Search

Khotbah-Khotbah

ርዕስ 9፡ ሮሜ (በሮሜ መጽሐፍ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[Chapter 8-8] ጻድቃንን የሚያግዘው መንፈስ ቅዱስ፡፡ ‹‹ሮሜ 8፡26-28››

‹‹ሮሜ 8፡26-28›› 
‹‹እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፡፡ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፡፡ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፡፡ ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደሆነ ያውቃል፡፡ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ለቅዱሳን ይማልዳልና፡፡ እግዚአብሄርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን፡፡›› 
 
 
መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሄር ጽድቅ በሚያምኑ ሰዎች ልብ ውስጥ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንዲጸልዩ ያደርጋቸዋል፤ ያግዛቸውማል፡፡ ሊነገር በማይቻል መቃተትም ስለ እነርሱ ይማልዳል፡፡ ይህ ማለት መንፈስ ቅዱስ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ እንዲጸልዩ ያግዛቸዋል ማለት ነው፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ሰዎች የእግዚአብሄር ልጆች ተብለው የተጠሩት ለዚህ ነው፡፡ ጌታ እስከ ዘመን ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜም ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ቃል ገብቶላቸዋል፡፡
 
መንፈስ ቅዱስ በጻድቃን ውስጥ ሆኖ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ይማልዳል፡፡ መንፈስ ቅዱስን መቀበል የምትችሉት እንዴት ይመሰላችኋል? በጸሎት? ሐጢያቶች ሁሉ እያሉባችሁ መንፈስ ቅዱስን መቀበል የምትችሉ ይመስላችኋልን? መንፈስ ቅዱስ የሚሰራውና የሚያድረው በእግዚአብሄር ጽድቅ በሚያምኑ ሰዎች ልብ ውስጥ ብቻ ነው፡፡
 
እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ መጸለይ የሚፈልጉ ክርስቲያኖች ከመንፈስ ቅዱስ እገዛን ያገኛሉ፡፡ ምን መጸለይ እንደሚገባቸው ተምረው ይረዳሉ፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን መንፈስ ቅዱስን ተቀብላችሁ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ይማልድላችኋል፡፡ መንገዳችሁንም ይመራችኋል፡፡
      
 

ነገር ሁሉ ለበጎ ነው፡፡

 
‹‹እግዚአብሄርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን፡፡›› (ሮሜ 8፡28)
 
እግዚአብሄር ከምዕመናን ጎን ሆኖ አምላክን ለሚወዱት ሰዎች ነገርን ሁሉ ለበጎ ያደርግላቸዋል፡፡ እግዚአብሄር ዳግም የተወለዱ ምዕመናንን ይወዳቸዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ እኛን ለመርዳት ሲል ጠላቶቻችንን ይጠቀም ይሆናል፡፡ በመጨረሻ ግን ስለ ሐጢያቶቻቸው ይቀጣቸዋል፡፡ የእኛ ጠላቶች በዘላለም ቅጣት ብን ብለው ይጠፋሉ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሄር የሚፈቅደው እያንዳንዱ ነገር ለምዕመናን በጎነት ብቻ የሚውል ነውና፡፡