Search

Perguntas Frequentes sobre a Fé Cristã

Assunto 4: Perguntas Frequentes de nossos Leitores.

4-9. የዕብራውያን ምዕራፍ 6ን የመጀመሪያ ክፍል ልትተረጉምልኝ ትወዳለህን?

የዕብራውያን 6፡1-8 አተረጓጎሜ ይኸውልህ፡- 
‹‹ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪየ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፤ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐና በእግዚአብሄር እምነት፤ ስለ ጠምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው፡፡ እግዚአብሄርም ቢፈቅድ ይህን እናደርጋለን፡፡ አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን፣ ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን፣ ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን፣ መልካሙንም የእግዚአብሄር ቃልና ሊመጣ ያለውን የዓለም ሐይል የቀመሱትን በኋላም የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው፤ ለራሳቸው የእግዚአብሄርን ልጅ ይሰቅሉታልና ያዋርዱትማልና፡፡ ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት፤ ለሚያርሱአትም ደግሞ የምትጠቅምን አትክልት የምታበቅል ከእግዚአብሄር በረከትን ታገኛለችና፤ እሾህና ኩርንችትን ግን ብታወጣ የተጣለች ናት፤ ለመረገምም ትቀርባለች፤ መጨረሻዋም መቃጠል ነው፡፡›› 
  

‹ቁ. 1-2› 
እግዚአብሄር በዛሬዎቹ ክርስቲያኖችና እንደዚሁም በኢየሱስ ዘመን በነበሩት ዕብራውያን አማኞች ውስጥ በክርስቶስ የመጀመሪያ ትምህርት ላይ ፍጹም የሆነ እምነትን ሊመሰርት ፈለገ፡፡ 
ከእነርሱ አንዳንዶቹ አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸው፣ እውነተኛውን ወንጌል የቀመሱ፣ የሐጢያት ስርየትን የተቀበሉና ስለዚህም መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ ነበሩ፡፡ በኋላ ግን ከእውነተኛው እምነት ወደቁ፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመቃወም ጥርጣሬን ማስተናገዳቸውን ቀጠሉ፡፡    
በዚህም መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የክርስቶስ የመጀመሪያ ትምህርቶች (ከሞቱ ሥራዎች ንስሐ፣ በእግዚአብሄር እምነት፣ የጥምቀቶችና የእጆች መጫን፣ የሙታን ትንሳኤና የዘላለም ፍርድ ትምህርት መሠረት) በእያንዳንዱ አማኝ ልብ ውስጥ በጽናት መተከል ይገባቸዋል፡፡
እዚህ ላይ እነዚህ የመጀመሪያ ትምህርቶች ከጥንቷ ቤተክርስቲያን ጀምሮ የእውነተኛው ወንጌል ፍሬ ነገር የነበሩ በመሆናቸው እውነታ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባናል፡፡
ከእነርሱ መካከልም የጥምቀቶችና የእጆች መጫን ትምህርት ይገኛል፡፡ ይህ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የዚያ ዘመን ሐዋርያቶችና ደቀ መዛሙርቶች የሰበኩት ወንጌል ለመሆኑ አሳማኝ ማስረጃ ነው፡፡ 
በእውነተኛው ወንጌል ላይ አመኔታ ያላቸው ሰዎች በክርስቶስ የመጀመሪያ ትምህርቶች ላይ ምንም ጥርጥር የላቸውም፡፡ ይልቁንም በወንጌል ላይ ጸንተው ይቆማሉ፤ ወደ እምነት ሕይወት፤ ወደ ፍጹም ሕይወት ይገሰግሳሉ፡፡ የሰው ምግባሮች ፍጹም ሊሆኑ አይችሉም፤ ነገር ግን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ስናምን ያን ጊዜ በእምነት ፈጽሞ ሐጢያት አልባ እንሆናለን፡፡
እግዚአብሄር አብርሃምን ‹‹በፊቴ ተመላለስ፤ ፍጹምም ሁን›› (ዘፍጥረት 17፡1) በማለት የጠየቀው ለዚህ ነው፡፡ ይህ ማለት ፈጽሞ ሐጢያት አልባ እንድትሆኑ የሚያደርጋችሁ ፍጹም እምነት ይኑራችሁ ማለት ነው፡
‹ቁ. 4-6›
ነገር ግን ሰው በእርሱ ካመነ በኋላ እውነተኛውን ወንጌል የሚክድ ከሆነ ዳግመኛ የሚድንበት መንገድ የለም፡፡ ያ የእግዚአብሄር ፈቃድ ነው፡፡ የእርሱ ፍቅር በጣም ትልቅና ፍጹም ስለሆነ በባላንጣዎቹ ላይም ያለው ቁጣው እንደዚሁ ትልቅና ዐካኝ ነው፡፡
 
