Search

Khotbah-Khotbah

ርዕስ 11፡ የመገናኛው ድንኳን

[11-8] የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ቀለም፡፡ ‹‹ ዘጸዓት 27፡9-19 ››

የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ቀለም፡፡
‹‹ ዘጸዓት 27፡9-19 ››
‹‹የማደሪያውንም አደባባይ ሥራ፡፡ በደቡብ ወገን የጥሩ በፍታ መጋረጆች ይሁኑለት፡፡ የአንዱም ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፡፡ ከናስ የተሰሩ ሃያ ምሰሶችና ሃያ እግሮች ይሁኑለት፡፡ የምሰሶቹም ኩላቦችና ዘንጎች የብር ይሁኑ፡፡ እንዲሁም በሰሜን ወገን መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጆች፣ ከናስ የተሰሩ ሃያ ምሰሶች፣ ሃያም እግሮች ይሁኑ፡፡ በምዕራብም ወገን ለአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጆች፣ አስርም ምሰሶች፣ አስርም እግሮች ይሁኑለት፡፡ በምሥራቅም ወገን የአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ይሁን፡፡ በአንድ ወገን የመጋረጆቹ ርዝመት አስራ አምስት ክንድ ይሁን፡፡ ምሰሶቹም ሦስት እግሮቹም ሦስት ይሁኑ፡፡ ለአደባባዩም ደጅ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊም፣ ከቀይም ግምጃ፣ ከጥሩ በፍታም በጥልፍ አሰራር የተሰራ ሃያ ክንድ መጋረጃ ይሆናል፡፡ ምሰሶቹም አራት እግሮቹም አራት ይሁኑ፡፡ በአደባባዩም ዙሪያ ላሉት ምሰሶች ሁሉ የብር ዘንጎች፣ የብርም ኩላቦች፣ የናስም እግሮች ይሁኑላቸው፡፡ የአደባባዩ ርዝመት መቶ ክንድ ስፋቱም አምሳ ክንድ ይሁን፡፡ ለማገልገል ሁሉ የማደሪያው ዕቃ ሁሉ፣ ካስማዎቹም ሁሉ፣ የአደባባዩም ካስማዎች ሁሉ የናስ ይሁኑ፡፡››
 
 
ዳግመኛ በተወለዱ ክርስቲያኖች እምነትና ተራ በሆኑ ክርስቲያኖች እምነት መካከል ግልጽ የሆኑ ልዩነቶች አሉ፡፡ ዳግመኛ የተወለዱ ክርስቲያኖች እግዚአብሄር ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንደደመሰሰ ያውቃሉ፤ ያምናሉም፡፡ ተራ ክርስቲያኖች ግን በራሳቸው አስተሳሰቦች ላይ ተመርኩዘው ይህ ሐይማኖታዊ ምግባር ብቻ እንደሆነ አድርገው በኢየሱስ ያምናሉ፡፡ ነገር ግን የሐይማኖት ጉዳይ አድርገው ብቻ በእግዚአብሄር የሚያምኑ በብዙ ስለበለጸጉ ትክክለኛውን እውነት የሚያምኑ እነዚህ የተሳሳተ እምነት ያላቸው ሰዎች የሐሰት ትምህርቶቻቸውን እያሰራጩ ሲበለጽጉ በማየታቸው ልባቸው ተሰብሮዋል፡፡ ልባቸው የተሰበረው ብዙ ክርስቲያኖች እንደዚህ ወዳሉት አታላይና አጭበርባሪ የሐሰት ሐይማኖቶች ውስጥ ተስበው መግባታቸውን ስለሚያውቁ ነው፡፡
 
እኔም ብሆን ለጊዜው በዚህ ነገር ከልቤ አዝኜ ነበር፡፡ ከእውነት ጋር ተገናኝቼ በትክክል ዳግመኛ ስለተወለድሁ በሥራዎቹ ውስጥ መጠቀሚያ መሳርያ አድርጎ እየተጠቀመብኝ በመሆኑ እግዚአብሄርን ከልቤ አመሰግናለሁ፡፡ ልቤ የእግዚአብሄርን እውነት በሩቅና በቅርብ ለማሰራጨት ስለሚናፍቅ ብዙ ሰዎች ውሸትን አምነው በመታለል የሐይማኖት ሕይወትን ሲኖሩ ስመለከት ሐዘኔ ጥልቅ ነው፡፡
 
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በልቤ ውስጥ ያለ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ድካሞች ቢኖሩብኝም በልቤ ውስጥ ሐጢያት የለም፡፡ ስለዚህ በልቤ ውስጥ የሚገኘው ምስጋና ነው፡፡ በማምነው ወንጌልም አላፍርም፡፡ ይህንን የእውነት ቃል ሰምተው የሚያምኑበት ከሆነ እነርሱም ደግሞ በእግዚአብሄርና በሰዎች ፊት አያፍሩም፡፡ ምክንያቱም በዚህ እውነት በሚያምኑበት ጊዜ ሁሉም በተጨባጭ የእግዚአብሄር ልጆች ይሆናሉና፡፡
 
እናንተም እንደዚሁ እነዚህኑ በረከቶች መቀበል ትችላላችሁ፡፡ የሥነ መለኮት ትምህርትን የተማራችሁ ባትሆኑም በዚህ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የምታምኑ ከሆነ የሐጢያቶቻችሁን ስርየት ተቀብላችሁ የእግዚአብሄር ልጆች ትሆናላችሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስንም በልባችሁ ውስጥ ትቀበላላችሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ስላላችሁ ከእግዚአብሄር ባሮች ጋር አብራችሁ መጓዝ ትችላላችሁ፡፡ ይህ ግልጽ የሆነ እውነት ነው፡፡ እንደዚህ ማመንም እውነተኛ እምነት ነው፡፡
 
የምኖረው ውሸቶችን በተሞላ ዓለም ውስጥ ቢሆንም በልቤ ውስጥ ይህ እውነተኛ እምነት ስላለ እስከዚህች ቅጽበት ድረስ የእውነትን ወንጌል በመስበክ ቆይቻለሁ፡፡ ቃሉን መስበክ የጀመርሁት በመገናኛው ድንኳን ርዕሰ ጉዳይ ላይ ስለሆነ የዋሾዎችን ድብቅ ዓላማዎች በግልጽ ወደ ማወቁ ደርሻለሁ፡፡ ከዚህ የተነሳም እውነቱን ከውሸቱ መለየት ላይ ደርሻለሁ፡፡ ይህንን የመገናኛውን ድንኳን የምመሰክረውም ለዚህ ነው፡፡ ትክክለኛው እውነት በመገናኛው ድንኳን አማካይነት መሰራጨቱ ሰዎች በእውነተኛውና በሐሰተኛው መካከል መለየት እንዲችሉ ስላደረጋቸው ከፍተኛ ደስታ ይሰጠኛል፡፡
 
ይህንን በመገናኛው ድንኳን ላይ የሚያነጣጥረውን መጽሐፍ ስጽፍ ለእኔ እጅግ አስቸጋሪው ተግባር ከቃላት አገባቡ ጋር ለመስማማት መሞከር ነበር፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የመጀመሪያዎቹን ቃለ ጽሁፎች በመመልከት ከመገናኛው ድንኳን ጋር የተያያዙ አስቸጋሪ የሆኑ የቃላት ዝርዝሮች የተሳሳተ መረጃን የሚያቀርቡ እንዳይሆኑ፣ አንባቢዎችም በዚህ መንገድ ስህተትን እንዳይቀበሉ ትልቅ ትኩረት ሰጥቼአለሁ፡፡ እኔ የመገናኛውን ድንኳን በሚመለከት አስተውሎትና ዕውቀት ቢኖረኝም የመገናኛው ድንኳን አቀራረቦችና ድብቅ የሆኑት መንፈሳዊ ትርጓሜዎቹ ዕውቀታቸው ውሱን ለሆኑት ሰዎች መብራራት ስላለበት የመገናኛውን ድንኳን ፋይዳ እንደምን በግልጽና በተጨባጭ ማብራራት እችል እንደሆነ እርግጠኛ ባልሆንም ስለ ተግባሩ በመጠኑም ቢሆን ማሰቤ አልቀረም፡፡
 
ሰዎች ይህንን መጀመሪያ እንደሰሙት ወዲያውኑ ገብቶዋቸው ማመን ቢችሉ ጥሩ ይሆን ነበር፡፡ ነገር ግን ሮም በአንድ ቀን እንዳልተገነባች ሁሉ እውነትንና እውነተኛ እምነትን ማሰራጨትም በአንድ ቀን ተሰራጭተው የሚያበቁ አይደሉም፡፡ ነገር ግን እስከ ታች ድረስ ቆፍረን ለመዝለቅ ጥቂት በጥቂት እንደምንቆፍር ሁሉ ይህም የሚከናወነው ቀስ በቀስ ነው፡፡ ስለዚህ የእኔ ለየት ያለ ትኩረት ገና ከመጀመሪያው ጀምሮ በጥልቅ መቆፈር ነው፡፡ እንደዚያ ካልሆነ ማንም ይህንን መረዳት አይችልምና፡፡ ይህንን መጽሐፍ ስጽፍ ከገጠሙኝ እጅግ አስቸጋሪ ተግዳሮቶች አንዱ ይህ ነበር፡፡
 
ነገር ግን በእግዚአብሄር እርዳታ በመጨረሻ ያለ ብዙ ችግር ታትሞ ወጥቶዋል፡፡ ለዚህም በጣም ደስተኛና አመስጋኝ ነኝ ማለቱ አስፈላጊ አይደለም፡፡ በዚህ መጽሐፍ አማካይነትና እውነቱን ከስህተቱ በመለየት ዛሬ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ያመኑ ምዕመናን እንዴት ባማረ፣ በግልጽና በማያጠራጥር መልኩ እንደዳኑና በንጽጽርም ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ውጭ በሌሎች ወንጌሎች የሚያምኑ ምዕመናን እምነት እንዴት ሐይማኖታዊና ከንቱ እንደሆነ አብራራለሁ፡፡ ስለዚህ ከሁሉም በላይ እኔን ከሐጢያቶቼ ስላዳነኝ እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ፡፡
 
ዛሬ በኢየሱስ ስለሚያምኑ ብቻ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሐጢያት አልባ እንደሆኑ የሚናገሩ ብዙ የወንጌል አማኞች ተብዬዎች አሉ፡፡ ልባቸው በሁሉም ዓይነት መሰረተ ቢስና አሳሳች እምነት ተሞልቷል፡፡ እኔ የመገናኛውን ድንኳን ሳጠና እምነታቸው በእርግጥም ምን ያህል ከንቱና ሐሰት እንደሆነ ይበልጥ በግልጽ ተመልክቻለሁ፡፡ ከዚህ ግንዛቤ የተነሳም እግዚአብሄርን ስለ መዳኔ ከሙሉ ልቤ ይበልጥ አመሰግነዋለሁ፡፡
 
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በርና አጥር፡፡ 
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በርና አጥር፡፡
 
ከዋናው ምንባብ ባለ አራት ማዕዘኑ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ ርዝመት 45 ሜትር ወርዱ ደግሞ 22.5 ሜትር (75 ጫማ) እንደነበር ማወቅ እንችላለን፡፡ አንድ ክንድ ከ0.45 ሜትር (1.5 ጫማ) ጋር እኩል ርዝመት አለው፡፡ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ በሁሉም ማዕዘኖች በ60 ቋሚዎች የተከበበ በመሆኑ የእያንዳንዱ ቋሚ ቁመት 2.25 ሜትር (7.5 ጫማ ነው፡፡ በስተ ምሥራቅ በኩል 9 ሜትር ወርድ ያለው የመግቢያ በር አለ፡፡ ከ135 ሜትር (123 ክንድ) የተረፈው አጥር በሙሉ (ወደ 126 ሜትር (115 ክንድ)) በጥሩ ነጭ በፍታ መጋረጃዎች ተሸፍኖዋል፡፡
 
የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ ተፈትሎ የተሰራ ሲሆን ወርዱ 9 ሜትር (30 ጫማ) ቁመቱ ደግሞ 2.25 ሜትር (7.5 ጫማ) የሚሆን መጋረጃ ለመስራት የተፈተሉ ነበሩ፡፡ በመጀመሪያው ሰማያዊው ማግ በሙሉ ቁመቱና ወርዱ ከነጩ ጥሩ በፍታ ጋር ይፈተላል፡፡ ከዚያም ሐምራዊው ማግ 2.25 ሜትር (7.5 ጫማ) ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር እነዚህ አራት የተለያዩ ማጎች 9 ሜትር (30 ጫማ) በ2.25 ሜትር (7.5 ጫማ) የሚሆን መጋረጃ ለመስራት የተፈተሉ ነበሩ፡፡ በመጀመሪያው ሰማያዊው ማግ በሙሉ ቁመቱና ወርዱ ከነጩ ጥሩ በፍታ ጋር ይፈተላል፡፡ ከዚያም ሐምራዊ ማግ 2.25 ሜትር ቁመት ይዞ ይፈተላል፡፡ ከዚያም ነጩ ማግ ይፈተላል፡፡ ይህም ልክ እንደ ስጋጃ 2.25 ሜትር (7.5 ጫማ) ቁመት ያለው ጠንካራና ወፍራም መጋረጃ ይሆናል፡፡ በዚህ መንገድ ቁመቱ 2.25 ሜትር (7.5 ጫማ) ሆኖ የተፈተለ መጋረጃ በስተ ምስራቅ ባሉት የመገናኛው ድንኳን አደባባይ አራት ቋሚዎች ላይ ይንጠለጠላል፡፡
 
ስለዚህ ሰዎች ወደ መገናኛው ድንኳን አደባባይ ለመግባት ስጋጃ የሚመስለውን መጋረጃ ወደ ላይ መሳብ ነበረባቸው፡፡ የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር እንደ አብዛኞቹ የመግቢያ በሮች ከሳንቃ የተሰራ አልነበረም፡፡ ቋሚዎቹ የተሰሩት ከእንጨት ቢሆንም በእነዚህ ቋሚዎች ላይ የተንጠለጠለው የመግቢያ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ የተፈተለ መጋረጃ ነበር፡፡
 
ከዚህ በፊት በሰርከስ ትዕይንት ላይ ተገኝታችሁ የምታውቁ ከሆነ የሰርከስ ድንኳን እንዴት እንደሚሰራ አይታችኋል፡፡ ብዙውን ጊዜ የመግቢያው በር የሚሰራው ወፍራም ከሆኑ ፈትሎች ነው፡፡ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በርም በመጠኑም ቢሆን ከዚህ ዓይነቱ የመግቢያ በር ጋር ተመሳሳይ ነበር፡፡ ከወፍራም ፈትሎች የተሰራ ስለሆነ በስበት ወይም በመግፋት የሚከፈት አይደለም፡፡ ነገር ግን ለመግባት ወደ ላይ መሳብ አለበት፡፡ ነገሩ እንደዚህ የሆነው ለመገናኛው ደንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ብቻ አይደለም፡፡ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያሉት የቅድስቱና የቅድስተ ቅዱሳኑም የመግቢያ በሮች እንደዚያ ናቸው፡፡
 
እግዚአብሄር እስራኤሎች የመገናኛውን ድንኳን፣ የቅድስቱንና የቅድስተ ቅዱሳኑን ሦስቱንም የመግቢያ በሮች ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ ፈትለው እንዲሰሩ የነገራቸው ለምንድነው? ከዚህ ትዕዛዝ ጀርባ የእግዚአብሄር ፈቃድ ምን እንደበር በግልጽ መረዳት ያስፈልገናል፡፡ የዕብራውያን መጽሐፍ ሊመጡ ያሉት በጎ ነገሮች ሁሉ ሊመጣ ያሉት በጎ ነገሮች ሁሉ ሊመጣ ላለው እውነተኛ ነገር ማለትም ለኢየሱስ ክርስቶስ ጥላዎች እንደነበሩ ይነግረናል፡፡ (ዕብራውያን 10፡1)
 
ልክ እንደዚህ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ በር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በመስቀል ላይ ከሆነው ሞቱና ከገዛ ራሱ ማንነት ጋር በሚገባ የተቆራኘ ነው፡፡ ስለዚህ ብሉይ ኪዳንን መረዳት ካዳገተን አዲስ ኪዳንን በመመልከት ወዲህ አስተውሎት መድረስ እንችላለን፡፡ እውነተኛውን አካል ካላወቅን ጥላውን መለየት አዳጋች ነው፡፡ ነገር ግን ጥላውን የጣለው ምን ወይም ማን እንደሆነ ስንመለከት ጥላው ምን ማለት እንደሆነ መገንዘብ እንችላለን፡፡ እውነተኛውን ሁላችንም እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳን ያዘጋጀው የሐጢያተኞች አዳኝ በትክክል ማን እንደሆነ መረዳት የመገናኛው ድንኳን ትክክለኛ አካል እርሱ እንደሆነ ማወቅና የእርሱ ሥራዎች ከሐጢያቶቻችን ሁሉ እንዳዳነን ማመን አለብን፡፡
 
ታዲያ የመገናኛው ድንኳን እውነተኛ አካልና የሐጢያተኞች አዳኝ የሆነው ማነው? ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ ማንም አይደለም፡፡ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ወደዚህ ምድር መጥቶ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ እንዳዳነን ስንመረምር እርሱ በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ አማካይነት ሐጢያተኞችን ያዳነበትን እርግጠኛ እምነት መረዳት እንችላለን፡፡
 
ኢየሱስ ሐጢያተኞችን ያዳነበትን መንገድ መረዳት በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በሮች ቀለማቶች ውስጥ የተገለጠውን እውነት ማወቅና ማመን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን ውስጥ ጠልቀን ስንገባ የምንረዳው የመጀመሪያው ነገር የአደባባዩ የመግቢያ በር ምስጢር ስንፈታ ያን ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስን ሥራዎች በሙሉ አጥብቀን ወደ መረዳቱ እንመጣለን፡፡ ከእነዚህ አራት ማጎች የተፈተለውን የመጋረጃውን በር በመመልከት እኛ እንደምን ኢየሱስን ማወቅና ማመን እንደሚገባንና የተሳሳተ እምነት ማለት ዓይነት እምነት እንደሆነ በትክክል እንረዳለን፡፡
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የበጎችን በረት ያስታውሰናል፡፡ መሲሃችን ኢየሱስ በእርግጥም የእግዚአብሄር በረት በር ነው፡፡ እርሱ እውነተኛ እረኛም ነው፡፡ (ዮሐንስ 10፡1-15) አደባባዩን ስለከበቡት ቋሚዎች ስናስብ በርና የበጎች ማለትም ዳግመኛ የተወለዱ ቅዱሳን እውነተኛ እረኛ የሆነው መሲህ ይታወሰናል፡፡
 
እረኛው በጎቹን ለመጠበቅ ሲል በበረቱ ዙሪያ መከለያዎች ይኖሩታል፡፡ በዚያም ላይ በር ይሰራል፡፡ በዚህ በር አማካይነትም በጎቹን ይጠብቃል፡፡ እረኛው በዚህ በር አማካይነት ከበጎቹ ጋር የቀረበ ግንኙነት ይኖረዋል፡፡ ይጠብቃቸውማል፡፡ የእርሱ በጎች ለሆኑት ሁሉ በዚህ በር በኩል እንዲገቡ አይፈቀድላቸውም፡፡ እረኛው በተኩላዎችና በበጎች መካከል ይለያል፡፡ በጎች እረኛ የሚያስፈልጋቸው ለዚህ ነው፡፡
 
ነገር ግን በእነዚህ በጎች መካከል በእረኛው መመራት የማይፈልጉ አንዳንድ በጎች መኖራቸው የማይቀር ነው፡፡ እነዚህ በጎች ወደ ሞት እየነጎዱ ያማረና ጥሩ መንገድ ነው ብለው ያስቡ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አሳሳችና አደገኛ መንገድ ነው፡፡ ምክንያቱም የእረኛውን ድምጽ ሰምተው በእርሱ ለመመራት እምቢተኞች ሆነዋልና፡፡ እነዚህ በጎች ሕይወታቸው ሊተርፍና በእረኛው በሚገባ ሊመገቡና በእርሱ የተነሳም ሕይወታቸውን ባማረ መንገድ ሊመሩ ይችሉ ነበር፡፡ እረኛችን መሲሃችን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
 
 
ኢየሱስ ክርስቶስ የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር አራት ቀለማቶች አሳይቶናል፡፡ 
 
የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ይሆን ዘንድ የተንጠለጠለው መጋረጃ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ የተፈተለ ነበር፡፡ ይህ አራት የተለያዩ ቀለማቶች ያሉት ማግ የመገናኛውን ድንኳን የመግቢያ በር ለመስራት አገልግሎዋል፡፡ እነዚህ ማጎች መሲሁ ወደዚህ ምድር በመምጣት የጠፉትን በጎች ማለትም በመላው ዓለም ያሉትን መንፈሳዊ እስራኤሎች ከሐጢያቶቻቸው ለማዳንና ሐጢያት አልባ የሆኑ የእግዚአብሄር ልጆች ሆነው እንዲለወጡ ለማድረግ የሚፈጽማቸውን አራቱን አገልግሎቶች ያመለክታሉ፡፡
 
አራቱን አገልግሎቶቹን ይዞ ወደ እኛ የመጣው መሲሃችን በትክክል ማን እንደሆነ ብናውቅ የማያሻማው እውነት በዚህ እምነት ሐጢያቶቻችን ሁሉ እንደተወገዱና ቀሪውን ዘመናችንን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለማሰራጨት ቀድሰን በመስጠት በዚህ እምነት አማካይነት ሰማይ የምንገባ መሆናችን ነው፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው መሲሁ በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ ወደ እኛ በመምጣት ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ያዳነንን የእውነት ቃል ማወቅ አለበት፡፡
 
በአራቱ የመሲሁ አገልግሎቶች በማመን የሐጢያቶቻችሁን ስርየት መቀበል ትፈልጋላችሁን? እንግዲያውስ ስለ መገናኛው ድንኳን እንማር፡፡ እነዚህን አራቱን አገልግሎቶች የሚያውቁ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ የተፈተለውን የሐጢያቶቻቸውን ስርየት በመቀበል ጻድቃን ይሆናሉ፡፡
 
የእስራኤል ሕዝብ ከአራት የተለያዩ ቀለማቶች የተፈተሉትን የመገናኛውን ድንኳን የመግቢያ በር ማጎች ሲመለከቱ መሲሁ በእርግጥም ወደፊት ይመጣና እነዚህን አራት አገልግሎቶች ይፈጸማል ብለው በተጨባጭ ማመን ነበረባቸው፡፡
 
 
እያንዳንዱ ሐጢያተኛ ሊያምንበት የሚገባ እውነት፡፡ 
 
በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ላይ ነጫጭ መጋረጃዎች ስንመለከት እግዚአብሄር በእርግጥም ምን ያህል ቅዱስ እንደሆነ በመገንዘብ አዳኝ እንደሚያስፈልገን እንረዳለን፡፡ የእግዚአብሄርን ቅድስና ወደ ማወቅ የደረሱ ሁሉ ‹‹አቤቱ በሐጢያቶቼ የተነሳ ለሲዖል የታጨሁ እንደሆንሁ አውቃለሁ፡፡ እኔ የሐጢያት ማከማቻ ነኝ›› ከማለት በስተቀር ማድረግ የሚችሉት ሌላ ነገር የለም፡፡ ንጣቱና ግርማ ሞገሱ ታላቅ ስለሆነ በአደባባዩ ቋሚዎች ላይ የሚውለበለበውን ነጩን በፍታ በማየት ሰዎች በልባቸው ውስጥ የሚገኙትን ሐጢያቶች ይገነዘቡና ከእግዚአብሄር ጋር ለመኖር ፈጽሞ ብቃት እንደሌላቸው ይረዳሉ፡፡ ልባቸው ቀና ያልሆኑ ሰዎች በእግዚአብሄር ፊት ለመቅረብ በሚፈልጉበት ጊዜ ሁሉ ሐጢያቶቻቸው ሁልጊዜም ይገለጣሉ፡፡ ስለዚህ ሰዎች በእግዚአብሄር ፊት ለመቅረብ ያቅማማሉ፡፡ ምክንያቱም ሐጢያቶቻቸው እንዳይገለጡባቸው ይፈራሉና፡፡
 
