Search

Kazania

ርዕስ 9፡ ሮሜ (በሮሜ መጽሐፍ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[Chapter 10-1] የምዕራፍ 10 መግቢያ፡፡

የራሳቸውን ጽድቅ ሲከተሉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የማያምኑ ሰዎች አሉን? መጽሐፍ ቅዱስ እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች በእግዚአብሄር ጽድቅ ባለማመናቸውና የራሳቸውን ጽድቅ በመከተላቸው እግዚአብሄርን እንደሚቃወሙ ይናገራል፡፡ እነዚህ ሰዎች ምን ያደርጋሉ?
 
እግዚአብሄር የአምላክ ጽድቅ የሆነውን ደህንነቱን ለሰው ሁሉ ለመስጠትና ኢየሱስ ክርስቶስን በእስራኤሎች በኩል ለመላክ ዕቅድ ነበረውን? በእርግጥም ነበረው! ኢየሱስ እያንዳንዱን ሐጢያተኛ ከሐጢያቶቹ ለማዳን እጅግ ከመፈለጉ የተነሳ ወደዚህ ምድር መጥቶ በመስቀል ላይ ተሰቀለ፡፡ ከሙታንም ተነሳ፡፡ በሌላ አነጋገር እርሱ የመጣው በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ለማዳን ነበር፡፡
 
እግዚአብሄር አብ እስራኤሎችን ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን ኢየሱስ ክርስቶስን ላከላቸው፡፡ እስራኤሎች ግን የእግዚአብሄር ጽድቅ የሆነውን ኢየሱስ አልተቀበሉትም፡፡ በፋንታው የራሳቸውን ጽድቅ በመከተል ተመሰጡ፡፡ አሁንም እንኳን የሕዝባቸው መሲህና የነፍሳቸው አዳኝ መሆኑን መቀበል አልቻሉም፡፡
 
ጳውሎስ እግዚአብሄር የላካቸው ሰዎች ስላሉ የተዋበው ወንጌል ሊደመጥ የሚችለው በእነርሱ በኩል እንደሆነ ተናግሮዋል፡፡ እግዚአብሄር ከላካቸው አገልጋዮቹ የሚደመጠው ወንጌል የእግዚአብሄርን ጽድቅ የያዘ ወንጌል ነው፡፡ ይህ ዕድል ሊያመልጣችሁ አይገባም፡፡ እግዚአብሄር የሐጢያቶቻችሁን ስርየትና ጽድቁን እንደሰጣችሁ ማመን የምትችሉት የእርሱን ጽድቅ በሚያውቁና በሚያምኑ የእግዚአብሄር ባሮች የተሰበከውን ይህንን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማመን ብቻ ነው፡፡
 
የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በዓለም ላይ ምርጡና እጅግ የተዋበ የምስራች ነው፡፡ ሐጢያተኞችን ከሐጢያቶቻቸው ያዳነው ይህ መልካምና ያማረ የምስራች ነው፡፡ ይህ ያማረ የምስራች የሰዎችን ነፍስ ፍሬያማ አድርጓል፡፡ ምክንያቱም በእግዚአብሄር የተሰጠው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ለነፍስ የሚሆን እውነተኛ ምግብ ነውና፡፡
 
እግዚአብሄር ባቀረበው ያማረ የደህንነት ወንጌል ውስጥ የእያንዳንዱን ሰው ሐጢያቶች የሚያስተሰርይ ሐይል አለ፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በሐጢያቶቻችን ስርየት ለአእምሮዋችን ሰላምን የሚሰጥ የበረከት ሐይል ነው፡፡
 
እስራኤሎች በእግዚአብሄር ላይ በማተኮራቸው የራሳቸውን ጽድቅ በመከተል ባዘኑ፡፡ ለሕጉ በመታዘዝ ጽድቃቸው እንደሚበዛ ስላሰቡ ኢየሱስን አዳኛቸው አድርገው አልተቀበሉትም፡፡ የሕግን ሥራዎች ለመከተል በጣም ጓጉተው ስለነበር የእግዚአብሄርን ጽድቅ መታገስ አልቻሉም፡፡ የራሳቸውን ጽድቅ በመከተል እየተፍጨረጨሩ በመሆናቸው አሁንም እንኳን ጌታን አዳኛቸው አድርገው አልተቀበሉትም፡፡
 
መጽሐፍ ቅዱስ እስራኤሎች የራሳቸውን ጽድቅ ለማቆም ሲሉ የእግዚአብሄርን ጽድቅ እንደተቃወሙ ይነግረናልን? ጳውሎስ በሕጉ ስለተመሰጡት እስራኤሎች ሲናገር ‹‹የሚያምኑ ሁሉ ይፀደቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና›› (ሮሜ 10፡4) በማል እምነታቸውን ይወቅሳል፡፡
 
የራሱን ጽድቅ የሚከተል በሕግ ላይ የተመሰረተ እምነት በእግዚአብሄር ፊት ትክክለኛ እምነት አይደለም፡፡ እስራኤሎች የብሉይ ኪዳንን ሕጎች በመከተል ብቻ ተጠምደው ሳሉ የእግዚአብሄር ጽድቅ የሆነው ኢየሱስ አዳኛቸው እንደሆነ አልተገነዘቡም፡፡ እንዲያውም በእርሱ ላይ ተነሱ፡፡ እስራኤሎች የእግዚአብሄር ቃል የተሰጣቸውና ቃሉንም የሚከተሉ ስለመሆናቸው እየተኩራሩ ሲቀኑ በመጨረሻ እንደ አንድ ሕዝብ የእግዚአብሄር ተቃዋሚዎች ሆኑ፡፡
 
 

የራሳችሁን ጽድቅ በማቆም ተጠምዳችኋልን?

