Search

Pertanyaan dan Jawaban atas Iman Kristen

Pokok 2 : Roh Kudus

2-4. መንፈስ ቅዱስ በየቀኑ እንደሚናገረን አስባለሁ፡፡ በጥንቷ ቤተክርስስቲያን ዘመንም እንኳን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ብዙ ተዓምራቶችን አደረጉ፡፡ በዚያን ዘመን የሰራው መንፈስ ቅዱስ ዛሬም በተመሳሳይ መንገድ እንደሚሰራ አስባለሁ፡፡ ስለዚህ ብዙ የእግዚአብሄር ሰዎች በኢየሱስ ስም ተአምራቶችን ያደርጋሉ፡፡ ለምሳሌ አጋንንቶችን ያስወጣሉ፤ ወይም በሽታዎችን ይፈውሳሉ፤ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ በመመለስ ላይ ያነጣጠሩ ሌሎች ሥራዎችን ይሰራሉ፡፡ እነዚህ ሥራዎች የተሰሩት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት እንደሆነ አስባለሁ፡፡ ይህ እውነት ካልሆነ በጥንቷ ቤተክርስቲያን ዘመን በብርቱ በሰራው መንፈስ ቅዱስና ዛሬ ተአምራቶችን በሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው? እግዚአብሄር ትናንት ዛሬም ለዘላለምም ሁሌም ያው አይደለምን? 

በጥንቷ ቤተክርስቲያን ዘመን በሰራው መንፈስ ቅዱስና ዛሬ በሚሰራው መንፈስ ቅዱስ መካከል ተጨባጭ ልዩነት የለም፡፡ ብቸኛው ልዩነት በዚህ ዘመን ተዓምራትን የሚያደርጉት ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ የመሆናቸው ጉዳይ ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ዘመኑ ምንም ይሁን የእግዚአብሄር መንፈስ ሁሌም ያው ቢሆንም ልዩነቱ ሰው መንፈስ ቅዱስን የሚቀበልበት ትክክለኛ የእውቀት መንገድ ያለው ወይም ሌለው የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ 
ዛሬ ብዙ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት ሳይኖራቸው ድንቆችን ያደርጋሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በሐዋርያት ሥራ 2፡38፤በ1ኛ ዮሐንስ 5፡2-8 እና በ1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 ላይ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ብቸኛው መንገድ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን እንደሆነ ያሳያል፡፡ ‹‹ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፡፡›› 
በእርግጥ በጥንቷ ቤተክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያቶች ውስጥ አድሮ ሳለ ደዌዎችን እንደ መፈወስና አጋንንቶችን እንደ ማስወጣት ያሉ ነገሮችን አድርጓል፡፡ ሆኖም እነርሱ ዛሬ አንዳንድ ሰዎች ለማድረግ እንደሚያዘነብሉት መንፈሳዊ ስጦታዎቻቸውን ሲጠቀሙ ገንዘብን አልተቀበሉም ወይም ሁካታን አልፈጠሩም፡፡ ሐዋርያቶች ችሎታዎቻቸውን ያሳዩት ወንጌልን የማሰራጪያ መንገድ አድርገው ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ደቄን መፈወስና አጋንንቶችን ማስወጣት በጥንቷ ቤተክርስቲያን ዘመን ሁሉም የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች አልነበሩም፡፡ የስራው ጥቂት ክፍል ነበሩ፡፡ 
ስለዚህ በዛሬው ክርስትና ውስጥ ደዌን መፈወስ፣ አጋንንቶችን ማስወጣትና በልሳን መናገር የመሳሰሉ ድንቆች ሁሉ በእርግጥ የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች ናቸው ብሎ ማሰብ በጣም አደገኛ ነው፡፡ ዛሬ በክርስትና ውስጥ በአይኖቻችን የምናየው ለየት ያለው ክስተት ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ሐይል የተደረገ እንዳልሆነ ማመን ይገባናል፡፡ በፋንታው ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ የተቀበሉትን እውነተኛ የእግዚአብሄር አገልጋዮች በክፉ መናፍስቶች ከተያዙት አጭበርባሪ አገልጋዮች መለየት ይገባናል፡፡ አንድ ሰው ደዌን መፈወስ፣ አጋንንቶችን ማስወጣትና በልሳን መናገር ቢችልም በልቡ ውስጥ ሐጢያት ካለበትና በእውነተኛው ወንጌል የማያምን ከሆነ በእርግጠኝነት በአጋንንቶች የተያዘ ነው፡፡
ኢየሱስም በማቴዎስ 7፡20-23 እንዲህ አለ፡- ‹‹በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማይ የሚገባ አይደለም፡፡ በዚያን ቀን ብዙዎች፡- ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተዓምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል፡፡ የዚያን ጊዜም፡- ከቶ አላወቅኋችሁም እናንተ ዓመጸኞች ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ፡፡›› 
አንድ ሰው ተዓምራቶችን ስለሚያደርግ ይህንን የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ስራ አማካይነት ነው ብለን ማሰብ የለብንም፡፡ በፋንታው የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የሚሰብክ መሆኑን ወይም ምሉዕ የሆነውን የሐጢያቶች ይቅርታ በመቀበል ጻድቅ እንደሆነ በቅርበት መመርመር ይገባናል፡፡ መንፈስ ቅዱስ በልቡ ውስጥ ሐጢያት ባለበት ግለሰብ ውስጥ በጭራሽ አያድርም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከሐጢያት ጋር ማበር አይችልም፡፡ 
በጥንቷ ቤተክርስቲያን ዘመን የሐጢያት ይቅርታ መንፈስ ቅዱስ ለመውረዱ ማረጋገጫ ነበር፡፡ እርሱ ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ይቅርታን ላገኙት የእግዚአብሄር ስጦታ ነበር፡፡ 
ሆኒም ብዙ ሰዎች አሁንም በኢየሱስ ስም ደቄዎችን መፈወስ አጋንንትን ማስወጣትና በልሳን መናገር ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የመንፈስ ቅዱስ ስራ ናቸው ብለው ያስባሉ፡፡ ይህ የተሳሳተና አደገኛ አመኔታ ነው፡፡ እነርሱ በእርግጥም ድንቆችን እያደረጉ ለመሆናቸው በግልጽ መናገር መቻል ይገባናል፡፡ አንድ ግለሰብ በኢየሱስ ስም ብዙ ድንቆችን ቢያደርግም እንኳን እውነተኛውን የውሃና የመንፈስ ወንጌል የማያውቅ ወይም የማያምን ከሆነ ሐሰተኛ አስተማሪ መሆን አለበት፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች የብዙ ሰዎችን ነፍሶች ይገድሉና ዓለማዊ ስስታቸውን ለማርካት ገንዘብን ይጠይቃሉ፡፡ 
ስለዚህ በልቡ ውስጥ ሐጢያት ያለበት ግለሰብ ሥራ በእርግጥም የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ሳይሆን የአጋንንቶች ሥራ ነው፡፡ በጥንቷ ቤተክርስቲያን ዘመን የሰራው መንፈስ ቅዱስና አሁን እየሰራ ያለው መንፈስ ቅዱስ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሆኖም በትክክል መንፈስ ቅዱስን ለተቀበሉ ሰዎች በተገለጠው የመንፈስ ቅዱስ ሥራና በሐሰተኛ ነቢያቶች አማካይነት በተገለጡት አጋንንቶች በተገለጠው ሥራ መካከል ግልጽ ልዩነት አለ፡፡