Search

Ujumbe wa Video kutoka kwa Wafanyakazi Wenza

ልዩ ወንጌል // Other or different Gospel

  • Mesfin Berhanu Ubba
  • Ethiopia
  • 05/09/2024 3063

መጽሐፍ(ብሉይ.ኪ/መጽሐፍ ቅዱስ) እንደሚል ሰው ኃጢአትን ከሰራ ለኃጢአቱ ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ፦

1ኛ. ነውርና እንኬን የሌለበትን እንስሳ ያቀርባል።

2ኛ. ባቀረበው እንሰሳው ራስ ላይ ሁለቱን እጆቹን በመጫን ኃጢአቱን ተናዝዞ በእንስሳው ላይ ያሸክማል። 

3ኛ. እንስሳውን አርዶ ስርየትን ይፈጽማል።

 

ስለዚህ ይህን መጽሐፍ የሚለውን የማይሰብክ ማለትም እነዚህን ሦስቱን የኃጢአትን ሥርየት ስርዓትን የማይገልጥ ወንጌል ሁሉ ልዩ ወንጌል ነው።

 

ነገር ግን በገላትያ ቤተክርስቲያን ጳውሎስ ከሰበከው ወንጌል የተለየው ወንጌል የትኛው ወንጌል ነበር? 

ይህ በኢየሱስ ማመን + የግርዘት  ወንጌል ማለትም ሕግን የመጠበቅ ወንጌል ነበር። 

 

ይህኑን ጳውሎስ እንዲህ ብሎ ገለጸ፦

“እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ፦ ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም።

 …  

በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል።” ብሎ ገለጸ(ገላ 5፥2፡4)።

 

ስለዚህ በገላትያ መጽሐፍ ውስጥ ልዩ ወንጌል ተብሎ የተወገዘው ወንጌል የግርዘት ወንጌል ነው። 

 

ጳውሎስ ልዩ ወንጌል ብሎ የጠራው "የሥጋ ግርዘትን" ነው።  

 

ታዲያ በዘመኑ ክርስትና ውስጥ የሥጋ ግርዘትን የሚመስለው ልዩ ወንጌል ምንድነው?

1ኛ. ኢየሱስን ማመን + የንስሐ ጸሎት

2ኛ. ኢየሱስን ማመን + የራስ ቅድስና  

3ኛ. የኢየሱስ ውኃና ደም ወንጌል መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰብከው ወንጌል ሆኖ ሳለ የኢየሱስ ጥምቀት ወንጌል(ውኃው) ተወግዶ የኢየሱስ ሞት ወንጌል(ደሙ ወንጌል) ብቻ የሚሰበክበት ወንጌልና......................... የመሳሰሉት ሁሉ ልዩ ወንጌሎች ናቸው። 

 

የዘሌዋውያን መጽሐፍ እንደሚናገረው የኃጢአት ስርየት የሚፈጸመው፦ እንከንና ነውር የሌለበትን እንስሳን በማቅረብና ባቀረቡት እንሰሳው ራስ ላይ ሁለት እጆችን በመጫን ኃጢአትን በእንስሳው ላይ ካሸከሙ በኋላ በማረድ ነበር፤

 

 ይህ ደግሞ በአዲስ ኪዳን ለኢየሱስ ጥምቀት(በእንስሳቱ ራስ ላይ እጆችን መጫን)ና ለኢየሱስ ሞት(የእንስሳቱ መታረድ) ጥላ ነበር። (ዕብ 10፡1)

 

ስለዚህ አሁን በዘመኑ ክርስትና ውስጥ የእጆች መጫን ወንጌል(የኢየሱስ ጥምቀት ወንጌል) ተወግዶ የእንስሳቱ መታረድ(የኢየሱስ ስቅለት) ወንጌል ብቻ እየተሰበከ ነው። ይህ ግልጽ የሆነ ልዩ ወንጌል ነው።

 

 ሐዋርያቱ የሰበኩት እውነተኛው ወንጌል የኢየሱስን ጥምቀትና ሞቱን ወንጌል ነው።(ሮሜ6፥3-6) (1ዮሀ5፥6-13)

 

የኢየሱስን ጥምቀት የማያምኑና የማይሰብኩ ሰዎች ግማሽና ሐሰት ወንጌል እየሰበኩ ነው። አንድ ሰው የኢየሱስን ሞት ብቻ ስላመነና ስለሰበከ እውነተኛውን ሙሉውን ወንጌል አመነ ሰበከ ማለት አይደለም።

 ሙሉ ወንጌል #ውኃውን #ደሙንና #መንፈሱን የያዘው የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል ነው። 

 

ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት ይህን ሁሉ የሆነው አስቀድሞ በጥምቀቱ የዓለምን ኃጢአት በሥጋው ስለተሸከመ ነው።

 ሲጀመር ኢየሱስ እንጨት ላይ ተሰቅሎ እንዲሞት ምክንያት የሆነው ኃጢአትን መሸከሙ ነው። ምክንያቱም በእንጨት ላይ የሚሰቀል የተረገመ መሆኑን ቅዱሱ መጽሐፍ ይናገራል። (ገላ3፥13)

ኢየሱስ የተረገመ ሰው የሆነው የዓለምን ኃጢአት በሥጋው በመሸከሙ ነው። ኢየሱስ ኃጢአትን በሥጋው መሸከሙን ሳይሰብኩ ኢየሱስ ሞቷል የሚለውን ብቻ መስበክ በእግዚአብሔር ላይ እንደመዘበት ነው።

 

 ኢየሱስ ኃጢአትን በሥጋው የተሸከመው በእንጨት ላይ ከወጣ በኋላ አይደለም። ወይም ኢየሱስ እንዲሁ ዝምብሎ ኃጢአታችሁን ተሸከምኩ ብሎ አይደለም የተሸከመው።

