Search

Perguntas Frequentes sobre a Fé Cristã

Assunto 4: Perguntas Frequentes de nossos Leitores.

4-8. በእርግጥ ሲዖል አለ?

መልሱ ‹‹አዎ›› ነው፡፡ 
አንዳንዶች እግዚአብሄር ሲዖልን ሊፈጥር አይችልም ብለው ክችች ይላሉ፡፡ እግዚአብሄር ፍቅር ነው፤ ሲዖል ከአፍቃሪ አምላከ እሳቤ ጋር አይስማማም በማለት ይከራከራሉ፡፡ እነርሱ ‹‹በዚህ የሐዋርያት እምነት ማብራሪያ ላይ ‹ሲዖል› የሚለው ቃል ‹የታችኛው ዓለም› የሙታን መኖሪያ ለዕብራውያኖች ‹ሼኦል›› ለግሪኮች ‹ሄደስ› ለላቲኖች ደግሞ ‹ኢንፌርኖ› ነው፡፡ በወቅቱ በነበሩት ጸሐፊዎች መሠረት ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ሙታንን ለመገናኘት የሄደው ወደዚያ ስፍራ ነው›› በማለት ቀስቃሽ በሆነ የቃላት አገላለጥ መራቀቃቸውን ይገልጡ ይሆናል፡፡
ሆኖም ጌታ ኢየሱስ በግልጽ እያንዳንዱ ሐጢያተኛ ሊፈረድበትና  በእርሱ/በእርስዋ ሐጢያት ምክንያትም ወደ ሲዖል እሳት ሊሄድ እንደሚገባ በግልጽ ተናግሮዋል፡፡ (ማቴዎስ 18፤9፤ ማርቆስ 9፡43)         
በእርግጥ እግዚአብሄር አብ በልጁ በኢየሱስ በኩል ያልተገደበ ፍቅሩን ሰጥቶናል፡፡ ሆኖም ይህ ፍቅር ዕውር ፍቅር ማለት ሳይሆን የእውነት ፍቅር ማለት ነው፡፡ (2ኛ ተሰሎንቄ 2፡10) እርሱ በደህንነት እውነቱ ማለትም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ወደደን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱና በስቅለቱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ደምስሶዋል፡፡ አሁን በዚህ እውነተኛ ወንጌል ውስጥ ሆኖ በኢየሱስ ለሚያምን ለማንኛውም ሰው የዘላለምን ሕይወት ሰጠ፡፡ ‹‹ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና፡፡ አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፤ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፤ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና፡፡ እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ልጅ እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ፡፡›› (ገላትያ 3፡27-29)
እግዚአብሄር ጻድቅ በመሆኑ እውነታ ላይ ትኩረት ማድረግ አለብህ፡፡ እርሱ በግልጽ ‹‹የሐጢአት ደመወዝ ሞት ነው›› በማለት አውጆዋል፡፡ (ሮሜ 6፡23) ይህ ‹‹ሞት›› ሁለተኛ ሞት፤ በእሳት ውስጥ ለዘላለም መሰቃየት መሆኑን በእርግጠኝነት ታውቃለህ፡፡ (ዮሐንስ ራዕይ 20፡14) ኢየሱስ በሉቃስ 16፡19-31 ላይ ከአካላዊ ሞት በኋላ ሁለት ዓይነት የዘላለም ሕይወቶች እንዳሉ ያስተምረናል፡፡ አንዱ የሰማይ ሲሆን ሌላው በሲዖል እሳት ለዘላለም የሚሰቃይ ሕይወት ነው፡፡ ዮሐንስ ራዕይ ከምዕራፍ 20 እስከ 22 ድረስ የቅዱሳኖችን የመጀመሪያ ትንሳኤ፣ የሺህውን ዓመት መንግስት፣ የመጨረሻውን ፍርድ ስለሚቀበሉበት ሁለተኛ የሐጢያተኞች ትንሳኤና ሁለቱን የሕዝቦች ቡድን ዘላለማዊ ዕጣ ፈንታዎች--ሰማይንና ሲዖልን በሚመለከት እያንዳንዱን ነገር በዝርዝር ያብራራሉ፡፡
       
ሰዎች ሁሉ በአንዱ ሰው በአዳም ምክንያት ሐጢያተኞች ሆነው ይወለዳሉ፡፡ ነገር ግን በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንደጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሄር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶዋል፡፡ ሆኖም የእግዚአብሄርን የእውነት ፍቅር በግትርነታቸውና ንስሐ በማይገቡት ልቦቻቸው ለሚንቁ አመስጋኝ ያልሆኑ ሰዎች ጻድቁ እግዚአብሄር የሲዖል እሳት የሆነውን የዘላለም ሞት ይበይንባቸዋል፡፡ ይህም ይገባቸዋል፡፡
  
ስለዚህ ይህንን ምንባብ ማስታወስ ይኖርብሃል፡- ‹‹ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ፡፡›› (ማቴዎስ 10፡28)