Search

Maswali ya kila mara juu ya Imani ya Kikristo

Somo la 1: Kuzaliwa mara ya pili kwa maji na kwa Roho

1-3. በእግዚአብሄር የጸኑት ሕጎች ምንድናቸው? 

እግዚአብሄር ዕቅድ አውጭ፣ ብቸኛ፣ እውነተኛ አምላክና ሉአላዊ ሕላዌ ነው፡፡ ስለዚህ ለሚከተሉት አላማዎች ሲል በዓለም ላይ ሕግን አጸደቀ፡፡ 
① ሐጢያተኞችን ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን ሕጉንና ትዕዛዛቱን ሰጣቸው፡፡ ‹‹ሐጢአት በሕግ ይታወቃልና፡፡›› (ሮሜ 3፡2) 
② ሁለተኛው ሕግ ሐጢያተኞችን የሚያድን የእምነት ሕግ ነው፡፡ ይህም አዳኛችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ደህንነትን የሚሰጥ ‹የሕይወት መንፈስ ሕግ› ነው፡፡ (ሮሜ 8፡2) ኢየሱስ ይህንን ሕግ ለመፈጸም ወደዚህ ዓለም መጣ፤ ተጠመቀ፤ በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰ፡፡ ከዚያም ተነሳ፡፡ ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያተኞች ሁሉ ለማዳን የደህንነትን ሕግ መሰረተ፡፡  
እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ደህንነት ለሚያምኑ ሰዎች የእምነትን ሕግ አጸና፡፡ ለመዳንና የእግዚአብሄር ልጅ ለመሆን የሚፈልግ ማንኛውም ሰው እግዚአብሄር ባዘጋጀው የእምነት ሕግ ማመን ይኖርበታል፡፡ ወደ ደህንነት የሚያደርሰው ብቸኛው መንገድ ይህ ነው፡፡ በዚህም በዚህ ሕግ መሰረት በመንፈሳዊው የደህንነት እውነት የሚያምኑ ሰዎች ሰማይ እንዲገቡ ፈቅዶዋል፡፡