 
እስራኤሎች ለሕጉ የነበራቸው ቅንዓት ችግሩ ጥማታቸው የራሳቸውን ጽድቅ ማቆማቸው ነበር፡፡ ከራሳቸው ጽድቅ የተነሳ በጌታችን የቆመው የእግዚአብሄር ጽድቅ ፈጽሞ ቸል ተብሎ ነበር፡፡
 
እስራኤሎች በሕጉ ላይ የነበራቸው እምነት ውጤቱ በእግዚአብሄር ጽድቅ ላይ መነሳት ነበር፡፡ ስለዚህ ይህ ውጤት ምንኛ የማይቀለበስ ጥፋት እያደረሰ እንደሆነ አሁንም አልተገነዘቡም፡፡ የሕጉን ሥራ መከተላቸው ምን ጠቀማቸው? የእግዚአብሄርን ቃል የመከተላቸው ጥማት የእግዚአብሄርን ጽድቅ ለማወቅና ለማመን እንቅፋት ሆነባቸው፡፡ ስለ ሕጉ ትክክለኛ መረዳት የሌላቸው ሰዎች ‹‹ቅንዓት›› በመጨረሻ የሚመራቸው በእግዚአብሄር ጽድቅ ላይ ወደ ማመጽ ብቻ እንደሚሆን ደግመን መረዳት ይገባናል፡፡
 
ኢየሱስ የሚያምኑትን ሁሉ ለማጽደቅ የሕግ ፍጻሜ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይነግረናል፡፡ ጌታችን የእስራኤሎችንና የአህዛቦችን ሐጢያቶች በሙሉ ለማንጻት በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በመውሰድ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ፈጽሞዋል፡፡ ስለዚህ ሕጉን ሳይሆን የእግዚአብሄርን ጽድቅ የያዘው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ለሐጢያተኞች ሁሉ በምድረ በዳ የሚገኝ ምንጭ ሆንዋል፡፡ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ደምስሶ እውነተኛ ቅባት የሰጠን የውሃውና የመንፈስ ወንጌል ነው፡፡ የዓለም ሐጢያተኞች በሙሉ በልባቸው ውስጥ እውነተኛ ቅባት ማግኘት የሚችሉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ካልሆነ በሌላ በምንድነው?
 
ጳውሎስ በዚህ የሮሜ መጽሐፍ ውስጥ በእግዚአብሄር ጽድቅ ሳያምኑ የራሱን ጽድቅ ማቆም የከፋ ሐጢያት እንደሆነ ነግሮናል፡፡ ለእኛ ለአሕዛቦች ያማረው ወንጌል ምን ዓይነት ወንጌል ነው? ጌታችን ኢየሱስ በጥምቀቱ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ እንደወሰደ የነገረን ወንጌል ነው፡፡
 
ይህ ወንጌል ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች መሸከሙን የሚመሰክርና በማቴዎስ 3፡13-17 ላይ የተመዘገበው ወንጌል ነው፡፡ ‹‹ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ ዮሐንስ ግን፡- እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር፡፡ ኢየሱስም መልሶ፡- አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጻም ይገባናልና አለው፡፡ ያን ጊዜ ፈቀደለት፡፡ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃ ወጣ፡፡ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ፡፡ የእግዚብሄርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፡፡ እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ፡- በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡›› ኢየሱስ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ የወሰደው እንዲህ ነው፡፡
 
ጳውሎስ ‹‹ወደ ሰማይ ማን ይወጣል? ይህ ክርስቶስን ከላይ ለማውረድ ነው›› ብሎ በመጠየቅ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑትን ሕግ አክራሪዎች ወቀሰ፡፡ በሌላ አነጋገር ‹‹ሕጉን በመከተል ብቻ ማን ከሐጢያቶቹ ሊድን ይችላል?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡ የጳውሎስ ጥያቄ አላማ ሕጉን መከተል ፈጽሞ ከሐጢያት የማያድን የመሆኑን ነጥብ ማብራራት ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር ራሳችንን ከሐጢያት ለማላቀቅ በራሳችን ማድረግ የምንችለው ምንም ነገር እንደሌለ እየነገረን ነው፡፡
 
ጳውሎስ ብዙውን ጊዜ በመልዕክቶቹ ስለ እግዚአብሄር ጽድቅ ተናግሮዋል፡፡ ጳውሎስ ለእውነተኛ እምነት የሰጠው ምላሽ በሮሜ 10፡10 ላይ ይገኛል፡፡ እንዲህ አለ፡- ‹‹ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፌም መስክሮ ይድናልና፡፡›› ጳውሎስ የሰበከው ወንጌል ይህ የእግዚአብሄር ጽድቅ የተገለጠበትን የጌታችንን ጥምቀትና የመስቀል ላይ ደሙን በማመን የእግዚአብሄርን ጽድቅ መቀበል እንደምንችል የሚነግረን ወንጌል ነው፡፡ ጌታ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እንደሰጠንና በዚህ ወንጌል ለሚያምኑትም የአእምሮ ሰላም እንደሰጣቸው ማመን ነው፡፡
               
 

እውነተኛ እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል በመስማት ነው፡፡

 
ጳውሎስ ስለ እውነተኛ እምነት ምን ይነግረናል? ሮሜ 10፡17 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው፤ መስማትም በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡›› በሌላ አነጋገር እወነተኛ እምነት የሚመጣው እግዚአብሄር የሚናገርባቸው የእርሱ ባሮች ቃሉን በሚሰብኩበት ጊዜ ወንጌሉን ስንሰማ ነው፡፡
   
የእውነተኛ እምነት ማረጋገጫችን የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል በማመን ነው፡፡ ስለዚህ እውነተኛ እምነት ያላቸው ሰዎች ለመሆን ቃሉን መስማትና ማመን አለብን፡፡ እውነተኛ እምነት ሊኖረን የሚችለው የእግዚአብሄርን ቃል በመስማት ብቻ ነው፡፡ እምነታችን የሚያድገውም በዚህ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር የእርሱን ጽድቅ የሚሰብኩተነ አገልጋዮቹን የላከው ለዚህ ነው፡፡
 
እግዚአብሄር ለሰው ዘር በሰጠው የውሃና የመንፈስ ወንጌል ስናምን የሐጢያቶቻችን ስርየት አግኝተን የልብ እረፍት አግኝተናል፡፡ ከሐጢያት መዳን የሚቻለው የአእምሮ ሰላም በምናገኝበት የእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ብቻ ነው፡፡
 
የጌታችን ጽድቅ ዕንባዎቻችንን ሁሉ እንደሚያብስና ከሕመሞቻችንና ከስቃዮቻችን ሁሉ እንደሚያድነን አልተገረንምን? በእርግጥ ተነግሮናል፡፡ እግዚአብሄር በሰጠው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ጽድቅ በማመን ስቃዮቻችን በሙሉ ይወገዳሉ፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በዓለም ላይ እጅግ ያማረ ዜናና የእግዚአብሄር ጽድቅ ፍጻሜ ነው፡፡
 
