Search

Maswali ya kila mara juu ya Imani ya Kikristo

Somo la 1: Kuzaliwa mara ya pili kwa maji na kwa Roho

1-30. በመስቀል ላይ የተሰቀለው ሌባ ያገኘውን መዳን እንዴት ልታብራራው ትችላለህ?

በዚያ ዘመን አይሁዶች በሙሉ ትንቢት የተነገረለትን መሲህ ይጠብቁ ነበር። ስለዚህ እነርሱ ከማንኛውም ሌላ ሕዝብ ይልቅ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ስለሰጠው “ሕግና የመሥዋዕት ስርዓት” በሚገባ ያውቁ ነበር። እነርሱ መሲህ በእግዚአብሔር የማስተሰርያ ሕግ መሠረት እንደሚመጣና ከኃጢአቶቻቸው ሁሉ እንደሚያላቅቃቸው አምነው ነበር።
ነገር ግን በመጥምቁ ዮሐንስ የሆነው የኢየሱስ ጥምቀት ከእግዚአብሔር እንደነበርና የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ በኢየሱስ ላይ የሚያኖር እንደነበር (ማርቆስ 11፡27-33) አላመኑም። በፋንታው እርሱን ሕዝቡን እንደሚያስት ሰው አድርገው ስለተመለከቱት ሰቀሉት።
ሮማውያን በሮም ሕግ መሠረት ከመገረፍ ወይም ከመሰቀል ከለላ ስለነበራቸው (የሐዋርያት ሥራ 22፡25-29፣ 23፡27) በመስቀል ላይ የተሰቀሉት ወንበዴዎች አይሁዶች እንጂ ሮማውያኖች እንዳልነበሩ እናውቃለን። “ጌታ ሆይ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ” (ሉቃስ 23፡42) ከሚሉት ቃሎች የተነሣም ሌባው እግዚአብሔርን የፈራ አይሁድ እንደነበርም እናውቃለን። አይሁዳዊው ሌባ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ሕግና የመሥዋዕት ሥርዓት ቀድሞውኑም የሚያውቅ ነበር። ስለዚህ መሲሁ በእግዚአብሔር የማስተሰርያ ሕግ መሠረት እንደሚመጣ አምኖ ነበር።
ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ ሰዎች በኃጢአቶቻቸው ምክንያት ሲዖል ለመውረድ የታጩ ኃጢአተኞች እንደሆኑ መናዘዝ አለባቸው። ሌባው “ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው” (ሉቃስ 23፡41) በማለት ኃጢአቶቹን ተናዘዘ። ሌባው እግዚአብሔርን እንደሚፈራና ተስፋውም መንግሥተ ሰማይ መግባት እንደሆነ “ጌታ ሆይ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ” (ሉቃስ 23፡42) ከሚሉት ቃሎች ደግሞ እናያለን።
ሌባም እንዲህ አለ፦ “ይህ ግን ምንም ክፋት አላደረገም” (ሉቃስ 23፡41)። ሌባው ኢየሱስ ስላደረገው ነገር እንዴት አወቀ? ሌባው ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ እንደተጸነሰ፣ ከማርያም እንደተወለደ፣ የሰው ዘር ሁሉ ወኪል በሆነው በመጥምቁ ዮሐንስ እንደተጠመቀ፣ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ እንደወሰደና እንደተሰቀለ አምኗል። እርሱን ጨምሮ ለሕዝቡ ሁሉ ኢየሱስ ያደረገውን ያመነ አይሁድ ነበር።
በዮሐንስ ጥምቀት አማካይነት ኃጢአቶቻቸውን የተናዘዙ ሰዎች ኃጢአቶቻቸው ሁሉ በእርሱ ጥምቀት አማካይነት ወደ ኢየሱስ እንደሚተላለፍ ሲሰሙ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አወቁ። ነገር ግን የዮሐንስን የንስሐ ጥምቀት ያልተቀበሉ ሰዎች በኢየሱስ ጥምቀትም ስላላመኑ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ንቀዋል (ሉቃስ 7፡28-30)።
በተቃራኒው፣ የዳነው ሌባ ከሌሎች አይሁዶች በተለየ መልኩ ኢየሱስ ያደረገው ነገር ሁሉ ትክክልና ጻድቅ እንደነበር ተናዘዘ። እርሱ “በመካከላችን ስለ ተፈጸመው ነገር ብዙዎች” (ሉቃስ 1፡1) በሙሉ ከሰሙ አይሁዶች አንዱ ሊሆን ይችላል። በመጨረሻም በመስቀል ላይ ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት የእርሱን ኃጢአቶች በሙሉ እንደወሰደ ወደ ማመን ስለመጣ ኢየሱስ ጻድቅና ትንቢት የተነገረለት መሲህ እንደነበር መናገር ቻለ። በዚህም መዳነ። የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማመንም ተድኗል።

እግዚአብሔር ጻድቅ ስለሆነ በሕይወት መንፈስ ሕግ መሠረት በኢየሱስ ጥምቀትና መስቀል የሚያምኑትን ያጸድቃል።