ነገር ግን እነዚህ ሐጢያተኛ ሰዎች አዳኛቸው በሰማያዊውና በቀዩ ማግ የሐጢያት ችግራቸውን እንደፈታላቸው ሲገነዘቡ በታላቅ የደህንነት አመኔታና በልባቸው ውስጥ ባለው ተስፋ በድፍረት በእግዚአብሄር ፊት መቅረብ ይችላሉ፡፡
 
በመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር የታየው አራት ዕጥፍ እውነት መሲሁ የሰው ሥጋ ለብሶ ወደዚህ ምድር በመምጣት ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀቱ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ እንደወሰደና ደሙንም በመስቀል ላይ እንዳፈሰሰ ይነግረናል፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት አራቱን የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ቀለማቶች እውነት በትክክል ያወቁና ያመኑ ዘላለማዊውን የሐጢያት ስርየት ማግኘት ይችላሉ፡፡ የኢየሱስ ጥምቀትና ስቅለቱ ክርስቶስ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ያዳነን መሆኑ በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ ካሉት አራት የደህንነት ቀለማቶች ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡
 
ሰማያዊው፣ ሐምራዊው፣ ቀዩ ማግና ጥሩው በፍታ ሐጢያተኞችን ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ያዳናቸውን የመሲሁን አገልግሎት በተጨባጭ ያሳየናል፡፡ እግዚአብሄር ለሰው ዘር የሰጠው የደህንነት እውነት በእነዚህ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና በጥሩው በፍታ ውስጥ ተገልጦዋል፡፡ በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ያለባቸውም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ውስጥ በተገለጠው የደህንነት እውነት በማመን ሐጢያቶቻቸው ሁሉ ይቅርታን አግኝተዋል፡፡
 
በዚህ ዓለም ላይ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሐይማኖቶች ብቅ ብለዋል፡፡ እነዚህ ዓለማዊ ሐይማኖቶች በሙሉ ከራሳቸው አስተሳሰቦች የፈለቁትን የራሳቸውን ትምህርቶች ይዘው ሰዎች ቅድስና ላይ እንዲደርሱ ለማድረግ ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን በእነዚህ ዓለማዊ ሐይማኖቶች በኩል ሐጢያቶቹ የተወገደለት አንድም ሰው የለም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በሐጢያት የተሞሉ መሆናቸውን ሳያውቁ በራሳቸው አስተሳሰቦች ላይ በተመረኮዙት የደህንነት ትምህርቶቻቸው ማመናቸው ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው መሰረታዊ ከሆነው የሐጢያት ተፈጥሮው ለመገላገል ምንም ያህል ጠንክሮ ቢሞክርም በራሱ ሐይል ቅዱስ ለመሆን ፈጽሞ የማይችል አንድ ትልቅ የሐጢያት ማከማቻ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ማንም ቅድስና ላይ ሊደርስ አይችልም፡፡ እያንዳንዱ ሰው ከሐጢያት የሚያድነው አዳኝ ማለትም ኢየሱስ የሚያስፈልገው ለዚህ ነው፡፡ ሰብዓዊ ፍጡራን ከኢየሱስ በስተቀር እውነተኛ አዳኝ እንደሌላቸው ማወቅ አለባቸው፡፡
 
 
የእግዚአብሄር ሕግ ሐጢያተኞች ወደ እግዚአብሄር ቤት እንዲገቡ ስለማይፈቅድላቸው መሲሁ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በተጨባጭ እንደደመሰሰ ማወቅና ማመን አለብን፡፡ 
 
ለሰው ዘር ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይቅርታን የሰጠው ወንጌል የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በዓለም ሐይማኖቶች የእምነት ትምህርቶች ማመን ከሐጢያቶቻችን የተነሳ ወደ ከፉ ችግሮች ይመራናል፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ የሆነው አምላካችን ያለ ምንም ማመንታት እያንዳንዱን የሐጢያተኞች በደል ይኮናልና፡፡
 
በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በነጩ በፍታ የተገለጠው እውነት በአዲስ ኪዳን ዘመን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ተፈጽሞዋል፡፡ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር የተሰራው በቀዩ ማግ ብቻ ወይም በቀዩ ማግና በሐምራዊው ማግ ብቻ ነው የሚል ሰው ሰምታችሁ ታውቃላችሁን? እንደዚያ ከሆነ አሁን ከዚህች ቅጽበት ጀምሮ የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር በትክክል የተፈተለው ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ እንደነበር መረዳት አለባችሁ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤሎች የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በፈታይ እጅ ከተሰራ ጥሩ በፍታ እንዲሰሩት አዞዋቸዋል፡፡
 
ነገር ግን ብዙ ሰዎች የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር የተፈተለው ከቀይ ማግ ብቻ ነው ብለው በተሳሳተ መንገድ ስላሰቡ የጌታችንን አራቱን እውነተኛ አገልግሎቶች ምስጢር መፍታት አልቻሉም፡፡ በኢየሱስ አምነው እንኳን በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ያለባቸው ለዚህ ነው፡፡ አሁን ክርስቶስ በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ አገልግሎቶች አማካይነት ሐጢያቶቻችሁን ሁሉ እንደወሰደ ተገንዝባችሁ በዚህ እውነት እመኑ፡፡ በእነዚህ በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ የተፈጸመው የደህንነት ሥራ በእርግጥም ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻችሁ አድኖዋቸዋል፡፡ ኢየሱስ በእነዚህ አራት አገልግሎቶች ሐጢያቶቻችሁን ሁሉ እንደወሰደ መገንዘብ አለባችሁ፡፡ በሌላ አነጋገር ይህንን እውነት ሳታውቁ የራሳችሁን የሐጢያት ስርየት መለኪያ ማስቀመጥ በአጭሩ ስህተት ነው፡፡
 
አንዳንድ ሰዎች ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋሉት የሰማያዊው፣ የሐምራዊውና የቀዩ ማግ ትርጉም ምን እንደሆነ ሳያውቁ ሰው ኢየሱስን አዳኙ አድርጎ በማመን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊድን ይችላል በማለት በስህተት ይናገራሉ፡፡ የክርስቲያን ማህበረሰብ መሪዎችን ስለ አራቱ የኢየሱስ አገልግሎቶች ብንጠይቃቸው ብዙዎቹ እንደማያውቁዋቸው እንገነዘባለን፡፡ እነርሱ የሚያምኑት በቀዩ ማግ ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በአንድ ተጨማሪ ነገር ቢያምኑ በሐምራዊው ማግም እንደሚያምኑ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ጌታችን የሰውን ዘር ለማዳን መስራት ያለበትን ተግባራት ሁሉ የፈጸመው በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ ነው፡፡ በመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ላይ ባሉት ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀዩ ማግና ጥሩ በፍታ የተገለጠውን እውነት የማወቅ ፍላጎት ያለው ሰው ሁሉ ያውቃል፤ ያምንበትማል፡፡
 
‹‹የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውን፣ የቀዩን ማግና የጥሩውን በፍታ ትርጉም መረዳት የሚኖርብኝ እንዴት ነው?›› የማጉንና የበፍታውን እውነት ለሚመረምር ሰው ይህንን ጥያቄ ብትጠይቁት ‹‹መጽሐፍ ቅዱስን በጣም ጠልቀህና በዝርዝር ለማወቅ መሞከር የለብህም፡፡ ሊጎዳህ ይችላል›› ተብላችሁ ትወቀሱ ይሆናል፡፡ የማወቅ ጉጉታችሁም ችላ ሊባል ይችላል፡፡ ብዙ ሰዎችም ተስፋ ቆርጠው ስለ ሰማያዊው፣ ሐምራዊው፣ ቀዩ ማግና ጥሩ በፍታ ለማወቅ ያላቸው ጉጉት ይጠፋል፡፡ በመግቢያው በር አማካይነት በስፋት የተገለጠውን መሲህም ምንጊዜም ቢሆን በፍጹም አይገናኙትም፡፡
 
ሰማያዊው፣ ሐምራዊው፣ ቀዩ ማግና ጥሩው በፍታ የሚጫወቱትን ሚና ሳያውቁ መሲሁን ለመገናኘት የሚሞክሩ ክርስትና ከዓለም ሐይማኖቶች እንደ አንዱ ነው ብለው የሚያምኑ ሐይማኖተኞች ብቻ ናቸው፡፡ ወደ እግዚአብሄር ቤት ለመግባት ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ጥቅም ላይ በዋሉት በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ የተገለጡትን አራቱን የእግዚአብሄር የደህንነት አገልግሎቶች እውነት በትክክል ማወቅ አለብን፡፡ ይህንን እውነት ያገኙ እግዚአብሄር በአዲስ ኪዳን ዘመን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እንደፈጸማቸው መረዳት አለባቸው፡፡
 
እግዚአብሄር ሙሴን የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ ፈትሎ እንዲሰራ አዘዘው፡፡ የዚህ መንፈሳዊ ትርጉም ምንድነው? ለመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋለው የሰማያዊው የሐምራዊው፣ የቀዩ ማግና የጥሩው በፍታ እያንዳንዱ ቀለም ሐጢያቶቻችንን ለማስወገድ ኢየሱስ ለእኛ የሰራው ሥራ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ማጎችና በፍታው እርስ በርሳቸው የተሳሰሩ ናቸው፡፡ በመሆኑም ለውሃውና ለመንፈሱ ወንጌል ትኩረት የሚሰጡና የሚያምኑ በአራቱ የኢየሱስ አገልግሎቶች በዘላለማዊ የሐጢያት ስርየታቸው ማመን ይችላሉ፡፡
 
ይህም ሆኖ በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ ቀለማት ውስጥ የተገለጠውን እውነት ለማወቅ አለመሞከርና ችላ ማለት አንድ ሰው ለመሲሁ ያለውን ፍጹም ግድየለሽነት የሚያሳይና እርሱን በመቃወም የእርሱ ጠላት መሆን ማለት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ የተገለጠውን እውነት ችላ በማለት ክርስትናን ከብዙ ዓለማዊ ሐይማኖቶች እንደ አንዱ አድርገው እየቀየሩት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች አራቱን የኢየሱስ አገልግሎቶች በቸልተኝነት የሚመለከቱዋቸው ከሆነ ክርስቶስን የሚቃወሙ የዓለም ሐይማኖተኞች መሆናቸውን የሚያሳዩባቸው ፍሬዎች እነዚህ ይሆናሉ፡፡ እንደ ዕድል ሆኖ አሁንም ተስፋ አለን፡፡ ምክንያቱም በዚህ ዓለም ውስጥ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል አሁንም የሚሹ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡
 
ሰዎች በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር የተገለጠው መንፈሳዊ የሐጢያት ስርየት ዕውቀት ሲኖራቸው የሰማይን በረከቶች ሁሉ መቀበል ይችላሉ፡፡ ሰው መሲሁን ለመገናኘት ማወቅና ማመን ያለበት ይህንን እምነት ስለሆነ በዚህ ላይ እርፍ ማለት ያለብን አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለዘላለም ነው፡፡ እናንተ በእርግጥም ክርስቲያን ከሆናችሁ በዚህ እውነት ላይ ማተኮር ይገባችኋል፡፡
 
ወደ እግዚአብሄር ቤት መግባት የሚፈልግ ሁሉ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በጥሩው በፍታ የተገለጠውን እውነት መረዳትና በዚያው መሰረትም እግዚአብሄርን ማመስገን አለበት፡፡
 
 
የትንቢቶች ፈጻሚ ሆኖ የመጣው መሲህ፡፡ 
 
እግዚአብሄር በድንግል ሰውነት አማካይነት እንደሚወለድ በቃሉ ተንብዮአል፡፡ ኢሳይያስ 7፡14 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች፡፡›› በሌላ በኩል ሚክያስ 5፡2 መሲሁ በቤተልሔም እንደሚወለድ ይናገራል፡- ‹‹አንቺም ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ አንቺ በይሁዳ ካሉት አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፡፡ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል፡፡›› መሲሁ በዚህ የብሉይ ኪዳን ቃል እንደተተነበየው በእርግጥም ወደዚህ ምድር መጥቶዋል፡፡ በእግዚአብሄር ቃል መሰረት የትንቢቶች ፍጻሜ ሆኖ የሰውን ስጋ በመልበስ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡
መሲሁ ወደዚህ ምድር መጣው በየትኛው የሰው ታሪክ ዘመን ውስጥ ነበር? ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣው መቼ ነበር? እርሱ ወደዚህ ምድር የመጣው የሮም ንጉሰ ነገሥት አውግስጦስ ሲገዛ በነበረበት ዘመን (ከ27 ዓ.ዓለም - 14 ዓ.ም) ነው፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣው ጥምቀትን ከዮሐንስ በመቀበል፣ በመሰቀልና በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ እናንተንና እኔን ከሐጢያቶቻችንና ከኩነኔያችን ለማዳን ነው፡፡
 
ኢየሱስ የሰው ዘር አዳኝ ሆኖ የመጣው እስራኤል በሮማውያን መንግሥት ቅኝ ትገዛ በነበረና አውግስጦስም የዚህ መንግሥት ንጉሰ ነገሥት ሆኖ እየገዛ በነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ እስራኤል የሮም ቅኝ ተገዥ ስለነበረች የሮምን ትዕዛዛቶች መታዘዝ ነበረባት፡፡ በዚህ ጊዜ ንጉሰ ነገሥት አውግስጦስ በመላው የሮማውያን ግዛት የሚኖር እያንዳንዱ ሰው ወደ መኖሪያ አገሩ ተመልሶ ለቆጠራ እንዲመዘገብ አወጀ፡፡ የአውግስጦስን አዋጅ ተከትሎ ይህ ቆጠራ ወዲያውኑ ጀመረ፡፡ ቆጠራው በመንግሥቱ ውስጥ የሚኖረውን በእስራኤል ውስጥ የሚኖሩትንም ጨምሮ እያንዳንዱን ግለሰብ የሚመለከት በመሆኑ እስራኤላውያን ሁሉ ወደ መኖርያ አገሮቻቸው መመለስ ነበረባቸው፡፡ በዚህች ቅጽበት ኢየሱስ ክርስቶስ በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ እየሰራ ነበር፡፡
 
 
የብሉይ ኪዳንን ቃል ፍጻሜ ተመልከቱ፡፡ 
 
በወቅቱ መሲሁ ከይሁዳ ምድር አስቀድሞ በድንግል ማርያም ማህጸን ውስጥ ተጸንሶ ነበር፡፡ ይህች ማርያም የዮሴፍ እጮኛ ነበረች፡፡ ማርያምና ዮሴፍ ከይሁዳ ነገድ ነበሩ፡፡ እግዚአብሄር ለአስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ቃል በገባው መሰረት ነገሥታቶች የሚወለዱት ከይሁዳ ነገድ ብቻ ነው፡፡
ስለዚህ ንጉሰ ነገሥት አውግስጦስ ቆጠራ እንዲሆን ባወጀ ጊዜ ከይሁዳ ነገድ የሆነችው ማርያም በማህጸንዋ ልጅ አርግዛ ነበር፡፡ የምትወልድበት ጊዜ ሲቃረብ ከንጉሰ ነገሥቱ አዋጅ የተነሳ ወደ ዮሴፍ የትውልድ ከተማ ሄዳ በቆጠራው መሰረት መመዝገብ ነበረባት፡፡ በመሆኑም ማርያም በማንኛውም ጊዜ እንደምትወልድ ተስፋ በማድረግ ከዮሴፍ ጋር ወደ ቤተልሔም አቀናች፡፡ ማርያም ምጥ ሲይዛት የምትገላገልበት ክፍል መፈለግ ጀመሩ፡፡ ነገር ግን በከተማው ውስጥ ባዶ ቤት ማግኘት አልቻሉም፡፡ ስለዚህ ያገኙትን ማንኛውንም ስፍራ መጠቀም ነበረባቸው፡፡ በመጨረሻም ግርግም አገኙ፡፡ ማርያምም ሕጻን ልጅዋን ኢየሱስን በከብቶች ግርግም ውስጥ ወለደች፡፡
 
በ1 ዓመተ ምህረት ኢየሱስ ተወልዶ በከብቶች በረት ውስጥ ተቀመጠ፡፡ ሁሉን የሚችለው አምላክ የሰው ሥጋ ለብሶ ወደዚህች ምድር መጣ፡፡ የሰው ዘር አዳኝ ወደ ከብቶች በረት መጣ፡፡ ይህ ማለት ኢየሱስ እንዲህ ባለው እጅግ አስከፊ ስፍራ የተወለደው መሲሃችን ለመሆን ነበር ማለት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች የተዘጋጁትና የታቀዱት ከዓለም ፍጥረት በፊት በእግዚአብሄር ነበር፡፡ ሰዎች የሆዋ አምላክ የሰውን ዘር ታሪክ የሚያንቀሳቅስ መሆኑን ቢያውቁም እነርሱን ለማዳን እግዚአብሄር ራሱ በተጨባጭ ወደዚህ ምድር እንደመጣ የተገነዘበ ማንም አልነበረም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ራሱን ዝቅ አድርጎ ሰብዓዊ ፍጥረቶችን ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን ዝቅ ባለ የሰው አካል ውስጥ ሆኖ በመወለድ እያንዳንዱን ሰው ለማዳን ወደዚህ ምድር መምጣቱን ሰው ሁሉ እንዲገነዘብ አስችሎዋል፡፡
 
ታዲያ ኢየሱስ ከሌሎች ስፍራዎች ሁሉ ይልቅ በቤተልሔም የተወለደው ለምንድነው? ለምን በከብቶች ግርግም ውስጥ ተወለደ? ከዘመን ሁሉ መርጦ እስራኤሎች በሮም ቅኝ ተገዥ በነበሩበት ዘመንስ ለምን ተወለደ? እነዚህ ነገሮች ሁሉ የመጡት የራሱን ሕዝብ ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን በጥንቃቄ በተነደፈ ግልጽ ጣልቃ ገብነቱ አማካይነት እንደሆነ ፈጥነን መረዳት እንችላለን፡፡
 
ዮሴፍና ማርያም በመኖሪያ ከተማቸው ለመቆጠር በተመዘገቡ ጊዜ በእርግጥም የዚህች ከተማ ሰዎች መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብና ትክክለኛ ማንነታቸውን በማስረጃ ማስደገፍ ነበረባቸው፡፡ ለቆጠራው መመዝገብ የሚችሉት ዘር ማንዘሮቻቸው ለብዙ ትውልዶች በቤተልሄም ይኖሩ እንደነበር የሚያረጋግጥ አስፈላጊ መረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ነበር፡፡ ስለዚህ ዘር ማንዘሮቻቸው እነማን እንደነበሩና በእነማን ቤቶች እንደተቀመጡ ማብራራትና የቤተሰብ የዘር ሐረጋቸውን ዝርዝሮች ሁሉ ማስመዝገብ ነበረባቸው፡፡ ከእነዚህ መረጃዎች አንዱ የፈጠራ ሊሆን ስለማይችል ወይም ስለማይገደፍ የዮሴፍንና የማርያምን ትክክለኛ የማንነት ታሪካዊ ዘገባዎች በመጠቀም እግዚአብሄር የሰው ዘር ታሪክ የኢየሱስን ውልደት እንደሚመሰክር አረጋገጠ፡፡ (ማቴዎስ 1፡1-16፤ ሉቃስ 3፡23-28) እነዚህ ሁሉ እግዚአብሄር የብሉይ ኪዳን ትንቢቶችን ለመፈጸም የሰራቸው የራሱ ሥራዎች ነበሩ፡፡
 
ሚክያስ 5፡2 እንዲህ ይላል፡- ‹‹አንቺም ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ አንቺ በይሁዳ ካሉት አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፡፡ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል፡፡›› ዮሴፍና ማርያም ወደ ከተማይቱ እንዲገቡ በማድረግ የመውለጃው ጊዜ መቃረቡና መድህንም በትክክል ትንቢት በተነገረላት በቤተልሔም ከተማ መወለዱ እግዚአብሄር የነቢያቶቹን ትንቢቶች ለመፈጸም ይህንን ሥራ መስራቱን የሚያሳይ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ለመደምሰስ ሲል በእርግጠኝነት ያቀደው ክንውን ነበር፡፡ ኢየሱስ በትንሽዋ የቤተልሔም ከተማ መወለድ የነበረበት የብሉይ ኪዳንን የትንቢት ቃል ለመፈጸም ነበር፡፡
 
ኢየሱስ በትንሽዋ የቤተልሔም ከተማ ከመወለዱ ከመቶ ዓመታቶች በፊት እግዚአብሄር ከላይ እንደተጠቀሰው የትንቢት ቃሉን በነቢዩ ሚክያስ በኩል ሰጥቶ ነበር፡፡ (ሚክያስ 5፡2) ነቢዩ ኢሳይያስም እንደዚሁ ጌታችን ከመምጣቱ ከ700 ዓመታቶች በፊት መሲሁ የሐጢያተኞች አዳኝ ለመሆን እንዴት ወደ ሕዝቡ እንደሚመጣ ተንብዮአል፡፡ (ኢሳይያስ 53) እግዚአብሄር በነቢዩ ሚክያስ በኩል እንደተነበየው ኢየሱስ ክርስቶስ በእርግጥም በቤተልሄም ተወለደ፡፡ እርሱ ሁልጊዜም የትንቢት ቃሉን ሁሉ ይፈጽማል፡፡
 
ማርያምና ዮሴፍ ለመቆጠር ይመዘገቡ ዘንድ ወደ ትውልድ ከተማቸው በሄዱ ጊዜ ይህ ትንቢት ታሪካዊ ሐቅ ሆኖ ተፈጸመ፡፡ እግዚአብሄር ሕጻኑ የሚወለድበት ጊዜ ማርያም ቤተልሔም ስትደርስ እንደሚሆን በማረጋገጥ ቃሉን ፈጸመ፡፡ እርስዋም በዚህች ከተማ ውስጥ ከመወለድ በስተቀር ምርጫ አልነበራትም፡፡
 
እዚህ ላይ አምላካችን ለእኛ የትንቢት ቃሉን በመናገር ያንን ቃል በሙሉ በዚህ መሰረት የሚፈጽም አምላክ መሆኑን እንረዳለን፡፡ ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋለው ‹‹ጥሩ የተፈተለ በፍታ›› የእግዚአብሄርን ቃል ድንቅነትና ምሉዕነት እንደሚያመለክት ከዚህ መረዳት እንችላለን፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ዘር ደህንነት ከፍጥረት በፊት በይፋ አቀደ፡፡ ይህንኑም ያለ ምንም እንከን በትንቢት ቃሉ መሰረት ፈጸመው፡፡
 
ስለዚህ የብሉይ ኪዳን ቃል በእርግጥም እንደሆነ የአዲስ ኪዳንም ቃል እንደዚሁ የእግዚአብሄር ቃል እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ እግዚአብሄር በእርግጥም በአጽናፈ ዓለማትና በዚህ ምድር ታሪክ ሁሉ ላይ እንደሚሰለጥንና ያንንም ታሪክ እንደሚያንቀሳቅስ እንገነዘባለን፤ እናምንማለን፡፡ በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር አጸናፈ ዓለማትን ሁሉ እንደፈጠረ ሁሉ በሰዎች ሁሉ ላይ፣ በታሪኮች ሁሉ ላይና በእያንዳንዱ ሰው ሁኔታዎች ሁሉ ሙሉ በሙሉ እንደሚሰለጥን እያሳየን መሆኑን እንረዳለን፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር እርሱ እስካልፈቀደው ድረስ በአንድ ሰው ፈቃድ የሚፈጸም ምንም ነገር እንደሌለ አሳይቶናል፡፡
 
ሕጻኑ ኢየሱስ ሲወለድና ወደዚህ ምድር ሲመጣ የተወለደው በከብቶች በረት ውስጥ ነበር፡፡ ምክንያቱም የማደርያ ስፍራ አልነበረምና፡፡ እርሱ ራሱ በእርግጥም በቤተልሔም ተወለደ፡፡ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እግዚአብሄር በታማኝነቱ መሰረት የተተነበየውን ጣልቃ ገብነት ያከናወነበት ድንቅ ክንውን እንደነበሩ መረዳት አለብን፡፡
 
