Search

Maswali ya kila mara juu ya Imani ya Kikristo

Somo la 3: Ufunuo

3-14. እኔ ቅዱሳን ከታላቁ መከራ በፊት እንደሚነጠቁ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በታላቁ የመከራ ዘመን ወቅት ገናም በዚህ ምድር ላይ ስለሚቀሩ ቅዱሳን አዘውትሮ ይጠቅሳል፡፡ እነዚህ ከዓለም ጋር በመስማማታቸው ምክንያት እምነታቸው ለብ ብሎ የቀሩ ሰዎች ናቸውን? 

በመጀመሪያ ደረጃ አንተ የምታምነው የቅድመ መከራ ንጥቀት ጽንሰ አሳብ የሐሰት ትምህርት መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ መረዳት ይገባሃል፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች በተሳሳተ መንገድ የተረዱት ክፍል ይህ ነው፡፡ ቅዱሳን ከታላቁ መከራ በፊት ቀደም ብለው ስለተነጠቁ ጊዜው ሲደርስ በዚህ ምድር ላይ የሚቀሩት ሐጢያተኞች ብቻ ናቸው ብለው ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ችግሩ መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳን በታላቁ የመከራ ዘመን ወቅት ገናም በዚህ ምድር ላይ ቀርተው ሳሉ ስደትን በጽናት ድል ነስተው ሰማዕት እንደሚሆኑ አዘውትሮ መጥቀሱ ነው፡፡ 
ስለዚህ ብዙ ሰዎች እነዚህ ያልተነጠቁና በመከራው ዘመን የተሰደዱ ቅዱሳን ከዓለም ጋር የተስማሙና እምነታቸውም ለብ ብሎ የቀረ እንደሆኑ በተሳሳተ መንገድ ያስባሉ፡፡ 
ይህንን አመለካከት የያዙ ሰዎች እንዲህ ባለ ግራ መጋባት ውስጥ የሚኖሩት ትክክለኛውን የንጥቀት ዘመን ከእግዚአብሄር ቃል ስለማያውቁ ነው፡፡ ታዲያ ትክክለኛው የንጥቀት ጊዜ መቼ ነው? ጳውሎስ በ2ኛ ተሰሎንቄ 2፡1-4 በዚህ ጉዳይ የሚከተለውን ተናግሮዋል፡- ‹‹ነገር ግን ወንድሞች ሆይ ሰለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱ ስለ መሰብሰባችን በመንፈስ ወይም በቃል ወይም ከእኛ እንደሚመጣ በመልዕክት የጌታ ቀን ደርሶአል ብላችሁ ከአእምሮአችሁ ቶሎ እንዳትናወጡ እንዳትደነግጡም እንለምናችኋለን፡፡ ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመጽ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ አይደርስምና፡፡ እኔ እግዚአብሄር ነኝ ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሄር ቤተመቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ አምላክ ከተባለው ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነውና፡፡››          
እዚህ ላይ ‹‹የዓመጽ ሰው…የጥፋት ልጅ›› የሚያመለክተው በታላቁ መከራ ውስጥ ብቅ የሚለውን ጸረ ክርስቶስን ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ጸረ ክርስቶስ ከንጥቀት በፊት በዓለም ላይ ይገለጥና ራሱን እንደ አምላክ ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ እርሱ ለራሱ ምስል አሰርቶ ሰዎች ለእርሱ እንዲሰግዱና እንዲያገለግሉት ያስገድዳቸዋል፡፡ እርሱ ሰዎችን ሁሉ በራሱ ቁጥጥር ስር በማድረግ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው የአውሬውን ስም ወይም የቁጥር ምልክት እንዲቀበሉ ያደርጋል፡፡ ይህ ምልክት የሌለው ሰውም ምንም ነገር እንዳይገዛና እንዳይሸጥ ይከለክላል፡፡ 
