Search

Вопрсы о Христианской Вере

Тема 4: Наиболее часто задаваемые вопросы читателей

4-5. የዳነ ሰው ለዘላለም የዳነ ነውን?

እንደምታውቀው ደህንነታችን የመጣው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ባለን እምነት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ ስናምን ዳግመኛ ልንወለድና ጻድቃን ልንሆን እንችላለን፡፡
እጅግ አስፈላጊው ነገር ‹‹ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና›› (ሮሜ 10፡10) ተብሎ እንደተጻፈ በልባችን እውነቱን ማመናችን ወይም አለማመናችን ነው፡፡ በእውነተኛው ወንጌል ላይ ያለንን እምነት ከልባችን በምንናዘዝበት ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ በልባችን ውስጥ ያድራል፡፡ ከዚያን ጊዜም ጀምሮ እርሱ ይጠብቀናል፡፡
እውነተኛውን ወንጌል እስካልካድህ ድረስ ደህንነትህን አታጣም፡፡ ነገር ግን ዳግመኛ ተወልዶ የነበረ ሰው ወንጌልን የሚክድ ከሆነ ‹‹ሞት የሚገባውን ሐጢያት›› (1ኛ ዮሐንስ 5፡16) ይፈጽማል፡፡ ዳግመኛ ለተወለዱ ቅዱሳን እውነተኛውን ወንጌል መካድ የማይቻል ይሆናል፤ ምክንያቱም በጣም ግልጽ ከመሆኑ የተነሳ ግራ አያጋባም፡፡
ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻው ዘመን እንዲህ ያለ የእምነት ክህደት እንደሚኖር ይናገራል፡፡ (2ኛ ተሰሎንቄ 2፡3) ማቴዎስ 13፡3-9 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በምሳሌም ብዙ ነገራቸው እንዲህም አላቸው፡- እነሆ ዘሪ ሊዘራ ወጣ፤ እርሱም ሲዘራ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ፤ ወፎችም መጥተው በሉት፡፡ ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀ፤ ጥልቅ መሬትም ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤ ጸሐይ በወጣ ጊዜ ግን ጠወለገ፤ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ፡፡ ሌላውም በእሾህ ላይ ወደቀ፤ እሾህም ወጣና አነቀው፡፡ ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀ፤ አንዱም መቶ፤ አንዱም ስድሳ፤ አንዱም ሠላሳ ፍሬ ሰጠ፡፡ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ፡፡›› 
መጀመሪያ ላይ የሰሙትና ያመኑበት ቢሆኑም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ያላቸውን እምነት ያጡ ሰዎች ውሎ አድሮ ደህንነታቸውን እንደሚያጡ ይህ ምንባብ ይነግረናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹እስከ መጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል፡፡›› (ማቴዎስ 24፡13) እውነተኛው ወንጌል በዓለም ላይ እጅግ ክቡር የሆነ ነገር መሆኑነ እስካወቅንና በወንጌል ላይ ያለንን እምነትም በማንኛውም መስዋዕትነት እስከ መጨረሻው ድረስ ተከላክለን እስከጠበቅን ድረስ ደህንነታችን አይሻርም፡፡ እባክህ ሕዝቅኤል 33፡12-16ን ተመልከት፡፡
ስለዚህ በእውነተኛው ወንጌል እምነት እስካለህ ድረስ ደህንነትህ ውጤታማ ነው፡፡ ጌታ እግዚአብሄር ‹‹ጻድቅ በእምነት ይኖራል›› (ሮሜ 1፡17፤ ዕንባቆም 2፡4) ያለው ለዚያ ነው፡፡ በመልሴ እንደረካህና በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ጸንተህ እንደምትቆም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