ስለዚህ የዚህን ዩኒቨርስ ታሪክ የሚያንቀሳቅሰው ከሐጢያቶቻችን ያዳነን አዳኝ የሆነው አምላካችን መሆኑን ማመን አለብን፡፡ ይህ እውነት እርሱ በሁሉም ላይ የሚሰለጥን መሆኑን የሚያሳየን የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ እግዚአብሄር የሁሉ ጌታ ነውና፡፡
 
ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሽዋ የቤተልሔም ከተማ መወለዱ አጋጣሚ እንዳልሆነ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በመጠምዘዝም ሆነ ተብሎ የተፈጠረ እንዳልሆነ አሁን ተረጋግጦዋል፡፡ እግዚአብሄር ራሱ በኢየሱስ አማካይነት የፈጸመውም ይህንኑ ነው፡፡
 
ይህንን ማወቅ አለብን፡፡ ልናምንበትም ይገባናል፡፡ በልባችን ውስጥ ልንቀብረውና የመሲሃችን ማዳን በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ የተፈጸመ እውነት መሆኑን ማመን አለብን፡፡ የሐጢያት ስርየትም እንደዚሁ በድንገት የተከናወነ ሳይሆን በእግዚአብሄር ጣልቃ ገብነት በአራቱ የኢየሱስ አገልግሎቶች አማካይነት የተከናወነ አንዳች ነገር እንደሆነ እግዚአብሄር አሳይቶናል፡፡
 
ይህም በተጨማሪ ክርስትና ከዓለማዊ ሐይማኖቶች አንዱ እንዳልሆነ ያሳየናል፡፡ የዓለማዊ ሐይማኖት መስራች ተራ ሟች ሰው ነው፡፡ የክርስትና መስራች ግን አዳኛችን ኢየሱስ ነው፡፡ የክርስትና እውነት የሚጀምረው የእኛ አዳኝ ራሱ አምላክ በመሆኑ እውነታ እንደሆነ እግዚአብሄር አሳይቶናል፡፡ በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር የምናምንበት ክርስትና ተራ ዓለማዊ ሐይማኖት እንዳልሆነ እየመሰከረልን ነው፡፡ ከሌሎች ምድራዊ ሐይማኖቶች በተቃራኒ ክርስትና የተመሰረተው በእግዚአብሄር በተሰጠው ጸጋ ሁሉ ላይ ነው፡፡ በሮሜ 11፡36 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን አሜን፡፡›› እርሱ አዳኛችን ይሆን ዘንድ አንድያ ልጁን ለሐጢያቶቻችን ስርየትም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በውስጣችን የሚያድረውን መንፈስ ቅዱስና መንግሥተ ሰማያት ሰጠን፡፡ ስለዚህ ሁላችንም እግዚአብሄርንና ቃሉን ከሙሉ ልባችን መፍራትና መታዘዝ እንደሚገባን ማወቅና በልባችን ማመን አለብን፡፡
 
መሲሁ በዚህ ምድር ላይ የተወለደው ከዓለም ፍጥረት በፊት በእግዚአብሄር አብ በተወሰነው የደህንነት ዕቅድ መሰረት ነው፡፡ ደህንነታችን በዚህ ውስጥ ፈጽሞ የታቀደ ነበር፡፡ እግዚአብሄር ይህ እውነት የሰማያዊው፣ የሐምራዊው፣ የቀዩ ማግና የጥሩው በፍታ ተጨባጭ ፍጻሜ እንደሆነ በግልጽ እንድናውቅ ፈቅዶልናል፡፡ ስለዚህ ለሐጢያቶቻችን ስርየት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በኩል የመጣውን ደህንነት መረዳትና እንደዚያው ማመን አለብን፡፡ እናንተና እኔ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ መዳን የምንችለው በዚህ እምነት አማካይነት ነው፡፡ ይህ የአራቱ ቀለማት እውነት ምሉዕ የሆነው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ቃል ባለን እምነት መሆኑን ማመን አለብን፡፡
 
 

በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ ያዳነን አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ 

 
ኢየሱስ ክርስቶስ ሐጢያተኞችን ከሐጢያቶቻቸው ያዳነባቸው ሥራዎች አራት ናቸው፡፡ እነርሱም ሰማያዊው ማግ፣ (የኢየሱስ ጥምቀት) ሐምራዊው ማግ፣ (ኢየሱስ የነገሥታት ንጉሥ መሆኑ -- በሌላ አነጋገር ራሱ አምላክ መሆኑ) ቀዩ ማግና (የኢየሱስ ደም) ጥሩው በፍታ (በተብራራው የብሉይና የአዲስ ኪዳናት ቃል አማካይነት ሐጢያተኞች ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ መዳናቸው መጠናቀቀቁ) ናቸው፡፡ ኢየሱስ በሰማያዊው ማግ፣ በሐምራዊው ማግ፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ በግልጽ አዳኝ ሆኖዋል፡፡
 
በውሃና በመንፈስ ወደ እኛ የመጣው ኢየሱስ በሰማያዊው ማግ፣ (የኢየሱስ ጥምቀት) በሐምራዊው ማግ፣ (ኢየሱስ አምላክ ነው) በቀዩ ማግና (የኢየሱስ ደም) በጥሩው በፍታ (በአዲስና በብሉይ ኪዳናት ቃል ደህንነትን የከወነው ኢየሱስ) ከሐጢያቶቻችን እንዳዳነን እስካላመንን ድረስ ከሐጢያቶቻችን፤ ከእነዚህ ሐጢያቶች ኩነኔ በፍጹም ነጻ አንወጣም፡፡ ጌታችን በዚህ ሁኔታ ከሐጢያቶቻችንና ከኩነኔ ባያድነን ኖሮ ፍጹም አዳኝ መሆን አይችልም ነበር፡፡
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር መጋረጃ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ ተፈትሎ የተሰራበትን መንፈሳዊ ምክንያት መረዳት አለብን፡፡ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ከእነዚህ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና ጥሩ በፍታ የተሰራው ሁሉም በግልጽ በሩን እንዲያውቀውና በቀላሉ እንዲያገኘው ነው፡፡ እግዚአብሄር በዚህ የመግቢያ በር አማካይነት ማንም ሰው ወደሚያበራው ቤቱ እንዲገባ ፈቅዶዋል፡፡
 
የመገናኛው ድንኳን ራሱ የሚያበራ የእግዚአብሄር ቤት ነው፡፡ ወደ እግዚአብሄር ቤት መግባት የሚፈልግ ሰው በአጥሩና በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር የተገለጠውን የደህንነት እውነት ሳይገነዘብ መግባት አይችልም፡፡ እግዚአብሄር በመገናኛው ድንኳን ላይ የሚውለበለበውን ነጩን የበፍታ መጋረጃ ቅድስና ችላ ብለው ወደ መገናኛው ድንኳን በበሩ በኩል ሳይሆን በሌላ መንገድ ዘለው የሚገቡ ሁሉ ሌቦችና ዘራፊዎች መሆናቸውን ተናግሮዋል፡፡ የደህንነቱ በር ኢየሱስ ክርስቶስን ያመለክታል፡፡ (ዮሐንስ 10)
 
መጽሐፍ ቅዱስ ይህ የመግቢያ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ የተፈተለ መሆኑን ሲናገር እግዚአብሄር እውነተኛ በሆነው የብሉይና አዲስ ኪዳናት ቃል አማካይነት ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅ ሆኖ ወደዚህ ምድር መምጣቱን፣ በመስቀል ላይ መሞቱን፣ ዳግመኛም ከሙታን መነሳቱንና መሲሃችንን መሆኑን በግልጽ እያሳየን መሆኑን መናገሩ ነው፡፡ በዚህም የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውን፣ የቀዩን ማግና የጥሩውንም በፍታ ምስጢር መፍታት እንችላለን፡፡ እግዚአብሄር ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከዚህ ዓለም ሐጢያቶች ፍርድ ለማዳን የመጣና በብሉይና በአዲስ ኪዳናት ቃል አማካይነትም አሁን የሰው ዘርን ደህንነት ያጠናቀቀ አዳኝ መሆኑን ማመን አለብን፡፡
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ለምን በእነዚህ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና ጥሩ በፍታ ተፈትሎ እንደተሰራ በትክክል መረዳት መቻል አለብን፡፡ ሰማያዊው ማግ ምን ይነግረናል? ሐምራዊው ማግ፣ ቀዩ ማግና ጥሩው በፍታስ ምን ይነግሩናል? የእግዚአብሄርን ፈቃድ ስንገነዘብ የሰማያዊው፣ የሐምራዊው፣ የቀዩ ማግና የጥሩው በፍታ ሥራዎች በሙሉ እግዚአብሄር ለእኛ ያለው የደህንነት ዕቅድና የዘላለም ሕይወት እውነት እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ በዚህም በሐጢያት ስርየት ላይ ባለን እምነታችን አማካይነት ወደ መንግሥቱ መግባት እንችላለን፡፡
 
ሰማያዊውን፣ ሐምራዊውንና ቀዩን ማግ እናውቀዋለን፤ እናምንበታለንም ስንል ኢየሱስ ለምን በአጥማቂው ዮሐንስ እንደተጠመቀና በመስቀል ላይ ደሙን እንዳፈሰሰ፣ መሲሁ ማን እንደሆነ፣ የብሉይ ኪዳን የመስዋዕት ስርዓት ምስጢራቶችን ሁሉና የአዲስ ኪዳንን የውሃና የመንፈስ ወንጌል እናውቃለን ማለታችን ነው፡፡ በአጭሩ በመገናኛው ድንኳን አደበባይ የመግቢያ በር የተገለጠው እውነት ለዘላለም ለመዳን ሲሉ እውነትን ከልባቸው ለሚሹ ምዕመናኖች ሁሉ አስፈላጊ ነው፡፡
 
ብዙ ሰዎች ስለ መገናኛው ድንኳን ዕውቀት ያላቸው ይመስላል፡፡ ነገሩ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ ሰዎች በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ ያሉት ሰማያዊው፣ ሐምራዊውና ቀዩ ማግ ምን ማለት እንደሆኑ አያውቁም፡፡ የእነዚህ የሰማያዊው፣ የሐምራዊው፣ የቀዩ ማግና የጥሩው በፍታ ምስጢር ለመረዳት አስቸጋሪ ስለሆኑ ብዙ ሰዎች የመማርና በእነርሱ የማመን እውነተኛ ፍላጎት አላቸው፡፡ ነገር ግን ይህ ምስጢር በማንም ሰው እንዲያው ዝም ብሎ የሚስተዋል ስላይደለ ከእነርሱ ብዙዎቹ በራሳቸው አመለካከቶች ላይ ተመስርተው በተሳሳተ መንገድ ተርጉመውታል፡፡ እንዲያውም ብዙ የሐይማኖት መሪዎች ለራሳቸው ሐይማኖታዊ ዓላማዎች በሚጠቅም መልኩ ብቻ ይህንን እውነት በመሰላቸው በማንኛውም መንገድ አሳስተው ተርጉመውታል፡፡ አሳስተውም አስተውለውታል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ክርስቲያኖች በእነዚህ ውሸታሞች በመታለል እንዲቀጥሉ አልፈቀደም፡፡ ስለዚህ በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ ያለውን የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውን፣ የቀዩን ማግና የጥሩውን በፍታ እውነት ትርጉም በግልጽ በማብራራት ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ማዳን ነበረበት፡፡
 
በአዲስ ኪዳን 1ኛ ዮሐንስ 5፡6-8 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በውሃና በደም የመጣ ይህ ነው፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ በውሃ ብቻ የመጣ ሳይሆን በውሃና በደም የመጣ ነው፡፡ የሚመሰክረውም መንፈሱ ነው፡፡ መንፈስ እውነት ነውና፡፡ በሰማይ የሚመሰክሩ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም አብ፣ ቃልና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ እነዚህ ሦስቱ አንድ ናቸው፡፡ በምድር ላይ የሚመሰክሩ ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም መንፈስ፣ ውሃና ደም ናቸው፡፡ እነዚህ ሦስቱ በአንድ ይስማማሉ፡፡›› (በቀጥታ ከእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ የተተረጎመ) ይህ ምንባብ ጌታችን የሰው ሥጋ ለብሶ ወደዚህ ምድር በመምጣት በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን እንደወሰደና ደሙን በማፍሰስም እንዳዳነን በግልጽ ይናገራል፡፡ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ የተፈተለው ለዚህ ነው፡፡
 
በመጀመሪያ ሰማያዊው ማግ የሚያሳየን ምንድነው? ወደዚህ ምድር መጥቶ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በመውሰድ እውነተኛ የሐጢያተኞች መሲህ የሆነውን በኢየሱስ ላይ ያለውን የእውነት ክፍል ያሳያል፡፡ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ከዮሐንስ የተቀበለው ይህ ጥምቀት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በራሱ ላይ የወሰደ መሆኑን የሚያሳይ እውነት ነው፡፡ ኢየሱስ የሰው ዘር ሁሉ ወኪል በሆነው በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በተጨባጭ በጫንቃዎቹ ላይ ተሸከመ፡፡ የሰብዓዊ ፍጡራን ሐጢያቶች በሙሉ በዚህ ሁኔታ ወደ ኢየስስ ክርስቶስ ራስ ላይ በመሻገራቸው በዚህ እውነት የሚያምኑ በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያት የለባቸውም፡፡
 
ሁለተኛ በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ ፈትሎ የተንጠለጠለው የሐምራዊ ማግ እውነተኛ ትርጉም ምንድነው? ኢየሱስ ትክክለኛው የነገሥታት ንጉሥ መሆኑን ያሳየናል፡፡ በእርግጥም ኢየሱስ አጽናፈ ዓለማትን ፈጥሮዋል፡፡ ፍጡር ሳይሆን ራሱ ፈጣሪ ነው፡፡ ወደዚህ ምድር የመጣ እውነተኛ መሲህም ነው፡፡ እርሱ መሲህ ሆኖ በሰው ሥጋ ምሳሌ ሆኖ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነተም የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በሥጋው በመሸከም በመስዋዕታዊ ሞቱና በትንሳኤው ኢየሱስ መሲሃቸውን ያወቁትን፣ የፈሩትንና ያመኑትን የእርሱን ሕዝቦች በሙሉ ከሐጢያቶቻቸው ሁሉና ከሐጢያት ኩነኔያቸው አዳናቸው፡፡
 
ኢየሱሰ በእርግጥም ፍጹም አምላካችንና ፍጹም መሲሃችን ነው፡፡ እርሱ ፍጹም አዳኝ ነው፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ፣ በመስቀል ላይ በመድማቱና በመሞቱ እንዲሁም ከሙታን በመነሳቱ የዓለም ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ ስለወሰደ ሐጢያቶቻችንን ከማስወገዱም በላይ በእኛ ፋንታም ይፋ የሆነ የሐጢያት ፍርድ ተቀበለ፡፡
 
ሦስተኛ ቀዩ ማግ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ያፈሰሰውን ደሙን ያመለክታል፡፡ ትርጓሜውም ክርስቶስን ለምናምን ለእኛ አዲስ ሕይወት የሰጠን መሆኑ ነው፡፡ ይህ የቀዩ ማግ እውነት ኢየሱስ ክርስቶስ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት የዓለምን ሐጢያቶች በራሱ ላይ በመውሰድ የሐጢያቶቻችንን ፍርድ መቀበሉን ብቻ ሳይሆን ለሐጢያት በመሞቱ ሕይወት የሚሰጠውን እምነት በመለገስ ለምዕመናን አዲስ ሕይወትን እንደሰጠ ይነግረናል፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱና ባፈሰሰው ደሙ ለሚያምኑት በእርግጥም አዲስ ሕይወትን ሰጥቶዋቸዋል፡፡
 
ታዲያ ጥሩው በፍታ ምን ማለት ነው? በአዲስ ኪዳን እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳን የተጻፈው የደህንነት ተስፋ መፈጸሙን ይገልጣል፡፡ ኢየሱስ በአዲስ ኪዳን በጥምቀቱ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በወሰደና ለሐጢያቶቻችንም በመስቀል ላይ በተኮነነ ጊዜ እግዚአብሄር በኪዳኑ ቃል ለእስራኤሎችና ለእኛ ቃል የገባውን ደህንነት መፈጸሙንም ይነግረናል፡፡
 
የሆዋ እግዚአብሄር በኢሳይያስ 1፡18 ላይ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሄር፤ ሐጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች፡፡›› የእሰራኤል ሕዝብ ሐጢያቶች በእጆች መጫን ለመስዋዕት ወደቀረበው ጠቦት የሚሻገርበትና መስዋዕቶች በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚቀርቡበትን መንገድ የሚያስተዳድረው የብሉይ ኪዳኑ የመስዋዕት ስርዓት እግዚአብሄር ለእሰራኤሎችና ለእኛ የሰጠው ተስፋ ነበር፡፡ ይህም እግዚአብሄር ወደፊት በሚመጣው የእግዚአብሄር በግ በኩል የዓለምን ሕዝቦች በሙሉ በየቀኑና በየዓመቱ ከሚሰሩዋቸው ሐጢያቶች እንደሚያድናቸው የሰጠው የእግዚአብሄር ተስፋ መገለጥ ነው፡፡
 
ይህ ተስፋ የተሰጠው መሲህ እንደሚመጣ የሚያሳይ ምልክትም ነበር፡፡ ስለዚህ በአዲስ ኪዳን ዘመን ኢየሱስ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን መንገድ መሰረት በጥምቀቱ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ በተሸከመ ጊዜ የእግዚአብሄር ኪዳን ተፈጸመ፡፡ እግዚአብሄር የተስፋ ቃሉን ሁሉ ከሰጠን በኋላ በሰጠው ተስፋ መሰረት ሁሉንም በትክክል እንደፈጸመ አሳየን፡፡ ኢየሱስ የተቀበለው ጥምቀት የቃል ኪዳኑ አምላክ ቃል ኪዳኖቹን በሙሉ የፈጸመ የመሆኑን ይህንን እውነት ይገልጣል፡፡
 
 

በውሃ፣ በደምና በመንፈስ የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ 

 
ኢየሱስ ለምን በዮሐንስ ተጠመቀ? የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ ለመውሰድና በእኛ ፋንታም የሐጢያትን ፍርድ ለመቀበል ነበር፡፡ ኢየሱስ የመላውን ሰው ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ለማስወገድና እውነተኛ አዳኛችን ለመሆን በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ ወደ መስቀል ሄደ፡፡ በመስቀል ላይም ደሙን አፈሰሰ፡፡ ሞተም፡፡ ይህንን በማድረጉም ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ከማስወገዱም በላይ የእነዚህን ሐጢያቶች ፍርድ በምትካችን ተቀብሎ ዘላለማዊ አዳኛችን ሆነ፡፡ ኢየሱስ በዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ሐጢያቶቻችን በሙሉ ወደ እርሱ ተሻገሩ፡፡ እነዚህን የዓለም ሐጢያቶች በሙሉም በመስቀል ላይ ተሸከመ፡፡ ኢየሱስ የተሰቀለው፣ ደሙን ያፈሰሰውና በእኛ ፋንታ የሞተው ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በጥምቀቱ ስለተሸከመ ነው፡፡
 
ኢሳይያስ 53፡5 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቆሰለ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደህንነታችንም ተግሳጽ በእርሱ ላይ ነበረ፡፡ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን፡፡›› በጌታችን ጥምቀት አማካይነት ከጋራ ቅድመ አያታችን ከአዳም የወረስናቸው የመጀመሪያ ሐጢያቶቻችንና በሕይወት ዘመናችን ሁሉ የፈጸምናቸው ሐጢያቶቻችን በሙሉ ወደ እርሱ ተሻግረዋል፡፡ እርሱም ለእነዚህ ሐጢያቶች በሙሉ ተኮንኖዋል፡፡ ጌታችን በውሃና በደም እንዲህ ሆኖ በመምጣት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ አስወገደ፡፡ (1ኛ ዮሐንስ 5፡5-8)
 
ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወስዶ ያስወገዳቸው ይህ አዳኛችንና መሲሃችን ኢየሱስ ከክርስቶስ ታዲያ ማነው? ዘፍጥረት 1፡1 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በመጀመሪያ እግዚአብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ፡፡›› አጽናፈ ዓለማትን በቃሉ የፈጠረው ይህ ብርቱ አምላክ ማነው? እርሱ እናንተንና እኔን ከዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ለማዳን በጥምቀቱ ውሃ የመጣው፣ ለዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ለመኮነን አዳኝ ሆኖ በመስቀል ላይ ለመድማት የመጣው የሐጢያተኞች መሲህ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ኢየሱስ በውሃው፣ በደሙና በመንፈሱ አማካይነት ከሐጢያቶቻችንና ከፍርድ አዳነን፡፡ ጌታችን ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለመውሰድና በእኛ ፋንታም ለእነዚህ ሐጢያቶች ለመኮነን ወደ እኛ መጣ፡፡
 
ኢየሱስ ክርስቶስ በእርግጥም የእግዚአብሄር ልጅና ራሱም አምላክ ነበር፡፡ መሲሁ በእርግጥም አምላካችን ነው፡፡ ‹‹ኢየሱስ›› የሚለው ስም ‹‹ሕዝቡን ከሐጢያቶቻቸው የሚያድን አዳኝ›› ማለት ነው፡፡ (ማቴዎስ 1፡21) በሌላ በኩል በግሪክ ‹‹ክርስቶስ›› ‹‹ባሲሊየስ›› ማለት ‹‹የነገሥታት ንጉሥ›› ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ አጽናፈ ዓለማትን ሁሉ የፈጠረ ፈጣሪና የሁሉ ፍጹም ገዥ፣ የሐጢያተኞች አዳኝና በሰይጣን ላይ የሚፈርድ የነገሥታት ንጉሥ ነው፡፡
 
ይህ ፍጹም አምላክ ሰውን በራሱ አምሳል ፈጠረው፡፡ የእርሱ ፍጥረት የሆንነው እኛ በድካሞቻችን ምክንያት በሐጢያት ወድቀን ለጥፋት በተፈረደብን ጊዜ ይህ የነገሥታት ንጉሥ ከሐጢያቶቻችን ሊያድነን ቃል ገባልን፡፡ ይህንን ተስፋ ለመፈጸምም ወደ እኛ መጣ፡፡ የእግዚአብሄር ሕዝብና ሐጢያት አልባ ሊያደርገንም ጌታችን ራሱ በውሃ፣ በደምና በመንፈስ መጣ፡፡
 
ፈጣሪ የሆነው መሲህ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ለማስወገድ በተጨባጭ የሰው ሥጋ ለበሶ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ በዮርዳኖሰ ወንዝም ከዮሐንስ በመጠመቅ ሐጢያቶቻችንን በራሱ ላይ ወሰደ፡፡ በመስቀል ላይ በመሞትም በምትካችን ለሐጢያቶቻችን ሁሉ ተኮነነ፡፡ ኢየሱስ በእርግጥም መሲሃችን ስለሆነ፣ አዳኛችንና የሕይወታችን ጌታም ስለሆነ በእርሱ በማመን አዲስና ዘላለማዊ ሕይወት ማግኘት ቻልን፡፡ ስለዚህ መሲሁ በእርግጥም አምላካችን ሆንዋል፡፡ የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ የተፈተለው ለዚህ ነው፡፡ ምክንያቱም ከሐጢያቶቻችን ሁሉና ከሐጢያቶቻችን ፍርድ የሚያድነን የውሃውና የመንፈሱ ምስጢር ይህ ነውና፡፡
 
ጌታ በእርግጥም ከሐጢያቶቻችን ያዳነን የመሆኑ እውነት ደብዛዛ አይደለም፡፡ ጌታችን መዳናችንን አሻሚ አላደረገውም፡፡ በደፈናውም አልከወነውም፡፡ በውሃውና በደሙ በተጨባጭ ያዳነን ከመሆኑ እርግጠኛ እውነት ውጭ በዘፈቀደ የሚያምኑትን ሰዎች እምነትም ሊደግፍ አይችልም፡፡ ስለዚህ ጌታችን እንዲያው በደፈናው በእርሱ ለሚያምኑት እንዲህ ብሎዋቸዋል፡- ‹‹በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡›› (ማቴዎስ 7፡21)
 