ይህ አውሬ በዓለም ላይ ሲገለጥ የዚህ ዓለም ሕዝብ የስሙን ምልክት ወይም የስሙን ቁጥር እንዲቀበል ይገደዳል፡፡ ስለዚህ ስሙ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ያልተጻፈ ማንም ሰው መጨረሻው ምልክቱን መቀበልና ለአውሬው መስገድ ነው፡፡ 
ሆኖም የእግዚአብሄር ሕዝብ የሆኑት ቅዱሳን በልባቸው ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ስላለ ከእውነተኛ ጌታ አምላካቸው ውጭ ማንኛውንም ፍጡር አምላክ አድርገው አይሰግዱለትም፡፡ በልባቸው ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ የሰይጣንንና የጸረ ክርስቶስን ማስገደድ እንዲቋቋሙና በሰማዕትነታቸውም እምነታቸውን እንዲጠብቁ ጉልበትን ይሰጣቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ጠላቶቻቸውን የሚቋቋሙበትን ቃሎችም ይሰጣቸዋል፡፡ 
ዮሐንስ ራዕይ 17፡12-13 እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፡፡ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ፡፡ እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፤ ሐይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ፡፡›› ጸረ ክርስቶስ ቅዱሳንን ለማሳደድ ሥልጣንን ይቀበልና በዓለም ሕዝቦች ላይ በጣም ለአጭር ጊዜ ይነግሳል፡፡ ስለዚህ ጸረ ክርስቶስ ምልክቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ የሚያቀርበው ጥያቄ የቅዱሳኖችን ሰማዕትነት ተከትሎ ወዲያውኑ የሚመጣ ነው፡፡ 
በሌላ በኩል ዮሐንስ ራዕይ 11፡11-12 እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹ከሦስቱ ቀን ተኩል በኋላ ከእግዚአብሄር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው፡፡ በእግሮቻቸውም ቆሙ፡፡ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው፡፡ በሰማይም፡- ወደዚህ ውጡ የሚላቸውን ታላቅ ድምጽ ሰሙ፡፡ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ በደመና ወጡ፡፡›› ሁለቱ ሰማዕት የሆኑ ምስክሮች በሦስት ቀን ተኩል ውስጥ ተነስተው እንደሚነጠቁ ከሚናገረው ከዚህ እውነት በሰማዕትነታችንና በንጥቀት መካከል ያለው ክፍት ጊዜ ረጅም ጊዜ እንዳልሆነ ማየት እንችላለን፡፡ እነዚህ ሁለቱ ምስክሮች ከትንሳኤያቸው በኋላ ወዲያውኑ ይነጠቃሉ፡፡ ጌታ ሲመጣ ሰማዕት የሆኑት ቅዱሳንና የአውሬውን ምልክት ያልተቀበሉ በሕይወት የተረፉ ቅዱሳን ትንሳኤን አግኝተው በአየር ላይ ይነጠቁና ጌታን በአየር ላይ ይቀበሉታል፡፡ 
ስለዚህ የጸረ ክርስቶስ መገለጥ፣ የቅዱሳኖች ሰማዕትነትና ትንሳኤ እንደዚሁም ንጥቀታቸው ሁሉም እርስ በርሳቸው የተሰናሰሉ ናቸው፡፡ ጳውሎስና ዮሐንስ የቅዱሳን ንጥቀት የሚሆንበትን ጊዜ በስፋት አብራርተዋል፡፡ ቅዱሳኖች በሙሉ በታላቁ መከራ የመጀመሪያ ሦስት ዓመታት ተኩል ውስጥ ያልፋሉ፡፡ በሌላ አነጋገር የሰባቱ መለከቶች መቅሰፍቶች እስከሚጠናቀቁ ድረስ ሁሉም በዚህ ምድር ላይ ይቆያሉ፡፡ 
ጸረ ክርስቶስ ሲገለጥ ቅዱሳን ወደ ሁለተኛው የታላቁ መከራ ሦስት ዓመት ተኩል ክፍለ ጊዜ ውስጥ ይገባሉ፡፡ የአውሬውን ምልክት ለመቀበል እምቢ በማለታቸውም ሰማዕት እስኪሆኑ ድረስ በዚህ ምድር ላይ ይቆያሉ፡፡ ይህንን በመረዳት ሁላችንም አሁን በዚህ ጊዜ ከእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን የእምነት ክብካቤን መቀበል አለብን፡፡