Search

Вопрсы о Христианской Вере

Тема 1: Рождение свыше от воды и Духа

1-21. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መናፍቅ ማነው? 

መናፍቅ በኢየሱስ እያመነ በልቡ ውስጥ ሐጢያት ያለበት ሰው ነው፡፡ በቲቶ 3፡11 እንዲህ ይላል፡- ‹‹መለያየትን የሚያነሳ ሰው ጠማማ እንዲሆን በራሱም ላይ አውቆ ሐጢአትን እንዲያደርግ አውቀህ፡፡››   
ኢየሱስ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰዶዋል፡፡ መናፍቅ ግን የእግዚአብሄር ለጋስ ስጦታ በሆነው በዚህ የተባረከ የውሃ ወንጌል (የቤዛነት ጥምቀት በሆነው የኢየሱስ ጥምቀት) አያምንም፡፡ በፋንታው ፍጹም የሆነውን ደህንነት በመናቅ ራሱን ሐጢያተኛ አድርጎ ይኮንናል፡፡  
መጽሐፍ ቅዱስ እንደ እነዚህ አይነት ሰዎችን በኢየሱስ የሚያምኑ ነገር ግን ራሳቸውን እንደ ሐጢያተኛ የሚኮንኑ ‹መናፍቃን› ብሎ ይገልጣቸዋል፡፡ (ቲቶ 3፡11) እናንተ ራሳችሁ መናፍቅ እንደሆናችሁ ወይም እንዳልሆናችሁ ትገረሙ ይሆናል፡፡ በኢየሱስ እያመናችሁ ነገር ግን አሁንም ድረስ ራሳችሁን ሐጢያተኛ ብላችሁ የምትጠሩ ከሆናችሁ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መንፈሳዊ እውነት አላወቃችሁም፡፡ 
በኢየሱስ የምታምኑ ነገር ግን አሁንም ድረስ ራሳችሁን ተስፋ ቢስ እንደሆነ ሐጢያተኛ የምትቆጥሩ ከሆናችሁ መናፍቅ ናችሁ፡፡ ይህ ማለት እውነተኛው የውሃና የመንፈስ ወንጌል ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ ለመደምሰስና እናንተን የእርሱ ልጆች ለማድረግ በጣም ደካማ እንደሆነ ታስባላችሁ ማለት ነው፡፡ እናንተ ከእነዚያ ሰዎች አንዱ ከሆናችሁ ማለትም ይቅርታን ለማግኘት በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያቶቻችሁን የምትናዘዙና አሁንም ድረስ ሐጢያተኞች መሆናችሁን የምትቀበሉ መናፍቃን ከሆናችሁ እምነታችሁን እንደገና በሚገባ ማጤን አለባችሁ፡፡   
ኢየሱስ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ ወስዶ ሳለ እንዴት አሁንም ድረስ ሐጢያተኞች ልትሆኑ ትችላላችሁ? ዕዳችሁ ለእናንተ የተሰጠ ስጦታ ሆኖ ቀድሞውኑም በኢየሱስ ተከፍሎ ሳለ ዕዳችሁን ለመክፈል የምትፍጨረጨሩት ለምንድነው? ዕዳውን ራሳችሁ ለመክፈል ሙጭጭ የምትሉ ከሆነ መናፍቅ ናችሁ፡፡ ምክንያቱም እምነታችሁ እግዚአብሄር ከሰጠው እምነት የተለየ ነውና፡፡ በኢየሱስ የሚያምን ነገር ግን ዳግም ያልተወለደ ማንኛውም ክርስቲያን መናፍቅ ነው፡፡ እውነቱን ማወቅ አለባችሁ፡፡ እግዚአብሄር የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወስዶዋል፡፡ የእርሱን ደህንነት ቸል ካላችሁ መናፍቅ ናችሁ፡፡   
በሌላ አነጋገር መናፍቅ ራሱን ሐጢያተኛ ብሎ የሚጠራ ራሱን የኮነነ ሰው ነው፡፡ ቅዱስ እግዚአብሄር ሐጢያተኛን የእርሱ ልጅ አድርጎ ሊቀበለው እንደሚችል ታስባላችሁን? ቅዱስ በሆነው አምላክ እያመናችሁ ራሳችሁን ሐጢያተኛ ብላችሁ የምትጠሩ ከሆነ መናፍቅ ናችሁ፡፡ መናፍቅ ላለመሆን የኢየሱስን ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰውን ደሙን ጥቅል እውነት አድርጋችሁ ማመን ይኖርባችኋል፡፡  
እናንተ መዳን የምትችሉት በአንድ ጊዜ በሁለቱም ማለትም በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ ስታምኑ ብቻ ነው፡፡