ሐሰተኛ አስተማሪዎች ሰዎች በተጨባጭ በኢየሱስ ስም መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ እንደሚያደርጉ፣ በስሙም አጋንንቶችን እንደሚያወጡና በስሙም ብዙ ድንቆችን እንደሚከውኑ ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሄር ግን በማቴዎስ 7፡23 ላይ እንዲህ ነግሮዋቸዋል፡- ‹‹ከቶ አላወቅኋችሁም እናንተ ዓመጸኞች ከእኔ ራቁ፡፡›› ይህም በክርስቲያኖች መካከል አሁንም ሐጢያተኞች ሆነው የቀሩ፣ በፍርድ ቀንም ለሐጢያቶቻቸው የሚኮነኑና ወደ ሲዖል የሚጣሉ ብዙዎች እንዳሉ ይነግረናል፡፡
 
‹‹ኢየሱስ አዳኛችን ነው፡፡ ኢየሱስ በማያሻማ መንገድ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ አድኖናል›› ብለው በግልጽ የሚያምኑ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸው እርግጥ ነው፡፡ ነገር ግን እንደዚህ ቢሉም መሲሁ በእርግጥም በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ ሐጢያቶቻቸውን እንደወሰደ፣ በእርግጥም በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ ሐጢያቶቻቸውንና የእነዚህን ሐጢያቶች ፍርድ እንደተሸከመ ለመማር እንኳን አይሞክሩም፡፡ እነዚህ ሰዎች ሁሉ አሁንም ሐጢያተኞች ሆነው በእግዚአብሄር ፊት ይቀርባሉ፡፡ ምክንያቱም ከዓለም ብዙ ሐይማኖቶች አንዱን እየተለማመዱ ያሉ ይመስል የሚያምኑት በዘፈቀደ ነውና፡፡
 
ስለዚህ ‹‹እውነትን ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል›› ብሎ ኢየሱስ በተናገረው እውነት መሰረት ስለሚያምኑ በጌታ ዘንድ ተቀባይነት አላገኙም፡፡ ሰዎች በኢየሱስ ቢያምኑም ባያምኑም በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ያለባቸው ሐጢያት ወደማይገኝበት የእግዚአብሄር መንግሥት መግባት አይችሉም፡፡ ምክንያቱም እዚያ ለመግባት ብቁ አይደሉም፡፡ ስለዚህ ሰማይ ለመግባት ብቃት እንዳላቸው ማረጋገጥ የሚችሉት በዚህ ምድር ላይ ሳሉ በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ እውነት ሲያምኑ ብቻ ነው፡፡ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር መጋረጃ በእነዚህ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና ጥሩ በፍታ ተፈትሎ እንዲሰራ ያደረገው የመሲሁ ቸርነት ነው፡፡ በሐጢያት ምክንያት ወደ ሲዖል እየነጎዱ ያሉ በዚህ ማመን አለባቸው፡፡
 
እነዚህ ሰዎች እውነቱን ስለማያውቁና በራሳቸው መንገድ በደረሱበት የተሳሳተ ዕውቀታቸው በኢየሱስ ስለሚያምኑ አሁንም ሐጢያተኞች ሆነው ቀርተዋል፡፡ አሁንም ሐጢያት አለባቸው፡፡ ምክንያቱም በመገናኛው ድንኳን ቁሶች ውስጥ በተደበቀው እውነት ከማመን ይልቅ በራሳቸው መንገድ ስለ አዳኛቸው በማሰብና በእነዚህ አስተሳሰቦች ላይ በመመርኮዝም የራሳቸውን የደህንነት ትምህርቶች በመፈብረክ ደህንነት ለእግዚአብሄር የንስሐ ጸሎቶችን በማቅረብ በራሰቸው ጥረቶች የሚገኝ እንደሆነ እያመኑ ደረጃ በደረጃ ወደሚደረስበት ቅድስና ለመድረስ ይሞክራሉ፡፡
 
በዚህ ዓለም ላይ ኢየሱስ አዳኛቸው እንደሆነ የሚያምኑ በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ በተጨባጭ የማያምኑ ብዙዎች አሉ፡፡ በዚህ ዓለም ላይ በተጨባጭ ሰማያዊው፣ ሐምራዊውና ቀዩ ማግ ደህንነታቸው እንደሆነ በማመን ፋንታ አሁንም ሐጢያተኞች ቢሆኑም እንኳን በኢየሱስ ደም በማመን ብቻ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት መግባት እንደሚችሉ የሚያስቡ ብዙዎች አሉ፡፡
 
 
የብሉይና የአዲስ ኪዳን ስምምነት፡፡ 
 
እግዚአብሄር በኢሳይያስ 34፡16 ላይ እያንዳንዱ የእግዚአብሄር ቃል ግጣሙን እንደማያጣ ይነግረናል፡፡ በሌላ አነጋገር የእግዚአብሄር ቃል ሁሉም ይስማማል፡፡ እግዚአብሄር የብሉይ ኪዳን ቃል ከአዲስ ኪዳን ቃል ጋር ይስማማ እንደሆነና እንዳልሆነ ለራሳችን እንድናይ ነግሮናል፡፡ በብሉይ ኪዳን የተጻፈው በአዲስ ኪዳን ውስጥ ተዛማጅ ቃል አለው፡፡ ለምሳሌ እስራኤሎች በብሉይ ኪዳን በእጆች መጫን ሐጢያቶቻቸውን ለመስዋዕት ወደቀረበው ጠቦት ሲያስተላልፉ ይህ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ የዓለም ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለመውሰድ ከመጠመቁና ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ ከማስተላለፉ ጋር ይዛመዳል፡፡
 
ኢየሱስ በውሃውና በደሙ የመስዋዕት በግና የሐጢያተኞች አዳኝ ሆኖ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ ጥምቀቱን ሲቀበል የዓለምን ሐጢያቶች ባይወስድ ኖሮ ፈጽሞ በመስቀል ላይ መሞት አያስፈልገውም ነበር፡፡ ጌታችን በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በግልጽ አስወግዶዋል፡፡ ይህም ደግሞ እግዚአብሄር በቃሉ ውስጥ ተስፋ የሰጠው ነው፡፡ ጌታችን በዚህ ቃል አማካይነት መጥቶ እንደ ደም የቀሉትን ሐጢያቶቻችንን በማጠብ እንደ በረዶ ነጭ አደረጋቸው፡፡
 
ይህንን እውነት ከማወቃችን በፊት ማለቂያ በሌላቸው ሐጢያቶች ተጥለቅልቀን እንደነበር አያጠራጥርም፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሄር ፊት የምንኮራበት ምንም ነገር የለንም፡፡ በእግዚአብሄር ፊት የምንኮራበት ምንም ነገር የሌለን ከመሆናችንም በላይ በእርሱ ፊት የምንጠባረርበትም ምንም ነገር ፈጽሞ የለንም፡፡ በሌላ አነጋገር ብልጣ ብልጥ ለመመስል የሚፈቅድልንም አንዳች ነገር የለም፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ማለት የምንችለው ነገር ቢኖር ‹‹አዎ አንተ ትክክል ነህ›› ብቻ ነው፡፡
 
እግዚአብሄር ‹‹አንተ የዓመጻ ዘር ነህ፤ ለሲዖልም ታጭተሃል›› ቢል፡- 
‹‹አዎ አንተ ትክክል ነህ፤ እባክህ አድነኝ፡፡›› 
‹‹በዚህ መንገድ በውሃው፣ በደሙና በመንፈሱ አድኜሃለሁ፡፡›› 
‹‹እሺ ጌታ! አምናለሁ!›› 
ሁልጊዜም ማለት የምንችለው ‹‹አዎ›› ብቻ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ቆመን ‹‹ይህንንና ያንን አድርጌያለሁ፡፡ ከሙሉ ልቤ በኢየሱስ አምናለሁ፡፡ ሌላ ማንም ሰው ማሰብ ከሚችለው በላይ እምነቴን በግትርነት ተከላክያለሁ!›› ልንለው አንችልም፡፡
 
ጌታ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በተጨባጭ ያስወገደው እንዴት ነው? ያስወገዳቸው በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በብሉይና በአዲስ ኪዳናት ቃል አማካይነት እንደሆነ አሳይቶናል፡፡ በብሉይ ኪዳን ሐጢያቶቻችንን በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀዩ ማግ ሲያስወግድ በአዲስ ኪዳን ደግሞ ኢየሱስ የሰው ሥጋ ለብሶ ወደዚህ ምድር በመምጣት ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወስዶ በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ ሐጢያቶቻችንንና የሐጢያትን ፍርድ ሁሉ አስወግዶዋል፡፡
 
ጌታችን በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በአንድ ጊዜ በራሱ ላይ ወሰደ፡፡ (ማቴዎስ 3፡15) ዓለማዊ ሐጢያቶቻችን በሙሉ ወደ ኢየሱስ ጫንቃ ተሻግረዋል፡፡ በዚህ መንገድ በጥምቀቱ የዓለም ሐጢያቶቻችንን ሁሉ በመውሰድ እነዚህን ሐጢያቶች በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ ተሰቀለ፤ ደሙንም አፈሰሰ፤ በመስቀል ላይም ሞተ፡፡ ዳግመኛም ከሙታን ተነሳ፡፡ በዚህም ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በተጨባጭ አስወገደ፡፡ በዚህ የተነሳ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አዳኛችን ሆነ፡፡
 
የተቀበልነው የእግዚአብሄር ጽድቅ በውሃው፣ በደሙና በመንፈሱ በኩል ወደዚህ ምድር በመጣው በዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የተገኘ ጽድቅ ነው፡፡ ይህ በገዛ ራሳችን የደረስንበት አንዳች ነገር ሳይሆን ከእግዚአብሄር የተቀበልነው ደህንነት ነው፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ጉራችንን የምንነዛበት ምንም ነገር የለንም፡፡
 
ከሐጢያቶቻችን ሁሉ የዳንነው እርግጠኛ አዳኛችን በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንደሆነ እርግጥ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር እኛ ሐጢያተኞች የነበርን በኢየሱስ ጥምቀትና ለእኛ ባፈሰሰው ደም በማመን የሐጢያት ስርየትን በተጨባጭ ተቀብለናል፡፡ የኢየሱስ የደህንነት ሥራ ከደህንነታችን 70ውን እጅ፤ ሐጢያት ባለመስራታችን ደግሞ የራሳችን ጥረቶች 30ውን እጅ ይዘዋል ብንል ቀስ በቀስ ለመቀደስና ደህንነታችንም ጥቂት በጥቂት ሊፈጸም ሌሊቱን በትጋት በመጸለይ መቆየት፣ ቀኑን ሁሉም የንስሐ ጸሎቶችን በማቅረብ ማሳለፍና ማህበረሰቡን ማገልገል አለበለዚያም ደግሞ የሚቻለውን እያንዳንዱንና ማናቸውንም ነገር ማድረግ ይኖርብናል! ሐዋርያው ጳውሎስ ግን በሮሜ ላይ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሥጋ ማን ያድነኛል? በኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን ለእግዚአብሄር ምስጋና ይሁን፡፡ እንግዲያስ እኔ በአእምሮዬ ለእግዚአብሄር ሕግ በሥጋዬ ግን ለሐጢአት ሕግ እገዛለሁ፡፡ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም፡፡›› (ሮሜ 7፡24-8፡1) ጳውሎስ እንደተናገረው እኛም እንደ እርሱ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን አለብን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህ ከሞት ሰውነት 100 እጅ እንዳዳነን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ታዲያ ማን ሊኮንነን ይችላል? ማንም ምንግዜም ሊኮንነን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ድካሞች ቢኖሩብንም ኢየሱስ ክርስቶስ 100 እጅ አድኖናለና፡፡
 
 
እናንተና እኔም ደግሞ መንፈሳዊ ፈሪሳውያን ነበርን፡፡ 
 
አንዳንዶቻችሁ ለረጅም ጊዜ ኢየሱስን አውቃችሁትና አምናችሁበት ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላ አነጋገር የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ከማመናችሁ በፊት ኢየሱስን አዳኛችሁ አድርጋችሁ አምናችሁበታል፡፡ እኔም ደግሞ ዳግመኛ ሳልወለድ ለአስር ዓመታት ክርስቲያን ነበርሁ፡፡
 
ኢየሱስን ለመጀመሪያ ጊዜ አዳኛችን አድርገን ባመንን ጊዜ አስደሳች ልምምድ ነበር፡፡ ይህ ጅማሬ የሚያረካ ስለነበር የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውንና የቀዩን ማግ እውነት ባናውቅም ኢየሱስን አዳኛቸን አድረገን በማመን ብቻ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንደምንድን አስበን ነበር፡፡
ለመጀመሪያ በኢየሱስ ባመንሁ ጊዜ ልቤ በእርግጥም በደስታ ተሞልቶ ነበር፡፡ ስለዚህ መጀመሪያ በኢየሱስ ሳምን በጣም ተደስቼ ነበር፡፡ ከአምስት ዓመታት በኋላ ግን ራሴን ተመልክቼ ያለ ማቋረጥ በምሰራቸው ሐጢያቶች መታሰሬን ተመለከትሁና አሁንም ነጻ እንዳልወጣሁ ተገነዘብሁ፡፡ በእነዚያ ቀደምት አምስት የክርስቲያን ሕይወት ዓመታቶቼ ሐጢያቶችን እንደሰራሁ ወይም በጭራሽ እንዳልሰራሁ ታስባላቸሁን? ብታውቁኝም ባታውቁኝም መልሱ በጣም ግልጽ ነው፡፡ በእርግጥ ሐጢያቶችን ሰርቻለሁ፡፡ በዚህ ወቅት እውነቱን ስላላወቅሁ ሐጢያት በሰራሁ ጊዜ ሁሉ እሰቃይ ነበር፡፡ ከዚህ ስቃይ ለመገላገልም የንስሐ ጸሎቶችን አቀርብ አንዳንዴም ለሦስት ቀናቶች እጾም ነበር፡፡ ያን ጊዜ የልቤ ሸክም በጥቂቱ የተነሳ ይመስለኝ ስለነበር ‹‹♫አስገራሚ ጸጋ! ♫እንደ እኔ ያለውን ጎስቋላ ሰው ያዳነው ድመምጽ እንደምን ጣፋጭ ነው♫!›› በማለት እግዚአብሄርን እንዳመሰግን ይፈቅድልኝ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ግን እንደገና ሐጢያትን እሰራ ነበር፡፡ እኔ ብዙ ድካሞች ስለነበሩብኝና በእንከኖች የተሞላሁ ስለነበርሁ በየቀኑ ሐጢያት በምሰራበት ጊዜ እንደዚያ በማድረጌ ራሴን እጠላ ነበር፡፡ አንድም ጊዜ የሐጢያት ችግሮቼን በጥሩ ሁኔታ ፈትቼ አላውቅም፡፡
 
በእነዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ ሆኜ አምስት ዓመታቶች ከነፉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ለአስር ዓመታት ያህል ክርስቲያን ሆኜ ከቆየሁ በኋላ ድንገት በእነዚያ ዓመታቶች ሁሉ ምን ያህል ሐጢያቶችን እንደሰራሁ ሳውቅ ደነገጥሁ፡፡ በየቀኑ እንደዚህ ያሉ ታላላቅ ሐጢያቶችን እየሰራሁ መሆኔን ስመለከት ክፉኛ አዘንሁ፡፡ ፈጽሞም ተስፋ ቆረጥሁ፡፡ በሕጉ ፊት ስቆም በእርግጥ ምን ያህል ሐጢያተኛ እንደነበርሁ ተረዳሁ፡፡ በእግዚአብሄር ፊት መቆሙ ይበልጥ አስቸጋሪ እየሆነብኝ መጣ፡፡ በመጨረሻም በጥሩ ሕሊና ኢየሱስን በሚገባ አውቀዋለሁ አምነዋለሁም ብዬ ለመናገር የማልችል ሐጢያተኛ ሆንሁ፡፡ ስለዚህ በአስረኛው የክርስቲያንነት ዓመቴ ሐጢያተኛነቴን ለእርሱ ከመናዘዝ በስተቀር ላደርገው የምችለው ነገር አልነበረም፡፡
 
ለመጀመሪያ ጊዜ በኢየሱስ ባመንሁበት ወቅት ጥሩ ክርስቲያን እንደነበርሁ አስብ ነበር፡፡ ነገር ግን ጊዜ እየከነፈ ሲሄድ በእግዚአብሄር ፊት የምኩራራበት አንዳች ነገር እንደሌለኝ ተገነዘብሁ፡፡ ‹‹በእርግጥም ፈሪሳዊ ነኝ፤ ፈሪሳውያን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ ያሉ አይደሉም፡፡ እኔም የዘመኑ ፈሪሳዊ ነንኛ!›› ብዬ ተረዳሁ፡፡
 
ፈሪሳውያን በአስመሳይ ቅድስና የተሞሉ ዓይነት ሰዎች ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳቸውን በጎናቸው ይዘው በየእሁዱ ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ለክርስቲያን ጓደኞቻቸው ‹‹እንደምን አደርህ! ሐሌሉያ!›› በማለት ይጮሃሉ፡፡ በሚያመልኩበት ጊዜም ስለ መስቀሉ የሚናገር ሰው ሲሰሙ ያለቅሳሉ፡፡ እኔም ራሴ ኢየሱስ ያፈሰሰውን ደም እያሰብሁ ብዙ ዕንባ አፍስሻለሁ፡፡ እውነተኛ አምልኮ ማቅረብ ማለት ይህ እንደሆነ አሰብሁ፡፡ ነገር ግን ሰው ሁሉ በዚህ ዓለም ላይ ሲኖር ውሎ አድሮ ሐጢያትን በተደጋጋሚ ሲሰራ ራሱን ያገኛል፡፡ ስለዚህ ሰዎች እንደገና የንስሐ ጸሎቶችን ወደ መጸለይ ይመለሳሉ፡፡ ለተወሰነ ጊዜ በእርግጥም ጥሩ ስሜት ሊሰማቸው ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ እነዚህ የንስሐ ጸሎቶች ሁሉ ያልቃሉ፡፡ ምክንያቱም እጅግ ብዙ ሐጢያቶችን ሰርተዋልና፡፡ አንዳንድ ሰዎች በልሳን ይናገራሉ፡፡ በኋላም ራዕዮችን ያያሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ከንቱ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ሙከራ ቢያደርጉም በልባቸው ውስጥ ያለውን የሐጢያቶቸቸውን ችግር ለማቃለል አይጠቅሙዋችሁም፡፡
 
ውለው አድረው በእግዚአብሄር ፊት የማይረቡ ፍጥረታቶች መሆናቸውን ቢገነዘቡና በሐጢያቶቻቸው ምክንያትም ለሲዖል የታጩ መሆናቸውን ቢያውቁ ግንዛቤው በረፈደ ሰዓት ላይ ቢመጣም ውጤቱ አስደሳች ይሆን ነበር፡፡ ለረጅም ጊዜ በኢየሱስ ስናምን በእርግጥ ምን ያህል አስከፊ ሐጢያተኞች እንደሆንን እንገነዘባለን፡፡ ፈሪሳውያን ግን ይህንን በመደበቅ የተካኑ ናቸው፡፡ በልባቸው ውስጥ ያሉትን ሐጢያቶች በመደበቅና ግብዝ በመሆን የተካኑ ስለነበሩ ስለ ሐይማኖተኝነታቸው በዙሪያቸው ባሉት ዘንድ ድጋፍ ነበራቸው፡፡
 
የዚህ ዓለም ሐይማኖተኞች እርስ በርሳቸው በአያሌው ይከባበራሉ፡፡ ነገር ግን ምንም ያህል አብዝተው ከሌሎች ክብርና ድጋፍ ቢያገኙም በእግዚአብሄር ፊት ሲቆሙ ግን የሐጢያት መጋዘን ናቸው፡፡
 
እኛም እውነትን ሳናውቅ በነበርንበት ጊዜ በትጋት የንስሐ ጸሎቶቻችንን እናቀርብ ነበር፡፡ ነገር ግን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ስለደከምን ጸሎታችን ‹‹አቤቱ ማድረግ የምትፈልገውን ሁሉ አድርግ፤ ብዙ ሐጢያቶች አሉብኝ፤ አሁንም እንደገና ሐጢያት ሰርቻለሁ፡፡ ስለዚህ ነገር ለአንተ መናገሩ በጣም አሳፍሮኛል›› የሚል ሆኖ ቀረ፡፡ ምንም እንኳን በጣም የሚያሳፍር ቢሆንም ሐጢያቶቻችንን ስንናዘዝ እግዚአብሄር እንደሚደት በጽድቁም ሐጢያቶቻችንን ይቅር እንደሚልና ከዓመጻም ሁሉ እንደሚያነፃን ስለተነገረን ‹‹አቤቱ ሐጢያት ሰርቻለሁ፤ አቤቱ እባክህ ይቅር በለኝ!›› ብለን ወደ እርሱ መጸለያችንን ቀጠልን፡፡ ሆኖም ሐጢያቶቻችን አሁንም በልባችን ውስጥ አሉ፡፡
 
ሰዎች ወደ እግዚአብሄር ለመጸለይ ራሶቻቸውን በሚያጎነብሱበት ጊዜ ሁሉ ሕሊናቸው ሐጢያቶቻቸውን ያስታውሳቸዋል፡፡ ልባቸውንም ይበላዋል፡፡ ሕሊናችን ልባችንን በማሰቃየት ‹‹እነዚህን ሁሉ ብዙ ሐጢያቶች ሰርተህ እንዴት ወደ እግዚአብሄር ለመጸለይ ትደፍራለህ?›› ብሎ ይነግረናል፡፡
 
ስለዚህ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የምንለው ምንም ነገር ስለማይኖረን ‹‹አቤቱ አቤቱ!›› በማለት እየጮህን እንጨርሳለን፡፡ ሁልጊዜም ወደ ተራራ እየወጣን የጌታን ስም በጩኸት መጥራታችንን እንቀጥላለን፡፡ የሰዎችን ትኩረት በመሳብ የሚመጣውን ሐፍረት ለመሸሽም በሌሊት ወደ ተራራው እንወጣለን፡፡ እዚያ ባለ አንድ ዋሻ ውስጥ እንገባለን፡፡ የጌታንም ስም እንጠራለን፡፡ ይህም ቢሆን የራሳችን ጥረት ስለሆነ ሐጢያቶቻችን አሁንም ከእኛው ጋር ያኖራሉ፡፡
ለራሳችን ዳግመኛ ሐጢያተኞች እንዳልሆንን ‹‹እግዚአብሄር በጣም መሃሪ ስለሆነ ሐጢያቶቼን አስወግዶዋል፡፡ ለሶስት ቀናት ስጾምና ስጸልይ ነበር፡፡ ከዚህም በላይ ያን ያህል ሐጢያት ሰርቻለሁ ብዬ አላስብም፡፡ ታዲያ መሃሪው አምላካችን ይቅር አይለኝምን?›› ብለን በመናገር ሕሊናችንን ለማሳመን እንሞክራለን፡፡
 
እግዚአብሄርን ስለ መሃሪነቱ ብናመሰግነውም ራሳችንን ማታለል እንችላለንን? ከቶውኑም ያንን አናደርግም! በቤተክርስቲያኖቻችን ውስጥ ባሉት የአመራር ቦታዎች ላይ ምንም ያህል ከፍ ብለን ብንሰቀልም ሌሎች ምንም ያህል ቢያመሰግኑንም በራሳችን አሁንም ሐጢያት በመስራት ከቀጠልን ከቶውኑም ከእነዚህ ሐጢያቶች ነጻ መውጣት ስለማንችል በመጨረሻ ፍጻሜያችን ግብዝ መሆን ይሆናል፡፡
 
የሐጢያት ምኞቶች በልባችን ውስጥ ብቅ ማለታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ጊዜያቶች በመስቀል ላይ ስለፈሰሰው የኢየሱስ ደም ብንናገርም፣ በመስቀል ላይ ስላፈሰሰው ደሙም በማሰብ ብዙ ዕንባዎች ብናፈስና ጥሩ ክርስቲያኖች ብንሆንም ፍጹም የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እሰክናገኝ ድረስ ሐጢያተኞች ነበርን፡፡ በክርስትና ስርዓቶች ሁሉ መሰረት ብንኖርም አሁንም ሐጢያት አለብን፡፡ ይህ የፈሪሳውያን ሐይማኖት ነበር፡፡ በዚህ ምድር ላይ የዚህ ዓይነት እምነት ያላቸው ብዙ ሰዎች አሁንም አሉ፡፡ በክርስቲያን ማህበረሰቦቻችን ውስም እንኳን ይገኛሉ፡፡
 
 

በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመናችን ሐጢያቶቻችን በሙሉ ተወግደዋል፡፡ 

 
የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ከማወቃችን በፊትና በዚህ ወንጌል ከማመናችን በፊት ሁላችንም በልባችን ውስጥ ሐጢያት ነበረብን፡፡ በዚህ በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ እውነት ከማመናችን በፊት ሕሊናችን በሐጢያት የተሞላ ነበር፡፡ ሁላችንም በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያተኞች ነበርን፡፡ በሐጢያቶቻችን ምክንያትም ሁላችንም ለሲዖል የታጨን ነበርን፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹የሐጢአት ደመወዝ ሞት እንደሆነ›› ይነግረናልና፡፡ ስለዚህ በሐጢያቶቻችን ምክንያት ክፉኛ ተሰቃይተናል፡፡ በሐጢያቶቻችን ምክንያት በእኛ ላይ ከመጣው የእግዚአብሄር ፍርድ የተነሳ በሥጋም በመንፈስም ለሲዖል ታጭተን ነበር፡፡
 
እኛ ብዙ ሰዎችን ወደ ክርስትና አምጥተን አስተምረናቸዋል፡፡ የሰራነው ግን የራሳችንን ሕሊና እንኳን ማንጻት ሳንችል ነበር፡፡ ልባችን በሐጢያት እንደተሞላና ለሲዖል የታጨን እንደሆንን በእግዚአብሄር ፊት ተረድተናል፡፡
 
እኔ ሁልጊዜም መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄ ነበረኝ፡፡ ‹‹ጌታችን ወደዚህ ምድር በመጣ ጊዜ ለምን ተጠመቀ?›› ኢየሱስ ለምን እንደተጠመቀ ማወቅ ፈለግሁ፡፡ ኢየሱስ ለምን ዓላማ ተጠመቀ? የእኛ የውሃ ጥምቀት በኢየሱስ የማመናችን ምልክት እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ለምን በአጥማቂው ዮሐንስ መጠመቅ እንደነበረበት በፍጹም ሊገባኝ አልቻለም፡፡ እርሱ የተጠመቀው ለምን ነበር? ለምን?
 
