Search

Maswali ya kila mara juu ya Imani ya Kikristo

Somo la 2: Roho Mtakatifu

2-3. ወላጆቼ ከመጋባታቸውም በፊት እንኳን ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖች እንደነበሩ ሙጭጭ አሉ፡፡ በተጨማሪም እኔም ከውልደቴ ጀምሮ ሐይማኖታዊ ሕይወትን መርቻለሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከተወለድሁበት ጊዜ ጀምሮ በውስጤ እንደነበር አሰብሁ፡፡ ሆኖም ስለ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት ስላልነበረኝ በጣም ግራ ተጋባሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በእርግጥ በአንድ ግለሰብ ላይ የሚመጣው ከውሃና ከመንፈስ ዳግም ሲወለድ ብቻ ነውን? 

አዎን ይህ እውነት ነው፡፡ ማንም ሰው መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ሐጢያቶቹ ይቅርታን ማግኘት ያስፈልጋቸዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ውሃ›› የደህንነት ምሳሌ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ (1ኛ ጴጥሮስ 3፡21) እዚህ ላይ ውሃው የሚያመላክተው ኢየሱስ ከዮሐንስ የተቀበለውን ጥምቀት ነው፡፡ (ማቴዎስ 3፡15) 
በመጀመሪያ እያንዳንዱ ሰው መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል የኢየሱስን ጥምቀት ትርጉም በማወቅ ከሐጢያቶቹ ሁሉ ይቅርታን ማግኘት ያስፈልገዋል፡፡ ገላትያ 3፡27 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና፡፡›› እዚህ ላይ ‹‹ከክርስቶስ ጋር የተጠመቃችሁ›› የሚጠቁመው የእኛን የውሃ ጥምቀት ሳይሆን ኢየሱስ በዮሐንስ የተጠመቀበትን ምክንያት በመረዳትና በማመን የሐጢያቶችን ይቅርታ መቀበል ማለት ነው፡፡ 
ሁሉም ሰው የሚወለደው በሐጢያተኛ አካል ነው፡፡ ሮሜ 5፡12 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ስለዚህ ምክንያት ሐጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በሐጢአትም ሞት፤ እንደዚሁም ሁሉ ሐጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፡፡›› በዚህ ዓለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ ሐጢያትን ከአዳምና ሔዋን በመውረስ ሐጢያተኞች ሆነው የተወለዱ ናቸው፡፡ 
ስለዚህ በመዝሙረ ዳዊት 51፡5 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹እነሆ በዓመጻ ተጸነስሁ፤ እናቴም በሐጢአት ወለደችኝ፡፡›› በኢሳይያስ 1፡4 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ሐጢአተኛ ወገንና በደል የተሞላበት ሕዝብ፤ የክፉዎች ዘር ርኩሰትንም የምታደርጉ ልጆች ሆይ ወዮላችሁ፡፡›› ሰዎች ከተወለዱበት ቀን ጀምሮ የሐጢያት ዘሮች አሉባቸው፡፡ በዚህ አለም ላይ ያሉ ሕዝቦች ሁሉ ሐጢያቶችን ከወላጆቻቸው ወርሰው በዚህ አለም ላይ ሐጢያተኞች ሆነው የተወለዱ ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር ሥጋችን በሕይወት ዘመናችን የሐጢያት ፍሬዎችን ያፈራል፡፡ 
የአንድ ሰው ሁለቱም ሥጋዊ ወላጆች ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖች ቢሆኑም ልጆቻቸውም ደግሞ መንፈስ ቅዱስን ይቀበላሉ ብሎ ማሰሰብ የማይመስልና ከባዕድ አምልኮ ጋር የተያያዘ እምነት የሆነው ለዚህ ነው፡፡ የዚህ አይነት እምነት ያለው ሰው መንፈስ ቅዱስን በራሱ አስተሳሰቦች አማካይነት ለመቀበል ይሞክራል፡፡ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስም በዚህ አይነቱ እምነት ሊመጣ አይችልም፡፡ 
ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ኢየሱስ በሰጠን የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ማመን ይገባዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ብቸኛው መንገድ ይህ ነው፤ ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፡፡ የእግዚአብሄር አንድያ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ በመጠመቅ የአለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፤ ከዚያም በመስቀል ላይ ተፈረደበት፡፡ በዚህም እውነትን የሚያምኑ አማኞችን በሙሉ ጻድቃን አደረጋቸው፡፡ እግዚአብሄር ለሰው ዘር ያለው ዕቅድና ፈቃድ ይህ ነው፡፡ እርሱ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ፈቃድ መሰረት በዚህ እምነት ላላቸው ሁሉ ሰጥቶዋል፡፡ 
በዚህ አለም ላይ የሚወለድ እያንዳንዱ ሰው የራሱን ሐጢያት ይዞ ይወለዳል፡፡ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስን እንደ ስጦታ መቀበል የሚችለው የሐጢያቶችን ስርየት ሲቀበልና በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ሲቀደስ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ይህንን በአእምሮው መያዝና መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ የሚመጣው ከውሃና ከመንፈስ ዳግም ሲወለድ ብቻ እንደሆነ ማመን ይገባዋል፡፡ 
እርሱ እኛ በምናደርገው ቅድመ ሁኔታ ወይም ጥረት ላይ በመመርኮዝ በእኛ ላይ አይመጣም፤ ነገር ግን የእርሱ መኖር ሙሉ በሙሉ ተስፋ በሰጠው አምላክ ታማኝነት ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር እርሱ በማናቸውም ሰብአዊ ወይም መንፈሳዊ ክንውን መሰረት አይመጣም፡፡ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ መቀበል የሚቻለው በእግዚአብሄር ፈቃድ መሰረት በእምነት ነው፡፡ 
የእርሱ ፈቃድ በዮሐንስ እንዲጠመቅና በመስቀል ላይ እንዲሞት በማድረግ መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ልቦች ውስጥ እንዲያድር ፈቅዶ የሰውን ዘር ሁሉ ከአለም ሐጢያቶች ለማዳን አንድያ ልጁ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን መላክ ነበር፡፡ የእርሱን ፈቃድ በመታዘዝና በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ድነው ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ መቀበል እንዲችሉ ነው፡፡ 
ስለዚህ አንድ ሰው ዳግም ከተወለዱ ወላጆች በመወለዱ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎዋል ብሎ ማመን ባዕድ አምልኮአዊና የማይመስል እምነት ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሄርን ፈቃድ በመተው በራሱ ፈቃድ መሰረት መንፈስ ቅዱስን ለቀበል ከመሞከር ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ አንድ ሰው ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ መቀበል የሚፈልግ ከሆነ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ከማመን በቀር ሌላ መንገድ የለም፡፡