Search

SÁCH IN,
SÁCH ĐIỆN TỬ VÀ SÁCH NÓI MIỄN PHÍ

Sáng Thế ký

Amharic 54

የሰውን ዘር ከጥፋት የሚያድን የወንጌል ምስክር ሁኑ

Rev. Paul C. Jong | ISBN 9788928260454 | Trang 306

Tải xuống sách điện tử và sách nói MIỄN PHÍ

Chọn định dạng tệp ưa thích và tải xuống an toàn vào điện thoại di động, máy tính hoặc máy tính bảng để đọc và nghe các bộ sưu tập bài giảng mọi lúc mọi nơi. Tất cả sách điện tử và sách nói đều hoàn toàn miễn phí.

Bạn có thể nghe sách nói qua trình phát bên dưới. 🔻
Sở hữu sách in
Mua sách in trên Amazon
የማውጫ ሰሌዳ
 
መቅድም
1. የሰውን ዘር ከጥፋት ማዳን የሚችሉ የወንጌል ሰባኪዎች ሁኑ (ዘፍጥረት 6፡5-22) 
2. አሁንም እንኳን ከሐጢያቶቻችሁ መዳን አለባችሁ (ዘፍጥረት 6፡1-4) 
3. በእነዚህ የመጨረሻ ቀኖች ለደህንነታችሁ ተዘጋጁ (ዘፍጥረት 6፡5-12) 
4. በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ደህንነት ላይ ደርሰናል (ዘፍጥረት 6፡5-12) 
5. እምነታችሁን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ በማኖር ልባችሁን ጠብቁ (ዘፍጥት 6፡13-14)
6. ኢየሱስ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ የመደምሰሱን እውነታ ታውቃላችሁን? (ዘፍጥረት 6፡14)
7. የእግዚአብሄር ሠራተኞች (ዘፍጥረት 7፡1-24) 
8. እየቀረበ ላለው የዓለም ፍጻሜ መዘጋጀት አለባችሁ (ዘፍጥረት 7፡1-24) 
9. ወደ ደህንነት የሚወስደን እምነት (ዘፍጥረት 7፡1-13) 
10. ዓለምን በእግዚአብሄር ዓይኖች እዩት (ዘፍጥረት 7፡1-12) 
11. ወደ መርከቡ ለመግባት ያለ ማመንታት የሐጢያቶችን ስርየት መቀበል አለባችሁ (ዘፍጥረት 7፡1-5) 
12. ወደ መርከቡ ውስጥ መግባት አለባችሁ (ዘፍጥረት 7፡1-5) 
13. እግዚአብሄር ለእኛ ያለው ዕቅድና ልብ (ዘፍጥረት 8፡20-21) 
14. በእምነት ሕይወታችን ውስጥ ስምንት ወቅቶች አሉ (ዘፍጥረት 8፡22) 
 
በአንድ ወቅት በብዙዎች ትልቅ ክብር የተሰጠው አንድ መጋቢ ነበር፡፡ ይህ መጋቢ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢየሱስ የመስቀል ላይ ደም ባመነ ጊዜ ባለፉት ሐጢያቶቹ ለጎዳው ለእያንዳንዱ ሰው ካሳ በመስጠት የታወቀ ነበር፡፡ ጠለቅ ባለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕውቀቱና የመፈወስ ሐይሉም እንደዚሁ የታወቀ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደ አለመታደል ሆኖ ይህ መጋቢ መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረለትን የውሃውንና የመንፈሱን እውነተኛ ወንጌል አላወቀም፡፡ በዚህም እርሱ በእግዚአብሄር ዓይኖች ከንቱ ነው፡፡ 
ታዲያ በዛሬዎቹ ክርስቲያኖች መካከል ይህ የተምታታ እምነት ያላቸው እነማን ናቸው? እነርሱ የጌታ ደቀ መዛሙርት ከሰበኩት የውሃና የመንፈስ ወንጌል ይልቅ በመስቀሉ ደም ብቻ የሚያምኑ ሰዎች ናቸው፡፡ በእነዚህ ተቋማዊ ክርስቲያኖች የተሰበከው ወንጌል የሚናገረው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስላፈሰሰው ደም ነው፡፡ ይህ ሐሰተኛ ወንጌል በክርስትና ላይ ትልቅ ጉዳት በማምጣት በርካታ ምዕመናኖችን የሥነ ምግባርና የራስ ጽድቅ ተገዥዎች በማድረግና ግብዛዊ የሐይማኖት ተለማማጆች ወደ መሆን ዝቅ አድርጎ ለውጦዋቸዋል፡፡ 
ዛሬም እንኳን ከእነዚህ ክርስቲያኖች ተብዬዎች ብዙዎች አሉ፡፡ ስለዚህ የዛሬው ክርስትና በትልቅ ግራ መጋባት ተጋርዶዋል፡፡ ጌታ በዚህ ዘመንና ጊዜ እንድንይዘው የሚፈልገው ቃል ይህንን የውሃና የመንፈስ ወንጌል ነው፡፡ እውነተኛውን እምነት የሚይዙት ይህንን የውሃና የመንፈስ ወንጌል የሚያምኑና የሚሰብኩ ብቻ ናቸው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ እነዚህ ክርስቲያኖች ሐጢያት አልባ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን የሌሎችን ሰዎች ሐጢያቶች የመደምሰስንም ሥራ መሥራት የሚችሉ መሆናቸው ነው፡፡
Thêm
Sách In Miễn phí
Thêm sách in vào giỏ
The New Life Mission

Tham gia khảo sát của chúng tôi

Bạn biết đến chúng tôi qua đâu?