እግዚአብሄር ጽድቁን የፈጸመለትን ጌታችንን ለእስራኤሎች ላከው፡፡ እነርሱ ግን የራሳቸውን ጽድቅ በመከተላቸው ወደ እርሱ ለመመለስ አሻፈረን አሉ፡፡ ታዲያ እግዚአብሄር ምን ያድርግ? እግዚአብሄር እስራኤሎችን ለማስቀናት የጽድቁ ፍጻሜ የሆነውን ወንጌል ያምኑ ዘንድ ለአሕዛቦች ሰጣቸው፡፡ እግዚአብሄር አሕዛቦች የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እንዲያምኑ ዕድል ሰጥቶዋቸዋልን? ባልፈለጉት፣ ባልጠሩትና ከእስራኤሎች በሚያንስ መልኩ ባመለኩት ጊዜ እንኳን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ያምኑ ዘንድ ዕድልን መስጠቱ እርግጥ ነው፡፡
 
አሕዛቦች ጽድቁን በፈጸመው ያማረ የምስራች በማመን የእግዚአብሄር ልጆች መሆን የቻሉት ለዚህ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም የእግዚአብሄር ጽድቅ ከእስራኤል ውጪ የተወደሰውና የተከበረው ለዚህ መሆኑን የሚነግረንም ለዚህ ነው፡፡
   
የእግዚአብሄርን ጽድቅ የፈጸመውን የውሃና የመንፈስ ወንጌል ለሁላችንም ስለሰጠን ጌታን በተጨባጭ ያመሰገኑ ምን ያህል ሰዎች ናቸው? ጌታችን የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ባማረው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አስወግዶዋል፡፡ ሆኖም በዚህ እውነት የማያምኑ በጣም ብዙ ክርስቲያኖች አሉ፡፡ ታዲያ በእግዚአብሄር ፊት ልናስቀምጠው የምንችለው አንዳች ጽድቅ በውስጣችን አለን? የለንም! ታዲያ የማናምነው ለምንድነው? የእግዚአብሄርን ጽድቅ የፈጸመው ወንጌል ምን እንደሆነ ስለማናውቅ ነውን? ይህንን ወንጌል ማወቅ ግን ቀላል ነው!
 
እኛም እስራኤሎች እንዳደረጉት የራሳችንን ጽድቅ የተከተልን ሰዎች ነን፡፡ እግዚአብሄር ግን ያማረውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመስጠት ከሐጢያቶቻችን ሁሉ አድኖናል፡፡ ጌታ እንድናምንበት የእግዚአብሄር ጽድቅ የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ስለሰጠን እናመሰግነዋለን፡፡
 
 
‹‹ወደ ሰማይ ማን ይወጣል?›› አትበሉ፡፡
 
ቁጥር 6 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፡- በልብህ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፡፡ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፡፡›› ደህንነታችንና የእውነትን ወንጌል ማገልገላችን ተግባራዊ የሆነው በሥራችን ሳይሆን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ባለን እምነት ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ በሚፈጽም እምነታችን ባይሆን ኖሮ የራሳቸውን ጽድቅ እንደሚከተሉ ሕግ አጥባቂዎች እግዚአብሄርን የሚያስቸግሩ ሐጢያተኞች ሆነን በቀረን ነበር፡፡
 
ደህንነታችን የመጣው የእግዚአብሄርን ጽድቅ በማመን ስለሆነ በዚህ ጽድቅ በማመን በእምነት ለጌታችን መኖር እንችላለን፡፡ በሕይወት ለመቀጠል የሚያስችለንን ጉልበት ያገኘነው በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ነው፡፡ ይህንን ጽድቅ ያወቅነውም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ባለን እምነታችን ነው፡፡
 
ለሚድኑ ሰዎች በእግዚአብሄር ጽድቅ ከማመን ውጪ አንዳች ሌላ እውነት አለን? የለም፡፡ የክርስትና መሰረት በእምነት ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ የክርስትና እምነት የእግዚአብሄር ጽድቅ ነው ማለት ማጋነን አይደለም፡፡ የጸደቁ ሰዎች በዚህ ጽድቅ ላይ በላቸው እምነት መኖርና ወንጌልን መስበክ ይችላሉ፡፡ ታዲያ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ሰዎች ችግሮች ይገጥሙዋቸዋልን? ይገጥሙዋቸዋል፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሄር ጽድቅ ላይ ባላቸው እምነት እግዚአብሄር ችግሮቻቸውን እንደሚፈታ በማመንና በመተማመን ችግሮቻቸውን ሁሉ ማሸነፍ ይችላሉ፡፡ የዚህ ዓይነቱ አመኔታ የሚፈልቀው በእግዚብሄር ጽድቅ ከሚያምን እምነት ነው፡፡
 
የእግዚአብሄርን ጽድቅ የማያካትቱ ሌሎች እምነቶችስ? ሁሉም በሰው ምግባሮች ላይ የተመረኮዙ የተሳሳቱ እምነቶች ናቸውን? በእርግጥም ናቸው፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ ሳያምኑ በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች እምነት እውነተኛ እምነት አይደለም፡፡
 
እናንተና እኔ መጀመሪያ በእግዚአብሄር ጽድቅ ሳናምን ከሐጢያቶቻችን መዳን እንችል ነበር? በእርሱ ጽድቅ ሳናምን በእግዚአብሄር ላይ ባለን እምነታችን መኖር ይቻለናልን? ሁለቱም አይቻልም፡፡ ጻድቃን እግዚአብሄርን የሚያገለግሉበት ጉልበት የሚመጣው በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመናቸው በስጦታ መልክ ከተሰጣቸው የመንፈስ ቅዱስ ሐይል ነው፡፡ በዚህ ዓለም በራሳችሁ ብርታት ወይም ምድራዊ ሐብት ብቻ መኖር ትችላላችሁን? በእነዚህ ነገሮች በእርግጥ የአእምሮ ሰላም ማግኘት ትችላላችሁን?
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ወንጌልን በሰላም መስበክ እንችላለን፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች እምነት፣ ድፍረት፣ ጉልበትና ሰላም አላቸው፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ፍጻሜ የሆነውን የውሃውን የመንፈሱን ወንጌል የማይሰብኩ ሰዎች ሰላምም ሆነ ደፍረት የላቸውም፡፡ የጻድቃን አእምሮ ሰላም ያስፈልገዋልን? ያስፈልገዋል፡፡ እነርሱ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለማሰራጨት ብቻ ሳይሆን ሕይወታቸውንም በሙላት ለመኖር ሰላም ያስፈልጋቸዋል፡፡
 
