው አንድ ሰው ነበር፡፡ ታዲያ አንድ ቀን ልጁ ሐብት አገኘና የአባቱን ዕዳዎች በሙሉ ከፈለ፡፡ አባቱ በዚያ በሚገኝ በእያንዳንዱ መሸታ ቤት ብዙ ዕዳ ቢኖርበትም ዳግመኛ መክፈል የለበትም፡፡ 
ኢየሱስም ለእኛ ያደረገው ይህንኑ ነው፡፡ ለሐጢያቶቻችን ከሚገባው በላይ በቅድሚያ ከፈለ፡፡ በዕድሜ ዘመናችን ለምንሰራቸው ሐጢያቶች ብቻ አይደለም፡፡ ለዓለም ሐጢያቶችም በሙሉ ነው፡፡ እነርሱ እርሱ በተጠመቀ ጊዜ ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል፡፡ አሁንም ገና ሐጢያተኞች ናችሁን? አይደላችሁም፡፡ 
ይህንን ወንጌል ከመጀመሪያው ጀምሮ አውቀነው ቢሆን ኖሮ በኢየሱስ ማመን እንዴት በቀለለን ነበር! ነገር ግን በጣም አዲስ ስለሚመስል ብዙ ሰዎች ግራ ተጋብተውታል፡፡ 
ይህ ግን አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ከሰው ታሪክ ጀምሮ የኖረ ነው፡፡ እኛ ከዚህ በፊት አላወቅነውም፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ሁልጊዜም በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ተመዝግቦ የነበረና ሁልጊዜም ሲተገበር የነበረ ነው፡፡ ሁልጊዜም እዚያው ነበር፡፡ እናንተና እኔ ከመወለዳችን በፊትም እዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነበረ፡፡ ከምድር ፍጥረት በፊትም እዚሁ ነበር፡፡  
 
 
የዘላለም ቤዛነት ወንጌል፡፡ 
 
በእግዚአብሄር ፊት ምን ማድረግ አለብን? 
በዘላለማዊው የቤዛነት ወንጌል ማመን አለብን፡፡ 

ሐጢያቶችንን በሙሉ ያነጻው ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ያደረገው እናንተና እኔ ከመወለዳችንም በፊት ነው፡፡ እርሱ ሁሉንም ወስዶዋቸዋል፡፡ አሁንም ድረስ ከሐጢያት ጋር ናችሁን? --አይደለም፡፡-- ነገር ግን የምትሰሩዋቸው ሐጢያቶችስ? እነርሱም በዓለም ሐጢያቶች ውስጥ ተጨምረዋል፡፡  
የነገን ሐጢያቶች አሁኑኑ እናስወግዳቸው፡፡ እስከ አሁን ድረስ የሰራናቸው ሐጢያቶችም እንደዚሁ በዓለም ሐጢያቶች ውስጥ ተካተዋል፡፡ አልተካተቱምን? ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል ወይስ አልተላለፉም? አዎ ተላልፈዋል፡፡   
ታዲያ የነገ ሐጢያቶችም ወደ እርሱ ተላልፈዋልን? አዎ፡፡ እርሱ ምንም ሳያስቀር ሁሉንም ወስዶዋል፡፡ አንድም የተወው ሐጢያት የለም፡፡ ወንጌል ኢየሱስ በአንድ ጊዜ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደና ለሁሉም ዋጋ እንደከፈለ ከሙሉ ልባችን እንድናምን ይነግረናል፡፡   
‹‹የእግዚአብሄር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፡፡›› (ማርቆስ 1፡1) የሰማይ ወንጌል የምሥራች ነው፡፡ እርሱ ‹‹እኔ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ ወስጃለሁ፡፡ እኔ አዳኛችሁ ነኝ፡፡ በእኔ ታምናላችሁን?›› ብሎ ይጠይቀናል፡፡ እጅግ ብዙ ቁጥር ካላቸው ሰዎች መካከል ‹‹አዎ አምናለሁ፤ አንተ እንደነገርከን አምናለሁ፡፡ በጣም ቀላል ስለሆነ ወዲያውኑ ልረዳው ችያለሁ›› ብለው የመለሱት ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ እምነታቸውን እንዲህ የሚመሰክሩ ሰዎች ልክ እንደ አብርሃም ጻድቃን ይሆናሉ፡፡  
ሌሎች ግን ‹‹ይህንን ማመን አልችልም፡፡ ለእኔ አዲስና እንግዳ ይመስላል›› ይላሉ፡፡ 
ያን ጊዜ ‹‹እስቲ ንገሩኝ፤ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ ወስጃለሁ ወይስ አልወሰድኩም?›› በማለት ይጠይቃቸዋል፡፡ 
‹‹የተማርኩት አንተ የወሰድከው በየቀኑ የምሰራቸውን ሐጢያቶቼን ሳይሆን የአዳምን ሐጢያት ብቻ እንደሆነ ነው፡፡›› 
‹‹የተነገረህን ለማመን በጣም ብልህ እንደሆንህ አያለሁ፡፡ የምነግርህ ምንም ነገር ስለሌለ ወደ ሲዖል መሄድ አለብህ፡፡›› 
በእርሱ ፍጹም ቤዛነት በማመናችን ድነናል፡፡ ሐጢያት እንዳለባቸው የሚሟገቱ ሁሉ ወደ ሲዖል መውረድ አለባቸው፡፡ ምርጫቸውን መርጠዋል፡፡ 
የቤዛነት ወንጌል የጀመረው ከአጥማቂው ዮሐንስ ምስክርነት ነው፡፡ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ስላነጻ ስናምን ተቀድሰናል፡፡ 
ሐዋርያው ጳውሎስ በመልዕክቶቹ ውስጥ ስለ ኢየሱስ ጥምቀት ብዙ ተናግሮዋል፡፡ በገላትያ 3፡27 ላይ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና፡፡›› ‹በክርስቶስ መጠመቅ› ማለት በእርሱ ጥምቀት በማመን ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆነናል ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ ሐጢያቶቻችን በሙሉ በአጥማቂው ዮሐንስ አማካይነት ወደ እርሱ ተላልፈው ሙሉ በሙሉ ነጽተዋል፡፡  
1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ይህም ውሃ ማለት ደግሞ ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፡፡ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም ለእግዚአብሄር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፡፡ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፡፡››   
የቤዛነትን ጸጋ ከላይ የሚቀበሉት በአጥማቂው ዮሐንስ ምስክርነት፣ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ ደም የሚያምኑ ሰዎች ብቻ ነው፡፡ 
የኢየሱስን ጥምቀት የደህንነታችን ምሳሌ አድርጋችሁ በልባችሁ ተቀበሉና ዳኑ፡፡