ስለዚህ መሃልይ ዘ ሰሎሞን 8፡6 እንዲህ ይላል፡- 
‹‹እንደ ማህተም በልብህ እንደ ማህተም በክንድህ አኑረኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና፤ ቅንዓትም እንደ ሲዖል የጨከነች ናትና፡፤ ፍንጣሪዋ አንደ እሳት ፍንጣሪ እንደ አግዚአብሄር ነበልባል ነው፡፡››  
ዕብራውያን 10፡26-27ም እንደዚሁ ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያ ይናገራል፡- ‹‹የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ሐጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ሐጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፡፡ የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ፡፡››     
አሁን በእውነት እውቀት ማለትም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ እምነት ሊኖርህ ይችላል፡፡ ታዲያ ‹‹ወዶ ሐጢያት ማድረግ›› ምን ማለት ነው? ሐጢያት በሁለት መደቦች ሊከፈል እንደሚችል ማወቅ አለብን፡፡ ‹‹ሞት የሚገባው ሐጢያት›› እና ‹‹ሞት የማይገባው ሐጢያት፡፡›› (1ኛ ዮሐንስ 5፡16)   
እኛ በየቀኑ ሐጢያት እንሠራለን፡፡ እነዚያ ሐጢያቶች ‹‹ሞት የማይገባው ሐጢያት›› ናቸው፡፡ ጌታም እነዚያን ሐጢያቶች በሙሉ ቀድሞውኑም ደምስሶዋቸዋል፡፡ ነገር ግን ‹‹ሞት የሚገባው ሐጢያት›› መንፈስ ቅዱስን የመሳደብ ሐጢያት ነው፡፡ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ሐጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም፡፡›› (ማቴዎስ 12፡31)
መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ እውነተኛ አዳኝ እንደሆነ ይመሰክራል፤ ዳግመኛ በተወለዱ ቅዱሳኖች አማካይነትም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ይመሰክራል፡፡ በአጭሩ ሰው መላውን ይዘቶቹን ከሰማ በኋላ እውነተኛውን ወንጌል የሚክድ ከሆነ ያን ጊዜ ይህ ሰው መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሐጢያት እየሰራ ነው፡፡ የሚያሳዝነው በወንጌል ምክንያት አንዳንድ ችግሮች በሚገጥሙዋቸው ጊዜ ወንጌልን የሚክዱ ሰዎች ያሉ መሆናቸው ነው፡፡
ሰው እውነት መሆኑን እያወቀ እውነተኛውን ወንጌል በውዴታ የሚክድ ከሆነ እግዚአብሄር የዚህን ሰው እንዲህ ያለ ሐጢያት ይቅር ሊለው ይችላልን? እግዚአብሄር እንዲህ ባለ ሐጢያት ላይ ዘላለማዊ ኩነኔን ያውጃል፡፡
ይህ መልስ መንፈሳዊ ጥማትህን እንደሚቆርጥልህ ተስፋ አደርጋለሁ፡፤ ነገር ግን ከሁሉም በላይ ጌታችን ኢየሱስ ከመጀመሪያው በሰጠን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል፤ በእውነተኛው ወንጌል ላይ ጸንተህ እንድትቆም እመኝልሃለሁ፡፡