አእምሮዋችሁ ሰላም አለው? ለራሳችሁ ብቻ የምትኖሩ ብትሆኑ ኖሮ በአእምሮዋችሁ ውስጥ ያለው ሰላም የሚያድግበት ምክንያት ባልኖረም ነበር፡፡ የሚያስፈልጋችሁ እንደ ሥጋ ለመኖር የሥጋን ፍላጎቶች ለማሟላት ብቻ ከሆነ ተጨማሪ ሰላም ወይም እምነት ለምን ያስፈልጋችኋል? ነገር ግን እግዚአብሄርን ማገልገል ካለባችሁ በአእምሮዋችሁ ውስጥ ያለው ሰላምም ማደግ ያስፈልገዋል፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ የፈጸመውን ወንጌል ለማገልገል እምነታችሁና ሰላማችሁ ማደግ አለበት፡፡
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ሰላማቸውን በመላው ዓለም የማሰራጨት ሐላፊነት አለባቸው፡፡ ይህ የግለሰብ ጉዳይ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ሁሉ የተሰጠውን የአእምሮ ሰላም የማሰራጨት ጉዳይ ስለሆነ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ወንጌል ለመላው ዓለም መስበክ ያስፈልገናል፡፡ ይህንን ሰላም ለሌሎች ለማሰራጨት ስንኖር የአእምሮ ሰላማችን ያድጋል፡፡ የሕይወታችንንም ግልጽና ክቡር ግብ እናገኘዋለን፡፡
 
በእግዚአብሄር የተሰጠውን እውነተኛ ሰላም ለማወቅ የምትፈልጉ ከሆነ የእርሱን ጽድቅ የፈጸመውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ማወቅና ማመን ያስፈልጋችኋል፡፡ እግዚአብሄር ለእናንተ ያዘጋጀውን የአእምሮ ሰላም ለራሳችሁ መለማመድ ያስፈልጋችኋል፡፡
 
እስከ አሁን ድረስ ጌታን በሚገባ አገልግላችኋል፡፡ ሌሎችም የእናንተን ሰላም ይጋሩ ዘንድ በእርሱ ፊት እስከምትጠሩ ድረስ እርሱን በሚገባ ማገልገላችሁን መቀጠል ያስፈልጋችኋል፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ ላይ ባላችሁ እምነት ሰላምን ስትሹ ደህንነትን ለማግኘት የእናንተን ዱካዎች የሚከተሉ ምዕመናን ለሌሎች ሰላም ይኖራሉ፡፡
 
በእምነታቸው ያልበሰሉ ሰዎች በእምነት ግዛተ ክልል ውስጥ ተማሪዎች ናቸው፡፡ ይህንን የመረዳት አቅማቸውም ውሱን ነው፡፡ ነገር ግን እኛ በእምነታችን ስንኖር የተወሰነ ጊዜ ቢወስድም ከኋላችን የሚከተሉን ሰዎች፣ የዳኑት ሰዎች ሕይወታቸውን እንዴት በሰላም እንደሚኖሩ ውለው አድረው ይረዱና የእምነት ዱካዎቻችንን ይከተላሉ፡፡
 
ምሪታችሁን ለሚከተሉ ሰዎች እንዴት በእምነት እንደሚኖሩ ማስተማር አስቸጋሪ ሆኖ እግኝታችሁታልን? እንደዚህ ያለ የማስተማር ሕይወት በአንድ ሌሊት የሚደረስበት አይደለም፡፡ በሰላም ለመኖር ወደሚያስፈልገው የእምነት ዓይነት እነርሱን መምራት ከመቻላችሁ በፊት በጣም ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄርን ሲያገለግሉ የነበሩት ቀደምት ምዕመናን ከፊት ካለነው ከእኛ በመማር ከእርሱ ዘንድ የአእምሮ ሰላማቸውን እንዳገኙ ሁሉ በጊዜው በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን የዳኑት ሰዎችም ውለው አድረው የእምነት ሰዎች በመሆን በሰላም መኖርን ይማራሉ፡፡
 
እናንተና እኔ ሁላችንም በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን መኖር አለብን፡፡ ጻድቃን በቃሉ ላይ ባላቸው እምነት መኖር አለባቸው፡፡ የአሁኑና የወደፊቱ ሕይወታችን በእምነት መወሰን አለበት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ይጠይቀናል፡- ‹‹ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?›› እኛ በእግዚአብሄር ጽድቅ ስለምናምን ወንጌልን ለዓለም መስበክ አለብን፡፡ ወንጌልን በምናሰራጭበት ጊዜ የሚገጥሙንን ተግዳሮቶች በሙሉ በእምነት መጋፈጥ እንችላለን፡፡ 
 
በእምነት ያልኖሩ ጻድቃን ሕይወት የአእምሮ ሰላም የለውም፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ ማመን ሰዎች የአእምሮ ሰላም እንዲያገኙ ይፈቅድላቸዋል፡፡ ለሁሉም ነገር በእግዚአብሄር ቃልና በጽድቁ ስናምን ሰላማችን ይመለሳል፡፡
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን በሰላማችሁና በእምነታችሁ ጸንታችሁ መቆም አለባችሁ፡፡ ጌታንም ማመስገን አለባችሁ፡፡ ምክንያቱም ጌታ በጽድቁ ደህንነትና ሰላም እንድትኖሩ ፈቅዶላችኋልና፡፡ ሕይወታችሁንና ሰላማችሁን በተቀበላችሁበት አምላክ አምናችሁ ወንጌልን በመስበክ ኑሩ፡፡
 
የእግዚአብሄር ጽድቅ ምንኛ ፍጹም እንደሆነ ከሮሜ መጽሐፍ መማር ችላችኋልን? የሮሜ መጽሐፍ ይህ የእግዚአብሄር ጽድቅ ምን እንደሆነ በዝርዝር ያብራራል፡፡ እኛ የምንናገርለት የእግዚአብሄር ጽድቅ ሰው ሰራሽ ጽድቅ ሳይሆን የእግዚአብሄር የራሱ ብቻ ጽድቅ ነው፡፡
 