 

 ኢየሱስ ኃጢአትን የተሸከመው #መጽሐፉ(የሕጉ መጽሐፍ) #እንደሚለው ነው።

መጽሐፉ ያለው ደግሞ ኃጢአት በእጆች መጫን ኃጢአት በሌለው ላይ ይተላለፋል፤ በዚያ ዘዴ ኃጢአት እንከንና ነውር በሌለው ላይ ያሸክማሉ ብሎ ተናገረ።

 

ኢየሱስ ኃጢአትን የተሸከመው በጥምቀቱ ማለትም በመጥምቁ በዮሐንስ እጆች መጫን አማካኝነት ነው።

 

 ኢየሱስ የሕግ ፍጻሜ(ሮሜ10፥4) ስለሆነ መጥምቁ ዮሐንስ የሊቀካህኑ የአሮን ዘር የሆነና የሕጉ ኪዳን ዘመን የመጨረሻው ሊቀካህን የሆነ አሮን እስራኤልን ወክሎ የመላውን እስራኤልን ኃጢአት በመሰዋዕቶች ላይ እንደሚያሸክም ልክ እንደ አሮን የዓለምን ሕዝብ ወክሎ የዓለምን ኃጢአት ወደ ኢየሱስ ያስተላለፈ ታላቁ ሰው ነው።

 

 ዮሐንስ ሊቀካን ስለመሆኑንና የዓለምን ኃጢአት በኢየሱስ ላይ የጫነ(ያሸከመ) ስለመሆኑ እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ክፍሎችን (ዘሌ 16፥21፣ ሚል4፥5-6፣ ዕብ10፥1፣ ማቴ 11፥11-13፣ ሉቃ 1፣5፣ 1ዜና24፥10፣  ማቴ 3፥15፣ ማር 1፥9፣ ዮሐ1፥29፣ ዕብ 6፥2) መመርመርና መረዳት ማወቅ ያስፈልጋል።

 

 አሁን በምድሪቱ ላይ የኢየሱስ ጥምቀት ወንጌል የሌለበት ሞቱ ብቻ እየተሰበከ ያለው ወንጌል ልዩ ሐሰተኛ ወንጌል እንጂ እውነተኛ ወንጌል አይደለም።

 

 ምክንያቱም የኢየሱስን ጥምቀት ሳያምኑ የኢየሱስን ሞት ብቻ ማመን ኃጢአትን በእንስሳው ላይ ሳያሸክሙ በከንቱ ማረድ ነውና።

 እጆች ሳይጫን የሚታረድ መሰዋእት ሐሰተኛ መሰዋዕት ነው። ምክንያቱም ኃጢአትን ሳይሸከም የሚታረድ ነውና።

 

 መጽሐፉ እንደሚል ኃጢአት የሚተላለፈው በእጆች መጫን ብቻ ነው።(ዘሌ16፥21) የእጆች መጫን አካሉ ደግሞ የኢየሱስ ጥምቀት ነው። (ዕብ6፥2፣ ማቴ3፥15)

 

ደኅንነትን የሚሰጥ እውነተኛው ወንጌል የኢየሱስ ጥምቀት፣ ሞቱና ትንሳኤው ወንጌል ነው።

 ይህ እውነተኛው ወንጌል የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል ይባላል።(ዮሐ3፥5)

 እዚህ ላይ ውኃው የኢየሱስን ጥምቀት የሚያመለክት ነው።(1ጴጥ3፥21)

 

 ከውኃውና ከመንፈሱ ወንጌል ውጪ የሆኑ ወንጌሎች ሁሉ ልዩ ወንጌሎች ናቸው።

 

የውኃውንና የመንፈሱን ወንጌል ያላመነና የማያምን ሁሉ በሐሰተኛው መገረዝ የሚያምን ሐሰተኛ ሰው ነው።

 

ስለዚህ አንድ ሰው ከኃጢአት ለመንጻት ኢየሱስ የዕድሜ ልኩን ኃጢአት በአንድ ጊዜ በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀ ጊዜ በሥጋው እንደተሸከመና በሞቱ እንደደመሰሰ ማመን አለበት።

 

ይህ እምነት የሌለው በጭራሽ ለዘላለሙን ከኃጢአት አይነጻም። አይድንም። አልዳነም።

 

ለአንዴና ለመጨረሻ ለዘላለም ድናችሁ፣ ጸድቃችሁና ኃጢአት አልባ ሆናችሁ የሚትቀሩበትን የውኃውንና የመንፈሱን ወንጌል እመኑ!!!

 

የውኃው፣ የደሙና የመንፈሱ ወንጌል ብቻ እውነተኛው ወንጌል ነው ከግማሹ ከሐሰተኛው ከደሙ ወንጌል ተፋቱ!!!

 

 ምክንያቱም እስካሁን ኃጢአት የለብኝም ማለት አልቻላችሁምና ሐሰተኛው መገረዝ የምንለው ለዚህ ነው።

ኢየሱስ ያዳነን በደሙ ብቻ አይደለም። በውኃውና በደሙ ነው። 

ይሄው መጽሐፍ ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦

 “በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው(በደሙ) ብቻ አይደለም። መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው። የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ።” ይላል(1ኛ ዮሐንስ 5፥6-10)።

 

ስለዚህ ይህን የውኃውንና የመንፈሱን ወንጌል በጥልቀት የሚያብራሩ ተከታታይ መጽሐፍቶች አሉን። በነፃ ይሰጣሉ። በሐርድም በሶፍት ኮፒም ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎችን ይጠቀሙ፦


-


ስልክ 0926467275/0910367615

#ነጻ_የክርስቲያን_መጽሐፍት #free_Christian_books!