በክርስቲየን ማህበረሰቦች ውስጥ ያሉ አንዳንድ መሪዎችን ጠየቅሁ፡፡ ‹‹ሬቨረንድ ጥያቄ አለኝ፤ ብጠይቅ ይፈቀድልኛል?›› እንድጠይቅ ነገሩኝ፡፡ ስለዚህ ጠየቅኋቸው፡፡ ‹‹ጥያቄው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፤ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ በዮሐንስ እንደተጠመቀ ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን ለምን እንደተጠመቀ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ሬቨረንድ እርሶስ ያውቃሉን?›› ከዚያም ፈገግ ብለው እንዲህ አሉኝ፡- ‹‹ይህንን እንኳን አታውቅም? ይህንን በእሁድ ትምህርት ቤት የሚማሩት ሕጻናቶቻችን እንኳን ያውቁታል! ይህ በቀድሞው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ ይገኛል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላቶች ውስጥም ይገኛል፡፡ ኢየሱስ የተጠመቀው ምሳሌና አርአያ ሆኖ ትህትናውን ሊያሳየን አልነበረምን?›› እኔም እንዲህ አልሁ፡- ‹‹ነገር ግን ሬቨረንድ መልሱ እንደዚህ ቀላል ቢሆን ኖሮ በሰንበት ትምህርት ቤት የሚማሩት ሕጻናት ልጆቻችን እንኳን በእርግጥም ያውቁት ነበር፡፡ እኔ በመጀመሪያዎቹ ቃለ ጽሁፎች ውስጥና ከታሪክም አንጻር መርምሬዋለሁ፡፡ ነገር ግን የእርሱ ጥምቀት እንደዚያ አይደለም፡፡ ኢየሱስ በእርግጥ ለምን በዮሐንስ እንደተጠመቀ የሚገልጥ ምክንያት ሊኖር አይገባምን?››
መጠየቄን ቀጠልሁ፡፡ ክርስቲያን ከሆንሁ በኋላ ወዲያውኑ መልሱን ለማግኘት ፈለግሁ፡፡ ለዚያ ጥያቄ መልስ ለማገኘት ስመረምር ዓመታቶችን ከማሳለፍ በቀር ምርጫ አልነበረኝም፡፡ በዚህ ጥያቄ ላይ በሊቃውንት የተጻፉ ሥራዎችን ሁሉ መረመርሁ፡፡ እንደዚህ ብመረምር፣ ብጠይቅና እያንዳንዱን ነገር አበጠርጥሬ ብመለከትም የኢየሱስን ጥምቀት በግልጽና በትክክል የሚያብራራ አንዳች ነገር ማግኘት አልቻልሁም፡፡ እግዚአብሄር በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ የገለጠውን የውሃና የመንፈስ ወንጌል እስከሚያበራልኝ ድረስ የመጨረሻውን መልስ ለማግኘት ታገልሁ፡፡
 
መፍትሄ በሌለው የኢየሱስ ጥምቀት እንቆቅልሽ ተወጥሬ ሳለሁ ማቴዎስ 3፡13-17ን በጥልቀት የማንበብ ዕድል አገኘሁ፡፡ ‹‹ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ ዮሐንስ ግን፡- እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር፡፡ ኢየሱስም መልሶ፡- አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው፡፡ ያን ጊዜ ፈቀደለት፡፡ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሄርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፡፡ እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡››
 
ይህንን ቃል አንብቤ በመጨረሻ ‹‹ስለዚህ ነገሩ ይህ ነው! ኢየሱስ የተጠመቀው የብሉይ ኪዳን የመስዋዕት በግ ስለሆነ ነው! በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ ውስጥ የተደበቀው የደህንነቱ እውነት ይህ ነው!›› ብዬ ተረዳሁ፡፡
 
አጥማቂው ዮሐንስ እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተስፋ የሰጠው ኤልያስ እንደነበር እርግጥ ነው፡፡ እግዚአብሄር በሚልክያስ 4፡5 ላይ ከፍርዱ ቀን በፊት ኤልያስን እንደሚልክ ተናግሮዋል፡፡ ማቴዎስ 11፡14ም ሊልክልን ቃል የገባው ይህ ኤልያስ አጥማቂው ዮሐንስ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ ይነግረናል፡፡ ስለዚህ ስለ ኤልያስ አወቅሁ፡፡ ነገር ግን አሁንም ኢየሱስ ለምን በአጥማቂው ዮሐንስ እንደተጠመቀ እርግጠኛ አልነበርሁም፡፡ እንደገና ወደ ማቴዎስ 3፡13-17 ተመለስሁ፡- ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና…ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃ ወጣ፤…እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥጦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡›› ያን ጊዜ ጥርጣሬዎቼ በሙሉ ተነኑ፡፡ የተጠመቀው ‹‹ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም›› ነበር፡፡ ኢየሱስ በእርግጥም በጥምቀቱ አማካይነት ሰዎችን ሁሉ የማዳን ይህንን የጽድቅ ሥራውን ፈጸመ፡፡
 
ጥምቀት ከብሉይ ኪዳኑ እጆችን መጫን ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ በመገናኛው ድንኳን የመስዋዕት ስርዓት መሰረት በመስዋዕቱ ቁርባን ላይ እጆች ይጫናሉ፡፡ ሐጢያተኞች እነዚህን የመስዋዕት ቁርባኖች በሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያ ፊት ያመጡና እጆቻቸውን በእነርሱ ላይ በመጫን ሐጢያቶቻቸውን እየተናዘዙ ወደ እነዚህ የመስዋዕት ቁርባኖች ላይ ያስተላልፋሉ፡፡ ሊቀ ካህኑም የእስራኤልን ሕዝብ ሐጢያቶች በሙሉ በመናዘዝ ለእስራኤሎችና ለራሱ ወደ መስዋዕቱ ቁርባኖች ላይ ያሻግራል፡፡ ኢየሱስም በአዲስ ኪዳን ዘመን በአጥማቂው ዮሐንስ መጠመቅ ነበረበት፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች እርስ በርሳቸው ይስማማሉ፡፡ በመጨረሻ ኢየሱስ የተጠመቀው (በእጆች መጫን) የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ ለመውሰድና የእያንዳንዱን ሰው ሐጢያት ለማስወገድ እንደነበር ተረዳሁ፡፡
 
ስለዚህ የመጀመሪያውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃለ ጽሁፎች ተመለከትሁ፡፡ ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና›› የሚለው ሐረግ እንዴት በግሪክ እንደተጸፈ ተመለከትሁ፡ ‹‹እንዲህ›› እና ‹‹ጽድቅ›› የሚሉት ሐረጎች በግሪክ ‹‹ሁቶስጋር›› እና ‹‹ዲካይኦሱኔ›› ከሚሉት ጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ‹‹በዚህ መንገድ›› ‹በትክክል›› ‹‹በዚህ ዘዴ ብቻ›› ‹‹እጅግ ተስማሚ›› ወይም ‹‹በዚሁ መልክ›› ማለት ነው፡፡ የኋለኛው ደግሞ ‹‹ጽድቅ፣ መንጻት ወይም በእግዚአብሄር ፊት ተቀባይነት ያለው ፍትህ›› ማለት ነው፡፡
 
ይህም ኢየሱስ ሐጢያተኞችን ከሐጢያቶቻቸው እንዳዳናቸው ይነግረናል፡፡ ኢየሱስ በመጠመቅና ደሙን በማፍሰስ የእግዚአብሄርን ጽድቅ እንደፈጸመ ይነግረናል፡፡ በሌላ አነጋገር ይህ ማለት ሐጢያቶቻችንን ሁሉ በጥምቀቱ ወስዶዋል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እንቆቅልሾቻችን በሙሉ ተፈትተዋል፡፡ አሁን ብዙ ግራ ያጋባንንና ያቅበዘበዘንን ነገር እውነተኛ ትርጉም ተረድተናልና፡፡ ኢየሱስ ወደ መስቀል የሄደው፣ ለእነዚህ ሐጢያቶች ሲል ፍርድን ተቀብሎ የሞተው ሐጢያቶቻችንን ሁሉ በጥምቀቱ ስለወሰደ ነው፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ውስጥ የሚገኘው እውነት ይህ ነበር፡፡
 
በሌላ አነጋገር እኛ ዳግመኛ የተወለድን ኢየሱስ ከዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀት የደህንነታችን መሰረታዊ መዋቅር እንደሆነ ወደ መረዳት መጥተናል፡፡ እርሱ በጥምቀቱ የዓለምን ሐጢያቶች በአንድ ጊዜ በራሱ ላይ ወስዶዋል፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ውስጥ ያለውን ተመሳሳይ እውነትም መረዳት ይኖርባችኋል፡፡ ነፍሳችሁ የሚበራው ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡
 
በእርግጥ ኢየሱስ በዮሐንስ የተጠመቀበትን ቀን መቼም ቢሆን መርሳት አንችልም፡፡ ሐጢያቶቻችን በሙሉ በተጨባጭ ወደ ኢየሱስ የተሻገሩበትን ቀን መቼም ቢሆን መርሳት አንችልም፡፡ ይህንን እውነት በማወቃችን በልባችን ውስጥ ለውጦችን አይተናል፡፡ በውቅያኖስ ላይ እንደሚወጅብ ማዕበል በልባችን ሁሉ ውስጥ ተሰራጭተዋል፡፡ ብሩህ የሆነው የንጋት ብርሃን ጨለማውን ሰንጥቆ ወደ ውስጣችን በመግባት የደህንነትን እውነት እንድናውቅ ፈቅዶልናል፡፡
      
 

ኢየሱስ የተቀበለው ጥምቀት የዓለምን ሐጢያቶች ወደ እርሱ አሻግሮዋል፡፡ 

 
ማቴዎስ 3፡13-17ን ካነበብሁ በኋላ ለረጅም ጊዜ አንዲትም ቃል መናገር አልቻልሁም፡፡ እኔ በእርግጥም ሐጢያተኛ ብሆንም ኢየሱስ ተጠምቆ ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና›› አለ፡፡ ስለዚህ በመስቀል ላይ ደሙን እንዲያፈስስ ያደረገው (ቀዩ ማግ) የኢየሱስ ጥምቀት (ሰማያዊ ማግ) ነበር፡፡ ይህ ኢየሱስ ራሱ አምላክ (ሐምራዊ ማግ) ነበር፡፡ በብሉይና በአዲስ ኪዳናት ቃል (ጥሩው በፍታ) እውነተኛውን የደህንነት እውነት አስተማረን፡፡ በሌላ አነጋገር ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ወስዶዋል፡፡
 
‹‹ታዲያ አሁንም ሐጢያት አለብን ወይስ የለብንም? ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ የእያንዳንዱ ሰው ሐጢያቶች ወደ እርሱ ተሻግረዋል፡፡ የእኛም ሐጢያቶች ወደ እርሱ ተሻግረዋልን? በዚያን ጊዜ የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ ተሻግረው ነበርን? ገና በእናታችን ማህጸን ውስጥ ሳለን የነበሩብን ሐጢያቶች ዓለማዊ ሐጢያቶች ነበሩ ወይስ አልነበሩም? የአንድ ዓመት ጨቅላ በነበርንበት ጊዜ የሰራናቸው ሐጢያቶችስ? እነርሱም ደግሞ የዓለም ሐጢያቶች አይደሉምን? በልጅነታችን የሰራናቸው ሐጢያቶችስ? እነርሱም የዓለም ሐጢያቶች አልነበሩምን?››
 
ትክክለኛ መሰረት ላይ መሆናችንን ለማረጋገጥ ራሳችንን እነዚህን ጥያቄዎች መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ እምነት ማለት በእግዚአብሄር ቃል ላይ በትክክል መመስረታችንን ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡ በልጅነታችን የሰራናቸው ሐጢያቶች በእርግጥም የዓለም ሐጢያቶች ናቸው፡፡ በጉርምስናችን ዘመን የሰራናቸው ሐጢያቶችም እንደዚሁ የዓለም ሐጢያቶች ናቸው፡፡ በሕይወት ዘመናችን የምንሰራቸው ሐጢያቶች በሙሉ አስቀድመው ወደ ኢየሱስ ተሻግረዋል፡፡ አልተሻገሩምን? በእርግጥ ተሻግረዋል! ጌታችን የወሰደው የእኛን ሐጢያቶች ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱን ሰብዓዊ ፍጡር ሐጢያትም ጭምር እንሆነ ተጽፎዋል፡፡ ስለዚህ ‹‹ሐጢያቶቻችን በሙሉ በእርግጥም ወደ ኢየሱስ ተሻግረዋል፡፡ ታዲያ አሁንም ሐጢያት አለብን? የለብንም፡፡ በውስጣችን የቀረ አንድም ሐጢያት የለብንም!›› የሚለውን ተገንዝበናል፡፡
 
አጥማቂው ዮሐንስ ‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ›› (ዮሐንስ 1፡29) በማለት የመሰከረው ኢየሱስ በእርግጥም በዮሐንስ ስለተጠመቀ ነበር፡፡ ኢየሱስ ከሰው ዘር መጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ እየኖረ ያለውንና የሚኖረውን የእያንዳንዱን ሰው ሐጢያቶች በሙሉ አስወግዶዋል፡፡ ማንም ሰው በሕይወት ዘመኑ የፈጸማቸው ሐጢያቶቹ የልጆቹም ሐጢያቶች ሳይቀር በኢየሱስ ተወግደዋል፡፡ ይህ ዓለም ለሺህ ዓመታቶች ወይም ለቢሊዮን ዓመታቶች ቢዘልቅም ጌታችን የሕዝቡን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ ወስዶ እነዚህን ሐጢያቶች በጫንቃው ላይ ተሸክሞ ወደ መስቀል በመሄድ ተሰቀለ፡፡ ስለ እኛ ሲልም የሐጢያትን ፍርድ በሙሉ ወሰደ፡፡ የተረዳነው ነገር ቢኖር ይህንን ነው፡፡
 
እኛ ዳግመኛ የተወለድን ከዚህ የተነሳ ኢየሱስ ዳግመኛ ከሙታን ተነስቶ አዳኛችን እንደሆነ በተጨባጭ ተረድተናል፡፡ እንደዚህ በማመናችንም ጥያቄዎቻችን በሙሉ ተመልሰዋል፡፡
 
ጌታችን በዚህ ሁኔታ በተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ አስወግዶዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ ስላለው ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና ጥሩ በፍታ የሚነግረን ለዚህ ነው፡፡ በ1ኛ ዮሐንስ 5፡4-6 ላይም ኢየሱስ ወደ እኛ የመጣው በውሃ ብቻ ሳይሆን በውሃና በደም እንደሆነ የሚነግረንም ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ መድህናችን ኢየሱስ በጥምቀቱ የእግዚአብሄርን ፈቃድ የፈጸመው ለዚህ ነው፡፡ እውነቱ ይህ ነው! ነገር ግን የክርስትና መሪዎች ይህንን እውነት አላስተማሩንም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም አያውቁትምና!›› ወደሚል ግንዛቤ መጣን፡፡
 
ሐጢያት አልባ የምንሆነው የእግዚአብሄር እውነት የሆኑት ሰማያዊው፣ ሐምራዊው፣ ቀዩ ማግና ጥሩው በፍታ ሐጢያት አልባ መሆናችንን ሲነግሩን ብቻ ነው፡፡ ማንም ሰው የሌላውን ሰው ደህንነት ማረጋገጥ አይችልም፡፡ የሌሎችን ጥሩ ቃሎች መቀበል ጥቅም የለውም፡፡ ሰዎች ጥሩ ክርስቲያኖች መሆናችንን ወይም ደግሞ ምርጥ ክርስቲያኖች መሆናችንን መናገራቸው ከሐጢያት ለመዳናችን እንዴት ማረጋገጫ ሊሆን ይችላል? ሐጢያት አልባ የምንሆነው በሰዎች ማረጋገጫ ሳይሆን የእግዚአብሄር ቃል ክርስቶስ በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ማስወገዱን ሲነግረን ብቻ ነው፡፡
የእግዚአብሄር ቃል ኢየሱስ ያስወገደው የእኔን ሐጢያቶች ብቻ ሳይሆን የእናንተንም ሐጢያቶች እንደሆነ ይነግረናል፡፡ መሲሁ ክርስቶስ የሰዎችን ሁሉ ሐጢያቶች በሙሉ በማስወገዱ ብናምን ሁላችንም የሐጢያት ስርየትን እንደምናገኝ ይነግረናል፡፡ የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር አልፈን የምንገባው በውሃውና በመንፈሱ አማካይነት የሐጢያት ስርየትን በመቀበል ነው፡፡
 
 

ፍጹም እምነት ምንድነው? 

 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ ተፈትሎ የተሰራ ነበር፡፡ እያንዳንዱ ሰው ጌታችን ወደዚሀ ምድር መጥቶ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ያዳነን በመሆኑ በዚህ ፍጹም እምነት ማመን አለበት፡፡ ጌታ የሰው ሥጋ ለብሶ ወደዚህ ምድር መወለዱን፣ በዮሐንስ መጠመቁን፣ በመስቀል ላይ መሞቱን፣ ከሙታን መነሳቱንና በዚህም አዳኛችን መሆኑን ስናምን ሁላችንም የእግዚአብሄር ልጆች መሆን እንችላለን፡፡ ምግባሮቻችን በቂ ባይሆኑም ሥጋችንም የማይረባ ቢሆንም በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ በማመን የእግዚአብሄርን ጽድቅ ለብሰናል፡፡ በአጭሩ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የእግዚአብሄር ልጆች ሆነናል፡፡
 
አንዳንዶቻችሁ አሁንም ሙሉ በሙሉ አልገባችሁ ይሆናል፡፡ እንደዚያ ከሆነ ማድረግ ያለባችሁ ነገር ቢኖር ይህንን መጽሐፍ በማንበብ መቀጠል ወይም በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ መቆየት ነው፡፡ እስካሁን ድረስ የተወያየነው የመገናኛውን ድንኳን ጠቅለል ያሉ ገጽታዎችን ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ጊዜ ዝርዝር የሆኑ ማብራሪያዎችን ማንበብ ስትጀምሩ የመገናኛውን ድንኳን በሚገባ መረዳት ትችላላችሁ፡፡ በጣም ቀላል ስለሆነ ሕጻን ልጅ እንኳን በሚገባ ያስተውለዋል፡፡
 
ሰዎች እምነታቸውን ግልብ በሆነ የኢየሱስ ዕውቀት ላይ የሚመሰረቱ ከሆነ ምንም ያህል በኢየሱስ ለረጅም ጊዜ ማለትም ለሚመጡት አንድ ወይም አስር ሺህ ዓመታት ያህል ቢያምኑም ከቶውኑም ከሐጢያቶቻቸው አይድኑም፡፡ በየቀኑ ሐጢያት ይኖርባቸዋል፡፡ በየቀኑም ያለቅሳሉ፡፡ ምክንያቱም ከሐጢያቶቻቸው እርግማን ማምለጥ አይችሉምና፡፡ እነዚህ ሰዎች ነገሮች ጥሩ ሊሆኑላቸው ሲጀምሩ እግዚአብሄር እየረዳቸው እንደሆነ ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ነገሮች ጥቂት እንኳን ፈራቸውን ከለቀቁ ‹‹አስራት ስላልሰጠሁ ይሆን? ወይስ ባለፈው እሁድ ቤተክርስቲያን ስላልሄድሁ ይሆን? ሐጢያት ሰርቻለሁ፡፡ እግዚአብሄርን በትክክል ማገልገል ተስኖኛል፡፡ ለእነዚህ ነገሮች በትክክል እየቀጣኝ ነው ብዬ አስባለሁ›› በማለት ግራ ይጋባሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ በሕጉ ውስጥ ተቆልፎባቸው ለመሞት ያጣጥራሉ፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ሕጉ ቁጣን ያመጣልና›› (ሮሜ 4፡15) ብሎ ይነግረናል፡፡
 
ምሉዕ የሆነ እምነት ለማግኘት በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ አማካይነት ወደ እኛ የመጣውን የኢየሱስ ክርስቶስን አራቱን አገልግሎቶች በትክክል ማወቅና ማመን አለብን፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠውን እውነት መረዳት አለብን፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ምሉዕ የሆነ እውነት ሊኖረንና የእርሱም ፍጹማን ልጆች ልንሆን የምንችለው ይህንን አራት ዕጥፍ እውነት በግልጽ ስንረዳና ስናምንበት ብቻ ነው፡፡ በእነዚህ በአራቱ የኢየሱስ አገልግሎቶች በማመን ሐጢያት አልባ ስለሆንን ራሳችንን ከሐጢያት ባርነት ነጻ ለማውጣት ሳንታገል ሁልጊዜም ሐጢያት አልባ ጻድቃን ነን፡፡ የራሳችንን የፈቃድ ሐይል ሳንጠቀም ሐጢያት አልባ የእምነት ሰዎች ነን፡፡ ጥሩ ምግባሮችን ሳናደርግ ወይም ሳንሞክር ሐጢያቶቻችን ታጥበው እንደ በረዶ ነጭ የሆኑልን የእግዚአብሄር ፍጹማን ልጆች ነን፡፡
 
ወላጆቹ ዓይኖቻቸውን ሳይነቅሉ እንደሚንከባከቡት ተጫዋችና በሰላም የሚያንቀላፋ ሕጻን እኛም በዚህ እውነት በማመን ምህረትን በሚፈነጥቁት የእግዚአብሄር ዓይኖች ፊት በልባችን ውስጥ ሰላምና ጸጥታ አለ፡፡ ምግባሮቻችሁ ብቁ ባይሆኑም ማድረግ ያለባችሁ ነገር በጌታ ሥራዎች ማመን ነው፡፡ ይበልጥ ብቁ ባልሆናችሁ መጠን የጌታችን ፍቅር ይበልጥ ይታወቃኋል፡፡
 
በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ የሚያምን አምነት መያዝ አቅቶዋችሁ የሐጢያቶቻችሁን ስርየት ለማግኘት እየጮሃችሁ ነውን? ይህንን እውነት የሚያውቁ የሐጢያት ስርየትን ለማግኘት አይጮሁም፡፡ ነገር ግን በዝምታ ያምናሉ፡፡ በእምነት የእግዚአብሄር ልጆች የሚሆኑት በውሃው፣ በደሙና በመንፈሱ አማካይነት ወደ እኛ የመጣውን ኢየሱስ ክርስቶስን በተጨባጭ የሚያውቁና የሚያምኑበት ናቸው፡፡ እነርሱ እግዚአብሄርን የሚያገለግሉት ጥራዝ ነጠቅ በሆኑ ድርጊቶች አይደለም፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያ እርሱን ይወዱታል፡፡ በእምነታቸውም ያገለግሉታል፡፡ እኛ ስለምናምን እግዚአብሄር የሚያደምጡንን ይሰጠናል፡፡ አብሮንም ይጓዛል፡፡ እኛ በእርሱ ስለምናምን እርሱ ይረዳናል፡፡ እምነታችንን ባኖርንበት በጥምቀቱና በደሙ ባዳነን ኢየሱስ ስለምናምን የእርሱን የጽድቅ ሥራዎች የምናገለግል የእግዚአብሄር ባሮች ሆነናል፡፡
 
አሁን እግዚአብሄር ተጨባጭ የሆነውን የሐጢያት ስርየት ደህንነት ይሰጠን ዘንድ በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ላይ ያለውን የደህንነት የመግቢያ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ የሰራው የመሆኑን እውነት ሁላችንም መረዳት አለብን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ በውሃው፣ በደሙና በመንፈሱ ወደ እኛ መጥቶ በብሉይ ኪዳኑ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ ባሉት ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና ጥሩ በፍታ ከሐጢያቶቻችን እንዳዳነን ይነገረናል፡፡ ጌታችን ከሐጢያት የምንድንበት የደህንነት በር ሆንዋል፡፡ በተጨባጭና በእርግጠኝነት ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ባዳኑን በእነዚህ የመሲሁ አራት ሥራዎች ማመንና አሁንም ማመን አለብን፡፡
 
 
ኢየሱስ ከዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀት በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ ለተገለጠው ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና ጥሩ በፍታ እውነተኛ አካል ነው፡፡ 
 
ኢየሱስ ከዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀት በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ ለተገለጠው ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና ጥሩ በፍታ እውነተኛ አካል ነው፡፡ 
 
ወደ ማቴዎስ 3፡13-17 እንመለስ፡- ‹‹ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ ዮሐንስ ግን፡- እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር፡፡ ኢየሱስም መልሶ፡- አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው፡፡ ያን ጊዜ ፈቀደለት፡፡ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሄርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፡፡ እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡›› ኢየሱስ በተጠመቀበት በዚህ ጊዜ ከድንግል ማርያም ከተወለደ 30 ዓመታት ሆኖት ነበር፡፡ ‹‹ያን ጊዜ›› የሚለው ቃል አጥማቂው ዮሐንስና ኢየሱስ 30 ዓመት የሆኑበትን ጊዜ የሚጠቁም ነው፡፡
 
ከኢየሱስ 6 ወራት ቀደም ብሎ የተወለደው አጥማቂው ዮሐንስ የንስሐ ጥምቀት ሲያጠምቃቸው ለነበሩት የዚህ ምድር ሰዎች ወኪል ነበር፡፡ (ማቴዎስ 3፡11፤11፡11) ኢየሱስ 30 ዓመት ሲሞላው በዮሐንስ ወንዝ ሰዎችን ያጠምቅ ወደነበረው ወደዚህ ዮሐንስ ሊጠመቅ መጣ፡፤ አጥማቂው ዮሐንስ ግን ‹‹እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?›› በማለት ሊከለክለው ሞክሮ ነበር፡፡ ኢየሱስ ግን ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና›› ብሎ መለሰለት፡፡ ያን ጊዜ ዮሐንስ ፈቀደለት፡፡ ኢየሱስም እርሱ ተጠመቀ፡፡ ኢየሱስ በዚህ ሁኔታ በተጠመቀ ጊዜ ሰማያት ተከፈተውለት ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው›› የሚል ድምጽ እንደመጣለት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡
 
እዚህ በማቴዎስ 3፡15 ላይ ኢየሱስ ለምን በዮሐንስ እንደተጠመቀ ይነግረናል፡፡ ይህ እውነት የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ ሰማያዊ ማግ የሚያመለክት ነው፡፡ ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና፡፡›› ኢየሱስ ከዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀት ዓላማው በመገናኛው ድንኳን ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ማግ በተገለጡት ሥራዎቹ አማካይነት የሐጢያተኞችን ሐጢያቶች ይቅር ማለት ነበር፡፡ ‹‹እንዲህ [ለእነርሱ] ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባ [ነበርና]፡፡››
 
ኢየሱስ ክርስቶስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የእያንዳንዱን ሰው ሐጢያቶች በራሱ መውሰዱ የእግዚአብሄርን ጻድቅ ፍቅርና ለሐጢያተኞች ሁሉ የሆነውን የደህንነት ሥራውን ፍጻሜ የሚያሳይ ነው፡፡ ዮሐንስ 3፡16 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሄር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፡፡›› ኢየሱስ የተጠመቀው በሐጢያቶቻችን ምክንያት እንዳንኮነን እኛን ከዓለም ሐጢያቶች ለማዳን ነው፡፡ ኢየሱስ በዮሐንስ በመጠመቅ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሁሉና የሰውን ዘር ሐጢያቶች ሁሉ በራሱ ላይ የወሰደው ለዚህ ነው፡፡ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ ለእነርሱ መፈጸም ይገባልና፡፡
 
‹‹የእግዚአብሄር ጽድቅ ሁሉ›› ምንድነው? ይህ የላይኛው ምንባብ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ የተጠመቀው የአብን ጽድቅ ሁሉ ለመፈጸም እንደነበር ይነግረናል፡፡
 
እዚህ ላይ የእግዚአብሄር ጽድቅ ሁሉ በትክል ምን እንደሆነ ማወቅ ያስፈልገናል፡፡ ‹‹ጽድቅ ሁሉ›› ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ በመጠመቅ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ የመውሰዱን እውነታ ያመለክታል፡፡ በጥምቀቱ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በአንድ ጊዜ ወሰደ፡፡ የተወለደበት ዓላማ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመደምሰስ ስለነበር ኢየሱስ ከዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀት በግልጽ የጽድቅ ጥምቀት ነበር፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሁሉ መፈጸም ማለት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ የሚያስወግዱትን የጽድቅ ሥራዎች መፈጸም ማለት ነው፡፡ ያም ማለት ይህ ደህንነትን መፈጸም ነበረበት፡፡
 
የኢየሱስ ጥምቀት እግዚአብሄር ከሐጢያቶቻችን ሊያድነን የተጠቀመበት ወሳኝ ዘዴ ነበር፡፡ እግዚአብሄር ሐጢያቶቻችንን ለመደምሰስ የሰው ዘር ወኪል ይሆን ዘንድ አጥማቂው ዮሐንስን እንደሚያስነሳ፣ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስንም እንደሚያጠምቅና ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወደ ልጁ እንደሚያሻገር በብሉይ ኪዳን ውስጥ አስቀምጦዋል፡፡ ይህ የእግዚአብሄር የምህረት ሥራ ነበር፡፡ እግዚአብሄር አብዝቶ ስለወደደን እግዚአብሄር ልጆቹ ሊያደርገንና ሐጢያቶቻችንን የመደምሰሱን የጽድቅ ሥራ ሊያጠናቅቅ ኢየሱስ በዮሐንስ እንዲጠመቅ አደረገው፡፡ ኢየሱስ ተጠምቆ ከውሃ በወጣ ጊዜ እግዚአብሄር ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው›› ያለው ለዚህ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር አብ ‹‹ልጄ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ በራሱ ላይ ወሰደ›› ማለቱ ነው፡፡
 
በሌላ አነጋገር ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ በዚህ በዮሐንስ የመጠመቅ ዘዴ አማካይነትም እጅግ ተገቢ በሆነ መንገድ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በአንድ ጊዜ በመውሰድ ሐጢያቶቻችንን ለማስወገድ የመስዋዕት ጠቦት ሆነ፡፡
 
እነዚህን ሐጢያቶች በመስቀል ላይ ተሸክሞ የተሰቀለው፣ ክቡር ደሙን ያፈሰሰውና የሁላችንም አዳኝ የሆነው የእግዚአብሄር ልጅ ስለ እኛ ስለተጠመቀና ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ ስለወሰደ ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር ኢየሱስ ለሐጢያቶቻችን በመጠመቁ፣ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙም ራሱን መስዋዕት በማድረጉና ዳግመኛም ከሙታን በመነሳቱ ስላመንን አድኖናል፡፡ ከሙታን ዳግመኛ ከተነሳና የደህንነት ሥራዎቹን ካጠናቀቀ በኋላ አሁን በእግዚአብሄር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦዋል፡፡ ጊዜው ሲደርስም በእርግጥም ተመልሶ ይመጣል፡፡ ይህ እውነት የውሃና የመንፈስ ወንጌልና የደህንነት መሰረት ነው፡፡
 
ዘጸዓት 27፡16 በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ ያለውን መዝግቦዋል፡፡ ‹‹ለአደባባዩም ደጅ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊም፣ ከቀይም ግምጃ ከጥሩ በፍታም በጥልፍ አሰራር የተሰራ ሃያ ክንድ መጋረጃ ይሆናል፡፡ ምሰሶቹም አራት እግሮቹም አራት ይሁኑ፡፡›› ስለዚህ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ከእነዚህ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ የተፈተለ ነበር፡፡ ይህም ወደ እግዚአብሄር መንግሥት የምንገባው በዚህ የደህንነት ስጦታ በማመን እንደሆነ እውነቱን ይነግረናል፡፡
 
ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር የተፈተለው ሰማያዊው ማግ ሐጢያቶቻችን በሙሉ ኢየሱስ ወደዚህ ምድር መጥቶ በተጠመቀ ጊዜ ወደ እርሱ የመሻገራቸውን እውነታ ያመለክታል፡፡
 
ሐምራዊው ማግ ለሐጢያቶቻችን የተጠመቀው ኢየሱስ ክርስቶስ አጽናፈ ዓለማትንና በውስጡ ያሉትን በሙሉ የፈጠረ ፈጣሪ የእናንተና የእኔም ጌታ ስለመሆኑ ይነግረናል፡፡ ሐምራዊ የነገሥታት ቀለም ነው፡፡ (ዮሐንስ 19፡2-3) ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ሁሉ ጌታ ነው፡፡ ‹‹ክርስቶስ›› የሚለው ቃል ‹‹ቅቡዕ›› ማለት ነው፡፡ ቅቡዕ መሆን የሚችሉት ነገሥታት፣ ካህናትና ነቢያት ብቻ ነበሩ፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ የሰው ሥጋ ለበሶ ወደዚህ ምድር ቢመጣም እውነተኛ ማንነቱ ግን የነገሥታት ንጉሥ መሆኑ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ኢየሱስ ጌታና የአጽናፈ ዓለማት ሁሉ ፈጣሪ ነበር፡፡ ኢየሱስ ራሱ ሁሉን ቻይ አምላክና የእግዚአብሄር አንድያ ልጅ ነበር፡፡
 
በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር ላይ የተፈተለው ቀዩ ማግ ይህ የነገስታት ንጉሥ የሰው ሥጋ ለብሶ ወደዚህ ምድር ከመጣና ሐጢያቶቻችንን በጥምቀቱ በራሱ ላይ ከወሰደ በኋላ መስዋዕት መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ እርሱ ተሰቀለ፤ በመስቀል ላይም ደሙን አፈሰሰ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጠመቅ ክቡር ደሙን በማፍሰስና ራሱን ስለ እኛ መስዋዕት በማድረግ በእኛ ፋንታ የሐጢያቶቻችንን ዋጋ ከፍሎዋል፡፡ ቀዩ ማግ የኢየሱስ ክርስቶስን መስዋዕትነት ያሳያል፡፡
 
በመጨረሻም ጥሩው በፍታ የእግዚአብሄርን የብሉይና የአዲስ ኪዳናት ያማረ ቃል ያመለክታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይና በአዲስ ኪዳናት ቃል አማካይነት ስላገኘነው ደህንነታችን ይነግረናል፡፡ እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሐጢያተኞች አዳኝ ሆኖ ወደ እኛ እንደሚመጣ ቃል ገብቷል፡፡ ደሙንም በመስቀል ላይ አፈሰሰ፡፡ ራሱን ለሐጢያቶቻችን መስዋዕት አደረገ፡፡
 
እግዚአብሄር በሰማያዊው ማግ አማካይነት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐጢያቶቻችን ሊያድነንና እነዚህን ሐጢያቶቻችንን በራሱ ላይ ሊወስድ ወደዚህ ምድር የመጣበትን ቃል ገለጠ፡፡ በሐምራዊው ማግ አማካይነትም የተጠመቀው ኢየሱስ በእርግጥም ራሱ አምላክ እንደነበር ገለጠ፡፡ በቀዩ ማግ አማካይነትም እግዚአብሄር አዳኛችን ሆኖ ወደዚህ ምድር በመምጣት የዓለምን ሐጢያቶች በመስቀል ላይ በመሸከምና ክቡር ደሙን በማፍሰስ እናንተንና እኔን ከሐጢያቶቻችን እንዳዳነን ገልጦዋል፡፡
 
በሌላ አነጋገር በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተስፋ በተሰጠው መሰረት በእግዚአብሄር ቃል የተገኘው ይህ ደህንነት በጥሩው በፍታ ተገልጦዋል፡፡ የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር እግዚአብሄር እንዴት ከሐጢያቶቻችን እንዳዳነንና የራሱ ሕዝብ እንዳደረገን በመግለጥ ሲያሳየን እንመለከታለን፡፡ ስለዚህ ሁላችንም በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ ጥቅም ላይ በዋሉት በአራቱ ማጎች መንፈሳዊ ትርጉም ማመን አለብን፡፡
 
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ቀለማቶች ሲናገር መጀመሪያ የጠቀሰው ሰማያዊውን ማግ ነው፡፡ እኛ ብዙውን ጊዜ የምናስበው ሐምራዊው እንደሚቀድምና ሰማያዊውና ቀዩ ማግ እንደሚከተል ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ቅድመ ተከተሉን ሲዘረዝር ሰማያዊውን ያስቀድምና ሐምራዊውንና ቀዩን ማግ ያስከትላል፡፡ ይህም የሰማያዊውን ማግ ጠቀሜታ ያሳየናል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በእርግጥም አዳኛችን ሆኖ ወደዚህ ምድር ቢመጣም በዮሐንስ ባይጠመቅ ኖሮ ከሐጢያቶቻችን መንጻት ባልቻልንም ነበር፡፡ ኢየሱስ ከዓለም ሐጢያቶች ሊያድነን ለአባቱ ፈቃድ በመታዘዝ በዮሐንስ የተጠመቀውና የተሰቀለው ለዚህ ነው፡፡
 
ኢየሱስ ሁሉን የፈጠረ የአጽናፈ ዓለማት ጌታ ነው፡፡ እርሱ አምላካችንም ነው፡፡ እርሱ ወደ ምድር እንድንወለድ ያደረገንና በሕይወታችን ላይ የሚሰለጥን አምላክ ነው፡፡ እርሱ እኛን ከሐጢያቶቻችን ለማዳን የሰው ዘር ሁሉ ወኪል በሆነው በዮሐንስ መጠመቅና ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ መውሰድ ነበረበት፡፡ በሌላ አነጋገር ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አዳኛችን የሆነው በዮሐንስ በመጠመቅ ነበር፡፡
 
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር የመጣው እኛን ከሐጢያቶቻችን ለማዳን ነው፡፡ ክርስቶስ ባይጠመቅ ኖሮ በፍጹም ሊሰቀል አይችልም ነበር፡፡ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያው በር ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ከሐጢያቶቻችን ሁሉ በትክክል እንዳዳነን በግልጽ የሚያሳየን ለዚህ ነው፡፡ ያም ማለት የእርሱ ግልጽ የሆነው የደህንነት ዘዴ ይህ ነው፡፡
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያው በር ቀለማቶች ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር መጥቶ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀቱ በራሱ ላይ እንደሚወስድና እንደሚሰቀል ይነግሩናል፡፡ በሌላ አነጋገር እርሱ ራሱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ያስወግዳል፡፡ ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ የሰማይ በር ተከፈተ፡፡ እግዚአብሄር አብም ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው›› ሲል ተናገረ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ መሲሃችንና አዳኛችን ነው፡፡ ነገር ግን ደግሞ የእግዚአብሄር ልጅ አጽናፈ ዓለማትን በራሱ ቃል የፈጠረ ፈጣሪም ነው፡፡ ቅዱስ አምላክ በመሆኑ ኢየሱስ እውነተኛ አዳኛችን ይሆን ዘንድ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ መሸከም ችሎዋል፡፡
 
አጽናፈ ዓለማትን የፈጠረውና የሚያስተዳድረው ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐጢያቶቻችን የምንድንበትን ግልጽ የሆነ ደህንነት አሳይቶናል፡፡ እናንተና እኔ በተጨባጭ የዳንነው ኢየሱስ ክርስቶስ ሐጢያቶቻችንን ለመደምሰስ ወደዚህ ምድር በመምጣት እነዚህን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ በራሱ ላይ በመውሰዱና በመስቀል ላይ በሞቱ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በሕይወታችንና በሞታችን ላይ የሚሰለጥን አጽናፈ ዓለማትን ሁሉ የፈጠረ፤ አያቶቻችንንና መላውን የሰው ዘር በዚህ ምድር ላይ የፈጠረ ፈጣሪያችን ነው፡፡ እርሱ የሰማያዊው፣ የሐምራዊው፣ የቀዩ ማግና የጥሩው በፍታ ዋና መሰረት ነው፡፡
 
እግዚአብሄር ራሱ ለሐጢያተኞች የመስዋዕት ቁርባን ለመሆን ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ በዚህ መንገድ ያዳነን ኢየሱስ ሁሉን የሚችል አምላክና የምህረት አምላክ ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሁሉ የፈጸመው ሐጢያቶችን በሙሉ በጥምቀቱ በራሱ ላይ በመውሰዱ ነው፡፡ የዓለምን ሐጢያቶች ወደ መስቀል የወሰደው፣ የተሰቀለውና ክቡር ደሙን ያፈሰሰው ለዚህ ነው፡፡ በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ በተገለጠው መሰረት ኢየሱስ ክርስቶስ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ለመደምሰስ የመስዋዕት ቁርባናችን ሆነ፡፡
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ብቻ ሳይሆን የቅድስቱ የመግቢያ በር ብቻ ሳይሆን የቅድስቱ የመግቢያ በር፣ የቅድስተ ቅዱሳኑ የመግቢያ በርና የእግዚአብሄር ቤት መሸፈኛው እንኳን ሳይቀር ሁሉም ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ ተፈትለው የተሰሩት ለዚህ ነው፡፡ እናንተና እኔ በዚህ በማመን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ የነጻነው ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እናንተ ስለተጠመቀ ነው፡፡ ኢየሱስ ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም ተጠመቀ፡፡ ይህም ጽድቅ በጥምቀቱ አማካይነት የሕዝቡን ሁሉ ሐጢያት በራሱ ላይ በመውሰዱ ተፈጸመ፡፡ ስለዚህ እኛ ማድረግ ያለብን ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በዚያን ጊዜ ወደ ኢየሱስ እንደተሻገሩ መረዳትና እንደዚያ ማመን ነው፡፡
 
ነገር ግን እንዲያው በዘፈቀደና በግድየለሽነት በእርሱ የሚያምኑ ብዙ ክርስቲያኖች አሉ፡፡ የራሳቸውን ዓመጸኛ የሐይማኖት እምነት ለመተው በጣም ግትሮች ስለሆኑ ገና ከመጀመሪያው እግዚአብሄርን ይገዳደሩታል፡፡ እርሱ በሰጠን የደህንነት መንገድ መሰረት በእርሱ ማመን ይኖርብናል፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹እኔ መንገድ እውነትም ሕይወትም ነኝ፡፡›› (ዮሐንስ 14፡6) እርሱ ‹‹እኔ መንገድ ነኝ፤ ወደ ሰማይ የማደርሳችሁ መንገድ እኔ ነኝ፤ እኔ እረኛ መንገድና እውነት ነኝ፡፡ እኔ በእርግጥም የማድናችሁ ሕይወት ነኝ›› በማለት እየነገረን ነው፡፡
 
 
በኢየሱስ ስናምን እርሱን የምንረዳውና የምናምነው እንዴት ነው? 
 
