Search

Câu hỏi thường gặp về Đức tin Cơ đốc

Chủ đề 1: Tái sanh bởi Nước và Thánh Linh

1-15. የሐጢያት ስርየት የተሰጠው በአንዴ ነው ወይስ ቀስ በቀስ? 

ይህ በአንድ ጊዜ የተሰጠ ነው፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ አንድ ጊዜ በመጠመቅና ፍርድንም አንድ ጊዜ በመውሰድ ሐጢያቶቻችንን ወስዶዋልና፡፡ በማቴዎስ 3፡15 ላይ እንደተመዘገበው እርሱ ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና›› ብሎዋል፡፡ 
በዮሐንስ 1፡29 ላይ አጥማቂው ዮሐንስ እንዲህ አለ፡- ‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ፡፡›› እንዲሁም በዮሐንስ 19፡30 ላይ ኢየሱስ ‹‹ተፈጸመ!›› አለ፡፡ 
ዕብራውያን 10፡9-18 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ቀጥሎ፡- እነሆ አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ ብሎአል፡፡ ሁለተኛውን ሊያቆም የፊተኛውን ይሽራል፡፡ በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ በማቅረብ አንድ ጊዜ ተቀድሰናል፡፡ ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ሐጢአትን ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መስዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፡፡ እርሱ ግን ስለ ሐጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘለዓለም አቅርቦ በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደፊት ይጠብቃል፡፡ አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና፡፡ መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፡፡ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ፤ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ ብሎ ከተናገረ በኋላ ሐጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል፡፡ የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ ከእንግዲህ ወዲያ ስለ ሐጢአት ማቅረብ የለም፡፡›› የኢየሱስ ጥምቀትና ደም የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለዘላለም ደምስሶዋል፡፡