HỌC KINH THÁNH
Câu hỏi thường gặp về Đức tin Cơ đốc
2-8. የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት መቀበል ማለት ምን ማለት ነው?
2-10. ሐኪሙ የጨጓራ ካንሰር እንዳለብኝ ከነገረኝ በኋላ ብዙ የሐዘን ቀኖችን አሳለፍሁ፡፡ አንድ ቀን አንድ ክርስቲያን የሆነ ጓደኛዬ ጎበኘኝና በእርሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚደረገውን የመነቃቃት ስብሰባ የሚካፈል ማንኛውም ሰው ከማንኛውም አይነት በሽታ እንደሚፈወስ ነገረኝ፡፡ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሄር መኖር ለማላምነው ለእኔ በሽታ በእግዚአብሄር ሐይል የመፈወሱ ነገር ለማመን የሚከብድ ነበር፡፡ በስብሰባው የመጨረሻው ቀን የእጆችን መጫን ለመቀበል ሁሉም ሰው ወደ አገልጋዩ ቀረበ፡፡ እጆቹን በእኔ ላይ በጫነብኝ ጊዜ አንዳንድ የማይስተዋሉ ቃሎችን እንድደጋግም ነገረኝና በኢየሱስ ክርስቶስ የፈውስ ሐይል አምን እንደሆነ ጠየቀኝ፡፡ በልቤ በትክክል ባላምንም ደነገጥሁና አዎ ብዬ መለስሁ፡፡ በዚያው ቅጽበት ልክ እንደ ኤሌክትሪክ ያለ ሙቀት በውስጥ ሲፈስስ ተሰማኝ፡፡ መላው ሰውነቴ ሲንቀጠቀጥ ይሰማኛል፡፡ ካንሰሬም እንደተፈወሰ ታወቀኝ፡፡ እዚያው እያለሁ በጌታ ለማመን ወሰንሁ፤ ከዚያ በኋላ ታላቅ ሐሴትና ሰላም በልቤ ውስጥ ገባ፡፡ አዲስ ሕይወትም ጀመርሁ፡፡ ራሴንም ለወንጌል ስርጭት ቀደስሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ነገሮች ሁሉ እንዳደረገ አስባለሁ፤ እርሱ በውስጤ እንደሚኖርም አምናለሁ፡፡ አንተም ስለ መንፈስ ቅዱስ በዚህ መንገድ አታስብምን?
Copyright © 2021 by The New Life Mission