ከሐጢያቶቻችን መዳን የምንችለው እርሱ ወደዚህ ምድር መጥቶ እኛን ባዳነበት ትክክለኛ መንገድ በማመን ብቻ ነው፡፡ ‹‹እምነት›› የሚለው ቃል ‹‹መደገፍ›› ‹‹መያዝ›› እና ‹‹መማረክ›› የሚሉ ትርጉሞችን ያካትታል፡፡ ሽማግሌዎች በጣም ሲያረጁ ብዙውን ጊዜ በልጆቻቸው ላይ ይደገፋሉ፡፡ ብቻቸውን መኖር በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ያውቃሉና፡፡ እኛም ራሳችንን ለእግዚአብሄር አስረክበን የምንኖረው ሐጢያቶቻችንን በራሳችን ማስወገድ ስለማንችል ነው፡፡ ሐጢያት ላለመስራት ብንሞክር እንኳን ሁልጊዜም ሐጢያት እየሰራን በመኖር እንቀጥላለን፡፡ በእግዚአብሄር የምናምነውና እርሱ ለእኛ ያደረገውን በማመን በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ የምንታመነው ራሳችንን ከሐጢያቶቻችን ነጻ ማውጣት ስለማንችል ነው፡፡
 
በኢየሱስ ስናምንና መዳናችንን ስንሻ በመጀመሪያ ትክክለኛው እምነት ምን ዓይነት እምነት እንደሆነ ማወቅ ያለብን ለዚህ ነው፡፡ ኢየሱስ ከ2,000 ዓመታት በፊት እናንተንና እኔን -- በእርግጥም በዚህ ዓለም ላይ የሚኖረውን እያንዳንዱን ሰው -- ከሐጢያቶቻችን ለማዳን መጣ፡፡ 30 ዓመት ሲሆን በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ የዓለምንም ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ ወሰደ፡፡ ሁላችንም በዚህ እውነት ማመን አለብን፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ የእናንተንና የእኔን ሐጢያቶች ብቻ ሳይሆን የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ በወሰደ ጊዜ ያለው የአሁኑና የወደፊቱ እያንዳንዱ ሐጢያት አስቀድሞ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደተወሰደ ማመን አለባችሁ፡፡
 
ነገር ግን ብዙ ሰዎች የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ብቻ ሳይሆኑ የእነርሱም ሐጢያቶች በሙሉ ኢየሱስ ሲጠመቅ ወደ እርሱ የተሻገሩ የመሆናቸውን ይህንን እውነታ ችላ በማለት በመስቀሉ ደም ብቻ ማመናቸውን ቀጥለዋል፡፡ የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በሮች በሙሉ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ የተፈተሉ መሆናቸውን ቢያዩም ማናቸውም ትክክለኛው እምነት የትኛው እንደሆነ በቀላሉ መለየት ያልቻሉት ለዚህ ነው፡፡
 
ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ወደዚህ ምድር በመጣ ጊዜ እንዲያው ግድየለሽ በሆነ ሁኔታ አላዳነንም፡፡ እናንተና እኔ ሙሉ በሙሉ የዳንነው እርሱ በተጨባጭ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ ስለወሰደና የሐጢያቶቻችንንም ኩነኔ ሁሉ በስቅለቱ ስለተሸከመ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር በሙሉ ያዳነው እንደዚህ ነው፡፡ ጌታቸን ‹‹ወደ እኔ የመጣውን ወደ ውጭ አልጥለውም›› (ዮሐንስ 6፡37) ያለው ለዚህ ነው፡፡
 
ኢየሱስን እናምናለን ስንል የምናምነው በባህሪው ብቻ አይደለም፡፡ በሁሉን ቻይነቱ ብቻም አይደለም፡፡ የዳንነው ክርስቶስ አምላክ ሆኖ ሳለ ወደዚህ ምድር በመምጣት በጥምቀቱ የእናንተንና የእኔን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ ወስዶ ስለ እኛ ሲል በመስቀል ላይ መስዋዕት መሆኑን በማመን ነው፡፡ በመገናኛው ድንኳን የተገለጠውን ደህንነት ስንመለከት በኢየሱስ እናምናለን ስንል በእርግጥ ሊኖረን የሚገባው ትክክለኛ እምነት ምን እንደሆነ በጣም ግልጽ ይሆንልናል፡፡
 
ዛሬ ‹‹♫ከሐጢያት ሸክም ነጻ መሆን ትወዳለህን? ♪በደሙ ውስጥ ሐይል አለ፤ በደሙ ውስጥ ሐይል አለ♫›› በማለት ባለማቋረጥ የሚጮሁ፣ በመስቀሉ ላይ ደም ብቻ የሚያምኑና ከራሳቸው በመነጨ ጉጉት ‹‹አቤቱ! አምናለሁ!›› እያሉ በእውር ድንብር የሚጮሁ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ምንም ያህል በኢየሱስ ተግተው ቢያምኑም በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደም በማመን ብቻ በፍጹም ከሐጢያቶቻቸው ነጻ መሆን አይችሉም፡፡
 
እኛ እንደዚህ ስለሆንን በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ፈጽሞ ከሐጢያቶቻችን ነጻ መውጣት አንችልምና አዳኝ ያስፈልገናል፡፡ ይህ አዳኝ የነገሥታት ንጉሥ፣ የአጽናፈ ዓለማት ሁሉና በዚያ ውስጥ ያለው የእያንዳንዱ ነገር ፈጣሪ የሆነው የሕይወታችን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እርሱ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ በጥምቀቱም ሐጢያቶቻችንን በራሱ ላይ ወሰደ፡፡ በመስቀል ላይ በመሞትም ከሐጢያቶቻችን አነጻን፡፡ በሌላ አነጋገር የዳንነው የሐጢያቶቻችንን ኩነኔ ሁሉ በጥምቀቱና በመስቀሉ በተሸከመው አዳኛችን በኢየሱስ ክርሰቶስ በማመን ነው፡፡ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያው በር በግልጽና በተጨባጭ እያሳየን ያለው ይህንን ነው፡፡
 
 
በሐይማኖታዊ መንገድ ብቻ በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች፡፡ 
 
በዚህ ዘመን በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደም ብቻ በማመን መዳን እንደሚችሉ የሚናገሩ ሰዎች አሉ፡፡ የዚህ ዓይነቱን ባዶ አባባል መናገር ሐይማኖታዊ እምነታቸውን የሚያሳይ ከመሆኑ በስተቀር የሚረባው ነገር የለም፡፡ እነዚህ ሰዎች ‹‹ለእግዚአብሄር የንስሐ ጸሎቶቼን ሳቀርብ መንፈስ ቅዱስ በልቤ ውስጥ ልጄ ሆይ ሐጢያቶችህን ይቅር ብያለሁ ብሎ ተናገረኝ፡፡ የእርሱን ድምጽ ስሰማ እንደምን በምስጋና ተሞላሁ!›› ይላሉ፡፡ እንደዚህ ማመናቸው የእምነታቸው ምስክርነት መሆኑን እየተናገሩ የዚህ ዓይነት አባባሎች ይጠቀማሉ፡፡
 
ነገር ግን ደህንነታችን ከራሳችን ስሜቶች የሚመጣ አይደለም፡፡ በፈንታው እኛ የዳንነው በሁለንተናዊ የስብዕና ደርዞች ማለትም በዕውቀት፣ በስሜትና በፈቃድ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር መዳን ያለብን መጀመሪያ አዳኛችን እግዚአብሄር እንዴት እንዳዳነን በማወቅና ከዚያም በዚህ እውነት በማመን ነው፡፡ ሐይማኖቶችን በሚመለከትስ? ሐይማኖቶች ምንድናቸው? ሐይማኖቶች በራሳቸው በሰዎች አስተሳሰቦች የተመሰረቱ ሰው ሰራሽ ተቋሞች እንጂ ሌላ ምንም አይደሉም፡፡
 
ከረጅም ጊዜ በፊት በቤተሰቤ ውስጥ እናቴ ምግብ አብሳይ ነበረች፡፡ እኔም ልክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጠቀሰው ያዕቆብ ምን ዓይነት ዕርዳታ እንደምትፈልግ እየጠየቅሁ በየማዕድ ቤቱ እርስዋን የምከተል ረዳቷ መሆን ለምጄ ነበር፡፡ እናቴ በኩሽና ውስጥ ምግብ በማዘጋጀት ስትባትል እኔ ደግሞ በመመገቢያ ክፍል ውስጥ ያለውን ገበታ በማሰናዳት እባትል ነበር፡፡ እኔና እናቴ ድንቅ የሆነ ጥምረት ነበረን፡፡ በማለዳ ተነስተን እሳቱን እናቀጣጥልና ገበታ እናዘጋጃለን፡፡ ከማዕዱ በኋላ የኩሽናውን ወለል በመጥረጊያ እንጠርጋለን፡፡ የማለዳው ተግባር በሙሉ የሚጠናቀቀው በዚህ መጥረጊያ ነበር፡፡
 
በዚያን ዘመን ይህ በኮርያ ለየት ያለ ትዕይንት አልነበረም፡፡ ነገር ግን አስደሳቹ ነገር የኩሽናውን ወለል ለመጥረግ ጥቅም ላይ የዋለው ይህ መጥረጊያ ድንገት የምንጠይቀውን ሁሉ የሚሰጠን በሚመስል መልኩ ወደ አማልክትነት መለወጡ ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር ለዚህ ለተበጣጠሰ መጥረጊያ በተጨባጭ የሚጸልዩ ሰዎች ነበሩ፡፡ እንደዚህ ያሉ ምጸቶች በሕይወታችን ውስጥ የተለመዱ ነበሩ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ በቤተሰቡ ውስጥ ወይም በጎረቤት አንድ ደስ የማይል ነገር በሚከሰትበት ጊዜ ሁሉ አስማት እንዲያደርግ ጠንቋይ መጥራት ለምደን ነበር፡፡በወቅቱ የነበሩ ሰዎች የፓንቴይስቲክ (እግዚአብሄር በሁሉም ነገር ውስጥ ይገኛል የሚል እምነት) አመኔታዎችን ይዘው ስለነበርና አማልክቶችም በሁሉም ስፍራ ይገኛሉ ብለው ስለሚያምኑ ወደ አምላክነት የሚለወጠው መሬት ለመጥረግ የሚያገለግለው ይህ መጥረጊያ ብቻ ሳይሆን የቅድመ አያቶቻቸው ስሞች በኮረብታ ላይ ባለው ትልቅ ዓለት ላይ ባሉ የዘር ግንድ ጽላቶች ወደ አምላክነት ይለወጣሉ፤ ወይም ዓይኖቻቸው ያዩት እያንዳንዱ ነገርም ወደ አምላክነት ሊለወጥ ይችላል፡፡
 
አሁን ዘመን እያለፈ ሲመጣ ሰዎች ቀስ በቀስ ከዚህ ዓይነቱ ድንቁርና እየወጡ ነው፡፡ ያን ጊዜ ግን ማንኛውም ነገር ወደ አማልክትነት ይለወጣል ማለት የዘወትር ሁነት ነበር፡፡ ስለዚህ በዚያን ዘመን እጅግ ፈጣን ከሆኑት የንግድ ሥራዎች አንዱ ጥንቆላ ነበር፡፡ ጠንቋዮች በሚጠነቁሉበት ጊዜ የማይስተዋሉ ቃሎችን ሲናገሩ መስማቴን አስታውሳለሁ፡፡ እኔም ‹‹አብራካዳብራ አብራካዳብራ ንጋት ይምጣ፤ ንጋት ሲመጣ ሁሉም የእኔ ይሆናል፡፡ ከታማኝነት ጉድለት የተነሳ የዱባው ቅል ተሰብሯል፡፡ አብራካዳብራ አብራካዳብራ›› እያልሁ በመጮህ የጠንቋዩን መንገድ ለማስመሰል እሞክር ነበር፡፡ ቃሎቹ ምን ማለት እንደሆኑ የማውቀው ምንም ነገር አልነበረኝም፡፡
 
እንዲህ ያለው ጥንቆላ ከጎረቤቶቼ ቤቶች በአንዱ ውስጥ ሲከናወን በነበረ ጊዜ በመንደሩ የሚኖር ሰው ሁሉ ይህንን ለማየት ግልብጥ ብሎ ይወጣ ነበረ፡፡ ይህ ሁነት ትኩረትን የሳበው በአንድ የሞተ አሳማ ራስ ላይ ገንዘቦች ተከመረው ያ አሳማ ያለ ምንም ፍንጭ ሲስቅ መታየቱ ነበር፡፡ የገንዘቡ መጠን የጠንቋይዋን የአስማት ብቃት የሚወስን ነው፡፡ ይህ ጥንቆላ እስኪነጋ ድረስ ሌሊቱን በሙሉ ይቀጥል ነበር፡፡
 
ድሮ ከማውቃቸው ሰዎች መካከል በአንዲት ድንግል መናፍስት ቁጥጥር ሥር እንደወደቀ የሚናገር አንድ ሰው ነበር፡፡ ድንግል በሆነች መናፍስት ስለተያዘ አጋንንቶችን ሁሉ ማባረር እንደሚችል መናገር ይወድ ነበር፡፡ ድንግል መናፍስቶች ከሌሎቹ የበለጠ ሐይል እንዳላቸው ይገመታል፡፡ በጣም ሐይለኛ የሆነ አጋንንት ከገጠመው ይህንን አጋንንት ከማባረር ይልቅ እርሱ ራሱ እንደሚታነቅ ተናግሮዋል፡፡ ነገር ግን እንደዚያም ሆኖ ሌሎች ዓይነት አጋንንቶችን ሁሉ ማባረር እንደሚችል አውርቷል፡፡ እርሱ ጠንቋይ ነበር፡፡
 
እርሱ የተለመደ ጊዜውን የሚያሳልፈው እንደ ማንኛውም ሰው ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው የጥንቆላ ችሎታውን እንዲያሳይ በሚጠይቀው ጊዜ ሁሉ ልብሶቹን ቀይሮ የጠንቋይ ልብሱን በመልበስ ድንቅ የሆነ ትዕይንቱን ይፈጽማል፡፡ ሰዎች ከእግዚአብሄር ቃል ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን የዚህ ዓይነት ኋላ ቀር ሐይማኖቶች የሚከተሉትና ሁሉንም ዓይነት ግራ የሚያጋቡና አሳፋሪ ነገሮች የሚያምኑት ልባቸው እንደዚህ ባሉ የባዕድ አምልኮ አስተሳሰቦች ስለተያዘ ነው፡፡
 
በሌላ አነጋገር ሰዎች የራሳቸውን ሐይማኖቶች ፈጥረዋል፡፡ ከላይ ያለው ታሪክ እንደሚያሳየው በራሳቸው መንገድ አማልክቶቻቸውን ሰርተዋል፡፡ ሰዎች የዚህ ዓይነት ደመ ነፍስ ስላላቸው ክርስቲያኖችም ቢሆኑ በኢየሱስ ለእነርሱ እንደተሰቀለ ሲነገራቸው ስሜቶቻቸው በዚህ ነገር በቀላሉ ይነኩና በእርሱ ከመጠን በላይ ተማርከው በዕውር ድንብር ያምኑታል፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅና አጽናፈ ዓለማትን ሁሉ የፈጠረ ፈጣሪ መሆኑ ሲነገራቸው ይህንንም በመውደድ እንደገና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ያምናሉ፡፡ ‹‹እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም›› የሚለውን ጥቅስም መስማት ይወዳሉ፡፡ እንደገናም አንዳች ተጨባጭ መረዳት ሳይኖራቸው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይህንንም ያምናሉ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ስሁት ስላይደለ መልካሙን ቃል ለመጀመሪያ ሲሰሙ የሚሉት ነገር ቢኖር ኢየሱስን የሚወዱት መሆኑን ነው፡፡
 
ነገር ግን ኢየሱስ በእርሱ እናምናለን ቢሉም ልባቸው አሁንም ሐጢያተኛ ሆኖ የቀረውን እነዚህን ሰዎች ለመፍረድ ይመጣል፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑትንም ሊወሰድ ይመጣል፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሳያውቁ በራሳቸው አስተሳሰቦች ላይ ብቻ ተመርኩዘው በኢየሱስ የሚያምኑ አብዛኞቹ ሰዎች ውሎ አድሮ የሐይማኖት ሕይወታቸውን በጀመሩ በ10 ዓመታት ጊዜ ውስጥ በእግዚአብሄር ሕግ መሰረት መኖር ያልቻሉ ሐጢያተኞች መሆናቸውን ይገነዘባሉ፡፡
 
እኔም እንዲያው በዘፈቀደ በኢየሱስ ሳምን ቆይቻለሁ፡፡ ክርስቶስን በማግኘቴ ብቻ ከመጠን በላይ ተደስቼ ሁልጊዜም የምስጋና መዝሙሮችን የመዘመር ልማድ ነበረኝ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስን ካወቅሁ በኋላ ሕጉን ወደ ማወቅ መጣሁ፡፡ ሕጉን ካወቅሁ በኋላም ሐጢያቶቼን ወደ ማወቅ መጣሁ፡፡ ሐጢያቶቼን ካወቅሁ በኋላ ዘላለማዊ የሐጢያት ፍርድና እርሱን ተከትሎም የሐጢያት ስቃይ እንዳለ ተረዳሁ፡፡
 
ይህንን የሐጢያት ስቃይ ለማቃለል ከልቤ የንስሐ ጸሎቶችን ጸለየሁ፡፡ ነገር ግን እንደዚህ ያለው እምነት ሰዎች ለመባረክ ሲሉ ለሁሉም ነገሮች ከሚጸልዩበት ባዕድ አምልኮአዊ እምነት ጋር የሚመሳሰል ነበር፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ የተጻፈውን ሕግ ወደ ማወቅ ከመጣሁና ሐጢያቶቼን ከተገነዘብሁ በኋላ የንስሐ ጸሎቶቼን መተው እንዳለብኝ አሰብሁ፡፡ የዚህ ዓይነት የንስሐ ጸሎት አንዳች የስሜት እፎይታ ያመጣልኝ ነበር፡፡ ሐጢያት ግን አሁንም በሕሊናዬ ውስጥ አለ፡፡ ነፍሴ አሁንም በሐጢያት ባርነት ውስጥ እንዳለች በማወቄ መሰቃየቴን ቀጠልሁ፡፡
 
በኢየሱስ ወደ ማመንና እርሱን ወደ መውደድ የመጣሁት በሐጢያቶቼ ስለተተበተብሁ ሳይሆን ሐጢያቶቼን ወደ መገንዘብ መጥቼ በኢየስስ ስላመንሁ ነበር፡፡ መጨነቅ የጀመርሁት በዚህ ሁኔታ ሐጢያቶቼን ከተገነዘብሁ በኋላ ነበር፡፡ ‹‹በኢየሱስ ያመንሁት ገና በወጣትነቴ በመሆኑ ተጸጽቼ ነበር፡፡ ሆኖም በኢየሱስ ማመኔን ማቆም አልቻልሁም፡፡ ስለዚህ ከዚህ የሐጢያት ባርነት ነጻ ለመውጣት የንስሐ ጸሎቶቼን አቀረብሁ፡፡ ነገር ግን ዋጋ አልነበረውም፤ ምክንያቱም እነዚህ ጸሎቶች ችግሩን በመሰረታዊ መልኩ ለመፍታት ያደረጉት አስተዋጽዖ ጥቂት ነበር፡፡
 
ተራ ሰዎች ሐጢያቶችን ቢሰሩም ምን ዓይነት ሐጢያቶች እንደሰሩ አያውቁም፡፡ ነገር ግን ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ሲጀምሩ ስለ ሕጉ ይሰሙና ሐጢያቶቻቸውን ወደ መገንዘብ ይመጣሉ፡፡ ስለዚህም በሐጢያቶቻቸው ይታሰራሉ፡፡ በመጀመሪያ የሐጢያቶቻቸውን ችግር ከስሜት የመነጩ የንስሐ ጸሎቶችን በማቅረብ ለማቃለል ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን ጊዜ እየነጎደ ሲሄድ በሐጢያቶቻቸው እንደታሰሩና ይቅርታን ማግኘት እንዳለባቸው ይበልጥ ይገነዘባሉ፡፡
 
የንስሐ ጸሎቶቻቸውን ምንም ያህል አብዝተው ቢጸልዩም ይበልጥ በጸለዩ መጠን ሐጢያቶቻቸው ከመወገድ ይልቅ ይበልጡኑ በይፋ ተገልጠው ስለመኖራቸው አብዝተው ያስታውሱዋቸዋል፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የእነዚህ ሰዎች ሐይማኖታዊ ሕይወት በስቃይ የተሞላ ይሆናል፡፡ እነርሱም መቸገራቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ‹‹ለመጀመሪያ ጊዜ ባመንሁበት ወቅት ጥሩ ስሜት ተሰምቶኝ ነበር፡፡ ታዲያ አሁን 5, 10 ዓመታት ካለፉ በኋላ ብዙ ጥሩ ስሜት የማይሰማኝ ለምንድነው? ችግር የገጠመኝ ለምንድነው?›› በማለት ግራ ይጋባሉ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያምኑ አጽንተው ይዘውት የነበረው የደህንነት አመኔታቸው እንኳን አሁን ፈጽሞ እንደሌለ ተገንዝበዋል፡፡ በኢየሱስ ካመኑ በኋላ ሐጢያተኞች መሆናቸውን በማሰብ ከእምነታቸው ጋር የሚስማሙ ሁሉንም ዓይነት የሐይማኖት ትምህርቶች ይቃርሙና ሐይማኖተኞች ሆነው ይቀራሉ፡፡
 
እነዚህ ሰዎች መጨረሻቸው ተራ ሐይማኖተኞች የሆነው ኢየሱስ በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ ያዳናቸው የመሆኑን እውነት ባለማወቃቸው ነው፡፡ በኢየሱስ እናምናለን ቢሉም አሁንም ግራ የተጋቡ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ልባቸው ሰላም የለውምና፡፡ እነዚህ ሰዎች ሌላ አምላክ የመቀየር አማራጭ ቢኖራቸውም ያንን ማድረግ አይችሉም፡፡ ቢሞክሩ እንኳን ከራሱ ከእግዚአብሄር ውጪ በማንኛውም ሌላ ነገር ማመን ጣዖት አምልኮ መሆኑን አስቀድመው ያውቃሉ፡፡ ኢየሱስ ብቻ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ፣ እርሱ ብቻ ራሱ አምላክ እንደሆነና አዳኙም እርሱ ብቻ እንደሆነ በግልጽ ስለሚያውቁ በአንድ የተለየ አምላክ ማመን አይችሉም፡፡ ነገር ግን እውነቱን ስለማያውቁ ሁልጊዜም በሐጢያቶቻቸው ግራ እየተጋቡ በችግር ይኖራሉ፡፡
 
በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ የመጣውን ኢየሱስን ማወቅና ማመን ያለባቸው ለዚህ ነው፡፡ ወደ ሐይማኖተኞች የተለወጡት እነዚያ ክርስቲያኖችም ኢየሱስ ንጉሥ እንደሆነ፣ በመስቀል ላይ ደሙን እንዳፈሰሰና የመጽሐፍ ቅዱስ ቃልም የእግዚአብሄር ቃል እንደሆነ ያውቃሉ፡፡
 
ነገር ግን ኢየሱስ በጥምቀቱ በራሱ ላይ የወሰደው የእነርሱን ሐጢያቶች ብቻ ሳይሆን የዓለምን ሐጢያቶችም ጭምር እንደሆነ አያውቁም፡፡ እምነት እንዳላቸው ቢናገሩም ሐጢያተኞች ሆነው እንዲኖሩ የሚያደርጋቸውና የሁሉም ፍጻሜ ለሐጢያተኞች ወደተመደበው ስፍራ መንጎድ የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡ እነዚህ ክርስቲያን ሐይማኖተኞች ኢየሱስ እንዴት በትክክል ሐጢያቶቻቸውን እንዳስወገደላቸው ስለማያውቁ በሚነቃቁበት ጊዜ ሁሉ በራሳቸው ስሜቶች ያምናሉ፡፡ ከዚህ የተነሳም አንድ ማየት የተሳነው ሰው የዝሆንን የአካል ክፍሎች በመዳሰስ ብቻ ዝሆን መሆኑን ለማወቅ እንደሚሞክር ሁሉ እውነተኛው ጭብጥ ከሚያምኑት ጋር አይጣጣምም፡፡ የእምነታቸው ስህተት ምን እንደሆነ ፈጽሞ የማያውቁትና እንደገና ግራ የሚጋቡት ለዚህ ነው፡፡
 
 
በሰማያዊው ማግ እውነት ባናምን ምን ይፈጠራል? 
 
