Search

Вопрсы о Христианской Вере

Тема 3: Откровение

3-12. ‹‹ማንም ሊቆጥራቸው የማይችላቸው እጅግ ብዙ ሕዝብ›› (ዮሐንስ ራዕይ 7፡9) የተነጠቁትን ቅዱሳን ያመለክታሉን?   

 
አዎ ይህ ትክክል ነው፡፡ ዮሐንስ ራዕይ 7፡9 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ፣ ከወገንም፣ ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፡፡›› ‹‹ከሕዝብና ከነገድ፣ ከወገንም፣ ከቋንቋም ሁሉ…ነጭ ልብስም ለብሰው›› ከሚለው ሐረግ ከአሕዛቦች መካከል በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ባላቸው እምነት እጅግ ብዙ ሰዎች ከጸረ ክርስቶስ ጋር ተዋግተው እንደሚያሸንፉ፣ ሰማዕት እንደሚሆኑ፣ የመጀመሪያውን ትንሳኤ እንደሚያገኙና እንደሚነጠቁ ማየት እንችላለን፡፡ 
በእነዚህ የመጨረሻ ቀናቶች ጸረ ክርስቶስ በትዕቢት ቢወጠርም በዚያው ጊዜ እግዚአብሄር በሰጠው የውሃና የመንፈስ ወንጌል የሚያምኑ ብዙ ሰዎች እንደሚነሱ መረዳት እንችላለን፡፡ ስለዚህ በአሕዛቦች መካከል በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ከሐጢያት የዳኑና ለእምነታቸው ሲሉም ሰማዕትነት የሚቀበሉ ማንም ሊቆጥራቸው የማይችሉ እጅግ ብዙ ሕዝብ ይነሳሉ፡፡ 
ዮሐንስ ራዕይ 7፡14 እንዲህ ይላል፡- ‹‹አለኝም እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነፁ፡፡›› ታላቁ መከራ በዚህ ምድር ላይ ሲመጣ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን በሰበከችው የውሃና የመንፈስ ወንጌል ከልባቸው በማመን ድነዋል፡፡ ስለዚህ ሰማዕት ሆኑ፡፡ ምክንያቱም ለጸረ ክርስቶስ አልሰገዱም፡፡ ምልክቱንም በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው አልተቀበሉምና፡፡ ከዚህ የተነሳ ከቅዱሳን ትንሳኤና ንጥቀት ጋር ተቀላቅለዋል፡፡ በእግዚአብሄርና በበጉ ዙፋን ፊት ቆመው ‹‹በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው›› እያሉ የሚያመሰግኑት ለዚህ ነው፡፡ 
ስለዚህ እግዚአብሄር አይሁድ አምላክ ብቻ ሳይሆን የአሕዛቦችም አምላክ ነው፡፡ በመሆኑም በመጨረሻው ዘመን ታላቁ መከራ ሲመጣ ከአሕዛቦች፣ ከነገዶች፣ ከሕዝቦችና ከቋንቋዎች እጅግ ብዙ የሆኑ አሕዛቦች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አምነው የሐጢያት ስርየትን በመቀበል በሰማዕታት ፋይል ውስጥ መግባታቸውን ያረጋግጣል፡፡