የእግዚአብሄር ጽድቅ ፍጹምና እኛን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ለማዳንም ከበቂ በላይ ነው፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በመውሰድ ፍጹምነት ባለው መንገድ አስወግዶዋቸዋል፡፡ እኛ በኢየሱስ ክርስቶስ የምናምነው የእግዚአብሄር ጽድቅ ፍጹም በመሆኑ እውነታ የተነሳ ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ጽድቅ ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻችን ስላዳነን የእርሱን ጽድቅ በፈጸመው ወንጌል ማመናችን ፈጽሞ  አስፈላጊ ነው፡፡
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ሕይወታችንን በአድናቆት፣ በአመስጋኝነትና በአወዳሽነት መኖር እንችላለን፡፡ ሰዎች በእግዚአብሄር ቅድስና ውስጥ መኖር የሚችሉት በእርሱ ጽድቅ በማመን ብቻ ነው፡፡ በዚህ ጽድቅ በማመን አእምሮዋችን ስለሚነጻ እግዚአብሄርን ማመስገን እንችላለን፡፡ ሕይወታችንም ለእርሱ ክብር መኖር ይችላል፡፡
 
የእግዚአብሄር ጽድቅ ፍጹም ባይሆን ኖሮ ከሐጢያቶቻችን መዳን ባልቻልን ነበር፡፡ በኢየሱስ በማመናችን የአዳም ሐጢያታችን ይቅርታ ቢያገኝም ከዚያ በኋላ ራሳችን በየቀኑ የምንሰራው ሐጢያት በየቀኑ የንስሐ ጸሎቶች የሚያስፈልጉት ነበር፡፡
 
ነገር ግን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በተገለጠው የእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ከዳንን በኋላ ይህ የእግዚአብሄር ጽድቅ ምሉዕ እንደነበር መረዳት ችለናል፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ለዘላለም የሚታመንና ፍጹም የመሆኑን እውነታ ወሰን በሌለው ምስጋና ወደ መቀበል የመጣሁት ለዚህ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ በሕይወት ዘመናችን ልንሰራቸው ከምንችላቸው ሐጢያቶች በሙሉ ስላዳነን በእርሱ ጽድቅ በማመን ከሐጢያት መዳን እንችላለን፡፡
 
የእግዚአብሄርን ጽድቅ ከሰብዓዊ ርኩሰታችን ጋር የማያነጻጽሩ ሰዎች በእርሱ ጽድቅ ሊያምኑ አይችሉም፡፡ ምክንያቱም ይህ ጽድቅ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ አይገነዘቡምና፡፡ እጅግ ፍጹም የሆነ ሰው እንኳን ከእግዚአብሄር ጽድቅ ጋር ሲነጻጸር ኢምንት ነው፡፡ በእርሱ ጽድቅ የምናምነውና በእርሱ ቅድስና እንድንኖር የተፈቀደልን ለዚህ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር በእርሱ ጽድቅ በማመንና በመኖር እግዚአብሄርን የሚያከብሩ ሰዎች የሆንነው ለዚህ ነው፡፡
             
በልባችን ውስጥ ትክክለኛ የሆነ የእግዚአብሄር ጽድቅ መረዳት ሊኖረን ያስፈልጋል፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻችን እንዳዳነን መገንዘብ አለብን፡፡ በሕይወት ዘመናችን ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሐጢያቶች አልሰራንምን? ታዲያ እግዚአብሄር እኛን ከእንደዚህ ስፍር ቁጥር ከሌላቸው ሐጢያቶች ያዳነንን የጽድቅ ድርጊት ያከናወነው እንዴት ነበር? ይህንን ያከናወነው በሥጋችን አምሳል ወደዚህ ምድር መጥቶ በዮሐንስ በመጠመቅ ሐጢያቶቻችንን በመውሰድ በመስቀል ላይ በመሞትና ከሙታን በመነሳት ነው፡፡ በአጭሩ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሁሉ በመፈጸም ነው፡፡
 
ሰው ሁሉ ወጣቱና ሽማግሌው፣ ሐብታሙና ደሃው፣ ብርቱውና ደካማው ሐጢያቶችን ይሰራል፡፡ ታዲያ ከእነዚህ የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ያዳነን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር፡፡ እግዚአብሄር ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንዲወስድ ኢየሱስን መላኩና ሐጢያቶቻችንን ሙሉ በሙሉ ማስወገዱ የእግዚአብሄር ጽድቅ ነው፡፡
 
ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ያዳነን ትክክለኛው የእግዚአብሄር ጽድቅ ይህ ነው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ በአንድ ጊዜ ከዓለም ሐጢያቶች በሙሉ አድኖናል፡፡ የእርሱ ጽድቅ ፈጽሞ እንከን የለሽ አይደለምን? እስከ ዕድሜያችን ፍጻሜ ድረስ ብቻ ሳይሆን እስከ ዘላለም ድረስ የሚዘልቀውን እግዚአብሄር የሰጠንን ይህንን ፍቅር የእግዚአብሄር ጽድቅ ብለን እንጠራዋለን፡፡
 
አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስን ካጠመቀው በኋላ በማግስቱ ሲያገኘው ‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ›› ብሎ አወጀ፡፡ ዮሐንስ በመጀመሪያ ሊያተምቀው አሻፈረኝ ባለ ጊዜ ኢየሱስ ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና›› (ማቴዎስ 3፡15) ብሎ ነገረው፡፡ እነዚህ ምንባቦች ምን ማለት ናቸው? የኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደሙ የእግዚአብሄር ጽድቅ ናቸው የሚለውን እውነት ማለታቸው ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ጽድቅ ስንደክምና የእግዚአብሄር ክብር ሲጎድለን አይተወንም፡፡
 
እግዚአብሄር እኛን ላዳነንና በጽድቁ ውስጥ እንድንኖር ለፈቀደልን ለዚህ የተትረፈረፈ ፍቅር ከማመስገን በቀር ሌላ ማድረግ የምንችለው ነገር የለም፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ሰዎች በቀሪው የሕይወት ዘመናቸው ለእርሱ ጽድቅ ይኖራሉ፡፡ በሰዎች ወይም በዓለም ከመታመን ይልቅ በእግዚአብሄር መታመን አብልጦ ይሻለናል፡፡ ያማረ ሕይወት ይህንን ሙሉ በሙሉ ከሐጢያት የሚያድነውን ወንጌል የሚሰብክ ሕይወት ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ፈጽመን ማወቅና ማመን የሚገባን ለዚህ ነው፡፡
 