ሰማያዊውን ማግ ከመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር አስወግደን ኢየሱስን አዳኛችን አድርገን ብናምነው ምን ይፈጠራል? እግዚአብሄር የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ ተፈትሎ እንዲሰራ ባዘዘ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤሎች የመግቢያውን በር በሐምራዊና በቀይ ማግ ብቻ እንዲሰሩ ቢነግራቸውና እስራኤሎችም የመግቢያውን በር በዚህ መንገድ ቢሰሩት እግዚአብሄር ምን ይል ነበር? እግዚአብሄር የመገናኛው ድንኳን የመግቢ በር ነው ብሎ ይቀበለው ነበር? በፍጹም አይቀበለውም፡፡ እግዚአብሄር ለእስራኤሎች የመገናኛውን ድንኳን የመግቢያ በር የተለያዩ ቀለማቶች ካላቸው አራት ማጎች እንዲሰሩት ነግሮዋቸዋል፡፡ በዚህ መሰረት ካልተሰራ የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ተብሎ በጭራሽ አይጠራም፡፡ ከአራቱ ማጎች አንዱም እንኳን መቅረት የለበትም፡፡
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ መፈተል ነበረበት፡፡ ራሱ አምላክ የሆነው ኢየሱስ የሰው ሥጋ ለብሶ ወደዚህ ምድር በመምጣትና በሰውነቱ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በመውሰድ በመስቀል ላይ ስለሞተ፣ ከሙታን ስለተነሳና ሐጢያቶቻችንንም እንደ በረዶ ነጭ ስላደረገው ከሐጢያቶቻችን የዳንነው በዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለታመንንና ስላመንን ነው፡፡ የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ቀለማቶች ከሐጢያቶቻችን ለመዳን እንዴት በኢየሱስ ማመን እንደሚገባን ይነግሩናል፡፡ በመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር በተገለጠው እውነት የሚያምኑ ሁሉ ከሐጢያቶቻቸው ድነዋል፡፡ ሁሉም የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ተቀብለው እንደ በረዶ ነጭ ሆነዋል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእናንተንና የእኔን ሐጢያቶች አጥቦ እንደ በረዶ ነጭ አድርጎናል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእናንተና የእኔ እውነተኛ አዳኝ ሆንዋል፡፡
 
በመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር የተገለጠው ዋና እውነት ይህ ነው፡፡ ነገር ግን ዛሬ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ እናምናለን እያሉ በሰማያዊው ማግ አንደምታ የማያምኑ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡
 
ይህንን መጽሐፍ ለመጻፍ ስነሳ በአንድ ወቅት ቀደምት ምርምር ለማድረግ ስል ወደ አንድ የክርስቲያን መጽሐፍ መሸጫ መደብር ሄጄ ነበር፡፡ እዚያም ስለ መገናኛው ድንኳን አደባባይ እጅግ ታዋቂ በሆኑ አንዳንድ የክርስቲያን መሪዎች የተጻፉ መጽሐፎችን አገኘሁ፡፡ ነገር ግን አንዳንዶቹ የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር አልጠቀሱትም፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ‹‹የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ሰማያዊ፣ ሐምራዊ ቀይ ማግና ጥሩው በፍታ ምን ይነግሩናል? ሰማያዊ የሰማይ ቀለም ነው፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ አምላክ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ቀይ ኢየሱስ ወደዚህ ምድር በመጣ ጊዜ በመስቀል ላይ ያፈሰሰውን ክቡር ደሙን ያመለክታል፡፡ ሐምራዊ እርሱ ንጉሥ መሆኑን ይነግረናል›› የሚል መሰረት የለሽ አባባል አስፍረዋል፡፡
 
የዚህ ዓይነቱ አረተጓጎም ዒላማውን በጣም የሳተ ነው፡፡ ኢየሱስ አምላክ መሆኑ የተነገረን በሐምራዊው ማግ ነው፡፡ እግዚአብሄር በሐምራዊው ማግ አማካይነት ኢየሱስ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ መሆኑን አስቀድሞ ነግሮን ሳለ ይህንኑ ነገር እንደገና በሰማያዊው ማግ የሚደግመው ለምንድነው? እነዚህ ሰዎች ሰማያዊውን ማግ በትክክል መተርጎም የተሳናቸው የሰማያዊውን ማግ ምስጢር ስለሚያውቁ ነው፡፡
 
እነርሱ የሚያውቁት በመስቀል ላይ የፈሰሰውን ደም ብቻ ስለሆነ በቀዩ ማግ ላይ ትልቅ ትኩረት አድርገዋል፡፡ የመገናኛውን ድንኳን ሥዕሎቻቸውን በምንመለከትበት ጊዜ በነጭና በቀይ ቀለማቶች መሞላታቸውን እንመለከታለን፡፡ የሰማያዊው፣ የሐምራዊው፣ የቀዩ ማግና የጥሩው በፍታ አራቱ ቀለማቶች በመገናኛ ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ በግልጽ መታየት ሲገባቸው የእነርሱ ስዕሎች የሚያሳዩት ግን ቀዩንና ነጩን ማግ አልፎ አልፎም ሐምራዊውን ማግ ብቻ ነው፡፡ ሰማያዊው ማግ ግን በጭራሽ የለም፡፡
 
በዚህ ዓለም ላይ የሰማያዊውን ማግ እውነት ሳያውቁ እንደዚህ ስላለ የማይጨበጥ እምነት የሚናገሩ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ በዚህ ዘመን ኢየሱስ ኩነኔያችንን ለመሸከም በጥምቀቱ የዓለም ሐጢያቶቻችንን በራሱ ላይ መውሰዱን ሳያውቁ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ብቻ በማመን መዳን እንደሚችሉ የሚያምኑ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ የእነዚህ ሰዎች ልብ ሁልጊዜም በሐጢያት እንደተሞላ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ዛሬም፣ ነገም፣ ከነገ በስቲያም፣ እንዲያውም እስኪሞቱ ድረስ ከሐጢያተኝነታቸው ነጻ መውጣት ስለማይችሉ እየተሰቃዩ ይኖራሉ፡፡ ስለዚህ አንዳንድ ሰዎች ‹‹እኔ እስክሞት ድረስ በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያተኛ ነኝ›› በማለት ይናዘዛሉ፡፡ ነገር ግን በኢየሱስ ቢያምኑም እስከሚሞቱ ድረስ ሐጢያተኞች ሆነው መቅረታቸው በእርግጥ ትክክለኛ እምነት ነውን?
 
በኢየሱስ ካመንን በኋላ ታዲያ በትክክል ጻድቃን የምንሆነው መቼ ነው? ሰማይ በኢየሱስ ጥምቀትና ደም በማመን ሐጢያት አልባ ለሆኑት የተዘጋጀ ስፍራ አይደለምን? ሰማይ በእርግጥም ለጻድቃን የተዘጋጀ ስፍራ እንጂ ለሐጢያተኞች የተዘጋጀ ስፍራ አይደለም፡፡ ሰማይ መግባት የሚችሉት ከሐጢያቶቻቸው በተጨባጭ የዳኑና ሐጢያት አልባ የሆኑ ብቻ ነው፡፡
 
በኢየሱስ ቢያምኑም እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ሐጢያተኞች ሆነው እንደሚቀሩ ስለ ራሳቸው እየተናገሩ በእርሱ ያላቸውን እምነት ምንም ያህል ደጋግመው ቢናዘዙም የመዳን አመኔታ የላቸውም፡፡ ምክንያቱም ስለ ሰማያዊው፣ ስለ ሐምራዊው፣ ስለ ቀዩ ማግና ስለ ጥሩው በፍታ አያውቁምና፡፡ በኢየሱስ ቢያምኑና ወደ እርሱ ቢጸልዩም ጸሎቶቻቸው የሚሰሙ ስለመሆናቸው እምነት የላቸውም፡፡ በኢየሱስ ቢያምኑም በእርሱ ረድኤት አላገኙም፤ አልተወደዱም፡፡ ታማኝነታቸውን ሲያሳዩ የተወደዱ መስሎ ተሰምቶዋቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከታማኝነታቸው ሲጎድሉ እግዚአብሄር የተዋቸው፣ እርሱ የጠላቸው መስሎ ይሰማቸዋል፡፡ እግዚአብሄር የሚወዳቸውና የሚባርካቸው መባዎቻቸውንና ታማኝነታቸውን ለእርሱ ሲሰጡ ብቻ እንደሆነ ያስባሉ፡፡ መባዎቻቸውን መስጠት ሲያቅታቸው ግን ከእንግዲህ እንደማይወዳቸው ያስባሉ፡፡ አስቸጋሪ ጊዜ ሲገጥማቸው እግዚአብሄር እንደጠላቸውና ለምን እንደዚህ ባለ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ እንደሚያልፉ ሊገባው እንደማይችል በማሰብ በመጨረሻ ለጉስቁልናቸው ተወቃሽ እርሱ ነው ብለው በመደምደም በእርሱ ማመናቸውን ያቆማሉ፡፡
 
በመጨረሻ በእነዚህ ሰዎችና በእግዚአብሄር መካከል ያለው መተማመን ይፈርሳል፡፡ እምነታቸው የአስተሳሰቦቻቸውና የስሜቶቻቸው ውጤት ስለሆነ የዘፈቀደ፣ የሚያወላውልና የተሳሳተ ነው፡፡ ወደ እግዚአብሄር ስንቀርብ ስሜቶቻችንን ማስወገድ አለብን፡፡ ወደ እግዚአብሄር ስንቀርብ ኢየሱስ ክርስቶስ በሐጢያቶቻችን ምክንያት ለሲዖል የታጨነውን በጥምቀቱና በደሙ እንዳዳነን በሚናገረው እውነት በግልጽ የሚያምነውን እምነታችንን ይዘን መቅረብ አለብን፡፡ በእግዚአብሄር ቃልና በሕጉ ቃል ፊት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ፊትና በሕሊናችን እኛም ያለምንም ጥያቄ ለሲዖል የታጨን ሰዎች እንደነበርን በግልጽ መረዳት አለብን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ እውነተኛ አዳኛችን እንደሆነ መረዳት የምንችለው እኛ በተጨባጭ ምን ያህል ሐጢያተኛ ፍጡራን እንደነበርንና እግዚአብሄርም ከሐጢያቶቻችን ሁሉ እንዴት እንዳዳነን ስናውቅ፣ ስንማርና ስናምን ብቻ ነው፡፡
 
 
የደህንነትን ስጦታ መቀበል የምንችለው በእውነተኛ እምነት ብቻ ነው፡፡ 
 
ስለዚህ እናንተና እኔ ከሐጢያቶቻችን የዳንነው የራሳችንን በጎ ምግባሮች በማድረግ ሳይሆን በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ በማመናችን መሆኑን ማወቅ ይገባናል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐጢያቶቻችን ሊያድነን በዚህ አራት እጥፍ እውነት በግልጽ እንደመጣ ማወቅና ማመን አለብን፡፡ እርሱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ መሲህ ሆኖ እንደሚመጣ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ በእርግጥም ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ በጥምቀቱም ሐጢያቶቻችንንና የሰውን ዘር ሐጢያት በሙሉ በአንድ ጊዜ በራሱ ላይ ወሰደ፡፡ ከዚያም እነዚህን የዓለም ሐጢያቶች በመስቀል ላይ ተሸክሞ ተሰቀለ፤ ክቡር ደሙንም አፈሰሰ፡፡ ‹‹ተፈጸመ!›› (ዮሐንስ 19፡30) ብሎ ከተናገረ በኋላም ለ40 ተጨማሪ ቀናቶች መስክሮ ዳግመኛ ለመመለስ ቃል በመግባት ወደ እግዚአብሄር ዙፋን ቀኝ አረገ፡፡ በእነዚህ ማመን አለብን፡፡
 
‹‹በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ አገልግሎቶቼ በተጨባጭ አድኛችኋለሁ፡፡ በዚህ የደህንነት እውነት የሚያምኑትንም ለመውሰድ ተመልሼ እመጣለሁ፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች ይሆኑ ዘንድም መብትን እሰጣቸዋለሁ፡፡ በልባቸው በዚህ እውነት የሚያምኑትንም ለመውሰድ ተመልሼ እመጣለሁ፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች ይሆኑ ዘንድም መብትን እሰጣቸዋለሁ፡፡ በልባቸው በዚህ እውነት የሚያምኑትን ከሐጢያቶቻቸው አነጻቸዋለሁ፡፡ እንደ በረዶም ነጭ አደርጋችኋለሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስንም እሰጣቸዋለሁ፡፡ የራሴም ልጆች አደርጋቸዋለሁ፡፡›› ጌታችን የነገረን ይህንን ነው፡፡
 
በዚህ ቃል ማመን አለብን፡፡ ጌታችን እነዚህን ተስፋዎች አስቀድሞ ፈጽሞዋል፡፡ በዚህ ምድር ላይ በሚኖሩ ሰዎች ሕይወት ውስጥም በተጨባጭ እየሰራ ነው፡፡ በዚህ እውነት የሚያምኑትንና የሚመሰክሩትንም ይጠብቃቸዋል፡፡ በጌታችን የጥምቀትና የደም ሥራዎች የዳንነው በእግዚአብሄር ጸጋ፣ ጥበቃና ፍቅር የምናርፈውና የጻድቃን ሕይወት የምንኖረው እንደዚህ ነው፡፡ በማመን ከሐጢያቶቻችን ነጻ የወጣነው እርሱ ስለዳንን ነው፡፡
ይህ በመገናኛው ድንኳን ላይ የተጻፈው መጽሐፍ በመላው ዓለም ቋንቋዎች ሁሉ ሲተረጎም በመላው ዓለም የሚኖሩ ሕዝቦች በእውነቱ ላይ ባላቸው እምነት አማካይነት ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ እንደሚድኑ እርግጠኛ ነኝ፡፡ የሐጢያት ስርየት የሚመጣው በኢየሱስ ደም ብቻ ነው የሚሉ ዳግመኛ እንደዚህ ማለት አይችሉም፡፡ በፈንታው አባባሎቻቸው ምን ያህል ሐሰት እንደሆኑ ወደ መረዳት ይመጣሉ፡፡ ሐሰት የሆነን ነገር ይዘው ደህንነት ይህ ነው ማለት አይችሉም፡፡ በኢየሱስ ደም ብቻ በማመን መዳን እንደሚችሉ ከቶውኑም መናገር አይችሉም፡፡
 
በመገናኛው ድንኳን የአደባባይ መግቢያ በር ላይ ግልጽ የሆነው የሰማያዊ፣ የሐምራዊ፣ የቀይ ማግና የጥሩ በፍታ የደህንነት ቃል የሆነው የውሃና የመንፈስ ወንጌል ይገኛል፡፡ ይህ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ቃል የተገባና የተተነበየ የእግዚአብሄር ቃል ስለሆነና እግዚአብሄርም በጥምቀቱና በስቅለቱ የሐጢያቶችን ደህንነት በመፈጸም በአዲስ ኪዳን ውስጥ ይህንን ተስፋ ስለጠበቀ በዚህ የደህንነት ስጦታ በደስታና በምስጋና ካመንን ሁላችንም ዘላለማዊውን የሐጢያት ስርየት መቀበል እንችላለን፡፡
 
ይህ በጣም ቀላልና ፍጹም የሆነ ቃል ነው፡፡ ነገር ግን ደግሞ በቃሉ ላይ ንጹህ እምነት ከሌላችሁ የመላው ዓለም ዕውቀት ሁሉ ቢኖራችሁም ሊስተዋል የማይችል እውነት ነው፡፡ ይህ ቸል ልንለው የማንችለው የከበረ እውነት ስለሆነ እናንተና እኔ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በእርግጠኝነት ማመን አለብን፡፡ እግዚአብሄር በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የተገለጠውን የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውን፣ የቀዩን ማግና የጥሩውን በፍታ እውነት በነጻና በቀላሉ በማስተማር በእምነታችን ይህንን በዋጋ የማይተመን የደህንነት ስጦታ እንድንወስድ ፈቅዶልናል፡፡
 
በዚህ እውነት የምናምን እናንተና እኔ ለእውነት ፍቅሩ እግዚአብሄርን ማመስገን አለብን፡፡ ሆኖም ተጨባጩን የሰማያዊ፣ የሐምራዊና የቀይ ማግ እውነት የማያውቁና ሰዎችን ያስተማሩ በሐሰተኛ መንገዶቻቸው የሚመሩ ብዙዎች አሉ፡፡ እውነትን ባለማወቃቸው ልባቸው ለሚሰቃይባቸው ይህንን የውሃና የመንፈስ ወንጌል እንሰብክላቸዋለን፡፡ ከሐጢያቶቻቸው ነጻ ወጥተውም በደህንነት በር ውስጥ አልፈው እንዲገቡ እንሻለን፡፡ የመገናኛውን ድንኳን እውነት ስንሰብክ በዚህ የሚያምኑ ይድናሉ፡፡ የማያምኑ ግን በሐጢያቶቻቸው ይኮነናሉ፡፡ በኢየሱስ ለማመን ከወሰንን የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውንና የቀዩን ማግ እውነት አውቀን በእርሱ ማመን አለብን፡፡
 
ከመጀመሪያው የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውንና የቀዩን ማግ እውነት ያወቀ የለም፡፡ እግዚአብሄር እንዲህ ብሎናል፡- ‹‹እውነትንም ታውቀላችሁ፤ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፡፡›› (ዮሐንስ 8፡32) እውነት ምንድነው? እውነት እውነተኛው ወንጌል ነው፡፡ (ኤፌሶን 1፡13) ያም ማለት በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ የተገለጠው የውሃና የመንፈስ ወንጌል ነው፡፡ ሰማያዊውን፣ ሐምራዊውንና ቀዩን ማግ በትክክል ማወቅና በእነርሱም ማመን በእውነት የማመን ትክክለኛው እምነት ነው፡፡
 
ኢየሱስ እውነት ነጻ እንደሚያወጣን የተናገረው ለምንድነው? ከሐጢያቶቻችሁ የዳናችሁት እንዴት ነው? በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ በማመናችሁ ከሐጢያቶቻችሁ የዳናችሁ ብቻ ሳትሆኑ መንፈስ ቅዱስም በልባችሁ አላደረምን? ሐጢያቶቻችሁ ከልባችሁና ከሕሊናችሁ በግልጽ አልተወገዱምን? እግዚአብሄር በእርግጥም አባታችሁ እንደሆነ በተጨባጭ በማመን ከልባችሁ ጥልቅ ትመሰክራላችሁን? እግዚአብሄር ልጆቹ አድርጎ የሚያወቃቸው ሐጢያት አልባ የሆኑትን ብቻ በመሆኑ የሚደግፈውም ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር የተፈተሉትን ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና ጥሩ በፍታ የሚያውቁና የሚያምኑ ሰዎችን እምነት ብቻ ነው፡፡ ሐጢያተኞች የእግዚአብሄር ልጆች አይደሉም፡፡ የእግዚአብሄር አብ ልጆች እግዚአብሄር በሰጠን ብቸኛ ወንጌል በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ዳግመኛ የተወለዱት ብቻ ናቸው፡፡
 
በዚህ ዓለም ላይ ስንኖር ብዙ ችግሮች፣ መከራዎችና ስቃዮች ቢገጥሙንም እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ስለሚኖር ደስተኞች ነን፡፡ ብቁ ባንሆንም በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመንና የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውንና የቀዩን ማግ ወንጌል በመላው ዓለም በመስበክ የተባረከውን ሕይወታችንን እየኖርን ነው፡፡ ይህ ወንጌል የእግዚአብሄርን ጽድቅ ለግሶናል፡፡
 
ከሁሉም በላይ ስለ ሰማያዊው፣ ስለ ሐመምራዊውና ስለ ቀዩ ማግ እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ፡፡ ገና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢየሱስ ሳምን ምንም ያህል በታማኝነት በኢየሱስ ባምንም ልቤ አሁንም ሐጢያተኛ ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳም ክፉኛ ተሰቃይቼ ነበር፡፡ ምንም ያህል ከልቤ በኢየሱስ ባምንም ሐጢያት በግልጽ በሕሊናዬ ውስጥ ነበር፡፡ የገዛ ራስን ሕሊና በእግዚአብሄር ፊት በማየት ብቻ ሐጢያተኛ መሆን አለመሆንን ማወቅ ይቻላል፡፡ በሌላ አነጋገር ሐጢያት አሁንም በሕሊናቸው ውስጥ የተጻፈባቸው የሐጢያቶቻቸውን ስርየት መቀበል አልቻሉም፡፡ ሕሊናቸው ከሐጢያቶች ሁሉ እጅግ ኢምንት የሆነ ሐጢያት ካለበት እንኳን የሐጢያት ስርየትን ላለመቀበላቸው ይህ ማስረጃ ነው፡፡
 
ነገር ግን የሐጢያቶቼን ችግሮች በሙሉ ሊያቃልል የሚችለውን ከሁሉም ኢምንቱን እውነት እንኳን ሳላውቅ በነበርሁበት ጊዜ ከዚህ የተነሳም በልቤ ውስጥ ሁሉም ዓይነት ጥያቄዎችና ግራ መጋባቶች ተፈጥረው በነበረ ጊዜ እግዚአብሄር በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ እውነት ተገናኘኝ፡፡
 
ይህ ቃል የተገኘው ቀደም ብለን ካነበብነው የማቴዎስ ወንጌል ምንባብ ነበር፡፡ ማቴዎስ 3፡13-15ን እያነበብሁ ሳለሁ ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና›› (ማቴዎስ 3፡15) ወደሚለው ምንባብ ደረስሁ፡፡ ያን ጊዜ ኢየሱስ ተጠምቆ ከውሃ ሲወጣ እግዚአብሄር ጽድቁን እንደመሰከረለት አወቅሁ፤ አመንሁም፡፡ በዚህ የኢየሱስ ጥምቀት ሐጢያቶች ሁሉ ሲደመሰሱ ጽድቅ ሁሉ ተፈጸመ፡፡
 
ኢየሱስ በዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ሐጢያቶች ሁሉ በግልጽ ወደ እርሱ ተሻገሩ፡፡ በአንድ ጊዜም በመስቀል ላይ ተወገዱ፡፡ ኢየሱስ ለምን እንደተጠመቀ ምክንያቱን ባወቅሁና ባመንሁ ጊዜ ወዲያውኑ ያልተፈቱትን ሐጢያቶቼን በሚመለከት ያሉበኝ ችግሮችና ጥያቄዎች በሙሉ በአንድ ጊዜ ከእኔ ተቆርጠው ወደቁ፡፡ እኔ ለዚህ የሐጢያት ስርየት እውነት በጣም አመስጋኝ ነበርሁ፡፡ ምክንያቱም ይህንን የሐጢያት ስርየት ያገኙት እውነተኛ የእግዚአብሄር ቃል የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማወቄና በማመኔ ነው፡፡
 
ጌታ በተጻፈው ቃሉ አማካይነት ወደ እኔ መጣ፡፡ እኔም ይህንን በልቤ በማመኔ በውሃውና በመንፈሱ ቃል አማካይነት የሐጢያት ስርየትን አገኘሁ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በብሉይና በአዲስ ኪዳናት ቃል አማካይነት የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውንና የቀዩን ማግ ወንጌል ለብዙ ሰዎች እየመሰከርሁ ነው፡፡ አሁንም እንኳን እነዚህን እውነቶችና የደህንነት ምስጢራቶች ሁሉ ማሰራጨቴን ቀጥያለሁ፡፡ እውነተኛው ወንጌል ከሰብዓዊ ፍጡራን አስተሳሰቦች፣ ትምህርቶች ወይም ስሜታዊ ተሞክሮዎች የተሰራ ነገር አይደለም፡፡
 
ጌታችን በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ ሐጢያቶቻችንን ደምሰሶዋል፡፡ በመላው ዓለም የሚኖር እያንዳንዱ ሰው በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ የደህንነትን እውነት በግልጽ ወደ ማየቱ ይመጣል፡፡ ይህ እውነትም የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል መሆኑን ይገነዘባል፡፡ ይህ በዚህ የመጨረሻው ዘመን በእጅጉ የሚያስፈልግ እውነት ነው፡፡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሕዝቦች በዚህ እውነት ወደ ማመን ይመጣሉ፡፡
 
ይህ ዘመን የሰዎች ጽድቅ እየተፈረካከሰ ያለበትና ክፋታቸውም እየገነነ ያለበት ዘመን ነው፡፡ በዙሪያችን ያሉት ሁኔታዎች እየተበላሹ ሲሄዱ ሰዎች ተሸክመዋቸው የነበሩትን ክፋቶች በሙሉ ይዘረግፉዋቸዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ጌታችን እናንተንና እኔን በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ ወንጌል አማካይነት ከሐጢያቶቸቻችን አድኖናል፡፡ ይህ በረከት ምንኛ የሚመሰገንና በዋጋ የማይተመን ነው? እኔ ለዚህ ግልጽ ለሆነው ደህንነት ጌታችንን አመሰግናለሁ፡፡ ምክንያቱም በደስታና በሐሴት ተጥለቅልቄያለሁና፡፡
 
ዓለም በአሁኑ ጊዜ በእግዚአብሄር ወደተተነበየው የዘመን መጨረሻ እየገሰገሰች ነው፡፡ ወደዚህ ዘመንም ገብታለች፡፡ እግዚአብሄርን በታማኝነት የሚያገለግሉት ሰዎች በጣም ጥቂት በሆኑበትና የምዕመናን እምነትም በደከመበት እንደዚህ ባለው ዘመን ራሳችሁን ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል እውነት ውጪ ለሆነ አንዳች ነገር በታማኝነት ለመስጠት የምትሞክሩ ከሆነ ፍጻሜያችሁ የልብ ቁስለት ይሆናል፡፡ በእግዚአብሄር እያመናችሁ በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ የማታምኑ ከሆናችሁ ታዝናላችሁ፡፡ ምክንያቱም ይህ በልባችሁ ውስጥ ትርጉም ያለው አንዳች ነገር አይተውላችሁም፡፡ አንዳች ተጨባጭ ፍሬዎችም አያፈራላችሁምና፡፡
 
የመገናኛው ድንኳን አራት ቀለማቶች እውነት -- ሰማያዊው፣ ሐምራዊው፣ ቀዩ መሰግና ጥሩው በፍታ -- ግልጽ እውነት ስለሆነ ለዚህ ጨለማ ዓለም ብቸኛውና ምርጡ ወንጌል ነው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የተገለጠውን እውነት በማወቃችንና በማመናችን የሐጢያቶቻችንን ስርየት ተቀብለን ሕይወታችንን እየኖርን መሆናችን ለእኛ በዋጋ የማይተመን በረከት፣ ክቡር ስጦታና ታላቅ ሐሴት ነው፡፡
 
በመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር የተገለጠውን የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውን፣ የቀዩን ማግና የጥሩውን በፍታ እውነት የሚያውቁና የሚያምኑ እያገለገሉ ያሉት ሐሰትን ሳይሆን እውነትን በመሆኑ በልባቸው ውስጥ ለዘላለም ታላቅ ደስታ ይገኛል፡፡
 
እናንተም ደግሞ በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር የተገለጠውን እውነት አውቃችሁ ታምኑበታላችሁን? ልታውቁት ይገባል፤ ልታምኑበትም ይገባል::