የሐጢያቶቻቸውን ስርየት የተቀበሉ ሰዎች ‹‹ኢየሱስ በዮሐንስ በመጠመቅ ሐጢያቶቼን ሁሉ ወስዶዋል! ለዓለም ሐጢያቶችም ሁሉ በእኔ ፋንታ ተኮንኖዋል!›› በማለት ይመሰክራሉ፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ ስናምን ለእነዚህ በረከቶች እናመሰግነዋለን፡፡
 
በድክመቶቻችሁ ምክንያት ስትሰናከሉ፣ በሥጋችሁ የተነሳ በሐጢያት ስትወድቁ ወይም በሐጢያቶቻችሁ ምክንያት ተስፋ ስትቆርጡና ስታዝኑ እናንተን ወዳዳነው የእግዚአብሄር ጽድቅ ተመልከቱ፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ጻድቃኖችስ አላደረገንምን? ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን ሙሉ በሙሉ አልወሰደምን? የእርሱ ማዳን ወደፊት የምንሰራቸውን ሐጢያቶች ጨምሮ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ አላዳነንምን?
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ የምናምነው ኢየሱስ ክርቶስ ሙሉ በሙሉ እንዳዳነን ስናምን ብቻ ነው፡፡ የምንጸድቀው በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ሰዎች የጽድቁ መሳሪያዎች መሆን ይችላሉ፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ፍጹምነት የተሟላ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውን ጽድቅ የሚከተሉ ሰዎች በእግዚአብሄር ለመገረም በራሳቸው ጥፋት ላይ የተቀመጡ ሞኞች ናቸው፡፡
  
 
‹‹በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሄር ይቀናሉ›› የሚለውን የጳውሎስ አነጋገር ትኩረት አድርጉበት፡፡ 
 
የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሳናውቅ እንዴት የእምነትን ሕይወት መኖር፣ መዳንና የእግዚአብሄር ሕዝብ መሆን እንችላለን? ሕግን የሚከተሉ ሰዎች ሐጢያቶቻቸው ወደ ጥፋታቸው እንደሚነዱዋቸው አውቀው የእግዚአብሄር ጽድቅ ሙሉ በሙሉ ስላዳናቸው አመስጋኞች ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡ ኢየሱስ አዳኛችን የሆነው፣ እኛም በእርሱ የምናምነውና የምናከበርው የእግዚአብሄርን ጽድቅ ስለምናውቅና ስለምናምን ነው፡፡ ሐጢያት አልባ የእርሱ ልጆች የምንሆነውና የታመነ ሕይወት የምንኖረው በእርሱ ጽድቅ ስናምን ብቻ ነው፡፡ በኢየሱስ እናምናለን፡፡ የታመነ ሕይወትንም እንኖራለን የሚሉ ነገር ግን የእግዚአብሄር ጽድቅ የማያውቁ ሰዎች ይረገማሉ፡፡
 
ጳውሎስ በሮሜ ውስጥ እስራኤሎች የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውን ጽድቅ ሊያቆሙ እንደፈለጉ መስክሮዋል፡፡ እንዲህ በማድረጋቸውም የእግዚአብሄርን ጽድቅ አልታዘዙም፡፡ እነርሱም ደግሞ በእግዚአብሄር ጽድቅ ማመን አለባቸው፡፡
 
እግዚአብሄር ከዓለም ሐጢያቶች እንዳዳነን ማመን አለብን፡፡ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በእነዚህ የዓለም ሐጢያቶች ውስጥ ተካተዋል፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ ፍጻሜም ሁሉም ተወግደዋል፡፡ በዚህ እውነት ታምናላችሁን?
        
 
‹‹የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና፡፡›› 
 
የእግዚአብሄር ጽድቅ የሕግ ፍጻሜ ነው፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱና በስቅለቱ በመውሰድ የሕጉን መጠይቆች በሙሉ መልሶዋልና፡፡
 
የሐጢያት ውጤት ሞት መሆኑ እርግጥ ነው፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄር ጽድቅ የሕግ ፍጻሜ እንደሆነ ተጽፎዋል፡፡ ለምን? ምክንያቱም እግዚአብሄር አንድ ልጁን ወደዚህ ምድር ልኮ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ይወስድ ዘንድ እንዲጠመቅ፣ በመስቀል ላይ እንዲሞትና ከሙታን እንዲነሳ በማድረግ ሙሉ በሙሉ አድኖናልና፡፡
 
የእግዚአብሄርን ጽድቅ በልባችሁ ማመንና የሕጉን ጽድቅ መከተል ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ የሐጢያቶችን ስርየት ያገኛችሁት በምግባሮቻችሁ ነውን? ደህንነታችሁን ያገኛችሁት በመልካም ምግባሮቻችሁ ነውን? በዚህ ዓለም ላይ ያሉ ሌሎች ሃይማኖቶች በሙሉ ሐጢያቶቻችሁን የምታስወግዱበት መንገድ መልካም ምግባሮችን በማድረግ እንደሆነ ያስተምራሉ፡፡ ለምሳሌ የቡድሂስት እምነት ስለ ሐጢያት ያለው ግንዛቤ ያለፈውን ሕይወት ሐጢያቶቻችሁን አሁን ባለው ሕይወታችሁ መልካም ምግባሮችን በማድረግ መዋጀት ይቻላል ብሎ የሚያስተምር ነው፡፡ ይህ ለእናንተ ስሜት ይሰጣችኋልን?
 
ሰው የሚወለደውና የሚሞተው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ፍርድ ይመጣል፡፡ ሰው በዚህ ምድር ላይ የሚወለደው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ እግዚአብሄር ስለሚመለስ ማንም ሰው በሌላ የሕይወት ዑደት ወደ ምድር ሊመለስ አይችልም፡፡ ሰዎች በዚህ ምድር ላይ ሳሉ በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን መዳን ያለባቸው ለዚህ ነው፡፡ ይህ የቡዲስት የካራማ ትምህርት እንዴት ያለ አይረቤ ነው?
 
ከሐጢያቶቻችን እንደተዋጀን ማመን በእግዚአብሄር ጽድቅ ማመን ነው፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ ማመን በራሳችን ምግባሮች ሳይሆን በእርሱ ጽድቅ ብቻ ማመን ነው፡፡ ታዲያ የእግዚአብሄር የእምነት ጽድቅ የሚናገረው እንዴት ነው? በሮሜ መጽሐፍ ውስጥ እንደተመዘገበው እንዲህ በማለት ይናገራል፡- ‹‹በልብህ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፡፡›› ምክንያቱም የእግዚአብሄር ጽድቅ የሚገኘው በሆነ ዓይነት ሥጋዊ ጉልበት ሳይሆን በልብ ማመን ነው፡፡
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን የዘላለምን ሕይወት የሚያገኙ የእግዚአብሄር ልጆችና ሐጢያት አልባ ሰዎች እንሆናለን፡፡ ምንም ያህል በጎ ምግባሮችን ብናደርግ ሐጢያቶቻችንን በራሳችን ማስወገድ ስለማንችል ጥረቶቻችን በእግዚአብሄር ፊት ተጨማሪ ሐጢያቶችን በመስራት ብቻ ይጠናቀቃሉ፡፡ እንዲህ ያለውን በራሳችን የማመን ነገር ትተን የእርሱን ጽድቅ ለመከተል በጻድቁ አምላክ ማመን የሚገባን ለዚህ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ‹‹የእግዚአብሄርን ጽድቅ ባናውቅም በኢየሱስ በማመን ብቻ መዳን አንችልምን? የጌታንም ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል ተብሎ አልተጻፈምን?›› ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ነገር ግን ደህንነት የእግዚአብሄርን ጽድቅ በማወቅና ሙሉ በሙሉ በማመን እንጂ የኢየሱስን ስም በመጥራት ብቻ አይመጣም፡፡
    
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምን ሁሉ አያፍርም፡፡ 
 
ቁጥር 11 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም፡፡›› የዚህ ምንባብ ፍቺ ምንድነው? በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም፡፡ ምክንያቱም በእግዚአብሄር ጽድቅ አምኖዋልና፡፡ ‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ›› የሚለው የሚያመላክተው በእርሱ ጽድቅ የሚያምነውን ምዕመን ነው፡፡
 
‹‹የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል›› የሚለውን ምንባብ በሚመለከትስ? ይህ ማለት የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የሚያውቁና የሚያምኑ ሰዎች እርሱን አዳኝ አምላክ አድርገው በማመን ኢየሱስን ይጠሩታል ማለት ነው፡፡ ደህንነታችንን በእግዚአብሄር ጽድቅ አማካይነት ስለተቀበልን ቤዛነታችን የተሰጠን በዚህ እውነት በማመናችን እንደሆነ እናምናለን፡፡
 
በሌላ አነጋገር ያለዚህ እምነት የጌታን ስም ደጋግመን በከንቱ ብንጠራውም ከሐጢያቶቻችን አንድንም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በሙላቱ በኢየሱስ ስላለው የእግዚአብሄር ጽድቅ ስለሚናገር የጌታን ስም መጥራት ብቻ ቤዛነታችንን አይሰጠንም፡፡ 
 
መጽሐፍ ቅዱስ ገና ከመጀመሪያው ስለ እግዚአብሄር ጽድቅ ይነግረናል፡፡ በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ እንደተጻፈው እግዚአብሄር የሕይወትን ዛፍና መልካምንና ክፉን የምስታውቀውን ዛፍ በኤድን ገነት ውስጥ በመትከል ለአዳምና ለሄዋን ከዚህች የእውቀት ዛፍ እንዳይበሉ ነገራቸው፡፡ እግዚአብሄር ያደረገው ነገር ቢኖር በቃሉ ላይ ያላቸውን እምነት ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር የዘላለምን ሕይወት ያገኙ ዘንድ ከሕይወት ዛፍ እንዲበሉ ነገራቸው፡፡
 
የእግዚአብሄር ቃል እንዲህ ይላል፡- ‹‹ጻድቅ በእምነት ይኖራል፡፡›› እኛም እንደዚሁ ደህንነታችንን ስንቀበል ለመዳን መጀመሪያ በእርሱ ካመንበት ጊዜ ጀምሮ በመጨረሻ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት እስከምንደርስ ድረስ በዕድሜ ዘመናችን ሁሉ በእግዚአብሄር ጽድቅ ላይ ባለን እምነት እንኖራለን፡፡
 
በዚህ ዓለም ላይ ብዙ ክርስቲያኖች ከሐጢያት መዳን የሚሰጠው በኢየሱስ በማመን ነው ይላሉ፡፡ በተጨባጭ ግን ከእነርሱ በጣም ብዙዎቹ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ባለማወቃቸው ከሐጢያቶቻቸው አልዳኑም፡፡ ሰዎች የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሳያውቁ በኢየሱስ ሲያምኑ ምን ይፈጠራል? እነዚህ ሰዎች በአምልኮዋቸውና በጸሎታቸው የተሰጡ ምዕመናን መሆናቸውን የሚያሳዩ ውጫዊ ጠቋሚዎች ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄርን ጽድቅ ስለማያውቁ የሃይማኖት ተለማማጆችና ያልዳኑ ሐጢያተኞች ሆነው ብቻ ይቀራሉ፡፡
 
በክርስትና ማህበር ውስጥ ያሉና እስራኤሎች የሆኑ ብዙዎች የእግዚአብሄርን ጽድቅ ስለማያውቁ የእርሱን ጽድቅ እየታዘዙ አይደሉም፡፡ በኢየሱስ እያመኑ በእግዚአብሄር ጽድቅ የማያምኑ ሰዎች ይህንን ጽድቅ ይረግጡታል፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ እስካላወቁ ድረስ በኢየሱስ የሚያምኑ ምዕመናን ይህንን ጽድቅ የሚቀበሉት በጎ ምግባሮችን በማድረግ፣ ብዙ የገንዘብ ስጦታ በመስጠት ወይም በሌሎች የራሳቸው ምግባሮች አይደለም፡፡
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ሰዎች ራሳቸውን በማናቸውም ሁኔታዎች ውስጥ ቢያገኙትም ይህንን ጽድቅ ያምኑታል፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር የሚያመሰግንና የሚያወድስ ሕይወትንም ይኖራሉ፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ የምናምን ሰዎች ጉድለቶቻችን አብዝተው በተገለጡ ቁጥር የእርሱ ጽድቅ በነፍሳችን ላይ ብሩህ ሆኖ ያበራል፡፡ እናንተም ደግሞ የዚህ ዓይነት ንቃት እንዲሆንላችሁ እጸልያለሁ፡፡
 
በሥጋችን ውስጥ የሆነ የተወሰነ ቅንነት ስላለ የእግዚአብሄርን ጽድቅ መቀበል እንችላለንን? አንችልም! ከእግዚአብሄር ጽድቅ ውጪ በውስጣችን ቅን የሆነ ምንም ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር በጽድቁ ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻችን ስላዳነን ይህንን ጽድቅ በማመን እናመሰግነዋለን፡፡ የእርሱ ጽድቅ ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻችን አድኖናል፡፡
      
በሕይወታችሁ ውስጥ ችግር ሲገጥማችሁ በምግባር ላይ በተመሰረተ እምነት ላይ አትውደቁ፡፡ ነገር ግን ሁኔታዎቻችሁ ምንም ይሁን ሁልጊዜም በእግዚአብሄር ጽድቅ እመኑ፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ለዘላለም ፍጹም ነው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ የሚኖር እያንዳንዱ ሰው የእግዚአብሄርን ጽድቅ ማወቅ አለበት፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመታዘዝም በዚህ ጽድቅ ማመን አለበት፡፡ በኢየሱስ እናምናለን የሚሉ ብዙ ሰዎች አሁንም የሚኖሩት በሕግ ጽድቅ ብቻ በመሆኑ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ስለማወቃቸው እርግጠኞች ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡
 
ጳውሎስ የእግዚአብሄር ወንጌል ጽደቁን ፈጽሞዋል በማለት ይደመድማል፡፡ ማንም ሰው እውነተኛውን የእግዚአብሄር ወንጌል ሳያወቅ ጽድቅ ምን እንደሆነ ማብራራት አይችልም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች የእግዚአብሄር ጽድቅ ትርጉም ምን እንደሆነ ያብራሩ ዘንድ ሲጠየቁ ‹‹ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሞተ፣ ከሙታን የተነሳና ከሐጢያቶቼ ያዳነኝ አዳኜ ነው›› ይሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በየቀኑ ለሚሰሩዋቸው ሐጢያቶች የንስሐ ጸሎትን ማቅረብ ፍጹማን ለመሆንም በሒደት መቀደስ እንዳለባቸውም ያክላሉ፡፡
 
የእግዚአብሄርን ጽድቅ ለማወቅ በመጀመሪያ ራሳችሁን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ራሳችሁንና የእግዚአብሄርን ጽድቅ ስታውቁ በእርሱ ጽድቅ ከማመን በቀር ምንም ምርጫ አይኖራችሁም፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሄር ጽድቅ ከእናንተ ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል የላቀ፣ ትልቅና የተለጠጠ እንደሆነ ትገነዘባላችሁና፡፡ የእርሱን ጽድቅ ካላወቃችሁ ግን የራሳችሁን ጽድቅ በመከተል ትጠመዳላችሁ፡፡ በራሳቸው ጽድቅ የተጠመዱ ሰዎች የእግዚአብሄርን ጽድቅ አይታዘዙም፡፡ ምክንያቱም ፍላጎታቸው የራሳቸውን ጽድቅ መከተል ብቻ ነውና፡፡
 
በእርሱ ከማመናችን በፊት የእግዚአብሄርን ጽድቅ ማወቅ አለብን፡፡ ለዚህም ጽድቅ አመስጋኞች መሆን ይገባናል፡፡ ይህንን የእግዚአብሄር ጽድቅ በማወቅ ኢየሱስ በጥምቀቱ በራሱ ላይ በመውሰድ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ እንደተሸከመና በመስቀል ላይ እንደሞተ ማመን እንችላለን፡፡ በራሳችን በጎ ምግባሮች መጽደቅ የምንችል ብንሆን ኖሮ በእግዚአብሄር ጽድቅ መዳን አያስፈልገንም ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ እንደማይቻል ስናውቅ እግዚአብሄር ስላዳነን የእርሱን ጽድቅ አብዝተን እናደንቃለን፡፡ ሕይወታችንንም ሰናይ ምግባሮችን በማድረግ አንኖርም፡፡
 
አስተሳሰቦቻችሁና ምግባሮቻችሁ ጥሩ ናቸውን? እግዚአብሄር ሙሉ በሙሉ በጽድቁ  ያዳነን ብዙ ጉድለቶች ስላሉብን ነው፡፡ ያዳነን የእግዚአብሄርን ጽድቅ ማመናችን ስለሆነ ይህንን ጽድቅ ለማያውቁት በዚህ ዓለም ላይ ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የእርሱን ጽድቅ ለመስበክ እንሻለን፡፡
 
ራስን የማያውቅ ሰው በሌሎች ላይ ስህተቶችን ይፈልጋል፡፡ እነርሱንም ያማል፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሄር ጽድቅ የማያምን ከሆነ ይህንን ጽድቅ በኩራት ያውጃል፡፡ በራሱም ጽድቅ አይመካም፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ የማያምኑ ሰዎች ግን የእርሱን ጽድቅ የማንጓጠጥ ሐጢያት ይሰራሉ፡፡ እግዚአብሄርም ሰለ ሐጢያቶቻቸው ይፈረድባቸዋል፡፡
 
እግዚአብሄር ልጁን ወደዚህ ምድር ልኮ ጽድቁን ሰጣችሁ፡፡ ወደ መጨረሻው ዘመን ስንቀርብ የማን የሕግ ጽድቅ የተሻለ ወይም የከፋ እንደሆነ እርስ በርሳችን መከራከር የለብንም፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ሰዎች ስለ ሥጋቸው ማሰብ አይገባቸውም፡፡ ነገር ግን በእርሱ ጽድቅ በማመን እግዚአብሄርን ማመስገን ይገባቸዋል፡፡
 
በጽድቁ ሙሉ በሙሉ ያዳነንን እግዚአብሄርን እናመስግነው፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ ስላስተሰረየ የራሳቸውን ጽድቅ በመከተል እግዚአብሄርን የሚቃወሙትን ሰዎች መምሰል የለባችሁም፡፡